18/12/2020
🚹🚺 🚺🚹
✴✳ ሳታነቡት እንዳታልፉ ✳✴
ማግባት የሚመኙ ግን ካገቡ በኋላ ምን እንደሚያደርጉ ያልተዘጋጁ፤ ገንዘብ የሚፈልጉ ግን ገንዘቡን ቢያገኙ ምን እንደሚሰሩበት በቅጡ ያላቀዱ፤ ውጭ ሀገር ለመሄድ የሚኳትኑ ግን ሄደው ምን እንደሚሆኑ ያላሰቡ፤ ተምሮ መጨረስ እንጂ ጨርሰው ምን እንደሚያደርጉ የተሰላ ዕቅድ የሌላቸው፤ ባለ ሀብት መሆን እንጂ ሀብቱን እንዴት እንደሚይዙት ዕውቀቱም ዝግጅቱም የሌላቸው፤ ስልጣን ላይ መውጣትን እንጂ ሲወጡ ለሚሆነው ነገር የሰለጠ ሐሳብ ያልቋጠሩ፤ ፌስ ቡክ መክፈት እንጂ ከፍተው ምን እንደሚያደርጉ ባለማቀዳቸው ሺ ጊዜ ፕሮፋይል ፎቶ የሚቀያይሩ፤ የሚዲያ ዕድል ለማግኘት እንጂ ሲያገኙ እንዴት ዘልቀውና ልቀው መቆየት እንደሚችሉ ያላሰላሰሉ "መኪና አሳዳጅ ውሾች"ተብለው ይጠራሉ።
ማግባት አንድ ነገር ነው በትዳር መዝለቅ ደግሞ ሌላ።ሀብት ማግኘት አንድ ነገር ነው ትውልድ የሚሻገር ተቋም መመስረት ደግሞ ሌላ። ታዋቂነትን ማግኘት አንድ ነገር ነው። እንደተወደዱና እንደተከበሩ መኖር ደግሞ ሌላ። ወደ ኪነ ጥበቡ አምባ መዝለቅ አንድ ነገር ነው። እንደተካኑና እንደተደነቁ መኖር ደግሞ ሌላ።
አንድ የሚጮህ ውሻ የነበረው ገበሬ ነበር አሉ። ውሻው መንገድ ዳር ይሆንና መኪና ባለፈ ቁጥር መኪናውን ለመያዝ እየጮኸ ይከተለዋል የውሻውን የዘውትር ተግባር ያየ ጎረቤቱ ገበሬውን ጠየቀው" ይኼ ውሻህ ምን ሞኝ ቢሆን ነው በፍጥነት የሚበርር መኪና ለመያዝ እንዲህ መከራውን የሚያየው? ለመሆኑ አንድ መኪና እንኳን መያዝ የሚችል ይመስልሀል?" ሲል ጠየቀው።
የውሻው ባለቤትም ሳቅ አለና "እኔ የሚገርመኝ እሱ አይደለም በዚሁ ከቀጠለ አንድ ቀን አንዱን መኪና ነክሶ ሊይዘው ይችል ይሆናል። እኔን የሚገርመኝ ሌላ ነው" አለው። ጎረቤቱም "ከዚህ የባሰ ምን ይገርምሀል?" ሲል ጠየቀ።
የውሻው ባለቤትም "እኔን የሚገርመኝ እንደምንም ብሎ መኪናውን አንድ ቀን ቢያገኘው ምን ሊያደርገው እንደሚችል አለማሰቡ ነው" አለው ይባላል።
መኪና አሳዳጅ ውሾች ዋና ጠባያቸው ይኼ ነው ቢያገኙም ምን እንደሚያደርጉት በሚገባ ያላሰቡትን አላማ ይከተላሉ። ከዚያስ? ለሚለው መልስ የላቸውም። የሚያደርጉት ሌላው ስላደረገው፣ ብዙ ስለተወራለት፣ ሰው ሲያደርገው ስላዩት ወይም ማስታወቂያዋች ስለጮሁለት ይሆናል።
መኪና ስለመያዝ እንጂ ወዴት አቅጣጫ እንደሚነዱት አስቀድመው አይዘጋጁም። ኮሌጅ ለመግባት እንጂ በኮሌጅ ለመዝለቅ ዘልቀውም ኮሌጅ ለመበጠስ አይዘጋጁም። ውጪ ሀገር ለመሄድ እንጂ እዚያ ለሚገጥማቸው ውጣ ውረድ በውጪም በውስጥም አላቀዱበትም። ፓርቲ ለመመስረት እንጂ በፓርቲ ውስጥ ለመዝለቅ የወጠኑት ስልት የለም። ማህበር ለማቋቋም እንጂ የማህበርን ማዕበልና ንውጥውጥ (ዳይናሚክስ)ችለውና አሸንፈው ለመዝለቅ የተለሙት ትልም የለም።
እቅድ ከምኞት የሚለየው በሦስት ነገር ነው። • ወደምታስበው አላማ የሚወስድህን ትክክለኛ መንገድ አጥርተህ ስታውቅው፣
• በመንገዱ ለሚገጥምህ ደስታና ሐዘን
እኩል ስትዘጋጅና፣
• አላማህ ላይ ስትደርስ በአላማህ ለመዝለቅ የሚያስችል በቂ ስልት ሲኖርህ ነው።
የትና እንዴት እንደሚኬድ፤ ሲደረስም ምን እንደሚደረግ ሳታውቅ በስሜት ብቻ ተነሳስቶ " እንሂድ"ተብሎ ከቤት አይወጣም። ሊቃውንት "በህይወት ውስጥ አስር በመቶው ከማግኘት ዘጠና በመቶው ግን ከአያያዝ ይሟላል" ይላሉ። ገንዘብ በሎተሪም ይገኛል ወድቆም ይገኛል በውርስም ይገኛል በስጦታም ይገኛል ተዘርፎም ይገኛል። አያያዝ ግን በስጦታም በውርስም በስረቆትም በሎተሪም አይገኝም። ካገኘኸው በኋላ ምን እንደምታደርገው እንዴት እንደምትይዘውና የት እንደምትወስደው የማታውቀውን ወይም አስቀድመህ በሚገባ ያላሰብክበትንና ያላቀድክበትን ነገር" ለማጣት አግኝተኸዋል" ማለት ነው።
(( በዚህ አነቃቂ ሀሳብ ምናልባት ልቦናቸውን የሚከፈት ሕይወታቸውንም የሚቀየር ሠዎች ሊኖሩ ይችላሉና በቅንነት ሼር ያድርጉ!))
ፔጁን ,shareእና follw ያድርጉ