
13/10/2024
ሸሂጅ ሸህ ሰይድ ይብሬ
ሸሂድ ሸህ ሙሐመድ ሲራጅ
ሸሂድ ወጣት ሰዒድ ይብሬ ሙሔ
በአማራ ክልል በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጎንደር ዙሪያ ወረዳ እንፍራዝ ከተማ በሚገኘው የስሆር ሳርውኃ የገጠር ቀበሌ ላይ በአንድ ወር ውስጥ ብቻ እነኚህ ሶስት ግለሰበች በተለያየ ጊዜ ሐሪማየን እና የትውልድ ቦታየን ለቅቄ አልሄድም በማለታቸው ብቻ የተ*ገደሉ ንፁኃን ናቸው።
አሁን ከመሸ ፅን*ፈኛ የፋኖ ታጣቂዎች ወደ ሐሪማውና የማህበረሰቡ መኖሪያ አካባቢ በመሄድ ጥቃት ከፍተውባቸው እየተ*ዋጉ ይገኛል።
የፅንፈኛ ታጣቂዎች ጥያቄ እንደነ ፍርቃ፣ ደልዳሊት፣ ግራምጢትና አምባገር ሐሪማዎች እናንተም ሐሪማችሁን ትታችሁ ደረሳዎቻችሁን በትናችሁ ላትመለሱ አካባቢውን ለቃችሁ ውጡ የሚል ነው።
የአካባቢው የመንግስት አካል ምንም አይነት እገዛ እና ድጋፍ እያደረገ እንዳልሆነ ከስፍራው ያሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ገልፀዋል።