Mihret. Walle

Mihret. Walle Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Mihret. Walle, Digital creator, Gondar.

27/07/2023

ወያኔ አረጀችና ከስልጣን ተገፍታ ወደቀች!
"የማይገርፉት ልጅ ሲቆጡት ያለቀሳል" ነውና ነገሩ ~ ከስልጣን መውደቃቸው አስቆጣቸው!

አፄ ሀይለስላሴ ከስልጣን ሲወርዱ ~ ሞት ነበር የጠበቃቸው!
መንግስቱ ሀይለማርያም ~ ስደትና በስደት ሀገር መቆዘም ነበር የጠበቀው!

ወያኔዎች ሞትም ሳይገጥማቸው፣ስደትም ሳያስቆዝማቸው የሰፈራቸው አለቃ ይሆኑ ዘንድ አዲሱ ንጉስ ፈቀደላቸው። አዲሱ ንጉስ ይሄን ማድረጉ ~ a man with a lion heart
~ a man with deep wisdom
~ A man with peculiar intelligence
የበቃና የነቃ በመሆኑ አልነበረም።

ራሱ በወያኔች ቤት አገልጋይ የነበረና በወያኔ ዘመን በተሰሩ ግፎች ሁሉ ተሳትፎ የነበረው ወንጀለኛ ስለነበር ነው። ቀበቶውን እያስተካከሉ ያሳደጉት ልጅ አለቃቸው ሆኖ መምጣቱ ያልተዋጠላቸው ወያኔዎች ጫማ መለካካት ጀመሩና ወደ ጦርነት ወረዱ።

ዝንጀሮ በወጣትነቱ የማይዘለው ገደል የልም እንደሚባለው ወያኔዎች በወጣትነታቸው የዘለሉት ገደል ሁሉ ትዝ አላቸውና በዚያ ሞራል ቆስቁሰው፣ቆስቁሰው ራሳቸውን ደብረ ሲና አገኙት።ቀበቶውን እያስተካከሉ ያሳደጉት ልጅ ደግሞ በልጅነቱና በወጣትነቱ የዘለለው ገደል አልነበረምና አረ ደረሱልኝ ሲል አማራ ነፍሱን ሳይሰስት ለጥሪው መልስ ሰጠ። ወያኔች ድንገት ዞር ብለው ቢያዩ እንደ ወጣት ዝንጀሮ በልጅነታቸው ገደላ ገደሉን ሲዘሉ የነበሩበት ጉልበት የለም። አንዱ ሀይል ጊዜ ተፍቶት አርጅቷል ~ ሌላኛው እንደ ዝንጀሮው የዘለለው ገደልና ሜዳ ባለመኖሩ ልምድም፣ ጀግንነትም ሆነ እውቀትም ካለመኖሩ አንፃር ቢራገጡ፣ቡራገጡ የጀምሩት ጦርነት አላልቅ አለና ሁለቱም ርግጫው ሲበቃቸው ታረቅን አሉ!

በአብይ አህመድና በወያኔዎች ቤትና አስተሳሰብ እንጂ
ከ Logic, common sense, societal norms ሆነ any kind of philosophy ጋ የማይታረቀው ተቃርኖ የሚከተለው ነው:–

ወያኔዎች የታረቁት ~ ያሳደጉት ልጅ ጋ ነው!
ወልቃትና ራያን መልሱልን የሚሉት ~ አማራን ነው!
አብይ አህመድ ~ ወንበሩን የነቀነቁበትና ጫማ የተለካኩት አሳዳጊዎቹ ወያኔዎች ናቸው!
አብይ አህመድን ~ ከጉድ የዳነው በአማራ ልጆች የትግል አስተዋፅኦ ነው!
አብይ አህመድ ዛሬ ከአማራ ልጆች ጋ ትግል ላይ ነው!

ምን ሆኖ ተብሎ ቢጠየቅ?
> ወያኔዎች ሊገለብጡት ሲሉ ከጎኑ ተሰልፈው ተጋድሎ በማድረጋቸው ~ ቢባል

ወይም

> ወያኔዎች ሊገለብጡት ሲሉ አብይን በመታደጋቸው በዚያ ንዴት በመስዋእትነት ከወያኔ እጅ የተረከቡትን ግዛታቸውን ከአማራ ልጆች እጅ ቀምቶ ከወንበሩ ሊያወረዱት ለነበሩት ወያኔዎች ወልቃይትና ራያን ለመመለስ ~ ቢባል

ጤነኛ አእምሮ ያለው ሰው በዚህ ምስቅልቅል ውስጡ እብዱ ማነው ተብሎ ቢጠየቅ ማን የሚል ይመስላችኋል?

እንዲህ አይነት ~ ቃርዳን ~ የሆነ ፖለተካ ነው የገጠመን!!!

10/07/2023
10/07/2023
25/06/2023

Hi

Address

Gondar

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Mihret. Walle posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share