25/04/2024
አሁናዊ መረጃ
ተወዳጁ ተዋናይ አማኑኤል ሐብታሙ እስራኤል አገር "እብደት በሕብረት" የተሰኘ ቴአትሩን ለማሳየት አውሮፕላን ሊሳፈር ሲል ከአዲስ አበባ ኤርፖርት በፖሊሶች ተይዞ ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ተወስዶ መታሰሩ ይታወሳል።
ከቤተሰብ ባገኘሁት መረጃ መሰረት ተዋናይ አማኑኤል ሐብታሙ እጁ ከተያዘበት ሰዓት አንስቶ የተከሳሽነት ቃል ሳይሰጥ እንዲሁ በእስር ላይ የሚገኝ ሲሆን፤ የቤተሰብ ጠበቃ የማግኘት መብቱ ተጠብቆለት ከቤተሰብ እና ከጠበቃ ጋር ዛሬ ጠዋት ሊገናኝ መቻሉን እና ያለበት አያያዝ መልካም መኾኑን ገልጸው በሕጉ መሰረት ወደ ቀጣይ ሕጋዊ ሂደቶች ለማምራት እስከ ነገ የሚሆነውን ለማየት መወሰናቸውን ለማወቅ ችያለሁ።
በሌላ በኩል በዛሬው ዕለት በአገረ እስራኤል ነስ ፅዮና ከተማ ሊካሄድ የነበረው እና ከ750 በላይ ተመልካቾች ሊታደሙበት የነበረው አማኑኤል ሐብታሙ የሚተውንበት "እብደት በሕበረት" ባለ አንድ ሰው ቴአትር መርሐ ግብር ለሌላ ጊዜ እንደተዘዋወረ በመግለጽ አዘጋጆቹ ተመልካቹን አክብረው ይቅርታ ጠይቀዋል።
ተወዳጁ ተዋናይ አማኑኤል ሐብታሙ በአስቸኳይ ከእስር ይፈታ ዘንድ የሚወዱት ሁሉ ምኞት ነው።
Yared Shumete - ያሬድ ሹመቴ