Bilal Tube ቢላል ቲዩብ

Bilal Tube ቢላል ቲዩብ እውነተኛ የሆኑ መረጃዎችን የፔጃችን ወዳጅ በመሆን ያግኙ

18/04/2024

የት እንሂድ? ወዴት እንሰደድ? 😥😥😥 ከክልላችን ውጭ በአማራነት ስም የደረሰብን ግፍ የተሰራብን በደል ልክ አልነበረውም። ክልላችን ውስጥ ደግሞ «እስላም» በሚል በየቀኑ የምንሰማው ዜና ያሳምማል።

ወላሂ ወቢላሂ ያልፃፍኩት ግፍ ብዙ ነው። በጌታዬ እምላለሁ እፍራንዝ በዙሪያዋ ያሉ ሙስሊሞች የሚላስ የሚቀመስ ሳይዙ ተፈናቅለው የከትማዋ መስጅድ ተጠልለዋል። በተለይ ደረሳዎችና ከ40 አመት በፊት ከወሎ አካባቢ የሄዱ ወገኖች የደረሰባቸው ግፍ ዘግናኝ ነው።

በግልፅ የሀይማኖት ጥቃት ነው። ሀሪማዎች ተቀጥለዋል። መኖሪያቸው ወድሟል። እንግዲህ ገንደር ዙሪያ «እርስታችንን አስመለስን» አይነት ጨዋታ ማኔ ከማን እንደሚያስመልስ ወደፊት ይታያል። በእሳት መጫወት ይቅር። የመከላከያን ቆም አንገታቸውን ደፍተው በሚኖሩ ሙስሊሞች ላይ መወጣት ጀግንነት አይደለም።

ይህንን ጉዳይ ቅን ክርስቲያኖች ቢያስቆሙት መልካም ነው። በተለይ በተለይ ስለጉዳዩ በቅርበት የምታውቁ የአካባቢ ሀገረ ስብከት መሪዎች እባካችሁ መፍትሄ ፈልጉ። ይህንን ጉዳይ ለሚመለከተው አድርሱ። እንፍራንዝ የምታውቁት ካለ ደውላችሁ ማረጋገጥ ትችላላችሁ። ህዝቡ ደንግጦ እንዲፈናቀል 4 ደረሳዎች ተረሽነዋል።

መጨረሻውያስከፋል ወላሂ። ከፖለቲካ ውጭ ያለ ማህበረሰብ በእምነቱም ሆነ በማንነቱ ሊነካ አይገባም። የሀይማኖት ግጭት በምንም ስሌት አያዋጣም። በምንም ሂሳብ ልክ አይደለም።

«ውሃን በመጎንጨት ቢሆን እንኳ ስሁርን ተጠቀሙ።»ነብዩ ሙሐመድ ‎ﷺ
10/03/2024

«ውሃን በመጎንጨት ቢሆን እንኳ ስሁርን ተጠቀሙ።»

ነብዩ ሙሐመድ ‎ﷺ

10/03/2024

የኑሮ ውድነቱን በሰደቃ ዘመቻ የምናጠፋበት ጾም ያድርግልን!
መልካም ረመዳን

05/03/2024

የሀጅ ምዝገባ ተራዝሟል።

ከጥቂት አመታት በፊት ሳውዲ አረቢያ ፡ ጅዳ ውስጥ አሮጌው ( አልባላድ ) ድልድይ የሚባለውን  አካባቢ የሚያውቅ  ሰው ይህንን የስምንት አመት ልጅ ያውቀዋል ።ይህ ታዳጊ ከ12 አመቷ እህቱና ...
23/02/2024

ከጥቂት አመታት በፊት ሳውዲ አረቢያ ፡ ጅዳ ውስጥ አሮጌው ( አልባላድ ) ድልድይ የሚባለውን አካባቢ የሚያውቅ ሰው ይህንን የስምንት አመት ልጅ ያውቀዋል ።

ይህ ታዳጊ ከ12 አመቷ እህቱና ከእናቱ ጋር ፡ ኑሮን ለማሸነፍ ከኢንዶኔዥይ ወደ ሳውዲ አረቢያ ጅዳ መጥተው የሚኖሩ ሲሆን ፡ ይሻላል ያሉት የሳውዲ ኑሮ እንዳሰቡት አልሆን አለና ችግር ላይ ወደቁ .
እና አንድ ቀን ይህንን የቤተሰቡን ችግር የተረዳው የ8 አመቱ ኢልያስ እህቱ ዩስራ አዘውትራ በደብተር ላይ የምትሞነጫጭራቸው ስእሎች እንድትሰጠው ጠየቃት ።

" እነዚህን ስእሎች ሽጨ ለእናታችን ገንዘብ ማምጣት እፈልጋለሁ "..

እነዚህን ስእል ብሎ ማን ይገዛሀል አለችው
ብቻ ዝም ብለሽ ስጭኝ
ከደብተሯ ላይ የሞነጫጨረችውን ስእሎች እየቀደደች ሰጠችው ።
ትንሹ ኤልያስ ስእሎቹን ይዞ ፡ አሮጌው የባላድ ድልድይ ስር ተቀመጠ ።....
አላፊ አግዳሚው እያየው ያልፋል ። አንዳንዶቹ ደግሞ ይህ ትንሽ ልጅ መሬት ላይ ያስቀመጣቸውን በደብተር ሉክ ላይ በስክሪብቶና በከለር የተሞነጫጨሩ የልጅ ስእሎች እያየ ምንድነው ሲሉት ፡ እህቴ ዩስራ የሳለቻቸውን ስእሎች እየሸጥኩ ነው
ስንት ነው ?
አንድ ሪያል
የልጁ ሁኔታ ያሳዘናቸው ሰወች የተወሰኑ ስእሎችን ገዙት
ከሰአታት በኋላ ኤልያስ ከያዛቸው ስእሎች ግማሹን በአንድ ሪያል ሂሳብ ሽጦ አስራ ሁለት ሪያል ይዞ ወደ ቤቱ ሄደ ።...
ምንም ብር ለሌለው ለነኤልያስ ቤተሰብ ይህ ገንዘብ ብዙ ነበር ። እቤት እደገባም ለእህቱ ሉክና እስክሪብቶ አምጥቶ ፡ ሌሎች ስእሎችን ሳይ አላት ።
ነገ የምሸጣቸው ተጨማሪ ስእሎች ያስፈልጉኛል

እህቱ ተጨማሪ ስእሎችን ስትስል አመሸች
ጠዋት ይዟቸው ወጣና የተለመደው ቦታ ተቀመጠ ።.......
በዚህ መልኩ ጥቂት ቀናትን እንዳሳለፈም አንድ የሳውዲ ጋዜጣ ( Saudi gazette ) ሪፖርተር ይህንን ህጻን ያየዋል።.........
እና ይህንን ለልመና እጁን ያልዘረጋ ፡ ከዛ ይልቅ የእህቱን ስእሎች ሽጦ ቤተሰቡን ለመርዳት ስላሰበው የ8 አመት ኢንዶኔዥያዊ ህጻን በተመለከተ በጋዜጣው ላይ ጻፈ ።
ይህንን ተከትሎም የህጻኑ ሁኔታ ልባቸውን የነካቸው ሰወች ፡ በትዊተር ላይ ፡ አንድ ሪያል ላንድ ስእል በሚል ሀሽታግ ዘመቻ ጀመሩ ።...
በዚህ የሶሻል ሚዲያ ካምፔን ብዙ ሰወች ዘመቻውን ተቀላቅለው የዚህን ታዳጊ ቤተሰብ ለመደገፍ ገንዘብ ሰበሰቡ ።........
የጉዳዩን ቫይራል መሆን ያዩት የሳውዲ አረቢያ የባህልና የኪነጥበብ ማህበር ሃላፊ ይህንን ታዳጊ ፈልጋችሁ አምጡልኝ ሲሉ ትእዛዝ ሰጡ ።.....
የሳውዲ ባህልና ኪነጥበብ አባላትና ትላልቅ ሚዲያዎች በተገኙበት አንድ ፕሮግራም ተዘጋጅቶ ታዳጊው ኤልያስ ፡ ከእህቱ ዩስራ እና ከእናቱ ጋር እንዲገኙ ተደረገ ።......
ባለሀብቶች ይህንን ቤተሰብ እንደግፋለን ሲሉ ቃል ገቡ ። ኤልያስና ዩስራ ትምህርት የሚገቡበት መንገድ ተመቻቸ ፡ ለእናቱ ስራ ተገኘላት ።...
የእህቱን ስእሎች ሽጦ ቤተሰቡን ለመደገፍ በሞከረው ታዳጊና ፡ ይህንን በተረዱ መልካም ሰወች እገዛ ምክንያት ነገሮች ተለዋወጡ ።

ይሄ ነገር ወዴት እያመራ ነው? ለሚልህ ወደሀላባ የደጎች ሀገር በለው።ለኡለማዎች የተደረገ አቀባበል
14/02/2024

ይሄ ነገር ወዴት እያመራ ነው? ለሚልህ ወደሀላባ የደጎች ሀገር በለው።

ለኡለማዎች የተደረገ አቀባበል

10/02/2024
ለሐጅ ሲባል አዲሰ  ፖስፖርት ማውጣትና እድሳት ማድረግ  መፈቀዱ ተገለጸየካቲት- 2/ 2016 ረጀብ 29/1445ሐጅ ለማድረግ ፈልገው ፓስፖርት ለሌላቸውና ለፓስፖርት እድሳት ለሚጨነቁ ምዕመናን...
10/02/2024

ለሐጅ ሲባል አዲሰ ፖስፖርት ማውጣትና እድሳት ማድረግ መፈቀዱ ተገለጸ

የካቲት- 2/ 2016
ረጀብ 29/1445

ሐጅ ለማድረግ ፈልገው ፓስፖርት ለሌላቸውና ለፓስፖርት እድሳት ለሚጨነቁ ምዕመናን፣ መጅሊስ ከኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ጋር በመነጋገር መፍትሔ ማመቻቸቱን ገልጿል።

ከመጅሊስ መደበኛ ገጽ ያገኘነውን መረጃ እንደሚከተለው እናቀርበዋለን።

በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሐጅና ዑምራ ዘርፋ ኃላፊና የሐጅ ዓብይ ኮሜቴ አቶ አብድልፈታህ መሐመድ ናስር ለሐጅ ጉዳይ አዲስ ፖስፖርት ማውጣት እና ፓስፖርት የማሳደስ ጥያቄን ከኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ጋር በተደረገው መልካም ውይይትና ሰምምነት ችግሩ የተፈታ መሆኑን አሳውቀዋል።

ጠቅላይ ምክር ቤቱ የ1445 ሐጅ ጉዞ ከዓምናው በተሻለ መልኩ ዘመናዊ አሰራሩን ከፍ ማድረጉን የገለጸ ሲሆን ሂደቱንም ለማሳለጥ ቀድሞ ከነበረው 18 የሐጅ ምዝገባ ጣቢያ ወደ 27 የሐጅ ምዝገባ ጣቢያ ከፍ ተደርጓል ተብሏል።

የሳውዲ አረቢያ የሐጅ ሚኒስተር የሐጅ ምዝገባው ለአጭር ጊዜ አንዲሆን ባወጀው መሰረት ማህበረሰባችን የሐጅ ምዝገባው ሂደት ገና መስሎት እዳይዘናጋ የሐጅ ዓብይ ኮሜቴ አቶ አብድልፈታህ መሐመድ ናስር ያስታወሱ ሲሆን በዚህ ዓመት ሐጅ ለማድረግ ኒያ ያለው የሙስሊሙ ማኀበረሰብ የሐጁ ምዝገባ ሂደቱ ለአጭር ጊዜ በመሆኑ የሐጅ ጊዜ ከማጠናቀቂያው የካቲት፣27/72016 (ማርች፣6/2024) በፊት ሁጃጆቾ በየምዝገባ ጣቢያዎች ተገቢውን መስፈርት አሟልተው ዝግጁ እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል።

የየከተማ አስተዳደሮች የክልል መጅሊስ አደረጃጀቶችና የሐጅ ምዝገባ ጣቢያዎች ለሁጃጆች ቀልጣፋ እና ተገቢውን አገልግሎት እዲሰጡ የሐጅ ዓብይ ኮሚቴው አሳስቧል።

ምንጭ :- ከመጅሊስ ገጽ

10/02/2024

ሰበር ዜና
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት የሐጅና ዑምራ ዘርፍ:-"የሳውዲ አረቢያ የሐጅ ሚኒስትር የሐጅ ምዝገባ ለአጭር ጊዜ አንዲሆን ባወጀው መሰረት የመጨረሻው ቀን:-
የካቲት 27/2016 ወይም ሻእባን 25/1445 ወይም ማርች 6/2024 መሆኑን አሳወቀ

10/02/2024

ያለፈው ሳምንት "ጀለሶች" የአክስቴን ልጅ ከባቲ (ከቤቱ ለሊት 6 ሰአት) ጠልፈው (አግተው) ወሰዱት… በራሱ ስልክ ደወሉልን… 500 ሺ ብር ጠየቁ የባንክ አካውንት ላኩ… በድርድር ቀንሰው ብር ገባላቸው… ለቀቁት… !"😊

ፖሊስ ከአቅማችን በላይ ነው ይልሀል…
እሺ በአካውንት ቁጥሩ ባንክ ሄዳቹህ ፎቶውን አሳዩን… ወይም ራሳቹህ እወቁትና እርምጃ ውሰዱ… ባንኩም እምቢ ፖሊሱም እምቢ… 😏

"እገታ" መንግስት የፈጠራት የስራ እድል ትመስለኛለች

02/02/2024

ትኩረት ካልተሰጠው ፣ ትልቅ አጅር ከሚያስገኙ ስራዎች መካከል እዳ ያለባቸውን ሰዎች እዳቸውን ማቃለል ነው ። እዳ ያለባቸው ሰዎች ዘካ ከሚገባቸውም ሰዎች መካከል ናቸው ። ሌላው እስረኞችን መመገብም የሚወደድ ስራ ነው ። የእዳ ክምር ያስጨነቃችሁ ሰዎች ደግሞ ይቺን ዱዓ ብትሃፍዙ እና ጠዋትም ማታም ብታደርጉ አላህ ፈረጃውን ያቅርብላችኋል ። የረሱል ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም ሀዲስ ነው ።

አንድ ጊዜ አቡኡማማ የተባለ ሶሃባ ከሶላት ሰዓት ውጭ መስጅድ ውስጥ ቁጭ ብሎ ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) አገኙት። ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ከሶላት ሰዓት ውጭ መስጅድ ያስቀመጠህ ጉዳይ ምንድን ነው አሉት

የከበበኝ ሃሳብ እና ጭንቀት ያለብኝ የሰው እዳ ብድር ነው አላቸው
እርሳቸውም ከዚህ ጭንቀት የምትገላገልበት ዱአ ላስተምርህን አሉት ?
አዎ አላቸው
እሳቸውም ይህን ዱዓ በጠዋትም በማታም በል ብለው አስተማሩት።
አቡ ኡማ ከዚያ በኋላ በጠዋትም በማታም ማለት ጀመርኩ። ጭንቀቴንም ተገላገልኩ ። እዳየም ተከፈለ አለ ።

ያስተማሩት ዱዓ ይኼ ነው። እናሃፍዘውና በጠዋት እና በማታ በሉት
ሀሳብና ጭንቀት ለገባችሁ ፣ የሰው እዳ ላስጨነቃችሁ እነሆ መፍትሄው የረሱል (ሰአወ) ብስራት ምርጥ ምክርና ዱአ ሀፍዙት
---
አሏሁመ ኢኒ አኡዙቢከ ሚነል ሀሚ ወሚነል ሀዘን
ወአዙቢኪ ሚነል አጅዚ ወሚነል ከሰል
ወአኡዙቢከ ሚነል ጁብኒ ወሚነል ቡኹል
ወአኡዙቢከ ሚን ኸለበቲ አድ ደይኒ..ወቃህሪ ሪጃል
አምላኬ ከሃሳብ እና ትካዜ ባንተ እጠበቃለሁ
ከመሳን እና ከስንፍና ባንተ እጠበቃለሁ
ከፈሪነት እና ስስታምነት ባንተ እጠበቃለሁ
ከብድር ሀያልነትና ከወንድ ልጅ ሽንፈት ባንተ እጠበቃለሁ

21/01/2024

በድጋሚ እጠይቃለሁ፤ ከሁለቱ በኢስላማዊ መስፈርት የተመሰረቱ ዘምዘምና ሂጅራ ባንክ ከተከፈተ ቡኃላ ታላላቅ የአገሪቱ ዓሊሞች የአቢሲኒያ እና የንግድ ባንክ ባጠቃላይ በወለድ ላይ የተመሰረቱ ባንኮች የሸሪዓ ቦርድ ሰብሳቢ ሆኖ እያገለገሉ ነው።

እኔ ከሁሉም ባንክ አክሲዮንም ሆነ ከ500 የዘለለ ገንዘብ የለኝም ግን መጠየቅ ስለ ፈለግኩ ነው።

ምክንያቱም ሁለቱ ከዚህ በፊት መስዋዕትነት የተከፈሉለት ኢስላሚክ ባንኮች ምሳሌ ሂጅራ እና ዘምዘም ሙስሊሙን ወደ እነርሱ ካላአዘነበሉ ጉድለቱ የባንኩ ነው ወይስ በእነዚያ ባንኮች ውስጥ አማካሪ ሆኖ የቀሩት የእኛዎች ዓሊሞች ችግር ነው?

Jafer

ሙሽራው አዲስቱን ሚስት ይዞ ጫጉላ ክፍል ገባ። ፊቷ ላይ የሸፈነችውን መቅረምያ ከፈት ሲያደርገው ፈፅሞ ያልጠበቃት ጥቁር ሴት ሁና ተመለከታት።ተበሳጭቶ ትቷት ተኛ። ብስጭቱ ለቀናት ኩርፍያን ወ...
14/01/2024

ሙሽራው አዲስቱን ሚስት ይዞ ጫጉላ ክፍል ገባ። ፊቷ ላይ የሸፈነችውን መቅረምያ ከፈት ሲያደርገው ፈፅሞ ያልጠበቃት ጥቁር ሴት ሁና ተመለከታት።

ተበሳጭቶ ትቷት ተኛ። ብስጭቱ ለቀናት ኩርፍያን ወልዶ ለተከታታይ ቀናት ብቻውን አደረ። ሙሽሪት በጥቁረቷ መ'ጠላቷን በተገነዘበች ግዜ፦‹‹ማሊክ! ምናልባት መልካም ነገር ከመጥፎ ስር ተሸሽጎ ይሆናል›› ብላ በቅኔ ወደ አልጋ ጠራችው። ያችን ሌት አብረው አደሩ።

ግና ጥቁረቷ ምቾት የነሳው ባል ዳግም ወደ ኩርፍያው ገባ። በዚህኛው ዙር ግን ኩርፍያው 20 አመታትን የፈጀ ነበር።

ባል ከእንዲት ቀን የጫጉላ አዳር በኋላ ከተማይቱን ትቶ ጠፋ። ከ20 አመታት ቆይታ በኋላ ባል ወደ ከተማይቱ ዳግም ተመለሰ። መዲና ሲገባ ወደ ቀዬው ከመሄዱ በፊት መስጅድ ለሰላት ገባ፤ ከመስጅዱ ውስጥ ሰዎች አንድን ሰው ከበውት በተመስጦ እና በፅሞና ሲያዳምጡት ተመልክቶ ጠጋ ብሎ ተቀመጠ።

ንግግሩ ማራኪ ነው፣ አገላለፁ እፁብ ነው፦‹‹ይሁ ምጡቅ ማን ይሁን?›› ብሎ ሀገሬውን ጠየቀ።
‹‹አባቱ ማሊክ ይባላል። ይህ ልጅ ሳይወለድ በፊት የዛሬ 20 አመት ነበር ከዚህ ከተማ የጠፋው›› ብለው የገዛ ታሪኩን ባዳ አድርገው አወጉት።

ግራ መጋባት ወረረው፣ የጥፋተኝነት ስሜት አሳፈረው። ወደ ልጁ ተጠግቶም፦‹‹እቤታችሁ ውሰደኝ›› ብሎ ተማፀነ።
ልጅም እንግዳውን ይዞ ወደ ቤቱ አመራ። ግና እንግዳው ደጅ ላይ ቁሞ፦‹‹ምናልባት መልካም ነገር ከመጥፎ ስር ተሸሽጎ ይሆናል ብለህ ለእናትህ ንገርልኝ›› ብሎ ላከው።

ልጅም ገብቶ መልዕክቱን አደረሰ። እናት በትዝታ ወደ ኋላ 20 አመታትን አወሳች፤ ቂም ስሜቷን ውጣ፦‹‹ልጄ ውጣ አባትህን ተቀብለህ አስገባው፤ ለ20 አመታት በመጥፋቱም ፈፅሞ እንዳትወቅሰው›› ብላ ትዳሯ ላይ ዳግም ህይወት ዘራች።

ይህች ጥቁር እናት ለበርካታ ዘመናት ትውልዶች የሚሸጋገር የሀዲስ ጥርቅሞችን የሰነደ ልጅም በመልካም አስተዳደግ አሳድጋ ለኡመቱ አበረከተች።

ረዥም ፁሁፍ ለማታነቡ ሙስሊሞች ቤተል ለመስጂድ መስሪያ ተብሎ የተሰጠው አዲሱ ቦታ 'በተቅዋ መስጂድ ምትክ ነው....' እየተባለ ነው። የውጫሌ ውል በጣሊያን'ና በኢትዮጲያ መሀል ያስከተለውን ...
11/01/2024

ረዥም ፁሁፍ ለማታነቡ ሙስሊሞች ቤተል ለመስጂድ መስሪያ ተብሎ የተሰጠው አዲሱ ቦታ 'በተቅዋ መስጂድ ምትክ ነው....' እየተባለ ነው። የውጫሌ ውል በጣሊያን'ና በኢትዮጲያ መሀል ያስከተለውን ጦርነት የሚያውቅ ማንኛውም ሙስሊም ይሄን ድርድር በቸልተኝነት አያልፈውም !

ሰሞኑ በኮሎምቢያ ይፋ በሆነ ጥናት በአንድ ሌትር የታሸገ ውሃ ውስጥ ከ250 ሺ በላይ በዐይን የማይታይ የፕላስቲክ ቁርጥራጭ እንደሚገኝ ይፋ ተደረገ ።የታሸገ የፕላስቲክ ውሃ የሚጠጡ ሰዎች የኩ...
11/01/2024

ሰሞኑ በኮሎምቢያ ይፋ በሆነ ጥናት በአንድ ሌትር የታሸገ ውሃ ውስጥ ከ250 ሺ በላይ በዐይን የማይታይ የፕላስቲክ ቁርጥራጭ እንደሚገኝ ይፋ ተደረገ ።

የታሸገ የፕላስቲክ ውሃ የሚጠጡ ሰዎች የኩላሊት ኢንፌክሽንን ጨምሮ ለተለያዩ ዐይነት በሽታዎች ተጋላጭ እንደሚሆኑ ጥናቱ ይፋ አድርጎዋል ።

በተለይ የታሸገ የፕላስቲክ ውሃ ለነፍሰጡር ሴቶችና ህጻናት አደገኛ ነው ተብሎዋል ።
ዘገባው የአል አረቢያ ነው

https://vm.tiktok.com/ZM6HUg1Bv/

"ዱንያ በኛ ፍጥነት፣ አቅልና ብልጠት የሚመጣ መስሎን፤ ሐራሙን ከሐላሉ ቀላቅለን የምንኖር ሰዎች ሆይ!የተወሰነልንን እንጂ አናገኝም! የተወሰነልን እንጂ አይደርሰንም!"© ኡስታዝ አቡበከር አሕ...
06/01/2024

"ዱንያ በኛ ፍጥነት፣ አቅልና ብልጠት የሚመጣ መስሎን፤ ሐራሙን ከሐላሉ ቀላቅለን የምንኖር ሰዎች ሆይ!
የተወሰነልንን እንጂ አናገኝም! የተወሰነልን እንጂ አይደርሰንም!"

© ኡስታዝ አቡበከር አሕመድ

አልሃምዱሊላህ «የቀጣይ ምእራፍ...» አሻራ በትናትናው እለት በሸገር ከተማ በመና አብቹ ክፍለ ከተማ የአከባቢው ሙስሊም ማህበረሰብ የዘመናት ጥያቄ የበረው የመስጂድ ቦታ  በዛሬው እለት  ቦታ...
06/01/2024

አልሃምዱሊላህ
«የቀጣይ ምእራፍ...» አሻራ

በትናትናው እለት በሸገር ከተማ በመና አብቹ ክፍለ ከተማ የአከባቢው ሙስሊም ማህበረሰብ የዘመናት ጥያቄ የበረው የመስጂድ ቦታ በዛሬው እለት ቦታውን በማስዳት በቦታው የመጀመርያ የሆነው ጁሙኣ ሰግዶ በታል

የከተማ አስተዳደሩ የተሟላ ካርታ ሳይት ፖላንና የግንባታ ፍቃድ የተሰጠው ሲሆን የክፍለ ከተማው መጅሊስም ብዙ ዋጋ ከፍሎ በትናንትናው እለት ህዝቡን በማስተባበር በአጥር አስከብሯል።

መንግስት የጀመረውን በጎ ምላሽ አጠናክሮ እንዲቀጥልና የህዝበ ሙስሊሙን እንባ እንዲባስ የተጀምረውን ከተቋም መልካም ግንኙነት ይገፋበታል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። ስትነካን የምንወቅስህ ስትገፋን የምንከስህ መንግስት ሆን መልካም ስትሰራ ያላመሰገንህ ስራህ ስለሆነ ነው።

05/01/2024

ሌላ ብስራት ከአንድ ወንድማችን «ብሎኬት እንዳይነካብኝ» ብሏል። ብሎኬት ለመግዛት ያሰባችሁ ወደ አሸዋ ቀይሩት። ወይም ሌላ ማቴሪያል።

05/01/2024

ከተቋማት አፍራን ሆስፒታል 1,000,000ብር
ከግለሰብ ሱፍያን ኡስማን 500,000ብር እየመሩ ነው።

በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አዲሱ ተቅዋ መስጂድ መነሻ ኘላንይህ አዲሱ ተቅዋ መስጂድ ነው።"መስጂድ አሽሹሐዳ" በሸሒድ ወንድሞቻችን ስም የሚገነባው የጠቅላይ ም/ቤቱ ፕሬዝዳንት ቃል በገቡት መ...
05/01/2024

በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አዲሱ ተቅዋ መስጂድ መነሻ ኘላን

ይህ አዲሱ ተቅዋ መስጂድ ነው።"መስጂድ አሽሹሐዳ" በሸሒድ ወንድሞቻችን ስም የሚገነባው የጠቅላይ ም/ቤቱ ፕሬዝዳንት ቃል በገቡት መሰረት ሸገር ሲቲ ላይ ይሆናል።

ገንዘቡን ጉልብቱን ግዜው ለተቋም እየሰዋ ነው። ዛሬም ለአዲሱ መስጅድ 500,000 ብር ሰጥቷል። ሱፍያን ኡስማን
05/01/2024

ገንዘቡን ጉልብቱን ግዜው ለተቋም እየሰዋ ነው። ዛሬም ለአዲሱ መስጅድ 500,000 ብር ሰጥቷል። ሱፍያን ኡስማን

ዒድ አል-አድሀ ወይ ዒድ አል-ፊጥር አይደለም።የዛሬ ጁምዓ ሰላት ነው ቤተል አዲስ ሰለሚገባን ባገኘነው መስጂደ አ-ሹሀዳእ ቅጥር ግቢ ውስጥ ነው።ሰደቃና የገቢ ማሰባሰቢያ
05/01/2024

ዒድ አል-አድሀ ወይ ዒድ አል-ፊጥር አይደለም።

የዛሬ ጁምዓ ሰላት ነው ቤተል አዲስ ሰለሚገባን ባገኘነው መስጂደ አ-ሹሀዳእ ቅጥር ግቢ ውስጥ ነው።

ሰደቃና የገቢ ማሰባሰቢያ

የአዲስ አበባ መጅሊስ ከፍተኛ አመራሮች ዛሬ ከዙሁር ሶላት በኃላ በቤተል ሹሃዳ መስጂድ በመገኘት መግለጫ ይሰጣሉ ።ህዝበ ሙስሊሙ የዙሁርን ሶላት በሹሃዳ መስጂድ እንዲሰግድ ጥሪ ተላልፎዋል ።
03/01/2024

የአዲስ አበባ መጅሊስ ከፍተኛ አመራሮች ዛሬ ከዙሁር ሶላት በኃላ በቤተል ሹሃዳ መስጂድ በመገኘት መግለጫ ይሰጣሉ ።

ህዝበ ሙስሊሙ የዙሁርን ሶላት በሹሃዳ መስጂድ እንዲሰግድ ጥሪ ተላልፎዋል ።

03/01/2024

ሰበሀልኸይር
ስራው ዛሬም ይቀጥላል። የቻለ ሰው ብሎኬትም ሌላ የግንባታ ማቴሪያል ይዞ ይገኝ ያልቻለ ጉልበቱን ይነይት። ጁመዓ ግን እዚያው ነን ለሰደቃው ተዘጋጁ..ቤተል

አስቸኻይ ጥሪ ደማቸው በአንዋር መስጂድ ውስጥ ፈሶ ሸሂድ በሆኑ ወንድሞች ስም በተሰየመው ሹሃዳ መስጂድ ዛሬ ከዙሁር ሶላት ጀምሮ  ሙስሊሙ ማህበረሰብ እንዲገኝ አስቸኻይ ጥሪ ተላልፎዋል ።መስጂ...
02/01/2024

አስቸኻይ ጥሪ

ደማቸው በአንዋር መስጂድ ውስጥ ፈሶ ሸሂድ በሆኑ ወንድሞች ስም በተሰየመው ሹሃዳ መስጂድ ዛሬ ከዙሁር ሶላት ጀምሮ ሙስሊሙ ማህበረሰብ እንዲገኝ አስቸኻይ ጥሪ ተላልፎዋል ።

መስጂዱ ሹሃዳ ከፍተኛ የሆነ የሰው ሃይል የሚፈልግ ስራ አለ አሁን ላይ በርካቶች ቦታው ላይ ቢኖሩም ከቦታው ስፋት የተነሳ ከፍተኛ የሆነ የሰው ሃይል ስለሚፈልግ ዛሬ ከዙሁር ሶላት ጀምሮ ቦታው ላይ በመገኘት በሸሂዶች መስጂድ ላይ የማይረሳ አሻራዎትን ያኑሩ ።

{{እነዚያን በአላህ መንገድ የተገደሉትን ሙታን አድርገህ አትገምታቸው፡፡ በእርግጥ እነርሱ እጌታቸው ዘንድ ሕያዋን ናቸው፤ ይመገባሉ፡፡}}

የሰው ሀይል ያስፈልጋል  ! ለመስጂዳቸው ሲሉ ሸሂድ በሆኑ ወንድሞቻችን ስም ወደተሰየመው  ሹሀዳ መስጂድ ከአሁን ሰዐት ጀምሮ በመሄድ በጉልበት በማገዝ የሹሀዳ መስጂድ ላይ አሻራችሁን አሳርፉ ...
02/01/2024

የሰው ሀይል ያስፈልጋል !

ለመስጂዳቸው ሲሉ ሸሂድ በሆኑ ወንድሞቻችን ስም ወደተሰየመው ሹሀዳ መስጂድ ከአሁን ሰዐት ጀምሮ በመሄድ በጉልበት በማገዝ የሹሀዳ መስጂድ ላይ አሻራችሁን አሳርፉ ።

ይህ መስጁዱ ሹሃዳ ቁጥር 1 ነው ! በተሰውት ሸሂዶች ቁጥር ልክ በሌሎች አከባቢዎችም ሸገር ሲቲን ጨምሮ መስጂድ እንገነባላቸዋለን ።

መስጂድ ሹሃዳ ከቤተል ወደ አየር ጤና በሚወስደው መንገድ ላይ በግ ተራ አከባቢ ይገኛል ከአሁን ሰዐት ጀምሮ ወደ ቦታው በመሄድ የአቅማችን ስራ እናግዝ ።

ነቢ ሰዐወ አሉ፦የአደም ልጅ ሞት በቀረበው ግዜ አላህ 5 መላዕክትን ይልክበታል። ነፍሱ በመውጣት ላይ ሳለች የመጀመርያው መልዓክ ይቀርበው'ና‹‹የአደም ልጅ ሆይ! ያ ፈርጣማ ጡንቻህ የት ገባ?...
30/12/2023

ነቢ ሰዐወ አሉ፦
የአደም ልጅ ሞት በቀረበው ግዜ አላህ 5 መላዕክትን ይልክበታል።

ነፍሱ በመውጣት ላይ ሳለች የመጀመርያው መልዓክ ይቀርበው'ና‹‹የአደም ልጅ ሆይ! ያ ፈርጣማ ጡንቻህ የት ገባ? ዛሬ ምን አደከመው? ያ ርቱዕ አንደበትህ የት ግባ፤ ዛሬ ስለምን ተለጎመ? ዘመድ አዝማዶች አልነበሩህ! ስለምን ጭርታ ሰፈነብህ?›› ሲል ይጣራል።

የአደም ልጅ ነፍሱ ወጥታ በተከፈነ ግዜም ሁለተኛው መልዓክ ይመጣ'ና፦‹‹የአደም ልጅ ሆይ! ከሀብትህ ለድህነቴ እለት ብለህ ያጠራቀምከው የት ገባ? ለመጠለያ ብለህ የገነባኸው ህንፃህ የት ሄደ? ከወዳጅ አዝማድ የያዝካቸው ጓደኞችህ የት ጠፉ?›› ሲል ይጣራው'ና ትቶት ይሄዳል።

የአደምን ልጅ ጀናዛ ሰዎች ተሸክመው ወደ ቀብሩ ሲሄዱ ሶስተኛው መልዐክ ይመጣ'ና ይጣራል፦‹‹የአደም ልጅ ሆይ! ዛሬ... ተጉዘህ የማታውቀውን አይነት ሩቅ ጉዙ ትጓዛለህ፤ ዛሬ...ጎብኝተህ እማታውቃቸውን አይነት ሰዎች ትጎበኛቸዋለህ፤ ዛሬ... ገብተህ በማታውቀው ጠባብ መግቢያ ውስጥ ትገባለህ። የአላህ ውዴታ ከተሳካልህ ምንኛ ታደልክ፤ በአላህ ጥላቻ ከተመለስክ ዋ! መጥፋትህ!››

ሟች ከቀብሩ ገብቶ በተጋደመ ግዜ አራተኛው መልዓክ ይመጣ'ና፦‹‹የአደም ልጅ ሆይ! ትናንት ከምድር በላይ ሆነህ ስትራመድ ነበር፤ ዛሬ ከስሯ ገብተህ ተኝተኻል። ትናንት ከላይዋ ሆነህ ስትስቅ ነበር፤ ዛሬ ከስሯ ሁነህ ታለቅሳለህ። ትናንት ከላይዋ ሆነህ ስታምፅ ነበር፤ ዛሬ ከስሯ ሆነህ ትፀፀታለህ።›› ሲል ይጣራል።

ቀባሪ ቀብሮ ሲመለስ የመጨረሻው መልዓክ ይመጣ'ና፦‹‹የአደም ልጅ ሆይ! ቀበሩህ እኮ፤ ትተውህም ሄዱ። አብረውህ ቢቀመጡም አይጠቅሙህም። ንብረት ሰበሰብክ፤ ግና ለሌላ ሰው ትተኸው ሄድክ። ዛሬማ! ወይ ከላዕላይቷ ጀነት ትከትማለህ፤ አልያም ከነዲዷ ጀሀነም ትነጉዳለህ›› ሲል ተጣርቶ ይሰናበተዋል።

Sefwan Sheik Ahmedin

ነጻ ህክምናነጻ የከንፈርና ላንቃ መሰንጠቅ ህክምና በወራቤ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል••••••••••••••••••••••••••••••ወራቤ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል መቀመጫ...
03/12/2023

ነጻ ህክምና

ነጻ የከንፈርና ላንቃ መሰንጠቅ ህክምና በወራቤ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል
••••••••••••••••••••••••••••••

ወራቤ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል መቀመጫውን አሜሪካን ሀገር ካደረገው ስማይል ትሬይን/Smile Train/ ከተሰኘ ግብረ - ሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር የከንፈር መሰንጠቅ ችግር ላለባቸ ህጻናት በነጻ ህክምና መስጠት ጀምሯል።

የከንፈር መሰንጠቅ ይህ ነው የተባለ ትክክለኛ ምክንያቱ አይታወቅም ። ይሁን እንጂ በህክምና ችግሩ ሙሉ በሙሉ እንደሚቀረፍ ከወራቤ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የፕላስቲክ ቀዶ ህክምና ክፍል ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ቀደም ሲል ወራቤ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የከንፈር መሰንጠቅ ላለባቸው ህጻናት አገልግሎቱን በክፍያና በዱቤ ሲሰጥ የቆየ ሲሆን በአሁን ሰዓት በተገኘው ድጋፍ መሠረት አገልግሎቱን በነጻ እየሰጠ ይገኛል።

በመሆኑም የከንፈር መሰንጠቅ ያለባቸው ህጻናትን ወደ ወራቤ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በማምጣትና በነጻ በማሳከም ልጆችን ከአካል ጉዳትና ከስነ-ልቦና ጫና ይከላከሉ።

20/11/2023

መርካቶ እገታ ተጀምሯል።
ተጠንቀቁ‼
Inbox

የሞባይል ባንኪንግ መጭበርበር የልጅቱን ሕይወት ቀጠፈ....😭ይህች መቅደስ የተባለች እህታችን  ወልቂጤ ሶሬሳ ህንፃ ስር ቸሩ የሚባል ሞባይል ቤት ተቀጥራ ትሰራ ነበር ። ሰሞኑን ሁለት አጭበር...
14/11/2023

የሞባይል ባንኪንግ መጭበርበር የልጅቱን ሕይወት ቀጠፈ....😭

ይህች መቅደስ የተባለች እህታችን ወልቂጤ ሶሬሳ ህንፃ ስር ቸሩ የሚባል ሞባይል ቤት ተቀጥራ ትሰራ ነበር ።

ሰሞኑን ሁለት አጭበርባሪ ሌቦች ከምትሸጥበት ሞባይል ቤት ገብተው አራት ስልክ በ ስልሳ ዘጠኝ ሺህ ብር ለመግዛት ይስማሙና ብሩን በአካውንት እንላክልሽ ብለው የአካውንት ቁጥሯን ይቀበላሉ።

በወሬ አደናብረዋትም ስልኳን ይቀበሉና የራሳቸውን ስልክ cbe ብለው save ያደርጉታል
በመቀጠል ስልኳን ይመልሱላት እና cbe ብለው save ባደረጉት ቁጥር ንግድ ባንክ ገንዘብ ሲገባ ሚልከውን ሜሴጅ edit ያደርጉና
ስልሳ ዘጠኝ ሺህ ብር እንደገባ አድርገው የፃፉት ሜሴጅ ይልኩላታል እሷም cbe ተብሎ save በተደረገው ስልክ ስልሳ ዘጠኝ ሺህ ብር እንደገባላት ተረዳች።

ሰዎቹንም ስልኩን ሰጥታ ሸኘቻቸው።

ነገር ግን ባንክ ሄዳ ስታጣራ ገንዘቡ እንዳልገባላት አረጋገጠች። ሜሴጁን ስታየው cbe ተብሎ save ተደረገ እንጂ ትክክለኛ cbe ሜሴጅ አልነበረም

ያኔ እንደተጭበረበረች የገባት ሰራተኛ ገንዘቡን መክፈል አልችልም ቤተሰቤም አይችልም በሚል የልጅነት ሀሳብ ራሷን አጠፋች።
በ 02/03/16 ቀብሯ በወልቂጤ ተፈፀም።

ህብረተሰቡም በኤሌክትሮኒክሰ ግብይት በሚፈፅሙበት ወቅት ጥንቃቄ ሊያደርግ ይገባል።
ወ/ሪት መቅደስ በደረጃ አራት በኮንስትራክሽን ከተመረቀች ሁለት አመት ያለፋት ቢሆንም በተማረችው የሙያ መስክ ስራ አላገኘችም ነበር።
ነፍስ ይማር😭

Via HuzHuzeyfa M Kasim

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Bilal Tube ቢላል ቲዩብ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Share