ጀማል ሀሰን Jemal Hassen

ጀማል ሀሰን Jemal Hassen Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ጀማል ሀሰን Jemal Hassen, Film/Television studio, A. A, Addis Ababa.

አመለሸጋው Joseph Bazezew እንኳን ደስ ያለህ አባቴ 😍
12/11/2022

አመለሸጋው Joseph Bazezew እንኳን ደስ ያለህ አባቴ 😍

ከማመን አትቦዝን !!በቃ ከዚህ በፊት ተጭበርብራችሁ ሊሆን ይችላል የደረሰባችሁ ጉዳት ልባችሁን ሸርፎት ሊሆንም ይችላል ተሰነጣጥቆ ባልደረቀው ልባችሁ ላይ በተደጋጋሚ የመከዳትን ፅዋ ተጎናጭታች...
11/11/2022

ከማመን አትቦዝን !!

በቃ ከዚህ በፊት ተጭበርብራችሁ ሊሆን ይችላል የደረሰባችሁ ጉዳት ልባችሁን ሸርፎት ሊሆንም ይችላል ተሰነጣጥቆ ባልደረቀው ልባችሁ ላይ በተደጋጋሚ የመከዳትን ፅዋ ተጎናጭታችሁም ይሆንም ይሆናል

ይኼን ሁሉ የበደል መከራ ተሸክሞ መጓዝ የሚቻል ይሆናል ወይ የሚለው ጉዳይ መፍትሔ ከማበጀት ይልቅ የጉዳቱ ውሽፍር በትዝታ እያስታወሱ ከፊት ላይ ደቅኖ በሚመጣው መጥፎ የቂም መንፈስ ታጅቦ የሚመጡትን ሰዎች በሙሉ እንደ በደለኛና አጭበርባሪ እየሳሉ መቀጠል ላም አለኝ በሰማይ አይነት ትግልና ራስን በቁም እየገደሉ መቅበር ነው

በማህበራዊ ኑሮ ላይ የትኛውም ዘመነኛ እራስ ከአደጋ መከላከያ ማሽኖችም ሆኑ መላ የተበጀላቸው ዘዴዎች ቋሚና እርግጠኛ የሰላምና የጤና መጠበቂያ ዜዴ ሊሆኑ አይችሉም ለምን ቢባል የእምነትህ ውሃ ልክ የሚሞላ ሰው ሰራሽ መላ ሊተካው አይችልምና '' ከልብ ማመንን '' መፈፀምና መተግበር የምድር ዋነኛ ግንብ ነውና

በትናንት ጉዳቶች ህመም እየታመሙ ዛሬን እየተብሰለሰሉ የመኖር ጉዞን መምራት የማይቻል የመሆኑ ጉዳይ ከእውነት ይልቃል ደግሞም የታመንን የቆሰለን አካል በከፍተኛ ጥራትና በላቀ ሁኔታ ፈጣሪ ሊያድንና ሊጠግን የሚችለው በሰዎች ምክኒያት በመሆኑም በእያንዳንዷ ደቂቃ ሰዎች ወደ ኑሮዓችን በድግግሞሽ ለሚመጡ ሁሉ ልብን በእምነት ጥሎ ቶሎ ከህመም ተፈውሶ በደስታና በማይደርቀው ባህር ውስጥ ስኬት መቆናዘፍ የድል ውጤት ነው

ለአማኝ ደግሞ ምርኩዙ እና ጠባቂው የእምነቱ ባለቤት ነውና።!!

ደግሞ ከማመን የተሻለ እውነትም ጤናማ ግኑኝነትም የለም።!!

እናም ከማመን አትቦዝን።!!

ጀማል ሀሰን Jemal Hassen

የሰውነት ልኩ የጨዋነት አርማ ፍቅሩ የቀለመ በሰዎች ልብ ማማ ።!!
11/11/2022

የሰውነት ልኩ የጨዋነት አርማ
ፍቅሩ የቀለመ በሰዎች ልብ ማማ ።!!

10/11/2022

የደግነት ዋርካና ባለ ንፁህ ልቡን Eliyas Eyob ን ብትወዳጁት ያልተበረዘ መልካምነትንና ሱስ የሚያሲዝ ደስ የሚል ጨዋታን የማይነትብ እና የማየሰቀጭጭ የልብ ወዳጅነትን ያተርፋሉ።

የነፃነት እና የደግነት ምርኩዙን ኤላን ተቆራኙት😍

የምርጥች ሎግ የዛሬው ሙሽራ እንኳንም ተወለድክልን ጀግናዬ😍 መልካም ልደት ኤፍዬ🎂🎂🎂
10/11/2022

የምርጥች ሎግ የዛሬው ሙሽራ እንኳንም ተወለድክልን ጀግናዬ😍

መልካም ልደት ኤፍዬ🎂🎂🎂

ሰላም  ዛሬ   ለሚሰራው እንዝርት የአባይ tv ቀረፃ ፕሮግራም ላይ መሳተፍ ለሚፈልግሰዓት 4:00-8:00 ነው ሚቆየውፍላጎት ያላችሁ መሳተፍ ትችላላችሁ  ለበለጠ መረጃ +251904103083 ...
10/11/2022

ሰላም ዛሬ ለሚሰራው እንዝርት የአባይ tv ቀረፃ ፕሮግራም ላይ መሳተፍ ለሚፈልግ
ሰዓት 4:00-8:00 ነው ሚቆየው

ፍላጎት ያላችሁ መሳተፍ ትችላላችሁ

ለበለጠ መረጃ +251904103083

Join and share
👇👇 👇👇👇👇👇👇👇👇

jemal

አመለሸጋው ኤፍሬም አቡሌ 🎂🎂 ደግነት መልኩ የአንተ አይነት እንደሆነ በእርግጠኝነት ማውራት እችላለሁ በቃ አንተን ነው የሚመስለው ልኬቱም ቢሆን ካንተ ውጪ ውሃ ልኩን የሚገኝ አይመስለኝ በቃ ...
09/11/2022

አመለሸጋው ኤፍሬም አቡሌ 🎂🎂

ደግነት መልኩ የአንተ አይነት እንደሆነ በእርግጠኝነት ማውራት እችላለሁ በቃ አንተን ነው የሚመስለው ልኬቱም ቢሆን ካንተ ውጪ ውሃ ልኩን የሚገኝ አይመስለኝ በቃ

ምክንያቱም እራስ ለሰዎች መኖር ሲባል ቢያንስ እንኳን የመደበኛውን የደስታ ደረጃ ባያሳልፉ እንኳን ለተጣበቀው አንጀታቸው ማስታገሻ ድንካይ ለቀዳደው ጀርባ መተኛ ቢጤ አቅምና ጉልበት ለከዳቸው አረጋዊያን ቤተቸው ሳይከዳቸው ቀድሞ ማከም ለዚህ ደግሞ ከጉልበት በላይ እራስ ለከፍተኛ በሽታ አጋልጦ መማገድን ካንተ ወጪ በማን አየሁ ጓዴ

ለሰዎች ደስታ ሲባል የከፈልካቸውን መሰዋትነት የሚዘነጋም አይደለም የጭንቀት ህመምህ አንዴ ደም ሲስተፋህ ሌላም ጊዜ ከመንገድ ላይ ሲጥልህ ብዙ አመታቶች አልፈዋል በጠራራ ፀሃይ ጨልሞ ከሞት አፋፍ ላይ ደራሰህ አመታቶች በህመም አልጋም ላይ ያሳለፍከውን ጊዜም መርሳት አልችልም ጀግናዬ

የቱ ጥሩ የቱ መጥፎ በማንለይበት በዛ ደቃቃ እድሜችን አሁንም እንደትዝታ እየተወረወረ የሚመጣው በጉነትህ የኔ ማስታወሻዬ ምስክር ነው አየህ በዚህም ምክንያት ነው የደግነት መልኩ አንተ ነህ የምለው አባቢ

ስለ አንተ ደጋግሜ ባወራም ሆነ ብፅፍ አይደክመኝም ነበር ነገር ግን ለአንተ የተቸረህን በጎነት በቃል እይቀናጁ መግለፅ ግን አቅም የለኝም ለበጎነትህ የሚሆንም ቃላትስ ይኖርስ ይሁን እኔጃ

ሁሌም ካንተ ጋር ስሆን ደስ ይለኛል ላንተ ሳስተው አክብሮትና ውዴታን ሰላምታዎች ፍቅርና አድናቆቶች ሲጎርፉ እኔም ካንተ እኩል እሞገሳለሁና ከስር መገኘቴ ደስታም ያላብሰኛል አባቢ

የዛሬው ሙሽራ የደግነቱ ብርሃን እንኳን ተወለድክልኝ ኤፍዬ

መልካም ልደት ደግነት 🎂🎂🎂

09/11/2022

ከማመን አትቦዝን !!

በቃ ከዚህ በፊት ተጭቀርብራችሁ ሊሆን ይችላል የደረሰባችሁ ጉዳት ልባችሁን ሸርፎት ሊሆንም ይችላል ተሰነጣጥቆ ባልደረቀው ልባችሁ ላይ በተደጋጋሚ የመከዳትን ፅዋ ተጎናጭታችሁም ይሆንም ይሆናል

ይኼን ሁሉ የበደል መከራ ተሸክሞ መጓዝ የሚቻል ይሆናል ወይ የሚለው ጉዳይ መፍትሔ ከማበጀት ይልቅ የጉዳቱ ውሽፍር በትዝታ እያስታወሱ ከፊት ላይ ደቅኖ በሚጣው መጥፎ የቂም መንፈስ ታጅቦ የሚመጡትን ሰዎች በሙሉ እንደ በደለኛና አጭበርባሪ እየሳሉ መቀጠል ላም አለኝ በሰማይ አይነት ትግልና ራስን በቁም እየገደሉ መቅበር ነው

በማህበራዊ ኑሮ ላይ የትኛውም ዘመነኛ እራስ ከአደጋ መከላከያ ማሽኖችም ሆኑ መላ የተበጀላቸው ዘዴዎች ቋሚና እርግጠኛ የሰላምና የጤና መጠበቂያ ዜዴ ሊሆኑ አይችሉም ለምን ቢባል የእምነትህ ውሃ ልክ የሚሞላ ሰው ሰራሽ መላ ሊተካው አይችልምና '' ከልብ ማመንን '' መፈፀምና መተግበር የምድር ዋነኛ ግንብ ነውና

በትናንት ጉዳቶች ህመም እየታመሙ ዛሬን እየተብሰለሰሉ የመኖር ጉዞን መምራት የማይቻል የመሆኑ ጉዳይ ከእውነት ይልቃል ደግሞም የታመንን የቆሰለን አካል በከፍተኛ ጥራትና የላቀ ሁኔታ ፈጣሪ ሊያድንና ሊጠግን የሚችለው በሰዎች ምክኒያት በመሆኑም በእያንዳንዷ ደቂቃ ሰዎች ወደ ኑሮዓችን በድግግሞሽ ለሚመጡ ሁሉ ልብን በእምነት ጥሎ ቶሎ ከህመም ተፈውሶ በደስታና በማይደርቀው ባህር ውስጥ ስኬት መቆናዘፍ የድል ውጤት ነው

ለአማኝ ደግሞ ምርኩዙ እና ጠባቂው የእምነቱ ባለቤት ነውና።!!

ደግሞ ከማመን የተሻለ እውነትም ጤናማ ግኑኝነትም የለም።!!

እናም ከማመን አትቦዝን።!!

ጀማል ሀሰን Jemal Hassen

"ወርቋማው ሰው ''  Eyob Getachew መልካም ልደት 🎂🎂
09/11/2022

"ወርቋማው ሰው ''

Eyob Getachew

መልካም ልደት 🎂🎂

ዛሬ እለተ እሮብ ከቀኑ ከ11: 00 ጀምሮ የሀገር ፍቅር ቲያትር ቤት ከፍተኛ የሆነ ደስታን  በሰዎች ልብ ላይ ብርሃን ሊያጎናፅፉ ሙሉ የማዝናናት ድግሱን ጨርሶ ዘመድ ጓደኛ የልብ ወዳጅ ሳይቀ...
09/11/2022

ዛሬ እለተ እሮብ ከቀኑ ከ11: 00 ጀምሮ የሀገር ፍቅር ቲያትር ቤት ከፍተኛ የሆነ ደስታን በሰዎች ልብ ላይ ብርሃን ሊያጎናፅፉ ሙሉ የማዝናናት ድግሱን ጨርሶ ዘመድ ጓደኛ የልብ ወዳጅ ሳይቀር በጥሪ ላይ እንዲገኙ ሲል # የሌሊት ሙሽሮች ቲያትር በላቀ ክብር ሁላችሁንም ጋብዟል።!!

08/11/2022

ውበታሟ ፍቅሬ 🥰

ስንት ጊዜ ልቁጠር መቼስ ይገባሃል
ግራዬ ነህ አንተ ቀኜን መች ገጥመሃል
ውዴታህ ብዙ ነው በቃል የቀለመ
መኖር በዛሬ እንጂ በትናንት አልቆመ

ትለኛለች ውዴ 🥰

ሁሌም እንባ ከአይኖቿ ሞልቶ
እስፍስፍ አንጀቴ ከልቧ ተሰፍቶ
ያንዘፈዝፈኛል ደስታዋ ሲጨልም
ልቤም በእንባዋ እሳት እያየሁ ሲከስም

ህመሙ ብዙ ነው ሰላም ያሳጣኛል
ምን ልሁን የት ልግባ ራሴን ያመኛል
ልክ ነች አልክድም እውነትም ያሻ:ታል
ሀገሩም በሙሉ ፍቅሬን ያማላታል

እኔ ግን ፈራለሁ 😟

ፍላጎቷም ቀላል ወዳጆቼን ማወቅ
የማፍቀሬን መጠን ጠይቆ ለማርቀቅ
ይኼ ነው ሀሳቧ ውበታሟ ፍቅሬ
ቁስሌም አገረሸ የካቻምናው ዛሬ

ምክንያቱም ??

እንኳንስ ስቃበት ልብ ያቀልጣል መልኳ
ሙትን የሚያነቃ ጨዋን የሚያንኳኳ
ሰማይን የሚያወርድ ምድርን
የሚያንሳፍፍ
ውበቷን ምን ላርገው በዛው እንዳትከንፍ

ስጋት ይገባኛል 😟

በዛውስ ባትመጣ ሞሽራኝ ከቤቴ
ምንስ እሆናለሁ ስጠፋ መብራቴ
ያችኛዋስ ቆንጆ የሰላም አርማዬ
ልትታወቅ ብላ ላትመለስ ጥላኝ
ቀረች ከጥላዬ።!!

ጀማል ሀሰን Jemal Hassen

የብቃት ማረጋገጫ የተጎናፀፉ የሙያ ረቂቆች ወግ።!!
08/11/2022

የብቃት ማረጋገጫ የተጎናፀፉ የሙያ ረቂቆች ወግ።!!

በቅርብ ቀን ከሚያሸበርቁ ፊልሞች መካከል            ህጋዊ ጋብቻ ዋነኛው መሆኑ ታውቋል።!! ሁላችሁም ተጋብዛችኋል።!!
08/11/2022

በቅርብ ቀን ከሚያሸበርቁ ፊልሞች መካከል
ህጋዊ ጋብቻ ዋነኛው መሆኑ ታውቋል።!!

ሁላችሁም ተጋብዛችኋል።!!

ድግሱ ከበር ደረሰ ።!!
06/11/2022

ድግሱ ከበር ደረሰ ።!!

ሀገር ፍቅር ቲያትር በደስታና በሳቅ ልትሞሸር የሁለት ቀናት እድሜ ብቻ ይቀራታል ።!!
05/11/2022

ሀገር ፍቅር ቲያትር በደስታና በሳቅ ልትሞሸር የሁለት ቀናት እድሜ ብቻ ይቀራታል ።!!

አዲስ ነገር ከተወዳጁ  ጋዜጠኛ አዳነ አረጋ  ጋር 😍
04/11/2022

አዲስ ነገር ከተወዳጁ ጋዜጠኛ አዳነ አረጋ ጋር 😍

04/11/2022
ለማይሰማ ምጣድ እሳት አታባክን በልቶ በሚጠፋ ዋጋህ አትመዝን።!! ጀማል ሀሰን Jemal Hassen
03/11/2022

ለማይሰማ ምጣድ እሳት አታባክን
በልቶ በሚጠፋ ዋጋህ አትመዝን።!!

ጀማል ሀሰን Jemal Hassen

መዝናናት ከያሲኖ ጋር።!!
03/11/2022

መዝናናት ከያሲኖ ጋር።!!

02/11/2022

ለክቶ መቁረጥን በራስ ልብ ልመድ
ምራጭ እንዳትሆን የሚጎተት ገመድ ።!!

ጀማል ሀሰን Jemal Hassen

መልካም ቀን።!!

አንዳንድ ቀን  ።!!
01/11/2022

አንዳንድ ቀን ።!!

ሰሜ ቡና ቡና 🎂🎂 ውሃም ቢሆን ኑሮው ነው የሚመስለው በደፈረሰ አካባቢ ያለ ውሃ ደፍራሳ መልክ ሲይዝ በጠራና ቦታ ደግሞ የጠራ የኑሮ መልክ እንዳለው የሚመሰክር  እውነት እንደሆነው ሁሉ ሰውም...
01/11/2022

ሰሜ ቡና ቡና 🎂🎂

ውሃም ቢሆን ኑሮው ነው የሚመስለው በደፈረሰ አካባቢ ያለ ውሃ ደፍራሳ መልክ ሲይዝ በጠራና ቦታ ደግሞ የጠራ የኑሮ መልክ እንዳለው የሚመሰክር እውነት እንደሆነው ሁሉ ሰውም እንደ ውሃ ከኑሮ መልክ ጋር የሚመሳስላቸው የራሳቸው የሆነ የኑሮ መስተጋብር አላቸው

የደግነት ልዕልና ከፍ ብሎ ሰማይን በቅንነት ቀስተ ደማና የሚኩልባቸውና መልካምነትና ቅን ተግባር ቅን ሃሳብ በሚሸራሸርባቸው ቦታዎችና አካባቢ የሚያዘወትር ሰው ልበ መልካምና የልብ ንፅህና ባለቤት ዋርካ ይሆናል

በዚህ በተቃራኒ ቦታ በገደፈና ሀሳበ ሸውራራ በሚበዛባቸው ቦታዎች ኑሮውን የመሰረተም የክፋትን ምንጭ እነቀዳ የሚመርዛቸውን ሰፊ ቆዶዎች እየኮተኮተ ቢውልም እንኳን በሰፈሩት ነውና እንዳሻው ይሁንለት

ውሃ ግን ደግ ነው ከሚችለው አቅም በላይ በላመሰልቸት ውስጥ ሁሌም ለምድር በረከት ሆኖ በሰዎች የመኖር ዋስትና ላይ ትልቁን ዋጋ ሲከፍል ይኖራል የሚገፋውም የሆነ የሚረግጠው ጉልበት ያለውም ሆነ አቅመ ደካማ እንደልቡ የሚፈነጭበት ቢሆን ባለ ደግ ልቡ ውሃ ከፋኝ ብሎ ሰው በህይወት የሚቆይበትን ተግባር ላይፈፅም ቀርቶ ክፋቱን ማሰብም ሳይችል ዛሬም በደግነቱ ዘመናትን በፍቅር ይሻገራል

ይኼ ውሃ የዛሬውን ባለ ልደት ሙሽራ የሆነውን #ሰሙዬ በደንብ አድርጎ ይገልፀዋል ሰሙ ብሎ ስሙን ለጠራው ሁሉ የሚከፍለው ዋጋ ለአብሮ አደጉ የልጅነት ምስሉ ከሚደርገው እኩል አይነጣጠልም ።

ጥሩነት ማነው ውሃ ቅንነትስ ማነው ውሃ መልካምነትስ ማነው ውሃ ከፍተኛ ዋጋ መክፈልስ ማንን ይመስላል ውሃን ውሃስ ማነው የቅንነት ዋርካው የአራድነት ሎጎው መስጠት የማያልቅበትና ሰው አስታዋሹ ሰመዶ ይባላል።

በእንዲህ ነው ተብሎ የሚገለፅልህ ብዙ ደግነቶችና የሰዎኛነት ልክነት ያሉህ ቢሆኑም እንኳን ደግነት ለታደለ ባለ ብዙ በረከት ሰው የሚሆን ፊደላትም ቢሆን ቋንቋ የሉትምና አንተ ማለት ሀገር ሙሉ ደግነት መሆን ግን የታወቀ ነው ጓዴ

እንኳንም ተወለድክልን ሙሽራው ክፉ ሳይነካህ በደስታ ተከበህ ስስት በማያውቀው ልብህና መስጠትን በማያቆመው እጅህ ልክ በምታውቃቸውና በሚያውቁህ ሰዎች ቁጥር ልክ ነፍ አመት ኑርልኝ ሰሙዬ።

እኔ ያንተ የልብ ወዳጅ Jemal Hassen ሁሌም ሳከብርህ እኖራለሁ አለሜ ።

መልካም ልደት ሰሙዬ 🎂🎂🎂

እንደ ማን መሆን ተፈልጋለህ ስትባል ሁሌም መሆን የፈለከውን ነገር  በመሆንህ  የዘላለም ደስታ ከልብ ላይ ብርሃን እያፈለቀ ለሰዎች ሁሉ እንዲያካፍልና የማይናወጥ ምርኩዝ ይሆን ዘንድ ፀሎት ከ...
31/10/2022

እንደ ማን መሆን ተፈልጋለህ ስትባል ሁሌም መሆን የፈለከውን ነገር በመሆንህ የዘላለም ደስታ ከልብ ላይ ብርሃን እያፈለቀ ለሰዎች ሁሉ እንዲያካፍልና የማይናወጥ ምርኩዝ ይሆን ዘንድ ፀሎት ከልብ ላይ አርፎ የመኖር ምቾት ሀይቅ አንጣሎ በፍቅር እንዲዘረጋ ቃልን በአንደበት አቀናጅቶ ይኼን ከማለት አይዘንጋ እንደ ደግ ሰው አንደ ትሁት ሰው ትህትናውን እንደ ዘመን የማይለዋወጥበት መልካምነቱ የበቃ ሰዎኛነቱ ውሃ ልኩን የጠበቀ ለሁሉም የሚሆን ለሁሉም የተፈጠረ የሰውነት ዋርካ ለሰዎች ደስታ እራሱን የሚገብርና ስስትን የማያውቅ አይነት ሰው አድርገኝ ማለትን አትዘንጋ ይላሉ በሳል ልቦች

#ፍቅረስላሴ ዩሃንስ (እሙሽ ) አንዳንድ መጠሪያ ስሞች በራሳቸው ለሰውየው በልኩ በቆንጆ ዲዛይነር ተሽቀርቅረው የተሰሩ እስኪመስሉ ድረስ አጃኢብ ይሆናሉ።

ሽቅርቅሯ ሃዋሳ ሽቅርቅሩን አመለ ሸጋውን የጥበቡ አለም አውታርና የብዙ ጥምር ሙያተኞች ባለቤትን አቅፋ በየጊዜው በሚፅፋቸው እና በሚተውንባቸው በልዩ ብቃቱ ጥንቅቅ አድርጎ በሚያዘጋጃቸው ቀርፆ በሚኩላቸው የጥበብ ተመልካችን ልብ ወገግ በሚደርጋቸው ተቆጥረው በማያልቁ ስራዎቹ እየሞሸረች ስትድረው ስትኩለው አመታቶች በዘመን እየተተኩ ዛሬም ላይ ደርሳለች።

ለሚጥር ሰው ስኬት የእጅ ጌጡ ለየዋህ ደግነት ስንቁ ነውና ይኼ ሁሉን የታደለው ረቂቁ ሰው ከብዙ የሀገራችን ፊልሞች ጀርባ ስሙን በታላቅ ችሎታና በድንቅ የአተዋወን ብቃቱ ከትናንት ዛሬ ከዛሬ ደግሞ ነገን በድንቅ ስራው እየሞረደ ማህበረሰብን በበጎ ተግባር እያነፃ ይኼው ከማይዋዥቅ ስብዕናው ጋር ዛሬ አለ ወርቅ ሰው ሁሌም በደስታ ተሞሽሮ ይኑር

ከዚህም ቀደም ከሰራቸው ብዙ ስራዎቹ ኢንስፔክተሩ የሚለው ስራው ዛሬም እንደ አዲስ ተደጋግሞ በፍቅር ይኮመኮማል አሁን ደግሞ ኢንስፔክተሩ 2 የሚለው ስራ ስርቶ ጨርሶ ለእይታ ሊያቀርብ ከሲኒማው በራፍ አካባቢ ይገኛል።

ከሁሉም በላይ ግን መታተሩና ደግነቱ የሚውቁትን ሁሉ ልብ በፍቅር ያሸፍታል።

ጀግናዬ አንተማ ደጋግመህ ስራልን።!!

22/10/2022

መማር ደጉ ማወቅ ልኩ
ለምስጋናም ቃል ማኘኩ (Tnx) ።!!

ጀማል ሀሰን Jemal Hassen

22/10/2022

ፌሮው ነው ረቂቅ ቃሉን የማያጥፍ
ከወጣበት በላይ እውነትን የሚያቅፍ።!!

ጀማል ሀሰን Jemal Hassen

ፍልቅልቋ ህፃን ከሞት አፋፍ ላይ ትገኛለች  እየሳቀች እየቦረቀች ከእኩያ ጓደኛቿ ጋር ስትሯሯጥ ባለችበት ቅፅበት ልክ ከፀሐይ ወደ ዳመና በሚቀየርበት ፍጥነት ድገተኛና አስደንጋጭ ህመም ገጠማት...
20/10/2022

ፍልቅልቋ ህፃን ከሞት አፋፍ ላይ ትገኛለች

እየሳቀች እየቦረቀች ከእኩያ ጓደኛቿ ጋር ስትሯሯጥ ባለችበት ቅፅበት ልክ ከፀሐይ ወደ ዳመና በሚቀየርበት ፍጥነት ድገተኛና አስደንጋጭ ህመም ገጠማት አንደኛው እግሯ ለመርገጥ አልችል ብሎ ወደ ህክምና ወሰዷት ከሰዓት ቡኋላ ሁሉትም እግሮቿ መስራት አቆሙ ህመሙም በከፋ ሁኔታ ወደ ወገቧ መሰራጨት ጀምሯል በተቀሩት 24 ሰዓታት ውስጥ በግምት 65 ሺ ብር የሚሸጥ መድሃኒት ተገዝቶ ካልቀረበላት የመተፈሻ አካሏን እስከመታፈን ልደርስ ትችላለች ብለዋል የህክምና ባለሙያዎች

የህፃኗን በህይወት ለማቆየት ውስን የደግ ልባም ሰዎችን እርዳታ ትሻለችና ይኸው ወደ እናንተ ደጋግ ሰዎች እጃችንን ዘርግተናል ያቅማችሁን አግዙን ።!!

የህፃኗን ቤተሰብ ለማግኘት

1000373753703 ህይረዴን ኡመር

0968706758 ስልክ የአባቷ ነው

https://t.me/+ky6W6L2aSaphZTBk    ለቲያትር አፍቃሪና ተመልካች ።!! ይኼ ተወዳጁ ከመጋረጃ ጀርባ የተሰኘው ቲያትር ዘወትር  አርብ በ12:00 ሰዓት በአለም ሲኒማ መታየት ...
19/10/2022

https://t.me/+ky6W6L2aSaphZTBk
ለቲያትር አፍቃሪና ተመልካች ።!!

ይኼ ተወዳጁ ከመጋረጃ ጀርባ የተሰኘው ቲያትር ዘወትር አርብ በ12:00 ሰዓት በአለም ሲኒማ መታየት ይጀምራል።

ሁላችሁም ተጋብዛችኋል

https://t.me/+ky6W6L2aSaphZTBk

Address

A. A
Addis Ababa

Telephone

+251903105353

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ጀማል ሀሰን Jemal Hassen posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to ጀማል ሀሰን Jemal Hassen:

Videos

Share