Ethio tena

Ethio tena ፈጣን፣ ወቅታዊ ፣እንዲሁም ታማኝ መረጃዎች እዚህ ያገኛሉ ።

https://m.youtube.com/watch?v=_TI_VO85lhY&t=4s
27/03/2024

https://m.youtube.com/watch?v=_TI_VO85lhY&t=4s

ሰላም ተመልካቾቻችን ስሜ ዶር ስንታየሁ ሲሳይ እባለሁ በ ቅዱስ ጳዉሎስ ሆስፒታል የ ማደንዘዣ ;ጽኑ ህሙማን እንዲሁም የህመም ትምህርት ክፍል ሁለተኛ አመት ተማሪ ነኝ ። ይህ አዲስ የ YouTube ...

07/03/2024
04/03/2024
02/03/2024

#ሰላም ውድ Ethio Health consultancy ቤተሰቦች እንደት ቆያችሁ?
Numbnes, Tingling and Burnning Sensation
• የእጅና የእጅ ጣት መደንዘዝ፡ መጠዝጠዝ፡ ማቃጠልና ህመም ስሜት በብዙዎች ዘንድ የተለመደ የጤና ችግር ነው።
• ይህ ችግር የሚፈጠረው ከአንገት ጀምሮ እስከ እጅ መዳፍና ጣት ድረስ በተዘረጋው የደም ቱቦና ነርቭ ላይ በሚፈጠር የተለያየ ችግር ነው። ከነርቭና የደም ቱቦ መጠምዘዝ፡ መታጠፍ፡ ሌላ አካል ሲጫነው፡ ሲለጠጥ፡ ሲጠብና የተለያየ ጉዳት ሲደርስበት የሚፈጠር ችግር ነው።
• አልኮል መጠጣት፡ ስትሮክ፡ የልብ ችግርና የተለያዩ ህመሞች ለመደንዘዝ፡ መጠዝጠዝ፡ማቃጠልና ህመም ስሜት ምክናየት ይሆናሉ።
#ተመሳሳይ ችግሮች
• የእግር ጣት መደንዘዝ
• የእጅ መቀዝቀዝ
• የጣት መቀዝቀዝ
• የእጅ መዛልና ሌሎችም አብረው የሚታይ ችግሮች ናቸው።
#ለእጅና ለእጅ ጣት መደዘዝ፡ መጠዝጠዝና ማቃጠል ዋና ዋና ምክናየቶች
• በተለያዩ የእጅ መገጣጠሚያ ላይ የነርቭ መጠምዘዝ ሲያጋጥም
• ከባድ ነገሮችን በሚያነሱና በሚጥሉ ወቅት
• ስብራትና ሌላም አደጋ ሲያጋጥም
• የእጅ መዳፍ አጠገብ ያለው መገጣጠሚያ(አምባር) ላይ ያለው ነርቭ ከታጠፈ
• የደም ቱቦ ከታጠፈ
• አንገት ላይ የሚፈጠር ማንኛው ችግር
• የኦክስጅን መብዛት
• የጨረር ህክምና
• የቫይታይሚን ቢ12 እጥረት
• የእጅ መገጣጠሚያ ላይ ውልቃት፡ ወለምታ ሲፈጠር
• የስኳር በሽታ
• ከፍተኛ አልኮል መጠጣት
• የነርቭ ጉዳት
• የመገጣጠሚያ ኢንፌክሽን
• ኤች አይቪ ኤድስ
• የእጅ ጣት መገጣጠሚያ ላይ ፈሳሽ ሲጠራቀም
• ለቀዝቃዛ ነገር መጋለጥ
• የስጋ ደዊ በሽታ
• የጀርባ ህመም
• የደም ቱቦ ኢንፌክሽን
• የተለያዩ መድሀኒቶች
• የራስ ምታትና ሌሎችም ለእጅና ጣት መደንዘዝና መጠዝጠዝ ምክናየቶች ናቸው።
#አብዛሀኛውን ጊዜ ይህ ችግር የሚፈጠረው አንገት፡ ትከሻ፡ ክንድ፡ እጅ፡ መዳፍና ጣት ላይ ከሚፈጠር የነርቭ መታጠፍና የደም ቱቦ ስፓዝም መፈጠር ጋር የተያያዘ ነው።
#ውድ Ethio Health Consultancy ቤተሰቦች የእጅና መዳፍ እስከ ጣት ድረስ ያለ ማንኛውም የመደንዘዝ፡ መጠዝጠዝና ማቃጠል ስሜት ዘርፈ ብዙ ምክናየቶች ሊኖሩት ቢችሉም በቀላሉ ተለይቶ በቀላሉ መታከም የሚችል የጤና ችግር ነው። ብዙ ጊዜ በፊዚኦቴራፒ(አካላዊ እንቅስቃሴና መታሸት) ከመድሀኒት ጋር የሚታከምበት መድሀኒት ቢሆንም ችግሩ እንድፈጠር ያደረገውን ምክናየት ማከም አዋጭ የህክምና ዘደ ነው። #ዉድ Ethio heath consultancy ቤተሰቦች ስለህክምናውና የእርስዎ የተለየ ችግር ካለ የ Ethio health consultancy #የጤና #ባለሙያዎችን #ማማከርና #መፍትሔ ማግኝት ይችላሉ።

Hey  እንዴት ናችሁ ,,, This is my YouTube health channel & pls support me to subscribe & promote my channel !
01/03/2024

Hey እንዴት ናችሁ ,,, This is my YouTube health channel & pls support me to subscribe & promote my channel !

ከፍተኛ የደም ግፊትን ለማስተካከል የሚረዱ ዋና ዋና ነገሮች (Hypertension Or high blood pressure) Ethio Health Care

Ethio health care
01/03/2024

Ethio health care

ከፍተኛ የደም ግፊትን ለማስተካከል የሚረዱ ዋና ዋና ነገሮች (Hypertension Or high blood pressure) Ethio Health Care

29/04/2022
13/02/2022

ጨጓራ ህመም ካለብን ማስተካከል ያሉብን የህይወት ዘይቤዎች
- ጠንከር ያለ የጨጓራ ስሜቶች ካሉብን ወደ ሃኪም ቤት ሄዶ መታየት
- የታዘዙ መድሃኒቶችን ተከታትሎ መውሰድ፣ ካልተሻለን ወይንም ስሜቱ ቶሎ ከተመለሰ ደግሞ ተመሳሳይ ሃኪም ካረ ቀርቦ እንዳልተሻለን መንገር
1- ብዙ ሰው የተለያዩ አይነት ምግቦች ህመሙን ይቀሰቅሱበታል፡፡ ስለዚህ ህመሙን የሚቀሰቅሱብንን ምግብና መጠጦች መለየትና አለመጠቀም፡፡

2- የተጠበሱ ምግቦች፣ ቸኮሌት፣ ቅመም፣ ነጭ ሽንኩርት እና ቅባት የበዛባቸውን ምግቦች ማስወገድ፡፡

3- ፈሳሽ ውሃና ቤት ውስጥ የተዘጋጀ ጭማቂ ብቻ መጠቀም
3- ቡና፣ አልኮል፣ ለስላሳ መጠጦች፣ ማንኛውም የታሸጉ መጠጦችን ማስወገድ
4- ሲጋራ የሚያጨሱ ከሆነ ባስቸኳይ ማቆም
5- ምግብ ሲበሉ በደንብ እስከሚጠግቡ አለመብላት፤ ትንሽትንሽ ቶሎ ቶሎ መመገብ
6- ምግብ ሲበሉ አለመጣደፍ፣ ቀስብለው በደንብ አላምጠው መመገብ
7- ክብደትን መቀነስ ሁልገዜም ወደመኝታ ከመሄድዎ 3 ሰኣታት አስቀድሞ መመገብ (ከምሽቱ ከ12 እስከ 1 ሰኣት ባለው ገዜ ውስጥ መመገብ) ፣ መኝታ ሰአት ከደረሰ በሃላ ምግብም ሆነ ፈሳሽ አለመጠቀም፡፡ ቢቻል በግዜ በልቶ የእግር እንቅስቃሴ ማድረግ፡፡
8- ከፍ ያለ ትራስ መጠቀም

የቴሌግራም ቻላናችንን ቤተስብ ይሁኑ
https://t.me/+UbojqWNhpSZ01_-m
https://t.me/+UbojqWNhpSZ01_-m
https://t.me/+UbojqWNhpSZ01_-m
https://t.me/+UbojqWNhpSZ01_-m

10/02/2022
08/02/2022

በስኳር ሕመም ምክንያት የዓይን ችግር( Diabetic macular edema) ላጋጠማችሁ ሕሙማን በመርፌ የሚሰጥ የመድኃኒት ሕክምና (Avastin injection ) ለመስጠት ዝግጅታችንን አጠናቀናል፡፡ ስለዚህ በስኳር ህመም ምክንያት የዓይን ችግር ( Diabetic macular edema) አለባችሁ ተብላችሁ መደኃኒቱን በተለያየ ምክንያት ማግኘት ያልቻላችሁሕሙማን 976 በመደወል ከየካቲት 2 -15 ድረስ መመዝገብ ትችላላችሁ፡፡
የቅዱስ ጳወሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ
የዓይን ሕክምና ትምህርት ክፍል

07/02/2022

የደም ግፊት መቼ እና በየስንት ጊዜው መለካት አለብዎ?
• የደም ግፊት እንዳለብዎት በሐኪምዎ ከተነገረዎት በኋላ ቢቻል በየጊዜው የደም ግፊትዎን መለካት ያስፈልጋል፡፡
• ምን ግዜም የደም ግፊት ልኬትዎን ይመዝግቡ፡፡
• የደም ግፊትዎን የሚለኩበት ግዜ በተመሳሳይ ሰአት ቢሆን ይመረጣል፡፡ ጠዋት ከእንቅልፍዎ ከተነሱ በኋላ ወይም ማታ ወደመኝታዎ ከመሄድዎ ቀደም ብለው ቢያደርጉት መልካም ነው።
• የሐኪምዎን ምክር ተግባራዊ ያድርጉ፡፡

05/12/2021
02/09/2021
29/05/2021

doctor video

23/05/2021

ፈጣን፣ ወቅታዊ ፣እንዲሁም ታማኝ መረጃዎች እዚህ ያገኛሉ ።

የስኳር በሽታ‼️(Diabetes Mellitus)• የስኳር በሽታ ማለት ሰውነታችን ግሉኰስ የሚባለውን ንጥረነገር መጠቀም ባለመቻሉ የሚፈጠር ችግር ነው። በዚህ ጊዜ በደም ውስጥ ያለው የግሉኰስ ...
05/04/2021

የስኳር በሽታ‼️
(Diabetes Mellitus)

• የስኳር በሽታ ማለት ሰውነታችን ግሉኰስ የሚባለውን ንጥረነገር መጠቀም ባለመቻሉ የሚፈጠር ችግር ነው። በዚህ ጊዜ በደም ውስጥ ያለው የግሉኰስ መጠን በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምራል።

• ይህ የሚሆነው ደግሞ ከሚከተሉት ባንዱ ነው።

1. ጣፊያ ውስጥ የሚገኝ ህዋስ ኢንሱሊን የሚባለውን ሆርሞን ማምረት አለመቻሉ

2. ሰውነታችን ኢንሱሊንን ተላምዶ ኢንሱሊኑ ጥቅም የማይሰጥ መሆኑ

• ኢንሱሊን ማለት ጣፊያ ውስጥ የሚመረት ሆርሞን ሲሆን በደም ውስክ ያለው የስኳር መጠን እንዳይጨምር የሚያደርግ ነው።

• በዋናነት ሁለት አይነት የስኳር በሽታዎች አሉ።

1. የመጀመሪያው አይነት የስኳር በሽታ፡ የራሳችን በሽታ ተከላካይ ሴል ኢንሱሊንን የሚያመርተውን ሴል በማጥቃቱና በአንዳንድ ቫይረስ ምክንያት የሚመጣ በሽታ ነው። አብዛኛውን ጊዜ እስከ 45 አመት ባለ የእድሜ ክልል የሚመጣ ሲሆን ኢንሱሊን ባለመኖሩና ባለመመረቱ የሚከሰት ነው። ይህ የስኳር በሽታ አይነት 10%ቱን ይይዛል።

2. ሁለተኛው አይነት የስኳር በሽታ፡ ጣፊያ ውስጥ ኢንሱሊን ቢመረትም የተመረተው ኢንሱሊን ጥቅም የማይሰጥና ሰውነታችን የተላመደው በመሆኑ የሚፈጠር ነው። ይህ በሽታ አብዛኛውን ጊዜ ከ45 አመት በኋላ የሚመጣና 90%ቱን የሚይዝ ነው። እድሜ መግፋት፡ ውፍረት፡ ንደትና ብስጭት እንደ አነሳሽነት ይቆጠራሉ።

3. በእርግዝና ጊዜ የሚመጣ የስኳር በሽታ ቢኖርም ከወሊድ በኋላ ለብዙዎቹ እናቶች ይጠፋል። ይህ የሚሆነው በእርግዝና ወቅት የሚመረት ሆርሞን የኢንሱሊንን መጠን ስለሚቀንስ ነው። ከወሊድ በኋላ ሆርሞኑ ስለሚጠፋ ኢንሱሊን ይስተካከላል።

🖌 አጠቃላይ የስኳር በሽታ ምልክቶች:-

• ቶሎ ቶሎ ውሀ መጠጣት፡ ቶሎ ቶሎ መሽናት፡ ቶሎ ቶሎ የሚመጣ የርሀብ ስሜት፡ ክብደት መቀነስ፡ የድካም ስሜት፡ እይታ ላይ ብጅታና በቀላሉ እጅና እግር መቁሰል።

• በወንዶች ላይ የወሲብ ስሜት መቀነስ፡ የብልት መልፈስፈስና የጡንቻ መልፈስፈስ

• በሴቶች ላይ ደግሞ የሽንት ቱቦ ኢንፌክሽን፡ በቀላሉ በፈንገስ ኢንፊክሽን መጠቃትና የቆዳ መገርጣትና ማሳከክ

🖌እነማን ተጋላጭ ናቸው?

1. በቤተሰብ ውስጥ የስኳር ተጠቂ ካለ

2. ውፍረት

3. እድሜ መጨመር

4. የአካል እንቅስቃሴ አለማድረግ

5. ከፍተኛ የደም ግፊት

6. ከፍተኛ ኮሌስትሮል

7. ከፍተኛ የስብ ጥርቅም ዋና ዋናዎቹ ናቸው።

የስኳር በሽታ የአኖኖር ዘይቤን በማስተካከልና በመድሀኒት ይታከማል።
አስቡ፡ የማይታከም የስኳር በሽታ በአንጎል፡ በልብ፡ በአይን፡ በኩላሊት፡ በደም ቱቦዎችና በእግር አካባቢ ከባድ ጉዳት ያስከትላል።

# የነርቭ መጎዳት፡ የአይን መጥፋት፡ መስማትን መነጠቅ፡ ኩላሊት ከጥቅም ውጭ መሆን፡ እግር መቆረጥ ሁሉ ሊያደርስ ይችላል።

# ነገር ግን የስኳር መጠኑን በየጊዜው እየተከታተለ የአኖኖር ዘይቤውን በሚያስተካክል ሰው ላይ ችግሩ እምብዛም አይደለም።

# አመጋገብ፡ የአካል እንቅስቃሴ፡ ከንደትና ብስጭት መራቅ፡ የታዘዘ መድሀኒትን በአግባቡ መውሰድና በየጊዜው በጤና ባለሙያ እየታዩ መረጃና ትምህርት የሚያገኙ ከሆነ ችግሩ በቀላሉ ይስተካከላል፡፡ የሚያስከትለውን ጉዳት መከላከል ይቻላል።

# የስኳር በሽታን ችላ ካልን ለከፍተኛ የስኳር በሽታ(ኬቶ አሲዶሲስ) ያጋልጠናል። ይህ ደግሞ ሰውነትን በቀላሉ ያጠቃል። ለሞትም ይዳርጋል!!!

Via:- IHC

Healthy Information For A Healthy Life

07/02/2021

የመገጣጠሚያ ህመም
******************
የመገጣጠሚያ ህመም ምን ማለት ነው?

መገጣጠሚያ አጥንቶች የሚገናኙበት ሰውነታችን ክፍል ሲሆን፤ ይህም በአላላችን ውስጥ ያሉ አጥንቶች በቀላሉ እንዲንቀሳቀሱ ይረዳል፡፡ ትከሻ፣ ዳሌ፣ ክርን፣ ጉልበት እና ቁርጭምጭሚትን መጥቀስ ይቻላል፡፡



የመገጣጠሚያ ህመም ስንል በማንኛውም መገጣጠሚያችን ላይ የህመም ስሜት፣ ማቃጠል፣ አለመመቸት እና የመሰርሰር ስሜት ሊሆን ይችላል፡፡ በርካቶች የሚያጋጥማቸው ቢሆንም የጤና ባለሙያ የሚያዩት ግነ ጥቂቶች ናቸው፡፡



የመገጣጠሚያ ህመም ብዙውን ጊዜ የሚከሰተው በመገጣጠሚያ ዙርያ ያሉ ስሮች እና ጅማቶች ላይ ጉዳት ሲደርስ ወይም በሌሎች ተጓጋኝ በሽታዎች ነው፡፡ መሰል ጉዳቶች በመገጣጠሚያ ዙሪያ ያሉትን ሌሎች ክፍሎችንም ሊያጠቃ ይችላል፡፡ ዋነኛው የመገጣጠሚያ ሀመም ምክንያት አርትራይቲስ (Arthritis) የተባለው በሽታ ነው፡፡


መንስኤዎቹ

አርትራይቲስ (Arthritis)

ይህ በሽታ የመገጣጠሚያ ህመምን ከሚያመጡ የጤና እክሎች ቀዳሚ ነው፡፡ ሁለት አይነት ሊሆን ይችላል፤ Osteoathritis እና Rheumatoid arthritis ናቸው፡፡



ሌሎች መንስኤዎች፡ ሪህ፣ አንዳንድ ተላላፊ በሽታዎች፣ የአጥንት ወይም የመገጣጠሚያ ኢንፌክሺን፣ ካንሰር፣ የአጥንት መሳሳት፣ የእድሜ መጨመር፣ በመገጣጠሚው አካባቢ ያሉ አካላት መቆጣት እና ጉዳት ይጠቀሳሉ፡፡


ምልክቶቹ የትኞቹ ናቸው?

- የመገጣጠሚያ ህመም

- መገጣጠሚያ አካባቢ ማበጥ

- የቆዳ መቅላት መገጣጠሚያ አካባቢ

- ሰውነታችን ለማንቀሳቀስ መቸገርና ህመም መሰማት

- ለመዘርጋት እና ለማጠፍ መቸገር


በቤት ውስጥ ምን ማድረግ ይቻላል?

ሳይንሱ እንደሚለው ከሆነ ዋነኛው የመገጣጠሚያ ህመምን የሚያመጣው አርትራይቲስ (Arthritis) አብሮ የሚኖር በሽታ እንደሆነ ነው፡፡ ህክምናውም ህመሙን ማስታገስ እና ድግግሞሹን መቀነስ ላ ያተኩራል፡፡

ከእነዚህመ ውስ የሚከተሉትን ማድረግ ይመከራል፤

- የሚቀቡ ወይም የሚዋጥ ህመም ማስታገሻ መውሰድ

- ቀለል ያሉ አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግ

- እንቅስቃሴ ከማድረጋችን በፊት ሰውነታችንን ማሳሳብ

- የተስተካከለ የሰውነት ክብደት እንዲኖረን ማድረግ

- ህመሙ በአርትራይቲስ (Arthritis) አለመምጣቱ ከተረጋገጠ ማሳጅ፣ ሙቅ ሻወር እና በቂ እረፍት መውሰድ ይመከራሉ

የመገጣጠሚያ በሽታን እንዴት በቀላሉ መከላከል እንችላለን?

1. ዝንጅብል

6 የሻይ ማንኪያ የተፈጨ ዝንጅብል እና 3 የሻይ ማንኪያ ሚጥሚጣ በተጨማሪም አንድ የሾርባ ውሀ ጋር በመቀላቀል በየቀኑ ህመም የሚሰማን የአጥንት መገጣጠሚያችን ላይ መቀባት ህመሙን ከማስታገሱ በተጨማሪም ቆዳችን ላይ ሊያጋጥመን የሚችል መቅላት ይከላከልናል።

ዝንጅብልን በመላጥ ጥሬው በመመገብ መከላከል እንችላለን።

2. መታሸት

ሰውነታችን መታሸት በተለይ መገጣጠሚያችን አካባቢ ይህን የመገጣጠሚያ በሽታ እንድንከላከል አቅሙን ይሰጠናል። ለሰውነት መታሻ ተብለው የተዘጋጁ ቅባቶችን (ለምሳሌ ከቀይ ሽንኩርት የተዘጋጁ) በመጠቀም መገጣጠሚያችን አካባቢ ቀስ እየሉ ማሸት በተለይ በመገጣጠሚያችን እብጠት ካለ ቀስ እያልን ማሸት ያስፈልጋል።

3. እርድ

እርድን በለት ተእለት ምግባችን ውስጥ አካተን ብንመገብ ሊፈጠር የሚችለውን በሰውነታችን የመቅላት ወይም መብለዝ ይከላከላል።



4. የእንግሊዝ ጨው (Epsom Salt):~

የእንግሊዝ ጨው በውስጡ ከፍተኛ የሆነ የማግኒዝየም ክምችት ስላለው የሰውነታችን PH (የአሲድነት) መጠን ይቆጣጠርልናል።



የሎሚ ጭማቂ እና የእንግሊዝን ጨው በእኩል መጠን ከግማሽ ብርጭቆ ለብ ያለ ውሀ ጋር በእኩል መጠን ቀላቅሎ በቀን ለሁለት ጊዜ ጠዋትና ማታ አንድ የሻይ ማንኪያ መጠጣት ይመከራል፡፡

5. ቀረፋ

ቀረፋ በውስጡ አንቲ~ኦክሳይዝ በመሆንና የሰውነትን መቅላት ወይም መብለዝን የመከላከል አቅም አለው። ግማሽ የሻይ ማንኪያ ቀረፋ በአንድ የሾርባ ማንኪያ ማር በመቀላቀል በውሀ አፍልቶ ጠዋት በባዶ ሆድ አንድ የሻይ ብርጭቆ መጠጣት በተከታታይ ለብዙ ቀናት መጠጣት። ማር እና የተፈጨ ቀረፋን በመቀላቀል ህመም የሚሰማንን ቦታ ቀስ እያልን መታሸት።

6. የአሳ ዘይት

የአሳ ዘይት ውስጥ የየሚገኘው ኦሜጋ~3 ፋቲ አሲድ የሰውነታችን መቅላትና ማበጥ የመከላከል ሀይል ስላለው ህመማችን ያስታግስልናል።

በቀን አንድ ወይም ሁለት የሻይ ማንኪያ የአሳ ዘይት በየቀኑ መጠጣት። በተጨማሪም የአሳ ዘይት በውስጣቸው የያዙ ምግቦችን ጠዋት ጠዋት ብንመገብ ሊያጋጥመን የሚችለውን የመገጣጠሚያ ድርቀት እንዲሁም የሰውነት አልታዘዝም ባይነት የመከላከል አቅም አለው።


ሃኪሞት ጋር መቼ መሄድ አለቦት?

· የመገጣጠሚያ ህመሙ ለምን እንደመጣ ካልታወቀ

· ሌሎች ተያያዥ ምልክቶች ካስተዋሉ

· የታመመው መገጣጠሚያ ዙሪያ ማበጥ፣ መቅላት፣ ህመም እና ሙቀት ካለ

· ህመሙ ለቀናት ከቆየ

· ትኩሳት ካለ

· ጉዳት ከደረሰቦት

· ድንገት መገጣጠሚያ ላይ እብጠት ካዩ

· መገጣጠሚያው የማይንቀሳቀስ ከሆነ

· ከፍተኛ የመገጣጠሚ ህመም ካለ



ይህንን መረጃ ሼር በማድረግ ለሌሎች ያጋሩ!

21/01/2021
31/12/2020

በዲላ ሠላም ሆስፒታል ከአንዲት እናት 26 ኪሎ ግራም ዕጢ ወጣ!

በዲላ ከተማ በሚገኘው ሠላም ሆስፒታል አንዲት እናት 26 ኪሎግራም የሚመዝን ዕጢ ዛሬ ቀን በተካሄደ የቀዶ ህክምና የወጣላቸው መሆኑን የሆስፒታሉ ሐኪም አስታወቁ።

ቀዶ ህክምና ያደረጉት የሆስፒታሉ ሐኪም ዶክተር ጌታቸው መርጊያ የ40 ዓመት ዕድሜ ያላቸው እኚሁ እናት ሆዴ አብጧል ብለው ወደ ጤና ተቋሙ መምጣታቸውን ገልጸዋል።

ምርመራ ሲካሄድም ከማህጸን ተነስቶ ሁሉንም የሆዳቸው አካባቢ የሸፈነ ዕጢ መሆኑ በመረጋገጡ ቀዶ ህክምና እንደተደረገላቸው አስረድተዋል።

በቀዶ ህክምና የወጣለቸው የዕጢው ክብደት 26 ኪሎግራም የሚመዝን መሆኑን ዶክታር ጌታቸው አመልክተው ችግሩን ለማወቅ ተጨማሪ ምርመራ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

ቀዶ ህክምናው ሰላሳ ደቂቃ ብቻ መፍጀቱን የተናገሩት ሐኪሙ ከቀዶ ህክምናው በኋላ እናቲቱ በመልካም የጤና ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ አስታውቀዋል። (ENA)

15/12/2020
15/12/2020
14/12/2020

የእጅ አመል-Kleptomania
=================
ዝነኛዋ ተዋናይት ሊንዚይ ሎሀን በስራዎቿ ከ28 ሚሊዮን ዶላር ተከፍሏት ያውቃል። ነገር ግን በተደጋጋሚ ከሱቆች የተለያዩ እቃዎችን 'ስታነሳ' ተይዛ ክስ ተመስርቶባታል። ሊንዚይ ግን " እቃዎችን የማነሳው ክሌፕቶማኒያ የሚባለው የአእምሮ ህመም ስላለብኝ እንጂ ገንዘብ አጥቼ አይደለም።" ብላ ትከራከራለች።

ክሌፕቶማኒያ (የእጅ አመል) ያለባቸው ሰዎች እቃ የሚሰርቁት በእቃው ለመጠቀም ፈልገው አይደለም። እቃው ፊትለፊት ሲሆኑ አእምሯቸው "አንሳው፣ አንሳው!" እያለ ይነዘንዛቸዋል። ንዝንዙን መቋቋም ስለማይችሉ እቃውን ይሰርቃሉ። ልክ እንደሰረቁ ቀለል ይላቸዋል። አንዳንዶቹ ሰርቀው እቃውን ይዘው ቤታቸው ከሄዱ በኋላ የሰርቁበት ቦታ ተመልሰው እቃውን ያስቀምጣሉ።

ክሌፕቶማኒያ ከፀጉር መንጨት እንዲሁም ከቁማር ሱስ ጋር የሚመደብ ስሜትን የመቆጣጠር ህመም ሲሆን ሴቶች ላይ የመከሰት እድሉ ከፍ ያለ ነው። እስካሁን በስራ ላይ አንዴ ብቻ ነው የሰማሁት። አንዲት ወጣት ከሱፐር ማርኬት እቃ ስትሰርቅ ተይዛ ለፍርድ ቤቱ "እኔ ክሌፕቶማኒያ የሚባል የአእምሮ ህመም ስላለብኝ ነው።" ብላ ለአእምሮ ምርመራ ተልካ ነው።

አንዳንድ ጊዜ ክሌፕቶማኒያን እና ስርቆትን መለየት አስቸጋሪ ነው። ለአመላቸው ዳቦ የሚልሱ ሌቦች ግን ካልገመጡት ወይም የሚልሱበት ምክኒያት ሌላ ሰው እንዳይበላው ለማበላሸት ሳይሆን እንደዚያ አድርግ የሚለውን ግፊት መቋቋም አቅቷቸው ከሆነ ከስርቆት ይልቅ ክሌፕቶማኒያ ይመስለኛል።

ያለ አእምሮ ጤና፤ ጤና የለም።
ዶ/ር ዮናስ ላቀው

11/12/2020

እንድናገለግልዎ ማስክዎን ያድርጉ!!

Address

Jimma

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio tena posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Ethio tena:

Videos

Share