16/04/2024
ለአዲሱ ትዉልድ የሚሰጠዉ ትምህርትና ስልጠና ብሎም የመምህራን ልማትና የምርምር ስራ ስራ ዘመኑ ባፈራቸዉ ቴክኖሎጂዎች የታገዘ ቢሆን ለትምህርት ጥራት መረጋገጥም ሆነ ለመምህራን ሙያዊ ዕድገት የጎላ ሚና እንዳለዉ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የተደረጉ ጥናቶች ያመላክታሉ፡፡
እኛም በሀገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ባካሄድነዉ ጥናት መሰረት የተዘጋጀ የአጭር ግዜ ስልጠና የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ማህበራዊ ሳይንስና ሥነ-ሰብ ኮሌጅ ለኮሌጁ መምህራን ባዘጋጀዉ ስልጠና መድረክ ላይ እኔና ባልደርባዬ ዶ/ር ተስፋዬ ባዩ ስልጠና ለመስጠት ችለናል፡፡
የሰልጠናዉ ይዘት፡- ከሳይንስ፣ ምርምር፣ የ21ኛ ክፍለ-ዘመን ተፈላጊ ክሂሎቶች፣ ሀገሪቱ ካቀደቸዉ ዲጅታል ኢትዮጵያ 2025 ዕቅድ፣ የትምህርት ፍኖተ ካርታ፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፍላጎትና አቅጣጫ እንዲሁም ከመምህራን ወቅታዊ ሙያዊ ፍላጎት ጋር የተጣጣመ ነዉ፡፡
ኮሌጁ በዚህ ጉዳይ ላይ ለወሰደዉ እርምጃ እና ላመቻቸዉ ዕድል ያለኝን አድናቆት ለመግለጽ እወዳለሁኝ፡:
ሌሎች (ከፍተኛ) ትምህርት ተቋማትም እንደ አስፈላጊነቱ ይህንን ተሞክሮ ቢወሰዱ መልካም ነዉ እላለሁ፡፡
ባልደረቦቼ ለተሳትፎአችሁና ለገንቢ አስተያየቶቻችሁ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ፡፡