“ሀገሬ ሰዉ አጣሽ ወይ ???? “ ወዳጆቼ የዕለቱ ግብዣ
ድምፃዊ ነዋይ ደበበ (በእንቁ ዜማ )
እንቁ ዜማ የሙዚቃ ቡድን አባላት በሙያቸዉ በተሰጥኦቸዉ ተወዳድረዋል እንምረጣቸዉ !!!
በGoogle ገብታችሁ
TikTok Creative Award
Best musician/ producer ላይ ታገኟችኋላቸዉ መልካም ዕድል ለብሩህና ጉበዝ ታዳጊዎቻችን ።
ሀገሬ ነይማ -“ ኢትዮዽያ “ነይማ ፡
የበላይ ጌጥ - የጃገማ ፡
የዮሐንስ - የምኒሊክ ሦስት ቀለም ሸማ ።
ሀገሬ ነይማ “ኢትዮዽያ “ነይማ
የካኦ ጦና - የዚያ ደፋር
የቴዎድሮስ - ያባጅፋር
የዼጥሮስ ወንዝ ዳር ።
አንቺማ አንቺ ነሽ የማልለዉጥሽ፡
ብፅፍ ፣ ባዜምልሽ ፣ ብዘምርልሽ ፡
አይታክትም ክንዴ ሰንደቅሽን የያዘዉ፡
ለሀገር መሰዋት ድሮም ያባቴ ነዉ ።
አቤል ሙሉጌታ ( በእንቁ ዜማ ) የሙዚቃ ቡድን
ግጥምን ማንቀባረር ተክኖበታል ባሻዉ መንገድ በልኳ ያሽሞነሙናታል ትታዘዘዋለች ፣ ይወዳታል ፣ ይተዋወቃሉ ፣ ይግባባሉ እሷም የዋዛ አይደለች አክባሪዋን ታከብራለች “መዜ “የዘመናችን ፋና ጥበበኛ ነዉ ። በትህትናዉ የምንደነቅ ከእዉቀቱ የምንማር ብዙዎች አለን ። ከታይታዉ ሩቅ -
ከእዉቀቱ ጥልቅ እኔስ ምኔ ሞኝ አክብሬዉ ዝቅ
..
እኔና ቴፔ -
መዘክር ግርማ (ከላሊበላ )
እና ጌታቸው መስፍን”
''ያስተዛዝበናል ይህም ቀን ያልፍና!''- ድምፃዊ ራሄል ጌቱ( በዕንቁ ዜማ )
“ሰንደቅሽን አትጣይ “ገጣሚ ኪሩቤል ዘርፉ
''የኢትዮጵያ አምላክ' ይፈርዳል ሳይዉል ሳያድር፡
ይጥልላታል ጠላቷን እባንዲራዉ ስር ፡
አይቀር አንድ ቀን መድረሱ ወቅቱን ጠብቆ፡
ማሪኝ ይላታል ጠላቷ ከግሯ ላይ ወድቆ !!!!!!!
የሃይልዬ ታደሰ ሙዚቃ በእንቁ ዜማ
ለምን ይሙት ደሀ!
“ለምን ይሙት ደሀ “
ደሀ ድሆ ድሆ
ድሆ ድሆ ደሀ
የሚልሰዉ የለ የሚቀምሰዉ ዉሀ
አስር ኪሎ ዱቄት
ሶስት ሊትር ዘይት
ሰባት ፍሬ እንቁላል
አምስት ኪሎ ሽንኩርት
አጣጥቶ በኖረ ላምሳሁለት ሳምንት
በግፍ በመከራ እንዴት ደሀ ይሙት ?
ድሆ ድሆ ደሀ
ለቁርስ
የብርድ ጥብስ
ምሳ ድብን ያለ ፀሀይ
መክሰሱን በእከክ በልቶት ለራት ተባይ
እንዴት ደሀ ይሙት ?
ተመስገን ይልሀል አንጋጦ ወደ ላይ …..
ከቪድዮዉ ላይ የተቀነጨበ
ገጣሚና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች አሊ ሁሴን ሰኢድ
ተፃፈ 1984 ዓ/ም
የተወደዳችሁ ቤተሰቦቼ ለዚህ ቪድዮ ርዕስ ፃፍኩ ሰረዝሁ ፣ ሰረዝሁ ፃፍሁ “አሊ ሁሴን ሰኢድ “ ቃል አስጠፋኝ ለካ እንዲህም ሀገር ይወደዳል ? ለካ እንዲህም ሀገር ይከበራል ? ለካ ገና አልደረስንበትም ? ወዳጆቼ የአሊን አደራ ተመልከቱ የሀገርፍቅር ስሜታችሁን ፈትሹና ምላሻችሁን ፃፋለት ።
"ለ72 ሰዓታት ብቻ ከእናቴ ጋር ኬንያ ተገናኘን በደረሰባት አደጋ ተለያየን"
“ኢትዮዽያ ጠላትሽን አንበርክከሽ ሰንደቅሽን ከፍ አድርገሽ ልይሽ “…
ገጣሚና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች አሊ ሁሴን ሰኢድ / ካናዳ ዊኒፔግ /
ሀገር እንዴት ትፈቀራለች በአሊ ልብ ፡ ፅናት መልኩ ምንይመስላል አሊን ። ናፍቆትና እንባ አድራሻቸዉ የአሊ አይን !! መጥኔ አዙሪታችን ሄደን ሄደን ግን እዛዉ ?ከትናንት የምንፈወሰዉ እንዴትና መቼ ? አሊን እናድምጠዉ እንመልከተዉ የትናንትን ፣የዛሬ ፣የነገን መልክና ዕጣ ፈንታችንን የምናይበት መስታወታችን ነዉ ።
ብንማርበት ?
ብንምርበት ?
…..::
የስደተኛዉ አባት “አሊ ሁሴን ሰኢድ “ለ43 ዓመታት ኢትዮዽያን በአይነስጋ አላየም !!!
/ዊኒፔግ ካናዳ/
ሙሉውን በአርትስ YouTube ያገኙታል፡፡
https://www.youtube.com/watch?v=M1uMMHjOPG4&t=756s
የሞት ፍርደኛዉ “ባለዉለታችን “ገጣሚና የሰብአዊ መብት ተሟጋች “ አሊ ሁሴን ሰኢድ “ የሚወዳት ሀገሩ ኢትዮዽያን በአይነ ስጋ ካያት 43 አመታትን እንዳስቆጠረ በናፍቆቷ እንደተቃጠለ ፣ የኢትዮዽያን አፈር ለመቀበሪያዉ ከሳሎኑ ከድኖ እንዳስቀመጠ ፣ በሚኖርበት ካናዳ ዌኒፔግ አገኘሁት ። ለሀገር ፍቅር የከፈለዉን መስዋዕትነት እና ለዓመታት ለበርካታ ኢትዮጵያዉያን ዋርካ መጠለያ ሆኖ የገዘፈበትን ረጅሙንና አስደናቂ የህይወት ታሪኩን አወጋኝ ነገ እሁድ ህዳር 8 ከ8 ሰዓት ጀምሮ በአርትስ ቲቪ ይተላለፋል በክብር ጋበዝናችሁ ።
አሊ ወደሀገር ቤት ስትመለሽ ኢትዮዽያን ሳሚልኝ ብሎ አልቅሶ አስለቅሶኛል እስቲ ንገሩኝ ማንን ልሳም ? አማራ ፡ ጉራጌ ኦሮሞ ፡ትግሬ ፣ ሱማሌ ፡ አፋር…..ማንን ? የአሊ ኢትዮዽያ ከዘር በላይ ናት ።
የኛስ ???
ጦቢያ እንዴትና ወዴት …ክፍል 03
የተወደዳችሁ የጦቢያ ቤተሰቦችና ደጋፊዎቻችን ከበርካታ ጥያቈዎቻችሁ መሀከል የመጨረሻዉ እና ክፍል 3
1 በረጅሙ የጦቢያ ጉዞ የምታመሰግኑት አለ ?
2 ጦቢያ ተቋርጧል ብለዉ ለሚያስቡ ሰዎች ምላሽሽ ምንድ ነዉ ?
3 ጦቢያ በ2024 በዋሽንግተን ዲሲ የሲድ አዋርድ ተሸላሚ ሆኗል ሂደቱ ምን ይመስል ነበር ?
4 ጦቢያ ከሲድ የተቀበለዉን ሽልማት ለአንድ አካል አበርክቷል ለማን ለምን ?
5 ለሚመለከተዉ ሁሉ ያለሽ መልዕክት ?
ከራፋቱኤል ወርቁ ጋር በነበረኝ ቆይታ ምላሽ ሰጥቼበታለሁ አድታደምጡኝ በክብር ጋበዝኋችሁ ::
ጦቢያ እንዴትና ወዴት …ክፍል 02
የተወደዳችሁ የጦቢያ ቤተሰቦችና ደጋፊዎቻችን ከክፍል 1 የቀጠሉ ጥያቈዎቻችሁ መሀከል ፦
1 አሁን ባለዉ ነባራዊዉ ሁኔታ ኢትዮዽያዉያን ለሀገራቸዉ ያላቸዉ ክብር ምን ያህል ነዉ ?
2 ትርክትን ለማስተካከል ኪነጥበብ ያላት ሚና ምንድን ነዉ ?
3 ጦቢያ ላይ ለሚጋበዙ ምሁራንና የፓለቲካ ፓርቲ መሪዎች እንዲሁ የሀይማኖት አባቶች ለሚያቀርቡት ሀሳብ መስፈርት አላችሁ ?
ከራፋቱኤል ወርቁ ጋር በነበረኝ ቆይታ ምላሽ ሰጥቼበታለሁ አድታደምጡኝ በክብር ጋበዝኋችሁ
https://youtu.be/kJbgTTQZi-8?si=R-otROKwSZ8SEhi9 ሙሉዉን ቪድዮ ለማየት
ጦቢያ እንዴትና ወዴት …
ጦቢያ እንዴትና ወዴት ..( ክፍል አንድ )
የተወደዳችሁ የጦቢያ ቤተሰቦችና ደጋፊዎቻችን ከበርካታ ጥያቈዎቻችሁ መሀከል ፦
1 “በነፃ ሀሳብና በሰከነ መንፈስ ኢትዮዽያን እና ኢትዮዽያዊነትን እናድምቅ “ ምን ማለታችሁ ነዉ ?
2 ጦቢያ እንዴት ፣ መቼ ፣የት ፣በማን ተመሰረተ?
3 ተፈጥሮአዊ ዉበት / ኢትዮዽያዊ ዉበት ላንቺ ምን ማለት ነዉ ?
4 የጦቢያ ፈተናዎች ምን ምን ነበሩ ምን ምን ናቸዉ ?
5 ጦቢያ ያንድ ብሄርና ያንድ ቋንቋ ነዉ ለሚሉ / ለሚመስላቸዉ / ሰዎች ምላሽሽ ምንድን ነዉ ?
ከራፋቱኤል ወርቁ ጋር በነበረኝ ቆይታ ምላሽ ሰጥቼበታለሁ አንድታደምጡኝ በክብር ጋበዝኋችሁ ::
ክፍል 2 ይቀጥላል ….
https://youtu.be/kJbgTTQZi-8?si=R-otROKwSZ8SEhi9 ሙሉዉን ቪድዮ ለማየት
አዲሱን የጦቢያን ሊንክ ሰብስክራይ ያድርጉ ቤተሰብ ይሁኑ
https://youtube.com/@-tobiya?si=bCRrJfWvqTulqKvo