''ኢስላም ለፈጣሪ እጅን መስጠት እና በትእዛዙ ማደር ማለት ሲሆን
አምልኮትን ሁሉ በብቸኝነት ፍጹም ለአላህ ማድረግ ። ሌሎችን ፍጡራን የስልጣኑ ተጋሪ አለማድረግ፡ ይህን ዩኒቨረስ
ብቻውን የፈጠረለፍጡራን ሁሉ ሲሳያቸውን እሱ ብቻውን የሚመግብለስልጣኑ ተጋሪ ወይም እረዳት ተባባሪ የሌለው
ሃያል ጌታ መሆኑን ማመን። ነገ የትንሳኤ ቀን የፍርዱ ቀን ብቸኛ ባለቤት አላህ መሆኑን ማመን። ይህን ይመስላል
ብለን የምንመስልበት አምሳያ የሌለው ሃያል አምላክ አላህ በመባል ይታወቃል።
ኢስላም ማለት ለአላህ በመመሪያው በማደር ለትእዛዞቹ መንበርከክ ፡ እምነትን እና ልቦናን ለአላህ ፍጹም ማድረግ እና
ከአላህ ዘንድ የመጡ መመሪያዎችን በፍጹምነት ማ
መን ነው።
* አንድ ሰው ''ሙስሊም'' ነው ሊባል የሚቻለው የዚህ ግዙፍ አለም ሆነ ሌላ አለ የሚባለው አለም እና በውስጧ
ያሉት ነገሮች ሁሉ ፈጣሪ ተቆጣጣሪ አስተናባሪ ብቸኛ አምላክ አላህ ነው ብሎ ማመን እና ነቢዩ ሙሃመድ የመጨረሻው
መልእክተኛ ናቸው ብሎ ማመን ነው። ይህም በሌላ አነጋገር በእውነት የሚያመልኩት አምላክ ከአላህ በስተቀር የለም።
ነብዩ ሙሐመድም(ሰላም ለእሳቸው ይሁንና) ባሪያው እና መላክተኛው ናቸው ብሎ ማመን ነው። ይህም በ አረብኛ
«''ላኢላሃ-ኢለሏህ ሙሃመድ ረሱሉሏህ''» በመባል ይታወቃል።
በዓለም ላይ የእምነቱ ተከታዮቹ ከ1.፮ ቢሊዮን በላይ ሆነው ይገኛሉ።
ሱና ማለት የነብዩ ሙሐመድ ንግግር እና ስራ/ስሩ ብለው ያዘዙት እና ሲሰራ እያዩ በዝምታያለፉት (አትስሩ ብለው
ያልከለከሉት) በአጠቃላይ በህይወታቸው የሰሩት ስራ እና እንዲሰራ ያዘዙት ሁሉ ሱና ይባላል።
ማንኛውም ሙስሊም ኢስላምን የሚተገብረው ከነብዩ ሙሐመድ በተማረው መሰረት ብቻ ነው። ኢስላም ሙሉ እምነት ስለሆነ
ከጊዜ ብዛት አነሰ ተብሎ የሚጨመርበት ወይም በዝቷል ተብሎ የሚቀነስለት ነገር የለውም።
- * ሙስሊሞች ለማንኛውም ቦታ እና ጊዜ/ዘመንየሚያገለገል ቁርዓን እና ሃዲስ የሚባል መመሪያ አላቸው። ይህን
መመሪያም ነብዩ ሙሐመድ ባስተማሯቸው ሱና መሰረት ይተገብሩታል።
እነዚህ የ እምነቱን ድንጋጌዎች የሚያስተምሩት መመሪያዎች ቁርአን እና ሃዲስ ሲሆኑ ቁርአን ማለት በ መልአኩ ጅብሪል
አማካኝነት ወደ መሃመድ በወህይ የተወረደ የአላህ ቃል ማለት ነው። ሃዲስ ማለት ደግሞ ነብዩ ሙሐመድ ንግግሮች
ናቸው ።
''ኢስላም'' የነብያት ሁሉ ሃይማኖት መሆኑን ሙስሊሞች ጠንቅቀው ያምናሉ።
ይህ በ መካ አሁን ያለው እና ካዕባ በመባል የሚታወቀው ግንብ በነብዩ ኢብራሂም አብርሃምእና
ልጃቸው ዒስማኤል የተሰራ ነው ብለው ሙስሊሞች ያምናሉ።
ከአላህ ሌላ ያለን ፍጡርም ይሁን ማንኛውም አይነት ነገር ማምለክ በኢስላም ታላቅ ወንጀል ነው።
ኢማን (የልብ ስራ)የእምነት 6 መሰረታዊ ነግሮችን አጠቃልሎ ይዟል።
:1ኛ በአላህ (በአምላክ ወይም በፈጣሪ) ማመን
:2ኛ መላእክት እንዳሉት ማመን
:3ኛ በ''ኪታቡ'' (በመጽሃፎች ማመን)
:4ኛ በ ''ሩሱሎች''(ነብያቶች ማመን)
:5ኛ በመጨረሻው ቀን የፍርድ ቀን (ሞቶ መነሳት) እንዳለ ማመን
:6ኛ በቀደር ማመንን
የሚሉት ሲሆኑ ሰፋ ያለ ትንታኔ የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ናቸው።
የ''ኢስላም''የተግባር መሰረታዊ ነገሮች 5 ሲሆኑ
:1ኛ አላህ አንድ ነው ሙሀመድ መላክተኛ ነው ብሎ ማመን
:2ኛ ሰላት መስገድ
:3ኝ ዘካ ምጽዋት ማውጣት
:4ና ጾም መጾም
:5ኛ ሃጅ (መካን መጎብኘት)ማድረግ ናቸው።
ከላይ የኢማን መሰረቶች 6 ናቸው ብለናል በመጠኑም ቢሆን በዝርዝር ለማየት እንሞክር
1ኛ በአላህ ማመን ማለት ሲዘረዘር ይህን ዓለም ብቻውን የፈጠረ፡ ብቻውን የሚያስተዳድር እና የሚቆጣጠር፡
ለፍጡራን ሲሳይ የሚለግስ፡ አምላክ አላህ ነው ብሎ ማመን ማለት ነው።
ይህ አለም ካለ ፈጣሪ አልተገኘም። የሰው ልጅም ካለ አላማ ወደዚህ ምድር አልመጣም። ያመጣው አንድ ፈጣሪ
አለው።የመጣውም ለአላማ ነው። የመፈጠራችን አላማም ፈጣሪያችንን ለማምለክ ነው። ይህን አለም መጥኖ አስተካክሎ
የፈጠረው፡ ሰማይን ካለ ምሰሶ ያቆመው
ጸሃይ እና ጨረቃ እንዲሁም ለሊት እና ቀን ሌሎችንም ፕላኔቶች መስመራቸውን ይዘውጠብቀው እንዲጓዙ የሚያደርግ
አምላክ ፈጣሪ አስተናባሪ ተቆጣጣሪ/አላህ ነው ብሎ ማመን አንዱ የኢማን መሰረት ነው።
ከማንኛውም አይነት እንከን እና ጉድለት የጠራ/በሰው ልጅ ላይ የሚታዩ የድክመት ምልክቶች ፍጹም የማይታዩበት
፡የማይበላ እና የማይጠጣ የማይወልድ የማይወለድ ፍጹም የ እሱም ቢጤም ሆነ አምሳያ ስለሌለው ይህን ይመስላል ብለን
ልንመስለው የማንችል ሃያሉ አምላክ አላህ ነው ብሎ ማመን ።
- * እሱ ለምን ሰራህ ተብሎ ሊጠየቅ የማይችል እሱ ግን የፈለገውን የሚሰራ እና የሚጠይቅየሚምር
የሚቀጣ/የሚፈጥር የሚገድል/የሚያስታምም የሚያድን/ የፈለገውን ሰሪ ብቻውን ቀሪ የፍርዱ ቀን ባለቤት አላህ ነው ብሎ
ማመን አስፈላጊ እና የግድ ነው።
2ኛ በመላእክት(በመላኢኮች ማመን) ከብርሃን የተፈጠሩ የማይበሉ የማይጠጡ ከተፈጠሩ ጀምሮ የፈጣሪን ትእዛዝ ብቻ
በመተግበር ላይ የሚዘወትሩ፡ መላእክት አሉት ብሎ ማመን የግድ ሲሆን ከነዚህ መላእክት ዋናዋናዎች ጂብሪል ሜካኤል
ኤስራፊል...የመሳሰሉት ይገኙበታል።
እነዚህ መላእክት ከራሳቸው ምንም ማድረግ የማይችሉ የማይጠቅሙ እና የማይጎዱ በመሆናቸው አምልኮ ለነሱ ተገቢ
አይደለም። እነሱ ፈጣሪያቸውን ሌት ከቀን በቅንንነት ያመልካሉ ፡አመጸኞች አይደሉም። ተግባራቸው የተለያየ ነው።
በጣም ትልቅ ፍጥረት ናቸው። ጅብሪል የሚባለው መላእክት 700 ክንፎች ሲኖሩት አንዱ ክንፍ ብቻ ሲዘረጋ ከጀምበር
መግቢያ እስከ መውጫ ይደርሳል። ይህ የሚያሳየው የ እነዚህ ፈጣሪ ምን ያህል ታላቅ መሆኑን ነው አሏሁ አክበር!!!