10/08/2023
የፕላስቲክ ተረፈ ምርቶችን ወደ ግንባታ ግብአትነት በመቀየር እስከ 12 ሚሊዮን ዶላር ማመንጨትና የውጭ ምንዛሪ ማዳን ለሚያስችል ፕሮጀክት ትግበራ የድጋፍ ስምምነት ተፈረመ፦
====
(በኢትዮጵያ ከ380,000 ሜትሪክ ቶን በላይ የፕላስቲክ ቆሻሻ ክምችት ያለ ሲሆን መልሶ መጠቀም የተቻለው 10 ከመቶ ብቻ ነው።)
የፕላስቲክ ተረፈ ምርቶችን በቴክኖሎጂ በመታገዝ ወደ ግንባታ ግብአቶች በመቀየር፣ የአካባቢ ብክለትን በመቀነስ፣ ለስራ እድልና ሃብት ፈጠራ ለማዋል ያለመ ፕሮጀክት ትግበራ አጋርነትና ድጋፍ ማመቻቸት ስምምነት ተፈርሟል።
ስምምነቱን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አማካሪ ሚንስትር ዲኤታ ክብርት ፎዚያ አሚን (ዶክተር) ና በአዲል ቴክኖሎጂስ እና የኢኖቬሽን ማእከል መስራችና ባለቤት ዶክተር አዲል አብደላ ፈርመውታል።
እንደ ዶክተር አዲል አብደላ፥ በኢትዮጵያ እና በአዲስ አበባ በርካታ ቦታዎች የፕላስቲክ ቆሻሻ በስፋት ተከማችቶ ይገኛል። ይህን አካባቢ የሚበክል ክምችት መልሶ ጥቅም ላይ ማዋል ላይ ያለመ ቴክኖሎጂ በበርካታ ዓለም አገራት እየተሰራበት ይገኛል።
በእኛም አገር ከ380,000 ቶን በላይ የፕላስቲክ ቆሻሻ ተከማችቶ እንደሚገኝ የቆዩ ጥናቶች እንደሚያመለክቱ ጠቁመው፥ ይህን ክምችት ለአካባቢ ተስማሚ ወደ ሆኑ ተኪ የግንባታ ቁሳቁሶች በመቀየር መጠቀም፥ ሃብት ማመንጨትና የውጭ ምንዛሪን መቀነስ የሚያስችል የቴክኖሎጂ አማራጭ ይዘው መቅረባቸውን አስረድተዋል።
ዶክተር አዲል አክለውም አስፈላጊው ድጋፍ ከተገኘ ከስድስት ወራት ባነሰ ተረፈ ምርቶቹን በማሰባሰብ ለግንባታ አስፈላጊ ወደ ሆኑ ግብአቶች ለመቀየርና ለበርካቶች የስራና የሃብት ምንጭ ለመሆን እንደተዘጋጁ አስረድተዋል።
ሚንስቴር መስሪያቤቱ የቴክኖሎጂውን ጠቀሜታና ችግር ፈችነት በማመን የመንግስት እና የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ምቹ ሁኔቻ እንዲፈጥርላቸው ጠይቀዋል።
ድርጅታቸው የሚፈልጋቸው ድጋፎች የቴክኖሎጂ መትከያ የኢንቨስትመንት ቦታ፣ የፕላስቲክ ማከማቻ በቂ ቦታ፣ ወጣቶችንና ስራ ፈላጊዎችን በአመቺነት ማደራጀት፣ ለፕሮጀክቱ አስፈላጊ የኢንዱስትሪ ምርቶችን ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገቡ ማገዝ እና ሌሎች አስተዳደራዊ ጉዳዮችን ያካተቱ መሆናቸውን አብራርተዋል።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ክብርት አማካሪ ሚንስትር ዲኤታ ፎዚያ አሚን (ዶክተር) የተጠየቀው ትብብር ቴክኖሎጂን እና ፈጠራን የሚያበረታታ፣ የተከማቹ በካይ ፕላስቲኮች የሚፈጥሩትን ችግር ለመፍታት መነሳሳቱ በራሱ የሚበረታታ ነው ብለውታል።
አክለውም ለአገሪቱ ወጣቶች የስራና የሃብት እድል በመፍጠር፣ የቴክኖሎጅ ሽግግርን የማመቻቸት እና ከውጭ የሚገቡ የግንባታ እቃዎችን በመተካት የግንባታ ዘርፉን የሚያበረታታ በመሆኑ አስፈላጊው ድጋፍ እንዲደረግለት ከሚመለከታቸው ጋር ለመነጋገር እንሰራለን ብለዋል።
መንግስት ኢትዮጵያን መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገራት ተርታ ለማሰለፍና የዳበረ ዲጂታል ኢኮኖሚ ለመገንባት በማሰብ በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በኩል የሚመለከታቸውን ባለድርሻ አካላት በማሳተፍ እየሰራ ይገኛል።
አክለውም ለፈጠራ ኢኖቬሽንና የቴክኖሎጂ ሽግግር ሥርዓቱ አጋዥ ለሆኑ የምርምርና ችግር ፈች ፕሮጀክቶች ወሳኝ ድጋፍ ለማድረግ እየተሰራ እንደሆነ የጠቀሱት ዶክተር ፎዚያ ለስምምነቱ ትግበራ ከሚመለከታቸው ጋር በመነጋገር ይሰራል ብለዋል።
ይህ ስምምነት ለችግር ፈች ቴክኖሎጂ ልማትና ሽግግር፥ ለስራ እድልና ሃብት ፈጠራ ምቹ ሁኔታን በማስገኘት ለአገሪቱ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እድገት አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ በውይይቱ የተሳተፉ የሚኒስቴር መስሪያቤቱ የቴክኖሎጂ ዘርፍ ተመራማሪዎ