ወቅታዊ ጉዳይ current Issue

  • Home
  • ወቅታዊ ጉዳይ current Issue

ወቅታዊ ጉዳይ current Issue focusing current issues

ስፖርት ለሰላም!!!የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተሳታፊ ክለባት ደጋፊዎች የእግር ኳስ ውድድር በአበበ ቢቂላ ስታዲየም እንደቀጠለ ነው።አሁን ቅዱስ ጊዮርጊስ ከወልቂጤ ከተማ በመጫወት ላይ ናቸው።አ...
25/09/2023

ስፖርት ለሰላም!!!

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተሳታፊ ክለባት ደጋፊዎች የእግር ኳስ ውድድር በአበበ ቢቂላ ስታዲየም እንደቀጠለ ነው።

አሁን ቅዱስ ጊዮርጊስ ከወልቂጤ ከተማ በመጫወት ላይ ናቸው።

አዘጋጆች:-ብራና ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ደጋፊዎች ማህበራት ጥምረት
የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ

የጅምላ ግድያ እንዲቆም ተጠየቀ!!!!!"እልቂትና ስር የሰደደ ድህነት የስልጣን ማስጠበቂያ ሆኗል።"
22/09/2023

የጅምላ ግድያ እንዲቆም ተጠየቀ!!!!!

"እልቂትና ስር የሰደደ ድህነት የስልጣን ማስጠበቂያ ሆኗል።"

Welcome to the official YouTube channel of AFRO ADDIS INFOTAINMENT. We are engaging in a current and updated information abut Ethiopia. We provide you update...

ሀገራችን የደረሰችበትን ጉድ ተመለከቱ!!!አዲስ አበባ ረቡዕ መስከረም 9/2015  አመሻሽ ላይ  ይሄ ሆነ              ፌደራል ፖሊስ ነን የሚሉ ሰዎች ከትራፊክ ፖሊስ ጋር በመተባበር ...
22/09/2023

ሀገራችን የደረሰችበትን ጉድ ተመለከቱ!!!

አዲስ አበባ ረቡዕ መስከረም 9/2015 አመሻሽ ላይ ይሄ ሆነ

ፌደራል ፖሊስ ነን የሚሉ ሰዎች ከትራፊክ ፖሊስ ጋር በመተባበር ኡስታዝ አቡበከርን አስቆሙት። «በመኪና ስርቆት ወንጀል ተጠርጥረሃል፤ የምትነዳው V8 መኪና የተሰረቀ ነው። ፖሊስ ጣቢያ ሂድ!» አሉት። ኡስታዝም የማጭበርበር ወንጀል መሆኑን ፈጥኖ በመረዳት ወደ ቤተሰብ ደውሎ አሳወቀ፤ ቤተሰብም በፍጥነት መጡለት ።

ከዚያም ቶታል 3 ቁጥር ማዞሪያ ወደ ሚገኘው ፖሊስ መምሪያ ይዘውት ሄዱ። ፌደራል ፖሊስ ነን ያሉት ግለሰቦች ሐሰተኛ መታወቂያቸውን ለፖሊሶች በማሳየት ኡስታዝ አቡበከርን እና መኪናውን ለፖሊስ መምሪያው አስረክበው ሄዱ።

ከለሊቱ 6 ሰዓት ሲሆን እነዚሁ አካላት ወደ ፖሊስ መምሪያው በመምጣት ተረኛ ፖሊሱን "ወንጀለኛው ፌደራል ፖሊስ ጋር ይፈለጋልና ስጡን!" አሏቸው። ፖሊሱም "ደብዳቤ ካላመጣችሁ አንሰጥም" የሚል ምላሽ ሰጣቸው።

አሳልፎ ቢሰጣቸው ኖሮ ኡስታዝን ገድለው መኪናውን ዘርፈው ይሰወሩ ነበር።

ትናንት ከሰዓት አከባቢ እነዚሁ አካላት ከለቡ ፖሊስ ጣቢያ ደብዳቤ በማምጣት ከሳሽ የሚገኘው ለቡ ፖሊስ ጣቢያ ነው በማለት ወደ ለቡ ፖሊስ ጣቢያ ወሰዱት።

ቤተሰብ የመኪናውን ሊብሬ ይዞ መንገድ ትራንስፖርት በመሄድ ሲያጣራ የመኪናው ሊብሬ በሌላ ሰው ስም ተቀይሯል።

ጉዳዩ አደገኛ የሆነ ሰንሰለት ያለበት ማጭበርበር ወንጀል መሆኑን በመረዳት ጉዳዩ ወደ ፌደራል ፖሊስ ወደ ከፍተኛ የፖሊስ አመራሮች እንዲደርስ ተደረገ።

መረጃው ወደ ሪፐብሊካን ጋርዶች ሲደርስ "የለቡ ፖሊስ ጉዳዩ እኔን አይመለከተኝም" በማለት ወደ ፔፕሲ ፋብሪካ ጎተራ ወደ ሚገኘው ፖሊስ ጣቢያ እንዲሄድ ተደረገ።

የፌደራል ፖሊስ አባላት ጎተራ ፖሊስ መምሪያ መጥተው ጉዳዩን ሲመረምሩ ፌደራል ፖሊስ ነን ያሉ አካላት ፌደራል ፖሊስ አባል እንዳልሆኑ እንዲሁም መኪናችንን ተሰርቀናል ብለው ሐሰተኛ ሊብሬ ያሰሩ አካላት በቁጥጥር ስር ዋሉ።

ኡስታዝ አቡበክር ሑሴን እንዲፈታ ተደረገ።

አሁን ጥያቄው የመኪና ሊብሬውን ማን ስሙን ቀየረ።
የእነዚህ ወንጀለኞች ሰንሰለት እስከምን ድረስ ነው? የሚለው ሲሆን በቀጣይ ፖሊስ የሚያጣራው ሆኖ ኡስታዝ አቡበከር ሁሴን ትናንት ሀሙስ ይህንን አስታውቋል።

ስፖርት ለሰላም!!!የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተሳታፊ ክለባት ደጋፊዎች የእግር ኳስ ውድድር በአበበ ቢቂላ ስታዲየም እንደቀጠለ ነው።አሁን ሲዳማ ቡና ከኢትዮጵያ መድን በመጫወት ላይ ናቸው።አዘጋ...
20/09/2023

ስፖርት ለሰላም!!!

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተሳታፊ ክለባት ደጋፊዎች የእግር ኳስ ውድድር በአበበ ቢቂላ ስታዲየም እንደቀጠለ ነው።

አሁን ሲዳማ ቡና ከኢትዮጵያ መድን በመጫወት ላይ ናቸው።

አዘጋጆች:-ብራና ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ደጋፊዎች ማህበራት ጥምረት
የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ

  የእንኳን አደረሳችሁ እና የምስጋና መርሀ-ግብር!!!!መስከረም 5 ቀን 2016 ዓ.ምፎቶ  #አቤልመስፍን
18/09/2023



የእንኳን አደረሳችሁ እና የምስጋና መርሀ-ግብር!!!!

መስከረም 5 ቀን 2016 ዓ.ም

ፎቶ #አቤልመስፍን

የትናንቱን የተከለከለው የኢትዮጵያ ታሪክ መጽሐፍ ምረቃ NBC እንደዘገበው!!!!
17/09/2023

የትናንቱን የተከለከለው የኢትዮጵያ ታሪክ መጽሐፍ ምረቃ NBC እንደዘገበው!!!!

National Media SC is here to support, the success of our country's transformational journey; to develop a civic-democratic political culture; which will be f...

እንኳን አደረሰን!!!!መልካም መመኘት መልካም ነው። በምንም ሁኔታ ውስጥ ከአመት አመት መሻገር መቻል መታደል ነው። በአዲሱ አመት ሀገራችንን ሰላም ትሁንልን!!!!የህዝብ ሰቆቃ ይብቃ!!!!መደ...
12/09/2023

እንኳን አደረሰን!!!!

መልካም መመኘት መልካም ነው። በምንም ሁኔታ ውስጥ ከአመት አመት መሻገር መቻል መታደል ነው።

በአዲሱ አመት ሀገራችንን ሰላም ትሁንልን!!!!

የህዝብ ሰቆቃ ይብቃ!!!!መደማመጥ ይስፈን!!!!እኛ የሚል መንፈስ ያሸንፍ!!!!!

ሞት፣እስር፣ስደት፣መፈናቀል ይብቃ!!!! ሀዘናችን ይብረድ፣ ደስታችን ይብዛ!!!

በእርግጥም አዲስ አመት ያድርግልን!!!!

01/09/2023

ልጅ ያሬድ የተባለውን ግለሰብ በህግ
ለመጠየቅ የሚያስችል ሥራ እየተሰራ ነው።

ነሐሴ ፳፮ ቀን ፳፻ ፲ወ፭ ዓ.ም

አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

ባለፉት ቀናት በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ቅጥር ውስጥ በመግባት ከእምነቷ ውጭ የሆነ መዝሙር የዘመረች ወጣት የፈጸመችው ተግባር ጥፋት መሆኑን አምና በፈጸመችው ጥፋት በመጸጸት በቅድስት ቤተ ክርሰቲያን አውደ ምህረት ተገኝታ ይቅርታ መጠየቋን ተከትሎ ልጅ ያሬድ የተባለ ግለሰብ እንኳን የኃይማኖት ሀገር በሆነችው ኢትዮጵያ ቀርቶ እምነት የለሽ በሚባሉት ሀገራት የማይደረግ የድፍረት ስድብና አጋንታዊ የሆነ ጸያፍ ቃላትን በመጠቀም በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ላይ በማህበራዊ ድህረ ገጹ ላይ በተደጋጋሚ ያስተላለፈውን መልዕክት ተመልክተነዋል።

በዚህ ድፍረት የተሞላበት ድርጊትም በርካታ ኦርቶዶክሳውያን አዝነዋል፣አልቅሰዋል፣ በድርጊቱ ክፉኛ በመበሳጨትም ከፍትህ አደባባይ ፍርድ
እንደሚጠብቁ በተለያየ መልኩ እያሳወቁ ናቸው።

ቤተ ክርስቲያን የክርስቶስን መስቀል ሁሌ መሸከም የየዕለት ተግባሯ ቢሆንም ከ፷ሚሊዮን በላይ ተከታይ ያላትንና ላለፉት ሁለት ሺህ ዘመናት ሀገርን በፍቅርና በስነምግባር ጥላ ሥር ሰብስባ ያኖረች ቤተ ክርስቲያን መሆንዋ እየታወቀ በእንዲህ አይነት በወረዳና ተሰምቶ በማያውቅ ድፍረት ቤተክርስቲያንን በመስደብ ሕዝበክርስቲያኑን ለማሳዘን መሞከር እጅግ አደገኛ ተግባር ነው።

ቤተክርስቲያንም ይህን ጸያፍ ተግባር የፈጸመና የተሳደበን ግለሰብ በዝምታ ማለፍ ስለማይገባት ጉዳዩን በህግ መምርያ በኩል በመከታተል ተገቢውን ሁሉ የምታደርግ መሆኑን ከወዲሁ እየገለጸች በህግ መምሪያችንና በህግ ባለሙያዎቻችን አማካኝነት አስፈላጊውን ሁሉ እስክታደርግ ድረስ ምዕመናን ከቅድስት ቤተክርስቲያን የተማራችሁትን ትዕግስትና ትህትናን መሰረት ባደረገ አግባብ በፍጹም ክርስቲያናዊ ጨዋነት እንድትጠብቁና በጉዳዩ ዙሪያ ከጸጥታ ከአካላት ጋር በትብብርና በአንድነት በመጠቆም እንድትተባሩ ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ጥሪዋን ታስተላልፋለች።

የ/ኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

ለምን አይናገር ይናገራል ፎቶ!!!!!
26/08/2023

ለምን አይናገር ይናገራል ፎቶ!!!!!

አረንጓዴው ጎርፍ!!ኢትዮጵያ!!!!እንኳን ደስ አለን!!!!!
26/08/2023

አረንጓዴው ጎርፍ!!

ኢትዮጵያ!!!!

እንኳን ደስ አለን!!!!!

26/08/2023

አረንጓዴው ጎርፍ!!!!!
ኢትዮጵያ!!!!!

22/08/2023

እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም በዓለ እርገት በሰላም አደረሰን ።

21/08/2023

ትናንት የሌላት ከተማ!!!!

ለዛሬው እናመሰግናለን!!!ነገም ሌላ ድል እንጠብቃለን!!!!
20/08/2023

ለዛሬው እናመሰግናለን!!!

ነገም ሌላ ድል እንጠብቃለን!!!!

ፈገግታሽ ይብዛ!!!!!!
20/08/2023

ፈገግታሽ ይብዛ!!!!!!

19/08/2023

ኢትዮጵያ ስታዝን፣ኢትዮጵያ አንገት ስትደፋ አትሌቲክስ የሚባል መጽናኛ ይሰጣታል!!!

19/08/2023

ምንም ማድረግ አይቻልም!!!

የመፅሐፍ ምርቃት!!!በገጣሚ የአብስራ ታምሩ የተጻፈው“ለተቀማጭ ሰማይ ቅርብ” የግጥም መድብልአርብ ነሐሴ 12 ከምሽት 11፡00ከአብርሆት ቤተመፅሐፍት ጀርባ በሚገኘውበዋሊያ ቤተመፅሕፍት ይመረቃ...
17/08/2023

የመፅሐፍ ምርቃት!!!

በገጣሚ የአብስራ ታምሩ የተጻፈው
“ለተቀማጭ ሰማይ ቅርብ” የግጥም መድብል
አርብ ነሐሴ 12 ከምሽት 11፡00
ከአብርሆት ቤተመፅሐፍት ጀርባ በሚገኘው
በዋሊያ ቤተመፅሕፍት ይመረቃል፡፡
በዚህ የተለያዩ ተጋባዥ እንግዶች ሐሳብ አስተያየታቸውን፣ ግጥምና ወጋቸውን በሚያቀርቡበት በሐገራችን ባልተለመደ መልኩ ደራሲንና ተደራሲን እያገናኘ በሚገኘው በዋሊያ ቤተመፅሐፍት እንድትገኙ በክብር ተጋብዛችኋል
ጠሪ አክባሪ ነው።
ፓስተር ቸሬ /ስለ ተቀማጭ ስነልቦና ሐሳብ ያካፍላል/
መጋቢ ሐዲስ እሸቱ አለማየሁ /የአካል ውስንነትና ስነፅሑፍን አያይዘው ለዛ ባለው ጨዋታቸው እያዋዙ ሐሳብ ያካፍላሉ/
እንዳለጌታ ከበደ /ስለመፅሃፉ አጭር ዳሰሳ ያካሂዳል/
አርቲስት ትዕግስት ግርማ ፣ ገጣሚ ምስራቅ ተረፈ፣ ደራሲና ዳይሬክተር ቢኒያም ወርቁና ገጣሚ የአብስራ ታምሩ ግጥም ለማቅረብ እናንተን ተጋባዥ እንግዶችን ይጠብቃሉ።
አርብ ነሐሴ 12 ከምሽቱ 11፡00
አራት ኪሎ በሚገኘው በዋሊያ ቤተመፃሕፍት እንገናኝ።
ጋባዣችሁ ገጣሚ የአብስራ ታምሩ
አትበሏት
የወላድ መካን ናት፣
ሐብት ጥሪት የሌላት፣
ሰላምም እራቃት፣
ፈረሰች አትበሏት፡፡
አትበሏት ሐገሬን!
ርስት ማረፊያየን፣
አልማዜ ናት ብርቅዬ፣
ዕንቁ ነች እምዬ፣
ምድሯ ሁኖ ለምለም፣
ፍሬዋ አይበሰብስም፣
አረም በዜቶ ቢታይም፣
ያፈራል ተውጦ አይቀርም፣
ችግር ቢያንዣብብ በማጀት፣
እህል ቢጠፋ ከሌማት፣
ታውቃለች ለራስዋ፣
አንድነት ነው ምስዋ፡፡ያፈራል ተውጦ አይቀርም፣
ችግር ቢያንዣብብ በማጀት፣
እህል ቢጠፋ ከሌማት፣
ታውቃለች ለራስዋ፣
አንድነት ነው ምስዋ፡፡

ፍቅር ተስፋን ያለመልማል...‼ "ለዕንቁዋ ዘመድ እንሁናት!" በሚል መሪ ቃል በሆስፒታል፣ በማረሚያ ቤት እንዲሁም በጎዳና ላይ የሚገኙ እህቶቻችንን የምንጎበኝበት "የበዓል መርሃ ግብር" ለ15...
16/08/2023

ፍቅር ተስፋን ያለመልማል...‼

"ለዕንቁዋ ዘመድ እንሁናት!" በሚል መሪ ቃል በሆስፒታል፣ በማረሚያ ቤት እንዲሁም በጎዳና ላይ የሚገኙ እህቶቻችንን የምንጎበኝበት "የበዓል መርሃ ግብር" ለ15ኛ ዙር የፊታችን መስከረም 1/2016 ዓ.ም "በአማኑኤል የአይምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል" የሚደረግ ይሆናል።

ከሆስፒታሉ ባገኘነው መረጃ መሰረት 88 ሴት ታካሚዎች የሚገኙ ሲሆን እነኚ እህቶቻችን የሚቸገሩት ደግሞ በዋናነት የውስጥ ሱሪ (ፓንት) ነው። ስለሆነም ሁላችንም የበኩላችንን ድጋፍ ብናደርግ ቢያንስ በነፍስ ወከፍ ሶስት ሶስት የውስጥ ሱሪ (ፓንት) የበዓል ስጦታ ማድረስ እንችላለን።

እንደሁልጊዜው ለዕንቁዎቻችንን ዘመድ በመሆን ደስ እናሰኛቸው ዘንድ የምትችሉ ሁሉ ለአንዲት እህታችሁ አንድ ፓንት እንድትገዙ እንጠይቃለን።

"ፍቅር ተስፋን ያለመልማል..ጨለማ በጨለመ ጊዜ እንኳ ብርሃን ይሆናል!!" እየሩ

ለተጨማሪ መረጃ
0911868458
0970070404

ዕንቁዋ ታብራ ውሜን ኢምፓወርመንት
ንግድ ባንክ 1000339685049
እናት ባንክ 0061112716013001
አዋሽ ባንክ 01308634871200

15/08/2023

ግራ ቀኝ!!!!

 #እንኳን ደሰ አላችሁ!!!! #ተመስገን🙏  OF TRADEMARK REGISTRATION LTM/13048ለአፍሪካ አፍሪካዊያን(Africa For Africans)ቤተሰቦች በአዕምሯዊ ንብረት ባለስልጣ...
13/08/2023

#እንኳን ደሰ አላችሁ!!!!
#ተመስገን🙏

OF TRADEMARK REGISTRATION LTM/13048

ለአፍሪካ አፍሪካዊያን(Africa For Africans)ቤተሰቦች በአዕምሯዊ ንብረት ባለስልጣን የዓለም አቀፍ ( Trademark )የባለቤትነቱን መብት ተረጋግጦ ሰርተፍኬቱን ወስደናል።

Abyssinia Business Network
For Africans
Union

 #ሀዋሳ  #ታቦርተራራ ተክያለሁ!!!!እኔ......በቅድመ አያቶቼ፣ አያቶቼ ፣አባቶቼ እና እናቶቼ/ሳምባ ተንፍሻለሁ!!!!እኔም ለቀጣይ ትውልድ መተንፈሻውን ተክያለሁ!!!!እንክብካቤውን ለከተማ...
12/08/2023

#ሀዋሳ
#ታቦርተራራ
ተክያለሁ!!!!

እኔ......በቅድመ አያቶቼ፣ አያቶቼ ፣አባቶቼ እና እናቶቼ
/ሳምባ ተንፍሻለሁ!!!!

እኔም ለቀጣይ ትውልድ መተንፈሻውን ተክያለሁ!!!!

እንክብካቤውን ለከተማው ነዋሪዎች አደራ ብያለሁ!!!!

እንኳን አደረሰን፣አደረሳችሁ!!!
07/08/2023

እንኳን አደረሰን፣አደረሳችሁ!!!

06/08/2023

አርሴዎች እንኳን ደስ አላችሁ!!!

100 ብር ለክለቤ!!!!የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ የደጋፊዎች ማህበር ገቢ ማሰባሰቢያ በሳፋየር አዲስ ሆቴል!!!
05/08/2023

100 ብር ለክለቤ!!!!

የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ የደጋፊዎች ማህበር ገቢ ማሰባሰቢያ

በሳፋየር አዲስ ሆቴል!!!

ቅዳሜ!!!!!ከሳምንት እስከ ሳምንት በጤና ላሻገርከኝ አምላክ ስምህ የተመሰገነ ይሁን!!!!አሜን!!!!!!"ኩርፊያ የሸፈነው ፈገግታ!!!"  እንዲል ስዩም ወልዴ ራምሴ ፈገግታችን ሙሉ ይሆን ዘ...
05/08/2023

ቅዳሜ!!!!!

ከሳምንት እስከ ሳምንት በጤና ላሻገርከኝ አምላክ ስምህ የተመሰገነ ይሁን!!!!

አሜን!!!!!!

"ኩርፊያ የሸፈነው ፈገግታ!!!" እንዲል ስዩም ወልዴ ራምሴ ፈገግታችን ሙሉ ይሆን ዘንድ ፈጣሪ ለኢትዮጵያ ሰላምን ይስጣት!!!!

እኛ እንደ ህዝብ ሰላምን ይዘን ውለን ለማደር ባለመታደላችን እነሆ ተስፋችን እግዚአብሔር ብቻ ሆኗል። መከራችን፣እልቂታችን፣ሀዘናችን መቼ እንደሚያበቃ አናውቅም።

የሀገሬ ጉዳይ "ጠብ ሲል ስደፍን!!" አይነት እየሆነ ተቸግረናል። አንዱን ችግር ሳንጨርስ ሌላው ይከተላል።

መደማመጥ፣ስክነት፣ብስለት፣ ሆደ ሰፊነትን ከተነጠቅን ቆየን። መንግስትም እንደ መንግስት ፣ህዝብም እንደ ህዝብ መሆን አቅቶን ሰርክ በውጥንቅጥ እንዳክራለን።

እንደ ሀገር በሰላም እጦት እና በሰቀቀን አምስት አመታትን አሳልፈን።በመሐከላችን ነገም ተስፋ ያለ አይመስልም።የጋራ ጉዞን ትተን ለየብቻችን መጓዝን መርጠናል። በውስጣችን ጫፍ እና ጫፍ እንጂ መሀከል የሚባል ነገር ጠፍቷል። ለዚህም ነው ተስፋችን እግዚአብሔር ብቻ ነው የምንለው።

ቢያንስ በዚህ ቀን እንኳን መልካሙን እንመኝ!!!!መልካም ነገሮችን እንከውን።

መልካም ቅዳሜ!!!!

ሁላችሁንም እወዳችኋለሁ!!!!

ዛሬ ወደ መቄዶኒያ ሔድኩ!!!!በእውነት ብዙ ቀን ወደዚያ ለመሄድ አሰብኩ ግን ዛሬ ተሳካልኝ። ደስም አለኝ!!!!!መቄዶኒያን የአረጋውያንና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከልን  በተለያዩ ጊዜአት ...
03/08/2023

ዛሬ ወደ መቄዶኒያ ሔድኩ!!!!

በእውነት ብዙ ቀን ወደዚያ ለመሄድ አሰብኩ ግን ዛሬ ተሳካልኝ። ደስም አለኝ!!!!!
መቄዶኒያን የአረጋውያንና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከልን በተለያዩ ጊዜአት በግልም በቡድንም ጎብኝቸዋለሁ። ሁሌም ደግሞ መሄድን እመኛለሁ።በሄድኩ ቁጥር ማዕከሉ እጄን በአፌ ያስጭነኛል። በማዕከሉ ሁሉም ግቢዎች ሁሌም አዲስ ነገር አለ። ዛሬም ማዕከሉን እንደ አዲስ ጎበኘሁት።

የሰው ጎርፍ ከወዲያ ወዲህ ይፈሳል። ወንዱ ሴቱ፣ታዳጊ ወጣቱ፣ አረጋውያን እና የአዕምሮ ጤና ህሙማን ከማዕከሉ ሰራተኞች እና በጎ ፈቃደኞች ጋር ሆነው ማዕከሉን ሞልተውታል። የመቄዶኒያ አያት ጠበል አካባቢ የሚገኘው ማዕከል ብቻውን ለ6,000 የቀረቡ ተጠቃሚዎችን ሸክፏል።ዝም ብላችሁ በዚያ ግቢ ብቻ የሚሆነውን አስቡ!!!

የማዕከሉ የህንጻ ግንባታ በአስገራሚ ፍጥነት እየተጓዘ ነው። ባለ አስራ አምስት ወለሉ ህንጻ የምድር ቤቱ እና የመጀመሪያው ወለል ገና ካሁኑ አገልግሎት ለመስጠት ተገዷል። ምክንያቱም የህንጻው ግንባታ ሙሉ በሙሉ እስኪጠናቀቅ መጠበቅ አልተቻለም ወደ ማዕከሉ በየዕለቱ በርካቶች ይመጣሉ። ያም ሆኖ የህንጻው ግንባታ ቀጥሏል። አሁን ወደ ማጠናቀቂያ ስራዎች እያመራ ነው።የህንጻው ግንባታ ይፋጠን ዘንድም ሁሉም ባለው አቅም እያገዘ ነው። ምናልባትም 2016 ዓ. ም አዲስ አመት ህልማቸው እውን የመሆን ዕድል ያለው ይመስላል ።እናም ግቢው ለጉድ በእንቅስቃሴ ሰጥሟል። ሁሉንም ዞሬ ተመለከትኩ።

መቄዶኒያ ግቢው በ50,00 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ በመሆኑ የተጀመረው የህንጻ ግንባታ ሲጠናቀቅ ቀጣይ የጋራ የቤት ስራ እንዳለብን የሚያሳይ መሰል የህንጻ ግንባታ እንቅስቃሴ ተጀምሯል። መቄዶኒያ በአዲስ አበባ ካሉት ማዕከላት በተጨማሪም በመላው ኢትዮጵያ ተደራሽነቱን በ25 ከተሞች አድርጎ ቅርንጫፎቹን አስፍቷል።
እናም ጉብኝቴን ስጨርስ ይሄንን ጥያቄ ራሴን ጠየኩ። መቄዶኒያ እና መሰል በጎ አድራጎት ድርጅቶች ባይኖሩ የእነዚህ ኢትዮጵያውያን ዕጣ-ምን ይሆን ነበር???

አቦ ለበጎነት የተፈጠራችሁ እግዚአብሔር ብድራችሁን ይመልስላችሁ።

እኛም የምንችለውን ማድረጋችንን እንቀጠል!!!!!

አስጎብኚዬን ቃለወልድን አመሰግናለሁ!!!!!

ዝግጁ ናችሁ!!!!!፻ ብር ለክለቤቅዳሜ ሐምሌ 29/2015 ዓ.ም ከማለዳው 12:00 ሰዓት እስከ ምሽት 12:00 ሰዓት
01/08/2023

ዝግጁ ናችሁ!!!!!

፻ ብር ለክለቤ
ቅዳሜ ሐምሌ 29/2015 ዓ.ም ከማለዳው 12:00 ሰዓት እስከ ምሽት 12:00 ሰዓት

 #ታማኙ
01/08/2023

#ታማኙ

30/07/2023

ለአለም እና አካባቢዋ ሎሬት Tewodros Teklearegay የቀረበ ጥያቄ???

እንደው ክረምትና ኤሌክትሪክ ምን እና ምን ናቸው???

ሀ/እሳትና ጭድ
ለ/ ጌታና ሎሌ
ሐ/ደመና እና ጨለማ

እንደው በክረምት መብራት እንዲህ ይናፍቀን????

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ወቅታዊ ጉዳይ current Issue posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share