Infra Ethiopia - ኢንፍራ ኢትዮጵያ

Infra Ethiopia - ኢንፍራ ኢትዮጵያ We report, research, network, identify, and audit Ethiopian infrastructure data. Our company aspires

አወዛጋቢው ኢግል ሂልስ የቢሊዮኖች ዳላር ኮንትራት አገኘ◉◉◉በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ለገሃር አካባቢ በሪል ስቴት ልማት ዘርፍ ላይ የተሠማራው እና ተቀማጭነቱ በአቡዳቢ ውስጥ ያደረገው ኢግል...
13/06/2024

አወዛጋቢው ኢግል ሂልስ የቢሊዮኖች ዳላር ኮንትራት አገኘ
◉◉◉
በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ለገሃር አካባቢ በሪል ስቴት ልማት ዘርፍ ላይ የተሠማራው እና ተቀማጭነቱ በአቡዳቢ ውስጥ ያደረገው ኢግል ሂልስ በ1.5 ቢሊየን ዶላር ባግዳድ ውስጥ የጎልፍ መጫወቻ ሪዞርት ሊገነባ ነው።

ኤግል ሂልስ ለጎልፍ መጫወቻ እና ለጤና መጠበቂያ ማዕከል መስሪያ የሚሆን መሬት በኢራቅ ዋና ከተማ ባግዳድ ውስጥ መረከቡን አስታውቋል።

ከዚህም በተጨማሪ የጎልፍ መጫወቻ ማዕከሉ የቅንጡ የመኖሪያ አፓርትመንቶች፣ ባለአምስት ኮከብ ሆቴል፣ ሪዞርት ክለብ ግንባታዎች ይኖሩታል።

መግለጫው ይፋ የተደረገው በኢራቅ ጠቅላይ ሚንስትር ሞሃመድ ሺያ አል ሱዳን እናመካከል
ሂልስ ሊቀመንበር ሞሃመድ አላባር መካከል ውይይት መካሄዱን ተከትሎ ነው።

በጋሞ ዞን ዳራማሎ ወረዳ በዋጫ ከተማ  በኀብረተሰቡ ዘንድ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የመንገድ ሥራ በዛሬው ዕለት የአስፋልት ንጣፍ ሥራ መጀመሩን የዳራማሎ ወረዳ አስተዳደር ገልጿል።
09/06/2024

በጋሞ ዞን ዳራማሎ ወረዳ በዋጫ ከተማ በኀብረተሰቡ ዘንድ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የመንገድ ሥራ በዛሬው ዕለት የአስፋልት ንጣፍ ሥራ መጀመሩን የዳራማሎ ወረዳ አስተዳደር ገልጿል።

የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው አሁናዊ ሁኔታ ልብ ሰባሪ እና አንገት አስደፊ ነው፦ ጥናት◉◉◉በቅርቡ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከተማና መሠረተ ልማት እንዲሁም የትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ...
09/06/2024

የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው አሁናዊ ሁኔታ ልብ ሰባሪ እና አንገት አስደፊ ነው፦ ጥናት
◉◉◉
በቅርቡ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከተማና መሠረተ ልማት እንዲሁም የትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በኢንዱስትሪው ተግዳሮቶችና መፍትሄዎቻቸው ላይ ጥናቶችን በዘርፉ ባለሙያዎች አሠርቶ እንዲመከርባቸው አድርጓል።

በመድረኩ አራት ጥናቶች የቀረቡ ሲሆን፣ ከጥናቶቹ መካከልም በኢንጂነር ዳዊት ኡርጌቾ "የሥራ ተቋራጮች፣ የአማካሪዎችና ግብአት አቅራቢዎች ተግዳሮቶችና መፍትሄዎቻቸው" በሚል ርዕስ የቀረበው ጽሑፍ አንዱ ነው።

ኢንጂነር ዳዊት የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ደግሞ በሀይድሮሎጂና ወተር ሪሶርስ ከቻይና ያገኙ ናቸው:: የኢትዮጵያ ኮንሰልቲንግ ኢንጂነርስ ኤንድ አርክቴክስ አሶሴሽንን በፕሬዚዳንትነት እያገለገሉ የሚገኙ ሲሆኑ፤ የኤልዳ ኢንጂነሪግ ኮንሰልታንት መስራችና ማኔጂንግ ዳይሬክተርም ናቸው:: በሙያው ከ30 አመት በላይ ተሞክሮ አላቸው::

ኢንጂነር ዳዊት ‹‹ኢንዱስትሪያችን በተለያዩ ፈተናዎች ውስጥ ስለመሆኑ እናውቃለን፤ ከዚህ አኳያ የኢንዱስትሪው ተሳታፊዎች አካፋና ዶማውን ይዘን፣ ግንባር ላይ ሆነን የዘርፉ ምልከታችን ምን ይመስላል፤ ከዚያ ባሻገር ያለውንስ በምን መንገድ እንጠቁም›› በሚል ጥናታቸውን አቅርበዋል።

የኢንዱስትሪው አሁናዊ ሁኔታ... ልብ ሰባሪ፣ አንገት አስደፊ ሁኔታ ነው፤ ይህ ሁኔታ መቀየር አለበት፤ ከዚህ ቅርቃር ለመውጣት ከስህተቶቻችን ከተማርን መፍትሄውን ራሳችን እንፈጥራለን ብለን እናስባለን። ስለዚህ በኢንዱስትሪው ላይ ተስፋ እንጂ ጨለምተኝነት የለንም ሲሉ አስገንዝበዋል።

ቻይናዎች ቀውስን በሁለት ከፍለው ይገልጹታል ያሉት ኢንጂነሩ፣ አንደኛውን ከአደጋ፣ ሁለተኛውን ደግሞ ከመልካም እድል አኳያ ብለው እንደሚመለከቱት ይገልጻሉ። ቀውስ መልካም አጋጣሚ ፈጣሪ መሆኑን እንደሚረዱ ነው ያመለከቱት። ቻይናውያን እኛ አሁን ካለንበት አስከፊ ሁኔታ በባሰ ሁኔታ ውስጥ ኖረው ያውቃሉ:: ከዚያ ወጥተው ነው አሁን ለደረሱበት ደረጃ የበቁት ብለዋል።

እኛም ከስህተቶቻችን ከተማርን ከዚያ ደረጃ የማንደርስበት ሁኔታ አይኖርም ብለን እናምናለን ያሉት ኢንጂነሩ፣ እኛ ማነን ለሚለው የሥራ ተቋራጮች፣ አማካሪዎች፣ የግንባታ ግብአት አቅራቢዎች እና በስሮቻችን የሚተዳደሩ ባለሙያዎች ይሳተፋሉ። ከውጪም ባለቤቶች፣ አሠሪዎችና ተቆጣጣሪ አካላት አሉ ሲሉ አመልክተዋል።

ኢንጂነሩ ‹‹ሁሉም ሰው ይህን ኢንዱስትሪ የሚረዳው በጊዜ አላለቀም፤ ከተያዘለት በጀት በላይ ሆኗል፤ ጥራቱ አሁንም እየወደቀ ነው ከሚሉት አኳያ ነው፤ እነዚህ ሦስቱ የፕሮጀክት ማኔጅመነት አካላት ናቸው›› ሲሉ ጠቅሰው፣ የችግሩ መገለጫዎች ናቸው እንጂ የችግሩ ጠቋሚዎች ሆነው መታየት አለባቸው እንጂ የችግሩ ምንጮች አይደሉም፤ ለእነዚህ ችግሮች ቶሎ ደራሽ መፍትሄ እንፈጥራለን ብለን ማሰብ የለብንም:: መሰረታዊውን ችግር ፈልገን ተንትነን ልንደርስበት ይገባል ብለዋል።

በተደጋጋሚ እንደተጠቆመው፤ ዘርፉ ለብልሹ አሰራር የተጋለጠ ነው፤ የግዥ ስርአቱ ሊዘምንና ጊዜውን የዋጀ ሊሆን ይገባል ካሉ በኃላ፦ የዘርፉ ዋነኛ ተግዳሮቶች ከሆኑት መካከል የፕሮጀክቶች ደካማ አፈጻጸም የሚለው አንዱ መስተካከል ያለበት መሆኑን ሲሆን፣ ሁለተኛው የኢንዱስትሪውን ተወዳዳሪነት መጨመር፣ ሦስተኛው የባለሙያ ብቃት ጉዳይ፣ አራተኛው ከውጭ የሚገቡ የግንባታ እቃዎች ላይ ያለውን ጥገኝነት መቀነስ መሆናቸውን ጠቁመዋል::

እሳቸው እንዳብራሩት፤ ኢንዱስትሪው የሥራ እድል በመፍጠርና ኢኮኖሚውን በማንቀሳቀስ ከፍተኛ ስፍራ እንዳለው ይታወቃል፤ የስራ ተቋራጮች ዝቅተኛ በሆነ የፕሮጀክት አስተዳደር ብስለት ደረጃ ላይ ይገኛሉ:: ከገንዘብና ተቋማዊ አቅም ውስንነት አኳያም እንዲሁ የተገደበ ኢንዱስትሪ ነው፤ ብዙ ጊዜ በክፍያ መዘግየት ክፍተቶች ሲፈጠሩ ድልድይ የሆነ የፋይናንስ አማራጭ ባለመኖሩ በቀላሉ ለአደጋና ለጉዳት ተጋላጭ ነው:: የስነ ምግባር ጉድለት በሁሉም የኢንዱስትሪው ተዋንያን ላይ ያለና ሊቀረፍ የሚገባው ነው::

ለሀገር በቀል ድርጅቶች ተወዳዳሪነትን የሚያጎለበት በቂ ጥበቃና ድጋፍ አለመኖር ይስተዋላል የሚል እይታም አለ፤ ይህ በምን ይገለጻል ከተባለም በሌሎች ሀገሮች ስራ ሲወጣ የሀገር ውስጥ ተቋራጮች በተቋራጭ መረጣ መስፈርት /ኢቫልዌሽን ክራይቴሪያ/ ሰባት ወይም አስር በመቶ የማሸነፍ እድል እንዲኖራቸው ይደረጋል:: ይህ ግን በኢትዮጵያ የለም፤ ለውጭ ተቋራጮች የውጭ ምንዛሪ አቅርቦት ሲደረግ ለሀገር ውስጥ ተቋራጮች አይደረግም። ለግብአት አቅርቦት የሚያስፈልጋቸውን 30 በመቶ የውጭ ምንዛሪ አግኝተው መስራት ሲገባቸው የሚያገኙበት ሁኔታ የለም፤ ይህም ተወዳዳሪ እንዳይሆኑ ያግዳቸዋል::

የሰው ኃይሉ ምርታማነት እንዲሁም የክህሎት ደረጃ ዝቅተኛ ደረጃ ላይ መገኘትም ሌላው ችግር ነው:: ከአማካሪ ውስጣዊ እይታም አኳያ ዝቅተኛ የፕሮጀክት አስተዳደር ብስለት ሁሉም ዘንድ ያለ ችግር ነው:: ከእቃ አቅራቢዎች ውስጣዊ እይታ አኳያም እንዲሁ የዘርፉ ዋና ዋና ተዋናዮች እንደ ባለቤት አለመታየትና መገፋት ነገር ይታያል የሚባል ቅሬታም ይሰማል::

የአቅርቦት ሰንሰለቱ ዘላቂ እንዲሆን በሚል ለሚዘጋጅ እቅድ ዳታ ሲፈልግ በተገኘ መረጃ መሰረትም ስራዎች ከወጡና ውለታ ከተገባባቸው በበኋላ እንጂ በጨረታ እና በሀሳብ ደረጃ እያሉ እነዚህን አካላት የማቅረብ ሁኔታ አይታይም፤ በዚህ በኩል ትልቅ እንቅፋት እየተፈጠረ ነው የሚል ቅሬታ ይነሳል::

ላለፉት ጥቂት ዓመታት በኛ በኩል የዘርፉን ተዋናዮች ቀርቦ በማነጋገርና በማወያየት አዋጆች ፖሊሲዎችና የመሳሰሉት ሲወጡ በረቂቅ ሰነድ ደረጃ ንቁ ተሳትፎ እንድናደርግና አብረን እንድንሠራ እየተደረገ ያለውን ጥረት ሳናደንቅ አናልፍም ሲሉም ኢንጂነር ዳዊት ጠቅሰዋል::

የፋይናንስ ተቋማት አለመኖራቸው፤ ለኮንስትራክሽን እቃዎች አንድ ወጥ የሆነ ሀገር አቀፍ ስታንዳርድ አለመኖሩ፣ አንዳንዴም ጥራትን ያላሟሉ እቃዎች በግንባታ ስራ ውስጥ ሲካተቱ የሚስተዋልበት ሁኔታም ሌሎች ችግሮች መሆናቸውን አመልክተዋል::

እሳቸው እንዳብራሩት፤ የዋና ዋና የዘርፉ ተዋንያን ውጫዊ ምልከታ ከተቆጣጣሪና አስፈጻሚዎቹ አኳያ ሲታይ ተቋማዊ ውስንነት ይስተዋላል:: በግዥ ፣በሙያ ምዝገባና ፈቃድ አሰጣጥ ላይ ወጥነት ያለውና በምርጥ ተሞክሮ ላይ የተመሰረተ ደንብና አሰራር አለመከተል፣ ምርጥ ተሞክሮን ለመቀበልና ጊዜውን የዋጀ አሰራርን ለመቀበል ዳተኛ መሆን፣ ዘርፉ የሚመራባቸው ወጥ የህግ ማእቀፎች፣ ስልቶች፣ መመሪያዎች፣ የአሰራር ደንቦችና ሂደቶች አለመኖር፣ የቁጥጥር ስራዎችን ለመተግበር ያለ የአቅም ውስንነት ይታያሉ::

አሰሪና ባለቤቶችን በሚመለከት የፕሮጀክት ማስተዳደር ደረጃ፣ የስነ ምግባር ጉድለቱም በሁሉም ዘንድ እንደሚስተዋል፣ ደካማ የፋይናንስ አቅምና የክፍያ መዘግየት ፣ ጣልቃ ገብነት እንደሚታይም ጠቁመዋል:: በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር በኩል ወሰን የማስከበር ስራው ከአቅም በላይ ሆኖ እንደሚታይም ጠቅሰው፣ በመንገድ በኩል አንዳንዴም ከግንባታ ክፍያው በላይ የወሰን ማስከበር ከፍያው ከፍተኛ እየሆነ ያለበት ሁኔታም ወጪውን እየተፈታተነው ያለበት ሁኔታ በትኩረት ሊታይ ይገባዋል ሲሉ አስገንዝበዋል::

ወደ ስኬት ለመሄድስ ምን ማድረግ ይገባል ሲሉም ጠይቀው፣ ችግር ላይ ቆም ከመቆዘም ይልቅ ከችግራችን በመማር ወደፊት ለመሻገር መስራት ያዋጣናል ሲሉም ነው ያስታወቁት::

አሁን ያለው ደካማ የፕሮጀክት አፈጻጸም እንዴት ሊቀረፍ ይችላል? ሲሉም ጠይቀው፣ ይህ ችግር ጊዜ ሊሰጠው አይገባም፤ ለሌሎች ወገኖች አሳልፈን የምንሰጠውም አይደለም:: በጋራ በመሆን በአስቸኳይ መፍትሄ ልንሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነው ብለዋል:: ሁለተኛ የኢንዱስትውን ተወዳዳሪነት በሀገር ውስጥና በቀጣናው የማሳደግ ጉዳይ መሆኑን አመልክተው፣ ይሄ በአዲሱ የዘርፉ ፖሊሲ ላይ መቀመጡን ተናግረዋል:: እንዴት እናሳካዋለን የሚለው በተወሰነ ደረጃ ሲታይም ሙያዊ ብቃትን ማሳደግ ይገባል የሚለው አንዱ መፍትሄ መሆኑን አመላክተዋል።

የግዥ ሂደቱን በተመለከተ ሲያብራሩ፣ ሂደቱ አንዳንዴ ሥራውን ከምንከውንበት የበለጠ ጊዜ ሲወስድ እንደሚታይ ጠቅሰው፣ ይህም ሊፈተሸ የሚገባው የጊዜ ሂደት አለ ማለት ነው ብለዋል።

የችግሮች መፍቻው መንገድ በእኔ እይታ እስከ አሁን ያለን አቀራረብ ሁለንተናዊና በስርአት የሚመራ (systematic) አካሄድን የተከተለ አይደለም ሲሉም ጠቅሰው፣ ብዙ ጊዜ ከባህል ጋር ተያይዞ ይሁን ከአስተዳደግ የጦሱን ዶሮ ፍለጋ ላይ ነው የምናተኩረው ሲሉ ያስገነዝባሉ። ማነው ጥፋተኛው እንላለን እንጂ ከዚህ ጥፋት ምን እንማራለን ብለን አንሰራም፤ ከዚህ አካሄድ ካልወጣን መፍትሄ አናገኝም ብለዋል።

በአቬዬሽን ኢንዱስትሪ ውስጥ አንድ የተለመደ ነገር አለ ያሉት ኢንጂነሩ፣ እያንዳንዱ የአውሮፕላን አደጋ የሚቀጥለውን የአውሮፕላን ጉዞ ጤናማ ያደርገዋል ተብሎ እንደሚታይ አስታውቀው፣ ከችግር የመማርን አስፈላጊነት አመልክተዋል::

ስኬትም ክሸፈትም ያለባቸው ብዙ ፕሮጀክቶችን ሰርተናል፤ ላለፉት ሰላሳ አመታት የዳበረ እውቀት አግኝተናል። እነዚህን ፕሮጀክቶች በሚገባ አጥንተን ወደ መፍትሄ ፍለጋ ከሄድን መፍትሄው እጃችን ውስጥ ነው፤ ከስኬታችን ከክሽፈታችን መማር ለችግሮቻችን ዋናው መፍትሄ ነው፤ ስለዚህ በችግሮች ስረ መሠረት ላይ ትንታኔ መሤራት ይኖርብናል ብለዋል።

የግንባታ ግብአቶችን በሚመለከት በፖሊሲው የገቢ ምርት መተካት በግልጽ ተቀምጧል። ይህንንም ‹‹የቲንክታንክ ቡድኑ›› የሚያየው ጉዳይ ይሆናል ሲሉም ጠቅሰዋል:: ኢንጂነሩ ሲዛር ፔሊ የሚባለው የማሌዢያው ፕትሮናስ ህንጻ አርክቴክት ‹‹ኮንስትራክሽን በጨለምተኝነት የመቆዘም ሳይሆን የብሩህ ተስፋ ጉዳይ ነው፤ የወደፊቱን በልበ ሙሉነት የመጋፈጥ ጉዳይ ነው›› ሲል የገለጸውን ጠቅሰው፣ ዘርፉ በችግሮች የተተበተበ ቢሆንም ተስፋም አብሮት እንዳለና የችግሮችን ስር መሰረት በመለየት ለመፍታት መረባረብ እንደሚገባም አስገነዝበዋል።
- EPA-
◉◉◉
ለተጨማሪ ዝርዝር መረጃዎች የቴሌግራም ቻናላችንን ይጎብኙ። t.me/infraethiopia

በኢትዮጵያ ትልቁ ሰማይ ጠቀስ ሕንፃ የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከአለም ትልልቆቹ ሰማይ ታካኪ ሕንፃዎች ጋር ሲወዳደር!Comparing the Commercial Bank of Ethiopia's...
09/06/2024

በኢትዮጵያ ትልቁ ሰማይ ጠቀስ ሕንፃ የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከአለም ትልልቆቹ ሰማይ ታካኪ ሕንፃዎች ጋር ሲወዳደር!

Comparing the Commercial Bank of Ethiopia's building with the tallest buildings in the world!
◉◉◉
(Driving in Ethiopia)

ኢራቅ ከነዳጅ ዘይት የምታገኘውን ገቢ ቀስ በቀስ በመሠረተ ልማት ላይ ማዋል ጀምራለች።ኢርቢል በተባለ በኢራቅ የኩርዲስታን ግዛት ውስጥ የተገነባው ዘመናዊ ፈጣን መንገድ በብዙዎች አድናቆት የተ...
08/06/2024

ኢራቅ ከነዳጅ ዘይት የምታገኘውን ገቢ ቀስ በቀስ በመሠረተ ልማት ላይ ማዋል ጀምራለች።
ኢርቢል በተባለ በኢራቅ የኩርዲስታን ግዛት ውስጥ የተገነባው ዘመናዊ ፈጣን መንገድ በብዙዎች አድናቆት የተቸረው ነው።

በናሚቢያ ዋና ከተማ ዊንድሆክ ውስጥ "ዞር ዞር" እያልን ነው።😍
06/06/2024

በናሚቢያ ዋና ከተማ ዊንድሆክ ውስጥ
"ዞር ዞር" እያልን ነው።😍

የዱርቤቴ - ቁንዝላ - ገላጎ - መተማ መንገድ ፕሮጀክቶች፦❇️ ዜጂአንግ ኮሚኒኬሽን ኮንስትራክሽን ግሩፕ እየገነባ ነው ❇️ ፕሮጀክቶቹ 5.4 ቢሊዮን ብር ይፈጃሉ◉◉◉ በአማራ ክልል ሰሜን ጎጃ...
06/06/2024

የዱርቤቴ - ቁንዝላ - ገላጎ - መተማ መንገድ ፕሮጀክቶች፦

❇️ ዜጂአንግ ኮሚኒኬሽን ኮንስትራክሽን ግሩፕ እየገነባ ነው

❇️ ፕሮጀክቶቹ 5.4 ቢሊዮን ብር ይፈጃሉ

◉◉◉
በአማራ ክልል ሰሜን ጎጃም ዞንን ከማዕከላዊ እና ምዕራብ ጎንደር ዞኖች ጋር የሚያስተሳስሩት የኮንትራት - አንድ ዱርቤቴ - ቁንዝላ - ሻውራ - ፍንጅት እንዲሁም የኮንትራት - ሦስት የገላጎ - ገንደ ውኃ መንገድ ፕሮጀክቶች አፈጻጸም ለማሻሻል እየተሠራ ነው።

የመንገድ ግንባታዎቹ በጥቅሉ 260 ነጥብ 5 ኪሎሜትሮችን የሚሸፍኑ ሲኾን፣ የአዲስ አበባ - ደብረማርቆስ - ባሕርዳር እና የጎንደር - አዘዞ - መተማ ዋና መንገዶችን የሚያገናኙ ናቸው፡፡

አሁን ላይ የዲዛይን፣ የአፈር ቆረጣ እና ጠረጋ፣ የሰቤዝ እንዲሁም የተፋሰስ እና የድልድይ ሥራዎች ተሠርተዋል፡፡ በተጨማሪም የአስፋልት ንጣፍ ለመጀመር የሚያስችሉ የክሬሸር እና የአስፋልት ፕላንት ተከላ ተካሂዷል፡፡

ዜጂአንግ ኮሚኒኬሽን ኮንስትራክሽን ግሩፕ ግንባታዎቹን በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡ ለፕሮጀክቶቹ 5 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር የተመደበ ሲኾን፣ ወጪው በፊደራል መንግስት በጀት ይሸፈናል፡፡

በክልሉ በተከሰተው የጸጥታ ችግር ምክንያት ግንባታው አልፎ አልፎ መቋረጡ እና ከዚህም ጋር በተያያዘ የግንባታ ግብዓቶችን በቀላሉ ወደ ፕሮጀክቱ ሥፍራ ማንቀሳቀስ አለመቻሉ እንዲሁም የሥራ ተቋራጩ ደካማ አፈጻጸም በግንባታው ላይ የገጠሙ ፈተናዎች ናቸው፡፡

ከጸጥታ ስጋት ጋር በተያያዘ ከየአካባቢው ሽማግሌዎች እና ጉዳዩ በቀጥታ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት ግንባታው እንዳይቋረጥ ማድረግ ተችሏል፡፡ በሥራ ተቋራጩ በኩል አፈጻጸሙን ለማሻሻል የሚያስችሉ የተለያዩ የእርምት ዕርምጃዎች ተወስደዋል፡፡ በመኾኑም በአሁን ወቅት ፕሮጀክቶቹን ወደ ተሻለ ቁመና ላይ ለማድረስ እየተሠራ ይገኛል፡፡

የመንገድ ፕሮጀክቶቹ ሲጠናቀቁ የዱርቤቴ፣ ይስማላ፣ ሊበን፣ ቁንዝላ፣ ዱባባ፣ ሽንፋ እና ሌሎች በርካታ ከተሞችን ደረጃውን በጠበቀ መንገድ ያገናኛሉ፡፡ በአካባቢው በስፋት የሚመረቱትን የጤፍ፣ ስንዴ፣ ቦቆሎ፣ ሽንብራ፣ ሰሊጥ፣ ጥጥ እና መሰል የአዝርዕት ምርት ውጤቶችን በቀላሉ ወደ ማዕከላዊ ገበያ ለማድረስ ያስችላል፡፡

ሳዑዲ ዓረቢያ በኢትዮጵያ በባቡር መሠረተ ልማትና በአየር ትራንስፖርት መስክ ለመሥራት ፍላጎት አላት◉◉◉ሳዑዲ ዓረቢያ በባቡር መሰረተ ልማት እና በአየር ትራንስፖርት መስክ ከኢትዮጵያ ጋር በጋ...
05/06/2024

ሳዑዲ ዓረቢያ በኢትዮጵያ በባቡር መሠረተ ልማትና በአየር ትራንስፖርት መስክ ለመሥራት ፍላጎት አላት
◉◉◉
ሳዑዲ ዓረቢያ በባቡር መሰረተ ልማት እና በአየር ትራንስፖርት መስክ ከኢትዮጵያ ጋር በጋራ ለመስራት ፍላጎት እንዳላት ገለጸች፡፡

የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ ዴንጌ ቦሩ በሳይንስ ሙዚየም በተካሄደው የኢትዮ-ሳውዲ ኢንቨስትመንትና ንግድ ፎረም ላይ በተሳተፉበት ወቅት በትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ዘርፍ ላይ ያሉ የኢንቨስትመንት እድሎችን በተመለከተ ለሳዑዲ አረቢያ የትራንስፖርት ሃላፊዎችና ባለሃብቶች ገለፃ አድርገዋል፡፡

በዘርፉ ስድስት ስትራቴጂክ የኢንቨስትመንት እድሎች መኖራቸውን ጠቅሰው፤ የሎጂስቲክስ ከተማ ማስፋፊያ፣ የባቡር ማስፋፊያ፣ የአቪዬሽን አገልግሎት፣ የትራንስፖርት አገልግሎት፣ የመንገድ መሠረተ ልማት እና የወደብ ማስፋፊያ መሠረተ ልማቶች ለኢንቨስተሮች ክፍት መሆናቸውን አብራርተዋል፡፡

ከባቡር መሠረተ ልማት አንፃር አሁን ላይ ከአዲስ አበባ ጅቡቲ የጭነትና የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት ላይ ቢሆንም ከሀገሪቱ እድገት ጋር የማይመጣጠን መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም የባቡር መሠረተ ልማት እና የባቡር መለዋወጫ እቃዎች ለማምረት የኢንቨስትመንት እድል መኖሩን አመላክተዋል፡፡

በኢትዮጵያ፦ ከአቪዬሽን አገልግሎት ማስፋፊያ ጋር በተያያዘ እስከ 25 ቶን ድረስ የጭነት ትራንስፖርት አቅም መኖሩንና የሀገር ውስጥ የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት ለኢንቨስትመንት ክፍት ነው፡፡

በተለይ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎትን ከማዘመንና ከማስፋፋት አንጻር ሰፊ ክፍተት በመኖሩ፣ በከተማ ውስጥና በሀገር አቋራጭ የብዙሃን ትራንስፖርት አገልግሎት፣ የገመድ ትራንስፖርት እና የተሽከርካሪ ማቆሚያ መሠረተ ልማት ለማስፋፋት ከፍተኛ ፍላጎት ስላለ ባለሃብቶች መዋዕለ ነዋያቸውን ቢያፈሱ ትርፋማ መሆን ይችላሉ ተብሏል፡፡

የሳዑዲ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲከስ ዘርፍ ልዑክ እና የትራንስፖርት ድርጅት ባለሃብቶች በበኩላቸው፥ በትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ዘርፍ ያለው የኢንቨስትመንት ዕድል ትልቅ መሆኑን መረዳታቸውን ገልጸዋል፡፡

በተለይ በባቡር መሰረተ ልማትና በአየር ትራንስፖርት ላይ በጋራ ለመሥራት ፍላጎት እንዳላቸው ማንሳታቸውን መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡
◉◉❇️
ለተጨማሪ ዝርዝር መረጃዎች የቴሌግራም ቻናላችንን ይጎብኙ። t.me/infraethiopia

ሚያሚ፦ በዩናይትድ ስቴትስ ፍሎሪዳ ግዛት ውስጥ የምትገኝ የባህር ዳርቻ ከተማ ስትሆን፣ በደቡብ ፍሎሪዳ የሚገኘው Miami-Dade County መቀመጫ ነች። እንደ 2020 ቆጠራ 442,241 ህ...
05/06/2024

ሚያሚ፦ በዩናይትድ ስቴትስ ፍሎሪዳ ግዛት ውስጥ የምትገኝ የባህር ዳርቻ ከተማ ስትሆን፣ በደቡብ ፍሎሪዳ የሚገኘው Miami-Dade County መቀመጫ ነች።

እንደ 2020 ቆጠራ 442,241 ህዝብ ያላት ሚያሚ በፍሎሪዳ ከጃክሰንቪል በመቀጠል ሁለተኛዋ በህዝብ ብዛት የምትገኝ ከተማ ናት።

ሚያሚ በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ከሚገኙ ከተማዎች በሰማይ ጠቀስ ሕንፃዎች ብዛት በሦስተኛ ደረጃ ላይ የምትገኝ ሲሆን፣ ከ300 በላይ ሰማይ ጠቀስ ሕንፃዎች ይገኛሉ። ከእነዚህ ውስጥ የ61 ሕንፃዎች ከፍታ ከ150 ሜትር በላይ ነው።
◉◉◉
ለተጨማሪ ዝርዝር መረጃዎች የቴሌግራም ቻናላችንን ይጎብኙ። t.me/infraethiopia

Seriousness of GERD ታላቁ ህዳሴ ግድብ ባለፉት 10 ወራት ከ2700 ጊጋ ዋት ሠዓት በላይ ኃይል አመነጨ፡፡ በሁለት ተርባይኖች ኃይል እያመነጨ የሚገኘው ግድቡ÷ ባለፉት 10 ወራት ...
05/06/2024

Seriousness of GERD

ታላቁ ህዳሴ ግድብ ባለፉት 10 ወራት ከ2700 ጊጋ ዋት ሠዓት በላይ ኃይል አመነጨ፡፡ በሁለት ተርባይኖች ኃይል እያመነጨ የሚገኘው ግድቡ÷ ባለፉት 10 ወራት ያመነጨው ከዕቅዱ የ26 በመቶ ብልጫ ያለው ነው፡፡

INFRASTRUCTURE for TOURISM በቻይና እየተካሄደ ያለው የመሠረተ ልማት ማስፋፊያ ተጠናክሮ ቀጥሏል። በቻይና የመንገድ መሠረተ ልማት የእርሻ ምርቶችን ለገበያ ለማቅረብ ሰፊ ዕድልን...
05/06/2024

INFRASTRUCTURE for TOURISM

በቻይና እየተካሄደ ያለው የመሠረተ ልማት ማስፋፊያ ተጠናክሮ ቀጥሏል። በቻይና የመንገድ መሠረተ ልማት የእርሻ ምርቶችን ለገበያ ለማቅረብ ሰፊ ዕድልን የፈጠረ ብቻ ሳይሆን፣ የሀገር ውስጥ ቱሪዝምን በከፍተኛ ሁኔታ እያሳደገ መሆኑም ታውቋል።

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ በካማሽ ዞን በዴዴሳ ወንዝ ላይ በ54 ሚሊዮን ብር የተገነባ ድልድይ ተመረቀ፡፡የዓባይ ወንዝ ገባር የሆነው የዴዴሳ ወንዝ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካማሽ ዞን የዞኑ ዋና ከተ...
05/06/2024

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ በካማሽ ዞን በዴዴሳ ወንዝ ላይ በ54 ሚሊዮን ብር የተገነባ ድልድይ ተመረቀ፡፡

የዓባይ ወንዝ ገባር የሆነው የዴዴሳ ወንዝ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካማሽ ዞን የዞኑ ዋና ከተማ በሆነው በካማሽ ከተማ እና በምዥጋ ወረዳ አዋሳኝ አካባቢ ላይ ይገኛል፡፡

የክልሉ መንግሥት ከኢትዮጵያ መንገድ አስተዳደር ጋር በመተባበር በ54 ሚሊዮን ብር ያስገነባው ደረጃውን የጠበቀ ተገጣጣሚ ድልድይ 88 ሜትር ርዝመት አለው።

አስመራ ኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል፣ ኤርትራ
05/06/2024

አስመራ ኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል፣ ኤርትራ

የጨረታ ማስታወቂያ◉◉◉የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለተለያዩ አገልግሎት ሊውሉ የሚችሉ ንብረቶችን ባሉበት ቦታና ሁኔታ በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፦❇️ ሎት-1- 20 (ሀያ...
04/06/2024

የጨረታ ማስታወቂያ
◉◉◉
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለተለያዩ አገልግሎት ሊውሉ የሚችሉ ንብረቶችን ባሉበት ቦታና ሁኔታ በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፦

❇️ ሎት-1- 20 (ሀያ) ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች፤ ቦታ ኮተቤ አካባቢ ብረታ ብረት ፊት ለፊት ከሚገኘው የተቋማችን ዋና መ/ቤት ግቢ ውስጥ፤

❇️ ሎት-2- ከባድ ጥቁር እና ቀላል ናፍጣ መጠኑ ከፍተኛ ፤ ቦታ በድሬድዋ ከተማ አስተዳደር የኢንዱስትሪ መንደር የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዲዝል ኃይል ማመንጫ ግቢ ውስጥ፤

❇️ሎት-3- የጠጠር ማምረቻ (መፍጫ) ክሬቸር ማሽን፤ ቦታ መልካ ዋከና ኃይል ማመንጫ ግቢ ውስጥ፤ ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡-

በጨረታው የሚወዳደሩ ተጫራቾች ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው ሆኖ ሰነድ ለመግዛት ሲመጡ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ማስረጃ ወይም የታደሰ መታወቂያ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፤

1. የጨረታው ሂደት የሚከናወንበት ቦታ አዲስ አበባ ኮተቤ አካባቢ ብረታ ብረት ፊት ለፊት ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና መ/ቤት፤

2. የመወዳደሪያ ሰነድ መግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች የፋይናንስ አሰተዳደር ቢሮ የማይመለስ ብር 1,000.00 (አንድ ሺ) በመክፈል የከፈሉበትን ደረሰኝ በመያዝ የንብረት አስተዳደር ቢሮ በመቅረብ የጨረታ ሁኔታን የሚገልጽ ዝርዝር መረጃ የያዘ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ መሙያ ቅጽ መውሰድ ይኖርባችኋል፤

3. ተጫራቾች ሰነድ ገዝተው ማስታወቂያ ከወጣበት ከሰባተኛው ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 10፡00 ሰዓት ንብረቶቹ በሚገኙበት ቦታዎች በመገኘት መመልከት ይችላሉ፤

4. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት ዋጋ 15% ቫትን ጨምሮ ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን ተቋሙ ባዘጋጀው ኦርጅናል ማህተም ባረፈበት ቅጽ ላይ ብቻ በመጠይቁ መሠረት በመሙላት በታሸገ ፖስታ ማዘጋጀት ግዴታ ሲሆን እንዲሞላ ከተዘጋጀው ስፍራ ውጭ የሚሞላ ጽሁፍ ከውድድሩ ሊያሰርዝ ይችላል፤

5. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የምታሰሩት ሲ.ፒ.ኦ ህጋዊነቱን ለማረጋገጥ አመቺ እንዲሆን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውስጥ ከሚገኙ ማንኛውም የባንክ ቅርንጫፎች በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ስም ብቻ በማሠራት ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ የጨረታ ሳጥኑ ውስጥ ማስገባት ግዴታ ሲሆን ከመመሪያው ውጪ የተሰራ ሲ.ፒ.ኦ. ተቀባይነት የለውም፤

6. ተወዳዳሪዎች በሎት ሁለት ላይ ለመሳተፍ በፋብሪካ ምርት ሥራ ላይ የተሰማራቹ ሆኖ ከአከባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ፋብሪካው በአካባቢ ላይ ጉዳት እንደማያደርስ የሚያረጋግጥ ሰነድ እንዲሁም የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ እና የዘመኑን ግብር የከፈለ መሆኑን የሚገልጽ ሰነድ አባሪ አድርጎ ማቅረብ ግዴታ ሲሆን ማቅረብ ያልቻለ ተወዳዳሪ ውጤቱ ውድቅ ይሆናል፡፡

7. ጨረታው ከ23/09/16 እስከ 07/10/2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ የሚቆይ ሲሆን ሰኔ 07 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ጠዋት 4፡00 ድረስ የመወዳደሪያ ሰነድ ወደ ሳጥኑ ውስጥ ማስገባት ይኖርባችኋል፤ ሳጥኑ በዚሁ ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን ከጠዋቱ በ4፡15 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት በተቋማችን አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል፤ ሆኖም ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ የቀረ ተጫራች ጨረታውን ከመከፈት ሊያስተጓጉል አይችልም፤

8. በጨረታው አሸናፊ ለምትሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታችሁ በሚገለፅላችሁ ቀን ጀምሮ የሚቆጠር አምስት ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የአሸነፉችሁበትን ዋጋ ሙሉውን ክፍያ ለወደፊት በምናሳውቃችሁ ደብዳቤ ላይ በሚገለፀው የተቋማችን ሂሳብ ቁጥር ገቢ በማድረግ የሽያጭ ውል ስምምነት መፈጸም ግዴታ ይኖርባችኋል፤ ሆኖም ግዴታቸውን የማይወጡ ተጫራቾች ያሲያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ. ለተቋማችን ገቢ ይደረጋል፤

9. ከላይ የተጠቀሰውን እና በዋጋ መሙያ ሠነድ ላይ የተቀመጡ መመሪያዎችን ያላሟላ ተጫራች ከጨረታ ውድድር ውድቅ/ሊሰረዝ ይችላል፤

10. ተቋሙ ጨረታውን ለመቀበል ወይም ላለመቀበል የሚችል ሲሆን በማንኛውም ጊዜ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤

11. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-558-14-24 ወይም 011-558-06-49 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

ተርኪዬ
04/06/2024

ተርኪዬ

የነቀምቴ ኤርፖርት በቅርቡ ሥራ ለመጀመር ዝግጁ ሆኗል። በዚህም መሠረት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሰኔ 10 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ነቀምቴ በረራ ለማስጀመርና በሳምንት አራት ጊዜ ለመብ...
04/06/2024

የነቀምቴ ኤርፖርት በቅርቡ ሥራ ለመጀመር ዝግጁ ሆኗል።

በዚህም መሠረት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሰኔ 10 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ነቀምቴ በረራ ለማስጀመርና በሳምንት አራት ጊዜ ለመብረር ዝግጅቱን አጠናቋል።

የአርባ ምንጭ ስታዲየም ግንባታ በ2017 ዓ.ም ለሚከበረው የብሔር ብሔረሰቦች ክብረ በዓል እንዲደርስ ግንባታው በቻይናው CCCC ሥራ ተቋራጭ በሚቀጥለው ሳምንት ይጀመራል።
04/06/2024

የአርባ ምንጭ ስታዲየም ግንባታ በ2017 ዓ.ም ለሚከበረው የብሔር ብሔረሰቦች ክብረ በዓል እንዲደርስ ግንባታው በቻይናው CCCC ሥራ ተቋራጭ በሚቀጥለው ሳምንት ይጀመራል።

ይህ እየሆነ ያለው በሰሜን ምስራቅ ቻይና ሼንያንግ ውስጥ ነው። በዚህ ቦታ የኤሌክትሪክ መኪናዎች ለተሽከርካሪዎቻቸው "ነዳጅ" የሚያገኙበት ቦታ ነው።ይህ የኤሌክትሪክ መኪናዎች የሱፐር ቻርጅ ጣ...
03/06/2024

ይህ እየሆነ ያለው በሰሜን ምስራቅ ቻይና ሼንያንግ ውስጥ ነው። በዚህ ቦታ የኤሌክትሪክ መኪናዎች ለተሽከርካሪዎቻቸው "ነዳጅ" የሚያገኙበት ቦታ ነው።

ይህ የኤሌክትሪክ መኪናዎች የሱፐር ቻርጅ ጣቢያ ኃይሉን የሚያገኘው ከፀሐይ ኃይል ከሚገኝ ኢነርጂ ሲሆን፣ ይህም ኃይል የሚሰበሰበው በጣራዎቹ አናት ላይ በተደረደሩ ሶላር ፓናሎች አማካኝነት ነው።
◉◉◉
ለተጨማሪ ዝርዝር መረጃዎች የቴሌግራም ቻናላችንን ይጎብኙ። t.me/infraethiopia

በዘመናዊ መንገድ በተሠራ የውሃ መውረጃ ቦይ (canal) ላይ የተገጠመ የፀሐይ ኃይል ማመንጫ (solar panal) ነው። ይህ ፓናል ሁለት ጥቅሞች አሉት፦ የመጀመሪያው የኤሌክትሪክ ኃይል ማመ...
03/06/2024

በዘመናዊ መንገድ በተሠራ የውሃ መውረጃ ቦይ (canal) ላይ የተገጠመ የፀሐይ ኃይል ማመንጫ (solar panal) ነው። ይህ ፓናል ሁለት ጥቅሞች አሉት፦ የመጀመሪያው የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት ሲሆን ሌላኛው ደግሞ የውሃ ትነትን (evaporation) መከላከል ነው።
◉◉◉
ለተጨማሪ ዝርዝር መረጃዎች የቴሌግራም ቻናላችንን ይጎብኙ። t.me/infraethiopia

የኢትዮጵያ የመጀመሪያው "ሴሜንቴሪያ"❇️በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ሲሚንቶ ፋብሪካ የተመሠረተው በ1928 ዓ.ም በጣሊያኖች ሲሆን፣ በዓመት 60 ሺሕ ቶን የማምረት አቅም ነበረው። ❇️ፋብሪካው "ድ...
02/06/2024

የኢትዮጵያ የመጀመሪያው "ሴሜንቴሪያ"
❇️
በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ሲሚንቶ ፋብሪካ የተመሠረተው በ1928 ዓ.ም በጣሊያኖች ሲሆን፣ በዓመት 60 ሺሕ ቶን የማምረት አቅም ነበረው።
❇️
ፋብሪካው "ድሬደዋ ኖራ እና ሲሚንቶ ፋብሪካ" ቢባልም፣ ከጣሊያንኛ በመዋስ በይበልጥ የሚታወቀው "ሴሜንቴሪያ" ወይም "ሼሜንቴሪያ" እየተባለ ነበር (በጣሊያንኛ ቃሉ "ሲሚንቶ ማምረቻ" ማለት ነው)።
❇️
ይህ የሀገራችን ቀዳሚ ሲሚንቶ ፋብሪካ ወደ ግል ይዞታ ሲዞር፣ "ናሽናል ሲሚንቶ አ.ማ" የሚለውን መጠሪያ ይዞ ቀጠለ። ወደ 90 ዓመታት ለሚጠጋ ጊዜ ያህል፣ በሀገር ግንባታ ውስጥ ቁልፍ ስፍራ ይዞ ቀጥሏል።
❇️
አሁን ናሽናል ሲሚንቶ አ.ማ በቀን 3,500 ቶን ክሊንከር የማምረት አቅም ያለው ሲሆን፣ እህት ኩባንያው ለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ደግሞ በቅርቡ ሥራ ሲጀምር በቀን 10 ሺህ ቶን ክሊንከር የማምረት አቅም ይኖረዋል።
❇️
East African Holdings
◉◉◉
ለተጨማሪ ዝርዝር መረጃዎች የቴሌግራም ቻናላችንን ይጎብኙ። t.me/infraethiopia

የባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ጉዳይ❇️ በጥር ወር የካፍ ውድድርን ያስተናግዳልበ2002 ዓ.ም የግንባታ ሂደቱ የተጀመረው የባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽ...
02/06/2024

የባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ጉዳይ

❇️ በጥር ወር የካፍ ውድድርን ያስተናግዳል

በ2002 ዓ.ም የግንባታ ሂደቱ የተጀመረው የባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (CAF) ደረጃን ባሟላ መልኩ ለማጠናቀቅ የክልሉ መንግሥት ከ1.8 ቢሊየን ብር በላይ በመበጀት ከተቋራጩ ሚድሮክ ኮንስትራክሽን ጋር ውል ገብቶ እየተሠራ ነው።

የባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ሲጠናቀቅ 52 ሺ ተመልካቾች የሚይዝና 29 የኦሎምፒክ ስፖርቶችን በተመሳሳይ ሰዓት ማወዳደር የሚችል የኦሎምፒክ ስታዲየም ደረጃ የሚይዝ ነው።

ይህ የኦሎምፒክ ስታዲየም ሁለት የመለማመጃ ሜዳዎችን ጨምሮ ከካፍ ደረጃ በላይ ተጨማሪ መሠረታዊ የደረጃ ማሟያ ግንባታዎች እና ባለአምስት ኮከብ የውስጥ ቁሶች እንዲሟሉለት ተደርጎ በከፍተኛ ወጪ፣ በጥራት እና በጥንቃቄ እየተገነባ መሆኑ ታውቋል።

አሁን ባለው የግንባታ ፍጥነት በጥር ወር የካፍ ውድድሮችን ለማስጀመር እንዲያስችል እየተሠራ ነው።

47 ሺህ ወንበሮች ጥሬ ዕቃቸው ከውጭ ገብቶ በሀገር ውስጥ መመረት መጀመራቸውን እና ለቪ.አይ.ፒ የሚያገለግሉ 4 ሺህ 5 መቶ ወንበሮች ከስፔን እና ከቱርክ ተመርተው እንዲገቡ በኮንትራክተሩ በኩል ስምምነት የተወሰደ ሲሆን፣ የፌደራል መንግሥት የዶላር ምንዛሪ በማቅረብ ግንባታው በፍጥነት እና በተያዘለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ እገዛ እያደረገ ነው።

የኤምኤች ኢንጅነሪንግ የአማካሪዎች ቡድን መሪ ኢንጅነር እስክንድር ገብረ ሚካኤል፦ የባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም የግንባታ ሂደት እስከ ጥር 2017 ዓ.ም ድረስ በገባነው ውል መሠረት የካፍ ውድድሮችን ለማካሄድ ከሚያስችል በላይ አጠናቅቀን እናስረክባለን ብለዋል።

በተለይ የሜዳ ሥራ ላይ የፊፋ ፈቃድ ያለው የፈረንሳዩ ግሪጎሪ ተቋራጭ ድርጅት በጥራት እና በፍጥነት ሥራውን እያከናወነ መሆኑ ተገልጿል።
◉◉◉
ለተጨማሪ ዝርዝር መረጃዎች የቴሌግራም ቻናላችንን ይጎብኙ። t.me/infraethiopia

ወደ አዲስ አበባ ቢመጣስ? ጀርመን "Wuppertal" ከተማ ነው።
02/06/2024

ወደ አዲስ አበባ ቢመጣስ?

ጀርመን "Wuppertal" ከተማ ነው።

የ25 ገጠር ከተሞች የፀሃይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት አፈጻፀም 61 በመቶ ደረሰ◉  ወጪው ከ1.3 ቢሊዮን ብር በላይ ነው◉◉◉የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የገጠር ከተሞችን  የኤሌክትሪክ ተ...
02/06/2024

የ25 ገጠር ከተሞች የፀሃይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት አፈጻፀም 61 በመቶ ደረሰ

◉ ወጪው ከ1.3 ቢሊዮን ብር በላይ ነው
◉◉◉
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የገጠር ከተሞችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ የሚስችል 25ቱ ከተሞች የሶላር ሚኒ ግሪድ ፕሮጀክት ቀርፆ ወደ ሥራ ገብቷል፡፡

ፕሮጀክቱ ከሰባት ክልሎች በተመረጡ 25 የገጠር ቀበሌዎች የሚገነባ ሲሆን፤ ግንባታው በሶስት ኮንትራክተሮች በ6 ሎት ተከፍሎ እየተከናወነ ይገኛል፡፡

የኦፍ ግሪድ ፕሮጀክቱ የገንዘብ ምንጭ የአፍሪካ ልማት ባንክና የኢትዮጵያ መንግሥት ሲሆኑ፤ አጠቃላይ ወጪው ከ1.3 ቢሊዮን ብር በላይ ነው፡፡

እየተገነባ የሚገኘው የሶላር ፕሮጀክት ዋና ዓላማ ከዋናው ግሪድ ርቀው የሚገኙ 25 የገጠር ቀበሌዎችን በፀሃይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ ነው፡፡

ፕሮጀክቱ ተግባራዊ ሲደረግ የዕውቀት ሽግግርንና ሰፊ የሥራ ዕድል የሚፍጥር ሲሆን፤ 145 ሺህ 169 አዳዲስ ደንበኞችም የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ያደርጋል፡፡

አጠቃላይ 8 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም ያለው ይህ ፕሮጀክት፤ 68 ነጥብ 7 የመካከለኛና 233 ነጥብ 3 ኪ.ሜ የዝቅተኛ መስመር ዝርጋታ ይከናወንበታል፡፡

ግንባታው በሁለት የቻይናና በአንድ የኮሪያ ኩባንያዎች እየተከናወነ ሲሆን የፕሮጀክት አጠቃላይ አፈጻፀም 61 በመቶ ደርሷል፡፡

ተቋሙ እ.ኤ.አ በ2030 ከዋናው ግሪድ 65 በመቶ እንዲሁም በአማራጭ የኃይል ምንጮች 35 በመቶ የሚሆነውን ህብረተሰብ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ ለማድረግ ርብርብ እያደረገ ይገኛል፡፡

-EEU-

በአማራ ክልል መንገድ ቢሮ ባለቤትነት፣ በአማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት ተቋራጭነት እና በልህቀት ኮርፖሬት አማካሪነት በደሴ ከተማ የሚገነባው የሮቢት ድልድይና የመዳረሻ መንገድ ለከተማው ነዋሪ...
01/06/2024

በአማራ ክልል መንገድ ቢሮ ባለቤትነት፣ በአማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት ተቋራጭነት እና በልህቀት ኮርፖሬት አማካሪነት በደሴ ከተማ የሚገነባው የሮቢት ድልድይና የመዳረሻ መንገድ ለከተማው ነዋሪዎች በርካታ ጥቅም እንዲሰጥ ታስቦ እየተገነባ ነው።

t.me/infraethiopia

ጊፍት ሪል ስቴት አያት ፈረስ ቤት አካባቢ ያስገነባው የመኖሪያ መንደር ተመረቀ◉◉◉ጊፍት ሪል ስቴት በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ልዩ ስሙ አያት ፈረስ ቤት አካባቢ ያስገነባውን ጊፍት መንደር ከፍተ...
01/06/2024

ጊፍት ሪል ስቴት አያት ፈረስ ቤት አካባቢ ያስገነባው የመኖሪያ መንደር ተመረቀ
◉◉◉
ጊፍት ሪል ስቴት በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ልዩ ስሙ አያት ፈረስ ቤት አካባቢ ያስገነባውን ጊፍት መንደር ከፍተኛ የመንግሥት አመራሮችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በዛሬው ዕለት አስመርቋል።

ከ54,000 በላይ በሆነ ካሬ ላይ ያረፈው ይህ የመኖሪያና የንግድ ቤት መንደር እስከ 24 ፎቅ ያላቸው ከ1000 በላይ የሆኑ አፓርታማዎችና 700 የንግድ ቤቶችን የያዘ እንደሆነ ተነግሯል።

የጊፍት መንደር ሦስትን ልዩ የሚያደርገው ወለላቸው ከ2-24 የሚደርሱ ፎቆችን ያካተቱ አፓርትማዎች፤ ቪላዎች፤ ታዎን ሃውሶችና ሮው ሃውሶችን የያዘ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን፣ ከዚህም በተጨማሪ በነዚህ ረጃጅም ፎቆች ውስጥ የተንጣለሉ የንግድ ቤቶች ሞል ግንባታ እየተፋጠነ ነው፡፡ በአጠቃላይ መንደር ሦስት 2117 ቤቶችን የያዘ መሆኑ ታውቋል።

ይህ ጊፍት ሪል ስቴት ያስመረቀው 3ተኛው የመኖሪያ መንደር ሲሆን፣ 4ተኛውን መንደርም በለገሀር አካባቢ በቅርቡ እንደሚያጠናቅቅ ተገልጿል።

ጊፍት ሪል ስቴት በተቋሙ ከ25 አመት በላይ ለሰሩ፣ ሠራተኞች የመኖሪያ ቤት ሽልማትም አበርክቷል።

እንዲሁም ለመቄዶንያ መስራች ቢኒያም ባለ አንድ መኝታ የመኖሪያ አፓርታማ በሽልማት አበርክቷል።

የዛሬውን 3ተኛ የመኖሪያ መንደር ምርቃት አስመልክቶ ጊፍት ሪል ስቴት በሁሉም መኖሪያ ቤቶች 15% ቅናሽ ማድረጉን አስታውቋል።

ከ27 አመታት በላይ በሪል ስቴት ዘርፍ ልምድ ያካበተው እና ደንበኞቹን እንደምርጫቸው የቤት ባለቤት ማድረግ የቻለው ጊፍት ሪል ስቴት አሁንም በቀላል እና በረጅም ጊዜ ክፍያ የመኖሪያ አፓርትመንቶችን እንዲሁም የንግድ ሱቆች በማቅረብ ላይ ይገኛል።

"በፋይበርግላስ ዘመን ዕንቁ ለመፈለግ እማስናለሁ" ◉◉◉መላው አለም "ዘመኑ የፋይበርግላስ ነው" እያለ ነው። አለም አሁን ለደረሰበት ፈጣን የኢኮኖሚ እንዲሁም የሳይንስና ቴክኖሎጂ ምጥቀት ፋይ...
01/06/2024

"በፋይበርግላስ ዘመን ዕንቁ ለመፈለግ እማስናለሁ"
◉◉◉
መላው አለም "ዘመኑ የፋይበርግላስ ነው" እያለ ነው። አለም አሁን ለደረሰበት ፈጣን የኢኮኖሚ እንዲሁም የሳይንስና ቴክኖሎጂ ምጥቀት ፋይበር ግላስ ያለው ድርሻ ከፍተኛ ነው።

በፋይበር የማይመረት ነገር የለም ማለት ሁሉ ይቻላል። ነባር ምርቶችን በመተካት እንደፋይበር ግላስ ያለ ማቴሪያል አለ ለማለት ይከብዳል። ፋይበር ብረትን ተክቶ ግልጋሎት እየሰጠ ነው።

በአርማታ ብረት መልክ እየተመረተ ጥቅም ይሰጣል። እንጨትን ተክቶ ደግሞ በርና መስኮቶች እንዲሁም የቤትና የቢሮ ዕቃዎችን እየተመረቱበት ነው። በእምነበረድ እና ግራናይት መልክ እየተፈበረከ የተኪነት ሚናውን እየተጫወተ ነው።

የአውሮፕላን እና የመኪና ቦዲዎች ዲዛይን ምጥቀት ከፋይበር ውጪ የሚታሰብ አልነበረም። አሁን አሁን መኖሪያ ቤቶች ሁሉ ሳይቀር በፋይበር ግላስ እየተሠሩ ነው። ፋይበር አሁን ወደ ሚሊተሪ ኢንደስትሪ ውስጥ እየገባ ነው። ብረት ለበስ ታንኮችና የጦር ተሽከርካሪዎች ፋይበርን እንደ ግብአት እየተጠቀሙበት ነው።

በአጠቃላይ ፋይበር ለምግብነት ብቻ ነው የማይውለው ብሎ ለመናገር የሚያስደፍርበት አጋጣሚ ሁሉ እየመጣ ነው ለማለት ይቻላል።ፋይበርን አለምን እንደተጠቀመበት ሁሉ በሀገራችን በስፋት እየተጠቀምንበት አይደለም።

በአሁኑ ወቅት በመቶዎች የሚቆጠሩ በsmall scale industry ደረጃ የሚገኙ አምራች ድርጅቶች የሚገኙ ቢሆንም የፋይበር ኢንደስትሪ ዘርፍ በሚፈለገው ደረጃ አላደገም።

በአፍሪካ ግብጽን የመሳሰሉ ሀገሮች ከፋይበር ኢንደስትሪ በሚሊዮን ዶላሮችን የውጭ ምንዛሪ እያገኙ ነው።

❇️ በኢትዮጵያ ከፋይበር ኢንደስትሪ ዘርፍ ተገቢውን ሀገራዊ ጠቀሜታ ለማግኘት እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው ቴክኖ ፋይበር ኢትዮጵያ ላለፉት ሃያ አመታት በሺህ ለሚቆጠሩ ወጣቶች በፋይበርግላስ ቴክሎኖጂ ዙሪያ በነፃ ስልጠና በመስጠት ሥራ ፈጣሪ ወጣቶችን ሲያግዝ ቆይቷል።

❇️ ቴክኖፋይበር በቀጣይም በፋይበርግላስ ቴክኖሎጂ በነፃ ስልጠና ለሚፈልጉ ወጣቶች ጥሪውን ያቀርባል።
❇️
ለበለጠ መረጃ፦ 0940516393/0948969696 ይደዉሉ።
🎆
ቴክኖ ፋይበርና ዋተርፕሩፊንግ ኃ/የተ/የግ/ማ

❇️በአቦል ኢንቴሪየር እና ፈርኒቸር የሚመረቱ ዘወትር የማይሰለቹ ውብ እና በጥንካሬቸው ወደር የማይገኝላቸው ዘመን ተሻጋሪ የሶፋ፣ የምግብ ጠረፔዛዎች እንዲሁም የቲቪ ስታንድ ምርቶችን በተለያዩ...
31/05/2024

❇️በአቦል ኢንቴሪየር እና ፈርኒቸር የሚመረቱ ዘወትር የማይሰለቹ ውብ እና በጥንካሬቸው ወደር የማይገኝላቸው ዘመን ተሻጋሪ የሶፋ፣ የምግብ ጠረፔዛዎች እንዲሁም የቲቪ ስታንድ ምርቶችን በተለያዩ የከለር እና የዲዛይን አማራጮች አቅርበንልዎታል።

🎇 በድርጅታችን ውስጥ የሚመረቱ የፈርኒችር ዕቃዎች በመኖሪያ ቤት ውስጥ ለውጥ የሚያመጡና ልዩነትን የሚፈጥሩ ስለሆኑ መኖሪያ ቤትዎን እንዲያሳምሩ ተጋብዘዋል።

🎆 ውበትና ጥንካሬን የተላበሱ ሁሉንም አይነት የፈርኒቸር ምርቶች በድርጅታችን ውስጥ በአንድ ቦታ ማግኘት ይችላሉ።

❇️ገንዘብና ጊዜዎትን ይቆጥቡ፤ አይድከሙ እኛ ጋር ይምጡ!!!

🎇እጃችሁ ይባረክ የተባልንባቸውን ሥራዎች ይጎብኙ፣ ሁለገብ በሆኑት የፈርኒችር ዕቃዎቻችን መኖሪያ ቤትዎን ያሳምሩ።

❇️ ሁሉንም አይነት የፈርኒቸር ዕቃዎች እንደ ምርጫዎ ትክክለኛ ዲዛይን መርጠው ለማሠራት አቦል ኢንቴሪየር እና ፈርኒቸር ትክክለኛ ቦታ ነው።
🎇🎆🎇🎆🎇🎆

0903555565/0912276506

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይጎብኙ t.me/abolinteriors

31/05/2024
ፖላንድ፦ በአንድ ወንዝ ላይ አምስት ድልድይ! ወንዙ "Five in One" ይባላል😍
31/05/2024

ፖላንድ፦ በአንድ ወንዝ ላይ አምስት ድልድይ! ወንዙ "Five in One" ይባላል😍

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Infra Ethiopia - ኢንፍራ ኢትዮጵያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Infra Ethiopia - ኢንፍራ ኢትዮጵያ:

Videos

Share


Other Media/News Companies in Addis Ababa

Show All