Prosperity Party - የብልጽግና ፓርቲ ልሳን

Prosperity Party - የብልጽግና ፓርቲ ልሳን to get fresh news, news story, articles, breaking news, opinions, intertain...like the page...

25/10/2023
10/09/2023

የሕዳሴው ግድብን አራተኛና የመጨረሻ ሙሌት በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን ሳበሥር በታላቅ ደስታ ነው። ኢትዮጵያውያን ተባብረን በመሥራታችን ፈጣሪ ረድቶናል። በገንዘባቸው፣ በዕውቀታቸው፣...

እንኳን ደስ አለን!!! 4ኛው የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሙሌት በሰላም ተጠናቋል...
10/09/2023

እንኳን ደስ አለን!!! 4ኛው የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሙሌት በሰላም ተጠናቋል...

07/09/2023

የአማራ ክልል አጋጥሞት ከነበረው የፀጥታ ስጋት በመውጣት ወደ መደበኛ ሁኔታ መመለስ መቻሉን የክልሉ መንግስት አስታወቀ
**************

ወቅታዊ የአማራ ክልል ሁኔታን አስመልክቶ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ በሰጡት መግለጫ፤ ክልሉ አጋጥሞት ከነበረው የፀጥታ ስጋት በመውጣት ወደ መደበኛ ሁኔታ መመለስ መቻሉን አስታውቀዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ ህገመንግስታዊ ስርዓትን መናድና ክልሉን የማፍረስ ተልዕኮ ከሽፏል ያሉ ሲሆን ፤ ሁሉንም ዞንና ወረዳዎችን ነፃ ማውጣት መቻሉንም ገልፀዋል።

ለዚህም የክልሉ ህዝብ፣የሀገርመከላከያ ሠራዊት እና የክልሉ የፖለቲካና የፀጥታ መዋቅር ለከፈሉት መሥዋዕትነት አመስግነዋል።

ከፀጥታ ማስከበር ተግባራት ባለፈ የሠላም ግንባታ ስራዎች ሲከናወኑ መቆየታቸውን የገለፁት አቶ አረጋ ከበደ፤ በዚህም የህዝብ ጥያቄዎችና ችግሮች ሊፈቱ የሚችሉት በሠላማዊ ሁኔታ ፣በህግ እና በድርድር መሆኑን ከማህበሰሠቡ ጋር መግባባት ላይ የተደረሰበት ስለመሆኑ አንስተዋል።

የተገኘውን ሠላም ዘላቂ ለማድረግ እየተሠራ መሆኑን የገለጹት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ በክልሉ ከታችኛው መዋቅር ጀምሮ አስከ ላይኛው የመንግስት አስተዳደርና ፀጥታ ዘርፍ የመልሶ ማደራጀት ስራ እየተከናወነ ነው ብለዋል።

በአጋጠመው የፀጥታ ችግር የመንግስት አገልግሎቶች ተቋርጠዋል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ መደበኛ የልማት ስራዎችን ከድህረ ግጭት ተግባራት ጋር ወደ ስራ ለማስገባት በትኩረት እየተሠራ ስለመሆኑም አስታውቀዋል።

ህብረተሠቡ የአካባቢው ሰላም ወደ ተሻለ ደረጃ እንዲሸጋገር ያሳየውን ትጋት አጠናክሮ እንዲቀጥልና ለመደበኛ የመንግስት አገልግሎቶች መመለስ የድርሻውን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።

ምንጭ፦ EBC

ከጅቡቲ ወደብ በባቡር ተጓጉዞ እንዶዴ ባቡር ጣቢያ የሚደርሰውን የአፈር ማዳበሪያ በፍጥነት ወደ ማሠራጫ ማዕከሎች እንዲደርስ እየተሰራ ነው።በ በባቡር ጣቢያው በየቀኑ በአማካይ እስከ 10 ሺህ ...
26/07/2023

ከጅቡቲ ወደብ በባቡር ተጓጉዞ እንዶዴ ባቡር ጣቢያ የሚደርሰውን የአፈር ማዳበሪያ በፍጥነት ወደ ማሠራጫ ማዕከሎች እንዲደርስ እየተሰራ ነው።

በ በባቡር ጣቢያው በየቀኑ በአማካይ እስከ 10 ሺህ ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ወደ ተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች እንደሚሠራጭ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አስታወቀ።

የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ዴንጌ ቦሩ በእንዶዴ ባቡር ጣቢያ ተገኝተው በባቡር ተጓጉዞ የሚመጣው የአፈር ማዳበሪያ ወደ ተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚሠራጭበትን ሂደት ተመልክተዋል።

ሰሞኑን የአፈር ማዳበሪያን በማጓጓዝ ሂደት የታየው የመፈፀም አቅም በቀጣይ የሎጂስቲክስ ቅልጥፍናን ለማሳደግ በሚሠሩ ሥራዎች ላይ ትልቅ ትምህርት ይሆናል ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው፣ ባለድርሻ አካላት ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ተቀናጅተው በትጋት መስራታቸው ውጤት ማስገኘቱን ገልጸዋል።

የአፈር ማዳደሪያ ተጓጉዞ እስከሚያልቅ ድረስ በከፍተኛ ክትትል የሚሠራ መሆኑን ጠቁመው የተጀመረውን ቅንጅታዊ አሠራር በማጠናከር ሁሉም ባለድርሻ አካላት ሙሉ አቅማቸውን ተጠቅመው ሊሰሩ እንደሚገባም ማሳሰባቸውን ከሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ENA

08/01/2023
"ብልፅግና ቃል የገባውን የሚፈፅም ፓርቲ ነው!!"- ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድየታላቁ ቤተ መንግስት የመኪና ማቆምያ ፕሮጀክት በዛሬው እለት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ፤ከንቲባ ...
04/12/2022

"ብልፅግና ቃል የገባውን የሚፈፅም ፓርቲ ነው!!"
- ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ

የታላቁ ቤተ መንግስት የመኪና ማቆምያ ፕሮጀክት በዛሬው እለት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ፤ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች በተገኙበት ተመርቋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በምርቃቱ ስነስርዓት ላይ እንደተናገሩት እነኚህ ፕሮጀክቶች ትናንትን ፤ዛሬን እና ነገን የሚያገናኙ ፕሮጀክቶች ናቸው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ማንኛውም ስራ ለኢትዮጵያ ብልፅግና የሚያመጡ መሆናቸውን ማረጋገጥ አለብን ያሉት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ በከተማዋ የተሰሩት እንደ መስቀል አደባባይ ፤የእንጦጦ ፓርክ፤ የአድዋ ፕሮጀክት እና ሌሎችም የትናንት ትውስታ እና የዛሬ አዲስ ምልከታ ያላቸው ናቸው ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም ኢትዮጵያ እንዲህ ፀዳ ፀዳ ያለ ፕሮጀክት ነው የሚያስፈልጋት ብለዋል፡፡

ቃል ገብቶ አለመፈፀም የኢትዮጵያውያን ባህል አይደለም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ ቃል ከገባነው በወቅቱ ያልፈፀምነው የኢዮቤልዩ ቤተመንግስት ነው ያሉ ሲሆን እርሱም ቢሆን በውስጡ ላለ ሃብት ጥንቃቄ ሲባል ጥናቶች እየተካሄዱ በመቆየታቸው መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በበኩላቸው ከተማችን አዲስ አበባ በየእለቱ አዳዲስ ዜናዎች የሚበሰሩባት ፤የመታደስ የመለወጥ አሻራዎች የሚያርፉባት ከሆነች ዋል አደር ብላለች ሲሉ ገልጸዋል፡፡

አዲስ አበባ የቱሪዝም መተላለፍያ ሳይሆን የቱሪዝም መዳረሻ እናደርጋለን ብለን ስንነሳ፤ በከተማችን ጎስቋላ ገፅታና የኢኮኖሚያዊ ሁኔታ የተነሳ ሀሳባችንን ቅዠት አድርገው ያሰቡ ነበሩ ያሉት ከንቲባ አዳነች ይህ ስህተት መሆኑን በተግባር እያረጋገጥን ነው ብለዋል፡፡

በአራት ኪሎና አካባቢው አዲስ ዘመናዊ ከተማን የማነፅ ያህል እርስ በእርሳቸው የተሳሰሩና የተናበቡ ፕሮጀክቶች ተሰርተዋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ለዚሁ ስራ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ራሳቸው እንደ ሳይት ማናጀርና እንደ ኢንጂነር ተከታትለው ፤አቅደው ከተማ አስተዳደሩ ይተግበረው ብለው የሚመለሱ ብቻ ሳይሆን ፤ ክትትል አድርገው እስከመጨረሻው ያስፈፀሙ መሪ ናቸው ሲሉ ከንቲባዋ ተናግረዋል፡፡

ከንቲባ አዳነች አክለውም የከተማችን አስተዳደር በአመት 50 ቢሊዬን የሚሆን በጀት ለካፒታል በጀት እየመደበ ነው ያሉ ሲሆን ይህ ደግሞ ባለፉት አመታት የአዲስ አበባ የሁለት አመት በጀት የነበረ ነው ብለዋል፡፡

አንዳንዶች የአዲስ አበባ ገፅታ የሚቀይሩ ስራዎች ላይ ብቻ ነው ትኩረት ያደረጋችሁ ይሉናል ያሉት ከንቲባ አዳነች ይህ እውነት አይደለም በከተማችን በርካታ ሰው ተኮር ፕሮጀክቶችን እየተገበርን ብዙዎችን ተጠቃሚ እያደረግን ነው ብለዋል፡፡

በተጨማሪም ፕሮጀክቶቹ የውል ማራዘምና የውል ማሻሻያ ሳይደረግባቸው ለሌብነት እና ዝርፊያ የማይመች ሆነው በታለመላቸው ጊዜና በጀት መጠናቀቃቸው ትልቅ ትምህርት የሚወሰድበትት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የፀረ ሙስና ብሔራዊ ኮሚቴ መቋቋምሙስና ሀገርን የሚበላ ነቀዝ ነው፡፡ የሀገርን አንጡራ ሀብት እየቦረቦረ ጥሪቷን ባዶ ለማስቀረት ሌት ተቀን የሚማስን ተባይ ነው። ዋልጌ ባለሥልጣናት፣ በፍቅረ ...
17/11/2022

የፀረ ሙስና ብሔራዊ ኮሚቴ መቋቋም

ሙስና ሀገርን የሚበላ ነቀዝ ነው፡፡ የሀገርን አንጡራ ሀብት እየቦረቦረ ጥሪቷን ባዶ ለማስቀረት ሌት ተቀን የሚማስን ተባይ ነው። ዋልጌ ባለሥልጣናት፣ በፍቅረ ነዋይ የታወሩ ደላሎች እና ባለሃብቶች አንድ ላይ ሲገጥሙ፤ ከነዚህ የሌብነት ፊታውራሪዎች ጀርባ ብዛት ያላቸው ዜጎች መሰለፍ ሲጀምሩ ሙስና የተባለው ነቀዝ ሀገርን እንደ ወረርሽኝ ያጠቃታል፡፡ ሙስና በየትኛው ቦታና በየትኛውም ዘመን ሊኖር ይችላል፡፡ ነገር ግን የሀገርን ልማት አጥንቱ ድረስ እስከ መጋጥ ከደረሰ ሙስና አንድ አደገኛ ወረርሽኝ ሆኗል ማለት ነው፡፡ ሙስና ሀገርን ሊያፈርስ የሚችል የደኅንነት ሥጋት መሆኑን ያስመሰከሩ ሀገሮችን በዘመናችን አይተናል፡፡ የአደንዛዥ ዕጽ፣ የኮንትሮባንድ፣ ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር፣ ሕገ ወጥ የጦር መሣሪያ ንግድ፣ የንግድ ማጭበርበር ሙስናን ለዓላማቸው ማስፈጸሚያነት ይፈልጉታል፡፡ በዓለማችን የተጀመሩ ጦርነቶች እንዳይጠናቀቁ፤ ግጭቶች እንዳይበርዱ፣ ሕዝቦች እርስ በርስ እንዲጋጩ፣ ከሚያደርጓቸው ምክንያቶች አንዱ ሙሰኞች ከዚህ አይነት ቀውሶች ስለሚያተርፉ ነው፡፡

ሙስና ዛሬ የሀገራችን የደኅንነት ሥጋት ሆኗል፡፡ ወደ ብልጽግና የምናደርገውን ጉዞ እጅ ተወርች አሥሮ ለመያዝ ከጠላቶቻች እኩል ሙሰኛው እየታገለን ነው፡፡ የተስተካከለ ቢሮክራሲ፣ የተቀናጀ መዋቅርና ዘመናዊ አሠራር ለሙስና ተጋላጭነትን ስለሚቀንሱ፣ እነዚህን ለማጥፋት ወይም ለማሰናከል ሙሰኛው ቀን ከሌት እየሠራ ነው፡፡ሕዝባችን በአገልግሎት አሰጣጥ፣ ከመሬት ጋር በተያያዙ አሠራሮች፣ በፋይናንስ ዘርፍ፣ በሽያጭና ግዥ ሂደቶች፣ በፍትሕ አደባባዮች፣ በተለያዩ የመንግስት ተቋማት፣ የልማት ድርጅቶች፣ የህዝብ ተቋማት ወዘተ. በሚያጋጥመው ሙስና እየተማረረ ነው፡፡ በተለያዩ ጊዜያት ከሕዝብ ጋር በተደረጉ ውይይቶች ከጸጥታ ሥጋቶች እኩል ሙስና የብልጽግና ጉዟችን ዋናው ዕንቅፋት መሆኑን አንሥቷል፡፡

መንግሥት በየደረጃው የሚገኘውን መዋቅር በመፈተሽ፣ አዳዲስ አሠራሮችን በመዘርጋት፣ በቴክኖሎጂ የታገዙ ሥራዎችን እያሳለጠ ሥራዎችን ከእጅ ንክኪ ነጻ በማድረግ፣ በሙስና ወንጀል የሚሳተፉ አመራሮችንና ሌሎች ተዋንያንን ለሕግ በማቅረብ፣ ሙስና ምቹ ሁኔታ እንዳይፈጠርለት ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ ነገር ግን ሀገራችን ያጋጠማትን ጦርነትና ኮሮናን የመሳሰሉ ወረርሽኞች የመንግሥትን ትኩረት ወስደዋል ብለው ያሰቡ ሙሰኞች፣ በየቦታው ተሠግሥገውና ኔት ወርክ ዘርግተው፣ ኢትዮጵያን ለማጥፋት እየሠሩ መሆናቸውን በዝርዝር የቀረበው የጥናት ሪፖርት ያሳያል፡፡ መንግሥት በጸጥታው ዘርፍ እንዳደረገው ሁሉ በሙስና ላይ ጠንካራና የማያዳግም ኦፕሬሽን ማድረግ እንዳለበት የጥናቱ ውጤትና የሕዝብ ውይይቱ ግምገማ ያመለክታል፡፡ በአንድ በኩል የመንግሥት ሕጎች፣ደንቦች፣ መመሪያዎችና አሠራሮች ለሙስና ያላቸውን ተጋላጭነት የማጥፋት ሥራ ይሠራል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የሙስና ተዋንያንን የማጋለጥና በሕግ የመጠየቅ ተግባር ይከናወናል፡፡

መንግሥት በጥናት በደረሰባቸው የመንግሥት ሹመኞች፣ የመንግስት ተቋማት ሰራተኞች፣ አቀባባዮችና ጉቦ ሰጪዎች ላይ ምርመራ እያደረገ ይገኛል፡፡ ነገር ግን ሙስና በባሕርዩ በረቀቀ መንገድ፣ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም፣ አንዳንድ ጊዜም በሕጋዊነት ሽፋን የሚካሄድ በመሆኑ በመንግሥት ጥናት የተደረሰባቸው አካላትን ብቻ ለሕግ በማቅረብ የሚፈታ አይደለም፡፡ ሙስናን ከሥር ከመሠረቱ ለመንቀል እንዲቻል ከሕግና ከአሠራር ማሻሻያዎች በተጨማሪ፣ የሙስና ተዋንያን ሁሉ ሙስናን እርም እንዲሉ የሚያደርግ ርምጃ ያስፈልጋል፡፡መንግሥት በሙስና ላይ የሚያደርገውን ዘመቻ የሚያስተባብር፣ በጥናት ተለይተው ከቀረቡት በተጨማሪ ሌሎችንም ተዋንያን የሚለይና ለሕግ እንዲቀርቡ የሚያደርግ ብሔራዊ ኮሚቴ አቋቁሟል፡፡

ብሔራዊ ከሚቴው ሰባት አባላት ያሉት ሲሆን፣ እነርሱም፡-
1. አቶ ተመስገን ጥሩነህ
2. ዶ/ር ጌዴዎን ጢሞቴዎስ
3. አቶ ተክለ ወልድ አጥናፉ
4. አቶ ሰሎሞን ሶቃ
5. አቶ ደበሌ ቃበታ
6. ዶ/ር ሳሙኤል ኡርቃቶ
7. አቶ አብዱሃሚድ መሃመድ ናቸው፡፡

ይህ የፀረ ሙስና ብሔራዊ ኮሚቴ የተሰጠውን ኃላፊነት በብቃት ለመወጣትና ትርጉም ያለው ውጤት ለማምጣት እንዲችል የኅብረተሰቡ ሙሉ ትብብር እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ ኅብረተሰቡ በሙስና ላይ በሚደረገው ዘመቻ ሊሳተፍ እንደሚገባ በተለያዩ መድረኮች ሲያነሣ ቆይቷል፡፡ መንግሥትም ይሄንን የሕዝብ ተሳትፎ በእጅጉ ይፈልገዋል፤ ምክንያቱም ሙስና በዋናነት የሚጠፋው ሕዝብ አምርሮ ሲታገለው ነውና፡፡

በመሆኑም ኅብረተሰቡ የሙስና ተዋንያንን በተመለከተ ያለውን መረጃ፣ ከቂምና ከበቀል ነጻ በሆነ መንገድ፣ ከዚህ በታች በተዘረዘሩት አድራሻዎች ለብሔራዊ ኮሚቴው በመላክ ሙስናን ለማጥፋት በሚደረገው ትግል ንቁ ተሳታፊ እንዲሆን ጥሪ እናቀርባለን፡፡ የሚቀርቡ ጥቆማዎች የጠቋሚዎችን ደህንነት ለማረጋገጥ ተገቢውን ጥንቃቄ እና ሚስጥራዊነት በጠበቀ መንገድ ተይዘው ይመረመራሉ። ብሄራዊ ኮሚቴው የሚወስዳቸው እርምጃዎች እና የእንቅስቃሴው ውጤት በየጊዜው ለህዝብ ይፋ ይደረጋል። የየክልሉ ርእሳነ መስተዳድሮች በየደረጃው የሚሠሩ ክልላዊ ኮሚቴዎችን በቅርቡ እንደሚያቋቁሙ በዚሁ አጋጣሚ እንገልጣለን።

▪ ስልክ ፡ 9555
▪ አጭር የፅሁፍ መልዕክት : 9555
▪ ድረ ገፅ ፡ http://www.9555pmo.et/
▪ ኢሜይል : http://9555pmo.et/
▪ ቴሌግራም ፡ https://t.me/PMOfeedback

የሶማሌ ክልል ምክር ቤት አባል እና የብልፅግና ፓርቲ ማእከላዊ ኮሚቴ አባል የሆኑት ወ/ሮ ጁዋሪያ መሀመድ ኢብራሂም  በጅግጅጋ ኤርፖርት  ውስጥ ከአንድ የፀጥታ ሀይል አባል በተተኮሰ ጥይት ህ...
25/10/2022

የሶማሌ ክልል ምክር ቤት አባል እና የብልፅግና ፓርቲ ማእከላዊ ኮሚቴ አባል የሆኑት ወ/ሮ ጁዋሪያ መሀመድ ኢብራሂም በጅግጅጋ ኤርፖርት ውስጥ ከአንድ የፀጥታ ሀይል አባል በተተኮሰ ጥይት ህይወታቸው አልፏል።

በማእከላዊ ኮሚቴ አባላችን ላይ በደረሰው ህልፈት ፓርቲያችን ብልፅግና የተሰማውን መሪር ሀዘን እየገለፀ ለወዳጅ ዘመዶቿ እና ለትግል አጋሮቿ መፅናናትን ይመኛል።

18/10/2022

በትግራይ ክልል የሰብዓዊ አቅርቦት እና አገልግሎት ማስጀመርን በተመለከተ ከመንግሥት ኮሙኒኬሽን የተሰጠ መግለጫ
የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የተወሰኑ የትግራይ ክልል ከተሞችን መቆጣጠሩ ይታወቃል።
የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት በቅርቡ ባወጣው መግለጫ፣ የኢትዮጵያ ሠራዊት ከተሞች የጦርነት ቦታ እንዳይሆኑ የሚያደርግ የጥንቃቄ አካሄድ እንደሚከተል መግለጡ ይታወሳል።
የመከላከያ ሠራዊት በከተሞች ጦርነት እንዳይደረግ የተከተለው ጥብቅ ዲሲፕሊን፣ በሲቪሎች ላይ ጉዳት እንዳይደርስ አድርጓል። የኢትዮጵያ መከላከያ በከተሞች ውስጥ ምንም ዓይነት ጦርነት ሳያካሂድ ሽሬን፣ አላማጣና ኮረም ከተሞችን ለመቆጣጠር ችሏል።
ይህ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የተከተለው ጥብቅ ወታደራዊ ዲሲፕሊን፣ የሕወሐትን ፕሮፓጋንዳ ሲያስተጋቡ የነበሩ አካላትን ሟርት ያመከነ ነው።
ከልዩ ልዩ የርዳታ ድርጅቶች ጋር በመቀናጀት፣ መከላከያ በተቆጣጠራቸው አካባቢዎች ርዳታ በተሣለጠ መንገድ እንዲደርስ የኢትዮጵያ መንግሥት በቂ ዝግጅት አድርጓል። ይሄም የሽሬ አውሮፕላን ማረፊያን ተጠቅሞ ርዳታ ማድረስን ይጨምራል።
መንግሥት ከሰብአዊ የርዳታ ተቋማት ጋር በመቀናጀት ሰብአዊ ርዳታ የሚደርስባቸውን መንገዶች እያስፋፋ ነው። በተቀናጀ መንገድ በሰሜን ጎንደር በኩል ወደ ሽሬ የሚወስደውን እና ከኮምቦልቻ - ደሴ- ወልድያ- ቆቦ- አላማጣ ያለውን መንገድ ለመክፈት እየሠራ ነው።
ይሄንን ሥራ የሚያሣልጥ ኮሚቴ ከሚመለከታቸው አካላት ተወጣጥቶ ሥራ ጀምሯል። እነዚህ ሥራዎች ቴክኒካዊ የሆኑ ጥናቶችን እና ግጭት በነበረባቸው አካባቢዎች አገልግሎቶችን ለማስጀመር የሚያስችሉ መሠረታዊ ሥራዎችን ይጨምራል።
ጥቅምት 8 ቀን 2015 ዓ.ም
አዲስ አበባ
የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

Statement on the Resumption of Humanitarian aid and Services in the Tigray Region
18/10/2022

Statement on the Resumption of Humanitarian aid and Services in the Tigray Region

በሰሜን ኢትዮጵያ የሚካሄደውን የመከላከል ርምጃ በተመለከተ የተሰጠ መግለጫ ፦በአሁኑ ወቅት በሰሜን ኢትዮጵያ የተፈጠረው ግጭት፤  ሕወሓት ነሐሴ 18 ቀን 2014 ዓ.ም በሙሉ ዐቅሙ የከፈተውን ...
17/10/2022

በሰሜን ኢትዮጵያ የሚካሄደውን የመከላከል ርምጃ በተመለከተ የተሰጠ መግለጫ ፦

በአሁኑ ወቅት በሰሜን ኢትዮጵያ የተፈጠረው ግጭት፤ ሕወሓት ነሐሴ 18 ቀን 2014 ዓ.ም በሙሉ ዐቅሙ የከፈተውን ጥቃት ተከትሎ የመጣ መሆኑን ማስታወስ ተገቢ ነው። ይህም የኢትዮጵያ መንግሥት በሚያዝያ ወር ያወጀውን በሰብአዊነት ላይ የተመሠረተ የተኩስ አቁም የጣሰ ነው። የመንግሥት ጥረት ምንም ዋጋ ስላልተሰጠው፣ ሕወሓት በሁለት ዓመት ውስጥ ሀገሪቱን ለሦስተኛ ጊዜ ወደ ግጭት አስገብቷታል።

ሕወሓት ሦስተኛውን ግጭት የከፈተው በአፍሪካ ኅብረት በኩል በሚደረገው የሰላም ንግግር፣ ያለ ቅድመ ሁኔታ በየትኛውም ጊዜና ቦታ ላይ ለመነጋገር የኢትዮጵያ መንግሥት ዝግጅነቱን ከገለጠ ከጥቂት ጊዜያት በኋላ ነው። ከዚህም በተጨማሪ ለልዩ መልእክተኞችና መቀመጫቸውን በአዲስ አበባ ላደረጉ ዲፕሎማቶች ጥቃት ለመሠንዘር ሕወሓት ያለውን ዝግጁነት አመልክቶ ነበር። ሕወሓት ለተለያዩ ዓለም አቀፍ አካላት በበተነው ደብዳቤ ላይ ይሄንን ጥቃት የመክፈት ፍላጎቱን በግልጽ አመልክቷል። በመሆኑም አሁን ለተፈጠረው ችግር ሁሉ ብቸኛ ተጠያቂው ሕወሓት መሆኑ የተረጋገጠ ነው። ጊዜና ቦታ ከተሰጠውም ሌላ ዙር ግጭት እንደሚፈጥር ከሰሞኑ መግለጫዎቹ ለመረዳት ይቻላል።

ሕወሓት በሙሉ ዐቅሙ ጥቃት ከመክፈቱ በፊት የኢትዮጵያን የአየር ክልል ደጋፊዎቹ በሆኑ የኢትዮጵያ የውጭ ጠላቶች ሲያስደፍር ቆይቷል። በዚህም የተነሣ የኢትዮጵያ መንግሥት የሀገሪቱን ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት የመጠበቅ ግዴታውን እንዲወጣ አስገድዶታል። የኢትዮጵያመንግሥት የሚወስዳቸው እርምጃዎች የግድ አስፈላጊ የሆኑት በሕወሓት ተደጋጋሚ ጥቃት የተነሣ ብቻ ሳይሆን ከሀገሪቱ ታሪካዊ ጠላቶች ጋርተቀናጅቶ በሚፈጽማቸውተግባራት ምክንያት ጭምር ነው። ስለሆነም የሀገሪቱን ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት ለማስከበር የኢትዮጵያ መንግሥት የአውሮፕላን ማረፊያዎችን፣ የፌዴራል ተቋማትንና ታላላቅ መሠረተ ልማቶችን የግድ መጠበቅ አለበት ማለት ነው። ይህም የሀገሪቱን ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት በተለይም የአየር ክልልን በሚገባ ከማስከበር አንጻር መጠበቅን የግድ አድርጎታል።

እነዚህ ተግባራት መፈጸሙ መንግሥት ሰብአዊ ርዳታን ለተረጂዎች በተገቢው ሁኔታ እንዲያሣልጥ የሚረዳው ይሆናል። በአንድ በኩል እነዚህን ዓላማዎች እያስፈጸመ በሌላ በኩል ደግሞ በአፍሪካ ኅብረት አማካኝነት ለሚካሄደውየሰላም ውይይት ዝግጁ መሆኑን የኢትዮጵያ መንግሥት በድጋሚ ያረጋግጣል። ዘላቂ ሰላም እንዲመጣ ሁለንተናዊና በንግግር ላይ የተመሠረተ ስምምነት አስፈላጊ መሆኑን መንግሥት ያምናል።

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አግባብነት ባላቸዉ አሠራሮችና በዓለም አቀፍ የሰብአዊ ሕጎች በጽኑ የሚገዛ መሆኑን መንግሥት ግልጽ ለማድረግ ይፈልጋል። ንጹሐን እንዳይጎዱ ለመከላከል እንዲቻል የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት ጦርነቱ በከተሞች ውስጥ እንዳይደረግ ጥንቃቄ እያደረገ ይገኛል። ይሄንን በጽኑ ለመፈጸም እንዲቻልም ለሁሉም ተዋጊ አሐዶች ጥብቅ መመሪያ ተላልፏል።

ከዚህም ባሻገር በመንግሥት ቁጥጥር ሥር በሆኑ አካባቢዎች ሰብአዊ እርዳታ በተሻለ መንገድ መቅረብ እንዲችልና የእርዳታ ሠራተኞች ደኅንነት የተጠበቀ እንዲሆን መንግሥት ከእርዳታ ድርጅቶች ጋር አብሮ ለመሥራት ዝግጁ ነው። ሕወሓት ንጹሐንን እንደ ጦር መከላከያ የመጠቀምና ሲቪል ተቋማትን ለወታደራዊ ሠፈርነት የመጠቀም የቆየ ልማድ አለው። ስለሆነም ሕዝቡና የእርዳታ ሠራተኞች ራሳቸውን ከሕወሓት ወታደራዊ ተቋማት እንዲያርቁ የኢትዮጵያ መንግሥት ጥሪ ያደርጋል። የርዳታ ሠራተኞችን ጨምሮ በሲቪሎች ላይ ለሚደርሰው ማንኛውም ጉዳት መንግሥት ኀዘኑን በዚህ አጋጣሚ ይገልጣል። እውነቱን ለማወቅና ያልተገደበ የእርዳታ ተደራሽነትን ለማረጋገጥ እንዲቻል ጉዳቶች ከተከሠቱ የሚያጣራ ይሆናል።

በመጨረሻም፣ በትግራይ ክልል የሚገኙ ዜጎቹን ደኅንነት ለመጠበቅ በሕግ የተሰጠውን ሕገ መንግሥታዊ ግዴታውን ለመወጣት የኢትዮጵያ መንግሥት ያለውን ዝግጁነት በዚሁ አጋጣሚ ያረጋግጣል።

ጥቅምት 7 ቀን 2015 ዓ.ም
አዲስ አበባ
የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

የመጣነው ችግኝ ለመትከል ብቻ ሳይሆን ወንድማማችነትንም  ለመትከል ነዉ _ ዶክተር  ቢቂላ ሁሪሳ  #የኢትዮጵያ  ልዑካን  ቡድን ናይሮቢ ገብቷል ፣ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የዴሞክራሲ ...
13/10/2022

የመጣነው ችግኝ ለመትከል ብቻ ሳይሆን ወንድማማችነትንም ለመትከል ነዉ _ ዶክተር ቢቂላ ሁሪሳ
#የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን ናይሮቢ ገብቷል ፣

በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ በዶክተር ቢቂላ ሁሪሳ የተመራ የልዑካን ቡድን በናይሮቢ ጆሞ ኬንያታ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል ፡፡

በኬንያ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ባጫ ደበሌ ለልዑካን ቡድኑ የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

የ'መጣነው ችግኝ ለመትከል ብቻ አይደለም' ያሉት ዶክተር ቢቂላ 'ወንድማማችነትን ለመትከልና የሁለቱን ህዝቦች የጋራ አንድነታችን ለማጽናት ነው' ብለዋል፡፡

ዶክተር ቢቂላ አያይዘውም ባለፉት አራት ዓመታት በኢትዮጵያ 22 ቢሊዬን ችግኞች መተከላቸዉን ገልጸው ፣ ዓለምን እየፈተነ ያለው የአየር ንብረት ለውጥ ኢትዮጵያ ብቻ በምታካሂደው የአረንጓዴ አሻራ ርብርብ መካላከል ስለማይቻል አፍሪካዊያን እርስ በእርስ ተሳስረን ልንሰራ ይገባል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በልኡኩ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማዕከል የወጣቶች ሊግ ፕሬዝደንት ወጣት አስፋው ተክሌ ጨምሮ
ከተለያዩ ክልሎች የተወጣጡ ወጣቶች እና ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ይገኙበታል፡፡

የልኡካን ቡድኑ በነገው ዕለት በዋና ከተማዋ ናይሮቢ ከአገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር በመሆን ችግኞችን እንደሚተክሉ ይጠበቃል፡፡

Address

Addis Ababa
33914

Telephone

+251111554564

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Prosperity Party - የብልጽግና ፓርቲ ልሳን posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Prosperity Party - የብልጽግና ፓርቲ ልሳን:

Videos

Share

Nearby media companies