28/11/2023
የአባላዘር በሽታ
ክፍል 5
የአባላዘር በሽታ አይነቶች
8 HIV
ይህ ቫይረስ ሌላ በሽታ የመከላከል አቅማችንን የሚያዳክምና ለሌላ ቫይረስ፣ባክቴሪያ ወይም ለካንሰር የሚያጋልጥ ነው።
በሰአቱ ካልታከምነው ወደ 3ተኛ ደረጃ HIV ይቀየራል ይህም AIDS በመባል ይታወቃል ነገር ግን ባሁን ሰአት ባለው ህክምና አማካኝነት HIV ያለባቸው ሰዎች ወደ AIDS እንዳይቀየርባቸው ያደርጋል።
የዚህ ቫይረስ የመጀመሪያ ደረጃ ምልክቶቹ ከጉንፋን ምልክቶች ጋር ተመሳሳይነት አላቸው።
የመጀመርያ ደረጃ ምልክት የምንላቸው ፦
*ትኩሳት
*የመንቀጥቀጥ ስሜት
*ቁርጥማት
*የጉሮሮ መድረቅ
*ራስ ምታት
*ማቅለሽለሽ
እነዚህ ምልክቶች በወር ውስጥ ይጠፋሉ ከዛ ምንም አይነት አስጊ ምልክት ሳያሳዩ ለብዙ አመታት የዚህ ቫይረስ ተሸካሚ ሆነው ይቆያሉ ነገር ግን አንዳንድ ሰዎች ከዚህ በታች ያሉትን ምልክቶች ሊያሳዩ ይችላሉ
*ትኩሳት
*የሆድ ህመም
*ድግግሞሽ የበዛበት የድካም ስሜት
*ራስ ምታት
እስካሁን ድረስ ለዚህ በሽታ የሚሆን ማሻያ መድሀኒት አልተገኘም ነገርግን ወደከፋ ደረጃ እንዳይደርስ መቆጣጠርያ መንገዶች አሉት።
ወዲያውን ህክምና ከተደረገ HIV በደሙ ያለበት ሰው እንደ HIV በደሙ የሌለበት ሰው ረጅም እድሜ መኖር ይችላል።
አግባብ ያለው ህክምና ከተደረገ ቫይረሱን ወደሌላ ሰው እንዳይተላለፍ እንዲሁም በደም ውስጥ ያለውን የቫይረስ መጠን ለመቀነስ ይረዳናል።
አብዛኛው ሰው በደሙ ውስጥ ቫይረሱ እያለ ነገርግን ያሰው ሳያውቀው ሊቀር ይችላል በዚህም ምክንያት እድሜያቸው ከ 13-64 ያሉ ሰዎች ቢያንስ አንድ ጊዜ ምርመራ ቢያደርጉ ይመከራል።
በዚህ በሽታ የመያዝ እድላቸው ከፍተኛ የሆኑ ሰዎች ምልክቱ ባይታይባቸውም በአመት አንድ ጊዜ መመርመር ይመከራል።
ባሁን ሰአት ባለው የምርመራና የህክምና እድገት አማካኝነት ቫይረሱ በደም ውስጥ ቢኖርም ረጅምና ጤናማ ኑሮ ለመኖር ይቻላል።
ክፍል 6 በቀጣይ ሳምንት ይጥብቁን