ስለ ኦቲዝም

ስለ ኦቲዝም Giving an information about otisim and otstic children as well as its treatment

እርስዎ የሚወልዱትን ልጅ ማን አሉት?1 ሩሐማ፦ምሕረት ማለት ነው።2 ዮዳሔ፦እግዚአብሔር ያውቃል ማለት ነው።3 ቴዎፍሎስ፦የእግዚአብሔር ወዳጅ ማለት ነው።4 ኑኃሚን፦ደስታየ ማለት ነው።5 ናትናኤ...
15/06/2023

እርስዎ የሚወልዱትን ልጅ ማን አሉት?
1 ሩሐማ፦ምሕረት ማለት ነው።
2 ዮዳሔ፦እግዚአብሔር ያውቃል ማለት ነው።
3 ቴዎፍሎስ፦የእግዚአብሔር ወዳጅ ማለት ነው።
4 ኑኃሚን፦ደስታየ ማለት ነው።
5 ናትናኤል፦የእግዚአብሔር ስጦታ ማለት ነው።
6 አዛሄል፦እግዚአብሔር ያያል ማለት ነው።
7 ኢዮስያስ፦እግዚአብሔር ይደግፋል ማለይ ነው
8 ኢዩኤል፦እግዚአብሔር አምላክ ነው ማለት ነው።
9 በርናባስ፦የመጽናናት ልጅ ማለት ነው።
10 ሶፎንያስ፦እግዚአብሔር ሰውሯል/ጠብቋል ማለት ነው።
11 ሕዝቅኤል፦እግዚአብሔር ብርታትን ይሰጣል ማለት ነው።
12 ኬልቅያስ፦እድል ፈንታየ እግዚአብሔር ማለት ነው
13 ሳሙኤል፦እግዚአብሔር ሰማኝ ማለት ነው።
14 ሚኪያስ፦ እንደ እግዚአብሔር ያለ ማን ነው! ማለት ነው።
15 ሆሴዕ፦እግዚአብሔር ያድናል ማለት ነው።
16 ሔዋን፦የሕያዋን ሁሉ እናት ማለት ነው።
17 ሕዝቅያስ፦እግዚአብሔር ኃይሌ ነው ማለት ነው።
18 መልከጼዴቅ፦የሰላም ንጉሥ ማለት ነው።
19 ሚልኪያስ፦መልእክተኛየ ማለት ነው።
20 ሣራ፦ልዕልት ማለት ነው።
21 ስምዖን፦ሰማ ማለት ነው።
22 ብንያም፦የቀኝ እጄ ልጅ ማለት ነው።
23 ናሆም፦መጽናናት ማለት ነው።
24 ናታን፦ እግዚአብሔር ሰጥቷል ማለት ነው።
25 አልዓዛር፦እግዚአብሔር ረድቷል ማለት ነው።
26 አስቴር፦ኮከብ ማለት ነው፣
27 አቤሜሌክ፦የንጉሥ አገልጋይ ማለት ነው።
28 አቤሴሎም፦አባቴ ሰላም ነው ማለት ነው።
29 አብድዩ፦የእግዚአብሔር አገልጋይ ማለት ነው።
30 አብራም፦ታላቅ አባት ማለት ነው።
31 አብርሃም፦የብዙዎች አባት ማለት ነው
32 አኪያ፦እግዚአብሔር ወንድሜ ነው ማለት ነው።
33 አክዐብ፦የአባት ወንድም ማለት ነው።
34 ባሮክ፦ቡሩክ ማለት ነው።
35 አዳም፦መልካሙ ማለት ነው።
36 ኢሳይያስ፦ እግዚአብሔር ደኅንነት ነው ማለት ነው።
37 ባርቅ፦መብረቅ ማለት ነው።
38 ኢያሱ፦እግዚአብሔር አዳኝ ነው ማለት ነው።
39 ኢዮሳፍጥ፦እግዚአብሔር ፈርዷል ማለት ነው።
40 ኢዮራም፦እግዚአብሔር ከፍ ከፍ አለ ማለት ነው።
41 ኢዮርብዓም፦ሕዝቡ እየበዛ ይሄዳል ማለት ነው።
42 ቤተልሔም፦የእንጀራ ቤት ማለት ነው።
43 ኢዮአስ፦እግዚአብሔር ሰጥቷል ማለት ነው።
44 ኢዮአቄም፦እግዚአብሔር አቆመ ማለት ነው።
45 ኢዮአብ፦እግዚአብሔር አባት ነው ማለት ነው።
46 ኢዮአታም፦እግዚአብሔር ፍጹም ነው ማለት ነው።
47 ኢዮአካዝ፦እግዚአብሔር ይዟል ማለት ነው።
48 ኤልሳዕ፦እግዚአብሔር ደኅንነት ነው ማለት ነው።
49 ኤልያስ፦እግዚአብሔር አምላክ ነው ማለት ነው።
50 ኤልያቄም፦እግዚአብሔር ያስነሳል ማለት ነው።
51 ኤዶም፦ቀይ ማለት ነው
52 እስራኤል፦ከእግዚአብሔር ጋር ይታገላል ያሸንፍማል ማለት ነው።
53 ኤልሳቤጥ፦እግዚአብሔር መሐላየ ነው ማለት ነው።
54 ኤልሻዳይ፦ሁሉን ቻይ አምላክ ማለት ነው።
55 ሀሌሉያ፦እግዚአብሔርን አመስግኑ ማለት ነው።
56 ሰሎሞን፦ሰላማዊ ማለት ነው።
57 ኬብሮን፦ኅብረት ማለት ነው
58 አዛርያስ፦እግዚአብሔር ረድቷል ማለት ነው።
59 ኤደን፦ደስታ ማለት ነው።
60 ዖዝያን፦እግዚአብሔር ኃይሌ ነው ማለት ነው።
61 ዘካርያስ፦እግዚአብሔር ያስታውሳል ማለት ነው።
62 ይሳኮር፦ ዋጋዬ ማለት ነው
63 ይዲድያ፦በእግዚአብሔር የተወደደ ማለት ነው።
64 ዮሐናን፦እግዚአብሔር ጸጋ ሰጪ ነው ማለት ነው።
65 ዮሐንስ፦እግዚአብሔር ጸጋ ነው ማለት ነው።
66 ዮሴፍ፦ይጨምር ማለት ነው።
67 ዮናስ፦ርግብ ማለት ነው።
68 ዮናታን፦እግዚአብሔር ሰጥቷል ማለት ነው።
69 ዮአኪን፦እግዚአብሔር ያቆማል ማለት ነው።
70 ዮካብድ፦እግዚአብሔር ክብር ነው ማለት ነው።
71 ምናሴ፦ማስረሻ ማለት ነው።
72 ዮፍታሔ፦እግዚአ

13/06/2023
ለተሻለ መረጃ ፎቶው ላይ ያለውን የፌስቡክ አድራሻ በተለይም የሴንተሩን መስራች እራሄል አባይነህን ማግኘት ይችላሉ። የዚህ ፔጅ አስተዳዳሪ በስራ ቦታ ምክንያት ቦታው ላይ ባይገኝም ያንድ ቲሸር...
27/03/2023

ለተሻለ መረጃ ፎቶው ላይ ያለውን የፌስቡክ አድራሻ በተለይም የሴንተሩን መስራች እራሄል አባይነህን ማግኘት ይችላሉ። የዚህ ፔጅ አስተዳዳሪ በስራ ቦታ ምክንያት ቦታው ላይ ባይገኝም ያንድ ቲሸርት ዋጋ በሴንተሩ የገቢ አካውንት ገቢ ለማድረግ ወስኗል። እናንተም እቦታው ባትገኙም ያንድ ቲሸርት ዋጋ ላንድ ሰው ተቀላቀሉ ይህ የኔ ሀሳብ ነው። ለሌሎች ይደርስ ዘንድ አጋሩ።

💙💙💙መጋቢት 24 ቴዎድሮስ አደባባይ እንገናኝ ዓለም አቀፍ የኦቲዝምን ቀን አብረን  እናክብር ለኦቲዝም ልጆ ድምፅ እንሁን ቲሸርቱን በ400 ብር በመግዛት አብራችሁን ቁሙ💙💙💙ከነህምያ ኦቲዝም ...
27/03/2023

💙💙💙መጋቢት 24 ቴዎድሮስ አደባባይ እንገናኝ ዓለም አቀፍ የኦቲዝምን ቀን አብረን እናክብር ለኦቲዝም ልጆ ድምፅ እንሁን ቲሸርቱን በ400 ብር በመግዛት አብራችሁን ቁሙ💙💙💙
ከነህምያ ኦቲዝም ማዕከል ነው።

የርሰዎስ ልጅ ምን እንዴተሰጠው ሊያውቁ ይችላሉ???እንግዳውስ እንድህም አለ። ይከተሉን
09/03/2023

የርሰዎስ ልጅ ምን እንዴተሰጠው ሊያውቁ ይችላሉ???
እንግዳውስ እንድህም አለ። ይከተሉን

ኦቲዝዝዠም ምንድነው? በጆን ዘለቀ👉 ኦቲዝም (Autism)  የቃሉ መሰረት Autos ከሚለው የግሪክ ቃል ሲሆን ትርጉሙም ራስ (Self)   ሲሆን፤ ይህ ችግር ያለባቸው ልጆች ወይም አዋቂዎች ...
09/03/2023

ኦቲዝዝዠም ምንድነው? በጆን ዘለቀ
👉 ኦቲዝም (Autism) የቃሉ መሰረት Autos ከሚለው የግሪክ ቃል ሲሆን ትርጉሙም ራስ (Self) ሲሆን፤ ይህ ችግር ያለባቸው ልጆች ወይም አዋቂዎች ራሳቸውን ከሌላው ማህበረሰብ በማግለል የራሳቸውን አለም እንደሚፈጥሩ ለማመልከት የተወሰደ ቃል ነው፡፡
ኦቲዝም ቋሚ የሆነ የማህበራዊ ተግባቦትና ግንኙነት ችግር ሲሆን፤ ዐዕምሮ በሚፈለገው ደረጃ በተለያዩ ለመኖር በሚያስፈልጉ ክህሎቶች ማሳደግ እና መበልፀግ ሳይችል ሲቀር ማለት ነው፡፡ ኦቲዝም ባብዛኛው ከ2 ዓመት የሚጀምር ወይም የሚታይ ሲሆን ከሴቶች ይልቅ ወንዶች ላይ በብዛት ይስተዋላል፡፡
በእርግጠኝነት የኦቲዝምን በሽታ መነሻነት መናገር ባይቻልም አንዳንድ ጥናጦች እንዳመላከቱት ግን ልጆች በሚረገዙበት ጊዜ የወላጆች ዕድሜ መግፋት ፣ ከበራሂ ጋር የተያያዙ ችግሮች (genetic problems)፣ በማህጸን ውስጥ ፅንሱ አስፈላጊውን የአዕምሮ እድገት ደረጃ አለመጨረስ በተጨማሪም በእርግዝና ወቅት የሚያጋጥሙ አካባቢያዊ ምክንያቶች ማለትም መርዛማ አየር፣ ውኃ፣ ምግብ ይጠቀሳሉ እንዲሁም በእርግዝና ጊዜ የሚወሰዱ አደንዛዥ ዕፆችም ይነሳሉ፡፡
👉 የኦቲዝም ምልክትን በተመለከተ የተለያዩ ነገሮች በተለያየ ደረጃ የተጠቀሱ ቢሆንም በዋናነት ከተነሱት መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል የተስተጓጎለ ማህበራዊ ግንኙነት፣ በግንኙነት ጊዜ የዓይን ለዓይን መተያየትን ባብዛኛው አያደርጉም በአንጻሩ የተናጋሪውን አፍ ነው የሚያዩት፣ ቋንቋን ለማዳበር ረዘም ያለ ጊዜ ይፍጅባቸዋል፣ የሚሰሙትን ቃላት እና አረፍተ ነገሮች ይደጋግማሉ፣ ከተመሳሳይ ዕድሜ ካላቸው ልጆች ጋር ግንኙነት የመመስረት ችግር ይስተዋላል፣ ውስን የሆኑ የሰውነት እንቅስቃሴዎች፣ ሌሎች ልጆችን የሚያጓጓ እና የሚያስደስት ነገር እነሱን አያስደስታቸውም ወይም አያጓጓቸውም፣ ተደጋጋሚ የሆኑ ባሕርያትን ያሳያሉ በዚህም ራሳቸውን ሊጎዱ ይችላሉ ፣ ነገሮች ከተልምዷዊው ሁኔታ ወጣ ሲሉ አይወዱም፣ ለተወሰኑ ድምጾች እና ሽታዎች እጅግ በጣም ስሜታዊ እና ያልተለመደ ምላሽ ሊኖራቸው ይችላል፡፡ በዚህም የአዕምሮ ዕድገት ውስንነት የሚያጠቃቸው ሰዎች የማህበራዊ ግንኙነታቸው እጅግ ዝቅተኛ ነው በተጨማሪም ለተወሰነ ነገር ብቻ ከፍተኛ ትኩረት እና ዝንባሌ ያሳያሉ፡፡እነዚህንም ምልክቶች ለማየት ወላጆች ቀዳሚዎች ናቸው፡፡
👉 ኦቲዝምን በህክምና ለማዳን ይሄ ነው የሚባል የህክምና መፍትሄ ባይኖረውም፡፡ ሆኖም ግን ልጆችን ምልክቶቹ በታዩባቸው ቀድም ያሉ ጊዜያቶች ባህሪያዊ፣ ስነ-ልቡናዊ እና ተግባቦታዊ ምክክሮችና እና ፕሮግራሞች የልጆቹ የማህበራዊ ግንኙነትን ክህሎት በጥቂቱ እንዲያገኙ ይረዳቸዋል፡፡ ሌላው በኦቲስቲክ ልጆች ላይ ብቻ ያተኮረ ትምህርት ቤት ውስጥ ልጆቹን ማስተማር የዐዕምሮ ብቃታቸውን በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምረዋል በዚህም የወላጆች ከፍተኛ እና ንቁ ተሳትፎ ወሳኝነት አለው፡፡ ለኦቲዝም በህክምና የሚታዘዙ መድኃኒቶች አሉ ሆኖም ግን በሽታውን ሙሉ ለሙሉ የማጥፋት ኃይል የላቸውም ስለዚህም ጊዜያዊ መፍትሄ እንጂ ዘለቄታዊ አይደሉም፡፡
👉 እርግጥ ነው ኦቲዝም በአንድ ልጅ ብቻ ላይ ቢያጋጥም እንኳን መላው ቤተሰብ ላይ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተፅዕኖ የሚያሳድር ችግር ነው ስለዚህ ልጅዎ የዚህ በሽታ ተጠቂ መሆኑ/ኗ በህክምና ከተረጋገጠ በኋላ በቅድሚ ማድረግ የሚኖርብን ችግሩን መቀበል ነው፡፡ በዚህም ልጆችን ጓዳ ውስጥ ደብቆ ከማስቀረት ይልቅ እርዳታ የሚያገኙበትን ሁኔታዎች ማመቻቸት የልጆቹን ሁለንተናዊ የሆነ ዐዕሮኣዊና አካላዊ እድገትን ያፋጥናል፡፡ቀጥሎ ቤት ውስጥ አቅም በፈቀደ መጠን ሁኔታዎችን ማሙዋላት ይኖርብናል ለምሳሌ መጫወቻዎች፣ ቤትን ለልጆች ምቹ ማድረግን እና የመሳሰሉትን ሌላው ትምህርት ቤት በሚገቡበት ጊዜ ከመምህራኖቻቸው ጋር የቅርብ ግንኙነት በመመስረት የየዕለት ልዩነታቸውን እና እድገታቸውን መከታተል ያስፈልጋል፡፡ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ከሆነ ኦቲዝምን ስር ሳይሰድ አውቆ አስፈላጊውን ክትትል ማድረግ ልጆቹ ላይ አስደናቂ የሆነ ለውጥ እንዲመጣ አድርጓል፡፡

24/02/2023

ስለ ኦቲዝም ልዩ መረጃ ያላችሁ እና ኦንላይን ሰፖርት ማድረግ የምትሹ ኢንቦክስ አድርጉልን።
ለትብብራችሁ አክብሮታችን ላቅ ያለ ነው

13/11/2022

ሰላም የፔጃችን ተከታዬች ፔጃችን ላይ ባሉት አድራሻዎች በጎ ፈቃደኛ አማካሪ ባለሙያዎችን ብናገኝ ደስ ይለናል። ምክንያቱም ቤት ውስጥ ሁነው ኦን ላይን እገዛ የሚፈልጉ ሰዎች ስላሉ ነው።
ለዚህ በጎ ምግባራችሁ ፈጣሪ መልካሙን ነገር ይፅፍላችኋል
መልካም ቀን ይሁንላችሁ

24/08/2022

ጠቃሚ ምክር ለ ወላጆች
ቤት ሲቀዩ ልጆችዎን ለነዚህ ተግባረት ትኩረተ ሰጥተው ያሰሩአቸው
የ እጅ እንቅስቃሴዎችን ማሰራት፡-
የሸሚዝ ቁልፎችን መፍታት(የተለያየ መጠን ያለውን በልብሶች ላይ የሚገኙ ቁልፎች መቆለፍ እና መፍታትእን ዲችሉ ማድረግ)
የጫማ ክሮችን በቀዳዳው ውስጥ ማስገባት እና ማውጣት( ይህነ ተግባር ሲያከናውኑ ጫማውን ማስር አይጠበቅባቸውም ነግር ግን ይን ማከናወን የሚችሉ ከሆነ በተጨማሪ ነት ጫማ ማሰር ማስተማር እንችላለን )
ወረቀጦችን በመቀስ(በእጅ ) መቆራረጥ( ለልጆቻችን የተለያ ወረቀጦችን በመስጠት ከተቻለ በመቀስ ካለሆነም በእጃቸው እነዲቆራርጡበማድረግ ማጠበቅያ ኮላ፣ግሉ ወይም ልላ ውረቀጡ ለመለጠፍ የሚረዳ ነግር በመጠቀም የተቆራጡ ወረቀጦችን ሌላ ወረቀት ላይ ወይም ካርቶን ላይ እንዲያጣብቁት ማስተማር) ይህን ተግባር ሲያከናውኑ ስራቸው ግዴታ ቅርጽ ሊኖረው አያስፈደልግም ከተቻለ ግን ስዕል ስለን በስዕሉ ላይ ቢለጣጥፉት የተሻለ ሊሆን ይችላል፡፡
የትዕዛዛትን ቃላትን መረዳት
የተለያዩ ትዛዛትን ዝናዘው ከማዘዘቻን በፊት ስሙን /ሟን በመጥራት ምላሽ አንድዲሰጠን ወይም እንድትሰጠን ማስቻል( ምላሹ በመምጣጥ፣ዞሮ በማየት ወይም አቤት በሚል ምላሽ ሊሆን ይችላል)
ማስታወሻ ፡- ስንጠራቸው በምክንያተው ቢሆን ስራችን ውጤታማ ይሆናል ችሏል ወይም ማቻል አለበት ብለን ያለምክንያት መደጋገም ማስልቸት እና ከመመማር ይልቅ ክህሎቱን እነዳይለምዱት የማድረግ እድሉ ሰፊ ነው ፡፡
ባለ አንድ ቃላት ትዛዛትን ማዘዝ /ማስተመር (ባለ አንድ ሂደት ትዕዛዛትን መከተል) በዚህ ጊዜ የምናዛቸው ትዕዛዛ የተወሰነ እና የተገደበ መሆን ይኖርበታል የትዕዛዝ ቃላቱ ባለ አነድ መሆን ይጠበቅባቸዋል ምሳሌ፡- ና ፣ ነይ፣ቁጭ በይ፣ቁጭበል፣ ስጠኝ፣ሰሃን ፣ሹካ ወዘተ ፡፡
የሰውነት ክፈሎችን መለየት ( ስንጠራለት የጠራነውን ሰውነት ክፈሎች በመንካት እንዲያሳየን ለምሳሌ ፡ አፍንጫ ፣ጆሮ ፣ዐይን ይህንን ማከናወን የሚችል ከሆነ ተግባራታቸውን መየቅ በምን ታሸታለክ ፣አይን ለምን ይጠቅማል ለማየት ቃላት መድገም ከቻለ በቃሉ ካቻለ ውረቀት ላይ ጽፈን እንዲያሣየን ማስተማር )

የማዛመድ ክህሎት
ከለሮችን ማዛመድ ( ተማሪው የተለያዩ ቁሳቁሶቹን በመጠቀም ከለሮች ተመሳሳያቸውን ፈልጎ እንዲያሥቀምጥ፣እነዲሰጠን የጠራነውን ቀለም እነደሰጠን ማድረግ ይህን ስናደርግ ቤት ውስጥ ምናገኛቸውን ቁሳቁሶች መጠቀም እንችላለን ለምሳሌ ቀለም ያለቸው ቲሸርት፣ካሲ፣ሰሀን)
ዕቃዎችን ከ ተመሳሰይ ዕቃወ ች ጋር ማዛመድ( በተለያየ ዕርቀት ላይ ዕቀዎችን አስቀምጠን እንዲያዛምድ/እንድታዛምድ ማዘዝ ዕቃዎቸሁ፡፡ የምንጠቀማቸወች ቁሳቁሶች በየዕለት እንቅስቃሲአቸው ውስጥ ሊጠቀሙባቸው የሚችሉ ቢሆኑ ይመረጣል ይህም በቀላ ሌሎች ክህሎቶችን ለማስተማር ይረዳናል፡፡
ነገሮችን በምድባቸው መለየት መቻል( የህን ተግባር ስናስተምር የተለያ ዕቃዎችነ ተጠቅመን እነዲሰጡን፣ እንዲያዛምዱ ወይም እንዲለዩ ማለማድ) ምሳሌ ፡ የሚለበሱ ነገሮች፣ ለምግብ መበውያነት የሚጠቅም ወዘተ፡፡
ተግባራትን ማስመሰል መቻል
የእጅ ፣የአፍ እና የእግር እንቅስቃሴዎችን በተለያየ መለኩ ማስተማር
ፊት ለፊት ለፊለፊት በተቀምጠን እኛ የምናደረገውን ተግባር ደግመው እንዲያደረጉ አንዲህ አድረግ በማለት ተግባሩን ማሳየት ምሳሌ፡ ማጨብጨብ ፣ምላስ ማውጣት፣አፍንጫን መንካት

እራስን የማገዝ ክሎት
ይህ ክህሎት እያንዳንዱ ልጅ በዚህ ወቅትም ሆነ ወደፊት እራሳቸውን ችለው የለማንም ድጋፍ ማከናውን እነዲችሉ እና በተለይ ልሎች ሰዎች ሊረዱአቸው በማይችሉበት ጊዜ እርሳቸውን ችለው

05/05/2022

በመጀመሪያ ለተወደዳችሁ የፔጃችን ቤተሰቦች በተለያዩ ምክንያቶች ዘግይተንም ቢሆን ለክርስቲያኖች ለብርሀነ ትንሳኤው ሙስሊም ቤተሰቦቻችነንም ለ1443 የኢድ አልፈጥር በአል አደረሳችሁ አደረሰን እያልን መጭውን ጊዜ አብረን በመልካም ጉዞ እንራመዳለን፡፡
መልካም ጊዜ ውድ ቤተሰቦቻችን!!!
ችግሮቻችን የሚፈቱበት ሸክሞቻችነም የሚቀሉበት ይሆንልን ዘንድ ምኞታችን ነው፡፡

12/04/2022
Otism is not disability but different ability!!!ለፎቶ ግብአቱ ሜሪን እናመሰግናለን፡፡ ነህምያዎች በርቱልኝ፡፡ ዛሬ አለም አቀፍ የኦቲዝም ቀን ነው፡፡
03/04/2022

Otism is not disability but different ability!!!
ለፎቶ ግብአቱ ሜሪን እናመሰግናለን፡፡ ነህምያዎች በርቱልኝ፡፡ ዛሬ አለም አቀፍ የኦቲዝም ቀን ነው፡፡

NEHEMIAH WE PROUD ON YOU, this center was formed by the most visionary women  Rahel Abayneh.We have to stand with it. Al...
02/04/2022

NEHEMIAH WE PROUD ON YOU, this center was formed by the most visionary women Rahel Abayneh.
We have to stand with it. All we are a future parent not only today. The admin say that be part of it! Good day for Us!

30/03/2022

We stand For US!!!

26/03/2022
እንዴት ናችሁ ቤተሰቦቻችን
26/03/2022

እንዴት ናችሁ ቤተሰቦቻችን

25/03/2022

ውድ ቤተሰቦቻችን ፔጃችን አሁን ባለበት ደረጃ ሌሎችንም መርዳት ይችል ዘንድ እንዴጀመራችሁ ሸር እና ላይክ አትዘንጉ፡፡ እንዴጀመርነው በኢንቦክስ እና በውስጥ መስመር እንወያይ፡፡ በተለይ ባለሙያዎች ያላችሁን ሙያዊ እገዛ ታደርጉ ዘንድ ፍላጎታችን ነው፡፡ ሶሻል አውዬርነስ በፌስቡክ ገፃችን እንፍጠር፡፡

20/03/2022
15/03/2022

ለቅን አሳቢዎች ብቻ
ሀሳቡ ይህን ፔጅ የተከታይ ብዛት በመጨመረ መፍትሔ የሚያመነጩ ባለሙያዎችን ማነቃቃት መቻል እና የፔጁን እሮል ከፍ በማድረግ በዝቅተኛ ደረጃ ላይ እዬኖሩ ኦትስቲክ ህፃናቶችን የሚንከባከቡ እናቶችን ሸክም በቻልነው መጠን ቀለል ማድረግ መቻል እና ማገዝ የሚል ነው፡፡
ቻሌንጁን በሸር እና በላይክ እንጀምር፡፡ መልካም ሀሳብ ያላችሁ ወገኖቻችን ፔጃችን ላይ ባለው መስመር አልያም [email protected] መገናኘት ይቻላል፡፡
መልካምነት የህይወት ዘመን ስንቅ ነው፡፡ ለቅንነታችሁ እናመሰግናለን፡፡

15/03/2022

የኦቲዝም ግንዛቤ ማስጨበጫ የእግር ጉዞ እና ሃይኪንግ ፕሮገራም መጋቢት 25/ 2014 ከ አዲሱ ገበያ አደባባይ እስከ ጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል የእግር ጉዞ እንዲሁም በጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል ተራራ የመውጣት ፐሮግራም ከጠዋቱ 12:30 ጀምሮ ። ቲ ሸርት በመግዛት ከኦቲዝም ጋር የሚኖሩ ልጆችን በመደገፍ ይዝናኑ ግንዛቤን ይፍጠሩ
የምትችሉ ሁሉ፡ በአመት አንዴ በምናደርገው በዚህ ፕሮግራም በአካል በመገኘት፡
ቲሸርት 400 ብር በመግዛት አብራችሁን የእግር ጉዞ ብታደርጉና ድምፃችችን ከኛ ጋር ሆናችሁ ብታሰሙልን።
በአካል መገኘት የማትችሉ ደግሞ፡ በሃገር ውስጥም ሆነ በውጭ ያላችሁ፡ የቲሸርቱን ዋጋ በመክፈል ብታግዙን።
ሃገር ውስጥ ያላችሁ፡ በሃገራችን አካውንት፡ ለአንድ ቲሽርት 400 ብር በማስገባት፥
ውጭ ያላችሁ ደግሞ ለአንድ ቲሽርት 10 ዶላር በአሜሪካን ሃገር አካውንት፡ በማስገባት ማገዝ ትችላላችሁ።

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር
1000009335308
ነህምያ ኦቲዝም ማዕከል

አዋሽ ባንክ አካውንት ቁጥር
013080330951000
ነህምያ ኦቲዝም ማዕከል

አሜሪካ አካውንት
Bank Of America 446037264761
Rout #052001633
Hands for Autistic children of Ethiopian
Contact person: Zinash Ayele
Email: [email protected]
Tel: 240-429-8362


ስልክ/Tel: 0930012652/0912660622/0911728141

Autism Awarness Walk & Hiking.
From Addis Gebeya roundabout to Gulele Botanical Garden and hiking inside the garden.
On April 3, Sunday, from 6:30 AM
Come, enjoy, create awarness and buy T-Shirt to support autistic children.
Those who can, you can attend this annual event by purchasing a T-shirt for 400 Birr and walk together and make our voices heard.
If you are unable to attend in person, thoses who live in Ethiopian and abroad.
please support us by paying the price of a T-shirt.
Those who live in Ethiopia, you can deposite 400 Birr per T-shirt in our local account:
And those who live abroad, you can deposite $ 10 in our US account.

Commercial Bank of Ethiopia
1000009335308
Nehemiah Autism Center

Awash Bank
013080330951000
Nejhemiah Autism Center

US Account
Bank Of America 446037264761
Rout #052001633
Hands for Autistic children of Ethiopian
Contact person: Zinash Ayele
Email: [email protected]
Tel: 240-429-8362

ኦቲዝም እና መሠል መረጃዎች ወዴ እናንተ ለሌሎች ወገኖቻችን እንድደርሱ ሸር እና ላይክ በማድረግ ይተባበሩን፡፡ በመጀመሪያ ጊዜዎን ሰጥተው ስለሚከታተሉ እናመሠግነዎታለን!!!
15/03/2022

ኦቲዝም እና መሠል መረጃዎች ወዴ እናንተ ለሌሎች ወገኖቻችን እንድደርሱ ሸር እና ላይክ በማድረግ ይተባበሩን፡፡ በመጀመሪያ ጊዜዎን ሰጥተው ስለሚከታተሉ እናመሠግነዎታለን!!!

ለሌሎችም አዳርሱ
28/02/2022

ለሌሎችም አዳርሱ

ባለሙያዎች ገባ ገባ በሉልን እኛ የጉዳዩን አሳሳቢነት ለማሳዬት ያክል እንጅ ጠለቅ ያለ እውቀት አልያዝንም ነገር ግን ፍቅር ይበልጣል

27/02/2022

ኑ...ጥሬያችን ነው እንሰብሰብ እንወያይ እንመካከር
አእምሮ መገንባት የህይወት ግደታችን ይሁን
ሰው በተፈጥሮ ሙሉዕ ባይሆንም ነገር ግን ይህን አለም የመረዳት አቅማችን ይለያይና አንዳችን አንዳችንን መግባባት ይወስነናል፡፡
ስለዚህ እንግባባ ዘንድ እንተባበር!!!
ኦቲዝም እክል ሳይሆን ተጨማሪ እውቀት ማመንጫ ነው

26/02/2022

እራሳችነን እንመልከት
ቤታችን እና ቤተሰቦቻችንን እናስተውል
ቅርብ ጎረቤቶቻችነን እንቃኝ
አካባቢያችንን መንደራችነን እንመርምር
ሁላችነም እንድህ ስናደርግ ከጥቃቅን እስከ ከፍተኛ የመግባባት ችግር ያለባቼውን ወገኖቻችንን እንለይ፡፡ እንድህ ሲሆን ስብዕናችን ከፍ ወዳለ ደረጃ ይደርሳል፡፡ ነፍሳችን እንድትደሰት ደግሞ የነዚህን ወገኖቻችን ፍላጎት እነሱ ወዴሚችሉት የህይወት ዘዬ ገብተን ወዴ እኛ አለም እናምጣቼው፡፡
ሲርበው ከሚያለቅስ እና ከሚነጫነጭ ይልቅ እጅህን ጎትቶ ምግብ የተሰራበትን እቃ እስኪያሳይህ ጣር ያኔ ደስ ይበልህ ምክንያቱም አንተ ተግባቦት ፈጥረሀል፡፡
ኦትስቲኮችን እንውደዳቼው አንተጋ የሌለ ጥበብ እነሱ ጋ በሽበሽ ነው፡፡

24/02/2022

ህያው ህይወት ህያው ሰውነት ነው፡፡ ሰው እና ስነ ህይወቱ በተለዬ መንገድ ሲጓዝ የተለዩ እውነታዎችን ይታደማል፡፡
ከነዚህ የህይወት እድምታዎች መካከል ደግሞ በቤታችን በአካባቢያችን ወይም በሀገራችን ቁጥር ስፍር የሌላቸው ውስጣቼውን ለኛ በግልፅ ሊነግሩን እና ሊያጋሩን የማይችሉ ግን ደግሞ የተለዬ ችሎታ ተሰጥኦ እና እውቀት ያላቼው ሰዎችን አይተናል፡፡ ኦትስቲክ እንላቼዋለን፡፡
ገራሚ ጥበብ ያላቼው ናቼው እንከባከባቼው!!!

18/02/2022

የሚኖሩት ከሳይንስ ሊቅ እና ፈላስፋ ልጄዎ ጋር እንዴሆነ ያውቃሉ?
እንግዳውስ በርትተው የነሱን አለም ገብተው ወዴ እርሰዎ አለም ለማምጣት ይጣሩ፡፡
ኦቲዝም እክልም በሽታም አይደለም ችግሩ መግባባት አለመቻላችን እንጅ ብዙ ነገር እነሱ ጋ በሽ ነው፡፡
ነገን ዛሬ እናሳያቼው፡፡ የነገ ማንነታቼው በዛሬው እናንተነት ነውእና በርቱ፡፡

Address

Gonder Ber
Woldia

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ስለ ኦቲዝም posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to ስለ ኦቲዝም:

Share