Bukmal

Bukmal ፈጣን ታማኝ እና እውነተኛ መረጃ ያግኙ Fast News Ethiopia
መረጃ እና መዝናኛ

አብነት ከበደ ለማይኮ መልስ ሰጠ
13/06/2024

አብነት ከበደ ለማይኮ መልስ ሰጠ






ማስተር አብነት ከበደ ለማይኮ መልስ ሰጠ ...

የቱ ይሻላል hamster List ተደረገ?
12/06/2024

የቱ ይሻላል hamster List ተደረገ?






የቱ ይሻላል hamster List ተደረገ? ...

አቡነ ሉቃስ ለኦርቶዶክስ ውግዘት መልስ ሰጡ        #ኦርቶዶክሳዊ
10/06/2024

አቡነ ሉቃስ ለኦርቶዶክስ ውግዘት መልስ ሰጡ

#ኦርቶዶክሳዊ

አቡነ ሉቃስ ለኦርቶዶክስ ውግዘት መልስ ሰጡ #ኦርቶዶክሳዊ ...

የዘሪቱ ከበደ ልጅ ክርስቲያን ላቃቸው የሞተበት የህክምና ስህተት      #ኢትዮጵያ     #ጴንጠ  #ሙዚቃ
09/06/2024

የዘሪቱ ከበደ ልጅ ክርስቲያን ላቃቸው የሞተበት የህክምና ስህተት

#ኢትዮጵያ

#ጴንጠ
#ሙዚቃ

የዘሪቱ ከበደ ልጅ ክርስቲያን ላቃቸው የሞተበት የህክምና ስህተት #ኢትዮጵያ #ጴንጠ #ሙዚቃ ...

የአቡነ ማትያስ መግለጫ          #ኦሮቶዶክስ  #ኢትዮጵያ
07/06/2024

የአቡነ ማትያስ መግለጫ




#ኦሮቶዶክስ
#ኢትዮጵያ

የአቡነ ማትያስ መግለጫ #ኦሮቶዶክስ #ኢትዮጵያ ...

ሰበር ዜና የአማራ ክልል ባለስልጣናት ላይ ጥቃት ተፈፀመ      #ኢትዮጵያ    #ፋኖ        #ኢትዮጵያ    #ፋኖ
06/06/2024

ሰበር ዜና የአማራ ክልል ባለስልጣናት ላይ ጥቃት ተፈፀመ

#ኢትዮጵያ

#ፋኖ



#ኢትዮጵያ

#ፋኖ

ሰበር ዜና የአማራ ክልል ባለስልጣናት ላይ ጥቃት ተፈፀመ #ኢትዮጵያ #ፋኖ #ፋኖ #ናሁሰናይ ...

ሰበር ዜና በፖሊስ ተደበደቡ የፋኖ መሪ ናሁሰናይ ተቀበረ      #ኢትዮጵያ    #ፋኖ  #ናሁሰናይ
03/06/2024

ሰበር ዜና በፖሊስ ተደበደቡ የፋኖ መሪ ናሁሰናይ ተቀበረ

#ኢትዮጵያ

#ፋኖ
#ናሁሰናይ

ሰበር ዜና በፖሊስ ተደበደቡ የፋኖ መሪ ናሁሰናይ ተቀበረ #ኢትዮጵያ #ፋኖ #ናሁሰናይ ...

  ሶማሊያ በኢትዮጵያ ላይ ወሰነች          #ኢትዮጵያ
03/06/2024

ሶማሊያ በኢትዮጵያ ላይ ወሰነች



#ኢትዮጵያ

ሶማሊያ በኢትዮጵያ ላይ ወሰነች #ኢትዮጵያ #ኢትዮጵያ ...

  ጠ/ሚ አበይ ስለ ስልጣን መልቀቅ ተናገሩ ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ኮንትራክተሮች የተላከው ማስፈራሪያ         #ፋኖ
03/06/2024

ጠ/ሚ አበይ ስለ ስልጣን መልቀቅ ተናገሩ
ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ኮንትራክተሮች የተላከው ማስፈራሪያ



#ፋኖ


ጠ/ሚ አበይ ስለ ስልጣን መልቀቅ ተናገሩ | ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ኮንትራክተሮች የተላከው ማስፈራሪያ #ኢትዮጵያ #...

  በአማራ ክልል ባለስልጣን ተገደለ ስለ ፓስፖርት ጉድ ተሰማ            #ኢትዮጵያ  #ፋኖ
02/06/2024

በአማራ ክልል ባለስልጣን ተገደለ
ስለ ፓስፖርት ጉድ ተሰማ




#ኢትዮጵያ
#ፋኖ

በአማራ ክልል ባለስልጣን ተገደለ | ስለ ፓስፖርት ጉድ ተሰማ #ኢትዮጵያ #ፋኖ #ኢትዮጵያ...

ሰበር ዜና ዋና አዛዡ ተገደሉ | የህወሓት ታጣቂዎች እርስ በእርስ ተዋጉ | ጌታቸው ረዳ ጠ/ሚ አብይን አደነቁ         #ኢትዮጵያ
01/06/2024

ሰበር ዜና ዋና አዛዡ ተገደሉ | የህወሓት ታጣቂዎች እርስ በእርስ ተዋጉ | ጌታቸው ረዳ ጠ/ሚ አብይን አደነቁ




#ኢትዮጵያ



ሰበር ዜና ዋና አዛዡ ተገደሉ | የህወሓት ታጣቂዎች እርስ በእርስ ተዋጉ | ጌታቸው ረዳ ጠ/ሚ አብይን አደነቁ #...

ሰበር ዜና ፋኖና ኦነግ ሸኔ ተዋጉ | ሊቀጳጳስ አቡነ ሉቃስ ተፈረደባቸው | የህወሓት ወታደሮች በአላማጣ       #ኢትዮጵያ
31/05/2024

ሰበር ዜና ፋኖና ኦነግ ሸኔ ተዋጉ | ሊቀጳጳስ አቡነ ሉቃስ ተፈረደባቸው | የህወሓት ወታደሮች በአላማጣ



#ኢትዮጵያ



ሰበር ዜና ፋኖና ኦነግ ሸኔ ተዋጉ | ሊቀጳጳስ አቡነ ሉቃስ ተፈረደባቸው | የህወሓት ወታደሮች በአላማጣ Orthodox church fano ...

በጂንካ ከተማ በኩፍኝ በሽታ ምክንያት የህጻናት ህይወት እያለፈ መሆኑ ተገለፀየኩፍኝ በሽታ ወረርሽኝ  ዳግም እየተከሰተ በመሆኑ  ማህብረሰቡ ጥንቃቄ እንድያደርግ የጂንካ ከተማ አስተዳደር ጤና ...
31/05/2024

በጂንካ ከተማ በኩፍኝ በሽታ ምክንያት የህጻናት ህይወት እያለፈ መሆኑ ተገለፀ

የኩፍኝ በሽታ ወረርሽኝ ዳግም እየተከሰተ በመሆኑ ማህብረሰቡ ጥንቃቄ እንድያደርግ የጂንካ ከተማ አስተዳደር ጤና ጽ/ቤት ኃላፊ ገልፀዋል ።

በጂንካ ከተማ አስተዳደር ከሚያዝያ 4 ጀምሮ የኩፍኝ በሽታ ስርጭት የቆመ ቢሆንም ከግንቦት 08 ቀን 2016 ጀምሮ ዳግም መቀስቀሱን በዚህ ህጻናት በህመሙ እየጠቁ ህይወታቸው እያለፈ መሆኑን የጂንካ ከተማ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሃላፊ አቶ በቃሃኝ ጥላሁን በተለይ ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

በያዝነው ሳምንት ብቻ ሁለት ታዳጊዎች ህይወት ሲያልፍ በርካታ ህጻናት በህመሙ እየተሰቃዩ መሆኑም ተጠቁሟል። በበሽታው የተጠቁ ሰዎች አሁን ላይ በጂንካ ሆስፒታል ከጂንካ ከተማና ከአጎራባች ወረዳዎች በመምጣት የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑ የተገለጸ ሲሆን በሽታው የተወሳሰበ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ማህበረሰቡ ጥንቃቄ እንዲደርግ ሃላፊው አሳስበዋል።

የበሽታው ምልክት ሽፍታ ፣ ትኩሳት እና መሰል ምልክቶች ሲገኙ ወደ ጤና ተቋም ሪፖርት እንዲደረግ ተጠይቋል። በከተማ አስተዳደሩ የቤት ለቤት ጉብኝት የተጀመረ ሲሆን ትምህርት ቤቶች የጥንቃቄ መልዕክትና ምልክቱ የታየበት ህፃን ሲገኝ ለጤና ባለሙያ ወይም ተቋም ሪፖርት እንዲያደረጉ ሲሉ አቶ በቃሃኝ ጥላሁን ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል ።

#ጅንካ

#ኢትዮጵያ


Bukmal

🇪🇹 የፖለቲካ ፓርቲዎች ምን ይላሉ ? 🇪🇹“ ... ያለፉትን ዘመናት እኮ   እንድናይ የተገደድንበት ጊዜ ነው ” - ጎጎት ፓርቲ   ? ' በሚል በህጋዊ መንገድ ተመዝገበው ለሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎ...
31/05/2024

🇪🇹 የፖለቲካ ፓርቲዎች ምን ይላሉ ? 🇪🇹

“ ... ያለፉትን ዘመናት እኮ እንድናይ የተገደድንበት ጊዜ ነው ” - ጎጎት ፓርቲ

? ' በሚል በህጋዊ መንገድ ተመዝገበው ለሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች እያቀረበ ያለውን ወቅታዊ ሀገራዊ ጥያቄዎች በመቀጠል ጎጎት ፓርቲን አነጋግሯል።

የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው አቶ ጀሚል ሳኒ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል።

Q. ከዜጎች ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ጥሰት አንፃር የፓርቲዎን ግምገማና መፍትሄውን ቢገልጹ ?

አቶ ጀሚል ሳኒ፦

“ ሰዎች በተደጋጋሚ ሕይወታቸውን እያጡ ነው። በዋና ከተማዋ ሲይቀር ሰዎች እየታሰሩ፣ እየታገቱ ነው።

የትኛውም ዜጋ የደህንነት ስሜት እየተሰማው አይደለም።

መንግስት #በዋነኛነት የተመሠረተበትና እንዲሰራው ኃላፊነት የተሰጠው ስራ ከየትኛውም ቅድሚያ የዜጎችን ደህንነት ማስጠበቅ የተዘነጋ የሚመስልበት ዘመን ላይ ነን።

በመወያየትና በመነጋገር ጦርነትን ማስቆም ይገባል።

ሰላምን ከማስፈን ይልቅ ፣ የፕሮፓጋንዳ ስራ በመስራት ነው አብዛኛው አቅም እየባከነ ያለው።

ከዚያ ይልቅ አገሪቱን በሚያሻግሩ ሀሳቦች ላይ አተኩሮ መስራት ያስፈልጋል።

ያለፉትን ዘመናት እንደ ቅንጦተ እንድናይ የተገደድንበት ጊዜ ነው። ”

Q. በሙስና ተዘፍቀው ስለሚገኙ ባለስልጣናት እንዲሁም በአጠቃላይ ስለብልሹ አሰራር ፓርቲዎ ምን ይላል ?

አቶ ጀሚል ሳኒ ፦

“ አሁን ላይ ፣ ሌላው ይቅርና የዜጎች ቤቶች ‘ሕገ ወጥ ናቸው’ ተብለው ቤታቸው የሚፈርስባቸው ሰዎች ላይ ገንዘብ የሚጠየቅበት ሁኔታ ነው ያለው።

ከኢትዮጵያ Norm ሁላ ያፈነገጠበት ወቅት ላይ ነው ያለነው። በአብዛኛዎቹ መስሪያ ቤቶች የተለመደውን አይነት አሰራር ከመስራት ይልቅ ከእግሮች እጆች እየቀደሙ ነው።

፣ ቢሮ ውስጥ ሥራ አስፈጻሚዎች እያደረጉበት ያለበት ሂደት ነው አሁን ያለው።

አለ የተባለ የትኛውም ችግርን ለመቅረፍ ላይከብድ ይችላል ፤ ነገር ግን ከተንሰራፋ የትኛውንም ችግር ልቅረፍ ማለት የማይታሰብ ይሆናል።

ሙስና የሀገር ተቋርቋሪነትን፣ ስሜትን ያጠፋል።

እያየነው ያለውም ይሄው ነውና ትኩረት ሊሰጠው ይገባል።”

Q. እንደ ፓርቲ የሚደርስባችሁ ጫና ምንድን ነው ?

አቶ ጀሚል ሳኒ ፦

“ የምስረታ ጉባዔ ባደረግንበት፣ የጉባዔውን ውጤትና የምርጫ ቦርድ ኮሮጆ ጭምር ይዘን በነበረበት ሰዓት ነው እስር የተጀመረው። ክፍለ አገርም አዲስ አበባም እስሮች አሉ።

በአባል ደረጃ አንድ የፓርቲው አባል ከ5 ወራት በላይ ያለ ክስና ዋስትና በእስር ላይ ይገኛሉ። ከአባላቶች እስራትና ተንቀሳቅሶ ከመስራት ጋር ዘተያያዘ ያለፉትን ዘመናት እንደ ቅንጦት እንድናይ የተገደድንበት ጊዜ ነው።

ፓርቲውን የሚደግፉ አባላት ማስፈራሪያ ያደርሱባቸዋል።

የጉራጌ የክልልነት ጥያቄ ሕገ መንግስቱን ያልከተለ በመሆኑ ምስረታው እንዲታገድ፣ ኢ - ሕገ መንግስታዊ ስራዎች በሰሩ ባለስልጣናት ላይ የመሰረትነው ክስ በቀጠሮ እየተጉላላ ነው ያለው። ”

Q. ሕዝቡ በኑሮ ውድነቱ ተማሯል። ለዚህም “ መንግስት ትኩረት አልሰጠም ” የሚሉ ወቀሳዎች ይቀርባሉ። የፓርቲዎ ግምገማ ምንድን ነው ?

አቶ ጀሚል ሳኒ ፦

“ የኑሮ ውድነት በራሱ የሚፈጠር ነገር አይደለም። እስካሁን ከላይ የተነጋገርንባቸው ነገሮች ናቸው እየገፉ የሚያመጡት።

አንዲት አገር #በጦርነት ላይ ሆና ሚሊዮን ዶላሮችም ለጦርነት እያወጣች ፣ አርሶአደር ማምረትና በሰላም ወጥቶ መግባት ባልቻለበት ፣ የመልካም አስተዳደር ፣ የአቅም ፣ የብቃት ጉዳዮች የመጨረሻ ውጤታቸው የኑሮ ውድነቱ ማምጣት ነው።

እነዚህን ችግሮች ማጥፋት፣ መቀነስ ካልተቻለ የኑሮ ውድነቱን ማረጋጋት፣ የተረጋጋ ኢኮኖሚ ማስፈን አይቻልም። ”

Q. ስለምርጫ ያላችሁ አስተያዬት ምንድን ነው ? በቀጣዩ ሀገራዊ ምርጫ ተመራጭ ሆኖ ለመቅረብ ዝግጅት እያደረጋችሁ ነው ?

“ ከምርጫ ጋር በተገናኘ ትኩረት ተደርጎ የሚሰራው፣ አጀንዳውም የሚያዘው ከሚደረገው #የፓርላማ እና ጋር በተገናኘ ነው።

ይሄ ስርዓቱን ለመቀየር የሚያስችል ብቸኛው መንገድ አይደለም። ከዚህ ይልቅ ምርጫ በየአካባቢው ማድረግ ያስፈልጋል። የአካባቢ ምርጫ የተደረገው ከ8 ዓመታት በፊት ነው።

የአካባቢ ምርጫ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል።

አሁን ባለንበት ሁኔታ ላይ #ምርጫ ሊደረግ ይችላል ብሎ ማለት ትንሽ አዳጋች ነው። ”

◾️በቀጣዩ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ፓርቲ የሰጠው ቃል ይቀርባል።

ሕወሓት በቀጣዩ ድርጅታዊ ጉባዔው የገጠሙትን ችግሮች መርምሮ የሕዝብን ተጠቃሚነት እንደሚያረጋግጥ አስታውቀዋል የሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ሊቀመንበር ደብረጽዮን ገብረ ሚካኤል (...
30/05/2024

ሕወሓት በቀጣዩ ድርጅታዊ ጉባዔው የገጠሙትን ችግሮች መርምሮ የሕዝብን ተጠቃሚነት እንደሚያረጋግጥ አስታውቀዋል

የሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ሊቀመንበር ደብረጽዮን ገብረ ሚካኤል (ዶ/ር)፣ ‹‹ቀጣዩ 14ኛ ድርጅታዊ ጉባዔ ሕወሓት እንደ ድርጅት የገጠሙትን ችግሮች መርምሮ፣ የሕዝብን ተጠቃሚነት የምናረጋግጥበት ይሆናል፤›› አሉ፡፡

ሊቀመንበሩ ይህንን የተናገሩት ከመገናኛ ብዙኃን ጋር ሰሞኑን ባደረጉት ቃለ ምልልስ ነው፡፡

እንደ ድርጅት አጋጥሞናል ያሉትን ስትራቴጂካዊ የአመራር ክፍተትና የሕዝብን ተጠቃሚነት የሚያጎላ አመራርን እንድንፈጥር ያስችለናል ያሉበትን ቀጣዩን 14ኛ ድርጅታዊ ጉባዔ ከማድረጋቸው በፊት፣ የጉባዔውን ዓላማና ከጉባዔው ምን እንደሚጠበቅ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ጉባዔው ከሚካሄድባቸው ዋና ዋና ዓላማዎች ውስጥ አንዱ ብዙ የማጣራት ሥራ እንደሚሆን ገልጸው፣ ይህም ተግባር አሁን መሬት ላይ አሉ ካሏቸው እውነታዎች በመነሳትና እነሱንም ለመቀየር የሚያስችል መሆኑን ጨምረው አስረድተዋል፡፡

‹‹ጉባዔው ብዙ መጣራት የሚያስፈልጋቸውን ነገሮች የሚፈታ ሲሆን፣ አሁን መሬት ላይ ያሉ እውነታዎችን ከግንዛቤ በመክተት፣ ያሉትን ችግሮች ለመፍታት የሚያስችልም ነው፤›› ብለዋል፡፡

ቀጣዩ ጉባዔ ሕወሓት እንደ ድርጅት ያጋጠሙትን ችግሮች የሚያጣራበት እንደሆነ ገልጸው፣ ከዚህ በፊት በተደረገ ድርጅታዊ ግምገማ የተደረሰበትን ስትራቴጂካዊ የአመራር ክፍተት ጨምሮ፣ የብቃትና የቅንነት ችግር፣ የሕዝብ ተጠቃሚነት ችግር በቀናነት ይስተካከሉበታል በማለት አስረድተዋል፡፡

ከፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በኋላ ብዙ የተቀየሩ ነገሮች እንዳሉ የገለጹት ሊቀመንበሩ፣ ‹‹ሆኖም አሁንም ብዙ ያላለቁ ችግሮች አሉ፡፡

ከተቻለ ለውጡ ካለው አካሄድና በሚመጥነው ፍጥነት አብሮ መጓዝ፣ ካልሆነ ግን ከለውጡ ጋር አብሮ መለወጥ ያስፈልጋል፤›› ብለዋል፡፡

‹‹ቀጣዩ ጉባዔ የአሠራርና የአተያይ ፍተሻ በማድረግ በተቀናጀ መንገድ መታረም ያለባቸውን ሥራዎች ማከናወን እንዲያስችል ያደርጋል፤›› ብለዋል፡፡

ሊቀመንበሩ በመቀጠል ጉባዔው ከላይ የተጠቀሱትን ጉዳዮች በሟሟላት መንገድ መካሄድ እንደሚጠበቅበት ገልጸው፣ መለወጥ ያለበትን ነገር እየለወጡ አብሮ መቀጠል የሚያስችል ጉባዔ መሆን እንዳለበትም ጨምረው ገልጸዋል፡፡

ደብረ ጽዮን (ዶ/ር) እንዳሉት፣ ከድርጅቱ ዋና ችግሮች ውስጥ አንዱ የአመራር ችግር ነው፡፡ ችግሩን ለመፍታት ግምገማና ውይይት አስፈላጊ ነው ብለው፣ ቀጣዩ ጉባዔ ይህንን በሚመጥን ደረጃ እንደሚካሄድና ለትግራይ ሕዝብ ቀና ሆኖ ለማገልገል እንዲያስችል ያደርጋል ብለዋል፡፡

‹‹የጉባዔው መድረክ ሕወሓትን በሚመጥን ደረጃ የሚዘጋጅና ከዚህ በፊት ካደረግናቸው ጉባዔዎች ትምህርት የወሰደ ሲሆን፣ ያሉብንን ችግሮች ማለትም አጠቃላይ ድርጅታዊና የአመራር ችግሮችን የሚፈታ ሆኖ መውጣት አለበት የሚል እምነት አለን፤›› ብለዋል፡፡

በተጨማሪ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደርና በሕወሓት መካከል አለ ስለተባለው ልዩነት እንዲያብራሩ የተጠየቁት ሊቀመንበሩ፣ በጊዜያዊ አስተዳደሩና በሕወሓት መካከል መሠረታዊ ልዩነት የለም ብለዋል፡፡

ሆኖም በሁለቱ ወገኖች መካከል ግን የፖለቲካ ልዩነት እንዳለ የገለጹት ደብረ ጽዮን (ዶ/ር)፣ የፖለቲካ ልዩነታቸው እንደ ሕወሓት አመራር ያለ ልዩነት እንጂ፣ እንደ ጊዜያዊ አስተዳደርና እንደ ሕወሓት የተፈጠረ አይደለም ሲሉ ገልጸውታል፡፡

‹‹ልዩነቱ በሁለቱ የሕወሓት አመራሮች መካከል ያለ ልዩነት እንጂ፣ የጊዜያዊ አስተዳደርና የሕወሓት ልዩነት አይደለም፡፡

ይህ ደግሞ ለሕዝብ ቅድሚያ በመስጠት የሚፈታ ነገር ነው፤›› ያሉት ደብረ ጽዮን (ዶ/ር)፣ ሕወሓት ተመሳሳይ ችግሮችን በሠለጠነ መንገድ የመፍታት ልምድ ስላለውና አሁን ያለውንም ፖለቲካዊ ልዩነት በተመሳሳይ እንደሚፈታው ገልጸው፣ ቀጣዩ ጉባዔ ለልዩነቱ ዓይነተኛ መፍትሔ ይኖረዋል ብለዋል፡፡

ከቀናት በፊት የሕወሓት ቃል አቀባይ ኮሎኔል አማኑኤል አሰፋ ስለቀጣዩ የሕወሓት ድርጅታዊ ጉባዔ ዝግጅትን በተመለከተ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ ቀጣዩ 14ኛው ጉባዔ ለክልሉ ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት ተናግረው ነበር፡፡

ጉባዔው የሚካሄደው በጣም ውስብስብ በሆነ ሁኔታ ውስጥ እንደሆነ፣ ሕወሓት ካለበት የውስጥ ተግዳሮት ወጥቶ በትግራይ ያሉትን ችግሮች ለመፍታት የመሪነት ሚናውን ለመወጣት ወሳኝ ነው ማለታቸው ይታወሳል፡፡

ሕወሓት የካቲት 14 ቀን 2016 ዓ.ም. ስትራቴጂካዊ የአመራር ክፍተት አጋጥሞኛል ባለበት ድርጅታዊ ግምገማ ወቅት፣ ጠላት እጅ ወድቀዋል ባላቸው የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ጉዳይ ላይ ውሳኔ ማስተላለፉ የሚታወስ ሲሆን፣ በፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ መሠረት ሌሎች የድርጅቱ አባላቶችን ጨምሮ ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂምንና ወ/ሮ ሙሉ ገብረ እግዚአብሔርን ከማዕከላዊ ኮሚቴና ከሕወሓት አባልነት ማሰናበቱ አይዘነጋም፡፡

Bukmal


ከካሳ ክፍያ ጋር በተያያዘ የመንግስት አስተዳደሮች፣ ዳኞች እና ደላሎች የሚያገኙትን ያልተገባ ጥቅም ያስቀራል የተባለለት አዋጅ ሊወጣ ነው።በካሳ ክፍያ ሂደት የመንግስት አስተዳደር ዳኞች እና ...
30/05/2024

ከካሳ ክፍያ ጋር በተያያዘ የመንግስት አስተዳደሮች፣ ዳኞች እና ደላሎች የሚያገኙትን ያልተገባ ጥቅም ያስቀራል የተባለለት አዋጅ ሊወጣ ነው።

በካሳ ክፍያ ሂደት የመንግስት አስተዳደር ዳኞች እና ደላሎች የሚያገኙትን ያልተገባ ጥቅም በማስቀረት ዋናው የመሬት ባለይዞታውን ተጠቃሚ የሚያደርግ አዋጅ እየተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል።

ይህ የተባለው መሬት ይዞታ የሚለቀቅበትን፣ ካሳ የሚከፈልበትን እና ተነሽዎች መልሰው የሚቋቋበትን ሁኔታ ለመወሰን የወጣውን ረቂቅ አዋጅ ለማሻሻል ውይይት በተደረገበት ወቅት ነው።

በውይይቱ የተሳተፉ አካላት እንደተናገሩት ለመሰረተ-ልማት ፕሮጀክቶች ግንባታ መዘግየት ዋናውና ትልቁ ማነቆ የልማት ተነሺዎች የሚጠይቁት የተጋነነ የካሳ ክፍያ መሆኑን ገልጸው፤ ንብረት የሚገምቱ እና ካሳ የሚከፍሉ ተቋማት ወደ አንድ ሊመጡ እንደሚገባ ጠቁመዋል።

በማህበረሰቡም ፕሮጀክቶች ተገንብተው ከሚሰጡት ጥቅም ይልቅ፤ ከካሳ ክፍያ የሚገኘውን ጥቅም አስበልጦ የማየት አስተሳሰብ በመኖሩ፤ ትክክለኛ እና ወቅቱን ያገናዘበ የካሳ ክፍያ ለመፈጸም የአዋጁ መሻሻል አስፈላጊነቱ የላቀ እንደሆነም ባለድርሻ አካላት አንስተዋል።

የፍትህ ሚኒስትሩ ጌዲዮን ጢሞቲዎስ በበኩላቸው የአዋጁ መሻሻል በካሳ ክፍያ ሂደቱ በታችኛው እርከን የመንግስት አስተዳደር፣ ዳኞች እና ደላሎች የሚያገኙትን ያልተገባ ጥቅም በማስቀረት ዋና የመሬት ባለይዞታውን ተጠቃሚ ማድረግ የሚያስችል ነው ብለዋል።

ማሻሻያ አዋጁ መሰረተ ልማቶች ሲገነቡ የንብረት ግመታው እና የካሳ ክፍያው በክልልና በወረዳ መዋቅሮች የሚፈጸም መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሩ፤ ዜጎች ቅሬታ ሲያነሱም በአቅራቢያቸው የፍትህ አገልገሎት እንዲያገኙ የሚረዳ መሆኑን ተናግረዋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም

Bukmal

ዜና: በሰሜን  #ሸዋ ዞን 8 ሺህ 73 ሰዎች በወባ በሽታ መጠቃታቸውን የዞኑ ጤና መምሪያ ገለጸ፣ የስርጭት መጠኑ 11 በመቶ መሆኑም ተጠቁሟልበማኅበረሰቡ ዘንድ መዘናጋት በመኖሩ ምክንያት በሰ...
30/05/2024

ዜና: በሰሜን #ሸዋ ዞን 8 ሺህ 73 ሰዎች በወባ በሽታ መጠቃታቸውን የዞኑ ጤና መምሪያ ገለጸ፣ የስርጭት መጠኑ 11 በመቶ መሆኑም ተጠቁሟል

በማኅበረሰቡ ዘንድ መዘናጋት በመኖሩ ምክንያት በሰሜን ሸዋ ዞን የወባ በሽታ ስርጭትን በሚፈለገው ደረጃ መቀነስ አለመቻሉን የሰሜን ሸዋ ዞን ጤና መምሪያ ገልጿል፡፡

ባለፉት ወራት 72 ሺህ 455 ሰዎች ላይ በተደረገ ምርመራ 8 ሺህ 73 ሰዎች በወባ በሽታ የተጠቁ መኾናቸውን ከዞኑ ጤና መምሪያ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

የወባ በሽታ በተጠቁ ሰዎች አቅራቢያ በተደረገ ተጨማሪ ምርመራ ደግሞ 159 ሕሙማንን መለየት ተችሏል ነው ያለው መምሪያው፡፡

የመምሪያው ኀላፊ ጸዳለ ሰሙንጉሥ በ2016 በጀት ዓመት የወባ ስርጭት ምጣኔ ወደ 5 በመቶ ዝቅ እንዲል ይጠበቅ ነበር ነው ያሉት፡፡ ይሁን እንጂ አሁን ላይ በዞኑ የስርጭት መጠኑ 11 በመቶ መድረሱን ተናግረዋል፡፡

በተለይ እንደ ሸዋሮቢት፣ መርሃቤቴ፣ እንሳሮ፣ ምንጃር እና መሰል ቆላማ የዞኑ አካባቢዎች የበሽታው ስርጭት ከፍተኛ የኾነባቸው ናቸው ብለዋል መምሪያ ኀላፊዋ፡፡

በማኅበረሰቡ ዘንድ የወባ በሽታ የሌለ እስኪመስል ድረስ መዘናጋት መኖሩን የጠቆሙት ሃላፊዋ ለአብነትም የወባ መከላከያ አጎበር ከወሰዱት መካከል 30 በመቶዎቹ ብቻ ናቸው በአግባቡ ጥቅም ላይ እያዋሉ የሚገኙት ሲሉ መናገራቸውን ከአሚኮ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

በአገር አቀፍ ደረጃ በ1,397 ወረዳዎች የወባ ወረርሽኝ መከሰቱን እና በ #ኦሮሚያ እና #አማራ ክልሎች ያለው ቁጥር ከፍተኛ መሆኑን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ ሪፖርትን ዋቢ በማድረግ መዘገባችን ይታወሳል።

ሰበር ዜና ህወሓት ችግር ገጥሞኛል አለ              #ኢትዮጵያ
30/05/2024

ሰበር ዜና ህወሓት ችግር ገጥሞኛል አለ






#ኢትዮጵያ

ሰበር ዜና ህወሓት ችግር ገጥሞኛል አለ ቨ? p? #ኢትዮጵያ ...

ሰበር ዜና ኦሮቶዶክስ አደጋ ላይ ነኝ አለች የአቡነ ማትያስ አነጋጋሪ መግለጫ | ፋኖ በአማራ ክልል ክልከላ ጣለ          #ፋኖ        #ኢትዮጵያ
30/05/2024

ሰበር ዜና ኦሮቶዶክስ አደጋ ላይ ነኝ አለች የአቡነ ማትያስ አነጋጋሪ መግለጫ | ፋኖ በአማራ ክልል ክልከላ ጣለ




#ፋኖ



#ኢትዮጵያ




ሰበር ዜና ኦሮቶዶክስ አደጋ ላይ ነኝ አለች የአቡነ ማትያስ አነጋጋሪ መግለጫ | ፋኖ በአማራ ክልል ክልከላ ጣለ #ፋኖ #ኢትዮጵያ....

ሰበር ዜና ኤርትራ ላይ ጥቃት ተፈፀመ የኢሳያስ አፈወርቂ መግለጫ እና ማስጠንቀቂያ           #ፋኖ
29/05/2024

ሰበር ዜና ኤርትራ ላይ ጥቃት ተፈፀመ
የኢሳያስ አፈወርቂ መግለጫ እና ማስጠንቀቂያ





#ፋኖ



ኤርትራ ላይ ጥቃት ተፈፀመ | የኢሳያስ አፈወርቂ መግለጫ እና ማስጠንቀቂያ | #ኢትዮጵያ #ሰበርዜና #ሰ...

ከየካቲት 15 እስከ 28 ቀን 2016 ዓ/ም በምዕራብ ጎጃም ዞን፣ ደጋ ዳሞት ወረዳ (ዝቋላ ወገም፣ ፈረስ ቤት01፣ ገሳግስና ጉድባ ሰቀላ ቀበሌዎች) እና ሰከላ (አጉት፣ ጉንድልና አምቢሲ ቀበ...
29/05/2024

ከየካቲት 15 እስከ 28 ቀን 2016 ዓ/ም በምዕራብ ጎጃም ዞን፣ ደጋ ዳሞት ወረዳ (ዝቋላ ወገም፣ ፈረስ ቤት01፣ ገሳግስና ጉድባ ሰቀላ ቀበሌዎች) እና ሰከላ (አጉት፣ ጉንድልና አምቢሲ ቀበሌዎች እና ግሼ ዓባይ ከተማ) በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎችና በታጣቂዎች መካከል የተካሄዱ የትጥቅ ግጭቶችን ተከትሎ በሲቪል ሰዎች ላይ ሞት፣ አካል ጉዳትና የንብረት ውድመት ደርሷል።

- የካቲት 20/2016 በሰሜን ጎጃም ዞን ሜጫ ወረዳ ብራቃት ቀበሌ በሚገኘው የጋፊት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን የአብነት ተማሪዎች የዕለቱን ትምህርትና ጉባኤ ከምሽቱ 5፡00 ሰዓት አካባቢ አጠናቀው ወደ ማደሪያ ጎጇቸው ከገቡ በኋላ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች አባላት ከሌሊቱ 6፡30 ሰዓት ገደማ ላይ ወደ ቦታው ደርሰው ተማሪዎችን “ #ውጡ ” እያሉ ተኩስ በመክፈት ቀድመው
በወጡ ላይ ግድያ እንደፈጸሙ፤ ሌሎች 8 ተማሪዎችንም ደግሞ በቁጥጥር ሥር አውለው ካሳደሩ በኋላ በማግስቱ ምንም ጥፋት የለባችሁም ብለው እንደለቀቋቸው ኢሰመኮ ለመረዳት ችሏል።

በወቅቱ በአቅራቢያው የሚንቀሳቀስ የታጠቀ ኃይል እንዳልነበር ምስክሮች አስረድተዋል።

- መጋቢት 2 ቀን 2016 ዓ/ም በኦሮሞ ብሔረሰብ ልዩ ዞን የተነሱ ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች በሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር እና #ቀወት ወረዳዎች በሚገኙ የተወሰኑ ቀበሌዎች ላይ በፈጸሙት ጥቃት በሲቪል ሰዎች ላይ ግድያ መፈጸሙን፣ የአካል ጉዳት መድረሱን፣ ንብረት መውደሙን፣ መኖሪያ ቤቶች መቃጠላቸውን እና የቀንድ ከብቶችና ባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪዎች መዘረፋቸውን ኢሰመኮ ተረድቷል።

- መጋቢት 6 ቀን 2016 በአማራ ክልል፣ በባሕር ዳር ከተማ ዘንዘልማ አካባቢ አቶ ብርሃኑ ሽባባው አካል ፣ አቶ በላይ አካል እና አቶ ተሾመ ይበልጣል የተባሉ ነዋሪዎች አንዱ በሚሠራበት ሱቅ እና ሁለቱ በመኖሪያ ቤታቸው ውስጥ " ኑ ለጥያቄ ትፈለጋላችሁ " በሚል በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር ከዋሉ በኋላ መጋቢት 7 ቀን 2016 በባሕር ዳር ቀበሌ 14 በተለምዶ ጉዶ ባሕር አካባቢ በጥይት ተገድለው ተገኝተዋል።

- በባሕር ዳር ዳግማዊ ምኒልክ ክ/ከተማ ጋጃ መስክ ተብሎ በሚጠራ ስፍራ መጋቢት 29 ቀን 2016 ዓ.ም. ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት አካባቢ ማንነታቸው ባልታወቁ አካላት በተፈጸመ ጥቃት ሶላት ስግደት አከናውነው ወደ ቤታቸው እየተመለሱ የነበሩ የእስልምና ተከታይ 5 ሰዎች (4ቱ የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ) ተገድለዋል።

ሚያዝያ 7/2016 ከጧቱ 3፡00 ሰዓት ላይ በደቡብ ጎንደር ዞን እስቴ ወረዳ አጎና ቀበሌ ላይ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ከእስቴ ወረዳ ወደ ላይ ጋይንት ወረዳ በመጓዝ ላይ እያሉ በአካባቢው ላይ በሚንቀሳቀሱ የታጠቁ ኃይሎች ( #ፋኖ ) ድንገተኛ የደፈጣ ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ ታጣቂዎቹ አካባቢውን ጥለው እንደሸሹ ወደ ቦታው በመግባት (1 ሴትና 6 ወንዶች) ሲቪል ሰዎች ላይ ከሕግ ውጪ ግድያ ፈጽመዋል።

ከ15 በላይ የሚሆኑ የቆርቆሮ ክዳን ያላቸው መኖሪያ ቤቶች እና 3 የገለባ ቤቶችና ንብረት መቃጠላቸውን እንዲሁም ከ100 በላይ የሚሆኑ የቀበሌው ነዋሪዎች ወደ ሌላ አካባቢ የተፈናቀሉ መሆኑን የቀበሌው ነዋሪዎች እና ተጎጂዎች ገልጸዋል።

- ግንቦት 4/2016 ዓ/ም ከቀኑ 7፡00 ሰዓት አካባቢ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ቀወት ወረዳ ተሬ ቀበሌ ውስጥ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት በጉሎ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ግቢ ውስጥ 2 ሲቪል ሰዎች ሲገደሉ አንድ ሴት መምህርትን ጨምሮ ሌሎች 9 ሲቪል ሰዎች የቆሰሉ መሆኑን ኢሰመኮ ተረድቷል።

Bukmal
#ኢትዮጵያ


ሠራተኛው 'በቂና ተመጣጣኝ' ክፍያ እንዲያገኝ ተጠየቀየ  #ኢትዮጵያ አሠሪዎች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢአማኮ) 'የሠራተኛው ተደጋጋሚ ጥያቄ የሆነውን' የአነስተኛ ደሞዝ ወለል ይወሰን ጥያቄ ም...
28/05/2024

ሠራተኛው 'በቂና ተመጣጣኝ' ክፍያ እንዲያገኝ ተጠየቀ

የ #ኢትዮጵያ አሠሪዎች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢአማኮ) 'የሠራተኛው ተደጋጋሚ ጥያቄ የሆነውን' የአነስተኛ ደሞዝ ወለል ይወሰን ጥያቄ ምላሽ ሊሰጠው ይገባል ሲል አሳሰበ፡፡

ኢአማኮ በስሩ ከሚገኙ የአሠሪ ፌዴሬሽኖች ጋር በትላንትናው ዕለት የ2015 እና የ2016 ዓ.ም ጉባኤውን ባካሄደበት ወቅት፤ በመንግሥት፣ በአሠሪውና በሠራተኛው የጋራ ምክከር ተደርጎ ሠራተኛው 'በቂና ተመጣጣኝ' ክፍያ እንዲያገኝ ጠይቋል።

ሠራተኛውን ወክለው ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አያሌው አህመድ፤ በአብዛኛው ድርጅቶች ለሠራተኞቻቸው የሚከፍሉት የደመወዝ ክፍያ እዚህ ግባ የማይባልና በሀገራችን የተፈጠረውን የዋጋ ግሽበት መቋቋም የማይችል ነው ብለዋል።

መንግሥት፣ አሠሪና ሠራተኛ በጋራ በመነጋገር ሊያኖር የሚችል የዝቅተኛ ደመወዝ ወለል በጥናት ላይ ተመርኩዞ ባልተቀመጠበት ሁኔታ ተፈላጊውን ጥራት ያለው ምርታማ ሠራተኛን ማፍራት አስቸጋሪ በመሆኑ አፋጣኝ ምላሽ ሊሰጠው ይገባል ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ አሠሪዎች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢአማኮ) ፕሬዝዳንት አቶ ታደለ ይመር በበኩላቸው የአነስተኛ ደመወዝ ወለል ጉዳይ ተረድተን ወደ ተግባር ለመለወጥ አሠሪዎች ቁርጠኛ መሆን ይገባቸዋል ሲሉ አሳስበዋል፡፡

የኢትዮጵያ አሠሪዎች ኮንፌዴሬሽን የተለያዩ አሠሪዎች ፌዴሬሽኖችን በማሰባሰብ ለአሠሪውም ሆነ ለሠራተኛው በተደራጀ መልኩ ጥያቄዎችን የማቅረብ አላማን ሰንቆ በ2010 ዓ.ም. የተመሰረተ ተቋም ነው።

Bukmal

  ' አልያንስ 2015 ' የተባለው 8 የአዉሮጳ የልማት ድርጅቶች ያቀፉት ተቋም ሀገራት ያሉበትን የረሃብ አደጋ ደረጃ የሚያመላክተውን የዓለም አቀፍ የረሃብ ኢንዴክስ (Global Hunger ...
28/05/2024



' አልያንስ 2015 ' የተባለው 8 የአዉሮጳ የልማት ድርጅቶች ያቀፉት ተቋም ሀገራት ያሉበትን የረሃብ አደጋ ደረጃ የሚያመላክተውን የዓለም አቀፍ የረሃብ ኢንዴክስ (Global Hunger Index) ይፋ አድርጓል።

በዚህ የረሃብ መለኪያ ሪፖርት ከ125 ሀገራት መካከል ኢትዮጵያ ከመጨረሻዎቹ 101ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።

የሰቆጣ ቃልኪዳን የፕሮግራም አስተባባሪ ዶክተር ሲሳይ ሲናሞ ምን አሉ ?

- ሪፖርቱ ሲዘጋጅ ሀገራት ካሉበት ደረጃ አንጻር የተለያየ ደረጃ ይሰጣቸዋል።
- የረሃብ ደረጃው ባለፉት 20 ዓመታት በተሰሩት ስራዎች ከ53 በመቶ ወደ 26.1 በመቶ ዝቅ ብሏል። በጣም alarming ከነበረበት ወደ serious ደረጃ ነው የወረደው።
- አሁንም ብዙ ስራ ይቀራል።
- በሀገራችን ያለው የምግብ እና የስርዓተ ምግብ ሁኔታ ብዙ መሰራት አለበት።
- ሪፖርቱ በየዓመት ነው የሚወጣው። በቀጣይ ወጣቶችን ማዕከል ባደረጉ ስራዎች ትኩረት በማድረግ ለመስራት ያለው ሁኔታ ለማሻሻል ይረዳል።
- በአፍሪካ ያለው ከፍተኛ የወጣት ቁጥር በግብርናው ዘርፍ አሰማርቶ መጠቀም አለመቻል አፍሪካ በምግብ ራሷን እንዳትችል አድርጓል።
- ኢትዮጵያ ውስጥ 70 በመቶ የስራ እድል የሚመነጨው ከግብርና ሆኖ እያለ ያላደገው የግብርና ዘርፍ የሚፈለገውን ያህል የስራ እድል እንዳይፈጠር እንቅፋት ሆኗል።

እንደ ዓለም አቀፉ ሪፖርት በኢትዮጵያ እና በዓለም ዙሪያ ለታየው በምግብ እራስን ያለመቻል ችግር ፦
➡ የአየር ንብረት ለውጥ
➡ በየቦታው የሚደረጉት #ጦርነቶች
➡ የኢኮኖሚ መላሸቅ
➡ የኮሮና ወረርሽኝ ዋነኞቹ ናቸው።

በከፍተኛ የምግብ እጥረት እና በረሃብ አደጋ ውስጥ ላሉ ሀገራት መፍትሄ ተብሎ የተቀመጠው መንግሥታት ፦

° ትልቅ አቅም ያላቸው ወጣቶችን ወደ ስራ ገብተው ውጤት እንዲያመጡ ቦታ መስጠት፤

° ብድር ማመቻቸት፤

° ለስራ የሚሆኑ የተለያዩ ስልጠናዎች ማመቻቸት ይኖርባቸዋል የሚሉት ይገኙበታል።

በግብርናው ዘርፍ ለመዘናት የቆየው በበሬ ማረስ ተግባር ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም በማዘመን በመጠንም በአይነትም ከፍ ያለ ምርት ማምረት ካልተቻለ ኢትዮጵያ አሁን ካለችበት አሳስቢ ደረጃ ወደ መጨረሻው አስከፊ ደረጃ ልትደርስ ትችላለች ሲል ሪፖርቱ አስጠንቅቋል።

⚠️ ኢትዮጵያ በ2022 ሪፖርት ላይ 27.6 በመቶ በማስመዝገብ ከ121 ሀገራት 104ኛ ደረጃ ላይ ነበረች።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የዚህ መረጃ ምንጮች ፦ ሸገር ኤፍ ኤም ፣ የAlliance 2015 እና የGlobal Hunger Index ድረገጽ መሆናቸውን ያሳውቃል።

Bukmal

በግንቦት 20 ጉዳይ መንግሥት መግለጫ ሰጠ            #ኢትዮጵያ
27/05/2024

በግንቦት 20 ጉዳይ መንግሥት መግለጫ ሰጠ





#ኢትዮጵያ

በግንቦት 20 ጉዳይ መንግሥት መግለጫ ሰጠ #ኢትዮጵያ ...

 #ኢትዮጵያበሀገሪቱ ውስጥ ያለ ማንኛውም የሃይማኖት ተቋም የፋይናንስ ኦዲት ሪፖርቱን ለሰላም ሚኒስቴር ማቅረብ እንደሚኖርበት ፤ ከውጭ አገር የሚመጣ የገንዘብ ዕርዳታ በሕግ ሥልጣን ለተሰጠው ...
27/05/2024

#ኢትዮጵያ

በሀገሪቱ ውስጥ ያለ ማንኛውም የሃይማኖት ተቋም የፋይናንስ ኦዲት ሪፖርቱን ለሰላም ሚኒስቴር ማቅረብ እንደሚኖርበት ፤ ከውጭ አገር የሚመጣ የገንዘብ ዕርዳታ በሕግ ሥልጣን ለተሰጠው አካል ማሳወቅ እንደሚኖርበት የሚደነግግ ረቂቅ አዋጅ መዘጋጀቱን ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል።

" የሃይማኖት ጉዳዮች አዋጅ " የተሰኘው ረቂቅ አዋጁ የሃይማኖት ተቋማቱ ተቀባይነት ያለው የሒሳብ አያያዝና የኦዲት ሥርዓት መዘርጋት እንደሚኖርባቸው፣ የኦዲት ሪፖርታቸውን ለሰላም ሚኒስቴር ማቀረብ እንዳለባቸው ይደነግጋል፡፡

ረቂቅ አዋጁ ምን ይዟል ?

- የሃይማኖት ተቋማት የሚጠቀሙት የሒሳብ አያያዝ ሥርዓት የገቢ፣ የወጪና አጠቃላይ የንብረት ዝርዝር የያዘ መሆን አለበት።

- የገቢ አሰባሰብና የወጪ አስተዳደር በሕጋዊ መንገድ ማከናወን አለባቸው።

- የሃይማኖት ተቋም በራሱ ሥራዎችን በሚያከናውንበት ጊዜ ለዚሁ ሥራ ሲባል የተለየ የባንክ ሒሳብ መክፈትና የተለየ መዝገብ መያዝ አለበት።

- ማንኛውም የሃይማኖት ተቋም ከውጭ የሚላክለትን የገንዘብ ዕርዳታ፣ ስጦታ ወይም ሌሎች የገንዘብ ድጋፎችን በሕግ ሥልጣን ለተሰጠው አካል ማሳወቅ አለበት። ሲያሳውቅም ፦
° የለጋሹን ድርጅት ወይም ግለሰብ ስም እና አድራሻ፣
° የተለገሰው የገንዘብ፣ ስጦታ ዓይነት እና መጠን ፣
° ስጦታው / ድጋፉ የተሰጠበት ልዩ ዓላማ መካተት አለበት።

- ማንኛውም የሃይማኖት ተቋም የበጀት ዓመቱ ባለቀ በ3 ወር ውስጥ የፋይናንስ እንቅስቃሴውን በገለልተኛ ኦዲተር ማስመርመር አለበት። የኦዲተሩን አቋም እና የውሳኔ ሐሳብም መያዝ ይኖርበታል።

- የሰላም ሚኒስቴር የደረሰውን የኦዲት ሪፖርት አመቺ በሆነ መንገድ ለሕዝብ ይፋ ማድረግ ይኖርበታል።

#ሪፖርተርጋዜጣ
#ኢትዮጵያ


#ቡክማል
#አሜሪካ
#ኦዲት

ሩሲያ በኻርኪቭ ሱፐርማርኬት ላይ ባደረሰችው ጥቃት 11 ሰዎች ተገደሉበሰሜን ዩክሬኗ ኻርኪቭ ከተማ የሚገኝ ሱፐርማርኬት በሩስያ ጦር ግላይድ ቦምብ ከደረሰበት በኋላ 11 ሰዎች ሲሞቱ በርካቶች ...
26/05/2024

ሩሲያ በኻርኪቭ ሱፐርማርኬት ላይ ባደረሰችው ጥቃት 11 ሰዎች ተገደሉ

በሰሜን ዩክሬኗ ኻርኪቭ ከተማ የሚገኝ ሱፐርማርኬት በሩስያ ጦር ግላይድ ቦምብ ከደረሰበት በኋላ 11 ሰዎች ሲሞቱ በርካቶች ቆስለዋል ሲሉ የአካባቢው ባለስልጣናት ተናግሩ።

በከተማው ሰሜናዊ ዳርቻ በሚገኘው ኤፒሴንተር ኬ በተባለው መደብር ላይ ከፍተኛ እሳት መነሳቱም ታይቷል።

የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዜለንስኪ፤ ጥቃቱ በተፈፀመበት ወቅት ከ200 በላይ ሰዎች በሱፐርማርኬቱ ውስጥ ሊገኙ እንደሚችሉ ተናግረዋል።
የኻርኪቭ ገዥ ኦሌህ ሲኒዬሁቦቭ የሟቾች ቁጥር ወደ 11 ከፍ ማለቱን እሑድ ዕለት አስታውቀዋል።

ቀደም ሲል ስድስት ሰዎች “በጥቃቱ ቦታ ሞተዋል" ሲሉ ተናግረው ነበር። 40 ሰዎች መቁሰላቸውን እና 16 ሰዎች የደረሱበት አለመታወቁንም ገልጸው ነበር።
የኻርኪቭ ከንቲባ ኢጆር ቴሬኮቭ “ብዙ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ጠፍተዋል፤ ይህ ግልጽ ሽብርተኝነት ነው” ብለዋል።

ፕሬዝዳንት ዜለንስኪ አክለውም “በኻርኪቭ ላይ የተደረገው ይህ ጥቃት የሩሲያ እብደት መገለጫ ነው” ሲሉ ገልጸዋል።

"እንደ (የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር) ፑቲን ያሉ እብዶች ብቻ ናቸው በዚህ መንገድ ሰዎችን መግደል እና ማሸበር የሚችሉት።"
ቴሬኮቭ አክለውም በማዕከላዊ ኻርኪቭ በደረሰ ሁለተኛ ጥቃት ስምንት ሰዎች ቆስለዋል።

ጥቃቱ ዩክሬናውያን የአየር መከላከያ ስለሌላቸው የሚሰማቸውን ጭንቀት የሚያጎላ ነው ተብሏል።

ዜለንስኪ አክለውም ዩክሬን እራሷን መከላከል እንድትችል ከምዕራባውያን አጋሮች የአየር መከላከያ መሣሪያዎችን እንደምትፈልግ በድጋሚ ገልጸዋል ።
በጣሊያን በተካሄደው የጂ7 የገንዘብ ሚኒስትሮች ስብሰባ ከታገዱ የሩሲያ ንብረቶች የሚገኘውን ትርፍ ለዩክሬን የጦርነት ዘመቻ እንዲውል ለማድረግ የቀረበውን ሃሳብ መደገፋቸውን ተከትሎ የመጣ ጥቃት ነው።

የአሜሪካ የግምጃ ቤት ኃላፊ ጃኔት ዬለን ሃሳቡ ሰፊ ድጋፍ አለው ብለዋል።
አሜሪካ ባዘጋጀቸው ዕቅድ መሰረት የጂ7 አባል አገራት እና አጋሮቻቸው ለኪዬቭ 50 ቢሊዮን ዶላር ብድር ለማግኘት በምዕራባውያን ባንኮች እንዳይንቀሳቀሱ የታገዱ የሩሲያ ንብረቶችን እንደ ብድር ማስያዣ ይጠቀማሉ። ሃሳቡ በሚቀጥለው ወር ተጨማሪ ውይይት ይደረግበታል።

ሩሲያ የበቀል እርምጃ እንደምትወስድ ዝታለች።
በካርኪቭ ላይ የተፈጸመው ጥቃት የሞስኮ ያላት በራስ የመተማመን ስሜት እያደገ መምጣቱን የሚያሳይ ሌላ ምልክት ነው ተብሏል። ዩክሬን ተጨማሪ የምዕራባውያን ጦር ድጋፍ ለማግኘት እየተጠባበቀች ባለችበት ጊዜ ሩሲያ ዕድሉን ተጠቅማ ለማጥቃት የወሰነች ይመስላል።

በጥቃቱ ላይ ጥቅም ላይ የሚውሉት ግላይድ ቦምቦች በአሮጌ የሶቪየት ቦምቦች ላይ የሚተጣጠፉ ክንፎችን እና የሳተላይት መረጃ እንዲያገኙ በማድረግ የተሠሩ ናቸው። ርካሽ ቦምቦች ቢሆኑም ግን አጥፊ ናቸው ተብሏል።
ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዜለንስኪ እንዳሉት ከሆነ በመጋቢት ወር ብቻ ሦስት ሺህ ያህል ግላይድ ቦምቦች በአገሪቱ ላይ ተጥለዋል።

የአውሮፓ የፖሊሲ የጥናት ማዕከል (ሲኢፒኤ) በቅርቡ ባወጣው ዘገባ እንደገለጸው ከሆነ በየካቲት ወር ቁልፍ የሆነችውን አቪዲቪካ ከተማ ለመያዝ ቦምቡ ወሳኝ ነበር።

#ኢትዮጵያ
#አሜሪካ

በ  #አሜሪካ የ  #ኢትዮጵያ አምባሳደር ስለሺ በቀለ (ዶ/ር) ያቀረቡት መልቀቂያ ተቀባይነት ማግኘቱ ተዘገበ በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ተደራዳሪነታቸው ስማቸው በጉልህ የሚነሳው፤ በአሜሪ...
26/05/2024

በ #አሜሪካ የ #ኢትዮጵያ አምባሳደር ስለሺ በቀለ (ዶ/ር) ያቀረቡት መልቀቂያ ተቀባይነት ማግኘቱ ተዘገበ

በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ተደራዳሪነታቸው ስማቸው በጉልህ የሚነሳው፤ በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው እያገለገሉ የሚገኙት ስለሺ በቀለ (ዶ/ር)፤ ከተሾሙበት የመንግሥት የሥራ ኃላፊነት ለመልቀቅ ያቀረቡት ጥያቄ ተቀባይነት ማግኘቱን ምንጮች ገለጹ።

የቀድሞው የውኃ ሀብት ሚኒስትር ስለሺ በቀለ (ዶ/ር) በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደርነት ሹመታቸው ብቻ ሳይሆን ሙሉ በሙሉ ከመንግሥት መዋቅር በመልቀቅ በግል ተቀጥረው በሙያቸው ለማገልገል ማቀዳቸውንም ሪፖርተር ጋዜጣ ምንጮቹን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

መንግሥት በእሳቸው ቦታ በአሁኑ ወቀት በሳዑዲ አረቢያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው እያገለገሉ የሚገኙት አምባሳደር ሌንጮ ባቲን ለመተካት መዘጋጀቱን ምንጮቹ ገልፀዋል። ነገር ግን፣ ሪፖርተር ይህንን መረጃ ኦፊሳላዊ በሆነ መንገድ ለማረጋገጥ አለመቻሉን ገልጿል።

የመንግሥት መዋቅርን ከመቀላቀላቸው አስቀድመው በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በውኃ ምኅንድስና ሙያቸው በግል ተቀጥረው ሲያገለግሉ የነበሩት አምባሳደር ስለሺ (ዶ/ር) ከመንግሥት የሥራ ኃላፊነት ለመልቀቅ የወሰኑት፣ ቀጣይ ጊዜያቸውን ከዚህ ቀደም ወደነበሩበት ተመድ ወይም መሰል ዓለም አቀፍ ተቋም በመመለስ በሙያቸው በማገልገል ለማሳለፍ በመፈለጋቸው እንደሆነ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ጠቁመዋል።

https://www.facebook.com/100076048904470/posts/465050956039864/

" የኢትዮጵያ መንግሥት የሶማልያው ፕሬዝዳንት እና ልዑካቸው በስብሰባው ላይ እንዳይገኙ አላደናቀፈም ፤ ወደ ኅብረቱ ቅጥር ጊቢ እንዳይገቡም አልከለከለም " - መንግሥት37ኛው የአፍሪካ ህብረት...
17/02/2024

" የኢትዮጵያ መንግሥት የሶማልያው ፕሬዝዳንት እና ልዑካቸው በስብሰባው ላይ እንዳይገኙ አላደናቀፈም ፤ ወደ ኅብረቱ ቅጥር ጊቢ እንዳይገቡም አልከለከለም " - መንግሥት

37ኛው የአፍሪካ ህብረት ጉባዔ በዛሬው እለት በአዲስ አበባ የተጀመረ ሲሆን የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ " ወደ ስብሰባው እንዳልገባ የመከልከል ሙከራ ተደርጎብኛል " የሚል ክስ አሰምተዋል።

ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሃሙድ ከስብሰባው መክፈቻ በኋላ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተው ነበር።

ፕሬዜዳንቱ በመግለጫቸው ምን አሉ ?

- በዝግ በሚደረገው ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ በምሞክርበት ጊዜ የኢትዮያ የፀጥታ ኃይሎች ካረፍኩበት ሆቴል እንዳልወጣ መንገድ ዘግተው ከልክለውኛል።

- በሌላ ፕሬዝዳንት መኪና ከሆቴል በመውጣት የስብሰባው ስፍራ ብደርስም፤ የፀጥታ አካት እንዳንገባ ክልከላ አድርገውብን ነበር።

በኋላ ላይ ግን ፕሬዝዳነቱ ወደ ስብሰባው መግባታቸው እና በስብሰባው መክፈቻ እንዲሁም የቤተሰብ ፎቶ ላይም ታይተዋል።

የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ ከሰዓት ላይ በሰጠው መግለጫው ፤ " የኢትዮጵያ መንግስት የሶማሊያ ፕሬዝዳንት እና ልኡካቸው ወደ 2024 የአፍሪካ መሪዎች ጉባዔ እንዳይገቡ ያደረገውን ሙከራ የሶማሊያ ፌደራላዊ ሪፐብሊክ መንግስ በጽኑ ያወግዛል” ብሏል።

" የኢትዮጵያ መንግስት ድርጊት የዲፕሎማሲ እና ዓለም አቀፍ ደንብን የሚጥስ ነው ፤ የአፍሪካ ኅብረትን የቆየ ባህል የሚቃረን በመሆኑም ህብረቱ ጉዳዩን በገለልተኛ ሆኖ እንደሚረምር " ሲል ጠይቋል።

የኢትዮጵያ መንግስት ምን ምላሽ ሰጠ ?

የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ፦

- የኢትዮጵያ መንግሥት ለአፍሪካ ኅብረት ስብሰባ ለመጡ ሁሉም ሀገራትና መንግስታት መሪዎች ያደረገውን የክብር አቀባበል ለሶማሊያ ፕሬዚዳንት አድርጓል።

- እንደ አስተናጋጅ ሀገር ኢትዮጵያ የሁሉንም ሀገራትና መንግስታት መሪዎችን በቆይታው ደህንነታቸውን የመጠበቅ ኃላፊነት አለበት። ነገር ግን የሶማሊያ ፕሬዝዳት ልኡካን በመንግሥት የተመደቡላቸውን የፀጥታ አካላት አንቀበልም ብለዋል።

- ከዚህ በላይ ግን የሶማሊያ ልዑክ የደህንነት አባላት የጦር መሳሪያ ታጥቀው ወደ አፍሪካ ኅብረት ለመግባት ሲሞክሩ በኅብረቱ የፀጥታ አካላት ተከልክለዋል።

- የኢትዮጵያ መንግሥት የሶማልያው ፕሬዝዳንት እና የልኡካቸውን ደህንነት ከመጠበቅ ባሻገር በስብሰባው ላይ እንዳይገኙ አላደናቀፈም ፤ ወደ ኅብረቱ ቅጥር ጊቢ እንዳይገቡም አልከለከለም።

- ኢትዮጵያ ከጎረቤቶቿ ጋር መልካም ግንኙነት ለመፍጠር ቁርጠኛ አቋም አላት።

Credit : AL AIN NEWS (Amh)

Mela Media


Address

Addis Abeba
Addis Ababa
USA

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Bukmal posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Bukmal:

Videos

Share


Other Media/News Companies in Addis Ababa

Show All