25/11/2023
ፀለይን ፀለይን እኛስ አንጋጠጥን
የምንፈልገውን ላምላክ እየላክን
ፍላጎት ምኞትን እየፈበረክን
ለመንን
ለመንን
ቃተትንን
ቃተትንን
ስንት ዘመን ሞላ አምላክን ከካድን?
ከምኞት አፀፋ የሚመለስ ጌታ እኛ ከፈለግን
ምን ትሻለህ ብለን እስኪ መች ጠየቅን?
ለመንን
ለመንን
ስለኛ ነው እንጂ ስለሱ ውብ ስሜት መቼ ተጨነቅን?