South Radio and Television Agency

South Radio and Television Agency This page is owned by South Radio and Television Agency, SNNPRS, Ethiopia.
(22)

In addition to this Meta Page, we have other social media accounts:

Website: https://srta.gov.et/

Telegram :
https://t.me/southRadioAndTelevisionAgency

Youtube:
https://www.youtube.com//featured

Twitter:
https://twitter.com/SouthRadioandTv
South Radio and Television Agency is a Government owned media that disseminates its news and programs worldwide via Television, Radio, and Website.

ጁሊያን ናጌልስማን ውላቸውን አራዘሙ የጀርመን ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ የሆኑት ጁሊያን ናጌልስማን በሃለፊነት ለመቆየት በመስማማት ውላቸውን አራዝመዋል።የ36 ዓመቱ አሰልጣኝ እኤአ 2026 ...
19/04/2024

ጁሊያን ናጌልስማን ውላቸውን አራዘሙ

የጀርመን ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ የሆኑት ጁሊያን ናጌልስማን በሃለፊነት ለመቆየት በመስማማት ውላቸውን አራዝመዋል።

የ36 ዓመቱ አሰልጣኝ እኤአ 2026 የዓለም ዋንጫ ድረስ ለመቆየት ተስማምተዋል።

አሰልጣኙ በወርሃ መስከረም ሃንሲ ፍሊክን በመተካት ብሔራዊ ቡድኑን የተረከቡ ሲሆን በእስካሁኑ ቆይታቸው ካከናወኗቸው 6 ጨዋታዎች 3ቱን ማሸነፍ ችለዋል።

ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ

የግብርና ግብዓቶችን ጥራት ማረጋገጥ ለምርትና ምርታምነት እድገት የጎላ  ፋይዳ አለው- አብዱልሃኪም አልቤ (ዶ/ር)ሀዋሳ፡ ሚያዝያ 11/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) የግብርና ግብኣቶችን ጥራትና ብ...
19/04/2024

የግብርና ግብዓቶችን ጥራት ማረጋገጥ ለምርትና ምርታምነት እድገት የጎላ ፋይዳ አለው- አብዱልሃኪም አልቤ (ዶ/ር)

ሀዋሳ፡ ሚያዝያ 11/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) የግብርና ግብኣቶችን ጥራትና ብቃት ማረጋገጥ ለምርትና ምርታምነት እድገት የሚኖረው ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የግብርና ግብአቶች ጥራት ቁጥጥርና ኳራንቲን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አብዱልሃኪም አልቤ (ዶ/ር) ገለፁ።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የግብርና ግብአቶች ጥራት ቁጥጥርና ኳራንቲን ባለስልጣን ከእፅዋት ዘር ጥራት ቁጥጥርና ምርመራ ማዕከላት ከባለድርሻ አካላት ጋር የዘጠኝ ወር እቅድ ክንውን አፈፃፀም ግምገማ መድረክ በዛሬው እለት በቡታጅራ ከተማ ተካሄዷል።

በመድረኩ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት ዋና ዳይሬክተሩ የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል እንደ አዲስ የተቋቋመ ክልል እንደመሆኑ ቢሮዎችን የማደራጀት ስራ ስለመከናወኑ በመድረኩ አንስተዋል።

በተለይም ለዘር አምራቾች አቅራቢዎች እና ቸርቻሪዎች ስልጠና መሰጠቱን ተናግረዋል።

የግብርና ግብኣቶችን ጥራትና ብቃት ማረጋገጥ ለምርትና ምርታምነት እድገት የሚኖረው ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑንም አብራርተዋል፡፡

ከዚህ መነሻም መስሪያ ቤቱ የግብርና ግብኣቶች ህገ ወጥ ዝውውርን በመከላከል፣ የዘር ጥራት ቁጥጥር፣ ጊዜ ያለፈባቸው ጸረ ተባይና ጸረ አረም ኬሚካሎችን በማስወገድ በኩል ባለፉት 9 ወራት የተለያዩ ስራዎችን ሲያከናውን ቆይቷል

ባለፉት ወራት እንደ ችግር ከሚስተዋሉ ጉዳዮች መሀል ህጋዊ መስለው ህገ-ወጥ ስራ ላይ የተሰማሩና ፍቃድ ሳይኖራቸው የሚንቀሳቀሱ አካላት እንዳሉ ታውቆ የእርምት እርምጃ እንደተወሰደባቸው ተገልጿል።

በቀጣይም በጠንካራ ጎን የተነሱ ስራዎችን ማስቀጠልና ክፍተት አለባቸው ተብለው የተለዩትን በማረም በትኩረት እንደሚሠራ ተገልጿል።

ባለስልጣኑ በሚሰራቸው ስራዎች የባለድርሻ አካላት አስተዋጽኦ የጎላ መሆኑንም ተናግረዋል።

ዘጋቢ፡ ትዝታ ተሰማ

የጉራጊኛ ቋንቋን ለማሳደግ እየተደረገ ባለዉ ጥረት ኃላፊነቱን እየተወጣ ይገኛል - የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ሀዋሳ፡ ሚያዝያ 11/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) የጉራጊኛ ቋንቋን ለማሳደግ እየተደረገ ባለ...
19/04/2024

የጉራጊኛ ቋንቋን ለማሳደግ እየተደረገ ባለዉ ጥረት ኃላፊነቱን እየተወጣ ይገኛል - የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ

ሀዋሳ፡ ሚያዝያ 11/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) የጉራጊኛ ቋንቋን ለማሳደግ እየተደረገ ባለዉ ጥረት ኃላፊነቱን እየተወጣ እንደሚገኝ የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ገለፀ፡፡

ይህ የተገለፀዉ ቋንቋን መሰረት ያደረገ መቅረዝ የተሰኘዉ መፅሀፍ በዩኒቨርሲቲዉ ግቢ በተመረቀበት ወቅት ነዉ፡፡

በመምህር ካሚል ኑረዲን ደራሲነት ጉራጊኛ ቋንቋን መሰረት በማድረግ መቅረዝ የተሰኘዉ ባለ ሁለት መቶ 20 ገፅ መፅሀፍ በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ እገዛ በአማርኛ ቋንቋ ታትሞ ለምርቃት በቅቷል፡፡

የወልቂጤ የኒቨርሲቲ የአካደሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሀብቴ ዱላ ዩኒቨርሲቲዉ ከመማር ማስተማር ባሻገር በማህበረሰብ አገልግሎት ዘርፍ ባህል፣ ታሪክና ቋንቋን መሰረት ያደረጉ ስራዎች እንዲታወቁ እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ለአብነትም አዳብና ነቋ፣ አንትሮሽት፤ ኩርፉወ፣ ባህላዊ መድሃኒቶችና ጀፎረ ላይ ጥናትና ምርምር ማድረጉን ተናግረዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲዉ በጉራጊኛ ቋንቋ ላይ መሰረት ያደረገዉን መቅረዝ መፅሀፍ ወጪውን ችሎ ማሳተሙ ቋንቋዉ ለትምህርት፣ ለመገናኛ ብዙሃን፣ ለስራና ሳይንስ ተግባራት ለማዋል እንደሚያግዝም ገልፀዋል፡፡

የመፅሀፉ ደራሲ ረዳት ፕሮፌሰር ካሚል ኑረዲን ጉራጊኛ ላይ በስፋት ጥናት ቢደረግም ወደ ተግባር አልተቀየረም ይህንን ክፍተት ለመቅረፍ የተዘጋጀ ነዉም ብለዋል፡፡

ወልቂጤ ዩኒቪርሲቲ የመፅሀፉን ጠቀሜታ በመረዳት ለህትመት በማብቃቱ መደሰታቸዉን ገልፀዉ ምስጋናቸዉን አቅርበዋል፡፡

ዶ/ር ፈቀደ ምኑታ፣ ዶ/ር መዘምር ተክለአብና ዶ/ር ጌታቸዉ መንግስቱ እንደገለፁት መፅሐፉ በቋንቋ ዉስጥ ታሪክ፣ ባህልና ማንነት እንዴት ማሳደግና መግለፅ እንደሚቻል ያሰየ ነዉ፡፡

በአፍ መፍቻ ቋንቋ መማር አከባቢን ቶሎ ለመረዳት፤ በፍጥነት ነገሮችን ለመገንዘብና ለአእምሮ እድገት ወሳኝ መሆኑንም አመላክተዋል፡፡

ሁሉም ባለድርሻ አካለት በጋራ በመስራት በመደማመጥና በመነጋገር ጉራጊኛ ቋንቋ መታደግ እንደሚገባቸውም ምሁራኑ አብራርተዋል፡፡

የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ደግነህ ቦጋለ የጉራጊኛ ቋንቋን በማሳደግ የብሄሩን ማንነት፤ ታሪክና ባህል ለማስተዋወቅ ለሚከናወነዉ ስራ ቢሮዉ ኃላፊነቱን እንደሚወጣ ገልፀዋል፡፡

መፅሃፉ በክልሉ የሚነገሩ ቋንቋዎችን ለማልማት ሚደረገዉ ጥረት አጋዥ መሆኑን አዉስተዋል፡፡

የጉራጌ ዞን ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ልክነሽ ስርገማ መፅሀፉ ጉራጊኛን በሁሉም ዘርፍ ተደራሽ ለማድረግ ለሚደረገዉ እንቅስቃሴ ይበልጥ የሚያነሳሳ መሆኑን ተናገረዋል፡፡

የመድረኩ ተሳታፊዎችም በሰጡት አስተያት መፅሀፉ ሳይንሳዊ ምልከታ ላይ ያተኮረ በመሆኑ በጉራጊኛም ሆነ በሌሎች ቋንቋዎች ለሚደረጉ የጥናትና ምርምር ስራዎች እንደሚረዳም ገልፀዋል፡፡

ዘጋቢ፡ እንዳልካቸው ደሳለኝ - ከወልቂጤ ጣቢያችን

በተጨማሪም የቪዲዮና ሌሎች መረጃዎቻችንን ለማግኘት የትክክለኛ አድራሻዎቻችን አባል በመሆን ይከታተሉ፡-
ዩቲዩብ- https://www.youtube.com/southradioandtelevisionagency
ቴሌግራም -https://t.me/southRadioAndTelevisionAgency
ዌብ ሳይት - https://srta.gov.et/
ትዊተር - https://twitter.com/SouthRadioandTv

በፍትሕ ዘርፍ የሚታዩ እሮሮዎችን ለማረም የተጠያቂነት ሥርዓት ሊጠናከር እንደሚገባ ተገለጸየደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት ከኣሪ ዞን ሽግግር ምክር ቤት ጋር በመቀናጀት ለፍትህ ዘርፍ ሪፎርም...
19/04/2024

በፍትሕ ዘርፍ የሚታዩ እሮሮዎችን ለማረም የተጠያቂነት ሥርዓት ሊጠናከር እንደሚገባ ተገለጸ

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት ከኣሪ ዞን ሽግግር ምክር ቤት ጋር በመቀናጀት ለፍትህ ዘርፍ ሪፎርም የሚሆን ግብዓት ማሰባሰቢያ የህዝብ መድረክ በጂንካ ከተማ በተካሄደበት ወቅት ነው ይህ የተገለፀው።

በመድረኩ ከየወረዳው የተገኙ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት ፖሊስ፣ አቃቢ ህግና ፍርድ ቤቶች ላይ የሚታዩ የጥቅም ትስስሮች፣ በማረሚያ ቤቶች የሚታዩ የማረምና የማነፅ ሥራዎች ለወጥ በሚያመጣ መንገድ አለመሆን፣ የሰው ኃይል እጥረት፣ የዳኞችና አቃቢ ህጎች የብቃት ማነስና ሌሎችም በዘርፉ እስከአሁንም ያልተፈቱ ተግዳሮቶች ናቸው ብለዋል።

ተሳታፊዎቹ አክለውም በፍትህ ዘርፍ በተለይም በፍርድ ቤቶች የሚታዩ ችግሮችን ለማረም የግልጽነትና ተጠያቂነት ሥርዓት በአግባቡ መስፈን ይገባዋል ብለዋል።

መድረኩን የመሩት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር አለማየሁ ማሞና በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት የህግ ጉዳዮች አማካሪ አቶ አዳነ ገበየሁ በጋራ በሰጡት ምላሽ ከተሳታፊዎች ትልቅ ግብዓት ማግኘታቸውንና ችግሮችን ለማቃለል የተጠያቂነት ሥርዓት በማስፈን እንደሚሰራ ተናግረዋል።

ዘጋቢ: ከተማ በየነ - ከጂንካ ጣቢያችን

በተጨማሪም የቪዲዮና ሌሎች መረጃዎቻችንን ለማግኘት የትክክለኛ አድራሻዎቻችን አባል በመሆን ይከታተሉ፡-
ዩቲዩብ- https://www.youtube.com/southradioandtelevisionagency
ቴሌግራም -https://t.me/southRadioAndTelevisionAgency
ዌብ ሳይት - https://srta.gov.et/
ትዊተር - https://twitter.com/SouthRadioandTv

የደቡባዊ ግሪድ ማስፋፊያ ፕሮጀክት የግንባታ ሥራ 45 በመቶ ደርሷልሀዋሳ፡ ሚያዝያ 11/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) የብሄራዊ የኤሌክትሪክ ግሪድ ደቡባዊ ማስፋፊያ ፕሮጀክት የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ...
19/04/2024

የደቡባዊ ግሪድ ማስፋፊያ ፕሮጀክት የግንባታ ሥራ 45 በመቶ ደርሷል

ሀዋሳ፡ ሚያዝያ 11/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) የብሄራዊ የኤሌክትሪክ ግሪድ ደቡባዊ ማስፋፊያ ፕሮጀክት የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ እና የኃይል ማስተላለፊያ መስመር የግንባታ ሥራ 45 በመቶ መድረሱን የፕሮጀክቱ ሥራ አስከያጅ አቶ መሐመድ ሽኩር አስታወቁ።

የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ አቶ መሐመድ ሽኩር እናዳስታወቁት የፕሮጀክቱ የዲዛይን ሥራ 94 በመቶ፣ ኤሌክትሮ ሜካኒካል ዕቃዎች የማምረት ሥራ 58 በመቶ እና የሲቪል ግንባታ ሥራ 6 ነጥብ 5 በመቶ ደርሷል፡፡

እንደ ሥራ አስኪያጁ ገለፃ የአምስቱም ሰብስቴሽኖች ዲዛይን ሥራ 92 በመቶ የኤሌክትሮ ሜካኒካል ዕቃዎች የማምረት ሥራ 54 በመቶ እና የሲቭል ግንባታ ሥራ 5 በመቶ ተጠናቋል፡፡

የወላይታ 2ኛ ጣቢያ ማስፋፊያ፣ ሽግዳን አዲስ፣ ጥርጋ አዲስ፣ አርባ ምንጭ 1ኛ ማስፋፊያ እና አርባ ምንጭ 2ኛ አዲስ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ የግንባታ ደረጃቸው 43.6 በመቶ መድረሱንም ሥራ አስኪያጁ ገልፀዋል፡፡

የአርባ ምንጭ 2ኛ ጣቢያ የመቆጣጠሪያ ክፍል እና የትራንስፎርመሮች ማስቀመጫ የመሰረት ቁፋሮ ሥራዎች መጠናቀቁንና የመሰረት ኮንክሪት ሙሌትና ብረት የማቆም ስራዎች በመከናወን ላይ ይገኛሉ፡፡

የወላይታ 2ኛ ማስፋፊያ ጣቢያ የትራንስፎርመሮች ማስቀመጫ የመሰረት ኮንክሪት ሙሌት መጠናቀቁን፣ ብረት የማቆም ሥራዎች እና የ400 ኪሎ ቮልት ኢሌክትሮ ሜካኒካል ዕቃዎች የመሰረት ቁፋሮ ሥራዎች በመከናወን ላይ መሆናቸውንም አቶ መሀመድ ተናግረዋል፡፡

የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ግንባታ የዲዛይን ሥራ 98 በመቶ፣ የአሌክትሮ መካኒካል ዕቃዎችን የማምረት ሥራ 65 በመቶ እና ሲቪል ግንባታ ሥራ 7 በመቶ የደረሰ ሲሆን አጠቃላይ የግንባታ ስራው 46 ነጥብ 4 በመቶ መድረሱንም አቶ መሀመድ አብራርተዋል፡፡

98 የኃይል ተሸካሚ ምሰሶዎች የቁፋሮ ስራ እና የ60 ተሸካሚ ምሰሶዎች የኮንክሪት ሙሌት ስራ በባለ 230 ኪሎ ቮልት የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች ላይ የተጠናቀቁ መሆናቸውንና ቀሪ ሥራዎች እየተከናወኑ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

በብሄራዊ የኤሌክትሪክ ግሪድ ደቡባዊ ማስፋፊያ ፕሮጀክት የደቡባዊ ኢትየጵያን የኃይል መሰረተ ልማት ማስፋፋትና መሻሻል፣ ከኦሞ ስኳር ፋብሪካዎች የሚመነጭን 189 ሜጋ ዋት ትርፍ ኤሌክትሪክ ኃይል ወደ ብሄራዊ ግሪድ ማስገባት እና በአርባ ምንጭ ዙሪያ ሊገነባ ለታቀደው አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክ በቂና አስተማማኝ የኃይል አቅርቦት ለማስገኘት ተቅዶ የተመሰረተ ታላቅ ፕሮጀክት መሆኑ እንደሚታወስ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል መረጃ ያሳያል፡፡

በተጨማሪም የቪዲዮና ሌሎች መረጃዎቻችንን ለማግኘት የትክክለኛ አድራሻዎቻችን አባል በመሆን ይከታተሉ፡-
ዩቲዩብ- https://www.youtube.com/southradioandtelevisionagency
ቴሌግራም -https://t.me/southRadioAndTelevisionAgency
ዌብ ሳይት - https://srta.gov.et/
ትዊተር - https://twitter.com/SouthRadioandTv

አቶ አደም ፋራህ በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ጋር ተወያዩሀዋሳ፡ ሚያዝያ 11/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ)   የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር...
19/04/2024

አቶ አደም ፋራህ በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ጋር ተወያዩ

ሀዋሳ፡ ሚያዝያ 11/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዣዎ ዢዋን ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም÷የጋራ ተጠቃሚነትን ለማስፋት፣ የሁለቱን ሀገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለማጠናከር እንዲሁም የኢንቨስትመንት አማራጮችን በማስፋት ዙሪያ መክረዋል፡፡

አቶ አደም ፋራህ÷የኢትዮ-ቻይና ዘመናትን የተሻገረ ወዳጅነት ይበልጥ ተጠናክሮ መቀጠሉንና የቻይናው ኮሙኒስት ፓርቲ አጋርነትም ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ እንደመጣ አንስተዋል።


ከዚህ በፊት በሁለቱ ፓርቲዎች ስምምነት መሰረት በትምህርት፣ በስልጠና እንዲሁም በተሞክሮና ልምድ ልውውጥ አብሮ መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ስምምነት መደረጉን ጠቅሰዋል፡፡

በቅርቡ የብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ተሳታፊ የሆኑበት የልዑካን ቡድን ውጤታማ ቆይታ አድረጎ መመለሱም የዚህ ስምምነት አካል መሆኑን ነው የገለጹት፡፡

ለልዑካን ቡድኑ ለተደረገው አቀባበልና ስኬታማ የቆይታ ጊዜ ያላቸውን ምስጋና ገልጻዋል ፡፡

በቀጣይም የፓርቲ ለፓርቲ ግንኙነቶች በመሰል የስልጠናና የልምድ ልውውጥ መርሐ ግብሮች ተጠናክሮ እንዲቀጥል ብልፅግና ፓርቲ ፍላጎቱ እንደሆነ አብራርተዋል።

አምባሳደር ዣዎ ዢዋን በበኩላቸው÷የብልጽግና ፓርቲ በኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ እየሰራቸው ያሉ ውጤታማ ስራዎችን አድንቀዋል፡፡

ኢትዮጵያ የቻይና ጠንካራ ስትራቴጂክ አጋር መሆኗን ጠቅሰው÷ይህ ግንኙነት በፓርቲ ለፓርቲም ሆነ በመንግስታዊ ወዳጅነት ወደ ተሻለ ደረጃ እንዲያድግ እንደሚሰሩ የፓርቲው መረጃ ያመላክታል፡፡

በተጨማሪም የቪዲዮና ሌሎች መረጃዎቻችንን ለማግኘት የትክክለኛ አድራሻዎቻችን አባል በመሆን ይከታተሉ፡-
ዩቲዩብ- https://www.youtube.com/southradioandtelevisionagency
ቴሌግራም -https://t.me/southRadioAndTelevisionAgency
ዌብ ሳይት - https://srta.gov.et/
ትዊተር - https://twitter.com/SouthRadioandTv

የተሳታፊ ልየታ በተከናወነባቸው አካባቢዎች የአጀንዳ ማሰባሰቢያ መድረኮችን ለመጀመር የሚያስችሉ ዝግጅቶች ተጠናቀዋል - የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽንለአገራዊ ምክክሩ የተሳታፊ ልየታ በተከ...
19/04/2024

የተሳታፊ ልየታ በተከናወነባቸው አካባቢዎች የአጀንዳ ማሰባሰቢያ መድረኮችን ለመጀመር የሚያስችሉ ዝግጅቶች ተጠናቀዋል - የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

ለአገራዊ ምክክሩ የተሳታፊ ልየታ በተከናወነባቸው አካባቢዎች የአጀንዳ ማሰባሰቢያ ህዝባዊ መድረኮች ለመጀመር የሚያስችሉ ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውን የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ገለጸ፡፡

በኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን እንደ ሀገር በሚስተዋሉ ችግሮች ላይ በመወያየት በዘላቂነት ለመፍታት፣ ብሔራዊ መግባባትና ሀገራዊ አንድነት ለመፍጠር በአዋጅ የተቋቋመ ገለልተኛ ተቋም ነው፡፡

ኮሚሽኑ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አዋጅ ቁጥር 1265/2014 ፀድቆ ወደ ሥራ ገብቷል፡፡

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ቃል አቀባይ ጥበቡ ታደሰ ለኢዜአ እንዳሉት፤ ከሚሽኑ ኃላፊነቱን ተረክቦ ወደ ሥራ ከገባበት ጊዜ ጀምሮ ለምክክሩ ስኬት የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን ሲያሰባስብ ቆይቷል፡፡

ባለፉት ሁለት ዓመታት ለምክክሩ ውጤታማነት አስፈላጊ በሆኑ የተሳታፊ ልየታ መድረኮች መካሄዳቸውን ገልጸዋል፡፡

በዚህም ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችና የህዝብ አደረጃጀቶች ጋር ሰፊ የውይይት መድረኮች በማዘጋጀት ተጨባጭ ውጤት ተገኝቷል ብለዋል፡፡

በተሳታፊ ልየታው የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች፣ ፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ሲቪክ ማህበራት፣ የኃይማኖት ተቋማት፣ የዲያስፖራና የተለያዩ ትምህርት ተቋማት፣ በዕድሜና ጾታ ጭምር ተካተዋል ብለዋል

የተሳታፊ ልየታ ባልተከናወነባቸው አካባቢዎች ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ስራዎችን ለማጠናቀቅ እንደሚሰራም ጠቁመዋል፡፡

በተጨማሪም ኮሚሽኑ ምክክር የሚደረግባቸው የአጀንዳ ሀሳቦችን ከጥናቶች፣ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችና ከህዝባዊ መድረኮች የማሰባሰብ ስልጣን እንደተሰጠው ገልጸዋል፡፡

በመሆኑም የተሳታፊ ልየታ በተደረገባቸው ክልሎች የአጀንዳ ሀሳብ ለማሰባሰብ የሚያስችሉ ህዝባዊ መድረኮችን ለመጀመር የሚያስችሉ ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውን አብራርተዋል፡፡

ምክክር ኮሚሽኑ በሀገሪቱ ከሚገኙ ከአንድ ሺህ 300 ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች የሚሳተፉ ተሳታፊዎች ጋር የአጀንዳ ማሰባሰቢያ መድረኮችን ያዘጋጃል ብለዋል፡፡

በተጨማሪም የቪዲዮና ሌሎች መረጃዎቻችንን ለማግኘት የትክክለኛ አድራሻዎቻችን አባል በመሆን ይከታተሉ፡-
ዩቲዩብ- https://www.youtube.com/southradioandtelevisionagency
ቴሌግራም -https://t.me/southRadioAndTelevisionAgency
ዌብ ሳይት - https://srta.gov.et/
ትዊተር - https://twitter.com/SouthRadioandTv

በዘጠኝ ወራት ውስጥ ከ 296 ሺህ በላይ ደንበኞች የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ሆነዋልሀዋሳ፡ ሚያዝያ 11/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) ተቋሙ ሁሉንም የህብረተሠብ ክፍል የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ ለ...
19/04/2024

በዘጠኝ ወራት ውስጥ ከ 296 ሺህ በላይ ደንበኞች የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ሆነዋል

ሀዋሳ፡ ሚያዝያ 11/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) ተቋሙ ሁሉንም የህብረተሠብ ክፍል የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ ለማድረግ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ሲሆን፤ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ውስጥ 296 ሺህ 963 አዲስ ደንበኞችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ አድርጓል፡፡

በዘጠኝ ወራት የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ለማድረግ የታቀደው 446 ሺህ 495 ውስጥ 296 ሺህ 963 አዲስ ደንበኞችን በማገናኘት የእቅዱን 66 ነጥብ 5 በመቶ አሳክቷል። ይህም ካለፈው በጀት አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ30 ነጥብ 66 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡

በዘጠኝ ወሩ የአገልግሎቱ አዳዲስ ደንበኞች መካከል 94 በመቶው የድህረ ክፍያ ተጠቃሚ ደንበኞች ሲሆኑ ቀሪ 6 በመቶ ያህሉ የቅድመ ክፍያ ተተቃሚ ደንበኞች ናቸው፡፡

በተጨማሪ ከዚህ በፊት የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ያልነበሩ አዳዲስ የገጠር መንደሮችና ከተሞችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ በዘጠኝ ወራት ውስጥ 63 የገጠር ከተሞችና መንደሮችን ተጠቃሚ ለማድረግ ታቅዶ 66 በማከናወን 104.76 በመቶ አፈፃፀም ተመዝግቧል፡፡

በሌላ በኩል የገጠር ከተሞችና መንደሮች 661.804 ኪ.ሜ የመካከለኛ እና 1098.22 ኪ.ሜ የዝቅተኛ መስመር እንዲሁም 66 ትራንስፎርመሮች የመትከል ስራ ተሰርቷል፡፡

እንደ ተቋም እስከ መጋቢተ 30 ቀን 2016 ዓ.ም. በተከናወነው ስራ የተቋሙን ጠቅላላ የደንበኞች ቁጥር ወደ 4 ሚሊን 649 ሺህ 90 ማሳደግ ተችሏል፡፡ ከዚህም ውስጥ 3 ሚሊየን 756 ሺህ 454 የድህረ ክፍያ ደንበኞች ሲሆኑ ቀሪዎቹ 892 ሺህ 636 ደግሞ የቅድመ ክፍያ ኃይል ተጠቃሚ ደንበኞች ናቸው፡፡

ምንጭ ፡ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት

በተጨማሪም የቪዲዮና ሌሎች መረጃዎቻችንን ለማግኘት የትክክለኛ አድራሻዎቻችን አባል በመሆን ይከታተሉ፡-
ዩቲዩብ- https://www.youtube.com/southradioandtelevisionagency
ቴሌግራም -https://t.me/southRadioAndTelevisionAgency
ዌብ ሳይት - https://srta.gov.et/
ትዊተር - https://twitter.com/SouthRadioandTv

ከ2011 ዓ.መ. ማህደራችን ለትውስታ
19/04/2024

ከ2011 ዓ.መ. ማህደራችን ለትውስታ

ከ2011 ዓ.መ. ማህደራችን ለትውስታ #ደሬቴድ የቪዲዮና ሌሎች መረጃዎቻችንን ለማግኘት የትክክለኛዎቹ አድራሻዎቻችን አባል በመሆን ይከታተሉ፡...

ከመማር ማስተማርና ከቴክኖሎጂ ሽግግር ባሻገር ገቢ በሚያስገኙ የግብርና ዘርፎች ላይ በመሰማራት የገቢ አቅሜን ለማሳደግ እየሰራሁ ነው - የሰላምበር ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ሀዋሳ፡...
19/04/2024

ከመማር ማስተማርና ከቴክኖሎጂ ሽግግር ባሻገር ገቢ በሚያስገኙ የግብርና ዘርፎች ላይ በመሰማራት የገቢ አቅሜን ለማሳደግ እየሰራሁ ነው - የሰላምበር ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ

ሀዋሳ፡ ሚያዝያ 11/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) ከመማር ማስተማርና ከቴክኖሎጂ ሽግግር ባሻገር ገቢ በሚያስገኙ የግብርና ዘርፎች ላይ በመሰማራት የገቢ አቅሙን ለማሳደግ እየሰራ እንዳለ የሰላምበር ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ አስታወቀ።

ኮሌጁ በ10 ሔክታር መሬት የተለያዩ ሰብሎችን በማልማት የሚስተዋሉ ክፍተቶችን በመሸፈን አቅሙን ለማሳደግ እየሰራ እንዳለም ተገልጿል።

የሰላምበር ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ከመማር ማስተማር፣ ከቴክኖሎጂ ሽግግር ባሻገር የውስጥ ገቢን ለማሳደግ ተስፋ ሰጪ ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ የገለፁት የሰላምበር ኢንዱስትሪና ኮንስትራክሽን ኮሌጅ ም/ዲን አቶ መኮንን ካባ ናቸው።

ለኢንተርፕራይዞች አጫጭር ስልጠናዎችን በመስጠት ከኢኮኖሚ ጥገኝነት ለመላቀቅ የሚያደርጉትን ጥረት እየደገፍን እንገኛለንም ሲሉ አክለዋል።

ሰልጣኝ መብራት ገዝሙ እና ጥሩነህ በየነ በሰላምበር ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ የሰርቨይንግ ዲፓርትመንት ተማሪ ሲሆኑ በኮሌጁ ከሚሰጠው ስልጠና ጎን ለጎን በጓሮ አትክልት ልማት ላይ በመሳተፍ የውስጥ አቅምን ለማሳደግ የሚደረገውን ጥረት እየደገፉ እንዳለ ገልፀዋል።

ከተረከበው 10 ሔክታር መሬት 6 ሔክታሩን በበቆሎ ሰብል መሸፈኑን ተናግረው በ 4 ሔክታ መሬት ላይም የጓሮ አትክልት ጨምሮ ቋሚ ሰብሎችን በማምረት ላይ እንደሚገኙ ጠቁመዋል።

በቀጣይም የንብ ማነብ፣ የዶሮ፣ የእንስሳት ድለባና እርባታ፣ የዓሳ እርባታ ስራዎችን ለመስራት እንቅስቃሴ መጀመሩን አብራርተዋል።

ኮሌጁ በ 12 የሙያ ዘርፎች ከደረጃ 1 እስከ 4 በግንቦት ወር በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ከደረጃ 1 እስከ 4 በቀን በማታ በሳምንት መጨረሻ የተማሩ 260 በላይ ተማሪዎችን እንደሚያስመርቅም ጠቁመዋል ዲኑ።

በ 6 ወራት ውስጥም ከጥቃቅን ገቢዎች ባሻገር ከ2 መቶ 93 ሺህ 65 ብር በላይ ገቢ መገኘቱ የገለፁት በኮሌጁ የልማት ዕቅድና ዝግጅት ባለሙያ አቶ ተፈሪ ካሎ ሲሆኑ በኮሌጁ የሚስተዋሉ ችግሮችን በመፍታት ከኢኮኖሚ ጥገኝነት ለመላቀቅ እየሰራ ይገኛልም ብለዋል።

ዘጋቢ፡ ተመኙህ ገረሱ - ከአርባምንጭ ጣቢያችን

በተጨማሪም የቪዲዮና ሌሎች መረጃዎቻችንን ለማግኘት የትክክለኛ አድራሻዎቻችን አባል በመሆን ይከታተሉ፡-
ዩቲዩብ- https://www.youtube.com/southradioandtelevisionagency
ቴሌግራም -https://t.me/southRadioAndTelevisionAgency
ዌብ ሳይት - https://srta.gov.et/
ትዊተር - https://twitter.com/SouthRadioandTv

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልልን የሰላምና የመቻቻል ተምሳሌት ለማድረግ እየተሰራ እንደሚገኝ የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች  ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሰናይት ሰለሞን ገለፁበሳምንቱ በክልሉ የተከናወኑ ተ...
19/04/2024

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልልን የሰላምና የመቻቻል ተምሳሌት ለማድረግ እየተሰራ እንደሚገኝ የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሰናይት ሰለሞን ገለፁ

በሳምንቱ በክልሉ የተከናወኑ ተግባራትን አስመልክተው ማብራሪያ የሰጡት ኃላፊዋ ክልሉን የሰላምና የመቻቻል ተምሳሌት ለማድረግ የክልሉ መንግስት የፀጥታ ሪፎርም ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የክልሉን ፀጥታ ለማጠናከር በሳምንቱ 1035 የፖሊስ መኮንኖችን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር በተገኙበት ማስመረቁን አስታውሰው ተጠናክሮ የሚቀጥል ተግባር መሆኑንም ገልጸዋል።

የተመረቁ የፖሊስ መኮንኖችም ለክልላዊ ሰላም ትልቅ ድርሻ እንዳላቸዉ ተናግረዋል።

እንደሀገር የተጀመረዉ የአረንጓዴ አሻራ ተግባር ተጠናክሮ በክልሉ መቀጠሉን ያነሱት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሰናይት ሰለሞን በተለይ እያንዳንዱ ዞን አንድ ተራራ እንዲያለማ በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እንሸቲቭ በሳምንቱ ዞኖች ከክልሉ መንግስት ጋር ተፈራርመዉ ወደ ተግባር መግባታቸዉን አብራርተዋል።

በክልሉ የሚገኘው የኦሞ ኩራዝ ስኳር ፋብሪካዎች የክልሉ ትልቅ ፀጋና ግዙፍ ሀገራዊ ፕሮጀክት ነዉ ያሉት ኃላፊዋ የፕሮጀክቱን አቅም ይበልጥ ለመጠቀም የክልሉ መንግስት ርዕሰ መስተዳድሩ በተገኙበት ከኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ፣ የደቡብ ኦሞ ዞን አመራሮች ጋር በአርባምንጭ ከተማ ውይይት መደረጉን አስታውቀዋል።

ፕሮጀክቶቹ ለስራ ዕድል ፈጠራ፣ ለአከባቢዉ ህብረተሰብ ተጠቃሚነትና ለቴክኖሎጂ ሽግግር ያለዉ ፋይዳ ከፍተኛ በመሆኑ በአከባቢዉ የሚስተዋሉ የፀጥታና ሌሎች ችግሮችን ለመፍታት ያለመ ውይይት መሆኑን ገልፀዋል።

ሚዲያ ትልቅ አቅም በመሆኑ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ኮርፖሬሽን ከክልሉ መንግስት ጋር ለመስራት በሳምንቱ ስምምነት መፈፀሙን አንስተዋል፡፡

በክልሉ ክህሎት መር የስራ ዕድል ፈጠራ ተግባራዊ ለማድረግ 209 ሚሊዮን ብር በመመደብ ከ36 ሺህ በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ተግባር በሳምንቱ መከናወኑን ገልጸዋል።

ዘጋቢ፡ ድልነሳዉ ታደሰ

“ከጉራጌ ዞን ወጣቶች ጋር ዛሬ ያካሄድነዉ የዉይይት መድረክ ሚዛናዊና ምክንያታዊ ወጣት የመገንባቱ ሂደት በበቂና ተከታታይ የስብዕና ግንባታ ሥራ ከተገዘ በመደመር እሳቤ የታነፀ ትዉልድ እና ሀ...
19/04/2024

“ከጉራጌ ዞን ወጣቶች ጋር ዛሬ ያካሄድነዉ የዉይይት መድረክ ሚዛናዊና ምክንያታዊ ወጣት የመገንባቱ ሂደት በበቂና ተከታታይ የስብዕና ግንባታ ሥራ ከተገዘ በመደመር እሳቤ የታነፀ ትዉልድ እና ሀገር የመገንባቱ ሂደት የተሳካ እንደሚሆን አመላካች ነዉ።“ - የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንደሻው ጣሰው ።

በተጨማሪም የቪዲዮና ሌሎች መረጃዎቻችንን ለማግኘት የትክክለኛ አድራሻዎቻችን አባል በመሆን ይከታተሉ፡-
ዩቲዩብ- https://www.youtube.com/southradioandtelevisionagency
ቴሌግራም -https://t.me/southRadioAndTelevisionAgency
ዌብ ሳይት - https://srta.gov.et/
ትዊተር - https://twitter.com/SouthRadioandTv

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ በ2017 የትምህርት ዘመን የሙያ ትምህርት የሚሰጥባቸውን የሙያ አይነቶች ይፋ አደረገሀዋሳ፡ ሚያዝያ 11/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ )  ቢሮው በክልሉ ከ...
19/04/2024

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ በ2017 የትምህርት ዘመን የሙያ ትምህርት የሚሰጥባቸውን የሙያ አይነቶች ይፋ አደረገ

ሀዋሳ፡ ሚያዝያ 11/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ ) ቢሮው በክልሉ ከቀለም ትምህርት ጎን ኑጎን ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የሙያ ትምህርት በ2017 የትምሀርት ዘመን መስጠት እንደሚጀምር አስታውቋል።

የሙያ ትምህርቱ በ12 የሙያ አይነቶች የሚሰጥ ሲሆን፣ የትግበራው ዝግጅት ተጠናቆ በቀጣዩ የትምህርት ዘመን ትግበራው እንደሚጀምርም ተገልጿል።

ምክትል ርዕሰ መስተዳድር፣ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምሀርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አንተነህ ፍቃዱ የሙያ ትምህርት ተማሪዎች የፈጠራ ክህሎታቸውን በማጎልበት ፍላጎታቸውን ያማከለ ስራ እንዲሰሩ ያስችላቸዋል ብለዋል።

የሙያ ትምህርቶች በ2017 የትምህርት ዘመን ወደ ትግበራ የሚገባ መሆኑን የጠቁሙት አቶ አንተነህ የሚሰጡት የሙያ ትምህርቶች የአካባቢውን የተፈጥሮ ፀጋ፣ የተማሪውን ፍላጎት፣ የሠው ኃይልና የግበዓት አቅርቦትን ማዕከል ባደረገ መልኩ የሚሰጡ መሆኑን ተናግረዋል።

እንደ አቶ አንተነህ ገለፃ በክልሉ በሁለተኛ ደረጃ ትምህርቶች በተፈጥሮ ሳይንስ በ7 የሙያ አይነቶች እና በማህበራዊ ሳይንስ ደግሞ በ5 የሙያ አይነቶች ትምህርቱ ይሰጣል።

በዚህ መሰረትም:-
-በተፈጥሮ ሳይንስ

1.የእንጨት ስራ ቴክኖሎጂ
2 ፊኒሺንግ ኮንስትራክሽን ስራ
3 ዌብ ዲዛይን እና ዴቬሎፕመንት
4 ኮምፒውተር ጥገናና ስራ
5 አኒማል ፕሮዳክሽን
6 ተፈጥሯዊ ሀብት አስተዳደር
7 ማህበረሰብ ጤና

- በማህበራዊ ሳይንስ:-
1 ጆርናሊዝም
2 ስነ ልቦናዊ ክብካቤ
3 አካውንቲንግ እና ፋይናንስ
4 ማርኬቲንግ እና ሽያጭ አስተዳደር
5 ቮካል ፐርፎርማንስ እና ዳንስ መሆናቸውንም ገልፀዋል።

እንደ ሀገር በ40 የሙያ አይነቶች ትምህርቱ የሚሰጥ ሲሆን፣ በክልሉ በ12 አይነት የሙያ ትምህርቶች የሚጀመረው የሙያ ትምህርት እንደየ ተማሪዎች ፍላጎት በቀጣይ ተጨማሪ የሙያ አይነቶች እንደሚካተቱም ከክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በተጨማሪም የቪዲዮና ሌሎች መረጃዎቻችንን ለማግኘት የትክክለኛ አድራሻዎቻችን አባል በመሆን ይከታተሉ፡-
ዩቲዩብ- https://www.youtube.com/southradioandtelevisionagency
ቴሌግራም -https://t.me/southRadioAndTelevisionAgency
ዌብ ሳይት - https://srta.gov.et/
ትዊተር - https://twitter.com/SouthRadioandTv

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመሆን በአፍላ ወጣቶችና በወጣቶች ስነ ተዋልዶ ጤና ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በአርባምንጭ ከተማ ሰጥቷል1/3ኛው እንደ ሀገራችን...
19/04/2024

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመሆን በአፍላ ወጣቶችና በወጣቶች ስነ ተዋልዶ ጤና ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በአርባምንጭ ከተማ ሰጥቷል

1/3ኛው እንደ ሀገራችን የወጣቱ ክፍል መሆኑን መረጃዎች ያመላክታሉ።

መድረኩን በንግግር የከፈቱት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የእናቶችና ሕፃናት ጤናና ስርዓተ ምግብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ መሪሁን ገብሬ፤ የአፍላ ወጣቶችና የወጣቶች ጤና አገልግሎትን በተመለከተ እየተሠሩ ያሉ ተግባራትን አባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት መገምገምና ያሉ ማነቆዎችን በመለየት እየሰራን እንገኛለን ብለዋል።

በዚህም ወጣቶቹ የተሟላ የስነ ተዋልዶ ጤና መረጃ እንዲኖራቸው መንግስት እስትራቴጂ ቀርፆ እየሰራ እንደሚገኝም ጠቁመዋል አቶ መሪሁን።

ዘጋቢ: ፀሐይ ጎበና - ከአርባ ምንጭ ጣቢያችን

በተጨማሪም የቪዲዮና ሌሎች መረጃዎቻችንን ለማግኘት የትክክለኛ አድራሻዎቻችን አባል በመሆን ይከታተሉ፡-
ዩቲዩብ- https://www.youtube.com/southradioandtelevisionagency
ቴሌግራም -https://t.me/southRadioAndTelevisionAgency
ዌብ ሳይት - https://srta.gov.et/
ትዊተር - https://twitter.com/SouthRadioandTv

በኢፌዴሪ የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ደኤታ በዶ/ር ተሻለ በሬቻ የተመራ የሱፐርቪዥን ቡድን በቡታጅራ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ  የመስክ ምልከታ እያደረገ ነዉ  ሀዋሳ፡ ሚያዝያ 11/2016 ዓ...
19/04/2024

በኢፌዴሪ የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ደኤታ በዶ/ር ተሻለ በሬቻ የተመራ የሱፐርቪዥን ቡድን በቡታጅራ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የመስክ ምልከታ እያደረገ ነዉ

ሀዋሳ፡ ሚያዝያ 11/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ ) በኢፌዴሪ የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ደኤታ በዶ/ር ተሻለ በሬቻ የተመራ የፌደራል፣የክልልና የዞን አመራሮች ቡድን በቡታጅራ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በመገኘት የመስክ ምልከታ አድርጓል።

በመስክ ምልከታው የቡታጅራ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ አብዱልዋሂድ መሀመድ ለሱፐርቪዥን ቡንድ በኮሌጁ ዋና ዋና ተግባራት ላይ ማብራሪያ አቅርበዋል።

ኮሌጁ ከፍተኛ የሰው ሃይል በረጅምና አጫጭር ስልጠናዎች በማብቃት በሀገር ውስጥም ሆነ በሀገር ውጭ የስራ ዕድል እንዲያገኙ ለማድረግ ጥረት የተደረገበትና ውጤቶች የመጡ መሆኑ አንስተዋል።

ሰልጣኞች ከተቀጣሪነት ይልቅ በስራ ፈጠራ ተግባራት እንዲሰማሩ በተለያዩ ዘርፎች የክህሎት መር ስልጠናዎችን መሰጠቱን አመላክተዋል።

አሁን ካለበት የፖሊ ቴክኒክ ኮሎጅነት ወደ ፖሊ ቴክኒክ ኮሎጅና ሳተላይት ኢንስቲትዩት ለማሳደግ አቅደው እየሰሩ እንደሚገኙ ለሱፐርቪዥን ቡድን ገልፀዋል።

ምንጭ፡ የምስራቅ ጉራጌ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።



በተጨማሪም የቪዲዮና ሌሎች መረጃዎቻችንን ለማግኘት የትክክለኛ አድራሻዎቻችን አባል በመሆን ይከታተሉ፡-
ዩቲዩብ- https://www.youtube.com/southradioandtelevisionagency
ቴሌግራም -https://t.me/southRadioAndTelevisionAgency
ዌብ ሳይት - https://srta.gov.et/
ትዊተር - https://twitter.com/SouthRadioandTv

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ስታርት አፕ ኢትዮጵያ አውደ ርዕይን ጎበኙ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በሳይንስ ሙዚየም የተከፈተውን ስታርት አፕ ኢትዮጵያ አውደ ርዕ...
19/04/2024

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ስታርት አፕ ኢትዮጵያ አውደ ርዕይን ጎበኙ

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በሳይንስ ሙዚየም የተከፈተውን ስታርት አፕ ኢትዮጵያ አውደ ርዕይን ጎበኙ።

በጉብኝቱ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ወርቁ ጋቸና ተገኝተዋል።

በአውደ ርዕዩ በመጀመሪያ ደረጃ በምርት ሙከራና ምርት ወደ ገበያ ማቅረብ የጀመሩ ስታርት አፖች በመሳተፍ ላይ ናቸው ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

መጋቢት 30/2016 ዓ.ም የተከፈተው ስታርት አፕ አውደርዕይ እስከ ሚያዚያ 20 ለህዝብ ዕይታ ክፍት ሆኖ ይቆያል።

በተጨማሪም የቪዲዮና ሌሎች መረጃዎቻችንን ለማግኘት የትክክለኛ አድራሻዎቻችን አባል በመሆን ይከታተሉ፡-
ዩቲዩብ- https://www.youtube.com/southradioandtelevisionagency
ቴሌግራም -https://t.me/southRadioAndTelevisionAgency
ዌብ ሳይት - https://srta.gov.et/
ትዊተር - https://twitter.com/SouthRadioandTv

በየወሩ የሚካሄደው የግንዛቤ ማስጨበጫ ሴሚናር አካል የሆነ እና የኮሚሽኑ ሰራተኞችን እና አመራሮች በተለይም ክሪፕቶ ከረንሲ እና የክሪፕቶ ከረንሲ ማይኒንግ ኢንቨስትመንት ለሀገራችን የሚያመጣቸ...
19/04/2024

በየወሩ የሚካሄደው የግንዛቤ ማስጨበጫ ሴሚናር አካል የሆነ እና የኮሚሽኑ ሰራተኞችን እና አመራሮች በተለይም ክሪፕቶ ከረንሲ እና የክሪፕቶ ከረንሲ ማይኒንግ ኢንቨስትመንት ለሀገራችን የሚያመጣቸው ዕድሎች እና ተግዳሮቶች ላይ ያተኮረ መድረክ ተካሄደ

ሀዋሳ፡ ሚያዝያ 11/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) በየወሩ የሚካሄደው የግንዛቤ ማስጨበጫ ሴሚናር አካል የሆነ እና የኮምሽኑ ሰራተኞችን እና አመራሮች በተለይም ክሪፕቶ ከረንሲ እና የክሪፕቶ ከረንሲ ማይኒንግ ኢንቨስትመንት ለሀገራችን የሚያመጣቸው ዕድሎች እና ተግዳሮቶች ላይ ያተኮረ መድረክ ተካሂዷል፡፡

በመድረኩ የብሄራዊ መታወቂያ ዋና ዳይሬክተር ዮዳሄ ዘሚካኤል በክሪፕቶ ከረንሲ እንዲሁም የክሪፕቶ ከረንሲ ማይኒንግ ኢንቨስትመንት ለሀገራችን በሚኖራቸው አወንታዊ እና አሉታዊ ጎኖች እንዲሁም በኢንቨስትመንት ዘርፉ ውስጥ ሊኖራቸው በሚችለው ጉልህ ድርሻ እና በመጪ ጊዜያት አለም ላይ ሊያመጣ በሚችለው ተፅዕኖ ዙሪያ ለተሳታፊዎች ሰፊ ማብራሪያን ሰጥተዋል፡፡ ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎችም ዝርዝር ምላሽን መስጠታቸውን የኢንቨስትመንት ኮሚሽን መረጃ ያመለክታል፡፡

በተጨማሪም የቪዲዮና ሌሎች መረጃዎቻችንን ለማግኘት የትክክለኛ አድራሻዎቻችን አባል በመሆን ይከታተሉ፡-
ዩቲዩብ- https://www.youtube.com/southradioandtelevisionagency
ቴሌግራም -https://t.me/southRadioAndTelevisionAgency
ዌብ ሳይት - https://srta.gov.et/
ትዊተር - https://twitter.com/SouthRadioandTv

በኮሬ ዞን ኬሌ ከተማ አስተዳደር "አንድ መጽሐፍ ለልጄ፣ ለእህቴ፣ ለወንድሜ" በሚል መሪ ቃል የማህበረሰብ ንቅናቄ መድረክ ተካሄደበመድረኩ 6 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር ለመጽሐፍ ህትመት እንደሚያስ...
19/04/2024

በኮሬ ዞን ኬሌ ከተማ አስተዳደር "አንድ መጽሐፍ ለልጄ፣ ለእህቴ፣ ለወንድሜ" በሚል መሪ ቃል የማህበረሰብ ንቅናቄ መድረክ ተካሄደ

በመድረኩ 6 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር ለመጽሐፍ ህትመት እንደሚያስፈልግ ተገልጿል።

የንቅናቄውን መድረክ በንግግር የከፈቱት የኮሬ ዞን ኬሌ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ዮሐንስ ሀይሉ ጥራት ያለውን ትምህርት ለዜጎች በማቅረብ የተማረ የሰው ኃይል በብዛትና በጥራት ማፍራት ለአንድ ሀገር እድገት ቁልፍ መሣሪያ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ለተማሪ ውጤት ስብራት በምክንያትነት የሚጠቀሱ በርካታ ችግሮች ቢኖሩም የተማሪ መጽሐፍ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ነው ብለዋል ፡፡

የትምህርት ሥራ ለአንድ አካል የሚተው አይደለም ያሉት ከንቲባው የመንግሥት አቅም የሆነው ህብረተሰብ፣ ለመጽሐፍ ተደራሽነት የድርሻቸውን እንዲወጣ ጠይቀዋል።

የኬሌ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቤቶች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ባይዛር ባንድራ የህብረተሰቡ ተሳትፎ እና ትኩረት፣ ለተማሪ ውጤትና ስነምግባር መሻሻል ጉልህ ድርሻ አለው ብለዋል።

የተማሪ መማሪያ መጽሐፍ አለመኖር በውጤቱ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እንዳለው የገለጹ ሲሆን ከሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ለመጽሐፍ ህትመት ወጪ የሚውል ገንዘብ እንደሚሰበሰብና የማሰባሰብ ሂደቱን ለህብረተሰቡ ግልጽ እንደሚያደርጉ አስረድተዋል።

ከተሳታፊዎች መካከል አቶ ተማሙ ጀማልና ጆኒ ከበደ በሰጡት አስተያየት አቅማቸው የፈቀደውን ያህል ለተማሪ መጽሐፍ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።

መምህር ተሻለ ተስፋዬ፣ መምህር ሽብሩ ሳህሉ እና ሌሎችም በበኩላቸው፣ ያለ መጽሐፍ ማስተማርና ውጤት ማስመዘገብ እንደማይቻል አስታውሰው የተማሪ መማሪያ መጽሐፍ ማሳተም ትውልድን የማዳን ጉዳይ እንደሆነ ተናግረዋል።

ዘጋቢ: ምርጫ መላኩ - ከይርጋ ጨፌ ጣቢያችን

በህብረተሰብ ኑሮ ማሻሻያ ላይ የሚሰሩ ፕሮግራሞችን በማስፋፋትና በመደገፍ ለህብረተሰቡ ተጨባጭ ለውጥ መስራት ያስፈልጋል-ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መ...
19/04/2024

በህብረተሰብ ኑሮ ማሻሻያ ላይ የሚሰሩ ፕሮግራሞችን በማስፋፋትና በመደገፍ ለህብረተሰቡ ተጨባጭ ለውጥ መስራት ያስፈልጋል-ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግሥት ደን፣አካባቢ ጥበቃና አየር ንብረት ለውጥ ቢሮ ክልላዊ የREDD+ ምዕራፍ ሁለት ማስጀመሪያ መድረክና ስትሪንግ ኮሚቴ ውይይት በቦንጋ ከተማ ተካሂዷል።

በክልሉ በ29 ወረዳዎች REDD+ የህብረተሰብ ኑሮ ማሻሻያ ፕሮግራም በመጀመሪያው ምዕራፍ ያከናወናቸው አፈፃፀም ግምገማና የምዕራፍ ሁለት ማስጀመሪያ ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሂዷል።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ በመድረኩ እንደገለጹት፤ በክልሉ በህብረተሰብ ኑሮ ማሻሻያ ላይ የሚሰሩ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን በማስፋፋትና በመደገፍ ለህብረተሰቡ ተጨባጭ ለዉጥ ለማምጣት በትኩረት መስራት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።

በክልሉ በሁሉም ዞኖች መጠኑ ቢለያይም በስፋት የደን ሀብት ይገኛል ያሉት ርዕሰ መስተዳደሩ ተፈጥሮን ለዘመናት ጠብቆ ያቆዩ ህዝቦችን የሀብቱ ተቋዳሽና ተጠቃሚ በማድረግ ላይ የሚታዩ የአሰራር ክፍተቶችን ለማስተካከል እንደሚሰራ አስገንዝበዋል።

በክልሉ በ29 ወረዳዎች በፕሮግራሙ ተጀምሮ የተመዘገቡ ምርጥ ተሞክሮችን በመቀመር ክፍተቶችን ማረም ይጠበቃል ያሉት ርዕሰ መስተደድሩ የክልሉ መንግስት በሚከናወኑ ተግባራት በህብረተሰቡ ህይወት ተጨባጭ ለውጥ እንዲያመጣ አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል።

የወጣቶችና የሴቶች አደረጃጀቶችን በህብረት ስራ ማህበር በኩል በማጠናከር የህብረተብ ኑሮ መቀየር በሚችልባቸው በሌማት ትሩፋትና በሌሎች በግብርና ስራዎች እንዲሁም በአረንጓዴ አሻራ ላይ በማተኮር ስፊ ለስራ ዕድል ፈጠራና ለኢኮኖሚ ዕድገት በትኩረት እንደሚሰራም ገልጸዋል።

የክልሉ ደን፣አከባቢ ጥበቃና የአየር ንብረት ለውጥ ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ኢንጂነር አስራት ገ/ማሪያም ክልሉ በተፈጥሮ ሀብት ግንባር ቀደም የሀገራችን አካባቢዎች መካከል እንደሚጠቀስ ገልጸው ሀብቱን መሠረት አድርገው ከሚንቀሳቀሱ መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች የREDD+ ኑሮ ማሻሻያ ፕሮግራም አንዱ ነው።

የREDD+ፕሮግራም በክልላችን በ29 ወረዳዎችበኖርዌይ መንግስት ድጋፍ በዚህ ዓመት ከ311 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት በተፈጥሮ ጥበቃ ልማት እና የማህበረሰብ ኑሮ ማሻሻያ በርካታ ተግባራትን ሲያከናዉን መቆየቱንም ጠቁመዋል።

ዶ/ር ኢንጂነር አስራት ገ/ማሪያም ተግባሩ በመንግሥት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተከናወነ ላለው ለአረንጓዴ አሻራ እና ለሌማት ትሩፋት ስራዎች ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑንም ተናግረዋል።
በREDD+ ፕሮግራም 281ሺ 6መቶ 41.1 ሄ/ር ደን በማከላል በ214 የደን አስተዳደር ከ33 ሺ 9መቶ በላይ ማህበረሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ መድረጉንና በፕሮግራሙ በታቀፉ ወረዳዎች 111 የችግኝ ጣቢያዎች መቋቋማቸውን ዶ/ር ኢንጂነር አስራት ገ/ማሪያም በመግለፅ ።

የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው በክልሉ በህብረተሰብ ኑሮ ማሻሻያ ፕሮግራም እየተሰሩ የሚገኙ ስራዎች እንዲጠናከሩና ወደ ሌሎች እንዲስፋፉ አመልክቷል።

የተፈጥሮ ሀብቶችን መጠበቅ፣መንከባከብ እንዲሁም ባልተገባ መንገድ በደኑ ላይ የሚደርሰውን አደጋዎችን ለማስቆም ሁሉም እንዲረባረብና የበኩላቸውን ሚና እንደሚወጡም ተሳታፊዎች ማንሳታቸውን ከክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በመድረኩ ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ፣ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸዉን ጨምሮ የስትሪንግ ኮሚቴ አባላትና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።

በተጨማሪም የቪዲዮና ሌሎች መረጃዎቻችንን ለማግኘት የትክክለኛ አድራሻዎቻችን አባል በመሆን ይከታተሉ፡-
ዩቲዩብ- https://www.youtube.com/southradioandtelevisionagency
ቴሌግራም -https://t.me/southRadioAndTelevisionAgency
ዌብ ሳይት - https://srta.gov.et/
ትዊተር - https://twitter.com/SouthRadioandTv

የመካከለኛው ምሥራቅ ቀጣና ችግሮች እንዲፈቱ ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በትብብር ትሰራለችኢትዮጵያ የመካከለኛው ምሥራቅ ቀጣና ችግሮች እንዲፈቱ ከወዳጅ አገራትና ከዓለም አቀፍ ተቋማት...
19/04/2024

የመካከለኛው ምሥራቅ ቀጣና ችግሮች እንዲፈቱ ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በትብብር ትሰራለች

ኢትዮጵያ የመካከለኛው ምሥራቅ ቀጣና ችግሮች እንዲፈቱ ከወዳጅ አገራትና ከዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በትብብር እንደምትሰራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለፀ።

በሰላም ዕጦት ውስጥ ያሉ የአፍሪካ ቀንድ አገራት ሰላምና መረጋጋት እንዲረጋገጥም አበክራ እንደምትሰራም ገልጿል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ፣ ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተለዋዋጭ በሆነው ዓለም ኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሟንና ፍላጎቷን መሰረት ያደረገ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲን ታራምዳለች።

'የኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ አልፋና ኦሜጋ ብሔራዊ ጥቅም ነው' ያሉት አምባሳደሩ፣ ዲፕሎማሲው ከሀገር ሰላም፣ ልማትና ደህንነት አኳያ ታሳቢ ያደረገ መሆኑን ነው ያነሱት። በዚህም በተለዋዋጩ ዓለም ውስጥ ኢትዮጵያ የምትወስዳቸው አቋሞች ከራሷ ብሔራዊ ጥቅም አኳያ መዝና እንደሆነ አንስተዋል።

ኢትዮጵያ ከመካከለኛው ምስራቅ ጋር ካላት መልክዓ ምድራዊና የህዝብ ለህዝብ ትስስር አኳያ የቀጣናው ቀውስና መረበሽ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም ቀጥተኛ አንድምታ እንዳለው ተናግረዋል።

በዚህም የቀጣናው ችግሮች እንዲፈቱና ኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅሞች እንዲከበሩ ከአጋር አገራት እና ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በትብብር እንደምትሰራ ገልፀዋል።

በተመሳሳይ ኢትዮጵያ በውጭ ጉዳይ ፖሊሲዋ ለጎረቤት ሀገራት ቀዳሚ ትኩረት እንደምትሰጥ ገልፀው፣ በተለይም የጎረቤት አገራት ቀውስ ለኢትዮጵያ እንደሚተርፍ ተናግረዋል።

በዚህም በሰላም ዕጦት ለሚቸገሩ ጎረቤት አገራት ሰላምና መረጋጋት እንዲፈጠር በታሪክ የነበራትን የሰላም ማስከበር ሚና አጠናክራ ትቀጥላለች ብለዋል።

ከሰላምና ደህንነት ጉዳዮች ባሻገርም ኢትዮጵያ በቀጣናው ኢኮኖሚያዊ ትስስር ለመፍጠር የሚያስችል የዲፕሎማሲ ስራዎችን ማከናወኗን ገልጸዋል።

የባሕር በርን ጨምሮ ፀጋዎችን አልምቶ በጋራ በመጠቀምና የመሰረተ ልማትና ንግድ ትስስር በማጎልበት የጋራ ዕድገትን ማረጋገጥና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ማጠናከር የሚያስችሉ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ተናግረዋል።

በተጨማሪም የቪዲዮና ሌሎች መረጃዎቻችንን ለማግኘት የትክክለኛ አድራሻዎቻችን አባል በመሆን ይከታተሉ፡-
ዩቲዩብ- https://www.youtube.com/southradioandtelevisionagency
ቴሌግራም -https://t.me/southRadioAndTelevisionAgency
ዌብ ሳይት - https://srta.gov.et/
ትዊተር - https://twitter.com/SouthRadioandTv

ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ የተሽከርካሪ መገጣጠሚያ እና ማምረቻ ኢንዱስትሪ ግንባታ የመሰረተ ድንጋይ አስቀምጡሀዋሳ፡ ሚያዝያ 11/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ )   የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ...
19/04/2024

ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ የተሽከርካሪ መገጣጠሚያ እና ማምረቻ ኢንዱስትሪ ግንባታ የመሰረተ ድንጋይ አስቀምጡ

ሀዋሳ፡ ሚያዝያ 11/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ ) የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ የተሽከርካሪ መገጣጠሚያ እና ማምረቻ ኢንዱስትሪ ግንባታ የመሰረተ ድንጋይ አስቀምጡ።

የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ ከተመሰረተ በርካታ ዓመታትን ያሳለፈው የመከላከያ ኢንዱስትሪ ዘመኑ ከደረሰበት የዕድገት ደረጃ ለማድረስ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙ ገልፀው፣ የፋብሪካው ግንባታ ለሀገርና ለተቋሙ የሚሰጠው ጠቀሜታ ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል።

ኢንዱስትሪው በአዲስ መልኩ ከተደራጀ በኋላ በተሰሩት ስራዎች ከኪሳራ ወደ ትርፋማነት መሸጋገሩን የገለፁት ጠቅላይ ኤታማዦር ሹሙ የኮርፖሬሽኑ አመራርና አባላቶች ለነበራቸው ቁርጠኝነት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ተቋሙ የራሱን ገቢ በማመንጨት ለሰራዊቱ መሰረታዊ ጥቅም ለማሟላት አቅጣጫ ተቀምጦ እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።

ጠቅላይ ኤታማዦር ሹሙ የሰራዊቱን የመኖሪያ ቤት ባለቤት ለማድረግና ተጠቃሚነቱን ለማረጋገጥ በኢንዱስትሪ ፤ በግብርና ፣ በማዕድንና በመሰረተ ልማት ዝርጋታ ላይ ከተሰማሩ ባለሀብቶች ጋር ለመስራት የተቀመጠው አቅጣጫ ማሳያ መሆኑን ጠቁመዋል።

የመከላከያ ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ሀይለማርያም የመከላከያ የተሽከርካሪ መገጣጠሚያ እና ማምረቻ ኢንዱስትሪ ከሽርሽር ኢንቨስትመንት ግሩፕ ጋር በመሆን የሚገነባው መሆኑን ተናግረዋል።

ኢንዱስትሪው በሰላሳ ሄክታር ላይ የሚያርፍና በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ መታቀዱንም ዋና ዳይሬክተሩ ገልፀዋል።

አለም አቀፍ ስታንዳርዳቸውን ያሟሉ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎችን ከመገጣጠምና ከማምረት ባለፈ በቀጣይ ፕሮጀክቱን የማስፋፋት ዕቅድ እንዳላቸው የገለፁት ዳይሬክተሩ ለፕሮጀክቱ ስኬት ያልተቋረጠ ድጋፍና ክትትል እንደሚደረግም ጠቁመዋል።
በዝግጅቱ ላይ የመከላከያ ሚንስቴር ዲኤታ አቶ ቶማስ ቶት የቢሾፍቱ ከተማ ከንቲባ አቶ አለማየሁ አሰፋ ወታደራዊ አታሼዎችና ከፍተኛ የሰራዊቱ አመራሮች መገኘታቸውን የመከላከያ ሠራዊት መረጃ ያመለክታል።

በተጨማሪም የቪዲዮና ሌሎች መረጃዎቻችንን ለማግኘት የትክክለኛ አድራሻዎቻችን አባል በመሆን ይከታተሉ፡-
ዩቲዩብ- https://www.youtube.com/southradioandtelevisionagency
ቴሌግራም -https://t.me/southRadioAndTelevisionAgency
ዌብ ሳይት - https://srta.gov.et/
ትዊተር - https://twitter.com/SouthRadioandTv

የወል ትርክትን መገንባትና ሕብረ ብሔራዊ አንድነት ማጽናት ለጋራ ተጠቃሚነት ያለው ፋይዳ የጎላ መሆኑ ተገለጸሀዋሳ፡ ሚያዝያ 11/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) ህብረ-ብሄራዊ አንድነት ላይ የተመሰረ...
19/04/2024

የወል ትርክትን መገንባትና ሕብረ ብሔራዊ አንድነት ማጽናት ለጋራ ተጠቃሚነት ያለው ፋይዳ የጎላ መሆኑ ተገለጸ

ሀዋሳ፡ ሚያዝያ 11/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) ህብረ-ብሄራዊ አንድነት ላይ የተመሰረተ የወል ትርክት በመገንባት ሰላምን ማጽናትና የጋራ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ እንደሚገባ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንደሻው ጣሰው ተናገሩ።

የአገረ መንግስት ግንባታ ስራችን በቅብብሎሽ የሚሰራ ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፥ በነበሩት ላይ አዳዲስ ነገሮችን እየጨመርን እንጓዛለን ብለዋል።

የወል ትርክት የአንድን አገር ሕዝብ አብሮነት በማጠናከርና የጋራ አገራዊ አላማ ለመሰነቅ ትልቅ አስተዋጽኦ ያለውና የታሪክ ሁነቶችን የሚያስተሳስር መሆኑን አመላክተዋል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የመንግስት ረዳት ተጠሪ አቶ ይግለጡ አብዛ በበኩላቸው፥ ወጣቶች ከነጠላ ትርክት በመላቀቅ ሰላም እንዳይጸና፣ ልዩነትና ተቃርኖ እንዲበረታ ከሚያደርጉ አካላት እራሳቸውን በመቆጠብ ሊሠሩ እንደሚገባ መክረዋል።

የጉራጌ ህዝብ ከሌሎች የኢትዮጵያውያን ጋር ለውጥን በመሻት የታገለ መሆኑን አስታውሰው፥ በወል ትርክት አብሮነትና አንድነትን ማጠናከር እንጂ የዞኑ ወጣቶች ለከፋፋይ አጀንዳ ትኩረት መስጠት እንደሌለባቸው አሳስበዋል።

የጉራጌ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ በበኩላቸው ወጣቶች ለጋራ የህዝብ ተጠቃሚነት ያላቸውን ተቆርቋሪነት አድንቀው፥ ይኸው ጥረታቸው በሠላም ግንባታ ላይ አንድነትን በሚያጠናክሩ የወል እውነትን መሰረት ባደረገ መልኩ መስራት ይገባናል ብለዋል።

የውይይቱ ተሳታፊ ወጣቶች በበኩላቸው አሉ ያሏቸውን የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮች በዝርዝር አቅርበዋል።

በተለያዩ ምክንያቶች የተጀመረው የተቋረጡ የልማት ፕሮጀክቶች፣ የመንገድ መሠረተ ልማት ግንባታ መጓተት፣ የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ችግር፣ ስራ አጥነትና የስራ ዕድል ፈጠራ ውስንነት፣ የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር የወሰን መካለልና የተጓተቱ የልማት ስራዎች ምላሽ ሊያገኙ እንደሚገባ አንስተዋል።

ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ከመድረኩ ምላሽና ማብራሪያ የተሰጠባቸው ሲሆን፥ በቀረቡ የውይይትና የምክክር አጀንዳዎች ዙሪያ የጋራ መግባባትና ግንዛቤ በመጨበጥ መድረኩ ተጠናቋል።

ዘጋቢ፡ ዘላለም ተስፋዬ

በተጨማሪም የቪዲዮና ሌሎች መረጃዎቻችንን ለማግኘት የትክክለኛ አድራሻዎቻችን አባል በመሆን ይከታተሉ፡-
ዩቲዩብ- https://www.youtube.com/southradioandtelevisionagency
ቴሌግራም -https://t.me/southRadioAndTelevisionAgency
ዌብ ሳይት - https://srta.gov.et/
ትዊተር - https://twitter.com/SouthRadioandTv

የአምራች ዘርፉን ሊመራ የሚችል ወጥና ሁሉን አቀፍ የአምራች ዘርፍ ፖሊሲ በማውጣት ወደ ስራ ተገብቷል፡- አቶ መላኩ አለበልሀገሪቱ ያላትን ዕምቅ አቅም ለመጠቀም የሚያስችል፣ ከዘርፉ ተለዋዋጭ ...
19/04/2024

የአምራች ዘርፉን ሊመራ የሚችል ወጥና ሁሉን አቀፍ የአምራች ዘርፍ ፖሊሲ በማውጣት ወደ ስራ ተገብቷል፡- አቶ መላኩ አለበል

ሀገሪቱ ያላትን ዕምቅ አቅም ለመጠቀም የሚያስችል፣ ከዘርፉ ተለዋዋጭ ባህሪያት ጋር የተጣጣመ እንዲሁም የአምራች ዘርፉን ሊመራ የሚችል ወጥና ሁሉን አቀፍ የአምራች ዘርፍ ፖሊሲ በማውጣት ወደ ስራ መገባቱን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል ገለጹ።

በተሻሻለው አምራች ኢንዱስትሪ ፖሊሲ ዙሪያ ከሚኒስትር ዴኤታዎች እና ከፌዴራል ተቋማት ስራ ኃላፊዎች፣ ከአምራች ኢንዱስትሪ የዘርፍ ማህበራት አመራሮች ጋር የግንዛቤ መፍጠሪያ ውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው።

በ2022 ኢትዮጵያ በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ አፍሪካዊት የብልጽግና ተምሳሌት ሆና እንድትታይ እየተሰራ መሆኑን ሚኒስትሩ በመድረኩ ገልፀዋል።

በተሻሻለው ፖሊሲ በዋናነት ትኩረት ከተደረገባቸው መካከል ገበያ መር ፣ በግሉ ዘርፍ የሚመራ፣ ግልፅ የመንግስት ሚና የተቀመጠበት፣ የኢንዱስትሪ ክላስተር፣ ለወጪና ተኪ ምርት የተመጣጠነ ትኩረት የሰጠ እንዲሁም ለዘላቂ አምራች ኢንዱስትሪ ልማት እና የተጣጣመ የሕግ ማዕቀፍ እንዲሆን መድረጉን ጠቁመዋል።

የምርት ልማትና ተወዳዳሪነት ለማረጋገጥ የኢንዱስትሪ ክላስተር አሰራር የተከተለ፣ በተጠናከረ የግብዓት ምርት ልማት ትስስር የሚደገፍ፣ለወጪ ንግድና ለተኪ ምርት ልማትና ግብይት እንዲሁም ለምርት ጥራት ሥራ_አመራር ትኩረት የሚሰጥ የፖሊሲ መሆኑንም አክለው ተናግረዋል።

የሰው ኃብት ልማትና አስተዳደር ለማሳደግ በኢንዱስትሪ ባህል እና በሥራ አመራር ክህሎት የዳበረ የሰው ኃይል ማቅረብ ፣ የቀረበውን የሰው ምርታማነትን ማሳደግ የሚያስችል ማድረግ ያስፈልጋል ያሉት ሚኒስትሩ፤ ምርታማነትና ተወዳዳሪነት ለማሳደግ እና ወደ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የምርት ሥርዓት ለማሻገር እንደሚሰራ አስረድተዋል።

የፋይናንስ አቅርቦትና ተደራሽነት ለማድረግ የተጠናከረ የብድር አቅርቦት፣ የውጪ ምንዛሬ ፣ የመድን ሽፋን እና ባንክ-ነክ ያልሆኑ ሌሎች የፋይናንስ ምንጮችን ለመጠቀም ትኩረት መደረጉንም ገልጸዋል።
ማክሮ ኢኮኖሚና የቢዝነስ ሥነ- ምህዳር መነሻ በማድረግ የተረጋጋና ተገማች የማክሮ ኢኮኖሚና አስቻይ የቢዝነስ ሥነ- ምህዳር መፍጠር የሚያስችል መሆኑን አቶ መላኩ መናገራቸውን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

በከተሞች በተጀመረው ልማታዊ ሴፍትኔት ኘሮግራም አቅመ ደካማ ወገኖች የተሻለ ህይወት እንዲኖሩ ለማሰቻል በርካታ ሥራዎች እየተሠሩ መሆኑ ተገለጸሀዋሳ፡ ሚያዝያ 11/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) በከ...
19/04/2024

በከተሞች በተጀመረው ልማታዊ ሴፍትኔት ኘሮግራም አቅመ ደካማ ወገኖች የተሻለ ህይወት እንዲኖሩ ለማሰቻል በርካታ ሥራዎች እየተሠሩ መሆኑ ተገለጸ

ሀዋሳ፡ ሚያዝያ 11/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) በከተሞች በተጀመረው ልማታዊ ሴፍትኔት ኘሮግራም አቅመ ደካማ ወገኖች የተሻለ ህይወት እንዲኖሩ ለማሰቻል በርካታ ሥራዎች እየተሠሩ መሆኑን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳዮች ቢሮ አሰታወቀ፡፡

ቢሮው በከተማ ልማታዊ ሴፍትኔትና ሥራ ፕሮጀክት ዙሪያ የአቅም ግንባታ ስልጠና ለተለያዩ ባለድርሻ አካላት እየሰጠ ይገኛል፡፡

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳዮች ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ መርክነህ ዋልቶሬ ለስልጠና ተሣታፊዎቹ ባስተላለፉት መልዕክት፤ የከተማ ልማታዊ ሴፍትኔት ኘሮግራም በከተሞች በድህነት ውሰጥ ያሉ ወገኖችን ለመደገፍ ትኩረት ተሰጥቶ በተሠራው ሥራ ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት መቻሉን ተናግረዋል፡፡

በከተሞች ልማታዊ ሴፍትኔት መጀመር ቀጥተኛ ድጋፍ ተጠቃሚ የህብረተሰብ ክፍሎች በነፃ የጤና አገልግሎት፣ የትምህርትና የፍትህ ጥያቄ ያላቸው ወገኖች ተጠቃሚ መሆን እንደቻሉ አቶ መርክነህ ጨምረው ተናግረዋል፡፡

በክልሉ ከተሞች ልማታዊ ሴፍትኔት የተሠሩ ተግባራት ዙሪያ የተዘጋጀ ሰነድ ቀርቦ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡

ዘጋቢ፡ ተሰፋዬ ወ/ማርያም

በተጨማሪም የቪዲዮና ሌሎች መረጃዎቻችንን ለማግኘት የትክክለኛ አድራሻዎቻችን አባል በመሆን ይከታተሉ፡-
ዩቲዩብ- https://www.youtube.com/southradioandtelevisionagency
ቴሌግራም -https://t.me/southRadioAndTelevisionAgency
ዌብ ሳይት - https://srta.gov.et/
ትዊተር - https://twitter.com/SouthRadioandTv

የቀን 6፡00 ዜና 24፤ ሀዋሳ፡ ሚያዝያ 11/2016 ዓ.ም  #ደሬቴድ - ቀጥታ ስርጭት
19/04/2024

የቀን 6፡00 ዜና 24፤ ሀዋሳ፡ ሚያዝያ 11/2016 ዓ.ም

#ደሬቴድ - ቀጥታ ስርጭት

የቀን 6፡00 ዜና 24፤ ሀዋሳ፡ ሚያዝያ 11/2016 ዓ.ም #ደሬቴድ - ቀጥታ ስርጭት የቪዲዮና ሌሎች መረጃዎቻችንን ለማግኘት የትክክለኛዎቹ አድራ...

19/04/2024

የቀን 6፡00 ዜና 24፤ ሀዋሳ፡ ሚያዝያ 11/2016 ዓ.ም

#ደሬቴድ - ቀጥታ ስርጭት

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በኬኒያ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ህልፈት የተሰማቸውን ሃዘን ገለጹየጦር  ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የኬኒያ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛ...
19/04/2024

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በኬኒያ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ህልፈት የተሰማቸውን ሃዘን ገለጹ

የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የኬኒያ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ጀኔራል ፍራንሲስ ኦሞንዲ ኦጎላን ህልፈተ-ሕይወት በማስመልከት የኃዘን መግለጫ አስተላልፈዋል።

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ በሃዘን መግለጫቸው ጀኔራል ፍራንሲስ ኦሞንዲ ኦጎላ ለሀገራቸውና ለቀጣናው ሠላምና ደህንነት መረጋገጥ የነበራቸው አስተዋጽኦ ከፍተኛ እንደነበር አስታውቀዋል።

እሳቸውና ሌሎች ከፍተኛ መኮንኖችን ባጋጠመቸው የአውሮፕላን መከስከስ አደጋ ህይወታቸው በማለፉ በራሳቸውና በኢ.ፌ.ዲ.ሪ መከላከያ ሠራዊት ስም የተሰማቸውን ሃዘን ገልጸዋል።

ጀኔራል ፍራነኪስ ኦሞንዲ ኦጎላ ለኬኒያና ለቀጣናው ሰላምና መረጋጋት ላበረከቱት አስተዋጽኦና በጎ ሥራ ሁልጊዜ ሲታወሱ ይኖራሉ ያሉት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ በዚህ አስቸጋሪ ወቅት የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ከኬኒያ ወንድም ህዝቦች ጋር መሆኑን አስረድተዋል።

በአደጋው ሕይወታቸውን ላጡ መኮንኖች ቤተሰቦችና ወዳጆች በራሳቸውና በኢ.ፌ.ዲ.ሪ መከላከያ ሠራዊት ስም መጽናናትን ተመኝተዋል።(ኢዜአ)

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት ከኣሪ ዞን ሽግግር ምክር ቤት ጋር በመቀናጀት ለፍትህ ዘርፍ ሪፎርም የሚሆን ግብዓት ማሰባሰቢያ የህዝብ መድረክ እያካሄደ ነውሀዋሳ፡ ሚያዚያ 11/2016 ዓ....
19/04/2024

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት ከኣሪ ዞን ሽግግር ምክር ቤት ጋር በመቀናጀት ለፍትህ ዘርፍ ሪፎርም የሚሆን ግብዓት ማሰባሰቢያ የህዝብ መድረክ እያካሄደ ነው

ሀዋሳ፡ ሚያዚያ 11/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት ከኣሪ ዞን ሽግግር ምክር ቤት ጋር በመቀናጀት ለፍትህ ዘርፍ ሪፎርም የሚሆን ግብዓት ማሰባሰቢያ የህዝብ መድረክ እያካሄደ ነው።

የኣሪ ዞን ሽግግር ም/ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ስመኝ ተስፋዬ በመክፈቻ ንግግራቸው እንደገለፁት፤ የመድረኩ ዋና አላማ ከ3ቱ ህግ አስፈፃሚዎች የህግ ተርጓሚው ከፊል ላይ ባሉ አሰራሮች ዙሪያ ህገ-መንግስቱ ለዝህብ የሰጠውን ኃላፊነት በሚመለከትና በቀጣይ በዘርፉ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ከማድረግ አኳያ ማነቆዎችን ለመለየት ከተለያዮ ማህበረሰብ ክፍሎች ጋር ምክክር በማድረግ ለመፍታት ታስቦ የተዘጋጀ ነው።

የኣሪ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብርሃም አታ በንግግራቸው በሀገራችን ባለፉት ጊዜያት ከፍትህ ተቋማት ጋር በተያያዘ በብዙ መንገድ ለማህበረሰቡ አገልግሎት ሲስጡ የነበሩ ክፍተቶችና በአጠቃላይ በጥንካሬ ጎንም የሚወሰዱ ሰፋፊ የህግ ማዕቀፎች ያለበት ሀገር እንደመሆኑ የሚታዮ ክፍተቶችን በማረም ሀገርን በጋራ ለመገንባት መሰራት ያሰፈልጋል ብለዋል።

አክለውም ከማንነት ጋር የተያያዙ የተለያዮ ጉዳዮች የሚነሱበት ሀገር እንደመሆኑ ለአንድ ሀገር የተረጋጋ ኢኮኖሚና ሠላም የህግ ተቋማት የሚያደርጉት ሚና ከፍተኛ በመሆኑ ከህዝብ ተወካዮች ጋር ውይይት መደረጉ ወሳኝነት አለው ብለዋል።

የውይይት መነሻ ሰነድ በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት የህግ ጉዳዮች አማካሪ አቶ አዳነ ገበየሁ እየቀረበ ነው።

ከተሳታፊዎችም የተለያዩ ጥያቄና አስተያየቶች ቀርበው ሰፍ ውይይት ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።

ዘጋቢ: ከተማ በየነ - ከጂንካ ጣቢያችን

Address

Hawassa
Hawassa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when South Radio and Television Agency posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to South Radio and Television Agency:

Videos

Share