Christ prophecy internation church

Christ prophecy internation church Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Christ prophecy internation church, Film/Television studio, Addis Ababa.

10/12/2022
12/07/2022
21/10/2021

ይህንን አስተማሪ ፁሁፍ እድታነቡት ጋብዤቹሃለው።
ባሏን የገደለው 'መርዝ'
///////////////////////////
ከለታት አንድ ቀን አንዲት ውብ የሆነች ልጃገረድ ባገባች በ ሁለተኛው ዓመት ትዳሯ ምርር ስላላት ባሏን ለመግደል ፈለገች።
ይህች ቆንጆ ልጅት አንድ ቀን ጠዋት ወደ እናቷ ቤት ብርር ብላ በመሄድ፦ "እማዬ የባሌ ነገር አድክሞኛል የሚያደርጋቸው የማይረባ ነገሮች ሰልችተውኛል ለኔ አያስብልኝም ዞር ብሎ አያየኝም እኔንጃ ከሌላ ሴት ጋር የጀመረው ነገር አለ እርሱን ገድዬ መገላገል ፈልጋለው በሌላ በኩል ህግ ያስረኛል ብዬ እፈራለው እባክሽ እርጂን " አለቻት።
እናቷም "እሺ ውድ ልጄ እረዳሻለው ነገር ግን አንዳንድ የምታደርጊያቸው ነገሮች አሉ"። አለቻት።
ልጅቷም " አንቺ ያልሽኝን ሁሉ አደርጋለው አለች"
እናትየውም "ባልሽ ሞቶ ሬሳው ከቤትሽ እስከሚወጣ ድረስ ከዛሬ ጀምሮ የምታደርገውን 6 ነገሮች በጥንቃቄ ፈጽሚው አለች፦
1. የገደለችው እሷናት ብለው ጎረቤት እንዳይጠረጥሩሽ ከአሁን ሰዓት ጀምረሽ ከባልሽ ጋር ሰላም ፍጠሪ
2. ሁልግዜ ውበትሽን ጠብቀሽ ወጣትና ቆንጆ ሆነሽ ታይ
3. በደንብ አድርገሽ ተንከባከቢው ጥሩ ሁኚለት አበረታችው
4. ትዕግስት አድርጊ ብዙም አትቅኚ ብዙ ግዜ አዳማጭ ሁኝ በማክበር ታዘዥው
5.በእጅሽ ያለውን ገንዘብ ለእሱ ጥቅም ብቻ አድርጊው እንዲች ብለሽ ለራስሽ እንዳትጠቀሚ ገንዘብ ከከለከለሽ አትናገሪ ዝም በይ
6. ማንም ገድላዋለች ብሎ እንዳይጠረጥርሽ የጭቅጭቅና የጩኸት ድምፅ አታሰሚ ሰላምና ፍቅር ብቻ ከአፍሽ ይውጣ ... እስከ ምትገላገይው ድረስ ብቻ ነው።
እናትዮዋ፦ በድጋሚ "ሳታዛንፊ ያልኩሽ ታደርጊያለሽ?" አለቻት።
ልጅቷም " እሱ ብቻ ሞቶ ሬሳው ይውጣልኝ እንጂ አደርገዋለሁ" አለች።
እናትየዋም የሆነ ብልቃጥ እየሰጠቻት፦ " ይህንን መርዝ ያዥው ቀስ እያለ ውስጡን አመንምኖ እንዲገድለው በየቀኑ ምግቡ ውስጥ ጠብ እያደረግሽ ስጭው" አለች።
ልጅቷም ድስ እያላት ወደ ቤቷ ተመለሰች።
ከአንድ ወር ብሓላ ልጅቷ ወደ እናቷ ቤት ተመልሳ መጣች። እንዲህ አለቻት" ወይ ጉድ ሰውዬው ወሬ ሰምቶ ይሁን ወይ ቀልቡ ነግሮት? ድሮ ዞር ብሎ የማያየኝ ሰውዬ ፣ ፍቅሬ፣ማሬ ፣ወለላዬ፣ ህይወቴ፣ ንግስቴ፣ በዓለም ላይ የምታክልሽ ሴት የለችም ይለኝ ጀምሯል ብቻ እኔንጃ ጸባዩ ልውጥ አለብኝ"
እናትየውም፦ መርዙን እየሰጠሽው ነው? አለቻት
ልጅቷም አይኗ ላይ እንባ እየቀረረ ፦ አዎ ግን አሁን ጸባየ ሸጋ ጣፋጭ አፍቃሪ ባል ሆኗል እንዲሞትብኝ አልፈልግም ማርከሻ ሌላ መድሃኒት ካለ ፈልጊልኝ እባክሽ ጸጸቱ ሊገለኝ ነው።
እናትየዋ፦ ልጄ በብልቃጥ የሰጠሁሽ መርዝ አይደለም የእርድ ዱቄት ነው። ነገር ግን ቀስ በቀስ ጸባየ መጥፎውን ባልሽን የገደልሽው "መርዟ አንቺ ነሽ" ማለቴ እሱን ማፍቀር ፣ መታዘዝ፣ መንከባከብ፣ መታገስ፣ ማክበር እና ውብ ሆነሽ ስትገኚ ባልሽን መለወጥ ችለሻል። አንቺ ለሌላው ሰው ምንም ነገር ሳትሰጭ እንዴት ከሌላ ሰው ያልሰጠሽውን ትጠቢቂያለሽ? ፍቅር ማለት ሰጥቶ መቀበል ነው። ቅድሚያ ግን መስጠት ያስፈልጋል ፍቅር ከሰጠሽው ፍቅር ታገኝያለሽ ጸብና ጭቅጭቅ ይዘሽ የምጠብቂው ከሆነ ያንኑ ታገኛለሽ።ምላሽ ሳትጠብቂ ከራስሽ አስበልጠሽ በሁሉም ነገር ባልሽን አስቀድሚ ፍቅር ስጭው!!!

15/10/2021

ሃያ ምርጥ የማርቲን ሉተር አባባሎች
1. ‹‹ ሕልም አለኝ! ››
2. ‹‹ መብረር ካልቻልክ ሩጥ፡፡ መሮጥ ካልቻልክ ተራመድ፡፡ መራመድ ካልቻልክ ዝግ ብለህም ቢሆን ሂድ፡፡ ምንም ነገር ስታደርግ ወደፊት መሄድህን አታቋርጥ፡፡ ››
3. ‹‹ ትክክል የሆነውን ነገር ለማድረግ ጊዜ ሁል ጊዜ ትክክለኛው ሠዓት ነው፡፡ ››
4. ‹‹ ከፍቅር ጋር ለመጣበቅ ወስኛለሁ፡፡ ምክንያምቱም ጥላቻ ሊሸከሙት የማይችሉ ታላቅ ቀንበር ነውና፡፡ ››
5. ‹‹ በስተመጨረሻ ከጠላቶቻችን ንግግር ይልቅ የወዳጆቻችንን ዝምታ ነው የምናስታውሠው፡፡ ››
6. ‹‹ በየትኛውም አካባቢ ያለ ህገወጥነት ለዓለም ፍትህ አደጋ ነው፡፡ ››
7. ‹‹ እምነት ምንም እንኳን ሙሉው የሕይወት መሰላል ባይታይህም የመሠላሉን የመጀመሪያውን እርካብ መርገጥ ነው፡፡ ››
8. ‹‹ እውነተኛው የትምህርት ዓላማ አዋቂነት እና መልካም ባህሪን አንድ ላይ ማድረግ ነው፡፡ ››
9. ‹‹ የማያልቀውን ተስፋ አጥብቀን በመያዝ የበዛውን ውድቀታችንን በፀጋ መቀበል አለብን፡፡ ››
10. ‹‹ ብርሃን ጨለማን ያሸንፋል እንጂ ጨለማ ጨለማን አይገፍም፡፡ ጥላቻም በጥላቻ አይሸነፍም፡፡ ያን ማድረግ የሚቻለው ፍቅር ብቻ ነው፡፡ ››
11. ‹‹ በዓለም ላይ ከመሃይምነት እና ከጅልነት የበለጠ አደገኛ ነገር የለም፡፡ ››
12. ‹‹ ጠላትን ጓደኛ ማድረግ የሚችለው ሃያሉ ፍቅር ብቻ ነው፡፡ ››
13. ‹‹ ማንም ሠው ቢሆን ሕገወጥ ለሆኑ ህጎች ያለመገዛትና ያለመታዘዝ ሞራላዊ ሃላፊነት አለበት፡፡ ››
14. ‹‹ ሁላችንም አብረን ተስማምተን ለመኖር መማር አለብን፡፡ አልያ ግን ልክ እንደ ጅል እርስበራስ መጨራረስ ሊኖርብን ነው፡፡ ››
15. ‹‹ ይቅርታ ማድረግ በሆነ ጊዜ ላይ ብቻ የምናደርገው ሳይሆን ቋሚ የሆነ የሁልጊዜ አመለካከት መሆን አለበት፡፡ ››
16. ‹‹ በዓለም ላይ እንደ ፍቅር ፅኑ እና ቋሚ ሃይል ምንም የለም፡፡ ››
17. ‹‹ ታሪክ ሠሪዎች ሳንሆን በታሪክ የተሠራን የታሪክ ፍጡራን ነን፡፡ ››
18. ‹‹ ጥላቻ ጠዪውን አጥፊ ነው፡፡ ››
19. ‹‹ ነፃነት በጨቋኞች ነቃ ፈቃድ የሚገኝ ሳይሆን በጭቁኖች የሚፈለግና ሚጠየቅ ነው፡፡ ››
20. ‹‹ ክዋክብቶችን ማየት የሚቻለው በጨለማ ብቻ ነው፡፡ ››

09/09/2021

* ለደቂቃዎች ይህን ማንበብ
ለዘላለም ሕይወትህን ይለዉጣል!
በኢዩኤል ዮሐንስ ( Eyuel J Yohanne )

በርግጥ ኢየሱስ ክርስቶስ ይማልዳል ?
' የእግዚአብሔር በግ '

ነቢዩ ኢሳያስ ክርስቶስ ወደዚህ ምድር ከመምጣቱ ከሰባት መቶ ዓመት በፊት በመገለጥ ዝም ብሎ ለመታረድ እንደሚሄድ በግ አየዉ :- ' ለመታረድ እንደሚነደ ጠቦት ፥ በሸላቶቹ ፊት ዝም እንደሚል በግ ፥ እንዲሁ አፋን አልከፈተም ' ኢሳ 53 : 7 ከሰባት መቶ አመት በሗላ መጥምቁ ዮሐንስ ክርስቶስ ኢየሱስን የዓለምን ሁሉ ሐጢአት እንደተሸከመ የእግዚአብሔር በግ አየዉ ጮህም ለሰዎችም የዓለምን ሁሉ ሐጢአት የተሸከመ/ የሚያስወግድ እዉነተኛ የእግዚአብሔር በግ አለ ( ዮሐ 1 : 36 ) በሶስተኛ ደረጃ ሐዋሪያዉ ዮሐንስ ጌታ ኢየሱስን በሰማይ እንደታረደ በግ ቆሞ አየዉ :- ' በዙፈኑ እና በአራቱ እንሰሶች መካከል በሽማግሌዎችም መካከል እንደ ታረደ በግ ቆሞ አየሁ ፥ ' ራዕ 5 : 6 ሚስጥሩ ያለዉ እዚህ ጋር ነዉ ? ' የታረደ በግ ' እንዴት ይቆማል ?! በግ ሲታረድ ይወድቃል እንጂ አይቆምም ሐዋሪያዉ ዮሐንስ ጌታ ኢየሱስን እንደ ታረደ በግ በሰማይ ቆሞ ሲያየዉ የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ለዘላለም ሕያዉና የሚሰራ ( Alive and Active ) እንደሆነ በእርሱ በኩል ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ሁሉ ሊያድን እንደሚችል ነዉ ያየዉ ፤ ብዙ ሰዎች እዚህ ላይ ጥያቄ ያነሳሉ ' ኢየሱስ ክርስቶስ የነገስታት ንጉስ የጌቶች ጌታ አምላክ ሆኖ ወደ ማን ነዉ የሚማልደዉ ' ይላሉ ስለ እግዚአብሔር ( Godhead ) ስለ ኢየሱስ መለኮትነት ( his DIVINITY ) እና ሰዉነት ( his HUMANITY ) ካወቅን ለዚህ ጥያቄ መልስ እናገኛለን . ኢየሱስ ክርስቶስ የዛሬ ሁለት ሺ ዓመት ሰዉ ሆኗል ( he became a GOD - MAN forever) ከሞት ከተነሳም በሗላ የትንሳኤ አካልን ( RESURRECTED /GLORIFIED BODY ) ለብሶ ለዘላለም በሰዉነቱ የመለኮት ሙላት ተሸክሞ ይኖራል ( The fullness of DEITY lives in him BODILY FORM ) ስለዚህ ከእግዚአብሔር ጋር ያስታረቀን የሚያስታርቀን በሰዉነቱ ነዉ ፤ አንድ ጊዜ በመስቀል ላይ ደሙን ለዘላለም አፍስሶ ( once and forever ) ለዘላለም እኛን ለማዳን ሕያዉ ሆኖ ይኖራል !ይህም ብቻ አይደለም ሁል ጊዜ ( 24/7 ) በእግዚአብሔር ፊት ስለ እኛ እየታየ በድካማችን ሁሉ የሚራራልን ታላቁ ሊቀ ካህናችን ፤ ሰለ እኛ በእግዚአብሔር ፊት የሚቆም ጠበቃ (Advocate,mediator and lawyer ) ሆኖ ለዘላለም ይኖራል ! ለምን እንደ ሆነ አላዉቅም ' ማስታረቅን ' ብዙ ሰዎች ከትንሽነት ጋር ያያዙታል ነገር ግን ሰዉን ከሰዉ ፣ መሪዎችን ከመሪዎች እና ሃገርን ከሃገር ያስታረቁ ትልቅ እንጂ በምንም ሂሳብ ትንሽ ሊባሉ አይችሉም ! ኢየሱስ ክርስቶስ ሰማይን ከምድር ያስታረቀ ( Universal Reconciler ) ነዉ ስንል ' ' ለምን ክብሩን ዝቅ ታደርጋላቹ ይሉናል ? ' እዉነቱ ግን ከዚህ በጣም የተለየ ነዉ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የመዋጀት ( Redemption ) ስራ ሲሰራ የመጨረሻ ክብሩን የገለጠዉ ሰማይና ምድርን በመፍጠሩ ሳይሆን ጥልቁ ጥበቡና ሃይሉ የተገለጠዉ የሰዉ ልጆችን በመስቀል ላይበማዳኑ ነበር :: በነገራችን ላይ ኢየሱስ ከርስቶስ ብዙ ስሞች እያሉት በ ራዕይ 21 እና 22 መሰረት ለዘላለም መጠሪያ አድርጓ የመረጠዉ ስም :- ' በጉ ' ወይም ' የእግዚአብሔር በግ ' የሚለዉ ነዉ ይህም ማለት እርሱ እንደ ሕያዉ የእግዚአብሔር በግ መስዋዕት የሆነልንን የመስዋትነቱን ስራ እንዳንረሳ ለዘላለም ' የእግዚአብሔር በግ ' የሚል ስም ይይዛል ኢየሱስ ክርስቶስ ድል የነሳዉ ያሻነፈዉ ታርዶ መስዋት ሆኖ ነዉ!

9-10 መጽሐፉን ትወስድ ዘንድ ማኅተሞቹንም ትፈታ ዘንድ ይገባሃል፥ ታርደሃልና፥

ክብር ለታረደዉ መስዋት ለሆነዉ ለእግዚአብሔር በግ!
Worthy is the lamb!

19/04/2021
15/02/2021

በግሬስ ላይፍ ኮሚዩኒት ችርች
የሮሜ መጽሐፍ ተከታታይ ትምህርት
የእግዚአብሔር ቁጣ
ሮሜ 1:18-32
18፤ እውነትን በዓመፃ በሚከለክሉ ሰዎች በኃጢአተኝነታቸውና በዓመፃቸው ሁሉ ላይ የእግዚአብሔር ቍጣ ከሰማይ ይገለጣልና፤...
ዘወትር ዕሮብ ከ 11:30 - 2:00 ሰዓት
በመጋቢ አማረ ሐጎስ

07/01/2021
11/12/2020

የአብያተክርስቲያናት ካውንስል ላይ ያለው አቋም......

16/11/2020

Addis Gurmesa - Alebign Wuletash - አዲስ ጉርሜሳ - አለብኝ ውለታሽ - New Ethiopian Music 2020 Nahom Records Inc.is the ultimate next generation Ethiopian Music, CD, Pro...

31/10/2020

በአለም ዙሪያ የምትኖሩ የተወደዳችሁ ወንድሞች አና እህቶች አግዚያብሔር በውስጣችን ባስቀመጠው የዝማሬ ፀጋ ሁላችሁም በየትኛውም ቦታ ሆናችሁ ለጌታ በዜማ መቀኘት የምትችሉበትን ዝማሬ በኦሮምኛ እና በአማርኛ አንድ ዝማሬ ከወንድሜ ከዘማሪ ቢቂላ ጋር አዘጋጅተንላችኋል በሚቀጥሉት ሁለት ቀናት በዚሁ Like page እና በራሴው YouTube Channel ላይ ይለቀቃል እየሰማችሁ ተባረኩበት ለወዳጆቻችሁም Share አድርጉላቸው።ጌታ ይባርካችሁ።

19/10/2020

“ሴት ሆይ!”
**** *****
መልካም ሚስት ለመሆን ሁሉም ሴት ሊያነበዉ የሚገባ
30 የህይወት መርህ (ህግ)
ሴት ሆይ
1) በምንም ምክንያት ባልሽ ላይ ጮክ ብለሽ አትናገሪ፡፡
ምክንያቱም ባል ላይ መጮህ የመናቅ ምልክት ነዉና፡፡
(ምሳሌ 15፣1)
2) የባልሽን ድክመት ለቤተሰቦችሽም ሆነ ለጓደኞችሽ
ከቶም አትግለጪ፡፡ ምክንያቱም መልሶ ወዳንቺ ነገሩ
ይመጣልና፡፡ አንቺ የእያንዳንዳችሁ ጠባቂ ነሽ፡፡ (ኤፌ
5፣12)
3) ከባልሽ ጋር ስትነጋገሪ የተለየ የአካል እንቅስቃሴንና
ምልክትን አትጠቀሚ፡፡ ባልሽ እነዚያን እንቅስቃሴዎችሽን
እንዴት እንደሚተረጉም አታዉቂም፡፡ ኃይለኛ እና ቁጡ ሴት
ደስተኛ ቤት አይኖራትም፡፡ (ምሳሌ 15፣13)
4) ባልሽን በፍጹም ከሌሎች ወንዶች ጋር አታመሳስይዉ፡፡
የሌሎች ወንዶች ህይወት ምን እንደሆነ ከባልሽ በቀር
አታዉቂም፡፡ ባልሽን ከሌሎች ጋር በማነጻጸር በራስ
መተማመኑን ከነጠቅሽ ላንቺ ያለዉን ፍቅር ከልቡ
ያጠፋዋል፡፡
5) የባልሽን ጓደኞች ህመም አታስታሚ ምክንያቱም
ትጠያቸዋለሽና፡፡ የነሱን ህመም ሊያስታም የሚገባዉ ራሱ
ባልሽ ሊሆን ይገባል፡፡ (ምሳሌ 11፣22)
6) ባልሽ ወዶሽ እንዳገባሽ እንዳትረሺ፡፡ አንቺ ሰራተኛዉ
ወይም ሌላ አየደለሽምና የሚስትነት ኃላፊነትሽን ተወጪ
(ዘፍ 2፣24)
7) ማንንም ባልሽ ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ አትፍቀጂ፡፡
ሌሎች ያሻቸዉን ሊያደርጉ ይችላሉ ባልሽ ግን ያንቺዉ
ኃላፊነት ነዉ፡፡ (ኤፌ 5፣33) 8) ባልሽ ባዶ እጁን ወደቤት
ቢመጣ አትዉቀሺዉ ይልቁንም አረታችዉ፡፡
9) ከቶም አባካኝ አትሁኚ፡፡ የባልሽ ላብ የማያባክኑት
እጅግ ዉድ ነዉና፡፡
10) ለግብረ ስጋ ግንኙነት በፍጹም ያመመሽ በማስመሰል
ባልሽን አትከልክይዉ፡፡ ባልሽ እስከ ፈለገዉ ሁኚለት፡፡
ለባል የግብረ ስጋ ግንኙነት መሰረታዊ ነዉ፡፡ አንቺ ግን
በተደጋጋሚ ከለከልሺዉ ከሌላ ሴት ጋር እንዲወሰልት በር
ትከፍቺለታለሽ፡፡ ወንድ በፍፁም የስጋ ግንኙነትን ለረጅም
ጊዜ ተቋቁሞ መዝለቅ አይችልምና፡፡ (መኃልይ 7፣12)
11) ባልሽን ከዚህ ቀደም ከሌላ ወንድ ጋር (ከቀድሞ
ፍቅረኛሽ ጋር) ግንኙነት አድርገሽ ምታዉቂ ከሆነ ግንኙነት
ካደረግሺዉ ሰዉ ጋር የሱን የስጋ ግንኙነት በፍጹም
አታነጻጽሪ፡፡ የሄ ትዳርሽ በቀድሞ ግንኙነትሽ ከቶ
አይካካስምና፡፡ (መኃልይ 5፣9)
12)ለባልሽ በአደባባይ መልስ አትስጪዉ፡፡ እሱ
በአደባባይ ተናግሮሽ ቢሆንም እንኳን ነገሩን በልብሽ
ያዥዉ፡፡ (ምሳ 31፣23)
13) ባልሽ ላይ በልጆቻችሁ ፊት አትቆጪ ወይም
አትቋቋሚዉ፡፡ ብልህ ሴት ይህን አታደርግምና፡፡ (ኤፌ
4፣31) 14) ባልሽ በሚሰነዳዳበት ጊዜ ታሰማምሪዉ እና
ሚያስፈልገዉን ታሟይለት ዘንድ አትዘንጊ፡፡ (ምሳ 12፣4)
15) ጓደኞችሽ ለባልሽ እጅግ እንዲቀርቡት አታድርጊ፡፡
16) በመዋቢያ እና በመጣጠቢያ ክፍልሽ ከቶ አትቻኮይ፡፡
ዉበትሽን ጠብቂ፡፡ ባልሽ በሌሎች ቆነጃጅት ተከቦ ሊዉል
ስለሚችል እንዳይሰናከል ሁሌም ዉብ ሁኚ፡፡ (1ሳሙ
25፣3)
17) ወላጆችሽ ወይም ቤተሰቦችሽ ወይም ጓደኞችሽ
የህይወትሽ ወሳኝ እንዲሆኑ አትፍቀጂላቸዉ፡፡ እነሱ ስላንቺ
ትዳር ዉሳኔ እንዲሰጡ አትጠብቂያቸዉ፡፡ ማድረግ ካለብሽ
ካለማንም ጣልቃ ገብነት በራስሽ አድርጊዉ፡፡ (ሉቃ
21፣16)
18) ገንዘብን የፍቅርሽ መሰረት አታድርጊዉ፡፡ 19) ባሎች
ትኩረት የምትሰጥንና በትኩረት የምታደምጥን ሚስት
እንደሚፈልጉ በፍጹም እንዳትዘነጊ፡፡ ለሱ የሚሆን ጊዜ
በፍጹም እንዳታጪ፡፡ መልካም ንግግር የደስተኛ በቶች
መሰረት ነዉ፡፡ (ገላት 6፣9)
20) ያንቺ ስራ ከባልሽ በብዙ ነገር የተሸለ ቢሆንም እንኳን
ከቶ ከባልሽ ጋር አታነጻጽሪ፡፡ ትዳር የህበረት ስራ ነዉ፡፡
(ገላት 6፣10)
21) ባልሽ ላይ ጨቅጫቃ አትሁኚበት፡፡ ባሎች ጨቅጫቃ
ሚስትን አይፈልጉምና፡፡ (ኤፌ 4፣29)
22) ሰነፍ ሚስት ለምንም ነገር ግድ የላትም፡፡ ሌላዉ
ቢቀር ለሰዉነቷ መታጠቢያ እንደሚያስፈልጋት እንኳን
አታዉቅም፡፡ ሰነፍ ሚስት አትሁኚ፡፡ (ምሳ 20፣13) 23)
ባልሽ በጥሩ ሞያ የተሰራ ምግብ የሚወድ ስለሆነ በጥሩ
ሞያ ግብ ስሪለት፡፡ ባል በምግብ ቀልድ አያዉቅም፡፡
(ምሳ31፣14)
24) ባልሽን በጣም አትቆጣጠሪዉ፡፡ ይልቁንም
እያንዳንዷን ቅጽበት ተዝናኑበት፡፡ ገቢያችሁን
ተጠቀሙበት፡፡ (ሉቃ 11፣3)
25) ባልሽ ከድካም ሲመጣ ሁሌም ቀዝቃዛ ዉሃ ስጪዉ፡፡
መልካም ባህሪሽ እና ትህትናሽ ዉበትሽ ነዉና፡፡ (ምሳ 31፣
11)
26) ስለትዳር መልካም አመለካከት ከሌላት ሴት ጋር
በፍጹም ህብረት አትፍጠሪ (ምሳ 22.14)
27) አንቺ ዋጋ የሰጠሸዉን ያክል ትዳርሽ ላንቺ ዋጋ
አለዉና ግዴለሽነትን አስወግጂ፡፡ (እብ 13፣14)
28) የማህጸንሽ ፍሬዎች የፈጣሪሽ ስጦታዎችሽ ናችዉና
ዉደጂያቸዉ፣ ተንከባበኪያቸዉ አስተምሪያቸዉም፡፡ (ምሳ
22፣6)
29) ቤትሽን ለማስተዳደር ሁሌም አታረጂምና መቼም
ቢሆን ቢሆን ለቤተሰቦችሽ ያለሽ እንክብካቤ አይቀንስ፡፡
(ምሳ 31፣28)
30) የምትጾም የምትጸልይ ሚስት ሁሌም ጠንካራ ሚስት
ናትና ሁሌም ስለ ባልሽና እና ስለ ቤተሰቦችሽ ጸልይ፡፡
(1ተሰ 5፣17)

14/10/2020

• Stay blessed and stay tuned for more videos • • visit Apostle Tamrat’s website at *www.tamratt.org* for prayer request to buy books for daily devotions and...

07/09/2020
26/06/2020

ሰለዶክተር አብይ መልክት

ኢሳይያስ 45¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¹ እግዚአብሔር ለቀባሁት፥ አሕዛብንም በፊቱ አስገዛ ዘንድ የነገሥታትንም ወገብ እፈታ ዘንድ፥ በሮቹም እንዳይዘጉ መዝጊያዎቹን በፊቱ እከፍት ዘንድ፥ ቀኝ እጁን ለያ...
16/06/2020

ኢሳይያስ 45
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ እግዚአብሔር ለቀባሁት፥ አሕዛብንም በፊቱ አስገዛ ዘንድ የነገሥታትንም ወገብ እፈታ ዘንድ፥ በሮቹም እንዳይዘጉ መዝጊያዎቹን በፊቱ እከፍት ዘንድ፥ ቀኝ እጁን ለያዝሁት ለዳንኤል እንዲህ ይላል፦
² በፊትህ እሄዳለሁ ተራሮችንም ትክክል አደርጋለሁ፥ የናሱንም ደጆች እሰብራለሁ የብረቱንም መወርወሪያዎች እቈርጣለሁ፤
³ በስምህም የምጠራህ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እኔ እንደ ሆንሁ ታውቅ ዘንድ በጨለማ የነበረችውን መዝገብ በስውርም የተደበቀችውን ሀብት እሰጥሃለሁ።

የአለም ሰጋት የሆነው ኮሮና ባይርሰ በአለም ይህን ቁጥር አሰመዘገበ ።
11/06/2020

የአለም ሰጋት የሆነው ኮሮና ባይርሰ በአለም ይህን ቁጥር አሰመዘገበ ።

የኢትዮጵያ ህክምና ባለሙያዎች በኮሮና ምክንያት ማትኤሪያል ይማላልን የሰው ህይውት ለማዳን የራሳችንን አናጣም በሜል መሪ ቃል ሰለማዊ ሰልፍ ውጡ ውላይታ ዞን
06/06/2020

የኢትዮጵያ ህክምና ባለሙያዎች በኮሮና ምክንያት ማትኤሪያል ይማላልን የሰው ህይውት ለማዳን የራሳችንን አናጣም በሜል መሪ ቃል ሰለማዊ ሰልፍ ውጡ ውላይታ ዞን

“ቃል ኪዳኔንም ከአንተ ጋር አቆማለሁ፤ ወደ መርከብም አንተ ልጆችህንና ሚስትህን የልጆችህንም ሚስቶች ይዘህ ትገባለህ።”  — ዘፍጥረት 6፥18
02/06/2020

“ቃል ኪዳኔንም ከአንተ ጋር አቆማለሁ፤ ወደ መርከብም አንተ ልጆችህንና ሚስትህን የልጆችህንም ሚስቶች ይዘህ ትገባለህ።”
— ዘፍጥረት 6፥18

የ103አመታ አዛውንት ከኮሮና ባይርሰ ማገገማን የአለም ጤና ሜኒሰተር አሰታውቀ
30/05/2020

የ103አመታ አዛውንት ከኮሮና ባይርሰ ማገገማን የአለም ጤና ሜኒሰተር አሰታውቀ

Jennie Stejna fought the virus for about three weeks.

በአድሰ አበባ በኮሮና የተያዙት የክፍለከተማ ብዛት ።
29/05/2020

በአድሰ አበባ በኮሮና የተያዙት የክፍለከተማ ብዛት ።

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Christ prophecy internation church posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Share