Sen'Q Mereja ስንቅ መረጃ

Sen'Q Mereja ስንቅ መረጃ Like በማድረግ ፈጣን ፣ ታማኝ ና ወቅታዊ መረጃ ያግኙ!

ወንድን አትናቁ ወንድ እንዴት ይናቃል፣ጉንዳን እንኳን በ'አቅሙሱሪ ያስወልቃል ። Real Hero 🔥🔥🔥🔥🔥💪💪💪💪💪💪💪💪💪
29/11/2021

ወንድን አትናቁ
ወንድ እንዴት ይናቃል፣
ጉንዳን እንኳን በ'አቅሙ
ሱሪ ያስወልቃል ።

Real Hero 🔥🔥🔥🔥🔥
💪💪💪💪💪💪💪💪💪

ዶ/ር እሌኒ ገብረመድህን ከዛሬ ጀምሮ ከገለልተኛ የኢኮኖሚ አማካሪነት መነሳታቸውን ተገለፀ፡፡የፕላንና ልማት ሚኒስቴር መግለጫ ያወጣ ሲሆን ሙሉ መግለጫው እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡ሀገራችን ኢትዮ...
28/11/2021

ዶ/ር እሌኒ ገብረመድህን ከዛሬ ጀምሮ ከገለልተኛ የኢኮኖሚ አማካሪነት መነሳታቸውን ተገለፀ፡፡
የፕላንና ልማት ሚኒስቴር መግለጫ ያወጣ ሲሆን ሙሉ መግለጫው እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡
ሀገራችን ኢትዮጵያን ለ27 ዓመታት በመራው በሕወሓት መራሹ መንግሥት ሀገሪቱ ያፈራቻቸው ምሁራን በየትኛውም የሀገራቸው ጉዳይ ተሳትፎ ማድረግ የሚችሉበት እድል ካለመኖሩም በላይ በሀገራቸው ጉዳይ ሐሳብ ባነሱ ጊዜ ሲሳደዱ እና ሲንገላቱ ቆይተዋል፡፡
በ2010 ዓ.ም. የመጣውን የመንግስት ለውጥ ተከትሎ በለውጡ አመራር ከተደረጉ ዘርፈ ብዙ ማሻሻያዎች ውስጥ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ምሁራን በሀገራችን የኢኮኖሚ ፖሊሲዎችና የልማት አቅጣጫዎች ላይ ገለልተኛ ምክር መስጠትና ግምገማ ማድረግ ይችሉ ዘንድ ዕድሎች ተመቻችቷል፡፡
በዚሁ መሠረት ሀገር እና ሕዝብ የሚሻገረው በሁሉም ኢትዮጵያዊና የኢትዮጵያ ወዳጅ ትብብር እንደሆነ የሚያምነው የለውጡ መንግስት፣ ምሁራን ሀገራቸውንና ወገናቸውን ከድህነት ወደ ተሻለ ሕይወት በፍጥነት እንዲሻገሩ የሚረዱ የኢኮኖሚ ፖሊሲዎች ላይ ምክር እንዲሰጡ ምቹ ምህዳር ከፍቷል፡፡
ይህ በተሻለ አደረጃጀት እና ቅንጅት ይፈጸም ዘንድ ታህሳስ 5፣ 2013 ዓ.ም በክቡር የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ አማካይነት አስራ ስድስት አባላት ያሉት ገለልተኛ የኢኮኖሚ አማካሪዎች ምክር ቤት እንደተሰየመ ይታወሳል፡፡
ከነዚህ አማካሪዎች መካከል ዶ/ር እሌኒ ገብረመድህን አንዷ ናቸው፡፡ ሆኖም የምክር ቤቱ አባል የሆኑት ዶክተር እሌኒ፣ በቅርቡ በዓለም አቀፍ ሰላምና ልማት ማዕከል በተዘጋጀ በድብቅ በተካሄደ የበይነ መረብ ስብስባ ላይ በሕጋዊ ምርጫ ቅቡልነት ያገኘውን የኢፌዴሪ መንግስት የመለወጥና የሽግግር መንግስት የማቋቋም አጀንዳ ላይ በመሳተፍ ሐሳቦችን ሲሰነዝሩ ተስተውለዋል፡፡
የምክር ቤት አባሏ በድብቅ በተካሄደው ስብሰባ ላይ ያነሷቸው ሐሳቦች በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት በሽብርተኝነት የተፈረጀን ቡድን በግልጽ የሚደግፍ ሆኖ ተገኝቷል፡፡
ምንም እንኳን የገለልተኛ ኢኮኖሚ አማካሪዎቹ በግል የራሳቸው የፖለቲካ አመለካከት ሊኖራቸው ቢችልም፣ አማካሪዎቹ ያቋቋሙት ም/ቤት ህገ ደንብ ግን የምክር ቤቱን አባላት የአማካሪነት ኃላፊነታቸውን ሲወጡ ከየትኛውም ፓርቲም ሆነ የፖለቲካ ድርጅት ነጻ መሆን እንደሚገባቸዉ በግልጽ ያስቀምጣል፡፡
በመሆኑም የአማካሪ ምክር ቤቱ ኅዳር 18፣ 2014 ዓ.ም ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ ዶ/ር እሌኒ ገብረመድህን በምርጫ ስልጣን የያዘን መንግስት የመለወጥና የሽግግር መንግስት የማቋቋም አላማ ባለው ስብሰባ ላይ ባራመዱት ጠንካራ አቋም በጣም ማዘኑን በመግለጽ፣ ግለሰቧ በገለልተኛ የኢኮኖሚ አማካሪ ም/ቤት አባል ሆነው መቀጠል እንደማይችሉ ውሳኔውን በጽሑፍ አሳውቆናል፡፡
በመሆኑም የገለልተኛ የኢኮኖሚ አማካሪ ም/ቤቱን ውሳኔ መነሻ በማድረግና ዶ/ር እሌኒ ገብረመድህን በመንግስትና በህዝብ ታምነው የተጣለባቸውን ከፍተኛ ኃላፊነት ወደ ጎን በመተው፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ በድምጹ ይሁንታ የሰጠውን መንግስት ቀይሮ የሽግግር መንግስት ስለማቋቋም በግልጽ ምክክር ሲያደርጉ በመገኘታቸው ከዛሬ ኅዳር 19፣ 2014 ጀምሮ ከገለልተኛ የኢኮኖሚ አማካሪነት መነሳታቸውን እናሳውቃለን፡፡

7ቱ የተመድ ሰራተኞች ከኢትዮጵያ ለቀው ወጥተዋል።ኢትዮጵያ በተለያዩ ህገወጥ ተግባራት ላይ ተሳትፈዋል ያለቻቸውን 7 የተመድ ሰራተኞች በ72 ሰዓታት ውስጥ የኢትዮጵያን ምድር ለቀው እንዲወጡ ማ...
05/10/2021

7ቱ የተመድ ሰራተኞች ከኢትዮጵያ ለቀው ወጥተዋል።

ኢትዮጵያ በተለያዩ ህገወጥ ተግባራት ላይ ተሳትፈዋል ያለቻቸውን 7 የተመድ ሰራተኞች በ72 ሰዓታት ውስጥ የኢትዮጵያን ምድር ለቀው እንዲወጡ ማዘዟ ይታወሳል።

ግለሰቦቹ በምን አይነት ህገወጥ የሆኑ ድርጊቶች ላይ ሲሳተፉ እንደነበረ በዝርዝር ይፋ መደረጉ አይዘነጋም።

እነዚህ ግለሰቦች እሁድ ዕለት ኢትዮጵያን ለቀው መውጣታቸውን የተመድ ምንጮቹን ዋቢ አድርጎ አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ (AFP) በድረገፁ አስነብቧል።

7ቱ የተመድ ሰራተኞች ላይ ኢትዮጵያ ያሳለፈችውን ውሳኔ አሜሪካ፣ ጀርመን፣ ዩኬ እና የአውሮፓ ህብረት አውግዘው ነበር ፤ ከዚህ በተጨማሪ ተመድ የኢትዮጵያ መንግስት ባልደረቦቼን ከሀገር የማባረር መብት የለውም ማለቱ አይዘነጋም።

እንደ AFP ዘገባ ግን በ72 ሰዓት ከሀገር እንዲወጡ ቀጭን ትዕዛዝ የተሰጣቸው የተመድ ሰራተኞች እሁድ እለት ኢትዮጵያን ለቀው ወጥተዋል።

የተመድ ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ም/ቃል አቀባይ ፈርሃን ሀቅ ባለስልጣናቱ ከኢትዮጵያ መውጣታቸውን ተናግረዋል። ሃቅ ፥ "ደህንነታቸው ለማረጋገጥ ሲባል ከሀገሪቱ ወጥተዋል" ብለዋል።

በUN ስር ባሉ ኤጀንሲዎች ውስጥ ሲሰሩ የነበሩት 7ቱ የውጭ ሀገር ዜጎች ፦

• የUNICEF የኢትዮጵያ ተወካይ - አዴል ኮደር
• የUN ሰብአዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽነር ቢሮ ባልደረባ - ሶኒ ኦኒግ ቡላ
• የUN የሰላምና ልማት አማካሪ - ከውሲ ሳንቼሎቲ
• የUN የተራድኦ ምክትል አስተባባሪ - ግራንት ሊያቲ
• የUN የተራድኦ ምክትል አስተባባሪ ተወካይ - ጋዳ ኤልታሂር ሙዳዊ፣
• የUN የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ፅ/ቤት UNOCHA ምክትል አስተባባሪ - ሰኢድ መሀመድ ሀርሲ
• የUN የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ፅ/ቤት UNOCHA ኃላፊ - ማርሲ ቪጎዳ ናቸው።

  ፌስቡክ ዛሬ በሰጠው መግለጫ ትላንት ከ6 ሰዓታት በላይ አገልግሎቶቹ የተቋረጡበት ምክንያት ከተሳሳተ የአወቃቀር ለውጥ ጋር የተያያዘ ነው ብሏል።የተሳሳተ የአወቃቀር ለውጥ መከሰቱን ተከትሎ ...
05/10/2021



ፌስቡክ ዛሬ በሰጠው መግለጫ ትላንት ከ6 ሰዓታት በላይ አገልግሎቶቹ የተቋረጡበት ምክንያት ከተሳሳተ የአወቃቀር ለውጥ ጋር የተያያዘ ነው ብሏል።

የተሳሳተ የአወቃቀር ለውጥ መከሰቱን ተከትሎ በአጠቃላይ የኩባንያውን ውስጣዊ መሳሪያዎች እና ስርዓቶች ላይ ተፅእኖ በማሳደሩ ችግሩን ለመፍታት አዳጋች አድርጎታልም ሲል ገልጿል።

መግለጫው አክሎም "ተቋርጠው በነበሩበት ሰዓታት የተጠቃሚዎች ግላዊ መረጃ ተጥሷል የሚል ማስረጃ የለም" ብሏል።

የፌስቡክ መስራች ማርክ ዙከርበርግ አገልግሎቶቹ በመቋረጣቸው ምክንያት ለተጎዱ ሰዎች ይቅርታ መጠየቃቸውን BBC / ቢቢሲ በድረገፁ አስነብቧል።

 ❗️ በህገ ወጥ መንገድ ከምዕራብ  ጎንደር ዞን  ወደ ጎንደር ከተማ  ለመግባት ሲንቀሳቀስ የነበረ የጦር መሳሪያ  መያዙ ተገለጸ።   የጦር መሳሪያው የተያዘው  መነሻውን ምዕራብ  ጎንደር ዞ...
19/09/2021

❗️
በህገ ወጥ መንገድ ከምዕራብ ጎንደር ዞን ወደ ጎንደር ከተማ ለመግባት ሲንቀሳቀስ የነበረ የጦር መሳሪያ መያዙ ተገለጸ።

የጦር መሳሪያው የተያዘው መነሻውን ምዕራብ ጎንደር ዞን አርማጭሆ ወረዳ በማድረግ ወደ ጎንደር ከተማ ለመግባት ሲንቀሳቀሰ ነው ።

የታርጋ ቁጥሩ ኮድ 3 አ/አ 17783 3F የሆነና እስማኤል ዳውድ በተባለ ግለሰብ ሲንቀሳቀስ በነበረ ተሽከርካሪ 82 ቱርክ ሰራሽ ሽጉጦች፣ ከ20 ሺህ መሰል ጥይቶች እንዲሁም 2 ክላሽንኮቭ ጠመንጄዎች እና 50 መሰል ጥይቶች በድብቅ ለማጓጓዝ ሲሞክር ነዉ እጅ ከፈንጅ የተያዘዉ፡፡

ብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ተጠርጣሪዉን ከመነሻው ጀምሮ ክትትል በማድረግ እና ሳንጃ የተባለዉ ኬላ ላይ ሲደርስ ጥቆማ በመስጠት በፀጥታ አካላት በቁጥጥር ስር እንዲውል መደረጉን አግልግሎቱ ገልጿል።

ዋና ተጠርጣሪውን ለመያዝ ክትትሉ ተጠናክሮ መቀጠሉንም አስታውቋል ፡፡

ህገ ወጥ የጦር መሳሪያዎችን በቁጥጥር ስር ለማዋል የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት እንዲሁም ጉምሩክ እና የፌደራል ፓሊስ ኮሚሽን በጋር እና በቅንጅት መሳተፋቸዉን ለመረጃዉ ቅርበት ያላቸዉ ምንጮቻችን አረጋግጠዋል፡፡

19/09/2021

:- በህወሓት ኃይሎች በቆቦ ከተማና በዙሪያው በሚገኙ ሲቪል ሰዎች ላይ እየተፈጸመ ያለው ጥቀት በአጅጉ አሳስቦኛል - የኢትዮጵያ ሠብዓዊ መብቶች ኮሚሽን

በህወሓት ኃይሎች በቆቦ ከተማና በዙሪያው ባሉ የገጠር ከተሞች ሲቪል ሰዎች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት እየተፈጸሙ መሆናቸው በእጅጉ አሳስቦኛል ሲል የኢትዮጵያ ሠብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ገለጸ፡፡

ኮሚሽኑ ዛሬ ባወጣው መግለጫ በህወሓት ወረራ ስር ባሉት አካባቢዎች በሚኖሩ ሲቪል ሰዎች ላይ የቤት ለቤት አደጋና ግድያ፣ ዝርፊያ እንዲሀም በመሠረተ ልማቶች ጥቃት እተየፈጸመ መሆኑን ሪፖርት እንደደረሰው ገልጿል፡፡

ኢሰመኮ የሚያደርገውን ምርመራ እንደሚቀጥልና በግጭቱ የሚሳተፉ ወገኖች በማናቸውም ወቅት ሲቪል ሰዎችን የመጠበቅ ግዴታቸውን እንዲያከብሩም አሳስቧል፡፡

19/09/2021

:- በአዲስ አበባ በሕገ-ወጥ መንገድ የሚንቀሳቀሱ ከ200 በላይ ሞተር ሳይክሎች ተወረሱ!!

በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ እንዲሠሩ ፈቃድ ከተሰጣቸው የሞተረኞች ሎጎ ጋር በማመሳሰል በሕገ-ወጥ መንገድ ሲሠሩ የተገኙ ከ200 በላይ የሚሆኑ ሞተር ሳይክሎች መውረሱን የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ገለጸ። “በሕገ ወጥ እንቅስቃሴ ሎጎ በማመሳሰል ሲያሽከረክሩ ተገኝተዋል’’ የተባሉት ሞተረኞቹ እንደየጥፋታቸው የእስራትና የገንዘብ ቅጣት እንደተፈረደባቸው የትራንስፖርት ቢሮ የኮሚዩኒኬሸን ዳይሬክተሩ አረጋዊ ማሩ ተናግረዋል።

  : የመንግስት ከፍተኛ የሥራ ሀላፊዎችና  የሚዲያ አመራሮች በደብረታቦር ሆስፒታል ተገኝተው በግንባር ላይ የቆሰሉ ታካሚዎችን ጠየቁ።በተጨማሪ ጁንታው 5 ቤተሰባቸውን በመድፍ የገደለባቸው አባ...
16/09/2021

: የመንግስት ከፍተኛ የሥራ ሀላፊዎችና የሚዲያ አመራሮች በደብረታቦር ሆስፒታል ተገኝተው በግንባር ላይ የቆሰሉ ታካሚዎችን ጠየቁ።በተጨማሪ ጁንታው 5 ቤተሰባቸውን በመድፍ የገደለባቸው አባት ቤት ተገኝተው አጽናንተዋል ።

በቡልቡላ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ምረቃ እየተካሄደ ነው!  : በቡልቡላ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ስልጠናቸውን የተከታተሉ ምልምል ወታደሮች የምረቃ ሥነ-ሥርዓት እየተካሄደ ነው፡፡ምልምል ወታደሮቹ አገራዊ ...
16/09/2021

በቡልቡላ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ምረቃ እየተካሄደ ነው!

: በቡልቡላ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ስልጠናቸውን የተከታተሉ ምልምል ወታደሮች የምረቃ ሥነ-ሥርዓት እየተካሄደ ነው፡፡ምልምል ወታደሮቹ አገራዊ ጥሪውን ተቀብለወ ከተለያዩ ክልሎች በፍላጎታቸው ተመዝግበው የመጡ መሆናቸውን የማሰልጠኛው አዛዥ ኮሎኔል ሰቦቃ በቀለ ገልፀዋል፡፡

መሰረታዊ የውትድርና ሙያ ትምህርት የተከታተሉት ምልምል ወታደሮቹ በአካል ብቃት፣ በወታደራዊ ሰልፍ፣ በተኩስና ውጊያ ስልት ስልጠናቸውን በብቃት ያጠናቀቁ ናቸው፡፡በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የመከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ አዛዦች ተገኝተዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል፡፡

11/09/2021
10/09/2021
ሰሜን ወሎ  #ወልዲያ ❗️😭😭😭😭😭😭😭Via Gobeze Sisay
10/09/2021

ሰሜን ወሎ #ወልዲያ ❗️

😭😭😭😭😭😭😭

Via Gobeze Sisay

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ሴኔጋል ገቡ!ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለአንድ ቀን የስራ ጉብኝት ሴኔጋል ገብተዋል፡፡ በሴኔጋል በሚኖራቸው ቆይታም ከሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ማኪ...
07/09/2021

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ሴኔጋል ገቡ!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለአንድ ቀን የስራ ጉብኝት ሴኔጋል ገብተዋል፡፡ በሴኔጋል በሚኖራቸው ቆይታም ከሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ማኪ ሳል ጋር በሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ዙሪያ እንደሚመክሩ ይጠበቃል፡፡

  : እንዴ ላሊበላ ነኝ አንዴ ወልዲያ ነን ገለመሌ እያለ በኩራት የሚመራውን የህወሓት ጉጀሌ ታጣቂ እየመራ በማዘረፍ ፎቶ ፖስት ሲያደርግ የነበረው የህወሓት ኮረኔል የሚመራው ጦር ተደምስሶ ኮ...
07/09/2021

: እንዴ ላሊበላ ነኝ አንዴ ወልዲያ ነን ገለመሌ እያለ በኩራት የሚመራውን የህወሓት ጉጀሌ ታጣቂ እየመራ በማዘረፍ ፎቶ ፖስት ሲያደርግ የነበረው የህወሓት ኮረኔል የሚመራው ጦር ተደምስሶ ኮረኔሉ በጀግናው ሰራዊታችን ተማርኳል

 #አፋር❗️በአፋር ግንባር የድል ዜናው ዛሬም እንደቀጠለ ነው   : በትናንትናል እለት የአፋር ልዩ ሀይልና ሚኒሻ  ጁንታውን ከእዋ ከተማ ያስለቀቀ ሲሆን ዛሬም  የአፋር ሚኒሻና ልዩ ሀይል  ...
07/09/2021

#አፋር❗️
በአፋር ግንባር የድል ዜናው ዛሬም እንደቀጠለ ነው

: በትናንትናል እለት የአፋር ልዩ ሀይልና ሚኒሻ ጁንታውን ከእዋ ከተማ ያስለቀቀ ሲሆን ዛሬም የአፋር ሚኒሻና ልዩ ሀይል የድል ግስጋሴውን ቀጥሌ የጁንታውን ሀይል ሙሉ በሙሉ ከአውራና ከከልዋን ከተማ ማስወጣቱታቸውንና በአሁን ሰአት ከተማዎቹም ሙሉ በሙሉ በአፋር ልዩ ሀይልና ሚኒሻ ቁጥጥር ስር መሆናቸውን አቶ አይዳሒስ አፍኬኤ አስታወቁ፡፡

አቶ አይዳሒስ ቀጥለውም በቀጣይ ቀናቶችም ጁንታውን ከገባባቸው የአፋር ከተሞች ሙሉ በሙሉ ለማስወጣት የአፋር ልዩ ሀይልም ግስጋሴውን ወደ የሎ ከተማ እያደረገ መሆኑን እና ጁንታውን የማፅዳት ስራውም ተጠናክሮ እንደቀጠለ አስታውቀዋል፡፡

ከ31 ሺህ በላይ ተተኳሽ ጥይቶች በቁጥጥር ስር ዋሉ‼  : በምዕራብ ወለጋ ዞን ነጆ ከተማ በህገ-ወጥ መንገድ ሲጓጓዝ የነበረ ከ31 ሺህ በላይ ተተኳሽ ጥይቶችን ከሁለት ተጠርጣሪ ግለሰቦች በቁ...
07/09/2021

ከ31 ሺህ በላይ ተተኳሽ ጥይቶች በቁጥጥር ስር ዋሉ‼

: በምዕራብ ወለጋ ዞን ነጆ ከተማ በህገ-ወጥ መንገድ ሲጓጓዝ የነበረ ከ31 ሺህ በላይ ተተኳሽ ጥይቶችን ከሁለት ተጠርጣሪ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉን የምዕራብ ወለጋ ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ፡፡

ህገ-ወጥ ጥይቶቹን በአይሱዙ የጭነት መኪና ሲጓጓዝ በተደረገ ክትትልና ፍተሸ መያዙን በምዕራብ ወለጋ ዞን ፖሊስ መምሪያ የአከባቢ ጸጥታና ደህንነት ምክትል ዳይሬክተር ሳጅን ምትኩ ብርሃኑ ገልጸዋል፡፡

ዳይሬክተሩ ህብረተሰቡ ህገ-ወጥ ተግባራትን በማጋለጥና ለፖሊስ ጥቆማ በመስጠት እያደረገ ያለውን ተግባር አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ማቅረባቸውን ከኦሮሚያ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

06/09/2021

ልዩ መረጃ‼️

የአፋር ልዩ ሀይል ሚሊሺያ እና ህዝባዊ ሰራዊት ጁንታውን ከኡዋ ወረዳ በማስወጣት ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር አድርገዋል።

: የህወሀት ጁንታ በፈንቲ ረሱ ያሎ በኩል ድንገተኛ ወረራ በማካሄድ ንፁሀንን በመጨፍጨፍ ወደ አፋር ክልለ ሰርጎ መግባቱ ይታወቃል። ሰርጎ ከገባም በኋላ ህዝብ ውስጥ በመመሸግ የቆየ ሲሆን የአፋር ልዩ ሀይል ሚሊሺያ እና ህዝባዊ ሰራዊት እና የሀገር መከላከያ ሰራዊት በጋራ በመሆን ካለበት እንዳያልፍና ጥበባዊ በሆነ መንገድ ህዝብ ሳይጎዳ ጁንታውን ለማስወጣት ትግል ሲደረግ ቆይተል።

በዚህ ሂደትም በዛሬው ዕለት የአፋር ልዩ ሀይል ሚሊሺያ እና ህዝባዊ ሰራዊት ጁንታውን ከኡዋ ወረዳ ሙሉ በሙሉ በማስወጣት ወረዳው ከወራሪው አሸባሪ የህወሀት ጁንታ በማስወጣት በአፋር ቁጥጥር ስር ሆኗል።

የህወሀት ጁንታ በማይሆን ስሌት ለአፋር ህዝብ ያነሰ ግምት ይዞ ቢነሳም ወረራ ባካሄደባቸው ሁሉም ግንባሮች ከባድ የሆነ ሽንፈትና ትልቅ ኪሳራ እየገጠመው ነው።

የአፋር ህዘብና መንግስት አሁንም ቢሆን ወራሪውን ሀይል ሙሉ በሙሉ ከክልሉ ወሰን ጠራርጎ ለማስወጣት ጥበብ በተሞላበት መልኩ ትግሉ የሚቀጥል ይሆናል።

ፍፁም ሰብአዊነት የማይሰማው ፣ ኢትዮጵያዊነት ፈፅሞ የማያውቀው አሸባሪው ህወሀት ሀገርን ለማፈራረስ ከተለያዩ የውጭና የውስጥ ሀይሎች ጋር ተባብሮ እየሰራ ቢገኝም ለወራሪ ሀገሩን አሳልፎ መስጠትን የማያውቀው የአፋር ህዝብ የሽብር ቡድኑን እየመከተ እና እያጠቃ በትግራይ ክልል ላሉ ወንድም የትግራይ ህዝብም ሰብአዊ ድጋፍ እንዲደርስ ጥረት እያደረገ መሆኑ ይታወቃል።

አሸባሪው የህወሀት ጁንታ ከአፋር ወሰን አንድ ስንዝር ውስጥ እሳከለ ድረስ የአፋር ልዩ ሀይል ሚሊሺያ እና ህዝባዊ ሰራዊት አስፈላጊውን እርምጃ በመውሰድ በግድ ከክልሉ ወሰን እንዲወጣ የሚደረግ ይሆናል።

በአፋር ክልልም የሚኖሩ የትግራይ ህዝቦች እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ መብታቸው ተከብሮ፣ ግዴታቸውን እየተወጡ በሰላም እየኖሩ መሆኑ ይታወቃል። በመሆኑም ይህ እኩይ ቡድን ለትግራይ ህፃናት ያልራራ ለማንም የማይራራ በመሆኑ የተግራይ ህዝብም ከማንም በበለጠ ተጎጂ በመሆኑ በቃቹህ ሊል ይገባል።

እጅግ ከፍተኛ ጥበቃ ከሚደረግበት እስር ቤት ያመለጡት ፍልስጥኤማውያን❗️6 ፍልስጤማውያን እስረኞች ጠንካራ ጥበቃ ከሚደረግለት እስር ቤት ካመለጡ በኋላ እስረኞቹን አድኖ ለመያዝ እስራኤል ኦፕሬ...
06/09/2021

እጅግ ከፍተኛ ጥበቃ ከሚደረግበት እስር ቤት ያመለጡት ፍልስጥኤማውያን❗️

6 ፍልስጤማውያን እስረኞች ጠንካራ ጥበቃ ከሚደረግለት እስር ቤት ካመለጡ በኋላ እስረኞቹን አድኖ ለመያዝ እስራኤል ኦፕሬሽን ጀመረች።

ከ6ቱ 5ቱ የእድሜ ልክ እስር የተፈረደባቸው ናቸው::

ከእስር ቤቱ ያመለጡት እስረኞች ለወራት ያህል የእስር ቤት ክፍላቸውን ውጪ ካለ መንገድ ጋር የሚያገናኝ ዋሻ ለመሥራት ሲቆፍሩ ቆይተዋል ተብሏል።

እስረኞቹ ትናንት ለሊት ላይ ማምለጣቸው የተገለጸ ሲሆን፤ እስረኞቹ በእርሻ ስፍራ ሲሯሯጡ የተመለከቱ አርሶ አደሮች ለእስራኤል ባለሥልጣናት ጥቆማ አድርሰዋል።

ፍልስጤማውያኑ እስረኞች ተረዳድተው ከመጸዳጃ ክፍላቸው ጀምረው የቆፈሩት ዋሻ ከእስር ቤቱ ውጪ ካለ መንገድ ጋር የሚያገናኝ ነው።

ጄሩሳሌም ፖስት እንደዘገበው ከሆነ እስረኞቹ ዋሻውን ለመቆፈር ያረጀ ማንኪያ ተጠቅመዋል። የእስራኤል ደኅንነት ኤጀንሲ በበኩሉ እስረኞቹ ከእስር ቤቱ ውጪ ካለ አካል ድጋፍ ሳያገኙ አይቀርም ብሏል።

የእስራኤል ማረሚያ ቤት አገልግሎት ኃላፊዎች የእስረኞቹን ማምለጥ፤ "ከፍተኛ የደኅንነት ውድቀት ነው" ሲሉት የፍልስጤም ታጣቂ ቡድኖች ደግሞ፤ "ጀግንነት" ሲሉ አወድሰዋል።

ከእስር ቤቱ ያመለጡት እስረኞች ዌስት ባንክ አልያም ጆርዳን እንዳይገቡ የእስራኤል ፖሊስ መንገዶችን በመዝጋት ፍተሻ እያካሄደ ነው ተብሏል። ይሁን እንጂ ዌስት ባንክ እና ጆርዳን ከእስር ቤቱ 14 ኪሎ ሜትሮች ብቻ እንደሚርቁ ተመልክቷል።

ምንጭ : ቢቢሲ

የአሸባሪው ህወሓት ወራሪ ኃይል ለሃገሪቱ ዳግም ስጋት እንዳይሆን እየተሰራ ነው❗️-አቶ ገዱ አንዳርጋቸው''የህወሓት ወራሪ ኃይል ዳግም የአገሪቱ ስጋት በማይሆን መልኩ በጋራ መከላከልና ህልውና...
06/09/2021

የአሸባሪው ህወሓት ወራሪ ኃይል ለሃገሪቱ ዳግም ስጋት እንዳይሆን እየተሰራ ነው❗️-አቶ ገዱ አንዳርጋቸው

''የህወሓት ወራሪ ኃይል ዳግም የአገሪቱ ስጋት በማይሆን መልኩ በጋራ መከላከልና ህልውናን ማስቀጠል የወቅቱ አንገብጋቢ አጀንዳ ሆኖ እየተከናወነ ነው'' ሲሉ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው አስታወቁ።

በደሴ ከተማ በወቅታዊ አገራዊ ጉዳይ ዙሪያ ምክክር እየተደረገ ነው።

አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በምክክር መድረኩ ላይ እንደተናገሩት አሸባሪው ቡድን ከውጭ ጠላቶች ጋር ወግኖ ኢትዮጵያን ለማፍረስ እየሰራ ነው።

ህወሓት ወራሪ ኃይሉን በአማራና አፋር ክልሎች በማሰማራት በሕዝብ ላይ በደል እየፈፀመ መሆኑን ገልጸዋል።

"የኢትዮጵያ ሕዝብ አንድነቱን ጠብቆ ወራሪ ሃይሉ ለአገርና ህዝብ ዳግም ስጋት በማይሆንበት መንገድ በመደምሰስ ህልውናውን የሚያስቀጥልበት ወቅት ነው" ብለዋል።

ወጣቱ በየአካባቢው ተደራጅቶና ሰልጥኖ የአገሪቱን ነፃነትና ሉአላዊነት በማስቀጠል ግዴታውን እንዲወጣ አቶ ገዱ አሳስበዋል።

መንግሥት ሕዝቡንና የጸጥታ ሃይሎችን በማስተባበር አሸባሪው ቡድን የሚያደርገውን ሁለንተናዊ ጥፋት ለመመከት በተደራጀ አግባብ እየሰራ መሆኑን አቶ ገዱ አብራርተዋል።

በውይይቱ የአማራ ክልል የሰላምና ደህንነት ቢሮ ኃላፊ ሰማ ጥሩነህ (ዶ/ር)ን ጨምሮ ሌሎች የፌዴራልና የአማራ ክልል ከፍተኛ ባለሥልጣናትና የደሴ ከተማ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በመሳተፍ ላይ መሆናውን ኢዜአ ዘግቧል።

ከሰሞኑ የጋምቤላ ግጭት ጀርባ ራሱን የጋምቤላ ነፃነት ግንባር የሚለው ቡድን እንደሚገኝበት ተነገረ❗️በጋምቤላ ክልል ባለፈው ሳምንት ተከስቶ ለአምስት ሰዎች ሞት ምክንያት ከሆነው ግጭት ጀርባ፣...
06/09/2021

ከሰሞኑ የጋምቤላ ግጭት ጀርባ ራሱን የጋምቤላ ነፃነት ግንባር የሚለው ቡድን እንደሚገኝበት ተነገረ❗️

በጋምቤላ ክልል ባለፈው ሳምንት ተከስቶ ለአምስት ሰዎች ሞት ምክንያት ከሆነው ግጭት ጀርባ፣ በክልሉ በተካሄደው ምርጫ ተሳታፊ የነበረውና ራሱን የጋምቤላ ነፃነት ግንባር (ጋነግ) በሚል ስያሜ መጥራት የጀመረው፣ የጋምቤላ ሕዝቦች ፍትሕ ለሰላምና ልማት ዴሞክራቲክ ንቅናቄ እንደሚገኝበት ተገለጸ፡፡

የጋምቤላ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡመድ ኡጁሉ ለሪፖርተር እንዳስታወቁት፣ በጋምቤላ ባለፈው ሳምንት የተከሰተው ግጭት መንስዔ፣ በክልሉ በተካሄደው ምርጫ ተሳታፊ የነበረው የጋምቤላ ሕዝቦች ፍትሕ ለሰላምና ልማት ዴሞክራቲክ ንቅናቄ (ጋሕፍሰልዴን) ነው፡፡ ፓርቲው በምርጫው ከተሸነፈ በኋላ ወደ ጫካ በመግባት ራሱን የጋምቤላ ነፃነት ግንባር ብሎ በማወጅ ለሽብር መንቀሳቀስ መጀመሩን ተናግረዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ ጨምረው እንዳስታወቁት፣ ፓርቲው ከምርጫው በኋላ ሽብር ለመፈጸም እንዲመቸው በአሸባሪነት ከተፈረጁት የሕወሓትና የሸኔ ቡድኖች ጋር በመተባባር የተለያዩ አፍራሽ ድርጊቶችን እያከናወኑ ናቸው፡፡ የክልሉን ሰላም ለማደፍረስ በተደጋጋሚ በግጭት የሚታወቁትን ሁለቱን ብሔረሰቦች ማለትም አኙዋክና ንዌር፣ እንዲሁም በክልሉ የሚገኙትን አምስቱን ብሔረሰቦችና ሌሎች ብሔረሰቦችን ለማጋጨት ጥረት ማድረጋቸው እንደ ተስተዋለ ርዕሰ መስተዳድሩ አስታውቀዋል፡፡

ዘገባዉ የሪፖርተር ነው ተጨማሪ ለማንበብ : https://bit.ly/3DPKPlc

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ወደ ሱዳን አጓጉዟል በሚል የተሰራጨው ዘገባ ከአውነት የራቀ ነው❗️፡- የኢትዮጵያ አየር መንገድየኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰሞኑን ህገ ወጥ የጦ...
06/09/2021

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ወደ ሱዳን አጓጉዟል በሚል የተሰራጨው ዘገባ ከአውነት የራቀ ነው❗️፡- የኢትዮጵያ አየር መንገድ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰሞኑን ህገ ወጥ የጦር መሰሪያ ወደ ሱዳን ጭኖ ማስገባቱንና በሱዳን የፀጥታ ኃይሎች መያዙን በሱዳኑ ዜና አገልግሎት የተሰራጨው ዘገባ ከአውነት የራቀ መሆኑን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታውቋል፡፡

አየር መንገዱ ከኢትዮጵያ ወደ ሱዳን ያጓጓዘው የአደን የጦር መሳሪያ ህጋዊና በአየር መንገዱ የንግድ ትራንስፖርት አስፋላጊውን ህጋዊ ሰነዶችን ያሟላ መሆኑን ገልጿል፡፡

የአደን የጦር መሳሪያውን ወደ ሱዳን ለማጓጓዝ ከሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፍቃድ ማግኘቱንም ነው አየር መንገዱ ባወጣው መግለጫ ያስታወቀው፡፡

የአደን የጦር መሳሪያ ጭነቱ በኢትዮጵያ የፀጥታ ኃይሎች ለረጅም ጊዜ ተይዞ አስፋላጊው የማጣራት ስራ ሲሰራ መቆየቱንና የማስረከቡ ሂደትም በመጓተቱ በሱዳን የአድን የጦር መሳሪያዎቹን ያስጫነው ድርጅት በሱዳን ፍርድ ቤት አየር መንገዱን በመክሰስ መሳሪዎቹን እንዲያስርክበው ወይም 250 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ካሳ እንዲከፈለው መጠየቁንም አየር መንገዱ አመልክቷል፡፡

ይሁን እንጂ የአደን የጦር መሳሪያዎቹን ወደ ሱዳን ለማጓጓዝ ከሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፍቃድ አግኝቶ ላስጫነው ወገን ለማስረከብ ሌሎች አስፈላጊ ህጋዊ ስርዓቶችን አሟልቶ ወደ ወደ አገሪቱ ያስገባው መሆኑን የኢትዮጵያ አየር መንገድ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

06/09/2021

የኢትዮጵያዊነት ቀን በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ተከብሯል❗️

ጳጉሜ 01 የኢትዮጵያዊነት ቀን በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ተከብሯል፡፡ሁሉም በያለበት ሆኖ ለሁለት ደቂቃ "ለኢትዮጵያ ክብር እቆማለሁ፤እዘምራለሁ " በሚል መሪ ቃል ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዊነትን ከፍ በማድረግ እያከበረ ይገኛል፡፡

በመስቀል አደባባይ በተካሄደው መርሀ ግብር ላይ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ፣የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ፣የሀገር መከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ ጀነራሎች እና በርካታ ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

  ተራዝሟል❗️የ2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ጥቅምት አጋማሽ ይሰጣል መባሉ ይታወሳል። ነገር ግን እሁን ባለው የሰላም ችግር በታቀደለት ጊዜ አይሰጥም በማለት በ...
04/09/2021

ተራዝሟል❗️

የ2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ጥቅምት አጋማሽ ይሰጣል መባሉ ይታወሳል። ነገር ግን እሁን ባለው የሰላም ችግር በታቀደለት ጊዜ አይሰጥም በማለት በውስጥ የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ከዚህ በፊት ቀኑን ሳይጠቅስ ጥቅምት አጋማሽ በማለት ተናግረው ነበር። ቢሆንም ግን አሁንም ላልተወሰነ ጊዜ ይረዘማል ተብሏል።

አሸባሪው ህወሓት በሶስት አቅጣጫ ያሰለፈው ቡድን ሙሉ ለሙሉ ተደምስሷል፡- ሌ/ጀነራል ባጫ ደበሌ  : በጀነራል ምግበይ የሚመራው አርሚ አንድ ተብሎ የሚጠራው ሃይል ሙሉ ለሙሉ መደምሰሱን የመከ...
04/09/2021

አሸባሪው ህወሓት በሶስት አቅጣጫ ያሰለፈው ቡድን ሙሉ ለሙሉ ተደምስሷል፡- ሌ/ጀነራል ባጫ ደበሌ

: በጀነራል ምግበይ የሚመራው አርሚ አንድ ተብሎ የሚጠራው ሃይል ሙሉ ለሙሉ መደምሰሱን የመከላከያ ሚኒስቴር የሠራዊት ግንባታ ዋና አስተባባሪ ሌተናል ጀኔራል ባጫ ደበሌ ገልጸዋል፡፡ ሌተናል ጄነራል ባጫ ደበሌ የሰራዊቱን ግዳጅ አፈጻጸም እና ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በጀነራል ምግበይ የሚመራው እና አርሚ አንድ የሚባለው ሃይል በሁመራ አካባቢ ደባርቅ እና ዳባትን በመቁረጥ ጎንደርን ለመያዝ ቢፈልግም ሙሉ ለሙሉ ተደምስሷል ብለዋል ጀነራሉ፡፡ በመሆኑም አሸባሪው ህወሓት ወደሱዳን ለመውጣት ያቀደው ሙከራ ሳይሳካለት ቀርቷል፡፡

አርሚ ሁለት የሚባለው እና በከሃዲው ሜ/ጀነራል ዮሐንስ ወ/ጊዮርጊስ የሚመራው ሃይል በጋሸና ከክምር ድንጋይ ጀምሮ በተደረገ ውጊያ ሁለቱ ክፍለጦሮች ተደምስሰውበታል፡፡ አርሚ ሦስት የሚባለው ደግሞ ከውጭ በብ/ጀነራል ፍስሃ የሚመራ እና የሰለጠነ በሽንፋ በኩል ከቅማንት ቅጥረኛ ቡድን ጋር በመተባባር ጥቃት ቢሰነዝርም ተደምስሷል የተረፈውም ወደመጣበት ተመልሷል ብለዋል፡፡

ይህ ሃይል በተለይ የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ስራ ለማስተጓጎል ቢያስብም እቅዱ በጀግናው ሃይላችን ተደምስሷል ብለዋል፡፡ አሸባሪ ቡድኑ እየደረሰበት ያለው ኪሳራ በጣም ብዙ ነው ያሉት ጀነራል ባጫ በተለይ የትግራይ ወጣቶችን እያስጨረሰ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የወገን እንባ ጠራጊዎች❗️የሸዋ ሰላምና ልማት ማህበር  (ሸዋሰማ) በአጣዬ ጉዳት ለደረሰባቸው ሶስት መቶ ለሚጠጉ ወገኖቻችን ለበዓል መዋያ ይረዳቸው ዘንድ የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል።ተቋም ያለው...
04/09/2021

የወገን እንባ ጠራጊዎች❗️

የሸዋ ሰላምና ልማት ማህበር (ሸዋሰማ) በአጣዬ ጉዳት ለደረሰባቸው ሶስት መቶ ለሚጠጉ ወገኖቻችን ለበዓል መዋያ ይረዳቸው ዘንድ የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል።ተቋም ያለው ህዝብ ችግሩን ይፈታል።ይደራጃል በተደራጀ ሁኔታም እራሱን ይከላከላል።ወንድሞቻችን እናመሰግናለን!

ውሾች ይጮኻሉ🐩
ግመሎች ይጓዛሉ 🐪

የድምፃዊ አለማየሁ እሸቴ ሥርዓተ ቀብር መቼ ይፈፀማል❓የድምፃዊ አለማየሁ እሸቴ ሥርዓተ ቀብር የፊታችን ማክሰኞ ጳጉሜን 2 ቀን 2013 በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል እንደሚፈጸም የ...
04/09/2021

የድምፃዊ አለማየሁ እሸቴ ሥርዓተ ቀብር መቼ ይፈፀማል❓

የድምፃዊ አለማየሁ እሸቴ ሥርዓተ ቀብር የፊታችን ማክሰኞ ጳጉሜን 2 ቀን 2013 በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል እንደሚፈጸም የአርቲስቱ የቀብር አስፈጻሚ ኮሚቴ አስታውቋል።

የአርቲስቱ የአስክሬን ሽኝት በመስቀል አደባባይ እንደሚከናወን መገለፁን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

አርቲስት አለማየሁ እሸቴ ከትናንት በስቲያ ነሐሴ 27 ቀን 2013 ባደረበት የልብ ሕመም በ80 ዓመቱ በድንገት ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ይታወሳል፡፡

አቶ ገብረጻዲቅ ገብረመድህን ይናገራሉ... ‼️👉 ጠንካራ ኢትዮጵያ  ተፈጠረች ማለት ጠንካራ አፍሪካ  ትፈጠራለች ማለት ስለሆነ ለሸቀጣቸው ማራገፊያ እንዳያጡና አሻንጉሊት መሪ ስለሚፈልጉ አሸባ...
04/09/2021

አቶ ገብረጻዲቅ ገብረመድህን ይናገራሉ... ‼️

👉 ጠንካራ ኢትዮጵያ ተፈጠረች ማለት ጠንካራ አፍሪካ ትፈጠራለች ማለት ስለሆነ ለሸቀጣቸው ማራገፊያ እንዳያጡና አሻንጉሊት መሪ ስለሚፈልጉ አሸባሪው ህወሓት ባንዳ ሆኖ እየሰራ ነው፣

👉 በማንኛውም መሰዋእትነት አሸባሪው ህወሓት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ይወገዳል፤ ኢትዮጵያም ሰላም ትሆናለች፤ በእጅ አዙር ሊያስተዳድሯት የሚፈልጉት ምእራባውያን ያበቃላቸዋል፣

👉 አሁን የገጠመንን ፈተና መሻገር፣ ችግሩን የመፍታትና የማስወገድ ብቃት ያለው ህዝብና አመራር ስላለ ይፈታል፣

👉 ለሕዝብ ቀና ደፋ ሲሉ የነበሩ አመራሮች በአሽባሪው ህወሓት ሕይወታቸውን አጡ፣ የተገደሉት አመራሮች ለህዝብ ምግብ መድሀኒትና ውሃ እያመጡ ነው፣

👉 ጊዜያዊ አስተዳደሩ ተናቦ ባለመሰራቱ ወርቃማው እድል ወደ ውጤት ሳይቀየር ቀርቷል፣

👉 አሽባሪው ህወሓት በፈጠረው መከፋፈል፣ የንግድ አሻጥር፣ የሀይማኖት ግጭት ዘርፈ ብዙ ሴራ ሰርቷል፣

👉 አሽባሪው ህወሓትን ህዝብ አንፈልግህም ብሎ ሲያባርረው ሽንፈቱን ባለመቀበልና የሚመጣውን ተጠያቂነት ለመሸሽ ኢትዮጵያን የመበታተንና የባንዳነት ተግባር ላይ የተሰማራ የሽብር በድን ነው፣

👉 በብሄር፣ በእምነት፣ በዘመድና ወዘተ ዜጎችን የመከፋፈሉና ፍትህ የማሳጣቱ ተንኮል ከህወሓት ጋር አብሮ ይነቀላሉ፣

👉 አሽባሪው ህወሓት ምን ይላል መሰላችሁ ትግራይ አንድ ነች፤ አትከፋፈሉ፤ ዋና ጠላታችን በመንደር ማሰብ ነው፣

👉 ከትራይ ጊዜአዊ አስተዳደር ጋር በተያያዘ ብዙ ችግሮች ነበር፣ ለውጥ የሚፈልግ አመራር ነበር፤ የሚዘርፍ አመራርም ነበር፤ አሽባሪው ህወሓትን የሚደግፍ አመራርም ነበር፣ ለጊዜያዊ አስተዳደሩ ውድቀት ዋናው ተጠያቂ ብልጽግና ነው የሚሉት ስህተት ነው፣

👉 እኔ አዲግራት ላይ ዞን እያስተካከልኩ በነበረበት ጊዜ ህዝብ ሲያንገላቱ፣ የመንግስት ነዳጅ የዘረፉ ሰዎችን አሰረናል፣

👉 አሸባሪው ህወሓት በተደጋጋሚ በጸብ አጫሪነት የትግራይንም ሆነ የኢትዮጵያ ዜጎችን ሰላምና እረፍት መንሳት የቆመበት አላማ ነው፣ በአማራና በአፋር ክልል ተደጋጋሚ ጥቃት መፈጸሙን ለዚህ በቂ ማሳያ ነው፣

👉 ሁሉም ኢትዮጵያዊ የጀመረውን ዘመቻ በማጠናከር የአሸባሪውን ህወሓት እድሜ ማሳጠር ለሁሉም መፍትሄ ነው፤

የብልጽግና ፓርቲ የትግራይ ቅርንጫፍ የአደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ አቶ ገብረጻዲቅ ገብረመድህን የህወሓት አባል በነበሩበት ስላሳለፏቸው ጊዜያትና በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ስለተሰሩ ስራዎች ያነሷቸውን ዝርዝር መረጃዎችን ለማግኘት ሊንኩን ይጫኑ ❗️
https://www.press.et/ama/?p=54885

በዳባት አካባቢ በጭና እና ወቅን ቆርጦ ለመግባት የሞከረው አሸባሪ ህወሓት ሙሉ ሉሙሉ ተደመሰሰ  : በዳባት አካባቢ በጭና እና ወቅን ቆርጦ ለመግባት የሞከረው የአሸባሪው ህወሓት ቡድን ሰሞኑን...
04/09/2021

በዳባት አካባቢ በጭና እና ወቅን ቆርጦ ለመግባት የሞከረው አሸባሪ ህወሓት ሙሉ ሉሙሉ ተደመሰሰ

: በዳባት አካባቢ በጭና እና ወቅን ቆርጦ ለመግባት የሞከረው የአሸባሪው ህወሓት ቡድን ሰሞኑን በተደረጉት ውጊያዎች የመከላከያ ሰራዊት እና የፀጥታ ሀይሉን ምት መቋቋም ተስኖት ተደምስሷል፡፡ ቀሪዎቹ ጥቂት የሽብር ቡድኑ ታጣቂዎችም ወደኋላ ማፈግፈጋቸው ነው ተገለጸው፡፡ በቀጣይም አሸባሪ ቡድኑን ከሰሜን ጎንደር ጠራርጎ ለማጥፋት የተጠናከረ እርምጃ እንደሚወሰድ የመከላከያ ሰራዊቱ አመራሮች ገልፀዋል፡፡ ከአሸባሪ ቡድኑ መደምሰስ ባለፈም በርካታ መሳሪያ መማረኩም ተገልጿል፡፡

ታሊባን የአዲሱን መንግስት አባላት በ3 ቀናት ውስጥ ሊያሳውቅ ነውከ20 አመታት በኋላ የአፍጋኒስታንን መንግስት ስልጣን የተረከበው ታሊባን፣ የመሰረተውን አዲስ መንግስት አባላት ከ2 እስከ 3ቀ...
04/09/2021

ታሊባን የአዲሱን መንግስት አባላት በ3 ቀናት ውስጥ ሊያሳውቅ ነው

ከ20 አመታት በኋላ የአፍጋኒስታንን መንግስት ስልጣን የተረከበው ታሊባን፣ የመሰረተውን አዲስ መንግስት አባላት ከ2 እስከ 3ቀናት ባለው ጊዜ ውስጥ እንደሚያሳውቅ ተዘግቧል፡፡ የታሊባንን ምክትል የባህል ኮሚሽን ሃላፊ ጠቅሶ እንደዘገበው፤ ታሊባን አዲስ መንግስት ለመመስረት ያደረገውን ስብሰባ አጠናቋል፤አባላቱንም ይፋ ያደርጋል፡፡

አሜሪካ ወታደሮቿን ከአፍጋኒስታን ካስወጣች በኋላ ለ20 አመታት ያህል ሲታገል የነበረውና በአሸባሪነት የተፈረጀው ታሊባን ቤተመንግስት መግባት ችሏል፡፡ ክስተቱ የአሜሪካን ሽንፈት ያሳየ ነው በሚል የበርካቶች መነጋገሪያ ሆኗል፡፡( )

ጠ/ሚር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት የሁርሶ የኮንቲጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ምልምል አባላትን እያስመረቀ ነው!በሀገር መከላከያ ሚኒሰቴር የሰላም ማስከበር ማዕከል የሁርሶ የኮንቲጀንት ማሰልጠ...
04/09/2021

ጠ/ሚር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት የሁርሶ የኮንቲጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ምልምል አባላትን እያስመረቀ ነው!

በሀገር መከላከያ ሚኒሰቴር የሰላም ማስከበር ማዕከል የሁርሶ የኮንቲጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ሶስተኛው ዙር በመሠረታዊ ወታደርነት ያሰለጠናቸውን ምልምል አባላትን እያስመረቀ ነው፡፡

በምርቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ፣ የመከላከያ ሰራዊት ኢታማዦር ሹም ጀነራል ብርሃኑ ጁላ እንዲሁም ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ደመቀ መኮንን ተገኝተዋል፡፡

Via EBC

142 የሽብር ቡድኑ አባላት ተደመሰሱ❗️በሰሜን ወሎ በኩል ሰርጎ የገባው ወራሪው የሕወሓት አሸባሪ ቡድን በጀግናው መከላከያ ሰራዊት አፀፋዊ እርምጃ ተወሰደበት፡፡በዚህም 142 የሽብር ቡድኑ ታ...
04/09/2021

142 የሽብር ቡድኑ አባላት ተደመሰሱ❗️

በሰሜን ወሎ በኩል ሰርጎ የገባው ወራሪው የሕወሓት አሸባሪ ቡድን በጀግናው መከላከያ ሰራዊት አፀፋዊ እርምጃ ተወሰደበት፡፡

በዚህም 142 የሽብር ቡድኑ ታጣቂ ኃይል ሲደመሰስ 4 ስናይፕር ፣ 6 የሞርታር ቅንቡላ ፣ 1 ብሬን ፣ 18 የእጅ ቦምብ ፣ 15 ክላሽ ፣ 7 ሺሕ የብሬን ጥይት ፣ 5 ሺሕ የክላሽ ጥይት ፣ 1 የመገናኛ ሬዲዬ (1187 አይኮም) ፣ 1 የዋይፋይ ሪሲቨር ፣ 6 የብሬን ሻንጣና 10 የነፍስ ወከፍ ወታደራዊ የወገብ ሻንጣ ከጠላት ተማርኳል።

ከግንባሩ አመራሮች መካከል የክፍለ ጦር ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽናል እንደተናገሩት ጠላት አሁን ላይ በሰራዊቱ እየደረሰበት ባለው ኪሳራና ባጋጠመው ሽንፈት የተስፋ መቁረጥ እንቅስቃሴዎችን እያደረገ ነው። ይሁን እንጅ ከገባበት መግደያ ወረዳ መውጣት እንደማይቻለው ጠቅሰው፥ ወራሪውን ኃይል በገባበት በማስቀረት በአጭር ጊዜ ውስጥ ለሕዝቡ የድል ዜና እናሰማለን ማለታቸውን የመከላከያ ሰራዊት መረጃ አመላክቷል፡፡

ሱዳን ምላሽ ሰጠች❗️ሱዳን በሰሜን ኢትዮጵያ ክፍል በኩል የኢትዮጵያ መንግስትን እየተዋጉ ለሚገኙት የትግራይ አማፅያን ድጋፍ ታደርጋለች መባሉን አጥብቃ አስተባበለች።ትላንት ሀገር መከላከያ ሰራ...
04/09/2021

ሱዳን ምላሽ ሰጠች❗️

ሱዳን በሰሜን ኢትዮጵያ ክፍል በኩል የኢትዮጵያ መንግስትን እየተዋጉ ለሚገኙት የትግራይ አማፅያን ድጋፍ ታደርጋለች መባሉን አጥብቃ አስተባበለች።

ትላንት ሀገር መከላከያ ሰራዊት ኢትዮጵያ እየገነባች ያለውን ግዙፉን የታላቁ ሕዳሴ የኃይል ማመንጫ ግድብ ግንባታ ለማደናቀፍ ከሱዳን በአልምሃል ሰርጎ ለመግባት የሞከረውን የህወሓት ቅጥረኛ ሃይል መደምሰሱን (50 መግደሉን፤ 70 ደግሞ ማቁሰሉን) ሪፖርት ማድረጉ ይታወሳል።

ይህንን ተከትሎ የሱዳን ጦር ቃል አቀባይ ብርጋዴር አል-ታሂር አቡ ሀጃ "መሰረተ ቢስ ውንጀላ" ሲሉ ውድቅ አድርገዋል።

አቡ ሃጃ ፥ "ሱዳን እና ሰራዊቷ በአጎራባች ኢትዮጵያ ወይም በሌሎች ሀገሮችን የውስጥ ጉዳይ ጣልቀ አይገቡም" ሲሉ ተናግረዋል።

አክለው፤ "ይህ መግለጫ የኢትዮጵያ ህዝብ የመብት ጥሰቶች በመቀጠላቸው ምክንያት የኢትዮጵያ አገዛዝ የገጠመውን ከባድ እውነታ ያንፀባርቃል” ብለዋል።

ከዚህ ቀደም ሱዳን ለአማፅያን የተለያዩ ድጋፎችን እያደረገችን እንደሆነ ሲገልፅ ነበር።

በትላንትናው ዕለት የሀገር መከላከያ ሰራዊት ከገለፀው በተጨማሪ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፖሊስ ፤ የፀጥታ ችግር ባለባቸው አካባቢዎች የታጣቂዎች እንቅስቃሴ በጣም ረጅም መሆኑን ገልጿል።

የክልሉ ም/ኮሚሽነር "በሱዳን አካባቢ የነበረው የፀረ ሰላም እንቅስቃሴ ከፍተኛ ነው፤ በመሳሪያ በሃሳብ፣ እዛ አካባቢ ያሉ ወጣቶችን መልምሎ ሱዳን አስቀምጦ የሚደግፉበትና ሽፋን የሚሰጡበት ሁኔታ አለ" ሲሉ አስረድተዋል።

ከሰሞኑን በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ፤ በካማሺ ዞን ፤ በሎ ጅጋንፎይ ወረዳ በታጣቂዎች በተፈፀመ ጥቃት ከ50 በላይ ሴቶች በጅምላ በግፍ መገደላቸውን የክልሉ ፖሊስ ሪፖርት ማድረጉ፤ ለጥቃቱ ደግሞ "ጉህዴን"ን ተጠያቂ ማድረጉ አይዘነጋም።

 ❗️መከላከያ ሰራዊቱ ደብረ ዘቢጥን አልፎ ኮኪትን ተቆጣጠረ!የአገር መከላከያ ሰራዊት ደብረ ዘቢጥን አልፎ ኮኪትን ሙሉ ለሙሉ በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ፡፡በሰሜን ምዕራብ እዝ የኮር አንድ...
03/09/2021

❗️
መከላከያ ሰራዊቱ ደብረ ዘቢጥን አልፎ ኮኪትን ተቆጣጠረ!

የአገር መከላከያ ሰራዊት ደብረ ዘቢጥን አልፎ ኮኪትን ሙሉ ለሙሉ በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ፡፡

በሰሜን ምዕራብ እዝ የኮር አንድ አዛዥ ብርጋዴል ጄኔራል ብርሀኑ ጥላሁን፤ የአሸባሪው ሕወሓት ቡድን ታጣቂዎች በአውደ ውግያ የሞቱባቸውን ህጻናት አስክሬን እንኳን ሳያነሱ፣ ትጥቅና መሳሪያቸውን ጥለው እየፈረጠጡም "እያሸነፍን ነው" ብለው የትግራይን ሕዝብ እያታለሉ ነው ሲሉ ገልፀዋል፡፡

በደብረ ዘቢጥ ግንባር ያለው የኢትዮጵያ ሠራዊት መልከዓምድሩና የአየር ጸባይ ሳይበግረው ድል እየተቀዳጀ ወደ ፊት እየገሰገሰ ይገኛልም ብለዋል፡፡

በአሁኑ ወቅትም ደብረ ዘቢጥን አልፎ ኮኪትን ሙሉ ለሙሉ በቁጥጥር ስር አውሏል ነው ያሉት፡፡ የሽብር ቡድኑ መሪዎች “እያሸነፍን ነው ካሉ ደብረ ዘቢጥ ሆነው መግለጫ መስጠት በቻሉ ነበር” በማለትም ሕዝቡ በአሸባሪው የሀሰት ወሬ መደናገር እንደሌለበት ስለመጠየቃቸው ኢፕድ ዘግቧል፡፡

 #ሰቆጣሰቆጣ ሙሉ በሙሉ በአማራ ልዩ ኃይል እና ሚሊሻ ስር ገብታለችጀግናው የአማራ ልዩ ኃይል እና የዋግ ሚሊሻ እና ወጣቶች ሰሞኑን ባደረጉት ዘመቻ ዛሬ ረፋድ ሦሰት ስዓት አካባቢ ሙሉ በሙሉ...
03/09/2021

#ሰቆጣ
ሰቆጣ ሙሉ በሙሉ በአማራ ልዩ ኃይል እና ሚሊሻ ስር ገብታለች

ጀግናው የአማራ ልዩ ኃይል እና የዋግ ሚሊሻ እና ወጣቶች ሰሞኑን ባደረጉት ዘመቻ ዛሬ ረፋድ ሦሰት ስዓት አካባቢ ሙሉ በሙሉ ሰቆጣ ከተማና አካባቢውን በቁጥጥር ስር አውለዋል፡፡

በዘመቻው የወገን ጦር ወራሪውን የትህነግ ኃይል አይቀጡ ቅጣት ቀጥቷል፡፡ በአሁኑ ጊዜም የማጽዳት እና የአሰሳ ሥራ እየሠራ መኾኑን አሚኮ ሰቆጣ በመገኘት ተመልክቷል፡፡

የሰቆጣ ከተማ ነዋሪ ለልዩ ኃይሉ እና ሚሊሻው ደማቅ አቀባበል አድርገዋል፡፡ ፡፡

ድሉ የመላው ሀገሪቱ እስከሚሆን ድረስ ትግላቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል፡፡

  : የወያኔን የውሸት ዜና እየሰማችሁ አታደንቁሩን እባካችሁ አንዳንዱ ጦርነት ላይ ያለንም አይመስለውም:: ጁመዓ እና ሀይቅ መስተጋብራቸው የተለየ ነው !!! የገበያ ቀን በመሆኑ ገበያተኛውም...
03/09/2021

: የወያኔን የውሸት ዜና እየሰማችሁ አታደንቁሩን እባካችሁ አንዳንዱ ጦርነት ላይ ያለንም አይመስለውም:: ጁመዓ እና ሀይቅ መስተጋብራቸው የተለየ ነው !!! የገበያ ቀን በመሆኑ ገበያተኛውም ፍፁም ሠላማዊ በሆነ መንገድ የተለመደ ገበያውን እየተገበያየ ነው ። ሀይቅ ምንም የተፈጠረ ነገር የለም! ወደ ተሁለድሬ እና ወረባቦ እየተምዘገዘገ የሚሄደውን ጀት ቤተሰብ ደውላችሁ ጠይቁ:: በተረፈ ህወሓት ተሁለድሬ እና ወረባቦ እየዋጀጀ ነው!

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Sen'Q Mereja ስንቅ መረጃ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share