JANO Ethiopia ጃኖ

JANO Ethiopia ጃኖ ይህ ትክክለኛው የጃኖ የፌስቡክ ገጽ ነው
LIKE & SHARE ?

ተከሳሽ ቶሎሳ ወይም ፍቅሩ አሸናፊ ይባላል።በአዳማ ከተማ ቦሌ ክፍል ከተማ በተለምዶ ደካ አዲ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ሚያዝያ 21 ቀን 2016 ዓ.ም እናቱን በአሰቃቂ ሁኔታ ገድሏል።ተከሳሹ እ...
01/06/2024

ተከሳሽ ቶሎሳ ወይም ፍቅሩ አሸናፊ ይባላል።

በአዳማ ከተማ ቦሌ ክፍል ከተማ በተለምዶ ደካ አዲ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ሚያዝያ 21 ቀን 2016 ዓ.ም እናቱን በአሰቃቂ ሁኔታ ገድሏል።

ተከሳሹ እናቱን በስለት (ቢላዋ) በአሰቃቂ ሁኔታ ወግቶ ነው ህይወታቸውን እንዲያጡ ያደረገው።

ተከሳሹ ድርጊቱን የፈጸመው ገንዘብ እናቱ ያላቸውን ንብረት በመሸጥ እንዲተኩለት ለማድረግ ሲል እየደበደበ ያሰቃያቸው እንደነበር ዐቃቤ ሕግ በማስረጃ አረጋግጧል።

በዚህ ብቻ ያላበቃው ተከሳሽ ሚያዚያ 21/ 2016 ዓ/ም ጠዋት በአሰቃቂ ሁኔታ የእናቱ ህይወት እንዲያልፍ በማድረጉ ከባድ የግድያ ወንጀል ክስ ቀርቦበታል።

ጉዳዩን የተመለከተው የአዳማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዛሬ በዋለው ችሎት በሞት እንዲቀጣ ወስኗል።

በተከሳሹ ላይ የተጣለው በአገሪቱ ርዕሰ ብሔር ሲጸድቅ ነው ተፈጻሚ የሚሆነው።

@ፋና

ህወሓት ህጋዊ ዕውቅናውን መልሶ ሊወስድ ነው ከህጋዊ እና ሰላማዊ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ማዕቀፍ ውጪ የቆዩ እንደ ህወሓት ያሉ የፖለቲካ ቡድኖች መልሶ መመዝገብ የሚያስችል ረቂቅ አዋጅን የሚኒስት...
31/05/2024

ህወሓት ህጋዊ ዕውቅናውን መልሶ ሊወስድ ነው

ከህጋዊ እና ሰላማዊ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ማዕቀፍ ውጪ የቆዩ እንደ ህወሓት ያሉ የፖለቲካ ቡድኖች መልሶ መመዝገብ የሚያስችል ረቂቅ አዋጅን የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ ግንቦት 23 ቀን 2016 ዓ.ም ከተወያየ በኃላ ለተወካዮች ምክር ቤት ላከ።

ከህጋዊ እና ሰላማዊ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ማዕቀፍ ውጪ የቆዩ የፖለቲካ ቡድኖች በሰላማዊ መንገድ ለመንቀሳቀስ ፍላጎት በሚያሳዩበት ጊዜ እነዚህን አካላት ህጋዊ የፖለቲካ ፓርቲ አድርጎ ለመመዝገብ የሚያስችል ስርዓት በነባሩ አዋጅ ላይ አልተካተተም ነበር።

ዜጎች ከሀገር እንዳይወጡ የማገድ ስልጣንን ለኢሚግሬሽን መስሪያ ቤት ኃላፊ የሚሰጥ የአዋጅ ማሻሻያ ለፓርላማ ቀረበማንኛውንም ሰው ከሀገር ውስጥ እንዳይወጣ የማገድ ስልጣንን፤ የኢሚግሬሽን እና ...
30/05/2024

ዜጎች ከሀገር እንዳይወጡ የማገድ ስልጣንን ለኢሚግሬሽን መስሪያ ቤት ኃላፊ የሚሰጥ የአዋጅ ማሻሻያ ለፓርላማ ቀረበ

ማንኛውንም ሰው ከሀገር ውስጥ እንዳይወጣ የማገድ ስልጣንን፤ የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት መስሪያ ቤትን በዋና ዳይሬክተርነት ለሚመራ ኃላፊ የሚሰጥ የአዋጅ ማሻሻያ ለፓርላማ ቀረበ። የአዋጅ ማሻሻያው፤ በህገ ወጥ መንገድ በኢትዮጵያ የሚኖሩ የውጭ ሀገር ዜጎች “በጥቁር መዝገብ እንዲመዘግቡ እና ከሀገር እንዲወጡ” የሚያስችል “አስተዳደራዊ ቅጣት” የመጣል ስልጣንን ለኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት መስሪያ ቤት ይሰጣል።

እነዚህን አዲስ ድንጋጌዎች ያካተተው የኢሚግሬሽን አዋጅ ማሻሻያ ለፓርላማ የተላለፈው፤ ከሁለት ሳምንት በፊት በተካሄደው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ ቀርቦ ከጸደቀ በኋላ ነው። በ1995 ዓ.ም. የጸደቀውን ነባሩን አዋጅ ማሻሻል ካስፈለገባቸው ምክንያቶች መካከል፤ መሰረታዊ ከሆኑ መብቶችን አንዱ የሆነውን “የመዘዋወር ነጻነትን ለማስከበር” እና የኢሚግሬሽን አገልግሎቶችን ለኢትዮጵያውያንና ለውጭ ሀገር ዜጎች “በተሻለ ጥራትና ቅልጥፍና መስጠት እንዲቻል” መሆኑን የሚኒስትሮች ምክር ቤት በወቅቱ አስታውቆ ነበር።

ሀገራት “ሉዓላዊ ስልጣንን” ተግባራዊ ከሚያደርጉባቸው ህጎች “በዋነኛነት” የሚጠቀስ ነው የሚባልለት የኢሚግሬሽን ህግ፤ “በህግ የተከለከሉ ሰዎች በህገ ወጥ መንገድ ከሀገር እንዳይወጡ እና ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ ቁጥጥር የሚደረግበትን አግባብ” የሚደነግግ ነው። በስራ ላይ ከዋለ 21 ዓመት የሞላው ነባሩ ህግ፤ “ከኢትዮጵያ እንዳይወጡ ስለሚታገዱ ሰዎች” እና “ከኢትዮጵያ እንዲወጡ ስለሚደረጉ የውጭ ሀገር ሰዎች” ድንጋጌዎችን አስቀምጧል።

በነባሩ ህግ መሰረት “ማንኛውም ሰው ከኢትዮጵያ እንዳይወጣ ሊታገድ የሚችለው በህግ መሰረት በፍርድ ቤት ሲታዘዝ ብቻ ነው” ይላል። ዛሬ ለፓርላማ የቀረበው የአዋጅ ማሻሻያ በነባሩ ህግ የተቀመጠውን የፍርድ ቤት “ብቸኛ ስልጣን” የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት መስሪያ ቤትን በዋና ዳይሬክተርነት ለሚመራ ኃላፊ በተጨማሪነት ያጋራ ሆኗል።

"ጻድቃኔ ማርያም"
29/05/2024

"ጻድቃኔ ማርያም"

ምንም ይሁን ምን መምከር፣ መወያየት፣ ችግርን በንግግር መፍታት መልካም እና ሰላማዊ አካሄድ ነው። እርግጥ ነው በአካታችነቱ፣ በወካይነቱ እና በአካሄዱ ኮሚሽኑ ላይ በርካታ ጥያቄዎች ተነስተዋል...
29/05/2024

ምንም ይሁን ምን መምከር፣ መወያየት፣ ችግርን በንግግር መፍታት መልካም እና ሰላማዊ አካሄድ ነው።

እርግጥ ነው በአካታችነቱ፣ በወካይነቱ እና በአካሄዱ ኮሚሽኑ ላይ በርካታ ጥያቄዎች ተነስተዋል። ቀናነት ካለ እነዚህንም ቢሆን በሂደት መፍታት ይቻላል።

ይህንን ሂደት ይበልጥ የተሳካ እና ተአማኒ ለማድረግ እና የመንግስትን ቆራጥነት ለማሳየት የፖለቲካ እስረኞችን፣ ታስረው የሚገኙ ጋዜጠኞችን እና ሌሎች በአስተሳሰባቸው ምክንያት ተይዘው የሚገኙ ዜጎችን በመፍታት ትልቅ ለውጥ ማምጣት ይቻላል ብዬ አስባለሁ። ለዚህ መቼም አይረፍድም።

ሰላም ለሀገራችን።

Meseret

በሜትር ታክሲ አሽከርካሪ ከመደፈር እንደተረፈች ድምፃዊት እግቱ ገለፀችበሜትር ታክሲ አሽከርካሪ ከመደፈር እንደተረፈች ድምፃዊት ትዕግስት ኃይሉ (እግቱ) ገለፀች። ትላንትና በከተማችን የሚሰራ ...
29/05/2024

በሜትር ታክሲ አሽከርካሪ ከመደፈር እንደተረፈች ድምፃዊት እግቱ ገለፀች

በሜትር ታክሲ አሽከርካሪ ከመደፈር እንደተረፈች ድምፃዊት ትዕግስት ኃይሉ (እግቱ) ገለፀች።

ትላንትና በከተማችን የሚሰራ የሜትር ታክሲ ሹፌር ሊደፍረኝ ነበረ ያለችው ድምፃዊቷ ከቤት ስወጣ ያደረሰኝን ሹፌር አመሻለሁ ሲለኝ ፕሮግራሜን ስጨርስ ቤቴን ስለሚያውቀውም መጀመሪያ በሰላም ስላደረሰኝም ወደ ቤት እንዲመልሰኝ ደወልኩለት ትንሽ ቢያረፍድም መጣ ስትል የተፈጠረውን አብራርታለች።

ቤት ልደርስ ትንሽ ሲቀረኝ መኪናውን አቁሞ ሲታገለኝ እወጋሻለሁ ብሎ ሲያስፈራራኝ፣ አምልጬ ወደ ቤት ገብቻለሁ። ሲታገለኝ ልብሴ ስለተቀደደ ኪሴ ውስጥ የነበረ ገንዘብ ሙሉ በሙሉ መኪና ውስጥ ወድቆብኛል ብላለች።

ትማሩበታላችሁ፣ የእኔን ስህተት ተዘናግታችሁ አትደግሙትም ብዬ አምናለሁ ስትል እግቱ የደረሰባትን ገልፃለች።

መንግስታዊ ገፈፋ 😓
29/05/2024

መንግስታዊ ገፈፋ 😓

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በአሁኑ ጊዜ በከባድ ፈተና ውስጥ እያለፈች ትገኛለች፤ እንደተነገረው የውጭው ፈተና ባይቀርላትም ከሱ በላይ ግን በውስጧ የሚነሡ ፈተናዎች ተልእኮዋ...
29/05/2024

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በአሁኑ ጊዜ በከባድ ፈተና ውስጥ እያለፈች ትገኛለች፤ እንደተነገረው የውጭው ፈተና ባይቀርላትም ከሱ በላይ ግን በውስጧ የሚነሡ ፈተናዎች ተልእኮዋን በአግባቡ እንዳትወጣ ዕንቅፋት ሆነውባታል፤ ከጥንት ጀምሮ የነበረ፣ በእግዚአብሔር ቃል የተቃኘ፣ የጸሊአ ሢመትና የጸሊአ ንዋይ መንፈሳዊ ባህሏ ተዘንግቶአል፤ በምትኩም ፍቅረ ሢመትና ፍቅረ ንዋይ ነግሦአል፤ መለያየትና መነቃቀፍ እየሰፉ መጥተዋል፣ ሃይማኖታችንንና ባህላችንን የማይወክሉ ኃይለ ቃላት፣ ኃላፊነት በጐደለው አገላለጽ እየተሰነዘሩ በጎቻችንን አስበርግገዋል፤ ድርጊቶቹ በበጎቻችን ዘንድ የነበረንን ተሰሚነትና ተደማጭነት ሊቀንሱብን እየተንደረደሩ ነው፡፡

ግንቦት 21 ቀን 2016 ቅዱስ ፓትርያርኩ በርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የተናገሩት

አንድ ጊዜ ቻርጅ ተደርጎ ለ1 አመት የሚያገለግል ድምፅ አልባ ጄኔሬተር የፈጠረው የወለጋው ፌዴሳ ሹማ። ፌዴሳ ሹማ ተወልዶ ያደገው በቄለም ወለጋ ሲሆን፣ በከተማው ውስጥ በኤሌክትሪክ ጥገና ሙያ...
29/05/2024

አንድ ጊዜ ቻርጅ ተደርጎ ለ1 አመት የሚያገለግል ድምፅ አልባ ጄኔሬተር የፈጠረው የወለጋው ፌዴሳ ሹማ።

ፌዴሳ ሹማ ተወልዶ ያደገው በቄለም ወለጋ ሲሆን፣ በከተማው ውስጥ በኤሌክትሪክ ጥገና ሙያው ይታወቃል፡፡ ይህን የኤሌክትሪክ ጥገና ሥራውን የመብራት መጥፋት እና መቆራረጥ ብዙ ጊዜ አስተጓጉሎበታል።

"ችግር ብልሃትን ይወልዳል" እንዲሉ ወጣቱ ሥራውን በተደጋጋሚ ላስተጓጎለበት ችግር መላ መዘየድ እንዳለበት አሰበ፤ አስቦም ወደ ተግባር ገባ።

ከብዙ ጥረት በኋላ አንድ ጊዜ ቻርጅ ተደርጎ እስከ አንድ ዓመት ድረስ አገልግሎት መስጠት የሚችል ቴክኖሎጂ እውን አደረገ።

ወጣት ፌዴሳ ሹማ በኃይል አማራጭ ዘርፍ አብዮት ይፈጥራል ተብሎ የታመነበት መሣሪያ የፈጠራ ባለቤት ነው፡፡

ፈዴሳ በሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር በሚመራው ልዩ የክረምት ወራት የቴክኖሎጂ እና የፈጠራ ሀሳቦች ማበልፀጊያ መርሐ ግብር ተሳትፎው ባገኘው ስልጠና እና ሙያዊ ድጋፍም ቴክኖሎጂውን ይበልጥ አዘምኖ መሥራት ችሏል።

ቴክኖሎጂው የመብራት አገልግሎት ከመስጠት ባለፈ ለሞባይል፣ ለቴሌቭዥን፣ ለፍሪጅ እና የትኛውንም ዓይነት የኤሌክትሮኒክስ መጠቀሚያዎችን ቻርጅ የሚያደርግ፣ የሚያንቀሳቅስ እና በገመድ እና ገመድ አልባ ቴክኖሎጂ መጠቀም እንዲቻል ተደርጎ የተሠራ ነው።

አንዴ የያዘውን ኃይል ደጋግሞ እያደሰ (recycling) ራሱን ቻርጅ ከማድረግ አልፎ ለረዥም ጊዜ ኃይል ማመንጨት የሚችለው ይህ ቴክኖሎጂ በሀገራችን ብቻ ሣይሆን ምን አልባትም በዓለማችን ላይ በኃይል አማራጭ ዘርፍ አብዮት መፍጠር እንደሚችል ተስፋ ተጥሎበታል።

ከ300 ዋት ጀምሮ እንደ ተጠቃሚው አቅም እና ፍላጎት የሚዘጋጀው ይህ ድምፅ አልባ ጄኔሬተር አንድ ጊዜ ቻርጅ ተደርጎ ከአንድ ዓመት በላይ አገልግሎት መስጠት እንደሚችል ነው ወጣቱ ያረጋገጠው።

በዚህም ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ በሀገራችን በቤቱ መብራት የማይጠፋበት ብቸኛው ሰው መሆኑን ከሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ የሚያመላክተው ሲል ኢቢሲ ዘግቧል።

አሁን ላይ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ወጣቱ የራሱን ኩባንያ የሚከፍትበትን እና ቴክኖሎጂው በስፋት ተመርቶ ለህብረተሰቡ ማድረስ የሚቻልበትን ሁኔታ እየተሠራ ይገኛል ተብሏል።

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ከሕግ ውጭ ግድያ፣ የሲቪል ሰዎች ሞት፣ የአካል ጉዳት፣ የንብረት ውድመትና ዘረፋን በተመለከተ ዛሬ ካወጣው ሪፖርት የተወሰደ: 1. ከየካቲት 15 እስከ 28 ...
28/05/2024

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ከሕግ ውጭ ግድያ፣ የሲቪል ሰዎች ሞት፣ የአካል ጉዳት፣ የንብረት ውድመትና ዘረፋን በተመለከተ ዛሬ ካወጣው ሪፖርት የተወሰደ:

1. ከየካቲት 15 እስከ 28 ቀን 2016 ዓ.ም. በአማራ ክልል፣ ምዕራብ ጎጃም ዞን፣ ደጋ ዳሞት ወረዳ (ዝቋላ ወገም፣ ፈረስ ቤት 01፣ ገሳግስ እና ጉድባ ሰቀላ ቀበሌዎች) እና ሰከላ ወረዳ (አጉት፣ ጉንድል እና አምቢሲ ቀበሌዎች እና ግሼ ዓባይ ከተማ) በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እና በታጣቂዎች መካከል የተካሄዱ የትጥቅ ግጭቶችን ተከትሎ በሲቪል ሰዎች ላይ ሞት፣ አካል ጉዳት እና የንብረት ውድመት ደርሷል።

2. የካቲት 20 ቀን 2016 ዓ.ም. በአማራ ክልል ሰሜን ጎጃም ዞን ሜጫ ወረዳ ብራቃት ቀበሌ በሚገኘው የጋፊት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን የአብነት ተማሪዎች የዕለቱን ትምህርትና ጉባኤ ከምሽቱ 5፡00 ሰዓት አካባቢ አጠናቀው ወደ ማደሪያ ጎጇቸው ከገቡ በኋላ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች አባላት ከሌሊቱ 6፡30 ሰዓት ገደማ ወደ ቦታው ደርሰው ተማሪዎችን “ውጡ” እያሉ ተኩስ በመክፈት ቀድመው በወጡ 11 ተማሪዎች ላይ ግድያ እንደፈጸሙ፤ ሌሎች 8 ተማሪዎችን በቁጥጥር ሥር አውለው ካሳደሩ በኋላ በማግስቱ ምንም ጥፋት የለባችሁም ብለው እንደለቀቋቸው ኢሰመኮ ለመረዳት ችሏል። በወቅቱ በአቅራቢያው የሚንቀሳቀስ የታጠቀ ኃይል እንዳልነበር ምስክሮች ለኢሰመኮ አስረድተዋል።

3. መጋቢት 2 ቀን 2016 ዓ.ም. ከአማራ ክልል፣ ኦሮሞ ብሔረሰብ ልዩ ዞን የተነሱ ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች በሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር በኤፍራታና ግድም እና ቀወት ወረዳዎች በሚገኙ የተወሰኑ ቀበሌዎች ላይ በፈጸሙት ጥቃት በሲቪል ሰዎች ላይ ግድያ መፈጸሙን፣ የአካል ጉዳት መድረሱን፣ ንብረት መውደሙን፣ መኖሪያ ቤቶች መቃጠላቸውን እንዲሁም የቀንድ ከብቶችና ባለ ሦስት እግር ተሽከርካሪዎች መዘረፋቸውን ኢሰመኮ ተረድቷል።

4. መጋቢት 6 ቀን 2016 ዓ.ም. በአማራ ክልል በባሕር ዳር ከተማ ዘንዘልማ አካባቢ አቶ ብርሃኑ ሽባባው አካል፣ አቶ በላይ አካል እና አቶ ተሾመ ይበልጣል የተባሉ ነዋሪዎች አንዱ በሚሠራበት ሱቅ እና ሁለቱ በመኖሪያ ቤታቸው ውስጥ ለጥያቄ ትፈለጋላችሁ በሚል በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር ከዋሉ በኋላ መጋቢት 7 ቀን 2016 ዓ.ም. በባሕር ዳር ከተማ ቀበሌ 14 በተለምዶ ጉዶ ባሕር አካባቢ የፊጥኝ እንደታሰሩ በጥይት ተገድለው ተገኝተዋል።

5. በባሕር ዳር ከተማ ዳግማዊ ምኒልክ ክፍለ ከተማ ጋጃ መስክ ተብሎ በሚጠራ ስፍራ መጋቢት 29 ቀን 2016 ዓ.ም. ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት አካባቢ ማንነታቸው ባልታወቁ አካላት በተፈጸመ ጥቃት ሶላት ስግደት አከናውነው ወደ ቤታቸው በመመለስ ላይ የነበሩ የእስልምና ተከታይ 5 ሰዎች (አራቱ የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ) ተገድለዋል።

6. ሚያዝያ 7 ቀን 2016 ዓ.ም ከጧቱ 3፡00 ሰዓት ላይ በአማራ ክልል ደቡብ ጎንደር ዞን እስቴ ወረዳ አጎና በተባለች መለስተኛ ቀበሌ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ከእስቴ ወረዳ ወደ ላይ ጋይንት ወረዳ በመጓዝ ላይ እያሉ በአካባቢው በሚንቀሳቀሱ የታጠቁ ኃይሎች (በተለምዶ ፋኖ) ድንገተኛ የደፈጣ ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ ታጣቂዎቹ አካባቢውን ጥለው እንደሸሹ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ወደ ቦታው (አጎና ቀበሌ) በመግባት 7 (1 ሴት እና 6 ወንዶች) ሲቪል ሰዎች ላይ ከሕግ ውጪ ግድያ መፈጸማቸውን፣ ከ15 በላይ የሚሆኑ የቆርቆሮ ክዳን ያላቸው መኖሪያ ቤቶች እና 3 የገለባ ቤቶችና ንብረት መቃጠላቸውን እንዲሁም ከ100 በላይ የሚሆኑ የቀበሌው ነዋሪዎች ወደ ሌላ አካባቢ የተፈናቀሉ መሆኑን የቀበሌው ነዋሪዎችና ተጎጂዎች ለኢሰመኮ ገልጸዋል። በወቅቱም ግለሰቦቹ ቃጠሎውን ለመቆጣጠርና ለማጥፋት ሙከራ ያደረጉ ቢሆንም የመንግሥት የጸጥታ ኃሎች ጥይት በመተኮስ እንደከለከሏቸውና ሆን ተብሎ የግለሰቦቹ ቤት እና ንብረት እንዲቃጠል እንደተደረገም ጨምረው አስረድተዋል። በዚህም የተነሳ በመኖሪያ ቤቶቹ ውስጥ የነበሩ የቤት ቁሳቁስ፣ አልባሳት፣ እህል እንዲሁም የአንድ ግለሰብ 8 በጎች ሙሉ በሙሉ እንደተቃጠሉ ለመረዳት ተችሏል።

7. ግንቦት 4 ቀን 2016 ዓ.ም. ከቀኑ ከ7፡00 ሰዓት አካባቢ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ቀወት ወረዳ ተሬ ቀበሌ ውስጥ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት በጉሎ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ግቢ ውስጥ 2 ሲቪል ሰዎች ሲገደሉ አንድ ሴት መምህርትን ጨምሮ ሌሎች 9 ሲቪል ሰዎች የቆሰሉ መሆኑን ኢሰመኮ ተረድቷል።

8. ታኀሣሥ 15 ቀን 2016 ዓ.ም. በግምት ከጠዋቱ 1፡30 ሰዓት አካባቢ በኦሮሚያ ክልል በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ጉዱሩ ወረዳ ውስጥ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት በየነ ጢቂ፣ ጉደታ ፊጤ፣ ሀብታሙ ንጋቱ፣ ታዴ መንገሻ፣ ዳመና ሊካሳ፣ ዱጋሳ ዋኬኔ፣ ሕፃን አብዲ ጥላሁን እና ሕፃን ኦብሳ ተሬሳ የተባሉ 8 ሰዎች ተገድለዋል። በተጨማሪም ስንታየሁ ታከለ፣ ሽቶ እምሩ፣ ተሜ ኑጉሴ እና አለሚ የተባሉት ላይ ደግሞ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል። በአካባቢው የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (በተለምዶ “ኦነግ ሸኔ”) በሰፊው ይንቀሳቀስ የነበረ መሆኑን እና የሀገር መከላከያ ሰራዊት በአካባቢው በሚደረጉ ውጊያዎች አልፎ አልፎ በድሮን ይጠቀም የነበረ መሆኑን ኢሰመኮ ያነጋገራቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል።

9. ጥር 9 ቀን 2016 ዓ.ም. በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ለሌላ ግዳጅ አካባቢውን ለቅቆ መውጣቱን ተከትሎ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (በተለምዶ “ኦነግ ሸኔ”) ታጣቂዎች በማግስቱ ጥር 10 ቀን 2016 ዓ.ም. አካባቢውን ከተቆጣጠሩ በኋላ “ለመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ምግብ ስታቀርቡ ነበር” በሚል ምክንያት በወረዳው 01 ቀበሌ የሚገኘው ሳላይሽ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ጥበቃ የነበሩት አቶ ስዩም ካሴን በጥይት በመምታት መግደላቸውን እንዲሁም ከበደ ዓለማየሁ የተባሉ ነዋሪን ከመኖሪያ ቤታቸው ከወሰዷቸው በኋላ በአካባቢው ጫካ ውስጥ አስክሬናቸው ወድቆ መገኘቱን ኢሰመኮ አረጋግጧል።

10. ጥር 13 ቀን 2016 ዓ.ም. ከጠዋት 2 ሰዓት ጀምሮ ማንነታቸው ያልታወቀ ታጣቂዎች በኦሮሚያ ክልል፣ ምዕራብ ጉጂ ዞን፣ ገላና አባያ ወረዳ ኤርገንሳ ቀበሌ ለሚኖሩ ነዋሪዎች የኩፍኝ በሽታ ክትባት ለመስጠት በመጓዝ ላይ በነበሩ ሠራተኞች ላይ በፈጸሙት ጥቃት የገላና አባያ ወረዳ አስተዳደር ጤና ጽሕፈት ቤት ምክትል ኃላፊን ጨምሮ ሁለት ሲቪል ሰዎች ተገድለዋል፤ እንዲሁም 3 ሰዎች የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል። ጥቃቱን ተከትሎ በገላና አባያ ወረዳ ጤና ጽሕፈት ቤት ሲሰጥ የነበረው የሕክምና አገልግሎት እና የኩፍኝ በሽታ መከላከያ ክትባት ስርጭት ተስተጓጉሎ እንደነበረ ለማወቅ ተችሏል።

11. ከየካቲት 28 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ በአማራ ክልል ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ የአማራ ታጣቂ ቡድኖች የኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ በሚገኙ አዋሳኝ ቀበሌዎች በሲቪል ሰዎች ላይ በተከታታይ በፈጸሟቸው ጥቃቶች 25 ሲቪል ሰዎችን ገድለዋል፤ 4 ሲቪል ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት አድርሰዋል እንዲሁም ለጊዜው ቁጥራቸው ያልታወቀ ሲቪል ሰዎችን አግተው ወስደዋል። በታጣቂዎቹ በተፈጸመው ጥቃት በርካታ የመኖሪያ ቤቶችም ተቃጥለዋል። በተመሳሳይ በዚሁ ደራ ወረዳ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (በተለምዶ “ኦነግ ሸኔ”) ታጣቂዎች ከኅዳር ወር 2016 ዓ.ም. ጀምሮ በወረዳው በሚገኙ የተለያዩ ቀበሌዎች በሲቪል ሰዎች ላይ በፈጸሟቸው ጥቃቶች 15 ሲቪል ሰዎች ተገድለዋል፤ ቁጥራቸው ለጊዜው በትክክል ያልታወቀ በርካታ ነዋሪዎችን አግተው ወስደዋል፤ በርካታ የቀንድ ከብቶችን ዘርፈዋል እንዲሁም መኖሪያ ቤቶችን አቃጥለዋል።

12. መጋቢት 1 ቀን 2016 ዓ.ም. በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ኖኖ ወረዳ ስልካምባ ከተማ ላይ የኦሮሞ ነጸነት ሰራዊት (በተለምዶ “ኦነግ ሸኔ”) ታጣቂዎች በከፈቱት ጥቃት የወረዳው አበዪ ሄቤን ቀበሌ ነዋሪ የነበሩ አቶ ሹመቴ ፋርስ እና ወ/ሮ ተቀባ አበጋዝ የተባሉ አረጋዊያን በመኖሪያ ቤቶቻቸው ፊት ለፊት ተገድለዋል። በወቅቱ የነበረውን ሁኔታ አንድ የቀበሌው ነዋሪ ለኢሰመኮ ሲያስረዱ፦ “የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በብዛት ወደ ስልካምባ ከተማ እያለፉ ነበር፤ ለሰዓታትም ተኩስ ነበር፤ በኋላ ላይ ታጣቂዎቹ ከከተማው ማፈግፈግ ሲጀምሩ ያገኙትን ነዋሪ ያለማመንታት ተኩሰው እየገደሉ ይሸሹ ነበር። አቶ ሹመቴ እና ወ/ሮ ተቀባም ያለምንም ምክንያት በቡድኑ ተገድለዋል” ብለዋል።

13. መጋቢት 16 ቀን 2016 ዓ.ም. ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00 ባሉት ሰዓታት ማንነታቸው በውል ያልታወቀ የታጠቁ ቡድኖች በኦሮሚያ ክልል፣ ምዕራብ አርሲ ዞን ዶዶላ ከተማ 02 ቀበሌ ውስጥ 7 ሰዎችን ተኩሰው መግደላቸውን ለማወቅ ተችሏል። በዕለቱ በተፈጸመ ጥቃት የቀበሌው ነዋሪ የሆነ እና የምዕራብ አርሲ ሃገረ ስብከት የዶዶላ ደብረ ቅዱሳን ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ የሆነ ግለሰብ፣ ከባለቤቱ እና ከሁለት ልጆቹ ጋር በመኖሪያ ቤታቸው እያሉ እንዲሁም ሌላ አንድ ዲያቆን ከባለቤቱ እና ከእህቱ ጋር በመኖሪያ ቤታቸው መገደላቸውን ለማወቅ ተችሏል። በተመሳሳይ ቀን በዶዶላ ወረዳ ደነባ ቀበሌ በግምት ከምሽቱ 5፡00 ሰዓት አካባቢ 4 የቀበሌው ነዋሪዎች ማንነታቸው ባልታወቀ የታጠቁ ሰዎች/ቡድኖች በጥይት ተመተው ሲገደሉ 5 ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን ለማወቅ ተችሏል።

14. የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (በተለምዶ “ኦነግ ሸኔ”) በኦሮሚያ ክልል፣ ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን፣ አመያ ወረዳ “የመንግሥት ሠራተኞችና የመንግሥት ጸጥታ ኃይል አባላት ቤተሰቦች ናችሁ” በሚል ወይም “ለመንግሥት አካላት ትብብር አድርጋችኋል” በሚል ምክንያት በወረዳው በተለያዩ ቀበሌዎች በየካቲት እና ሚያዝያ ወራት በፈጸማቸው ተከታታይ ጥቃቶች በሲቪል ሰዎች ላይ ግድያ፣ አካል ጉዳት፣ እገታ፣ ንብረት ውድመት እና ዘረፋ ፈጽሟል። ለምሳሌ በወረዳው አቡዬ ጀብላል ቀበሌ የካቲት 7 ቀን 2016 ዓ.ም. በፈጸመው ጥቃት 11 ሲቪል ሰዎችን ገድሏል፤ መኖሪያ ቤቶችንና ሞተር ብስክሌቶችን አቃጥሏል፤ የቀንድ ከብቶችን ዘርፏል። መጋቢት 27 ቀን 2016 ዓ.ም. በወረዳው ቆታ ከተማ ላይ በፈጸመው ጥቃት 31 ሲቪል ሰዎችን ገድሏል፣ 3 ሲቪል ሰዎችን አቁስሏል፣ የቀንድ ከብቶችንና ሌሎች ንብረቶችን ዘርፏል እንዲሁም ንብረቶችን አቃጥሏል። ሚያዝያ 8 ቀን 2016 ዓ.ም. በወረዳው ደራ ቲርቲሪ ቀበሌ ላይ ታጣቂ ቡድኑ በፈጸመው ጥቃት 2 ሲቪል ሰዎችን ገድሏል፣ ከ100 በላይ የተለያዩ የቀንድ ከብቶች ዘርፏል እንዲሁም በሚያዝያ 13 ቀን 2016 ዓ.ም. በጎምንቦሬ አሊይ ቀበሌ 36 የቀንድ ከብቶችንና 3 የሞቶር ብስክሌት ዘርፏል።

15. በሲዳማ ክልል በወንዶ ገነት ወረዳ፣ ኤዶ ቀበሌ ከዚህ ቀደም የተፈጠረውን የጸጥታ ችግር ተከትሎ በአካባቢው ተሰማርቶ ጸጥታ ሲያስጠብቅ የነበረው የፌዴራል ፖሊስ የጸጥታ ኃይል ከአካባቢው መልቀቁን ተከትሎ የካቲት 14 ቀን 2016 ዓ.ም. በቀበሌው ነዋሪ በሆኑ እና ወደ ኦሮሚያ ክልል የመካለል ጥያቄ ሲያነሱ በቆዩ የኦሮሞ ብሔር ተወላጆች እና በወረዳው የጸጥታ አካላት መካከል በተከሰተ ግጭት ቢያንስ አንድ ሰው የአካል ጉዳት እንደደረሰበትና ከሐዋሳ ወደ ወንዶ ገነት ከተማ የሚወስደው ዋና መንገድም ለሰዓታት ተዘግቶ እንደነበረ ለማወቅ ተችሏል። በተመሳሳይ የካቲት 17 ቀን 2016 ዓ.ም. ከቀኑ 6፡ 00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ምሽቱ 1፡00 ሰዓት ድረስ በቀበሌው በሁለቱ ወገኖች መካከል እንደገና የተኩስ ልውውጥ ተካሂዶ በግጭቱ የአንድ ሰው ሕይወት ሲያልፍ 4 ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል። በኤዶ ቀበሌ የተከሰተውን አለመረጋጋት ተከትሎ አጎራባች በሆነው እና በተመሳሳይ ወደ ኦሮሚያ ክልል የመካለል ጥያቄ ሲነሳበት በነበረው በወተራ ቀጨማ ቀበሌም በተወሰነ መልኩ አለመረጋጋት እንደነበረ ለመረዳት ተችሏል። ግጭቱን ተከትሎ የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ወደ አካባቢው ተመልሶ በመግባት ግጭቱን ማስቆም ችሏል። ይህ ግጭት በአካባቢው እየጨመረ የመጣ የጸጥታ ሥጋት እና ለሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች መነሻ ሊሆኑ የሚችሉ ሁኔታዎች መኖራቸውን ያሳያል።

16. የካቲት 22 ቀን 2016 ዓ.ም. በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ ባስኬቶ ዞንላስካ ዙሪያ ወረዳ፣ ቡኒ ባሳ ክላስተር ከደቡብ ኦሞ ዞን፣ ሰላማጎ አካባቢ የመጡ መሆናቸው የተገለጸ ታጣቂዎች የአካባቢው ነዋሪዎች ከብቶችን ለመዝረፍ በተደጋጋሚ ጥይት በመተኮስ በአካባቢው በነበረው የኢንቨስትመንት ማሳ በጥበቃ ሥራ ላይ ተሰማርተው የነበሩ 4 ሰዎችን ገድለዋል። በአካባቢው ከዚህ ቀደምም ተመሳሳይ ጥቃቶች የተፈፀሙ መሆኑንና ከመስከረም 2016 ዓ.ም. ጀምሮ ባሉት ጊዜያት የአሁኑን ጨምሮ 10 ሰዎች (4 ሴቶች እና 6 ወንዶች) በተመሳሳይ ሁኔታ መገደላቸውን እንዲሁም የአካባቢው ነዋሪዎች 66 ከብቶች እና 29 ፍየሎች መዘረፋቸውን ኢሰመኮ ተረድቷል።

17. መጋቢት 27 ቀን 2016 ዓ.ም. ከቀኑ 11.00 ሰዓት አካባቢ ከኦሮሚያ ክልል፣ ምዕራብ ጉጂ ዞን፣ ገላና ወረዳ ቀበሌዎች የመጡ ታጣቂዎች በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ጎርካ ወረዳ በፈጸሙት ጥቃት አንድ የእርሻ ሥራ ላይ የነበረ የቀበሌው ነዋሪ በተተኮሰበት ጥይት ተገድሏል። በተመሳሳይ መጋቢት 30 ቀን 2016 ዓ.ም. ከቀኑ 11.00 ሰዓት አካባቢ በዚሁ ወረዳ ቆቦ ቀበሌ በታጣቂዎቹ በተፈፀመ ጥቃት ከብት በመጠበቅ ላይ የነበረ አንድ ሕጻን በተተኮሰበት ጥይት ተመቶ ተገድሏል። ታጣቂዎቹ ሚያዝያ 8 ቀን 2016 ዓ.ም. በግምት ከቀኑ 10፡00 ሰዓት አካባቢ በወረዳው ዳኖ ቀበሌ በፈጸሙት ሌላ ጥቃት 2 በእርሻ ሥራ ላይ የነበሩ የቀበሌው ነዋሪዎች በተተኮሰባቸው ጥይት ተገድለዋል። በተመሳሳይ ሚያዝያ 13 ቀን 2016 ዓ.ም. በግምት ከቀኑ 6፡00 ሰዓት አካባቢ በወረዳው ቆቦ በተባለ ቀበሌ በተፈፀመ ተጨማሪ ጥቃት ከብቶች በመጠበቅ ላይ የነበሩ 3 ሕፃናት እና አንድ በእርሻ ሥራ ላይ የነበረ ግለሰብ በድምሩ 4 ሰዎች በተተኮሰባቸው ጥይት ተመተው የተገደሉ ሲሆን ከሟቾቹ መካከል ሁለቱ ወንድማማቾች መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል። እነዚህ ታጣቂዎች በኮሬ ዞን ጎርካ ወረዳ በሚገኙ ቀበሌዎች ላይ ተደጋጋሚ ጥቃቶችን እየፈጸሙ የሚገኙ ሲሆን፣ ከግድያ በተጨማሪ በአካባቢው ያሉ ከብቶችን ዘርፈው እንደሚሄዱ እንዲሁም የአካባቢው ነዋሪዎችን የእርሻ ሥራዎችን እንዳይሰሩ እያደረጉ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።

(ይህን ሪፖርት ያወጣው የመንግስት ተቋም ቢሆንም የመንግስት ሚድያዎች ለህዝብ እንደማያደርሱት በማሰብ እንደወረደ አቅርቤዋለሁ)

Elias Meseret

የእስራኤል ታንኮች ዛሬ ወደ ማዕከላዊ የራፋህ ከተማ ሰንጥቀው መግባታቸውን የሃገሪቱ የመከላከያ ሰራዊት አስታወቀ። በውግያው 45 ስቪል ፍልስጤማውያን መገደላቸውን የፍልስጤም ባለስልጣናት ገልጸ...
28/05/2024

የእስራኤል ታንኮች ዛሬ ወደ ማዕከላዊ የራፋህ ከተማ ሰንጥቀው መግባታቸውን የሃገሪቱ የመከላከያ ሰራዊት አስታወቀ።
በውግያው 45 ስቪል ፍልስጤማውያን መገደላቸውን የፍልስጤም ባለስልጣናት ገልጸዋል።

እስራኤል አሜሪካን ጨምሮ ከተለያዩ ሐገራትና ዓለም አቀፍ ተቋማት ወደ ራፋሕ የምታደርገው ወታደራዊ ዘመቻ ከፍተኛ የሰብአዊ ቀውስ ያስከትላል በማለት ቢቃወሙትም እስራኤል ግን ጥቃቷን ቀጥላበታለች።

የአይን እማኞች ለአዣንስ ፍራንስ እንዳሉት የእስራኤል ታንኮች ወደ ማዕከላዊ የራፋሕ ከተማ በመግባት አልአዋዳ በተባለ መንደር መሽገዋል መባሉን የጀርመን ድምጽ ዘግቧል ።

27/05/2024

"እኔ አልወሰድኳትም፣ የት እንዳለችም አላውቅም"  ጋዜጠኛ ጥበቡ በለጠይህች የ8ወር ህፃን ማስተዋል አንዳርጌ እንደምትባልና እናትና አባቷን በሚያሳዝን ሁኔታ አጥታ አሳዳጊ እንደምትፈልግ በፌስ...
27/05/2024

"እኔ አልወሰድኳትም፣ የት እንዳለችም አላውቅም"
ጋዜጠኛ ጥበቡ በለጠ

ይህች የ8ወር ህፃን ማስተዋል አንዳርጌ እንደምትባልና እናትና አባቷን በሚያሳዝን ሁኔታ አጥታ አሳዳጊ እንደምትፈልግ በፌስቡክ ሰዎች አጋርተውት ተመልክተን የምናከብረው የአሀዱ ሬድዮ ስራ አስኪያጅ ጋዜጠኛ ጥበቡ በለጠ"እኔ አሳድጋታለሁ ብሎ ወስዷታል"የሚል መረጃ አይተን ሁላችንም ደስ ብሎን ነበር!!

ትላንት በውስጥ መስመር አንዲት እህቴ መልዕክት ላከችልኝ "ይህችን ህፃን ጋዜጠኛ ጥበቡ አሳድጋታለሁ ብሎ የነበረ ቢሆንም ያለችበትን አድራሻ አጣነው፣ እባክህን እንፈልጋት🙏"አለችኝ!

ለማረጋገጥም የማከብረው ጋዜጠኛ ጥበቡ በለጠ ጋር ስደውል በትህትና እንዲህ አለኝ:- "እኔ ጋር አልደረሰችም፣ አድራሻዋንም አላገኘሁም፣የት እንዳለችም አላውቅም፣ መረጃውን ያጋሩ ሰዎች ያለችበትን ይንገሩኝና ህጋዊ ነገሮችን ጨርሰን እንደ ልጄ አሳድጋታለሁ" ብሏል!!

ህፃን #ማስተዋል የት ነው ያለችው?ምንስ ሁኔታ ላይ ናት? እባካችሁን #ሼር በማድረግ በደግነት አባት ለመሆን ከተዘጋጀው ጋር እናገናኛት🙏

© ሄኖክ ፍቃዱ

27/05/2024

🤭🤭

በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስለሺ በቀለ ያቀረቡት መልቀቂያ ተቀባይነት ማግኘቱ ተሰማ።በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው እያገለገሉ የሚገኙት የቀድሞው የውኃ ሀብት ሚኒስትር ስለሺ በቀለ...
26/05/2024

በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስለሺ በቀለ ያቀረቡት መልቀቂያ ተቀባይነት ማግኘቱ ተሰማ።

በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው እያገለገሉ የሚገኙት የቀድሞው የውኃ ሀብት ሚኒስትር ስለሺ በቀለ (ዶ/ር) ከተሾሙበት የመንግሥት የሥራ ኃላፊነት ለመልቀቅ ያቀረቡት ጥያቄ ተቀባይነት ማግኘቱን ምንጮች ገለጹ።

ስለሺ በቀለ (ዶ/ር) በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደርነት ሹመታቸው ብቻ ሳይሆን ሙሉ በሙሉ ከመንግሥት መዋቅር በመልቀቅ በግል ተቀጥረው በሙያቸው ለማገልገል ማቀዳቸውንም ምንጮቹ ገልጸዋል። ስለሺ (ዶ/ር) በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የሥልጣን ዘመን ወቅት የፓርቲ አባል ሳይሆኑ የመንግሥት መዋቅርን መቀላቀላቸው የሚታወስ ሲሆን፣ ከዚያ አስቀድመው በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በውኃ ምኅንድስና ሙያቸው በግል ተቀጥረው ሲያገለግሉ ነበር። ስለሺ በቀለ (ዶ/ር) ከአሜሪካ አምባሳደርነታቸው በመልቀቅ ወደ ቀደመ የግል ሥራቸው ለመመለስ መፈለጋቸውን የጠቀሱት የሪፖርተር ምንጮች፣ ጥያቄያቸውንም ለመንግሥት አቅርበው ተቀባይነት ማገኘቱን ገልጸዋል።

አምባሳደር ስለሺ በቀለ መልቂቂያ ስለማቅረባቸውና መልቀቂያውም ተቀባይነት ማግኘቱን በመጥቀስ መረጃውን እንዲያረጋግጡ የጠየቅናቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ነብዩ ተድላ (አምባሳደር)፣ ስለዚህ ጉዳይ የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ገልጸዋል።

ቃል አቀባዩ አምባሳደር ነብዩ በሳምንቱ ውስጥ የተካሄዱ የውጭ ግንኙነት ጉዳዮችን አስመልክቶ ባለፈው ሐሙስ ግንቦት 15 ቀን 2016 ዓ.ም. በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ሰሞኑን ለ24 የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባልደረቦች የአምባሳደርነት ሹመት መስጠታቸውን ተናግረው ነበር።

ከዚህ ቀደም በአምባሳደርነት የሚመደቡ ተሿሚዎች ከውጭ ጉዳይ ይመረጡ እንዳልነበረ ያስታወሱት ቃል አቀባዩ፣ ሰሞኑን ሹመት ያገኙት 24ቱም አምባሳደሮች ግን ከውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የተመረጡ መሆናቸውንና ይህም በተቋሙ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የተደረገ እንደሆነ አስረድተዋል።

ሹመቱ ብቃትንና ልምድን መሠረት ያደረገ መሆኑን ገልጸው፣ ሁሉም አምባሳደሮች በዲፕሎማሲ ዘርፍ አገራቸውን ሲያገለግሉ የቆዩና ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተጣለበትን ከፍተኛ አገራዊ አደራ ለመወጣት የሚያግዙና ለቦታው ይመጥናሉ ተብሎ የታመነባቸው መሆናቸውን ገልጸዋል።

የተሾሙት 24 አምባሳደሮች የሥራ ምደባ (የሚመደቡበት አገር) በሚቀጥለው ሳምንት የሚታወቅ ይሆናል።

መንግሥት አምባሳደር ስለሺ ያቀረቡትን ጥያቄ ከመቀበሉ ባሻገር እርሳቸውን የሚተካ ሌላ አምባሳደር ለመመደብ መሰናዳቱንም የሪፖርተር ምንጮች ጠቁመዋል። እንደ ምንጮቹ መረጃ፣ አምባሳደር ስለሺ በቀለን (ዶ/ር) በመተካት በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው የሚመደቡት በአሁኑ ወቀት በተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው እያገለገሉ የሚገኙት አምባሳደር ሌንጮ ባቲ ናቸው። ነገር ግን፣ ሪፖርተር ይህንን መረጃ ኦፊሳላዊ በሆነ መንገድ ለማረጋገጥ አልቻለም።

በአሜሪካን የኒውዮርክ ግዛት ውስጥ በሚገኘው በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋናው መሥሪያ ቤት፣ የማኅበራዊ ጉዳዮች ክፍል የኢኮኖሚና ዘላቂ ልማት አማካሪ ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት አምባሳደር ስለሺ (ዶ/ር)፣ ለመጀመሪያ ጊዜ የኢትዮጵያ መንግሥት መዋቅርን የተቀላቀሉት በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ መምህር በነበሩበት ወቅት ወዳጅና ባልደረባቸው የነበሩት የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ባቀረቡላቸው ጥሪ ነበር።

የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም አገራቸውን እንዲያለግሉ ያቀረቡላቸውን ጥሪ በመቀበል፣ ከተመድ የአማካሪነት ሥራቸው ለቀው ወደ ኢትዮጵያ የተመለሱት ስለሺ (ዶ/ር) የውኃ፣ መስኖና ኤነርጂ ሚኒስትር በመሆን የሥራ አስፈጻሚውን መንግሥት ለመጀመሪያ ጊዜ በጥቅምት ወር 2009 ዓ.ም. ተቀላቅለዋል።

የውኃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትርነት የተሾሙት ስለሺ (ዶ/ር)የገዥው ፓርቲም ሆነ የየትኛውም የፖለቲካ ድርጅት አባል ያልነበሩ ከመሆናቸው ባሻገር፣ በ2012 ዓ.ም. ከሚኒስትርነት ኃላፊነታቸው ለመልቀቅ ጭምር ጥያቄ አቅርበው የሚተካቸው ሰው እስኪገኝ ደረስ በኃላፊነት እንዲቆዩ ተደርጎ ነበር። በኋላ ግን ብልፅግና ፓርቲን በመቀላቀል በ2013 ዓ.ም. መጨረሻ ላይ በተካሄደው አገር አቀፍ ምርጫ በአዲስ አበባ ከተማ ተወዳድረው በማሸነፍ፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ሆነዋል። ነገር ግን ምርጫውን ተከትሎ በ2014 ዓ.ም. መጀመሪያ ላይ በተመሠረተው የጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ካቢኔ ውስጥ በሚኒስትርነት ሳይሾሙ ቀርተዋል። በኋላም የአሜሪካ አምባሳደር ሆነው ተሹመዋል።

የውኃ፣ መስኖና ኤነርጂ ሚኒስትር ሆነው ካገለገሉ አምስት ዓመታት በኋላም ያለፉትን ሁለት ዓመታት በአምባሳደርነት ያገለገሉት ስለሺ (ዶ/ር)፣ በተለይም የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ዋና ተደራዳሪ በመሆን ባበረከቱት ከፍተኛ ዲፕሎማሲያዊ ተጋድሎ በኢትዮጵያውያን ዘንድ በስፋት የሚታወቁ ሲሆን፣ አንድ የውጭ ሚዲያ፣ ‹‹ኢትዮጵያ የህዳሴ ግድቡን ከግብፅ ጋር በመሆን በጋራ ለማስተዳደር ፈቃደኛ ትሆን?›› ሲል ላቀረበላቸው ጥያቄ ‹‹ግድቡ የኔ ነው!›› በማለት በሰጡት ምላሽ ከፍተኛ ዝናን አትርፈዋል።

አምባሳደር ስለሺ በሲቪል ኢንጂነሪንግ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ያገኙ ሲሆን፣ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ደግሞ ዩናይትድ ኪንግደም ከሚገኘው ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ኒውካስል በሃይድሮሊክ ኢንጂኒየሪንግና ሃይድሮሎጂ አግኝተዋል። በኋላም የዶክትሬት ዲግሪያቸውን ጀርመን አገር ከሚገኘው ከድሬስደን ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ቴክኖሎጂ አግኝተዋል።

አምባሳደር ስለሺ (ዶ/ር) ከመንግሥት የሥራ ኃላፊነት ለመልቀቅ የወሰኑት፣ ቀጣይ ጊዜያቸውን ከዚህ ቀደም ወደነበሩበት ተመድ ወይም መሰል ዓለም አቀፍ ተቋም በመመለስ በሙያቸው በማገልገል ለማሳለፍ በመፈለጋቸው እንደሆነ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ጠቁመዋል።

@ሪፖርተር

ትላንተ ሳሪስ አደይ አበባ ቀለበት መንገድ ላይ የደረሰ አደጋ።
25/05/2024

ትላንተ ሳሪስ አደይ አበባ ቀለበት መንገድ ላይ የደረሰ አደጋ።

ለዛ አዋርድ
25/05/2024

ለዛ አዋርድ

በኪነ-ጥበብ ሥራዎችና ባለሙያዎች ላይ የሚደረጉ ጫናዎች እንዲቆሙ ተጠየቀ።በኪነ-ጥበብ ባለሙያዎችና የኪነ-ጥበብ መድረኮች ላይ እየደረሱ ያሉ ጫናዎች ከዕለት ዕለት እየበረቱ መምጣታቸው አሳስቦኛ...
24/05/2024

በኪነ-ጥበብ ሥራዎችና ባለሙያዎች ላይ የሚደረጉ ጫናዎች እንዲቆሙ ተጠየቀ።

በኪነ-ጥበብ ባለሙያዎችና የኪነ-ጥበብ መድረኮች ላይ እየደረሱ ያሉ ጫናዎች ከዕለት ዕለት እየበረቱ መምጣታቸው አሳስቦኛል ሲል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል ባወጣው መግለጫ ገልጿል።

የማዕከሉ ዋና ዳይሬክተር ያሬድ ሃይለማሪያም “ኪነ-ጥበብን ማፈን የሃሳብ ነፃነትን መጋፋት ስለሆነ ተገቢ ጥበቃ ሊደረግለት ይገባል" ሲሉ ተናግረዋል።

የኪነ-ጥበብ ዘርፉ ሰፊ የሕግ ጥበቃ ያለው መሆኑን ያነሳው መግለጫው፥ በተለይም በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ-መንግስት አንቀፅ 29 ላይ በግልጽ እንደተደነገገው ጥበብ እንደ አንድ ሃሳብን በነፃነት የመግለጫ መንገድ የህግ ከለላና እውቅና ማግኘቱን ጠቅሷል።

ማዕከሉ በጥር ወር “ቧለቲካ" የተሰኘው የቴአትር መድረክ መከልከሉ፤ በሚያዚያ ወር "እብደት በህብረት" የተሰኘው የመድረክ ተውኔት አዘጋጅና ተዋናይ ባለሙያዎች መታሰራቸውን አንስቷል።

በተጨማሪም፥ "የተለያዩ እንደ ስነ-ፅሁፍ፣ ተውኔት እና የመሳሰሉት ስራዎች የሚቀርቡባቸው የጥበብ መድረኮች የስብሰባ ፍቃድ ያስፈልጋችኋል በሚል መስተጓጎጎላቸውን ተረድተናል" ሲል አንስቷል።

መግለጫው ባስቀመጠው ምክረ ኃሳብም፥ መንግስት ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት እንድያከብር፤ በዘፈቀደ እንዳይጣስ ጥበቃ እንድያደርግ፤ በሥራቸው ምክንያት የታሰሩ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች እንዲፈቱ ወይም የተፋጠነ ፍትህ እንዲያገኙና የተከለከሉ የኪነ-ጥበብ መድረኮችም በነጻነት እንዲሰሩ ሲል ጠይቋል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

ተዋናይ አማኑኤል የሺ ወንድ በእስር የሚገኘውን የተዋናይ አማኑኤል ሀብታሙን ልጅ ይዞ በለዛ አዋርድ ተገኝቷል።  አማኑኤል የሺወንድ እና አማኑኤል ሐብታሙ የዘንድሮው "ለዛ አዋርድ" ምርጥ ወን...
24/05/2024

ተዋናይ አማኑኤል የሺ ወንድ በእስር የሚገኘውን የተዋናይ አማኑኤል ሀብታሙን ልጅ ይዞ በለዛ አዋርድ ተገኝቷል።

አማኑኤል የሺወንድ እና አማኑኤል ሐብታሙ የዘንድሮው "ለዛ አዋርድ" ምርጥ ወንድ ተዋናይ ዘርፍ ተወዳዳሪ መሆናቸው ይታወቃል ።
አማኑኤል ሐብታሙ በእስር ላይ ቢገኝም ልጁ ተወክላ ተገኝታለች ።

ከአቅሜ በላይ ነው!በመንግስት ፕሮጀክቶች ላይ የሚቀርብ የካሳ ጥያቄዎች በሙሉ የመክፈል አቅም እንደሌለው የገንዘብ ሚኒስትር ገለፀሚኒስትሩ እንዳለዉ የፌደራል ፕሮጀክቶች በሚተገበሩበት ወቅት  ...
24/05/2024

ከአቅሜ በላይ ነው!

በመንግስት ፕሮጀክቶች ላይ የሚቀርብ የካሳ ጥያቄዎች በሙሉ የመክፈል አቅም እንደሌለው የገንዘብ ሚኒስትር ገለፀ

ሚኒስትሩ እንዳለዉ የፌደራል ፕሮጀክቶች በሚተገበሩበት ወቅት የሚመጣው የካሳ ጥያቄ እጅግ የተጋነነ እና የመንግስትን እቅም እየተፈታተነ መሆኑን ጠቁሟል።

የገንዘብ ሚንስቴር ዴኤታ እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) ለቋሚ ኮሚቴዉ የሚኒስትሩን የዘጠኝ ወራት የእቅድ አፈፃፀም በገለፁበት ወቅት እንደተናገሩት መንግስት በሚያከናውናቸው የልማት ስራዎች የካሳ ጥያቄ ዋነኛ ችግር እየሆኑ መጥተዋል ብለዋል።

የሚጠየቀው የካሳ ጥያቄ ከመንግስት አቅም ጋር የሚጣጣም አይደለም ያለዉ ሚኒስትሩ በመሆኑም መንግስት የተጠየቀውን የካሳ ጥያቄን በሙሉ የመክፍል አቅም የለውም በማለት አስረድተዋል ።

(Capital)

በኢትዮጵያ የአሜሪካን ኤምባሲ የሰሞኑን የኬንያ ፕረዝደንት የሓይትሀወስ ጉብኝት መነሻ በማድረግ እኤአ በ1960 ዎቹ የንጉሰ ነገስት አፄ ኃ/ስላሴን ተመሳሳይ ጉብኝት አስታውሷል።
24/05/2024

በኢትዮጵያ የአሜሪካን ኤምባሲ የሰሞኑን የኬንያ ፕረዝደንት የሓይትሀወስ ጉብኝት መነሻ በማድረግ እኤአ በ1960 ዎቹ የንጉሰ ነገስት አፄ ኃ/ስላሴን ተመሳሳይ ጉብኝት አስታውሷል።

የስፔኑ ሀያል ክለብ ባርሴሎና አሰልጣኝ ዣቪ ሀርናንዴዝን ከሀላፊነታቸው ማሰናበቱን ይፋ አድርጓል፡፡
24/05/2024

የስፔኑ ሀያል ክለብ ባርሴሎና አሰልጣኝ ዣቪ ሀርናንዴዝን ከሀላፊነታቸው ማሰናበቱን ይፋ አድርጓል፡፡

24/05/2024
ፈርሶ ለሽያጭ ከተዘጋጀ በኋላ ለጨረታ ከቀረበው፣ የፒያሳ መሬት፣ አንድ ካሬ ሜትር መሬት፣ 350 000 ብር ተሽጧል።አዋሽ ባንክ ከዋናዎቹ  አሸናፊ ተጫራቾች አንዱ በመሆን 977 ካሬ ሜትር በ...
23/05/2024

ፈርሶ ለሽያጭ ከተዘጋጀ በኋላ ለጨረታ ከቀረበው፣ የፒያሳ መሬት፣ አንድ ካሬ ሜትር መሬት፣ 350 000 ብር ተሽጧል።

አዋሽ ባንክ ከዋናዎቹ አሸናፊ ተጫራቾች አንዱ በመሆን 977 ካሬ ሜትር በእጁ አስገብቷል።

ለዚሁም ባንኩ ሙሉውን 303 847 000 ብር ወዲያውን ለመክፈል ዝግጁ መሆኑ ታውቋል።

JANO Ethiopia ጃኖ
Fortune

ተማሪዋን በአሰቃቂ ሁኔታ የገደለው የ18 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአሶሳ ዩኒቨርስቲ ተማሪን በአሰቃቂ ሁኔታ በጩቤ ወግቶ የገደለውን...
23/05/2024

ተማሪዋን በአሰቃቂ ሁኔታ የገደለው የ18 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጣ

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአሶሳ ዩኒቨርስቲ ተማሪን በአሰቃቂ ሁኔታ በጩቤ ወግቶ የገደለውን ተከሳሽ በ18 ዓመት ጽኑ እስራት ቀጣ::

የፍርድ ቤቱ ፕሬዝዳንት አቶ አምነላ ሰበባ እንደገለጹት የሗንስ መርጋ ኢትቻ የተባለው ነዋሪነቱ ቢሾፍቱ ከተማ የሆነው ተከሳሽ በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የአራተኛ ዓመት ተማሪ የሆነችውን ወጣት ደራርቱ ለሜሳ ላይ የግድያ ወንጀል ፈጽሟል::

ተከሳሹ የግድያ ወንጀሉን የፈጸመው በከተማው አሶሳ ዩኒቨርሲቲ አካባቢ በተለምዶው ሞቢል በሚባል ሰፈር ግንቦት 07 / 2016 ዓ.ም. ሶስት ጊዜ ጀርባዋ ላይ በጩ ቤ ደጋግሞ በመው ጋት በአሰቃቂ ሁኔታ ግድያ በመፈጸም ህይወቷ እንዲያለፍ በማድረግ እንደሆነ አብራርተዋል::

አቃቢ ህግ በከሳሹ ላይ ባቀረበው ከባድ የሰው መግደል ወንጀል ክስ ወንጀሉን መፈጸሙን የሚያሳይ የሰው እና የህክምና ማስረጃ ማቅረቡን ገልጸዋል::

ግለሰቡ የግድያ ወንጀሉን ለመፈጸም የተነሳሠው " ለአንድ ዓመት አብረን በእጮኛነት በፍቅር ከቆየን በኃላ እኔን ትታ ከሌላ ሰው ጋር የፍቅር ግንኙነት ጀመረች" በሚል ተነሳስቶ መሆኑን የአቃቢ ህግ ማስረጃ እንደሚያስረዳ አመልክተዋል::

ተከሳሹ የቀረበበትን የወንጀል ክስ መፈጸሙን ማመኑን አቶ አምነላ አብራርተዋል::

የአሶሳ ከተማ ፍርድ ቤት ዛሬ በዋለው ግልጽ የወንጀል ችሎት የግራ ቀኙን ካዳመጠ በኃላ በግለሰቡ ላይ የ18 ዓመት ጽኑ እስራት ቅጣት እንደጣለበት ፕሬዝዳንቱ አስታውቀዋል::

ዳኞች የወንጀል ክስ መዝገብ ቅጣቱን ውሳኔ ያሳለፉት ያለልዩነት መሆኑንም ጨምረው ገልጸዋል::

@የአሶሳ ከተማ ወረዳ አንድ ፖሊስ ጽ/ቤት

ፎርብስ ያወጣው የአውሮፓ ክለቦች የሐብት ግምት ሪያል ማድሪድ በቀዳሚነት ለሶስት ተከታታይ አመታት እየመራ ይገኛል ።አርሰናል 10ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።ሌሎችን ለማየት👇👇👇
23/05/2024

ፎርብስ ያወጣው የአውሮፓ ክለቦች የሐብት ግምት ሪያል ማድሪድ በቀዳሚነት ለሶስት ተከታታይ አመታት እየመራ ይገኛል ።
አርሰናል 10ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
ሌሎችን ለማየት👇👇👇

«ወይ አዲስ አበባ» ሰርቶ ለማጠናቀቅ 500ሺ ብር ፈጅቶብኛል። አኩቻ «ወይ አዲስ አበባ» የተሰኘ ሁለተኛ ሙዚቃ ሰርቶ ማጠናቀቁን ለፋስት መረጃ ገልጿል። ሌሎች በጣም ቆንጆ ስራዎችን ደሞ ስቱ...
23/05/2024

«ወይ አዲስ አበባ» ሰርቶ ለማጠናቀቅ 500ሺ ብር ፈጅቶብኛል።
አኩቻ «ወይ አዲስ አበባ» የተሰኘ ሁለተኛ ሙዚቃ ሰርቶ ማጠናቀቁን ለፋስት መረጃ ገልጿል። ሌሎች በጣም ቆንጆ ስራዎችን ደሞ ስቱዲዮ ላይ ጨርሼ ነው ያለሁት በተከታታይ በአኩቻ ቲዩብ ይለቀቃሉ ያለ ሲሆን «ወይ አዲስ አበባ» ሙዚቃን እስከ ቪዲዮ ሰርቶ ለማጠናቀቅ ግማሽ ሚሊዮን የኢትዮጵያ ብር እንደጨረሰ ለፋስት መረጃ ተናግሯል ።
«ወይ አዲስ አበባ» ነገ አርብ በአኩቻ ቲዪብ ይለቀቃል።

ጀርመን የእስራኤሉን  ጠቅላይ ሚኒስትር አስራለሁ አለች፡፡የጀርመኑ መራሄ መንግስት ኦላፍ ሾልዝ  የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ወደ ሀገራችን ድርሽ ካሉ  እናስራቸዋለን ብለዋል፡፡የአለም አቀፉ ...
23/05/2024

ጀርመን የእስራኤሉን ጠቅላይ ሚኒስትር አስራለሁ አለች፡፡

የጀርመኑ መራሄ መንግስት ኦላፍ ሾልዝ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ወደ ሀገራችን ድርሽ ካሉ እናስራቸዋለን ብለዋል፡፡
የአለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት አባል የሆነችዉ ጀርመን የፍርድ ቤቱን ህግ እንደመረታከብርም አስታዉቀዋል፡፡

እናም ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ወደ ጀርመን ከተጓዙ ለእስር እንደሚዳረጉ በርሊን ገልጻለች፡፡
ኦላፍ ሾልዝ ይህንን ዉሳኔ ያሳለፉት በጀርመን የእስራኤል አምባሳደር በርሊን ከድርጊቷ እንድትቆጠብ ማሳሰባቸዉን ተከትሎ ነዉ ሲል አፈርቲ ኒዉስ ዘግቧል፡፡

የአለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት በጋዛዉ ጦርነት ምክንያት በእስራኤሉ ጠቅላ ሚኒስትር ላይ የእስር ማዘዣ እንዲወጣ መጠየቁ ይታወሳል፡፡
አሜሪካ በበኩሏ ዉሳኔዉን አሳፋሪ ነዉ ብለዋለች፡፡

መ/ር መንግሥቱ መግሶ እባላለሁ ።  #የአራት ልጆች አባት ነኝ። 👉በአሁኑ ሰዓት ሁለቱም ኩላሊቶቼ መሥራት በማቆማቸዉ በአፋጣኝ ወደ ዉጪ ሀገር በመሄድ የኩላሊት ንቅለ ተከላ እንዳደርግ የሐኪሞ...
23/05/2024

መ/ር መንግሥቱ መግሶ እባላለሁ ። #የአራት ልጆች አባት ነኝ። 👉በአሁኑ ሰዓት ሁለቱም ኩላሊቶቼ መሥራት በማቆማቸዉ በአፋጣኝ ወደ ዉጪ ሀገር በመሄድ የኩላሊት ንቅለ ተከላ እንዳደርግ የሐኪሞች ቦርድ ወስኗል።

👉 ለህክምናው ከ 3.5ሚሊዮን ብር በላይ የተጠየኩ ስለሆነ የአቅማችሁን በመርዳት የኔንም ህይወት በመታደግ ቤተሰቦቼን ከመበተንና ጎዳና ከመዉጣት እንድትታደጉልኝ በፈጣሪ ስም እማፀናለሁ🙏🙏🙏

ሼር ማድረግም ትልቅ ዋጋ አለዉና
ሌሎች መርዳት የሚትፈልጉ ደጋጎች

CBE : 1000150452407
Mengistu Megiso

በአፈር መደርመስ የአንድ ሰው ህይወት አለፈ ።ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክ/ከተማ በግንባታ ላይ ከነበረ ህንጻ አጠገብ ያለ ቤት ውሃልክ እና አፈር ተደርምሶ የአንድ ወጣት ህይዎት አልፏል።...
23/05/2024

በአፈር መደርመስ የአንድ ሰው ህይወት አለፈ ።

ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክ/ከተማ በግንባታ ላይ ከነበረ ህንጻ አጠገብ ያለ ቤት ውሃልክ እና አፈር ተደርምሶ የአንድ ወጣት ህይዎት አልፏል።

አደጋው የደረሰው ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 በተለምዶ " የረር ጉሊት " ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ነው።

በግንባታ ስራ ላይ የነበሩ ሰራተኞች ከአጠገቡ ዳገት ላይ የነበረ የግለሰብ መኖሪያ ቤት ውሃ ልክ እና አፈር ተደርምሶ የ28 ዓመት ወጣት ህይወት አልፏል።

አደጋው መፈጠሩ ከተሰማ ጀምሮ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ሰራተኞች በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው ሁለት ሰራተኞችን ህይዎት ለመታደግ ከፍተኛ ርብርብ ማድረጋቸው ተነግሯል።

Address

Arada
Addis Ababa
8912

Telephone

+251911270330

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when JANO Ethiopia ጃኖ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Share

Category

ይህ ትክክለኛው የጄ ቲቪ ኢትዮጵያ የፌስቡክ ገጽ ነው Comment, LIKE & SHARE ስላደረጉን እናመሰግናለን

ይህ ትክክለኛው የጄ ቲቪ ኢትዮጵያ የፌስቡክ ገጽ ነው

LIKE & SHARE ስላደረጉን እናመሰግናለን



You may also like