Kolfe Media Network

Kolfe Media Network Committed to deliver reliable information to our Facebook community.
ትክክለኛ እና ወቅ?

  ❤️🇪🇹 💙🇪🇹  for watch more 👆👆👆👆.                                                     ❤️ ✍️█▓▒F░O░L░L░O░W▒▓█┊┊┊▕▔╲▂▂▂╱▔▏╭...
29/08/2024

❤️🇪🇹
💙🇪🇹

for watch more 👆👆👆👆.










❤️
✍️
█▓▒F░O░L░L░O░W▒▓█
┊┊┊▕▔╲▂▂▂╱▔▏
╭━━╮╭┈╮⠀╭┈╮╭━━╮
╰╰╰┃▏╭╮⠀╭╮▕┃╯╯╯
┈┃⠀┃▏┈┈▅┈┈▕┃⠀┃
┈┃⠀┃▏┈╰┻╯┈▕┃⠀┃
┈┃⠀╰█▓▒░M░E░▒▓█

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአቶ ክርስቲያን ታደለን ያለመከሰስ መብት አነሳ ******************የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እያካሄደ በሚገኘው 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 16ኛ መደበኛ...
14/03/2024

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአቶ ክርስቲያን ታደለን ያለመከሰስ መብት አነሳ
******************
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እያካሄደ በሚገኘው 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 16ኛ መደበኛ ጉባዔው የአቶ ክርስቲያን ታደለን ያለመከሰስ መብት አንስቷል።

የፍትህ ሚንስትሩ ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ የምክር ቤት አባሉን ያለመከሰስ መብት መነሳት አስመልክቶ ለህዝብ ተወካዮች ማብራሪያ አቅርበዋል።

በማብራሪያቸውም፤ አቶ ክርስቲያን በአማራ ክልል ሕገመንግስታዊ ስርዓቱን በኃይል ለመናድ ከሚንቀሳቀሱ አካላት ጋር አብረው ሲሰሩ እንደነበር የፌዴራል ፖሊስ መርምሮ ለአቃቢ ሕግ ልኳል ብለዋል።

ምክር ቤቱም በውሳኔ ቁጥር 9/16 የአቶ ክርስቲያን ታደለን ያለመከሰስ መብት አንስቷል።

07/03/2024
29/07/2023
የአዲስ አበባ ምክር ቤቱ የከተማ አስተዳደሩን ለ2016 ዓ.ም በጀት አመት የ140.29 ቢለየን ብር በጀት አፀደቀ፤---------የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የከተማ አስተዳደሩን የ2016 ...
09/07/2023

የአዲስ አበባ ምክር ቤቱ የከተማ አስተዳደሩን ለ2016 ዓ.ም በጀት አመት የ140.29 ቢለየን ብር በጀት አፀደቀ፤
---------
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የከተማ አስተዳደሩን የ2016 ዓ/ም በጀት እቅድ መርምሮ ያፀደቀ ሲሆን
በበጀት አመቱ:-
=> ለመደበኛ በጀት ወጪዎች ብር 23,498,446,197.00
=> ለካፒታል ወጪዎች 69,336,835,072.00
=> ለመጠባበቂያ በጀት 5,300,000,000.00
---
ለክፍለ ከተሞች:-
=> መደበኛ በጀት ወጪዎች ብር 33,498,495,001.00
=> ለፒታል ወጪዎች 8,657,773,794.00 የመደበ ሲሆን፣
በጥቅሉ ለከተማ አስተዳደሩ የ140,291,550,064.00 ብር በጀት ለመደበኛ፣ ካፒታልና መጠባበቂያ በጀት አፅድቋል፡፡

የበጀት እቅዱን ለምክር ቤቱ ያቀረቡት የአዲስ አበባ ከተማ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ አብድር ቃድር ሬድዋን እንደገለፁት አጠቃላይ አሁናዊ በጀቱ ከአምና ተመሳሳይ ወቅት ሲነፃፀር የ40% እድገት እንዳለው ገልፀው የተያዘውን በጀት ለማሳካት ከታክስ ነክና ታክስ ነክ ካልሆኑ ገቢዎች፣ ማዘጋጃቤታዊ፣ መንገድ ፈንድ፣ የውጭ እርዳታ የውጭ ብድር ገቢን ታሳቢ ያደረገ መሆኑን ገልፀዋል።

ኃላፊው አክለው እንደገለፁት የገቢና ወጭ አፈፃፀምን ለማሳካት የኢኮኖሚውን እድገት ማስቀጠል፣ ምርታማነትንና ተወዳዳሪነትን ማሳደግ ከተማ አስተዳደሩ በቀጣይ በትኩረት የሚሰራበት ይሆናል ብለዋል።

የኑሮ ውድነት ድጎማ  ከ8 ቢሊዮን ብር በላይ በመመደብ ከ/አስተዳደሩ እየደጎመ ይገኛል ይህም፦=>ለህዝብ ትራንስፖርት እስከ1.9ቢሊየን፣=> ለተማሪዎች ምገባና የትምህርት ቁሳቁስ ማሟያ እስከ ...
08/07/2023

የኑሮ ውድነት ድጎማ ከ8 ቢሊዮን ብር በላይ በመመደብ ከ/አስተዳደሩ እየደጎመ ይገኛል ይህም፦
=>ለህዝብ ትራንስፖርት እስከ1.9ቢሊየን፣
=> ለተማሪዎች ምገባና የትምህርት ቁሳቁስ ማሟያ እስከ 2.5ቢሊዮን ብር፣
=> ለሰብል ምርት አቅርቦት 1.4ቢሊዮን ብር፣
=> ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ለመንግስት ሰራተኞች የመኖሪያ የቤትና የካፍቴሪያ ድጎማ 2.6ቢሊዮን፣
=> ከፍለው መታከም ለማይችሉ የከተማችን ነዋሪዎች 3ዐዐሚሊዮን እንዲሁም
=> ለሸገር ዳቦ 3ዐዐ ሚሊየን ድጎማ በማድረግ የኑሮ ጫናውን ለማቃለል እየሰራ ይገኛል

በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ከ2.1 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ። ከግብር እዳ ነጻ መንደር ለመፍጠር እየተሰራ ባለ ስራ በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ከ2.1 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ተሰበ...
17/06/2023

በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ከ2.1 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ።

ከግብር እዳ ነጻ መንደር ለመፍጠር እየተሰራ ባለ ስራ በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ከ2.1 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ።

የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ሳምንታዊ የገቢ አሰባሰብ አፈፃፀም ያለበትን ደረጃ ግምገማ ማካሄዱን አስታውቋል።

በክፍለ ከተማው በሁሉም ወረዳዎች የግብር አሰባሰብ ንቅናቄ ያለበትን ደረጃ የክፍለ ከተማው አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሀላፊ ፣የመሬት ልማት አስተዳደር ምክትል ሀላፊ ፣የክፍለ ከተማው ፋይናንስ ጽ/ቤት ሀላፊ እንዲሁም የወረዳ የገቢ ግብረ ሀይል አመራሮች በየዘርፉ የተሰሩ ስራዎች ሳምንታዊ አጭር ሪፖርት አቅርበዋል፡፡

ግምገማውን የመሩት የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው በሁሉም ወረዳዎች በግምገማው በጥንካሬ እና በድክመት የተቀመጡ ስራዎች በመኖራቸው በቀጣይ የገቢ አሰባሰብ ሂደቱ በታቀደው ልክ እንዲሳካ እንዲሁም ገቢ መሰብሰብ እንዲቻል በትኩረት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

በድክመት እና በጥንካሬ የተሰሩ ስራዎችን በየደረጃው በመለየት በቀጣይ ቀሪ ጊዜያቶች ዕቅዳችንን እናሳካለን ሲሉ የግምገማው ተሳታፊዎች ተናግረዋል፡፡

እስካሁን በተሰበሰበው የገቢ ግብር 1.45 ቢሊየን እንዲሁም በማዘጋጃቤታዊ ግብር አሰባሰብ 710 ሚሊየን ብር መሰብሰብ መቻሉን በግምገማው ወቅት ተገልጿል ።
ምንጭ:- ኮልፌ ቀራንዮ ኮሙኒኬሽን

"አረንጓዴ አሻራችን ለሌማት ቱሩፋታችን" በሚል መሪ ቃል የችግኝ ጉድጓድ ቁፋሮ ማስጀመሪያ ተካሄደ፡፡ የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ በዚህ የክረምት ወቅት እንደ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የተለያዩ...
01/06/2023

"አረንጓዴ አሻራችን ለሌማት ቱሩፋታችን" በሚል መሪ ቃል የችግኝ ጉድጓድ ቁፋሮ ማስጀመሪያ ተካሄደ፡፡

የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ በዚህ የክረምት ወቅት እንደ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የተለያዩ ቅድመ የችግኝ ተከላ ጉድጓድ ቁፋሮ በሁሉም ወረዳዎች ዝግጅቶችን ሲያደርግ መቆየቱ የሚታወቅ ነው።የክፍለ ከተማው አስተዳደር በዛሬው እለት ወረዳ 08 ፊናስ ጫካ አካባቢ የችግኝ ተከላ ቅድመ ዝግጅት መርሀ ግብር ጉድጓድ ቁፋሮ አስጀምሯል።

በጉድጓድ ቁፋሮ መርሃ ግብሩ ላይ የክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው፣የዲሞክራሲ ስረዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙሉጌታ ጉልማ፤ ዋና አፈ ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ቦግአለች ተድላ ፤ የክፍለ ከተማው አስተባባሪ ኮሚቴ አባል፣የወረዳ8 ዋና ሰራአስፈጻሚ አቶ ያሲን እና በየደረጃው ያሉ የክፍለ ከተማና ወረዳ አመራሮች፣ ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

የክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ንጋቱ ዳኜቸው በቅድመ ችግኝ ተከላ መርሀ ግብር ጉድጓድ ቁፋሮ ላይ ተገኝተው ይህን መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል የአየር ሁኔታ ለውጥን መመከትና ለአረንጓዴ ኢኮኖሚ ዕድገት ሁኔታዎችን ማመቻቸት የብልጽግና ጉዟችን አንዱ መንገድ ነው ሲሉ አሁን አለማችን እያወከ ያለው የአየር ብክለት መንስኤ ምክንያቶች ናቸው ተብለው እየተጠቀሱ ያሉት የደን ሀብቶቻችንን በአግባቡ ባለመያዝ እና ተገቢውን እንክብካቤ ካለማድረግ የተነሳ መሆኑንም ታሳቢ በማድረግ የተተከሉ ችግኞችን መጠበቅና መከባከብ ቅንጦት ሳይሆን የመኖራችን ህልውናም መሠረት እንደሆነ ማህበረሰቡ ተገንዝቦ በዚህ ዘመቻ ላይ በንቃት ሊሳተፍ እንደሚገባም ጠቁመዋል።

የክፍለ ከተማው የዲሞክራሲ ስረዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ሙሉጌታ ጉልሜ በችግኝ ተከላ ቅድመ ዝግጅት ላይ እንደ ተናገሩት የለውጡ መንግስት ከመጣ ጀምሮ በጠቅላይ ሚኒስትሩ አስጀማሪነት በባለፉት አራት አመታት በቢሊዮን የሚቆጠሩ ችግኞች እንደ ተተከሉ አስተውሰው በዚህ የችግኝ ተከላ ቅድመ ዝግጅት ማስጀመሪያ ላይ ችግኞችን መትከል ብቻ ሳይሆን ተንከባክቦ ለቀጣዩ ትውልድ የአየር ንብረቷ የተጠበቀ ሀገር ማስረከብ ያስፈልጋል ብለዋል።

በ2015/16 የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በክፍለ ከተማው 1.5 ሚሊየን ችግኞችን ለመትከል መታቀዱን የገለጹት የኮልፌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዛየደ ቢወጣ በበኩላቸው በክፍለ ከተማ ባለፉት አራት ዙሮች በሚልዮን የሚቆጠሩ ችግኞች መተከላቸውን አስታውሰው ፣ ለዚህ ስኬት መላው የክፍለ ከተማው ነዋሪዎችና አመራሩ በጋራ በመረባረብ ያደረጉትን ተሳትፎ በአምስተኛውም ዙር አጠናክረው በመቀጠል አረንጓዴ ልማትን ዕውን ለማድረግ በሚደረገው ጥረት የማይተካ ሚናቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

የክፍለ ከተማው ከፍተኛ አመራሮች ከጉድጓድ ቁፋሮ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ጎን ለጎን የወረዳ 08 ችግኝ ማፊያ ጣቢያ ጉብኝት ተደርጓል፡፡
Source KOLFE keranio KOLFE keranio communication/ኮልፌ ኮሙኒኬሽንKOLFE keranio communication/ኮልፌ ኮሙኒኬሽንKOLFE keranio communication/ኮልፌ ኮሙኒኬሽን (ግንቦት 24/2015 ዓ.ም)

የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ንጋቱ ዳኛቸዉ  የአጉስታ ወይራ መንገድ ግንባታ ያለበትን ደረጃ ምልከታ አደረጉ ፡፡************መጋቢት 21/2015 ዓ.ምየኮልፌ ቀራ...
30/03/2023

የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ንጋቱ ዳኛቸዉ የአጉስታ ወይራ መንገድ ግንባታ ያለበትን ደረጃ ምልከታ አደረጉ ፡፡
************
መጋቢት 21/2015 ዓ.ም
የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው የህብረተሰቡን መሰረታዊ የልማት ጥያቄ ዉስጥ አንዱ የሆነዉን የቤተል አጉስታ መንገድ ስራ ያለበትን ደረጃ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ምልከታ አድርገዋል።
በምልከታው ከዚህ በፊት የመንገድ ወሰን ማስከበር ጉዳይ 4 መኖሪያ ቤቶች መንገድ ወቶባቸዉ ተነሺ እንደሆኑ ተነግሮአቸዉ የካሳ ጉዳይ ያላለቀላቸው በመሆኑ ሳይነሱ በመቅረታቸዉ የመንገድ ስራዉ ለመቋረጥ ምክኒያት ሆነው ቆይተዋል ።
የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በመነጋገር በአንድ ሳምንት ዉስጥ ለነዋሪዎቹ ካሳም ሆነ የመኖሪያ ቤት የኪራይ እንዲሁም ተለዋጭ ቦታ ተሰጥቷቸው መነሳት እንዳለባቸዉ መወሰኑን የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው በምልከታው ወቅት ገልፀዋል ።

በኮልፌ እፎይታ የገበያ ማዕከል በደረሰ እሳት 42 የንግድ ሱቆች ወደሙ ከእሳት አደጋው ግምቱ ያልታወቀ ጥሬ ገንዘብ በማትረፍ ፖሊስ ተረክቧልበአዲስ አበባ በትላንናው እለት መጋቢት 7 ቀን 20...
17/03/2023

በኮልፌ እፎይታ የገበያ ማዕከል በደረሰ እሳት 42 የንግድ ሱቆች ወደሙ ከእሳት አደጋው ግምቱ ያልታወቀ ጥሬ ገንዘብ በማትረፍ ፖሊስ ተረክቧል

በአዲስ አበባ በትላንናው እለት መጋቢት 7 ቀን 2015 ዓ.ም ምሽት 2:20 ሰዓት ላይ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ኮልፌ እፎይታ ገበያ ጀርባ በደረሰ የእሳት አደጋ 42 የንግድ ሱቆች መውደሙን የእሳት አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።

“ዕውቀትን የሚያከብር ባህል ለመገንባት፤ በሐሳብ የበላይነት ማመንን ይጠይቃል።ከዚህም በአንድ ወቅት የሚሠራ ሐሳብ በሌላ ጊዜ ፋይዳ ቢስ ሊሆን እንደሚችል ተገንዝቦ፤ ያለማቋረጥ አዲስ ሐሳብን ...
15/03/2023

“ዕውቀትን የሚያከብር ባህል ለመገንባት፤ በሐሳብ የበላይነት ማመንን ይጠይቃል።ከዚህም በአንድ ወቅት የሚሠራ ሐሳብ በሌላ ጊዜ ፋይዳ ቢስ ሊሆን እንደሚችል ተገንዝቦ፤ ያለማቋረጥ አዲስ ሐሳብን ለማድመጥና በምክንያታዊነት ለመቀበል ዝግጁ የሆነ ትውልድ መፍጠር አለብን።”

#መደመር

16/02/2023
16/02/2023

Address

Bethel
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Kolfe Media Network posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Share

Category