07/11/2023
በሃዋሳ ከተማ ጥንታዊ ሰፈሮች እና የንግድ ስፍራ ከሆኑን የህዝብ መኖሪያ አከባቢ የሚባለው 02 ሰፈር ወይንም የአሮጌው ገብያ ጫፍ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ በቅርብ ጊዜ ጀምሮ የኗሪውን ሆነ የህብረተሰቡን ድህነነት ባልጠበቅ መልኩ ለየት ያለ ስራዎች እየተሰሩ ነው።
በቅርብ ጊዜ ወዲህ በዚህ አከባቢ የምጣድ ስራ ላይ የተሰማሩት ግለሰቦች የምጣድ ብረት ለማጣጠፍ በሚያደርጉት ቅጥቀጣ ህዝቡ ላይ ከፍተኛ የሆነ ሁከት እና ረብሻ እየተፈጠረ ነው።
ይህን ጉዳይ የሰፈሩ ሰዎች ለቀበሌ እና ለክ/ከተማው መዋቅር በማስተጋባት እና አመራርቹም ቦታው ላይ በመገኘት የተመለከቱ ቢሆንም ለህብሰተሰቡ ምንም አይነት መፍህቴ አልተሰጠውም።
በሃዋሳ ከተማ በመሃል ከተማ ብቻ የሚሰሩ ሰራዎችን ብቻ በመመልከት ህዝቡ ወደ ታች የሚገኙ ሰፈሮች ወርዶ እንዳይመለከት ተደረጋል መንግስትም ለአይን የሚታዩ አከባቢዎች ከማልማት ባለፈ ሌሎች በውስጥ ለውስጥ ሰፈሮች ላይ የሚሰሩ ምንም አይነት መሠረተ ልማት ሆነ ለህዝብ የተመቸ ከተማ የለም።
02 ሰፈር በተለመዶ ፀጥ ያለ ሰፈር የነበረ ቢሆን የገብያ ሰፈር አቅራቢያ እንደመሆኑ መጠንም ሰኞ እና ሀሙስ ከወትሮ ለየት ብላ ትደምቅ ነበር። ዛሬ ግን የአከባቢው ማህበረሰብ እሁድን ጨምሮ ፀጥታ የራቀው ሰፈር ሆኗል።
ይህም ህዝብ 20አመት በላይ ከኖረበት አከባቢ እንዲለቅ እና አብዛኛው የጭንቅላት መታወክ እንዲደርስባቸው ይህ የምጣድ ስራ አስጊ እና አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል።
መንግስት ይህን ሁኔታ በተገቢው መንገድ ተመልክቶ ለህዝብ አስፈላጊውን ስራ እንዲሰራ ለማለት እወዳለሁ።
አከባቢው ላይ ከሁከት ባለፈ ምጣዶቹ ከተሰሩ ብኋላ በመሃል መንገድ ላይ መቀመጣቸው የመንገድ መጨናነቅ እንዲፈጠር የተለያዩ የተሽከርካሪ አደጋ እየደረሰ ይገኛል።
ከአመታት በአከባቢው ላይ የወጣቶች እና የህፃናት መዝናኛ እና የእግር ኳስ መጫወቻ ቦታ ነበረ ቢሆንም የተደረገው የመሬት ወረራ ሜዳውን የአጣና ሻጮች ሙሉ ለሙሉ በመውረስ ወጣቱ ላላስፈላጊ ሱስ እያደረጉ ይገኛል።
ከምንም በላይ ግን የወጣቱንም እና አሮጊቱን ስነልቦና የሚጉዳ እና የአከባቢ ጠንቅ የሆነውን ሁከት መንግስት በአፋጣኝ ተመልክቶ ለህዝብ ምላሽ እንዲሰጥ እንፈልጋለን።