02/09/2023
ለሀዋሳ ከተማ ምክር ቤት
ሀዋሳ
ጉዳዩ :- ሁሉን አቀፍ መፍትሄ ስለመጠየቅ ይሆናል
ከላይ ለመጥቀስ እንደተሞከረው በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ሀዌላ ቱላ ክፍለ ከተማ ስር ካሉት ቀበሌያት አንዷ የሆነችው ዳቶ ኦዳሄ ቀበሌ በእናንተ ዘንድ የታወቀ መሆኑን እንገነዘባለን። ግዴታችንን እየተወጣን መብታችን ያልተከበረልን ህብረተሰብ ነን ብንል ማጋነን አይሆንም ። ግዴታችንን ተወጥን መብታችን እንድከበር ማፈናፈኛ አሳጥተን ስልጡን በሆነና በሰከነ አካሄድ የትግል ስልታችንን አጠናክረን ስንቀጥል ፣ እናንተ የሾማችኋቸው ስራ አስፈጻሚዎቻችን እንደ ውሃ ሽታ የሆነውን ተግባር የለሽ ንግግር አብዝተው ፣ ከንቱ ተስፋ አሰንቀው እንደወረዱ ለእናንተ ግልጽ ነው። እናንተ ተታለላችሁ፤ እነርሱ አታለሏችሁ። እኛ ከልማት ሳንሆን ቀረን።
ማሳያ:- ስራውን መሰራት ባለበት ጊዜ ሳይሰሩ ፣ የእናንተ ስብሰባ ሊካሄድ አንድ ሳምንት ሲቀር የፎቶ ትዕይንት ለማሳየት ፣ በፎቶ አስጀምረው በፎቶ አስጨርሰው ባቀረቡት ሪፖርት ያለ ልክ ተታለላችሁ፤ እነርሱም አታለሏችሁ። የወከላችሁን ህብረተሰብ መብት ማስከበር ስላልቻላችሁ እናንተም ተወቃሽ ናችሁ። እነርሱ በቀደዱት ቦይ ብቻ መፍሰስን መርጣችሁ እውነተኛውን የህዝብ ጩኸት አልሰማ ስላላችሁ። ደግመን እንላለን አዎን ተወቃሽ ናችሁ። ቢሆንም ግን አሁንም ያልተዘጋ የማስተካከል ዕድል አላችሁ።
ስለሆነም እኛ አሁን እናንተን የምንጠይቀው፣ የምናሳስበው:-
፩/ የባለፈውን ስህተት እንዳትደግሙ - ተግባር የለሽ ትወናን ፈጽሞ እንዳትሞክሩ
፪/ ቃል ተገብቶ ፣ የመሰረት ድንጋይ ተጥሎ ያሉ ፕሮጀክቶችን በሚገባ እንድታስፈጽሙ
፫/ ፍትሃዊ ያልሆነውን ፣ ለብዙ እንግልት የዳረገውን በሀዌላ ቱላ ክፍለ ከተማ ስር ተዋቅሮ መቆየትን ገላግሉን።
፬ / Daato Keelli በሙሉ ኃይሉ ህጋዊ እውቅና ተሰጥቶት ወደ ስራ እንድገባ ይደረግ፣
የስራ ዕድል ፈጠራም ለዳቶ ስራአጥ ልጆች ይመቻች።
፭/ ብቃትን መሰረት ያላደረገ የቅብብሎሽ ሹሜት ያሳዝነናል ፤ አይፈይድምና።
፮/ ሀዋሳ የመሯት አመራሮቿ እስካሁን ሀዋሳን
የዳቶ፣ ጨፌ፣ ሂጣታ፣ ጥልቴ፣ ቱሎ--- ወዘተ ባለ ዕዳ አድርገዋት አልፈዋል። ሞልቶም ተርፏል። ዕዳቸውን ከመመለስም ያለፈ ዳጎስ ባለ ካሳ ልትሸልሟቸው ይገባል።
ይህ እንዲሆን ህዝቡን ወክላችሁ የተቀመጣችሁ ክቡራን የምክር ቤት አካላትና አባላት በሙሉ የአዳሬ ህብረተሰብ ችግርና ሰቆቃ እንድገዳችሁ ማሳሰብን ወደድን።
ማሳሰቢያውም:-
፩/ ሁሉን አቀፍ የሆነ ችግር ፈቺ መመሪያና ደንብ እንድዘጋጅ ወይም እንድጸድቅ የበኩላችሁን ብርቱ ጥረትና ትግል እንድታደርጉ፤ በማስፈጸምም እንድታሳርፉን እንፈልጋለን
፪/ ስብዕናው የበሰበሰ ፣ በሞራል የላሸቀ( Moral decay) አመራር ወደፊት አታውጡ፣ ብቃትን መሰረት ያላደረገ በደም ቆጠራ የሚላክ ፣ ህዝብን ሳይሆን ሊያገለግላቸው የሚሰዱትን በብርቱ ትግላችሁ እንድታርቁት።
የህዝብ ውግንና ያለውን ፣ የማይስገበገበውን ራሱን የገዛውን ሞዴል አመራር ብቻ እንድትመረጥ
፫/ ዳቶን ከልማት ገለል አድርጋችሁ ሌላ አስተዳደር እንዳላት እንዳትስመስሉ ብቻ ሳይሆን ልዩ ትኩረት ከሚሹ ቀበሌያት ውስጥ ቀዳሚዋ ናትና ልዩ ጉብኝታችሁ ካሁን በኋላ እንዳይለየን አደራ እንላለን።
ቀሪ ዘመናችሁ በተግባር የታጀበ ብቻ ይህንም
Daato News
27/12/2015
Daato