ሮሃ ሚዲያ / Roha Media

ሮሃ ሚዲያ / Roha Media #ፈጣን የመረጃ ምንጭ!
════════
https://www.youtube.com/

B.Dortmund 0 -2  R.Madrid
02/06/2024

B.Dortmund 0 -2 R.Madrid

31/05/2024




 #ይግምቱ....
27/05/2024

#ይግምቱ....

አምባሳደር ስለሺ በቀለ (ዶ/ር) ከአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደርነት በአስቸኳይ እንዲነሱ ዐቢይ አህመድ ውሳኔ አሳለፉየአገዛዙ መሪ ዐቢይ አህመድ ስልጣን ከያዙ ጀምሮ በተለያዩ ኃላፊነቶች ላይ ...
24/05/2024

አምባሳደር ስለሺ በቀለ (ዶ/ር) ከአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደርነት በአስቸኳይ እንዲነሱ ዐቢይ አህመድ ውሳኔ አሳለፉ

የአገዛዙ መሪ ዐቢይ አህመድ ስልጣን ከያዙ ጀምሮ በተለያዩ ኃላፊነቶች ላይ ባለስልጣናትን እንዳሻቸውና ውዝግብ በሚፈጥር መልኩ መሾምና መሻሩን ቀጥለውበታል።
በአስፈፃሚ ደረጃ እነብርሃኑ ነጋና በለጠ ሞላን ሳይቀር አሽከር በማድረግ የስልጣን ጥማችሁን ስለቆረጥኩ ታዘዙኝ የሚሉት ዐቢይ አህመድ መንግስታቸውንም ሀገርንም ያገለገሉትን ደግሞ እንደ ዕቃ ተጠቅመው መወርወሩን ተያይዘውታል።
ሰውየው ሰሞኑን ደግሞ የሹም ሽር ዛራቸው ተነስቶ አነጋጋሪ የመሆን ፍላጎታቸውን ለማርካት ግብ ግብ እየፈጠሩ ይገኛሉ።
በዚህም በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው ሲሰሩ የቆዩት አምባሳደር ስለሺ በቀለ (ዶ/ር) ከኃላፊነታቸው ተነስተው በሌንጮ ባቲ ሊተኩ መሆኑን ሮሃ ከውስጥ ምንጮች አረጋግጣለች።
የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሲነሳ ስማቸው በቀዳሚነት ከሚጠቀሱ ሰዎች መካከል አንዱ የሆኑት የቀድሞው የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጅነር ስለሺ በቀለ አውላቸው በአምባሳደርነት ወደ አሜሪካ ለመሄዳቸው በፊት በዓባይ ጉዳይ ዋና ተደራዳሪ እንደነበሩም ይታወሳል።
ዛሬ ሮሃ ከውስጥ ምንጮቿ እንደሰማችው ከሆነ አምባሳደር ስለሺ ከኃላፊነት ተነስተው በሳዑዲ አረቢያ የኢትዮጵያ አምባሳደር በሆኑት ሌንጮ ባቲ ሊተኩ እንደሆነ ታውቋል።
አምባሳደር ኢንጅነር ስለሺ (ዶ/ር) ለምን ከአሜሪካ አምባሳደርነት እንደሚነሱና በቀጣይ ምን አይነት ቦታ ላይ እንደሚመደቡ ሮሃ ዝርዝር መረጃዎችን: ለጊዜው አላገኘችም።
የብልፅግናው አለቃ ዐቢይ አህመድ ዛሬ የሚኒስትር ባለስልጣናትን ቦታ የማቀያየር ሹመት መስጠታቸው የሚታወቅ ሲሆን በሚቀጠሉት ጥቂት ቀናት በርካታ ሹም ሽሮችና የስልጣን ሽግሽጎች እንደሚኖሩ ተጠቁሟል።
ዐቢይ በተለይም የሚታዘዟቸውን፣ የሚያገለግሏቸውን እንዲሁም የሚያሸረግዱላቸውን ሁሉ ይበልጥ እየናቁ አመድ አፋሽ አድርገው ማዋረዳቸውን ተያይዘውታል።
ይህ የብልፅግና ቡድን መሪ አካሄድ ለማንም እንደማይመለሱና እሺ ብሎ መታዘዝና ማገልገልም የትም እንደማያደርስ በተደጋጋሚ አረጋግጠዋል።
ዐቢይ አህመድ የለውጥ ጓድ ፊታውራሪ እያሉ ሲደልሏቸው የነበሩ እንደ ለማ መገርሳ፣ ገዱ አንዳርጋቸው፣ ደመቀ መኮንንና ሌሎች ሹመኞችን በሂደት ገዝግዘው ከጥቅም ውጭ ማድረጋቸውም ይታወቃል።

አሳዛኝ የሰባዊ መብት ጥሰት በከምባታ ዞን በዱራሜ ማረሚያ በሚገኙ የዶንጋ ብሔረሰብ ተወላጅ እስረኞች ላይ እያደረሰ ይገኛል ።በዱራሜ ማረሚያ ቤት በግፍ ለምን የዶንጋ ብሔረሰብ ጥያቄ አነሳችሁ...
10/04/2024

አሳዛኝ የሰባዊ መብት ጥሰት
በከምባታ ዞን በዱራሜ ማረሚያ በሚገኙ
የዶንጋ ብሔረሰብ ተወላጅ እስረኞች ላይ
እያደረሰ ይገኛል ።

በዱራሜ ማረሚያ ቤት በግፍ ለምን የዶንጋ
ብሔረሰብ ጥያቄ አነሳችሁ በሚል
በእስረኞች ላይ ማታ ማታ ከፍተኛ ደብደባ
እና እንግልት እያደረሰ ይገኛል ። ከእስረኞች
ባገኘነው መረጃ መሠረት በተለይ በዱራሜ
ደረቅ ጣቢያ ከፍተኛ ደብደባ በፖሊስ በኩል
ደርሶባቸዋል ።

ስለዚህ በወገኖቻችን ላይ ከፍተኛ የሰባዊ
መብት ጥሰት እያደረሰ ስለሆነ

የኢትዮጵያ ሰባዊ መብት ኮሚሽን እሰከ
ቦታው ሄዶ እንድመለከት እንጠይቃለን።

ፍትህ ለዶንጋ

ሚያዝያ 2/2016 ዓ.ም

ሼር ይደረግ

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ከፍተኛ የስራ ኃላፊ የሆኑት አቶ ባቴ ኡርጌሳ ተገደሉ! የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ከፍተኛ የስራ ኃላፊ የሆኑት አቶ ባቴ ኡርጌሳ ተገደሉ። አቶ ባቴ በተወለዱበት መቂ (ዝዋ...
10/04/2024

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ከፍተኛ የስራ ኃላፊ የሆኑት አቶ ባቴ ኡርጌሳ ተገደሉ!

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ከፍተኛ የስራ ኃላፊ የሆኑት አቶ ባቴ ኡርጌሳ ተገደሉ። አቶ ባቴ በተወለዱበት መቂ (ዝዋይ) ከተማ ህይወታቸው እንዳለፈ ነው የተነገረው።

 #ዛሮ UEFA Champions League..... 10/04/24 @ 4:00 Local time #ይግምቱ  #ይሽለሙ     ....
10/04/2024

#ዛሮ UEFA Champions League.....
10/04/24 @ 4:00 Local time

#ይግምቱ
#ይሽለሙ




....

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን  ለኢድ አል ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳቹህ!
10/04/2024

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለኢድ አል ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳቹህ!

UEFA Champions League result
10/04/2024

UEFA Champions League
result

 #ዜና እረፍት የቀድሞው ድምፃዊ ከብዙ አስርት አመታት ወዲህ ደሞ ዘማሪ የሆነው አንጋፋው የኪነ-ጥበብ ሰው  ሙሉቀን መለሰ በ70 አመቱ ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል።ወደ ሙዚቃው አለም በ12 ...
09/04/2024

#ዜና እረፍት

የቀድሞው ድምፃዊ ከብዙ አስርት አመታት ወዲህ ደሞ
ዘማሪ የሆነው አንጋፋው የኪነ-ጥበብ ሰው ሙሉቀን መለሰ በ70 አመቱ ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል።ወደ ሙዚቃው አለም በ12 አመቱ እንደተቀላቀለ ቃለመጠይቆቹ ላይ ሲናገር አድምጠናል። ወደ ሀገረ አሜሪካ ካቀና 38 አመታትን አስቆጥሯል። በህመም ምክንያት ብዙ አመታትን ያሳለፈው ጋሽ ሙሉቀን ዛሬ ማረፉ ከባህርማዶ ተሰምቷል።
ላበረከትክልን ነገሮች ሁሉ እናመሰግናለን። ለወዳጅ ዘመዶቹ ለቤተሰቦቹ መፅናናትን እንመኛለን።
ነፍስህ በሰላም ትረፍ ጋሽ ሙሉቀን!

09/04/2024

በአዲስ አበባ እየተከናወነ የሚገኘው አፈሳ እና የታሰሩ ሰዎችን ለማስለቀቅ በገንዘብ የሚደረግ ድርድር

ካለፉት ሁለት ሳምንታት ወዲህ በከተማው 'ወቅታዊ' በሚል ምክንያት ከፍተኛ አፈሳ እየተፈፀመ እንደሆነ፣ በዚህም በርካታ ግለሰቦች ወደ እስር ቤቶች እየተጋዙ እንደሆነ የሚደርሱኝ መረጃዎች ያመለክታሉ።

እስሩ በብዛት የአማራ ተወላጆች ላይ ያነጣጠረ እንደሆነ፣ ከሬስቶራንት፣ መዝናኛ ስፍራዎች እና የስራ ቦታ ጭምር አፈሳው እየተፈፀመ እንደሆነ ምንጮች የጠቆሙኝ ሲሆን ጉዳዩ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ጋር ደርሶ ምርመራ እየተደረገበት እንደሆነም ታውቋል።

አፈሳውን በአብዛኛው የሚፈፅሙት ሲቪል የለበሱ 'ክትትል' የሚባሉ አካላት ሲሆን ለምሳሌ 22 አካባቢ አደይ አበባ ስታዲየም ፊት ለፊት የሚገኘው ፖሊስ ጣብያ አይነት ማቆያዎች ለዚህ ተግባር እየዋሉ እንደሆኑ እና ከሞሉ ደግሞ ኮንቴይነሮች ውስጥ እንዲታሰሩ እየተደረገ እንደሆነ ታውቋል።

ታዲያ ይህን እስር ለየት የሚያደርገው አንዳንድ የፀጥታ አካላት በግልፅ የገንዘብ ድርድር በማድረግ ታሳሪዎችን በገንዘብ መልቀቃቸው ነው፣ ከ30,000 ብር እስከ 80,000 ብር ያውም በግልፅ በባንክ ትራንስፈር እንደሚደረግ ታውቋል።

በርካታ ምስጉን የፀጥታ አካል እንዳሉ ብናውቅም እንዲህ አይነት በጫካ ከሚደረግ እገታ ያልተናነሰ ወንጀል መሀል ከተማ እንደሚፈፀም መንግስት መረጃው ይኖረው ይሆን?
Via:- Elias Meseret

 #ዛሮ UEFA Champions League..... 09/04/24 @ 4:00 Local time #ይግምቱ  #ይሽለሙ     ....
09/04/2024

#ዛሮ UEFA Champions League.....
09/04/24 @ 4:00 Local time

#ይግምቱ
#ይሽለሙ




....

«ሌላ ትርጉም እንዳይሰጠዉ ብለን በሆደ ሰፊነት ብንታገስም ሙስሊሙን ማህበረሰብ መከራ ዉስጥ ጨምሮታል» የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት በአማራ ክልል ባለፉት 8 ወራትና መጋ...
08/04/2024

«ሌላ ትርጉም እንዳይሰጠዉ ብለን በሆደ ሰፊነት ብንታገስም ሙስሊሙን ማህበረሰብ መከራ ዉስጥ ጨምሮታል» የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት

በአማራ ክልል ባለፉት 8 ወራትና መጋቢት 29/2016 በባህር ዳር ከተማ ሙስሊም ወንድሞች ላይ በተፈጠሩ ግድያ ላይ የተሰጠ መግለጫ፡-

እንደሚታወቀዉ ሀገራችን ኢትዮጵያ የብዝህ ብሄር እና እምነት መገኛ ነች፡፡ በረጅሙ የሀገር ግንባታ ሂደት የተለያዩ ብሄሮችና እምነቶች በመደጋገፍ የጋራ ጠላት በገጠማቸዉ ጊዜ አብረዉ በመቆምና መስዋት በመክፈል በጋራ ደማቸዉን አፍሰዋል፣ አጥንታቸዉን ክስክሰዉ ሀገራችንን አስረክበዉናል፡፡ የተለያዩ እምነቶች በሰላምና በችግር ጊዜ አብረዉ በመቶም ለሀገር መጽናት ዉድ ዋጋ ከፍለዉ የጋራ የሆነችን ሀገራችንን አስረክበዉናል፡፡ የዚህ ታሪክ ወራሽ የሆን ልጆቻቸዉ አባቶቻችን በከፈሉት ዋጋ ኩራት ይሰማናል፡፡

ነገር ግን ባለፋት ስምንት ወራት በአማራ ክልል መንግስትና በታጣቂ ቡድኖች መካከል የተፈጠረዉ ግጭት ህዝባችንን የከፋ ዋጋ እያስከፈለዉ ስለሆነ በዋናነት በሙስሊሞች ላይ እየደረሰ ያለዉ ግፍ፣ መፈናቀል፣ ዘረፋ፣ መታገትና መገደል ከጊዜ ጊዜ እየተባባሰ በመሄድ ላይ ነዉ፡፡ ሌላ ትርጉም እንዳይሰጠዉ ብለን በሆደ ሰፊነት ብንታገስም ጉዳዩ ሀይል ከቀን ወደ ቀን ንጹሀን ዜጎችን በማገትና በመሰወር እንዲሁም በመግደል የክልሉን ህዝብ በተለይ ሙስሊሙን ማህበረሰብ መከራ ዉስጥ ጨምሮታል፡፡

ለማሳያ ያህል-
1. በቀን በ29/07/16 በባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 14 የመቅሪብ ሶላት ሰግደዉ ወደ ቤታቸዉ በሚሄዱ አማኞች ላይ ማንነታቸዉ ያልታወቁ የታጠቁ ኃይሎች 4 (አራት) የአንድ ቤተሰብ አባላትንና 1 (አንድ) ጎረቤታቸዉን በመግደል ተሰዉረዋል፡፡

2. 28/07/16 በጎንደር ከተማ ማክሰኝት አካባቢ 4 (አራት) ሙስሊሞች ተገድለዋል፡፡

3. 29/07/16 በሞጣ ከተማ አንድን ወጣት ካገቱ በኋላ ቤተሰቦቹን በማስፈራራት ሶስት መቶ ሺ ተቀብለዉ ታጋቹን በአሰቃቂ ሁኔታ ገድለዉ ጥለዉታል፡፡

4. በቢቸና ከተማ በቀን 26/07/16 ንጹሀን ባልና ሚስት ለምን ለመንግስት ግብር ከፈላችሁ ተብለዉ በግፍ ተገድለዋል፡፡

በአጠቃላይ በክልሉ በተለያዩ ቦታዎች ባለፉት ስምንት ወራት ከ80 (ሰማኒያ) በላይ ሙስሊሞች ሲገደሉ፤ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊሞች ተፈናቅለዋል፤ 47 ሰዎች ታግተዋል፣ ከ260 በላይ ዘረፋ ተፈጽሟል፡፡ ስለሆነም የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ይህን ዘረፋ! ብዙ ስቃይ እና እንግልት፤ መገደልና መፈናቀል በጽኑ እናወግዛለን፡፡

ከዚህም በላይ ይህን እኩይ ተግባር ለማስቆም መንግስት፣ ሰላማዊዉ የክልሉ ህዝባችን፤ የሌላ እምነት ተከታይ ወገኖቻችን የኃይማኖት አባቶች እንዲሁም ጉዳዩ የሚመለከታችሁ አካላት በሙሉ የበኩላችሁን እንድትወጡ ወገናዊ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

ይህ ሰላማዊ ዜጎች ላይ ያነጣጠረ ግፍና ግድያ ለዘመናት አብሮና ህብረት ፈጥሮ የኖረዉን ህዝባችንን አብሮነት ለማናጋት የታሰበ ስለሆነ በጋራ እንድንታገለዉ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡ በእኛ እምነት ይህን የሚያደርገዉ ገዳይ ዘራፊ ቡድን የማንንም እምነትና ብሄር የማይወክል መሆኑን እናምናለን፡፡

አሏህ አክብር!
የአማራ ክልል እስ/ጉ/ከ/ም/ቤት
መጋቢት 30/2016
ባህር ዳር

በቲክቶክ ዝነኛ የሆነው ኢትዮጵያዊው the pingo pikago ማነው? አስገራሚ ታሪኩ!በቲክቶክ "ከአበደው ጋር ማበድ" በማለት ትሬንድ የሆነው the pingo pikago የተሰኘው የቲክቶክ ...
08/04/2024

በቲክቶክ ዝነኛ የሆነው ኢትዮጵያዊው the pingo pikago ማነው? አስገራሚ ታሪኩ!

በቲክቶክ "ከአበደው ጋር ማበድ" በማለት ትሬንድ የሆነው the pingo pikago የተሰኘው የቲክቶክ አካውን ባለቤት ማነው የሚለውን አሳዛኝ ታሪክ በፋስት መረጃ እንደሚከተለው ይቀርባል።

መሐመድ ዑስማን ይባላል፣ ተወልዶ ያደገው በምስራቅ ሐረርጌ በዴሳ መሆኑን ፋስት መረጃ ከመሐመድ ሰምቷል። በ1992 የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትን የተቀላቀለው መሐመድ በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት መሳተፉን ይገልፃል። ከጦርነቱ በኋላ የነበረበት ክፍለ ጦር ወደ ድሬዳዋ ስትመደብ መሐመድ በመጥፋት ወደ ጂቡቲ በመጥፋት ከዛም ኤርትራ በመሄድ ኦነግን መቀላቀሉን ይናገራል። ህይወቴንም አደጋ ላይ የጣልኩት በዚህ ወቅት ነው ይላል መሐመድ።

በፈረንጆች አቆጣጠር ከ2002 እስከ 2014 በኤርትራ በረሃ መቆየቱን ይናገራል፣ በ2014 ፈጣሪ ረድቶኝ ከኦነግ እጅ ወጥቼ ሱዳን ገባው የሚለው መሐመድ እስከ 2018 በሱዳን መቆየቱን ይናገራል።

ከሱዳን ወደ ሊቢያ በመግባት ትንሽ ገንዘብ ካገኘው በኋላ አንድ ደላላ አግኝቼ 700 ዶላር ከፍዬ 15 ሰው ሆነን በትንሽዬ ጀልባ በሜዲትራንያን ባህር ላይ ጉዞ ጀመርን… እንዳሰብነው አልሆነም መንገድ ጠፋብን 23 ሰዓታት ተጉዘን ጀልባው ነዳጅ ጨረሰች።

ጀልባዋ ጉዞ አቁማ ተንሳፋ ባህር ላይ ቀረች ስደተኞቹ ተስፋ ቆረጡ ማልቀስ ጀመሩ ሽንታቸውን መጠጣት፣ የባህር ውኃ መጠጣት ጀመሩ ይላል መሐመድ በወቅቱ የነበረውን አስጨናቂ ጊዜ ሲያስረዳ፣ እኔ ከሻዕቢያ የተሰጠኝ ስልጠና ስለነበር የባህር ውኃ እና ሽንት አልተጠቀምኩም ብሏል።

ልክ 11ኛ ቀን ሲሞላን አንዳንዱ መሞት ጀመረ ሌላው ወደ ባህር እየተወረወረ ራሱን አጠፋ፣ ሶስት ብቻ ቀረን ይላል መሐመድ። (እዚህ ጋር ህይወታቸውን ለማትረፍ የበሉት ዘግናኝ ስለሆነ ዘለነዋል) ከበላን በኋላ አብረውኝ የቀሩት ሁለቱ ሶማሌዎች ከሞት አልተረፉም እነሱም ሞቱ እኔ ብቻ በህይወት ቀረው የሚለው መሐመድ ወደ ምሽት አከባቢ አንድ ሂሊኮፍተር ደርሳልኝ ከጀልባዋ ላይ አንስተው ወደ ማልታ ሆስፒታል ተወስዶ ለአንድ ወር ህክምና ሲያገኝ ቆይቶ ህይወቱ ሊተርፍ ችሏል።

በአሁኑ ወቅት በስደት በፈረንሳይ ሀገር መኖሪያን አድርጎ በቅርቡ በቲክቶክ በሚለቃቸው ቪዲዮች ከመቶ ሺህ በላይ በማፍራት በበርካታ ሰዎች ቀልብ ውስጥ እየገባ ይገኛል።

Via:- ፋስት መረጃ

በፖርቹጋል የታየው የፀሀይ ግርዶች ነው። የተፈጥሮ ተአምር 👌
08/04/2024

በፖርቹጋል የታየው የፀሀይ ግርዶች ነው። የተፈጥሮ ተአምር 👌

የዒድ-አልፈጥር በዓል ረቡዕ ይከበራል*********ዛሬ በሳዑዲ ዓረቢያ አካባቢ ጨረቃ ባለመታየቷ 1445ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል ረቡዕ ሚያዚያ 2 ቀን 2016 እንደሚውል ተረጋግጧል።መጋቢት ...
08/04/2024

የዒድ-አልፈጥር በዓል ረቡዕ ይከበራል
*********

ዛሬ በሳዑዲ ዓረቢያ አካባቢ ጨረቃ ባለመታየቷ 1445ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል ረቡዕ ሚያዚያ 2 ቀን 2016 እንደሚውል ተረጋግጧል።

መጋቢት 30 ቀን 2016 ዓ.ም

07/04/2024

ዉድ የ ሮሃ ሚዲያ #ቤተሰቦቻችን እንዴትናቹ ፔጃችን የበለጠ ተደራሽ እንድሆን #ላይክ እና #ሼር እንድታርጉን ሰንል በአክብሮት አንገልፃልን።
ኢትዮጵያ ለዘላለም ተኑር።

📊 በዚህ የፕሪምየር ሊግ የውድድር ዘመን ሊቨርፑል በማንቸስተር ዩናይትድ ላይ ባጠቃላይ 62 ኳሶችን ጎል ላይ ቢሞክርም ቀያይ ሰይጣኖቹን ማሸነፍ አልቻለም! (34 ኳሶችን በአንፊልድ እና 28 ...
07/04/2024

📊 በዚህ የፕሪምየር ሊግ የውድድር ዘመን ሊቨርፑል በማንቸስተር ዩናይትድ ላይ ባጠቃላይ 62 ኳሶችን ጎል ላይ ቢሞክርም ቀያይ ሰይጣኖቹን ማሸነፍ አልቻለም! (34 ኳሶችን በአንፊልድ እና 28 ኳሶችን በኦልድ ትራፎርድ ወደጎል ሞክሯል).

Manchester United  vs Liverpool FC 🔥    | ሦስቱም የፕሪምየር ሊጉ ተፎካካሪዎች ከሜዳቸው በሚወጡበት የሳምንት መጨረሻ ማንቸስተር ሲቲም ሆነ አርሰናል አሸንፈዋል። የደር...
07/04/2024

Manchester United vs Liverpool FC 🔥

| ሦስቱም የፕሪምየር ሊጉ ተፎካካሪዎች ከሜዳቸው በሚወጡበት የሳምንት መጨረሻ ማንቸስተር ሲቲም ሆነ አርሰናል አሸንፈዋል።

የደርቢው ስሜት ሊቨርፑልን በኦልድ ትራፎርድ ነጥብ ያስጥለው ይሆን?

ኦልድ ትራፎርድ ምንጊዜም ቢሆን ለሊቨርፑል አይተኛም ይባላል።

ስለዛሬው የዩናይትድና ሊቨርፑል ጨዋታስ ምን ትገምታላችሁ?

It is Match Day.

Manchester United vs Liverpool

vs 🔥

Drop your predictions.
It is Match Day.

Manchester United vs Liverpool

vs 🔥

Drop your predictions.

06/04/2024

የሸዋና የወሎው ትንቅንቅ !

በሸዋና በወሎ ግዛቶች ከባድ ትንቅንቅ እየተካሄደ መሆኑ ተሰማ።
በአማራ ክልል ከወሎ እስከ ሸዋ ባሉ አካባቢዎች ፋኖ የአገዛዙን ሃይል በደፈጣ ጥቃት መውጪያ መግቢያ እያሳጣ መሆኑ ታውቋል፡፡ በአንጻሩ የብልጽግና ጦር በፋኖ የደረሰበትን ሽንፈት ለማካካስ ሲል በንጹሃን ላይ ጭፍጨፋ እየፈጸመ ነው፡፡
በዓማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ በከሰም ክፍለጦር በሃይለማርያም ማሞ ብርጌድ እና በአገዛዙ ጠባቂ ሰራዊት መካከል ከትናንት በስቲያ ከባድ ጦርነት ተካሂዷል፡፡

ዛሬ የሚደርጉ የኢንጊልዝ ፕርምር ልግ ጫዎታዎች።
06/04/2024

ዛሬ የሚደርጉ የኢንጊልዝ ፕርምር ልግ ጫዎታዎች።

ዐቃቤ ሕግ የወንጀል ሕጉን እና የፀረ ሽብር አዋጅን ጠቅሶ የመሠረተው የክስ የተከፈተው የአማራ ክልል ምክር ቤት አባል በሆኑት በአቶ ዮሐንስ ቧያለው ስም ነው።ከ52ቱ ተከሳሾች መካከል 14ቱ ...
05/04/2024

ዐቃቤ ሕግ የወንጀል ሕጉን እና የፀረ ሽብር አዋጅን ጠቅሶ የመሠረተው የክስ የተከፈተው የአማራ ክልል ምክር ቤት አባል በሆኑት በአቶ ዮሐንስ ቧያለው ስም ነው።
ከ52ቱ ተከሳሾች መካከል 14ቱ ባለፈው ሳምንት በነበረው የችሎት ውሎ ፍርድ ቤት ተገኝተው ክሳቸውን ተቀብለዋል። ቀሪ ሰላሳ ስምንቱ ተከሳሾች ፍርድ ቤት አለመቅረባቸውን ከተከሳሽ ጠበቆች አንዱ የሆኑት አቶ ሄኖክ አክሊሉ ተናግረዋል።
ምንጭ:- ቢቢሲ አማሪኛ

🚨🇳🇬 ሰሞኑን በቱርክ ሊግ ፊነርባቸ ከ ትራብዞንስፖር  ጋር በነበራቸው ጨዋታ ላይ ባለሜዳዎቹ  የትራብዞንስፖር ደጋፊዎች ወደ ሜዳ በመግባት የፊነርባቸ ተጫዋቾችን ለመደብደብ ሙከራ አድርገው ነ...
21/03/2024

🚨🇳🇬 ሰሞኑን በቱርክ ሊግ ፊነርባቸ ከ ትራብዞንስፖር ጋር በነበራቸው ጨዋታ ላይ ባለሜዳዎቹ የትራብዞንስፖር ደጋፊዎች ወደ ሜዳ በመግባት የፊነርባቸ ተጫዋቾችን ለመደብደብ ሙከራ አድርገው ነበር።ይሁንና የፊነርባቸው ተጫዋች የሆነው ናይጀሪያዊው ኦሳይ ሳሙኤል ሊደበድቡት የመጡትን ደጋፊዎች የአፅፋ ምላሽ በመስጠት ቅጥቅጥ አድርጓቸዋል።ይህም ምስል በማህበራዊ ሚዲያ በስፋት እየታየ ይገኛል።

የፊነርባቸ ደጋፊዎችም ለዚህ ጀግንነቱ ለናይጀሪያዊው ተጫዋች ኦሳይ ሳሙኤል በኢስታንቡል ከተማ ትልቅ ባነር በመስቀል አወድሰውታል።

ሲዲ ስፖርት/CD Sport

በትግራይ ፤ የወንድ የዘር ፈሳሽ (ስፐርም) ለሚለግሱ ሰዎች 10ሺ ብር ስጦታ ይሰጣል ተባለ'አዶ' በሚል ስም እሚታወቅ አንድ የግል የህክምና ማዕከል በተፈጥሮአዊ መንገድ ፅንስ ለመቋጠር ላልቻ...
21/03/2024

በትግራይ ፤ የወንድ የዘር ፈሳሽ (ስፐርም) ለሚለግሱ ሰዎች 10ሺ ብር ስጦታ ይሰጣል ተባለ

'አዶ' በሚል ስም እሚታወቅ አንድ የግል የህክምና ማዕከል በተፈጥሮአዊ መንገድ ፅንስ ለመቋጠር ላልቻሉት ልጅ እእዲኖራቸው ለማድረግ እየሰራሁት ነው ባለው ስራ ሴት እንስቶች 'እንቁላል' ወንዶች ደግሞ 'የዘር ፍሬ (ስፐርም) እንዲለግሱ ጥሪውን አቅርቧል።

በትግራይ ክልል መቀለ ከተማ መቀመጫውን ያደረገው 'አዶ' የእናቶች፣ ሕጻናት እና የነቃ ሕይወት ሕክምና ማዕከል ይህንን ሕክምና ለመስጠት ዝግጅት የጀመረው ከትግራይ ጦርነት በፊት እንደሆነና ህክምናውን ለመጀመር የተደረገው ጥረት በጦርነቱ ምክንያት ቢቋረጥም ጦርነቱ ሲጠናቀቅ ግን ሂደቱ መቀጠሉን ይገለፃል።

ማዕከሉ በአሁኑ ሰዓት ታድያ ለስራው አስፈላጊ የሆኑ ቅድመ ዝግጅቶች በመከወን ስፐርም እና እንቁላል ለመለገስ ፈቃደኛ የሆኑ ሰዎችን እየጠበቀ ነውም መባሉን ዳጉ ጆርናል ታዝቧል። የድርጅቱ ባለቤት የሆኑት ዶ/ር ሳምሶን ሙልጌታ እንዳሉት ከሆነም ለጋሾችን እየጠበቅን ነው ነገር ግን ሁሉም ሰው የወንድ የዘር ፍሬ ወይም እንቁላል መለገስ አይችልም። ከሁለቱም ፆታዎች ፈቃድ በተጨማሪ የብቃት መስፈርቶች አሉ ብለዋል።

የወንድ ዘር ለጋሾች የዘር ፍሬያቸው መጠን ከ 1.5 ሚ/ሊ በላይ መሆን አለበት፣በአንድ ሚ/ሊ ስፐርም ውስጥ ከ15 ሚሊዮን በላይ የወንድ የዘር ህዋስ (s***m cells) መኖር አለበት በተጨማሪም ለጋሾች ለኤችአይቪ፣ ለሄፐታይተስ ቫይረስ እና ሌሎች ተላላፊ በሽታዎች ምርመራ ማድረግ አለባቸውም ብለዋል።

እንቁላል ለሚለግሱ ሴቶች የእድሜ ገደብ እንዳለና እንቁላል ለመለገስ ብቁ የሆኑ ሴቶች በ 20 እና 30 አመት መካከል ናቸው በተጨማሪም ሴት ለጋሾች ቀደም ብለው የወለዱ መሆን አለባቸው ይላሉ ዶ/ር ሳምሶን። ይህ መስፈርት የተቀመጠው ለምን እንደሆነ ሲገልጹም “[የወለዱ ሴቶች] እንቁላሎቻቸው ተፈትነዋል ብለዋል።

የሕክምና ማዕከሉ ባለቤት እነዚህን መስፈርቶች የሚያሟሉ ለጋሾች ከድርጅቱ ጋር በስምምነት መስራት እንደሚችሉም የገለፁ ሲሆን ከስምምነቱ አንዱ የተበረከተው የወንድ ዘር ወይም እንቁላል ለማን እንደሚሰጥ አለመገለፅ ነው ብለዋል።

በዚህ ልገሳ ለሚሳተፉ ሰዎች ማለትም ስፐርም ለሚለግሱ ወንዶች 10ሺ ብር ስጦታ እንደሚሰጥም ገልፀዋል።

ምንም እንኳ ተቋሙ በአሁኑ ሰዓት ከትግራይ ምግብና መድሓኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ፍቃድ ተሰጥቶት እየተንቀሳቀሰ ቢሆንም በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የጤና ኢንስፔክሽን፣የጤና ተቋማት እና ባለሙያዎች ስራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ እንዳልካቸው ፀዳል ይህ በትግራይ ጤና ቢር በኩል ተሰጠ ስለተባለው ፍቃድ እሚያውቁት ነገር እንደሌለ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

20/03/2024
የቤተልሔም ታፈሰ ሁለተኛ መጽሐፍ ለገበያ ሊውል ነውበአሁኑ ወቅት በስርጭት ላይ በሌለው “ኤል ቲቪ” ቴሌቪዥን ጣቢያ ታቀርባቸው በነበሩ አነጋጋሪ ቃለ መጠየቆቿ የምትታወቀው ቤተልሔም ታፈሰ፤ የ...
20/03/2024

የቤተልሔም ታፈሰ ሁለተኛ መጽሐፍ ለገበያ ሊውል ነው

በአሁኑ ወቅት በስርጭት ላይ በሌለው “ኤል ቲቪ” ቴሌቪዥን ጣቢያ ታቀርባቸው በነበሩ አነጋጋሪ ቃለ መጠየቆቿ የምትታወቀው ቤተልሔም ታፈሰ፤ የኢትዮጵያ ፖለቲከኞችን ታሪኮች የያዘ ሁለተኛ መጽሐፏን በዚህ ሳምንት መጨረሻ ለንባብ ልታበቃ ነው። “አምስት ጉዳይ” የሚል ስያሜ የተሰጠው ይህ መጽሐፍ፤ በኦሮሞ ትግል ታሪክ ስማቸው በጉልህ ከሚነሱ ሰዎች አንዱ የሆነውን የባሮ ቱምሳ “ትክክለኛ ገዳይ” ማንነት እና አማሟቱን በዝርዝር የያዘ ነው።

“አምስት ጉዳይ” ቤተልሔም “ራሳቸውን እንደ ኮከብ የሚያዩ” ስትል የምትገልጻቸውን “የኢትዮጵያ ፖለቲካ ተዋንያን” ማንነት ላይ የሚያጠነጥን መሆኑ በመጽሐፉ መግቢያ ላይ ተጠቅሷል። በአምስት ምዕራፎች ተከፋፍሎ በ220 ገጾች በተዘጋጀው በዚህ መጽሐፍ፤ እንደ ደራሲያዋ የመጀመሪያ ስራ ሁሉ የጃዋር መሐመድ፣ አንዳርጋቸው ጽጌ እና ሌንጮ ለታ ታሪኮች ተካትተውበታል።

“እኔ እና የኤልቲቪ ምስጢሮቼ” በተሰኘው መጽሐፍ ውስጥ ያልነበሩት፤ ልደቱ አያሌው እና ነአምን ዘለቀ በአዲሱ መጽሐፍ ቦታ አግኝተዋል። ስማቸው በይፋ ያልተገለጸ ባለሀብቶች እና ባለስልጣናት አጫጭር ገጠመኞችም፤ እንደ ማዋዣ ከቀረቡት የደራሲዋ የጉዞ ታሪኮች ጋር ተዳምረው የመጽሐፉ አካል ሆነዋል። የጉዞ ታሪኮች የተካተቱት “ደረቅ ፖለቲካዊ ጉዳዮችን ብቻ ከማቅረብ ይልቅ አንባቢን እያንሸራሸሩ መረጃ ለመስጠት” በማሰብ መሆኑ በመጽሐፉ መግቢያ ላይ ተጠቅሷል።

“ወደ ስምንት ዓመታት በሚጠጋው የሚዲያ ስራዬ፤ በሃገራችን ውስጥ የሚከወኑ ጉዳዮችን አይቻለሁ። በኢትዮጵያ ባሉ፤ በገዘፉ፣ በሁሉም የእምነት ቦታዎች ምን ምን እንደሚከወን ተገንዝቤአለሁ። ወደፊትም እመረምራለሁ” ስትል በመጽሐፉ መንደርደሪያ ላይ ያሰፈረችው ቤተልሔም፤ “አምስት ጉዳይን” የጻፈችው “ችግሮቻችንን ካወቅን፣ ሰላማዊ ዛሬን እንፈጥራለን በሚል ተስፋ ብቻ” መሆኑን ገልጻለች።

Via:- ethiopian insider

ፋኖኖኖ💚💛❤Today,s Best photo  ❤❤❤
20/03/2024

ፋኖኖኖ💚💛❤
Today,s Best photo
❤❤❤




















Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ሮሃ ሚዲያ / Roha Media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Share

Category