#መቐለ
በትግራይ ክልል፣ መቐለ ዓይደር ኮምፕሬሄንሲቭ ሪፈራል ሆስፒታል የላፕራቶሪ ማሽኖች ላይ ወድመት ደርሷል።
ከሰሞኑን አንድ በጭንቅላቱ ላይ ካርቶን ያደረገ ማንነቱ የማይታይ ግለሰብ በሆስፒታሉ የህክምና ቁሶች ላይ ጉዳት ሲያደርስ የሚያሳይ የCCTV ቅጂ ተሰራጭቷል።
ግለሰቡ ለምን እንዲህ ያለውን ተግባር እንደፈጸመ የሚታወቅ ነገር የለም።
ሆስፒታሉ ለቢቢሲ ትግርኛ ክፍል በሰጠው ቃል ፥ በትክክል ድርጊቱ የተፈፀመው ዓይደር ውስጥ እንደሆነ አረጋግጧል።
ድርጊቱ የተፈፀመው በራሱ ሰራተኛ እንደሆነ አመልክቷል።
ድርጊቱ የተፈፀመው ቅዳሜ መጋቢት 21 ለሊት ሲሆን በሚሊዮኖች የሚገመት ዋጋ ያላቸው በርካታ የህክምና መሳርያዎች ላይ ጉዳት ደርሷል ብሏል።
➡ የጉበት፣
➡ የኩላሊት እጥበት፣
➡ የሰውነት ሆርሞን መለኪያ
➡ የካንሰር አመላካቾች እንዲሁም በተለያዩ እንደ የልብ ህመም ያሉ ድንገተኛ ሁኔታዎች መመርመሪያዎች፣ የሆርሞኖች፣ የሰውነት ስብን መለኪያ መሳሪያዎች ከተጎዱት የሆስፒታሉ መገልገያዎች መካከል ናቸው።
ጉዳት ከደረሰባቸው የህክምና መሳሪያዎች አንዱ ለተለያዩ ምርመራዎች የሚውለው " ኮባስ 6000 " የሚል መጠሪያ ያለው ሲሆን፣ በትግራይ ያለው ብቸኛው እና ትልቁ የሆስፒታሉ መሳሪያ ነው።
አሁን ከአገልግሎት ውጪ ሆኗል።
መሳሪያው ቀደም ብሎ በ20 ሚሊዮን ብር የተገዛ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ዋጋው 30 ሚሊዮን ብር እንደ
በሀገራችን አንዳንድ መልካም የስራ ስነምግባር የጎደላቸው ፣ ከአሸከርካሪዎች ጉቦ ካልተቀበሉ ቀኑ መሽቶ የማይነጋ የሚመስላቸው ፣ አንዳንዴም ሆን ብለው ምክንያት ፈልገው የቅጣት ወረቀት ለመፃፍ በኃላም #ጉቦ ለመቀበል የማይፈነቅሉት ድንጋይ የሌላቸው ፣ ፀሀዩ በረታብኝ ፥ ዝናቡም አካፍብኝ ብለው የሚጠለሉ የትራፊክ የፖሊስ አባላት እንዳሉት ሁሉ ፦
- ለስራቸው ታማኝ
- ህግን አክባሪ
- ቅን አገልጋይ
- ፀሀይ ፣ ዝናብ ሳይሉ ህዝብን አክብረው የሚሰሩ በርካታ የትራፊክ ፖሊስ አባላት አሉ።
ለእነዚህ አይነት ህዝብን አክብረው ምንም አይነት ሁኔታ ሳይገድባቸው ለሚሰሩ የትራፊክ ፖሊስ አባላት #ምስጋና ይገባል።
በሀገራችን ካሉ ከተሞች አንዷ በሆነችው የሰላም ተምሳሌቷ #ድሬዳዋ ❤️ የትራፊክ ፖሊስ አባላቶቿ በተለያየ ጊዜ በመልካም ስነምግባራቸው ስማቸው ተደጋግሞ ይነሳል።
ትላንትና በከተማው ከባድ ዘናብ ዘንቦ በነበረበት ወቅት የትራፊክ መጨናነቅና አደጋ እንዳይከሰት አንድ የትራፊክ ፖሊስ አባል በዝናብ ውስጥ ሆኖ ስራውን ሲያከናውን የሚያሳይ የተቀረጹ ቪድዮዎች እና ፎቶዎች ብዙዎች በማህበራዊ ሚዲያ ሲያጋሩት ውለዋል።
በድሬዳዋ ከተማ ትናንት መጋቢት 18 ማታ አካባቢ ከባድ ዝናብ መጣሉን ተከትሎ በከተማዋ ድንገተኛ ጎርፍ ተከስቶ የንብረት ጉዳት ደርሷል።
ለጉልት ገበያ ሲያገለግሉ የነበሩ በሸራ የተሰሩ ቤቶች በጎርፉ ተወስደዋል።
እስካሁን በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት ስለመኖሩ የታወቀ ነገር የለም።
የብሄራዊ ሜትሮሎጂ ኤጀንሲ በምስራቁ የሀገራችን ክፍል የዝናቡ ሁኔታ በዚህ ከቀጠለ ድንገተኛ ጎርፍ ሊያስከትል ይችላል ብሏል።
#ሞስኮ
ዛሬ አርብ ታጣቂዎች በሩስያ ፣ ሞስኮ ወደሚገኝ ህዝብ ወዳለበት ትልቅ የሙዚቃ ኮንሰርት አዳራሽ በመግባት አውቶማቲክ የጦር መሳሪያ በመተኮስ በርካታ ሰዎችን መግደላቸው ተሰምቷል።
የአካል ጉዳት የደረሰባቸውም አሉ።
አንዳንድ ሪፖርቶች እስካሁን ድረስ ባለው በትንሹ 40 ሰዎች መገደላቸውን እና ከ100 በላይ ሰዎች መቁሰላቸውን ጠቁመዋል።
በአዳራሹ ውስጥ ሰዎች ተሰባስበው የነበረው ለአንድ የሙዚቃ ድግስ ነበር።
ታጣቂዎቹ ቦንብም ሲወረውሩ ነበር የተባለ ሲሆን አዳራሹ ያለበት ህንፃ በእሳት ሲያያዝ ታይቷል።
የሩሲያ ሀገር ውስጥ ስለላ አገልግሎት ከጥቃቱ በኋላ #ሞት እና #የአካል_ጉዳት መድረሱን አረጋግጧል ፤ የሟቾች ቁጥርን ግን አልገለጸም።
የሩስያ ጤና ሚኒስቴር የተጎዱ ሰዎች ሆስፒታል መግባታቸውን አሳውቋል።
በስፍራው የነበረ አንድ ጋዜጠኛ ፥ ታጣቂዎቹ አውቶማቲክ መሳሪያ እየተኮሱ መግባታቸውን ፤ የእጅ ቦምብ / ተቀጣጣይ ቦምብ ሲወረውሩም እንደነበር ገልጿል።
ጋዜጠኛው ፤ " በአዳራሹ ውስጥ የነበሩ ሰዎች ለ15 እና 20 ደቂቃዎች እራሳቸውን ከጥይት ለመከላከል ወለል ላይ ተኝንተው እንደነበር በኃላ ሁኔታው ጋብ ሲል እና የፀጥታ ኃይል ሲመጣ መውጣታቸውን አስረድቷል።
የሩስያ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ድርጊቱን " የሽብር ተግባር " ብሎታል።
እስካሁን ለጥቃቱ ኃላፊነት የወሰደ ወይም ሩስያ ይህ አካል ነው ያለችው የለም።
ቪድዮ ፦
ማይክ ሀመር በጦርነት የሚፈታ ምንም አይነት ነገር እንደሌለ በአፅንኦት ተናገሩ::
ቪድዮ ፦ በትላንትናው ዕለት በኔዘርላንድስ ፤ ሄግ ከተማ የኤርትራን መንግሥት በሚደግፉ እና በሚቃወሙ ኤርትራውያን ቡድኖች መካከል በተከሰተ ግጭት የፖሊስ ተሽከርካሪዎች በእሳት ጋይተዋል።
የኔዘርላንድስ ፖሊስ ግጭቱን ለመቆጣጠር ሲል አስለቃሽ ጋዝ ለመጠቀም ተገዷል። የኔዘርላንድ ፖሊስ መኪኖችም መቃጠላቸው ተነግሯል።
የአይን እማኞች ግጭቱ በተካሄደበት ስፍራ በርካታ ሰዎች በጎዳና ላይ እንደነበሩ ፤ አንዳንዶች ድንጋይ ሲወረውሩ እንደነበር ፤ በእሳት የተያያዙ መኪኖችም መመልከታቸውን ታናግረዋል።
በግጭቱ ሰዎች ላይ ጉዳት ስለመድረሱ የታወቀ ነገር የለም።
የሄግ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ግጭቱ የተከሰተው የኤርትራ መንግሥት ደጋፊዎች ስብሰባ እያካሄዱ ሳለ ተቃዋሚዎች ወደ ስብሰባው ስፍራ በመሄድ ጥቃት በመፈጸማቸው ነው።
ሁኔታው አሳሳቢ ሆኖ ከቁጥጥር ውጪ መሆኑን የገለፀው ማዘጋጃ ቤቱ በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን አረጋግጧል።
መሰል ግጭት ከዚህ ቀደምም በኤርትራውያን መካከል አውሮፓ ውስጥ መከሰቱ የሚዘነጋ አይደለም።
መረጃው የትግርኛው የቢቢሲ ክፍልና የኤፒ ነው።
ቪድዮው ፦ ከኔዘርላንድስ የማህበራዊ ትስስር ገፆች የተወሰደ ነው።
አዲሱ ያ ቴሌቪዥን በእሳት አደጋ ከፍተኛ ዉድመት ደረሰበት‼️
ጎተራ አከባቢ በሚገኘው አጎና ሲኒማ ህንፃ ላይ በቅርቡ የተቋቋመው እና የሩቅ ምስራቅ ፊልሞችን በአማርኛ ትርጉም ለተመልካቾች ሲያቀርብ የነበረዉ ያ ቴሌቪዥን ማምሻዉን ባጋጠመዉ የእሳት አደጋ ከፍተኛ ዉድመት እንዳጋጠመው ተሰምቷል።
ጎተራ አካባቢ የቀድሞው አጎና ሲኒማን በመያዝ ወደ ስራ የገባዉ የቴሌቪዥን ተቋሙ ፤ አዳዲስ ፕሮግራሞችን በማካተት ስራ መጀመሩን በቅርቡ ማስታወቁ አይዘነጋም። በእሳት አደጋዉ ሌሎች መደብሮችም ጉዳት እንደደረሰባቸዉ ታውቋል።
የአዲስአበባ እሳት ፣ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች እሳቱን ለማጥፋት ርብርብ ያደረጉ ሲሆን የወደሙ ንብረቶችን በሚመለከት እስካሁን የተገለፀ ነገር የለም።
የዑራዔልና የካ ሚካዔል ታቦታት 22 ማዞሪያ አደባባይ ጋር ሲገናኙ
ታሪክን የኋሊት! #addisababa
መርካቶ ገበያ በ 1980ዎቹ! አዲስ አበባ!
#USA #Election
" ስደተኞች የሀገራችንን ደም እየበከሉ ነው " - ዶናልድ ትራምፕ
ሪፐብሊካንን በመወከል ለፕሬዝዳንትነት የሚወዳደሩት ዶናልድ ትራምፕ ስደተኞች " የሀገራችንን ደም እየበከሉ ነው " በማለት ተናገሩ።
ትራምፕ ይህ ያሉት #ከሜክሲኮ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ስደተኞች በሚገቡበት " ኒው ሄሚስፌር " ግዛት ባደረጉት የምርጫ ቅስቀሳ ላይ ነው።
ትራምፕ ለ4 አመት የስልጣን ዘመን በድጋሚ የሚመረጡ ከሆነ ህገወጥ ስደትን እንደሚያስቆሙ እና በህጋዊ ሰደተኞች ላይ ደግሞ ጥብቅ ቁጥጥር እንደሚያደርጉ ተናገረዋል።
ትራምፕ ለደጋፊዎቻቸው ስደተኞች ከደቡብ አሜሪካ በተጨማሪ #ከአፍሪካ፣ ከእስያ እየመጡ ነው ሲሉም ተናግረዋል።
" ከሁሉም የዓለም ክፍል ወደ ሀገራችን የፈሰሱ ነው " ሲሉ አክለዋል።
ዶናልድ ትራምፕ ባለፈው መስከረም ወር " ናሽናል ፐልስ " ከተባለው የቀኝ ዘመም ዌብሳይት ባደረጉት ቃለ ምልልስ ስደተኞች " ደማችንን እየበከሉት ነው " የሚል ተመሳሳይ ንግግር አሰምተው ነበር።
በወቅቱ ይህ የትራምፕ ንግግር " ዘረኝነት እና ጥላቻ " የሚያንጸባርቅ ነው የሚል ትችት አስነስቶ ነበር።
የያሌ ፕሮፌሰር እና በዘረኝነት ጉዳይ መጸሀፍ ያሳተሙት ጆናታን ስታንሊ ትራምፕ ቋንቋውን አሁንም ደግመው መጠቀማቸው አደገኛ ነው ብለዋል።
ፕሮሬሰሩ እንደተናገሩት ትራምፕ " የጀርመኖች ደም በጅዊሾች እየተበከለ ነው " የሚለውን የሂትለር ንግግር ያስተጋባ
የቢቢሲ ዜና አንባቢዋ መሪያም ሞሺሪ በቀጥታ ስርጭት ወቅት ጣቶቿን በመጠቀም ጸያፍ ስድብ ስትሳደብ ታየች
የቢቢሲ ዜና አንባቢዋ መሪያም ሞሺሪ በዛሬው እለት በነበረዉ የዜና ቀጥታ ስርጭት ወቅት ጣቶቿን በመጠቀም ጸያፍ ስድብ ስትሳደብ ታይታለች።
የጋዜጠኛዋን አጋጣሚ ተከትሎም በርካቶች ተንቀሳቃሽ ምስዕሉን በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሲቀባበሉት ዉለዋል። ይህንኑ ተከትሎም ጋዜጠኛዋ ይቅርታ ጠይቃለች።
ቀልድ ላይ ነበርን ያለችዉ ጋዜጠኛዋ ለፈጸመችዉ የሞኝ ቀልድ ተግባር ይቅርታ ጠይቃለሁ ብላለች። በቅጽበት ዉስጥ የቀጥታ ስርጭት ላይ መሆኗን የተረዳችዉ ጋዜጠኛዋ በፍጥነት ለተመልካቾች ሰላምታን አስከትላ ስራዋን በአፋጣኝ ቀጥላ ነበር።
ሞሺሪ በቢቢሲ ዉስጥ ካሉ ልምድ ካላቸዉ ጋዜጠኞች መካከል አንዷ ነች። ጋዜጠኛዋ ለድርጊቷ የይቅርታ መልዕክቷን በኤክስ ገጿ ላይ ጽፋለች።
Via:- ዳጉ ጆርናል
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በዛሬው የፓርላማ ቆይታቸው ስለ ሬሜድያል ከተናገሩት👇
💥አምና በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች #105,000 የሬሜዲያል ተማሪዎች ትምህርታቸውን ተከታትለዋል፤ #63,033 ተማሪዎች አልፈዋል።
💥አምና በግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት #44,500 የሬሜዲያል ተማሪዎች ትምህርታቸውን ተከታትለው፥ #27,587 የሚሆኑት አልፈዋል።
💥በአጠቃላይ #145,500 ተማሪዎች በሬሜዲያል ፕሮግራም ትምህርታቸውን ተከታትለው #90,620 አካባቢ ተማሪዎች ከሬሜዲያል ወደ ፍሬሽማን አልፈዋል።
🛟በዚህ ዓመት ፍሬሽማን የሚኖረው አምና በሬሜዲያል ፕሮግራም ትምህርታቸውን ተከታትለው ያለፉት #90,620 ተማሪዎች እና በ#2015 የኢንትራንስ ፈተና 50% እና ከዚያ በላይ ያመጡት #27,200 ተማሪዎች ናቸው።
💥ዘንድሮ በዩንቨርሲቲዎች(በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት) ውስጥ በአጠቃላይ የሚመደቡት #191,509 ተማሪዎች ሲሆኑ ከነዚያ ውስጥ በሬሜዲያል #164,242 ተማሪዎችን ይቀበላሉ።( የመንግስት እና የግል ተቋማት ላይ)
💥የተማሪዎች ምደባን በተመለከተ በምንም አይነት መልኩ አግባብ ያልሆነ በአድሎ ላይ የተመሰረተ ምደባ ሚባል ነገር እንደማይኖር አስረግጠው ተናግረዋል። ብቸኛው ከምደባ አሰራር በተለየ መልኩ የሚስተናገደው የህክምና አስገዳጅ ጉዳይ ሲኖር ብቻ መሆኑን ተናግረዋል።
💥ከምደባ ጋር በተያያዘ የተለያዩ ስልኮች እንደሚደወሉላቸው የገለፁት ሚኒስትሩ ባለስ
ቪድዮ ፦ ፑቲን እና #የኒውክሌር_ማዘዣ ብሪፍኬዝ / ባርሳቸው ወይም “ ቼጌት ” በካሜራ እይታ ውስጥ መግባቱ የዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃንን ትኩረት ስቦ እየተቀባበሉት ነው።
ይህ መሰሉ ቪድዮ ሲሰራጭ ብዙም ያልተለመደ ነው።
የሩስያው ፕሬዜዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከቀናት በፊት ወደ ቻይና ማቅናታቸው ይታወሳል።
ትላንት ረቡዕ ፑቲን #ቤጂንግ ውስጥ በደህንነቶች ተከበው ወደ ስብሰባ ሲያመሩ በካሜራ እይታ ውስጥ የገቡ ሲሆን አብረዋቸው (ከኃላ) እያንዳንዳቸው ብሪፍኬዝ / ቦርሳ የያዙ ሁለት የሩሲያ የባህር ሃይል መኮንኖች ዩኒፎርም የለበሱ ሰዎች ታይተዋል።
እነዚህ መኮንኖች የያዙት የኒውክሌር ጥቃትን ለማዘዝ የሚያገለግለውን የኒውክሌር ብሪፍኬዝ/ቦርሳ ወይም ቼጌት የሚባለውን ነው ተብሏል። ይህ በአስፈላጊ ሰዓት የኒውክሌር ጥቃት የሚታዘዝበት ቦርሳ አስፈላጊውን ኮዶች የያዘ ነው።
ከላይ በተያያዘው ቪድዮ ካሜራው አንደኛውን ቦርሳ አቅርቦ ሲያሳይ ተስተውሏል።
የሩስያን የኒውክሌር ብሪፍኬዝ በተለምዶ የሚያዘው በባህር ኃይል መኮንን ነው።
ይህ ብሪፍኬዝ / ቦርሳ በማንኛውም ጊዜ ከፕሬዚዳንቱ አጠገብ የማይለይ ቢሆንም ብዙም በካሜራ እይታ ውስጥ አይገባም / አይቀረጽም።
አንዳንዶች ይህ የማዘዣ ብሪፍኬዝ #በቪድዮ_ተቀርፆ እንዲሰራጭ የተደረገው ሆን ተብሎ ለባላንጣዎቻቸው መልዕክት ለማስተላለፍ ነው ብለውታል።
ከፑቲን በተጨማሪ ፤
ባይደን እስራኤል በሆስፒታሉ ላይ ጥቃት አልፈፀመችም አሉ‼️
ዛሬ እስራኤል የገቡት የአሜሪካው ፕሬዜዳን ጆ ባይደን በጋዛ በሚገኘው አል አህሊ ሆስፒታል ላይ ፍንዳታ የተፈፀመው በእስራኤል ሳይሆን " በሌላኛው ቡድን " ነው ሲሉ ተናግረዋል።
ባይደን ለእስራኤሉ ጠ/ሚ ኔታንያሁ ፤ " ትናንት በጋዛ ሆስፒታል በደረሰው ፍንዳታ በጣም አዝኛለሁ " ያሉ ሲሆን " ባየሁት መሰረት፣ የተደረገው በሌላው ቡድን ነው እንጂ በአንተ (እስራኤል) አይደለም " ሲሉ ተናግረዋል።
እስራኤል ትላንት በሆስፒታሉ ላይ ለደረሰው ጥቃት ያልተሳካ የኢስላሚክ ጂሃድ ቡድን ሮኬት ነው ያለች ሲሆን ሃማስ እንዲሁም " የፍልስጤም ኢስላሚክ ጂሃድ " ድርጅት ጥቃቱ የተፈፀመው በእስራኤል ነው ብለዋል።
ኢስላሚክ ጂሃድ እስራኤል ከጭፍጨፋው ተጠያቂነት ለማምለጥ የተለመደ የሀሰት እና ቅጥፈት ፈጠራዋን ነው ያቀረበችው ብሏል።
በሳዑዲ አረቢያ እስር ቤት የታሰሩ ኢትዮጵያውያን መንግሥት እንዲደርስላቸው ተማፀኑ