Gondar Online/ጎንደር

Gondar Online/ጎንደር Gondar Online/ጎንደር

31/12/2023

በእነ አርበኛ ሲሳይ አሸብር የሚመራው ዋዋ ጎቤ ብርጌድ በአርማጭሆ እና አካባቢው የተሠማራውን የጠላት ተላላኪ በማፅዳት ላይ ይገኛሉ።

ጎንደር ከተማ በአንድ ሳምንት ሁለት መንፈሳዊ ሊቆች በአገዛዙ ተገድለዋል። ይህ ግድያ አካባቢውን ሊቅ የማሳጣት የአገዛዙ ፕሮጀክት አካል ነው። ጎንደርን የአክራሪ ውብያ እና የሀሳዊ ጨፋሪ ሀይ...
10/12/2023

ጎንደር ከተማ በአንድ ሳምንት ሁለት መንፈሳዊ ሊቆች በአገዛዙ ተገድለዋል። ይህ ግድያ አካባቢውን ሊቅ የማሳጣት የአገዛዙ ፕሮጀክት አካል ነው። ጎንደርን የአክራሪ ውብያ እና የሀሳዊ ጨፋሪ ሀይማኖት መፈንጫ ለማድረግ የማመቻቸት ፕሮጀክት ነው። አካቢውን ከሊቅም ከጀግናም በማፅዳት ለመጣ ለሄደው ተንበርክኮ እና ገብሮ እንዲኖርና ከሌላው አማራ ለመነጠል እየተሰራ ነው። ሳይቃጠል በቅጠል ብሎ ህዝቡ መዥገሮቹን ካላፀዳ ከዚህም በላይ ዘግናኝ ነገሮች ፤ እንደ ክርፋት የሚሸት ጥቃት ይገጥመዋል።

በጎርጎራ የሚገኜው ጥንታዊ ገዳም ተዘርፏል።ከመዘረፍ አልፎ ክብሩን አርከሰውታል😭ተዋህዶ ዛሬም ያለክብሯ ክብር እየተሰጣት ነው።በጎርጎራ የሰፈረው የብልፅግና ሰራዊት ጥንታዊው የማን እንደ አባ ...
22/09/2023

በጎርጎራ የሚገኜው ጥንታዊ ገዳም ተዘርፏል።ከመዘረፍ አልፎ ክብሩን አርከሰውታል😭ተዋህዶ ዛሬም ያለክብሯ ክብር እየተሰጣት ነው።

በጎርጎራ የሰፈረው የብልፅግና ሰራዊት ጥንታዊው የማን እንደ አባ ገዳም ክብር አራክሶታል።መነኮሳት በጥይት ተመተዋል፤መነኮሳት ታስረዋል፤ገዳሙ ተዘርፏል፤ዲያቆናት በጥይት ተመተው ሙተዋል😭

አሁንም የበለጠ እንድናታገል የሚያደርገን እንጅ ከትግላችን የሚያቆመን ነገር እንደሌለ በየቀኑ አጀንዳዎች እየተጨመሩ ነው።

ድል ለታላቁ አማራ✊

22/09/2023

የአብይ አህመድ ሰራዊት የአማራን ህዝብ ለማንበርከክ የሚጠቀምባቸው ስልቶች (ጅምላ ጭፍጨፋ፣ መድፈር፣ ማገት፣ መሰረተ ልማት ማውደም፣ ህክምና ተቋማትን መዝጋት ..... ወዘተ ) የህዝቡን ቁጣ በመጨመር ህዝቡ በሰራዊቱ ላይ ጭላንጭል ተስፋ እንዳይሰንቅና በጠላትነት ፈርጆ እንዲታገለው ምክንያት ሆኗል። ከዚህ ቀደም ለስርዓቱ ሽማግሌ በመሆን ጃንጥላና ካባ ለብሰው ወደፋኖ የሚሄዱ የሀገር ሽማግሊዎችና የሀይማኖት አባቶች አሁን ደጃችን ድረስ መጥቶ የሚጨፈጭፈንን ወራሪ ሁሉም የህበረተሰብ ክፍል እንዲዋጋው አዋጅ እየተናገሩ ይገኛሉ።

እንዲያ ያሰባሰባቸሁ ድሎትና ምቾት ሳይሆን የአማራ ህዝብ በደል ብቻና ብቻ ነው!ይህ የምናየው በደል ሁሉ ደግሞ  ታሪክ ይሆናል👌
09/08/2023

እንዲያ ያሰባሰባቸሁ ድሎትና ምቾት ሳይሆን የአማራ ህዝብ በደል ብቻና ብቻ ነው!

ይህ የምናየው በደል ሁሉ ደግሞ ታሪክ ይሆናል👌

08/08/2023

ጎንደር የኦነግን ጦር እየደመሰሰ፣ሙት እና ቁስለኛ አድረጎታል።

ድል ለአማራ ፋኖ

ሰበር የድል ዜና ..💪🔥የዳባቱ ውጊያ በፋኖ አሸናፊነት ተጠናቀቀ፤ ቁጥሩ ለጊዜው ያልታወቀ የአብይ ታጣቂ ተደም**ስሷል፤ 855 ተማርኳል ተብሏል። የተማረከው የጦር መሳሪያ ገና ኦዲት እየተደረ...
08/08/2023

ሰበር የድል ዜና ..💪🔥

የዳባቱ ውጊያ በፋኖ አሸናፊነት ተጠናቀቀ፤ ቁጥሩ ለጊዜው ያልታወቀ የአብይ ታጣቂ ተደም**ስሷል፤ 855 ተማርኳል ተብሏል። የተማረከው የጦር መሳሪያ ገና ኦዲት እየተደረገ ነው ተብሏል❗️
ዝርዝሩ እንደደረሰን እናጋራችሁዋለን።

በጎንደር ከተማ አዘዞ ክ/ከተማ ፤ አጣጥ አካባቢ ህፃናት እና እናቶችን ያለርህራሄ እየገደለ የሚገኘው ወራሪው የኦነግ መከላከያ ሰራዊት ማንኛውንም ህዝባዊ አገልግሎቶች እንዳያገኝ ስንል ለከተማ...
02/08/2023

በጎንደር ከተማ አዘዞ ክ/ከተማ ፤ አጣጥ አካባቢ ህፃናት እና እናቶችን ያለርህራሄ እየገደለ የሚገኘው ወራሪው የኦነግ መከላከያ ሰራዊት ማንኛውንም ህዝባዊ አገልግሎቶች እንዳያገኝ ስንል ለከተማችን ነዋሪ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
በምስሉ የምትመለከቷት እህታችን በጉልበቷ ጥራ ግራ ቤተሰብ የምታስተዳድረ የቀን ሰራተኛ ነበረች።

#ሞት ለአማራ ጠላቶች
#ድል ለአማራ ህዝብ

ሰበር ዜና ‼️አዲስ ዘመን የገባው የኦህዴድ ጦር ሙትና ቁስለኛ ሆነ ደቡብ ጎንደር አዲስ ዘመን ከተማ መውጫ ላይ መሽጎ የነበረው የስርዓቱ ጦር በፋኖዎች ድንገተኛ ጥቃት ሙትና ቁስለኛ ሆነ።በደ...
02/08/2023

ሰበር ዜና ‼️

አዲስ ዘመን የገባው የኦህዴድ ጦር ሙትና ቁስለኛ ሆነ

ደቡብ ጎንደር አዲስ ዘመን ከተማ መውጫ ላይ መሽጎ የነበረው የስርዓቱ ጦር በፋኖዎች ድንገተኛ ጥቃት ሙትና ቁስለኛ ሆነ።በደቡብ ጎንደር ዞን የአዲስ ዘመን ህዝብ የቡድን መሳሪያ ታጥቆ ሊገድለው የመጣውን ወራሪው ኃይል ከቦ በወሰደው የመከላከል ዕርምጃ ነው መከላከያው ሙትና ቁስለኛ የሆነው ሲሉ ጦርነት ከሚካሄድበት ስፍራ መረጃ ያደረሱን።

"እስካሁን ድረስ የመከላከል ዕርምጃው አልቆመም፤በስፍራው የሚገኘው ኃይል ያለው አማራጭ እጅ መስጠት ብቻ ነው" ብለዋል መረጃ ሰጭዎቻችን።

ድል ለአማራ ፋኖ ‼️

ሰበር ዜና‼️ጎንደር ከተማ ከፍተኛ ተኩስ ተከፍቷልጎንደር ከተማ በሁሉም አቅጣጫ ተኩስ የተከፈተ ሲሆን አዘዞ የሚገኘው የመከላከያ ካምፕ ላይ ከፍተኛ የተኩስ ድምጽ እየተሰማ ነወ።የጎንደር ከተማ...
02/08/2023

ሰበር ዜና‼️

ጎንደር ከተማ ከፍተኛ ተኩስ ተከፍቷል

ጎንደር ከተማ በሁሉም አቅጣጫ ተኩስ የተከፈተ ሲሆን አዘዞ የሚገኘው የመከላከያ ካምፕ ላይ ከፍተኛ የተኩስ ድምጽ እየተሰማ ነወ።
የጎንደር ከተማና አካባቢው ማህበረሰብ ህዝባዊ ትግሉን በማስቀጠል የተለመደውን ታሪኩን ዳግም እንዲጽፍም ጥሪ ቀርቧል።

የብልጸግና አገዛዝ በአማራ ላይ የከፈተውን ተኩስ በማስቆም የጎንደር ህዝብ ነጻነቱን እንዲያረጋግጥም ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።
ድል ለአማራ ፋኖ

02/08/2023

~ ማሳሰቢያ!
ከአማራ ፋኖ በጎንደር!

ከአዲስ አበባ ወደ ጎንደር፤ ከጎንደር ወደ አዲስ አበባ በረራ ለማድረግ ላሰባችሁ ወገኖቻችን በሙሉ!

የጎንደር ኤርፖርት የሲቪል አገልግሎት የሚሰጥ መሆኑ ይታወቃል። ይሁን እንጂ አገዛዙ ገዳይ ጦር በሲቪል አውሮፕላንና በወታደራዊ አውሮፕላን እንዳያራግፍና ለጥንቃቄ ሲባል ከኤርፖርቱ ውጭና ውስጥ የፋኖ ጦር ስለሚኖር ምንም አይነት ድንጋጤ ሳይኖራችሁ እንድትገለገሉ እና ተገልጋዮችም የኤርፖርቱ ሠራተኞችም በተለመደው አግባብ እንድታገለግሉ ስንል መልዕክት እናስተላልፋለን።

አማራነት፤ አሸናፊነት!
ድል እናደርጋለን!

ሰበር ዜና‼️በመላው አማራ የትጥቅ ትግል ታወጀ‼ሐምሌ 26 ቀን 2015 ዓ.ምበመላው አማራ የትጥቅ ትግል መታወጁን የጎንደር ፋኖዎች በይፋ ተናግረዋል ።ጎንደር ከተማ መንገዶች ሁሉ ዝግ እንዲሆ...
02/08/2023

ሰበር ዜና‼️

በመላው አማራ የትጥቅ ትግል ታወጀ‼

ሐምሌ 26 ቀን 2015 ዓ.ም

በመላው አማራ የትጥቅ ትግል መታወጁን የጎንደር ፋኖዎች በይፋ ተናግረዋል ።

ጎንደር ከተማ መንገዶች ሁሉ ዝግ እንዲሆኑ ትዕዛዝ ተላልፏል።
በዚህ ሰዓት ጎንደር ከተማ የተማረከው የመከላከያ መኪና እና የስርዓቱ ዘቭ ጠባቂ ሰራዊት በዚህ መልኩ የአማራ ፋኖ በጎንደር ቴድሮስ ብርጌድ ሰራዊት በዚህ መልኩ እያጋደመው ይገኛል።

"ብትችሉ ከጎናችን ሁኑ፤ እምቢ ካላችሁ ግን ከፊታችን ልናያችሁ አንፈልግም" የአማራ ፋኖ በስሜን ጎንደርየአማራ ፋኖ በስሜን ጎንደር በዛሬው ዕለት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ለመምከር ስብሰባ አድር...
01/08/2023

"ብትችሉ ከጎናችን ሁኑ፤ እምቢ ካላችሁ ግን ከፊታችን ልናያችሁ አንፈልግም" የአማራ ፋኖ በስሜን ጎንደር

የአማራ ፋኖ በስሜን ጎንደር በዛሬው ዕለት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ለመምከር ስብሰባ አድርጎ ነበር። ከብአዴን ተልእኮ ተሰጥቶት በዞኑ እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው ኮሚሽነር ደስየ ማንንም ሳያማክር በመድረኩ ተገኝቶ 'ችግሮችን በሰላም መፍታት ይሻላል' በማለት ፋኖዎችን ለማወያየት ሞክሮ ነበር። ይሁንና ፋኖዎች "የውይይትና የሽምግልና ጊዜው አልፏል፤ በውይይትና በሽምግልና ብዙ ጊዜ አምነናችሁ ቀርበን ነበር። ሁኖም በቃላችሁ አልተገኛችሁም። እንወያይ ባልን ወደ ወህኒ ተወርውረን ተገርፈናል ብዙ ግፍ ተፈፅሞብናል። አሁን ከቻላችሁ ከጎናችን ሁኑ እምቢ ካላችሁ ከፊታችን ልናያችሁ አንፈልግም" በማለት አሳፍረው መልሰውታል።

በስሜን ጎንደር የአማራ ፋኖዎች ኮሚሽነር ደስየን ከአዳራሹ ካስወጡ በኋላ ለእውነተኛ ትግል እና መስዋዕትነት ለመክፈል ተማምለው ውይይታቸውን ቋጭተዋል።

ድል ለአማራ ሕዝብ‼️

የሕዝብ ልጅ የሆነው ነበልባሉ ፋኖ ከአገዛዙ ዙ-23 ተቀብሏል።ይቀጥላል‼️ድል ለአማራ ሕዝብ‼️
01/08/2023

የሕዝብ ልጅ የሆነው ነበልባሉ ፋኖ ከአገዛዙ ዙ-23 ተቀብሏል።

ይቀጥላል‼️
ድል ለአማራ ሕዝብ‼️

ሰበር ዜና!በዚህ ውድቅት ሌሊት በቆቦ ከተማ ዙሪያ ጦርነት ተከፍቷል።ሀምሌ 24/2015 ከእኩለ ለሊት 6:30 ጀምሮ በቆቦ ከተማ ዙሪያ ልዩ ስሙ ካራይላ አከባቢ ከባድ የሆነ ውጊያ እየተካሄደ ...
01/08/2023

ሰበር ዜና!

በዚህ ውድቅት ሌሊት በቆቦ ከተማ ዙሪያ ጦርነት ተከፍቷል።

ሀምሌ 24/2015 ከእኩለ ለሊት 6:30 ጀምሮ በቆቦ ከተማ ዙሪያ ልዩ ስሙ ካራይላ አከባቢ ከባድ የሆነ ውጊያ እየተካሄደ ስለመሆኑ ተገልጧል።

የምስራቅ አማራ ፋኖዎች ከዙ 23 እስከ መድፍ ከታጠቀው የኦህዴድ ብልጽግና አገዛዝ ጦር ጋር በከፍተኛ ውጊያ ላይ መሆናቸው ታውቋል።

በዚህ ውድቅት ለሊት ከምሽግ ምሽግ እየዘለሉ በጠላት ኃይል ላይ የማያዳግም እርምጃ እየወሰዱ ነው ተብሏል።

አካባቢው በተኩስ እሩምታ እየተናወጠ ነው።
ምንጭ_አማራ ድምጽ ሚዲያ

ሰበር ዜና!በኮሎኔል ፈንታው ሙሀባና በኮሎኔል ሞገስ ዘገየ የሚመራው ፋኖ በሰሜን ወሎ ሳንቃ ላይ ወሰድኩት ባለው ድንገታዊ ጥቃት ብዙ ሰራዊት ሙትና ቁስለኛ ሆኗል፤ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ተሽከር...
31/07/2023

ሰበር ዜና!

በኮሎኔል ፈንታው ሙሀባና በኮሎኔል ሞገስ ዘገየ የሚመራው ፋኖ በሰሜን ወሎ ሳንቃ ላይ ወሰድኩት ባለው ድንገታዊ ጥቃት ብዙ ሰራዊት ሙትና ቁስለኛ ሆኗል፤ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ተሽከርካሪዎች ከጥቅም ውጭ አድርጌያለሁ ብሏል።

ፋኖዎችም በርካታ የትጥቅ መሳሪያዎችን ማርከዋል፤ ቀሪው ሀይል እግሬ አውጭኝ በማለት ፈርጥጧል ሲል ገልጧል።

በአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር አደረጃጀት ስር የሚገኘው የቋረኛው ብርጌድ የፋኖ አባላት የሆኑት በቀን 19/11/2015 ዓ.ም  በሃይማኖታዊ ጉዳይ በጯሂት ከገዥው ሰራዊት ጋር አንገት ላንገት...
31/07/2023

በአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር አደረጃጀት ስር የሚገኘው የቋረኛው ብርጌድ የፋኖ አባላት የሆኑት በቀን 19/11/2015 ዓ.ም በሃይማኖታዊ ጉዳይ በጯሂት ከገዥው ሰራዊት ጋር አንገት ላንገት ተናንቀው መስዋት የከፈሉትን የትግል ጓዶች የአማራ ፋኖ አንድነት የስራ አስፈፃሚ አካላት፣ድፍን የደንቢያ ፋኖ እና ህዝብ በተገኘበት በቀን 23/11/2015ዓ.ም ዛሬ በደመር ሸኝቷል።

ታጋይ ጓዶች መስዋት የከፈሉት:-
ለሃይማኖታቸው፣ለነፃነታቸው እንዲሁም ለታሪካቸው ሲባል እንደሆነ የአማራ ፋኖ አንድነት ተቋም የበላይ አመራሮች እና የቋረኛው ብርጌድ ዋና አዛዥ ገልፀዋል!!
የወንድሞቻችን መስዋትነት የክብር መስዋትነት እንደሆነም ጭምር ተገልጿል።

በደመሩ ፕሮግራም ላይ ከአማራ ፋኖ አንድነት የበላይ አመራሮች ከተላለፉት መለዕክቶች መካከል:-
1. ሁለተናዊ ህልውና ገጥሞናል ይህን ከበባ ልንሰብረው የምንችለው፣ህልውናችን የምናረጋግጠው ውስጣዊ አንድነትን በመገንባት እንደሆነ።ምክንያቱም አንድነት ብቼኛ መውጫ በር ስለሆነ።
2. የገጠመን ጥቃት ዘውጋዊ/ማንነታዊ ተኮር እንደሆነ አንስተው ይህ ጥቃት የሚሊሻውም ሆነ የፓሊሱ ጭምር ነው ምክንያቱም አማራ ከሆነ።ስለሆነም በአማረነታችን መተሳሰር እንዳለብን
3. በፋኖ ስም የምንታገልለትን ህብረተሰብ የሚጨቁን ካለ ዕርምጃ እንወስዳለን!!
4. ለፋኖ አባላት ለቁሳቁስ ሳይሆን ለነፃነት ታገሉ!!ትጥቃቹህን አጥብቁ!! ጥይታቹህን በአጉል ነገር አታባክኑ።ቦንባቹሁን ጨምሩ።
5. ነገራችን ከፓለቲከኛው እንጅ ከፀጥታው ሃይል ጋር አይደለም።ይህ የሚሆነው የፀጥታው ክንፍ ለፓለቲከኛው አስፈፃሚ ካልሆነ ብቻ ነው።
6. ለውጤት እንታገል!!ትግላችን እንዳይጠለፍ ጥንቃቄ ይደረግም ተብሏል።
7. አጠቃላይ እንደ አማራ ማዕከላዊነቱ የተጠበቀ ትግል ማድረግ ከቻልን በአጭር ጊዜ ውስጥ አማራው የድል ባለቤት መሆን እንደሚችል ተነስቷል
8. ለወረኞች፣ለፎቶ አቢወተኞች፣ለጥቅመኞች ማለትም በየ ሆቴሉ፣በየ ግሮሰሪው ምንጩ ያልታወቀ ገንዘብ ለሚከፋፈሉ ፋኖ ነን የሚሉ ሃይሎች በሚያደርጉት የከንቱ ትግበራ አትበገሩ። ምክንያቱም ነፃነትህን የምታገኘው ተርበህ፣ተጠምተህ እንደሆነ ከአባቶችህ ታሪክ ተማር!!

አጠቃላይ የትግል አቅጣጫወችም ተቀምጠዋል።
የተሰውትን የትግል ጓዶች ነብስ ይማር!!
ለቤተሰቦቻቸው እና ለትግል ጓዶቻቸው መፅናናትን እንመኛለን!!

ድል ለነፃነት ታጋዮች!!
አንድነት ሃይል ነው!!
በሚል ተቋጨ።

አፄ ፋሲለደስ ሻለቃ ተመሰረተ...የአማራ ፋኖ በጎንደር ቴውድሮስ ብርጌድ አፄ   ፋሲልደስ ሻለቃ በዛሬው ዕለት ሃምሌ 23/2015 ዓ/ም በይፋ ተመሰረተ።ይህንን ምስረታ አስመልክቶ ከዚህ ቀደም...
30/07/2023

አፄ ፋሲለደስ ሻለቃ ተመሰረተ...

የአማራ ፋኖ በጎንደር ቴውድሮስ ብርጌድ አፄ ፋሲልደስ ሻለቃ በዛሬው ዕለት ሃምሌ 23/2015 ዓ/ም በይፋ ተመሰረተ።

ይህንን ምስረታ አስመልክቶ ከዚህ ቀደም በርካታ ስራ ሲሰራ የቆየው ቴውድሮስ ብርጌድ ዛሬ አፄ ፋሲለደስን ሻለቃ ሲያቆም ሻለቃ መሪ አድርጎ የሾመው
👉ፋኖ ተስፍሽ መንጌና
ምክትል ሻለቃ
👉ፋኖ ናሁሰናይ አንዳርጌን አድርጎ ሰይሟል።

የአማራ ፋኖ በጎንደር ቴውድሮስ ብርጌድ አመራርና አባላቶች በምስረታው ተገኝተው ይህን መሰል ለአማራ የጀርባ አጥንት የሚሆኑ ወጣቶችን መልምሎ ወደዚህ ሻለቃ ስያካትት ከኮብልስቶን እሰከ ነፍጥ የታጠቀውን ነባር ታጋይ ተካታችና መሪ ያደረገ መሆኑ ይበል የሚያስብልና ትግሉን ለማሻገር የስራ ድርሻ ቅብብሎሽ ማሳየቱ ዘመናዊ እና ስልታዊ ትግል መሆኑን በማሳወቅ በአንድነት እንደሚሰሩ የጋር ወሳኔ አሳርፈዋል።

ድል ለአማራ ነፃነት ናፋቂዎች👊

Address

Gondar
T14T14

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gondar Online/ጎንደር posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share