Wollo Tv - ወሎ ቲቪ

Wollo Tv - ወሎ ቲቪ WOLLO TV -The best destination for Ethiopian BREAKING News, Information, Entertainment,Fun Facts, Celebrity Stories, Historical Happenings, and much more!
(1)

እንኳን አደረሳችሁ‼
28/09/2023

እንኳን አደረሳችሁ‼

ለመላው ኢትዮጵያዊያን እንኳን ለ2016ዓም አደረሳችሁ።መልካም በዓልWollo TvWollo Tv - ወሎ ቲቪወሎ ቲቪ
12/09/2023

ለመላው ኢትዮጵያዊያን እንኳን ለ2016ዓም አደረሳችሁ።
መልካም በዓል
Wollo TvWollo Tv - ወሎ ቲቪወሎ ቲቪ

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ እህት/ወንድሞቻችን እንኳን ለ1444ኛው የኢድ አል‐አድሀ በዓል አደረሳችሁ! መልካም በአል!
28/06/2023

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ እህት/ወንድሞቻችን እንኳን ለ1444ኛው የኢድ አል‐አድሀ በዓል አደረሳችሁ!

መልካም በአል!

ለክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን አደረሳችሁ።Wollo TvWollo Tv - ወሎ ቲቪወሎ ቲቪ
16/04/2023

ለክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን አደረሳችሁ።

Wollo TvWollo Tv - ወሎ ቲቪወሎ ቲቪ

22/03/2023

ዛሬ ከተሰሙ መረጃዎች አንዱ👇
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ ህወሃትን ከሽብርተኝነት ሰርዟል።

127ኛው የዓድዋ ድል በዓል እየተከበረ ነው‼️127ኛው የዓድዋ ድል በዓል  በተለያዩ መርሐ ግብሮች እየተከበረ ይገኛል፡፡የዓድዋ ድል በዓል የዓድዋ ከተማን ጨምሮ በአዲስ አበባ እና በተለያዩ ...
02/03/2023

127ኛው የዓድዋ ድል በዓል እየተከበረ ነው‼️

127ኛው የዓድዋ ድል በዓል በተለያዩ መርሐ ግብሮች እየተከበረ ይገኛል፡፡

የዓድዋ ድል በዓል የዓድዋ ከተማን ጨምሮ በአዲስ አበባ እና በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ለሀገር የተዋደቁ ጀግኖችን እና ድሉን በሚዘክሩ መርሐ ግብሮች በድምቀት እየተከበረ ይገኛል፡፡

በምኒሊክ አደባባይ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴን ጨምሮ የተለያዩ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ለበዓሉ መታሰቢያ በምኒልክ ሃውልት ስር የአበባ ጉንጉን አስቀምጠዋል፡፡

Wollo TvWollo Tv - ወሎ ቲቪወሎ ቲቪ

ውጤቱን ዛሬ ምሽት 5:30 ይለቀቃየ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤትን ተማሪዎች ከዛሬ ለሊት ጀምሮ ማየት እንደሚችሉ ተገልጿል።ተፈታኞች ከዛሬ ጥር 18 ቀን 2015 ዓ.ም  #ከሌሊቱ 5፡30 ጀ...
26/01/2023

ውጤቱን ዛሬ ምሽት 5:30 ይለቀቃ

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤትን ተማሪዎች ከዛሬ ለሊት ጀምሮ ማየት እንደሚችሉ ተገልጿል።

ተፈታኞች ከዛሬ ጥር 18 ቀን 2015 ዓ.ም #ከሌሊቱ 5፡30 ጀምሮ ፡-

• በዌብ ሳይት https://eaes.edu.et/ ወይም
• በ6284 አጭር የጽሑፍ መልዕክት መላኪያ ላይ የምዝግባ ቁጥራቸውን (Registration Number) ብቻ በመላክ ወይም
• በቴሌግራም ላይ https://t.me/eaesbot
ማየት የሚችሉ መሆኑን ተገልጿል።

ማሳሰቢያ፡-

• ማንኛውም ቅሬታ ያላቸው ተፈታኞች በአካል መምጣት ሳያስፈልግ እስከ ጥር 26/2015 ዓ.ም ድረስ በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዌብ ሳይት https://eaes.edu.et/ ላይ Compliant የሚለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን ማቅረብ ይችላሉ ተብሏል።

• ተማሪዎች ፤ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አድራሻ ላይ ብቻ እንዲጠቀሙ #ከተመሳሳይ እና ለማሰራጫት ከሚሞክሩ አካላት እራሳቸውን እንዲጠብቁ መልዕክት ተላልፏል።

ምንጭ ፦ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

Educational Assessment and Examinations Services (EAES) among others has a powers and duties of preparing country wide national examinations based on the country's education curriculum and training policy, Administer and ensure the confidentiality and safety of national exams, Establish and administ...

ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ አሳለፈ።ቅዱስ ሲኖዶስ ፤ ጥር 14 ቀን 2015 ዓ.ም በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት በሶዶ ዳጩ ወረዳ ሐሮ ባለወልድ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ፦1ኛ. አባ ሳዊሮስ2ኛ. አ...
26/01/2023

ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ አሳለፈ።

ቅዱስ ሲኖዶስ ፤ ጥር 14 ቀን 2015 ዓ.ም በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት በሶዶ ዳጩ ወረዳ ሐሮ ባለወልድ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ፦
1ኛ. አባ ሳዊሮስ
2ኛ. አባ ኤዎስጣቴዎስ
3ኛ. አባ ዜና ማርቆስ የቤተ ክርስቲያንን ቀኖና በመጣስ ባልተሰጣቸው ስልጣን 26 ኤጴስ ቆጰሳትን ሾመናል፤ ሲኖዶስ አቋቁመናል በማለት በማኅህበራዊ እና በብሮድካስት ሚዲያዎች በሰጡት መግለጫ የተረጋገጠ መሆኑን ገልጿል።

በዚሁ ድርጊታቸውም በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭው ዓለም የሚኖረውን ሕዝበ ክርስቲያንን በማታለል የክህደት እና የኑፋቄ ተግባር ፈፅመዋል ብሏል።

ቅዱስ ሲኖዶስ ይህንን ተግባር እንደሚያወግዝ ገልጾ ከቤተ ክርስቲያን የተሰጣቸውን ከዲቁና ጀምሮ ያለው ሙሉ ሥልጣነ ክህነት በመሻር አውግዞ እንደለያቸው አሳውቋል።

ፈጣን ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት ይህንን የቴሌግራም ቻናል Join በማለት ይከታተሉ👇
http://t.me/wasulife http://t.me/wasulife

Subscribe👇
https://youtu.be/TibDfXKiqo0

ጥቆማ ለመስጠትና በቻናሉ ማስታወቂያ ለማሰራት
https://t.me/WasuMohammed

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለከፍተኛ የመንግስት ሃላፊነት ቦታዎች ሹመቶች ሠጡጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 74(2) መሰረት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፤ የሚከተ...
20/01/2023

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለከፍተኛ የመንግስት ሃላፊነት ቦታዎች ሹመቶች ሠጡ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 74(2) መሰረት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፤ የሚከተሉትን ሹመቶች እንዲያጸድቅ ጠይቀዋል፦

1. ዶ/ር አለሙ ስሜ - የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር
2. ኢንጂነር ሀብታሙ ተገኝ - የማዕድን ሚኒስትር
3. ዶ/ር ግርማ አመንቴ - የግብርና ሚኒስትር

በተጨማሪም ከጥር 10፣ 2015 ጀምሮ የሚከተሉትን ሹመቶች ሰተዋል፦
1. አቶ ማሞ ምሕረቱ - የብሔራዊ ባንክ ገዢ
2. ወ/ሮ አለምፀሐይ ጳውሎስ - የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ኃላፊና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር
3. ዲያቆን ዳንኤል ክብረት - የማኅበራዊ ዘርፍ አማካሪ ሚኒስትር
4. አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ - የውጭ ፖሊሲ አማካሪ ሚኒስትር
5. አቶ መለሰ አለሙ - በሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ የዘርፍ አስተባባሪ ሆነው መሾማቸውን የጠ/ሚ ጽ/ቤት አስታውቋል።

ይህ በፎቶ የሚታየው አማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን መርሳ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ነው። ይሄ ሆስፒታል በጦርነቱ ጉዳት ከደረሰባቸው የጤና ተቋማት አንዱ ሲሆን አካባቢው ከጦርነቱ ነፃ ከሆነ አመ...
19/01/2023

ይህ በፎቶ የሚታየው አማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን መርሳ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ነው። ይሄ ሆስፒታል በጦርነቱ ጉዳት ከደረሰባቸው የጤና ተቋማት አንዱ ሲሆን አካባቢው ከጦርነቱ ነፃ ከሆነ አመት ቢሆነውም የመርሳ ሆስፒታል የውሃ ችግር ሊፈታ እንዳልቻለ ሀኪሞችና ተጠቃሚዎች ይናገራሉ።በፎቶ የሚታዩት አህዮች ለሆስፒታሉ ውሃ የሚያመላልሱ ናቸው ብለውናል።ሆስፒታሉ የመርሳ ከተማንና የሀብሩ ወረዳን ህዝብ ያስተናግዳል ነገር ግን ውሃ የለም።በዚህ ችግር ክፉኛ ተጎሳቁሏል።የእናቶች ማዋለጃ ክፍል ለመግለፅ በሚከብድ የንፅህና ጉድለት ውስጥ ስለሚገኝ ለመውለድ የሚመጡ እናቶች ለመስተናገድ መቸገራቸውንም ሰምተናል።የሚመለከተው አካል ለዚህ ችግር አፋጣኝ መፍትሄ እንድሰጥ በማክበር እንጠይቃለን።
Wollo TvWollo Tv - ወሎ ቲቪወሎ ቲቪ
t.me/wollotv2022

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለከተራ እና ጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ! መልካም በዓል እንዲሆንላችሁ እንመኛለን‼    Wollo Tv - ወሎ ቲቪ
18/01/2023

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለከተራ እና ጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ! መልካም በዓል እንዲሆንላችሁ እንመኛለን‼
Wollo Tv - ወሎ ቲቪ

18/01/2023

ኢ/ር ታከለ ኡማ

የፈጣሪ ስራ ይገርማል።ህፃኑ ከተወለደ ሶስት ወራት ሆኖታል።ህፃኑ የተወለደው አላማጣ ነው።ከወገቡ በታች ሶስት እግር ሁለት ብልት አለው።አሁን ላይ ከአላማጣ ለተጨማሪ ህክምና ወልድያ ሆስፒታል ...
11/01/2023

የፈጣሪ ስራ ይገርማል።

ህፃኑ ከተወለደ ሶስት ወራት ሆኖታል።ህፃኑ የተወለደው አላማጣ ነው።ከወገቡ በታች ሶስት እግር ሁለት ብልት አለው።አሁን ላይ ከአላማጣ ለተጨማሪ ህክምና ወልድያ ሆስፒታል ይገኛል።
👇ምስሉን ማየት ለምትፈልጉ
t.me/Wollotv2022

በነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ጭማሬ ተደርጓል።በአዲስ አበባ ከነገ ጥር 1/2015 ጀምሮ ✔ቤንዚን በሊትር - 61 ብር ከ29 ሣንቲም✔ነጭ ናፍጣ በሊትር - 67 ብር ከ30 ሣንቲም ✔ኬሮሲን...
08/01/2023

በነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ጭማሬ ተደርጓል።በአዲስ አበባ ከነገ ጥር 1/2015 ጀምሮ

✔ቤንዚን በሊትር - 61 ብር ከ29 ሣንቲም

✔ነጭ ናፍጣ በሊትር - 67 ብር ከ30 ሣንቲም

✔ኬሮሲን በሊትር - 67 ብር ከ30 ሣንቲም

✔ቀላል ጥቁር ናፍጣ - 49 ብር ከ67 ሣንቲም

✔ከባድ ጥቁር ናፍጣ - 48 ብር ከ70 ሣንቲም

✔የአውሮፕላን ነዳጅ - 67 ብር ከ91 ሣንቲም መሆኑን የንግድ እና ቀጣናዊ ትሥሥር ሚኒስቴር ገልጿል።

እንኳን ደህና መጡ‼ ✔ማስታወቂያ ለማሰራት እና ጥቆማ ለመስጠት በዚህ ይጠቀሙ ☞https://t.me/WasuMohammed ✔ ቻናሉን ለመቀላቀል Join ☞http://t.me/Wasulife ከልብ አመሰግናለሁ♥🙏

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን አደረሳችሁ።በዓሉ የሰላምና የጤና ይሁንላችሁ።        Wollo TvWollo Tv - ወሎ ቲቪወሎ ቲቪ
07/01/2023

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን አደረሳችሁ።በዓሉ የሰላምና የጤና ይሁንላችሁ።
Wollo TvWollo Tv - ወሎ ቲቪወሎ ቲቪ

ሬፑቴሽን ፖል ኢንተርናሽናል (RPI) የተሰኘው ዓለም አቀፍ ድርጅት ባወጣው የስመ ጥር አፍሪካውያን ዝርዝር ውስጥ አራት ኢትዮጵያዊያን ባለስልጣናት እንደሚገኙበት ተገለፀ።ዓለም አቀፉ ድርጅት ...
04/01/2023

ሬፑቴሽን ፖል ኢንተርናሽናል (RPI) የተሰኘው ዓለም አቀፍ ድርጅት ባወጣው የስመ ጥር አፍሪካውያን ዝርዝር ውስጥ አራት ኢትዮጵያዊያን ባለስልጣናት እንደሚገኙበት ተገለፀ።

ዓለም አቀፉ ድርጅት ባወጣው ዝርዝር ውስጥ የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ የዕቅድና ልማት ሚኒስትር ወ/ሮ ፍፁም አሰፋ፣ የኢፌዲሪ ጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ እንዲሁም የምስራቅ አፍሪካ የልማት በየነ መንግሥታት (ኢጋድ) ዋና ፀሀፊ ወርቅነህ ገበየሁ ይገኙበታል።

የስመ ጥር ዝርዝሩ ከአስተዳደር፣ ከአመራር፣ ከመዝናኛ፣ ከሰብአዊ መብት ተሟጋች፣ ትምህርት እና ንግድን ጨምሮ ከተለያዩ ዘርፎች የተውጣጡ ግለሰቦችን አካቷል።

"ቁልፍ በሆኑ የሁለትዮሽ እና የባለብዙ ወገን ጉዳዮች ላይ ከቱርክ ፕሬዝዳንት ሬሴፕ ታይፕ ኤርዶጋን ጋር በስልክ ተነጋግረናል። በኢትዮጵያ እና በቱርክ መካከል ያለውን የንግድ ግንኙነት ለማሳደ...
03/01/2023

"ቁልፍ በሆኑ የሁለትዮሽ እና የባለብዙ ወገን ጉዳዮች ላይ ከቱርክ ፕሬዝዳንት ሬሴፕ ታይፕ ኤርዶጋን ጋር በስልክ ተነጋግረናል። በኢትዮጵያ እና በቱርክ መካከል ያለውን የንግድ ግንኙነት ለማሳደግ እና ሽብርተኝነትን በጋራ ለመዋጋት ተስማምተናል።"

- ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ

የኮምቦልቻ ኤርፖርት የማስፋፊያ ግንባታ ተጀምሯል።የኮምቦልቻ ከተማ ከንቲባ አቶ መሀመድ አሚን በይፋዊ ገፃቸው እንዳስታወቁት የኤርፖርቱ ማስፋፊያ እየተከናወነ ይገኛል።
28/12/2022

የኮምቦልቻ ኤርፖርት የማስፋፊያ ግንባታ ተጀምሯል።የኮምቦልቻ ከተማ ከንቲባ አቶ መሀመድ አሚን በይፋዊ ገፃቸው እንዳስታወቁት የኤርፖርቱ ማስፋፊያ እየተከናወነ ይገኛል።

ወሎ የትምህርት፣ የሳይንስ፣ የባህል ኮንፈረንስ እና ፌስቲቫል ''ከዛሬ ታህሳስ 19 እስከ 23 በአዲስ አበባ እንዲሁም ከታህሳስ 29 እስከ ጥር 7 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ በደሴ ከተማ ይካሄ...
28/12/2022

ወሎ የትምህርት፣ የሳይንስ፣ የባህል ኮንፈረንስ እና ፌስቲቫል ''ከዛሬ ታህሳስ 19 እስከ 23 በአዲስ አበባ እንዲሁም ከታህሳስ 29 እስከ ጥር 7 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ በደሴ ከተማ ይካሄዳል።

ከደቂቃዎች በኋላ በቀጥታ ስልከ መስመር እገባችሁ አስተያየት የምትሰጡበት የቀጥታ ስርጭት ይጀምራል፡፡
23/12/2022

ከደቂቃዎች በኋላ በቀጥታ ስልከ መስመር እገባችሁ አስተያየት የምትሰጡበት የቀጥታ ስርጭት ይጀምራል፡፡

https://www.youtube.com/channel/UCrdWHrcXNEhMfbp1ucgxd1g አዳዲስ መረጃዎች ቶሎ ቶሎ እንዲደርስዎ ይህንን ቻናል ሰብስክራይብ ያድርጉ፡፡በቅንነት ቤተሰብ ይሁኑ!! WOLLO TV -The best destination for ...

አሚኮ ደሴ ከተማ ባለ12 ወለል የሚዲያ ኮምፕሌክስ ግንባታን በይፋ አስጀመረ።አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን በደሴ ከተማ የሚያስገነባውን ባለ 12 ወለል ዘመናዊ ህንጻ ግንባታ በዛሬው ዕለት አስጀምሯል...
23/12/2022

አሚኮ ደሴ ከተማ ባለ12 ወለል የሚዲያ ኮምፕሌክስ ግንባታን በይፋ አስጀመረ።

አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን በደሴ ከተማ የሚያስገነባውን ባለ 12 ወለል ዘመናዊ ህንጻ ግንባታ በዛሬው ዕለት አስጀምሯል።

የሚዲያ ኮምፕሌክሱ በአማራ ህንጻ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ተቋራጭነት በ544 ሚሊየን ብር ወጭ የሚገነባ ሲሆን በቀጣይ 3 ዓመታት ግንባታው ይጠናቀቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሙሉቀን ሰጥየ ተናግረዋል።

የግንባታ ሥራውን የሚያከናውነው የአማራ ህንጻ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ታደሰ ግርማ በበኩላቸው ግንባታው ከተቀመጠለት ጊዜ ቀድመን ለማጠናቀቅ ጥረት እናደርጋለን ብለዋል።

በም/ ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የህዝብ ግንኙነትና አደረጃጀት አማካሪ እንዲሁም የአሚኮ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ግርማ የሽጥላ አሚኮ ተወዳዳሪ የሚዲያ ተቋም ሆኖ እንዲወጣና የህዝቡ የትግል መሳሪያ ሆኖ እንዲያገለግል የክልሉ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታውቀዋል።

ለህዝቡ ኑሮ መሻሻልና ዕድገት አሚኮ እያከናወነው ላለው ውጤታማ ተግባር የሚዲያ ኮምፕሌክሱ ግንባታ አጋዥ እንደሚሆንም ገልጸዋል።

በግንባታ ማስጀመሪያ ፕሮግራሙ ላይ በም/ ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የህዝብ ግንኙነትና አደረጃጀት አማካሪና የአሚኮ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ግርማ የሽጥላ፣ በሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ አቶ ዛዲግ አብረሃ፣ የመከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ ዶ/ር አህመዲን መሀመድና ሌሎች የደቡብ ወሎ ዞን፣ የደሴና ኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደሮች የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

መረጃው ከደቡብ ወሎ ዞን ኮሙኒኬሽን ገፅ የተገኘ ነው።

Join http://t.me/wollotv2022

እናመሰግናለን🙏 የወሎ ቲቪ የዩቲዩብ ቻናልን ወደነበረበት ለመመለስ ጥረት ላደረጋችሁ የድርጅታችን አጋር ባለሙያዎችና ቤተሰቦች ከልብ እናመሰግናለን።የዩቲዩብ ቻናሉ ተመልሷል።በቅርብ ቀን በአዲስ...
15/12/2022

እናመሰግናለን🙏

የወሎ ቲቪ የዩቲዩብ ቻናልን ወደነበረበት ለመመለስ ጥረት ላደረጋችሁ የድርጅታችን አጋር ባለሙያዎችና ቤተሰቦች ከልብ እናመሰግናለን።የዩቲዩብ ቻናሉ ተመልሷል።በቅርብ ቀን በአዲስ አቀራረብ ይጀምራል።
አሁኑኑ ግቡና Subscribe አድርጉት።
https://www.youtube.com/channel/UCrdWHrcXNEhMfbp1ucgxd1g

WWollo Tv - ወሎ ቲቪTWollo Tv - ወሎ ቲቪWollo Tv - ወሎ ቲቪWollo Tv - ወሎ ቲቪቲWollo Tv - ወሎ ቲቪ

ጥንቃቄ አድርጉ‼  ሼር አድርጉት  በገፃችሁ ለጥፉት“የአንድ ብሩን ሳንቲም በሺዎች በሚቆጠር ገንዘብ እንገዛለን” ከሚሉ አጭበርባሪዎች ኅብረተሰቡ ራሱን ሊጠብቅ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባ...
12/12/2022

ጥንቃቄ አድርጉ‼ ሼር አድርጉት በገፃችሁ ለጥፉት

“የአንድ ብሩን ሳንቲም በሺዎች በሚቆጠር ገንዘብ እንገዛለን” ከሚሉ አጭበርባሪዎች ኅብረተሰቡ ራሱን ሊጠብቅ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አሳሰበ።

ከሰሞኑ በተለያዩ ማኅበራዊ ድረገፆች አራት የግዕዝ ፊደላት ያሉትን የአንድ ብር ሳንቲም በ2 ሺህ ብር እና ከዚያም በላይ እንገዛለን የሚሉ ከእውነት የራቁ ሀሰተኛ ማስታወቂያዎች በስፋት ተስተውለዋል። ማስታወቂያዎቹ ኅብረተሰቡን ለማጭበርበር እየተነገሩ ያሉ እና ከእውነት የራቁ መሆናቸውን ባንኩ አሳስቧል።

ሀረጎሀረጎ በኮምቦልቻና ደሴ መካከል ከዬጎፍ ጥብቅ ደን ሰሜን ምዕራብ አቅጣጫ የሚገኝ ጠመዝማዛ መንገድ ነው ። ማራኪውን የሀረጎ የተራራ ሰንሰለት ተከትሎ የተሰራውን የመኪና መንገድ ብዙዎች ው...
11/12/2022

ሀረጎ

ሀረጎ በኮምቦልቻና ደሴ መካከል ከዬጎፍ ጥብቅ ደን ሰሜን ምዕራብ አቅጣጫ የሚገኝ ጠመዝማዛ መንገድ ነው ።

ማራኪውን የሀረጎ የተራራ ሰንሰለት ተከትሎ የተሰራውን የመኪና መንገድ ብዙዎች ውበትን እና ፍቅርን ለመግለጽ ይጠቀሙበታል፡፡

“እንደ ሀረጎ መንገድ፣ ሽንጠ ጠመዝማዛ
በወሎ ልጅ ፍቅር፣ አበሳየ በዛ ፡፡”

ብሎ ፍቅር የያዘው ጉብል ለወሎ ቆንጆ ቅኝቱን ሲቃኝ ኮረዳዎም
“አድምጠኝ ሸጋዋ” በማለት ፦

“ከኮምበልቻ በላይ፣ ስሙ ነው ሀረጎ
ደሴ መሄድ ነበር፣ አንተን ከጎን አርጎ፡፡” በሚል የስንኝ ቋጠሮ ትመልስለታለች ።

ሀረጎ ጠመዝማዛ መንገድ እና ዬጎፍ ጥብቅ ደን ከስንኝ ቋጠሮ ባለፈ ለሁለቱ ከተሞች ( ለኮምቦልቻ እና ደሴ ) በቱሪዝም ገበያው ሊያስተሳስራቸው አልቻለም !! እንጦጦ ፓርክን ሳስብ በዚህ ቦታ ላይ ቢሆን ብየ መንፈሳዊ ቅናት ያድርብኛል። ደረጃውን የጠበቀ የቱሪዝም መዳረሻ እንዲሆን የሁለቱም ከተሞች የቤት ሰራ ሆኖ ይቀጥላል ።
Visit wollo

Jon 👉 t.me/wollotv2022

👇የዩቲዩብ ቻናላችንን Subscribe ያድርጉ

https://www.youtube.com/channel/UCrdWHrcXNEhMfbp1ucgxd1g

05/12/2022

አርባ ምንጭ‼

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የመምህራን ማህበር ምክትል ሰብሳቢ መለሰ ተሾመ እና የማህበሩ የስራ አስፈፃሚ አባል የሆነው ጌታሰው ቃኜ ቅዳሜ እለት መታሰራቸው ታውቋል።የእስራቱ ምክንያትም ዛሬ የተጀመረው የስራ ማቆም አድማ እንደሆነ ተሰምቷል።በሂደቱ ውይይት ሲያደርጉ ከግቢ በፖሊስ ተመወሰዳቸውን ምንጮች አረጋግጠዋል።የዩኒቨርስቲ መምህራን የደመወዝ ጥያቄን ምላሽ ለማሰጠት ከዛሬ ህዳር 26/2015 ጀምሮ የስራ ማቆም አድማ እያደረጉ ነው።

 የሁለት ህፃናትን ህይወት በአሰቃቂ ሁኔታ ያጠፋችው ህይወት መኮንን በዛሬው ችሎት ዐቃቤ ህግ በሞት እንድትቀጣ ካለ በኃላ ፦- ከዚህ ቀደም ወንጀል ፈፅሜ የማላውቅ፣ - ወንጀሉን የፈጸምኩት ከ...
05/12/2022



የሁለት ህፃናትን ህይወት በአሰቃቂ ሁኔታ ያጠፋችው ህይወት መኮንን በዛሬው ችሎት ዐቃቤ ህግ በሞት እንድትቀጣ ካለ በኃላ ፦

- ከዚህ ቀደም ወንጀል ፈፅሜ የማላውቅ፣
- ወንጀሉን የፈጸምኩት ከእውቀት ማነስና ያልተማርኩ በመሆኔ መሆኑ፣
- እጄን ለፖሊስ አምኜ የሰጠው በመሆኔ ከግምት ገብቶ ቅጣቱ ይቅለልልኝ በማለት የቅጣት ማቅለያዎችን ከመንግስት በተመደበላት የተከላካይ ጠበቃ አማካኝነት የጠየቀች ቢሆንም የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ሰው ግድያና ከባድ ውንብድና ወንጀል ችሎት ተከሳሿ ያቀረበችውን ማቅለያዋን #አልተቀበለውም፡፡

ፍርድ ቤቱ ሌሎች አጥፊዎችን ያስጠነቅቃል በማለት ተከሳሿ #በሞት እንድትቀጣ ሲል ወስኖባታል፡፡

03/12/2022

የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን(አሚኮ)

03/12/2022

ምስራቅ ወለጋ

የኦሮሚያ ልዩ ሀይል አንገር ጉትን ከተማ የሚገኙና መንግስት ያስታጠቃቸው የሸኔን ጥቃት ሲከላከሉ የነበሩ ሚኒሻዎችን ትጥቅ አስፈታለሁ ብሎ በመነሳቱ ነው ግጭቱ የተነሳው ተብሏል። በዚህም የበርካቶች ህይወት ጠፍቷል።

25/11/2022

የባጃጅ ነገር‼

የጎንደር ከተማ በባጃጅ ተሽከርካሪዎች ላይ ያወጣው አዲስ ውሳኔ

✔አዲስ ባጃጅ ወደ ከተማው ለማስገባት=70,000 (ሰባ ሺህ ብር ለከተማ አስተዳደሩ የገቢዎች ተቋም ገቢ ማድረግ ይኖርበታል)

✔የከተማ ፍቃድ ባይኖራቸውም የነዳጅ ድጎማውን እንዲጠቀሙ የተፈቀደላቸው የከተማ ፍቃድ ለማግኘት 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር ለገቢዎች ተቋም ስለመክፈላቸው መረጋገጥ አለበት)

✔ከሰው እጅ ያለ ባጃጅ ወደከተማው በማስገባት የከተማ ፍቃድ ለማግኘት 100,000(መቶ ሺህ ብር ለገቢዎች ተቋም ስለመክፈላቸው መረጋገጥ አለበት)

✔ከጉሙሩክ በጨረታ አሸንፈው የከተማ ፍቃድ ለማግኘት ለሚመጡ ባጃጆ 100,000 ብር (ለገቢዎች ተቋም ስለመክፈላቸው መረጋገጥ አለበት)

✔ከኮድ ሁለት ወደ ኮድ አንድ ለመቀየር ለሚፈልጉ =30,000(ሰላሳ ሽህ ብር ለገቢዎች ተቋም ስለመክፈላቸው መረጋገጥ አለበት)

✔እስከ ህዳር 30 ባለው ቀነገደብ ውስጥ የሚጠበቅበትን አሟልቶ የከተማ ፍቃድ ሳይኖረው ከተማው ላይ አገልግሎት ሲሰጥ የተገኘ ባጃጅ=30,000 ብር ተቀጥቶ ከከተማው እንዲወጣ የሚደረግ ሲሆን ተግባሩም ከህዳር 19/2015 እስከ ህዳር 30/2015 ዓ/ም ብቻ የሚፈፀም ይሆናል።

የጎንደር ከተማ አስተዳደር ከባጃጅ ጋር ተያይዞ ያገጠሙ እያጋጠሙ ያሉና ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችን በጥናት እንዲለዩ አድርጓል።በጥናቱም ቀላል የማይባሉ የአሰራር ግድፈቶች ስለመኖራቸው አረጋግጧል።ከተማ አስተዳደሩ ከ2011 ዓ/ም ጀምሮ ባጃጅ ወደ ከተማው እንዳይገባ ክልከላ ቢያደርግም የተለያዩ አካላት ቅንጅት ፈጥረው በሰሩት ሀላፊነት የጎደለው ተግባር በሽ የሚቆጠሩ የወረዳ ባጃጆች ወደ ከተማው እንዲገቡ በማድረግ ህጋዊ የከተማ ባጃጆች ክፉኛ እንዲጎዱ ማድረጋቸውን ጥናቱ አመላክቷል።

እነዚህንና ሌሎችንም ግኝቶች መሰረት በማድረግ ከተማ አስተዳደሩ አዳዲስ ውሳኔዎችን ለመወሰን የተገደደ ሲሆን ወሳኔዎችን ተግባራዊ ለማድረግም የተለያዩ ኮሚቴዎችን አቋቁሟል።ውሳኔውን ለማደናቀፍና የመንግስትንና የህዝብን ጥቅም በማሳጣት የራሳቸውን ፍላጎት ለማሟላት የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦች የሚያጋጥሙ ከሆነም ህጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃ ለመውሰድ በሚያመች መንገድ ልዩ የምርመራ ቡድን እንዲቋቋም ተደርጓል።

ተግባሩን በውጤታማነት ለመምራት የሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችም እንዲጠናቀቁ ተደርጓል። ጎን በጎንም የመንግስትንና የህዝብን ጥቅም በማሳጣትና ተግባሩን ለማደናቀፍ የሚሞክሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ ለማጣራት የሚያስችል ስራ ተሰርቷል። የከተማ ፍቃድ ሳይኖራቸው አላቸው የሚል መረጃ በመስጠት ግለሰቦችን ላልተፈለገ ወጭ የዳረጉ አካላትን ለይቶና ከግለሰቦች የሚመጣን ጥቆማ መሰረት በማድረግ ምርመራም የሚካሄድ ይሆናል።

ውሳኔው ተግባራዊ ይሆን ዘንድ አስፈላጊውን እገዛ ከማድረግ ይልቅ ለማደናቀፍ የሚሞክሩና ያለከተማ አስተዳደሩ እውቅና በራሳቸው ስልጣን የወረዳ ባጃጅ አስገብተው በተገኙ አካላት ላይ ህጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃም ለመውሰድ የምንገደድ ይሆናል።ህጋዊ ሆነው ሳለ ኮምፒዩተር ያልገባላቸው ካሉ በጥንቃቄና በጥልቀት በማጣራትና እውነታውን ፈልገን በማግኘት መፍትሄ የምንሰጥ ሲሆን የተሳሳተ መረጃ በመያዝ ለማጭበርበር የሚሞክር ካለ ሰንዶችን ይዘን የምርመራ አካል የምናደርግ ይሆናል።

የጎንደር ከተማ አስተዳደር

Address

22
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Wollo Tv - ወሎ ቲቪ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Wollo Tv - ወሎ ቲቪ:

Videos

Share

Category