Ethio News -ኢትዮ መረጃ

Ethio News -ኢትዮ መረጃ We are here to provide you true and fair informations....

የዓለም ምግብ ፕሮግራም WFP በትግራይ ክልል ከፍተኛ የሆነ የምግብ ዕርዳታ በአገር ውስጥ ገበያ መሸጡን የሚያሳይ ማስረጃ በማግኘቱ የምግብ አቅርቦቱን ማቆሙን አስታውቋል:: WFP በትግራይ ክ...
25/05/2023

የዓለም ምግብ ፕሮግራም WFP በትግራይ ክልል ከፍተኛ የሆነ የምግብ ዕርዳታ በአገር ውስጥ ገበያ መሸጡን የሚያሳይ ማስረጃ በማግኘቱ የምግብ አቅርቦቱን ማቆሙን አስታውቋል::

WFP በትግራይ ክልል ምርመራ መጀመሩንም የገለጸ ሲሆን WFP አስፈላጊው እርዳታ በጣም ተጋላጭ ለሆኑ ሴቶች፣ ወንዶች እና ህጻናት በትክክል መድረሱን ለማረጋገጥ አዳዲስ የመከላክያ እና ቁጥጥርን ዘዴዎች ለማዘመን እየሰራ እደሆነም ገልጿል::

WFP ዋና ዳይሬክተር ሲንዲ ማኬን በትግራይ ክልል የእርዳታ ምግቦች ለተራቡ ለተቸገሩ ሰዎች እንዳይደርስ ለሚደረገው ትልቅ ስርቆት ላይ WFP ከዚህ በኃላ ትዕግስት የለውም ብለዋል ። በትግራይ ክልል ይህን ዘረፋ የሚያደርጉ ሰዎች ክልልሉ ኃላፊነት በመውሰድ በህግ መጠየቅ አለበትም ብለዋል ዋና ዳሬክተሯ:: WFP ይህን መልስ የሰጠው ትናት በትግራይ ክልል እርዳታ ለምን ቆመ በማለት ህዝቡ በሰላማዊ ሰልፍ ለጠየቀው ጥያቄ መልስ እደሆነም ተገልጿል:: ሙሉ ዝርዝሩን ከመግለጫው ላይ ያንቡ 👇 https://www.wfp.org/news/wfp-statement-strengthened-actions-address-food-diversion-ethiopia

እኛ የሃገራችንን ቋንቋ ተማሩ ስንል ለብሽሽቅና ተንኮል ክፋት እንጠቀምበታለን ሞስኮ አማርኛን ለልጆች ለማስተማር ደፋ ቀና ትላለች:: ቋንቋ መግባቢያ ነው እንኳን የሃገራችንን የውጭ ቋንቋዎችን...
25/05/2023

እኛ የሃገራችንን ቋንቋ ተማሩ ስንል ለብሽሽቅና ተንኮል ክፋት እንጠቀምበታለን ሞስኮ አማርኛን ለልጆች ለማስተማር ደፋ ቀና ትላለች:: ቋንቋ መግባቢያ ነው እንኳን የሃገራችንን የውጭ ቋንቋዎችን እናወራ የለ እንዴ? የሃገራችንን 2 እና 3 ቋንቋ ማወቅ ይጠቅመና እንጂ አይጎዳንም ቅን እንሁን ውጪ ወጥተን በስደት የሰው አገር ቋንቋ ተምረን ስራ እየሰራንበት መሆኑንም አንዘንጋ:: አማርኛ ትግርኛ ኦሮምኛ... የምትችሉ እድለኞች ናችሁ 🙏

የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት በሞስኮ ትምህርት ቤቶች ከመስከረም ጀምሮ ሊሰጥ ነው!!

በሞስኮ ትምህርት ቤቶች ከመስከረም ጀምሮ አማርኛ ቋንቋ ማስተማር ሊጀመር መሆኑ ተገለጸ፡፡

ጉዳዩን አስመልክቶ የስፑትኒክ አለም አቀፍ የዜና አገልግሎት ድርጅት እና ሬዲዮ÷ በሩሲያ - አፍሪካ የኢኮኖሚ ትብብር ተስፋዎች ዙሪያ ውይይት አካሂዷል። ውይይቱ በአሌክሳንደር ጎርቻኮቭ ፐብሊክ ዲፕሎማሲ ፈንድ እና በሰብአዊ እርዳታ ማእከል ድጋፍ የተዘጋጀ ሲሆን÷ በሩሲያ እና በመካከለኛው ምስራቅና በአፍሪካ ሀገራት መካከል አዲስ የትብብር አድማስ” ለመፍጠር ያለመ የባለሙያዎች እና ትምህርታዊ ዝግጅት አካል መሆኑ ተጠቁሟል።

በውይይቱ ላይ ከሩሲያ እና አፍሪካ የተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች የተውጣጡ የታሪክ ተመራማሪ ምሁራንና የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡የእስያ እና አፍሪካ ጥናት ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር አሌክሲ ማስሎቭ ከፈረንጆቹ መስከረም 2023 ጀምሮ ቢያንስ አራት የሞስኮ ትምህርት ቤቶች ለህጻናት የአማርኛ እና የስዋሂሊ ቋንቋ ማስተማር እንደሚጀምሩ ይፋ አድርገዋል።

ማስሎቭ አክለውም በአዲሱ ልዩ መርሐ-ግብር በሞስኮ ትምህርት ቤቶች ዮሩባ ቋንቋን የሚያስተምሩበትን ዕድልም እየተመቻቸ መሆኑን ነው የገለፁት።ወደ አፍሪካ በፍጥነት ፊትን ለማዞር ከኢኮኖሚው ጋር በቀጥታ ሊሰሩ የሚችሉ ፍጹም የተለዩ ባለሙያዎችን ማፍራት ያስፈልጋል ሲሉም ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡

24/05/2023

የፌደራል እንባ ጠባቂ ተቋም የአዲሱ የሸገር ከተማ አስተዳደር ከሚያካሂደው ቤት የማፍረስ እንቅስቃሴ ከ100 ሺህ በላይ አቤቱታዎች ቀርበውልኛል ማለቱን ቪኦኤ ዘግቧል። የተቋሙ ዋና ኃላፊ እንዳለ ኃይሌ፣ የሸገር ከተማ አስተዳደር "ሕገወጥ" በማለት ለሚያፈርሳቸው መኖሪያ ቤቶች ምትክ ቦታ እንደማይሰጥና ቤታቸው ለፈረሰባቸው ወገኖች ጊዜያዊ መጠለያ እንደማያዘጋጅ መናገራቸውን ዘገባው ጠቅሷል።

24/05/2023

#በቆጂ

በቀናት በፊት በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን በቆጂ ከተማ የታጠቁ ኃይሎች በከፈቱት ጥቃት 4 ሰዎች መገደላቸውን እና ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ የነበሩ እስረኞችን ማስመለጣቸውን ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል።

ጋዜጣው ቃላቸውን ሰጡኝ ያላቸው የአይን እማኞች ፤ አርብ ዕለት ከምሽት 4 ሰዓት እስከ ለሊት 8 ሰዓት ከፍተኛ ተኩስም ከተማ ውሥጥ ይሰማ እንደነበር ገልጸው ፤ በማግስቱ ግን የፌዴራል ፖሊስ ወደ ከተማው መግባቱን ተከትሎ ተኩስ እንደቆመ አመልክተዋል።

የአይን እማኞቹ ተኩስ የከፈቱት መንግሥት " ኦነግ ሸኔ እያለ የሚጠራቸው የታጠቁ ቡድኖች መሆናቸውን ገልጸው ፤ ለሊት በነበረው ተኩስ አንድ የአካባቢው የሚሊሻ አሰልጣኝን ጨምሮ ነዋሪዎች መገደላቸውን አሳውቀዋል።

አንድ የሚሊሻው አሰልጣኝ የቅርብ ጓደኛ ነኝ ያሉ የአይን እማኝ ፤ ታጣቂዎቹ " ይህንን ቤት ከምናፈነዳው አንተ ብትወጣ ይሻላል " በማለት በለሊት ከመኖሪያ ቤቱ አስወጥተው እንደገደሉት ጠቁሟል።

ታጣቂዎቹ በከተማው ተኩስ የከፈቱት በእስር ቤት ያሉ ታራሚዎችን ለማስፈተት መሆኑን የገለፁት ነዋሪዎች የሚሊሻ አባሉንና ከነዋሪዎችን ሰው ከገደሉ በኃላ በከተማው ወደሚገኝ አንድ የፖሊስ ጣቢያ ሰብረው በመግባት ታሳሪዎችን ከእስር አስወጥተው መውሰዳቸውን ነዋሪዎች ለጋዜጣው ገልጸዋል።

ጋዜጣው ከከተማው ከንቲባ ምላሽ ለማግኘት የድምፅ እንዲሁም ፅሁፍ መልዕክት በመላክ ሙከራ ቢያደርግም ምላሽ ለማግኘት እንዳልቻለ አሳውቋል።

የበቆጂውን ጥቃት በተመለከተ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ የበቆጂ ቤተሰብ አባላት ተመሳሳይ መልዕክቶች መላካቸውን ተመልክተናል።

ጆ የተባለ የቤተሰባችን አባል አርብ ከምሽቱ 5:30 ጀምሮ ከተማው ውስጥ ከባድ የተኩስ ድምፅ እንደነበር እና ተኩሱ ቢያንስ ከ1 ሰዓት በላይ እንደቆየ ጠቁሟል።

ሌላ ኤቢ የተባለ የቤተሰባችን አባል በበኩሉ ፤ በአርሲ ዞን በቆጂ ከተማ መንግስት " ሸኔ " ብሎ የሚጠራው አካል በከተማ አስተዳደሩ ውስጥ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ላይ ያነጣጠረ ጥቃት በመክፈት 20 የሚደርሱ የህግ ታራሚዎችን አስለቅቋል ሲል ገልጿል።

የተኩስ ልውውጡ ከበድ ያለ እንደነበር የገለፀው ይኸው የቤተሰባችን አባል ከበቆጂ ከተማ ወጣ ባለ ስፍራ በከተከፈ ድንገተኛ ጥቃት ሁለት የኦሮሚያ ፖሊስ አባላት መገደላቸውን ጠቁሟል።

ከዚህ በተጨማሪ ስሜ ፥ የተባለ የበቆጂ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል በቆጂ ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ የታጠቀ ኃይል ፖሊስ ጣብያ ሰብሮ እስረኞችን ማስመለጡንና ወዳልታወቀ ቦታ እንደወሰዳቸውን ጠቁሟል። በጥቃቱ ወደ ሶስት ፖሊሶችን እንዲሁም ሌሎች ሰዎችም መገደላቸውን አመልክቷል።

የበቆጂ ከተማን በተመለከተ ስለተከፈተው ጥቃት እና ስለደረሰው ጉዳት በመንግስት በኩል የተሰጠ መረጃ የለም።

ከዚህ ቀደም በኦሮሚያ ክልል ቢሾፍቱ፣ እንዲሁም በወለንጪቲ ከተማ የታጠቁ ኃይሎች ከተማ ድረስ ዘልቀው በመግባት ተኩስ በመክፈት ሰዎችን መግደላቸውና እስረኞችን ከማስመለጥ ሙከራ ማድረጋቸው መነገሩ አይዘነጋም።

የኦሮሚያ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ኮሎኔል አበበ ገረሱ በበቆጂ ጨምሮ በቢሾፍቱ፣ ወለንጪቲ ስለተፈፀሙት ጥቃቶች ከሪፖርተር ጋዜጣ ተጠይቀው " የተባለውን ዓይነት የተደራጀ ጥቃት በየትኛውም አካባቢ አልተፈፀመም " ያሉ ሲሆን " አልፎ አልፎ #ሽፍታ ወይም #ሌባ ሊኖር ይችላል እንጂ ጥቃት የሚባል ነገር የለም። ሁሉም አካባቢ ሰላም ነው " ብለዋል።

Credit : Reporter Newspaper ,

የህወሃቱ ስብሰባ ምን ውጤት ያመጣ ይሆን፤ ለለውጥ አዲስ ምዕራፍ ይከፍታልን?የህወሃት አመራሮች እስከታችኛው ድረስ ሰብሰብ ብለው የሽግግር ሂደቱ ላይ ያላቸውን ሚና ለመገምገም ቀጠሮ ይዘዋል። ...
19/05/2023

የህወሃቱ ስብሰባ ምን ውጤት ያመጣ ይሆን፤ ለለውጥ አዲስ ምዕራፍ ይከፍታልን?

የህወሃት አመራሮች እስከታችኛው ድረስ ሰብሰብ ብለው የሽግግር ሂደቱ ላይ ያላቸውን ሚና ለመገምገም ቀጠሮ ይዘዋል። ውይይቱ በመቀሌ ከተማ የሚካሄድ ሲሆን እለቱም ነገ ግንቦት 12/2015 ዓ/ም መሆኑን ሰምተናል። በዚህ ውይይት ላይ ከ500 በላይ የህወሃት አባላትና አመራሮች እንደሚሳተፉ ይጠበቃል። ስብሰባውን እንደሚመሩ የሚጠበቀው አኩራፊው ዶ/ር ደብረፂዮን (የህወሓት ሊቀመንበር) እና ፈትለወርቅ (ሞንጀሪኖ)(የህወሓት ስራ አስፈፃሚ እና የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል) መሆናቸውን አፈትልከው የወጡ መረጃዎች ይናገራሉ፤ ስብሰባው የሽግግር መንግስቱ ውስጥ ህወሃት የነበረውን ሚና ለመገምገም እንደተጠራ ለአባላትና አመራሮች የሚነገር ቢሆንም ዋናው አላማ ከመስመራችን አፈንግጧል በሚል ጥርስ የነከሱበተን የጌታቸው ረዳ ቡድን በማሸማቀቅ ወደሚፈልጉት አቅጣጫ ለማስገባት ታሰቦ እንደሆነ እየተነገረ ይገኛል።

በዚህ ሂደት ውስጥ የነጌቾን ቡድን ለመምታት የተደራጁት አሮጊቶቹ ህወሃቶች ቀላል መልስ ምት እንደማያጋጥማቸው መገመት ይቻላል። በአሮጊቶቹ የተማረረው ወጣቱ የህወሃት ክንፍ እነ ደፂ በየስብሰባው የሽግግር አስተዳደሩን የመተቸት አካሄድ ቅሬታ እየፈጠረበት ቢሆንም እስኪ ጊዜ ይሰጣቸው በሚል ታዝቦ ሲመለከታቸው ቆይቷል።

ይሁን እንጂ አሁን ላይ ሊበቃቸው ይገባል በሚል ጊዜ እየጠበቀላቸው መሆኑን ሰምተናል፤ ምናልባት ይህ ስብሰባ አሮጊቶቹ ከጠበቁት በተቃራኒ ለራሳቸው ጦስ ይዞ እንዳይመጣ ስጋት ያላቸው የሽማግሌዎቹ ቡድን ሰዎች እንዳሉ ሰምተናል። ዙሩን አታክርሩት የሚል ምክር ቢጤ የሰጡም አልጠፉት።

ለማንኛውም የነገው የህወሃት ስብሰባ ዱላ ቀረሽ እንደሚሆን ይጠበቃል፤ ተስፋ እናደርጋለን ጭቅጭቁ በአዳራሹ ተገድቦ ይጠነቃቃል።

አመራር በመግደል የአማራ ክልልን ችግር መፍታት አይቻልም - ዶ/ር ይልቃል ከፋለ“ፈተናዎችን ወደ እድል በመቀየር ህዝባችንን እናሻግራለን” በሚል መሪ ቃል የከፍተኛና መካከለኛ አመራር ኮንፈረን...
18/05/2023

አመራር በመግደል የአማራ ክልልን ችግር መፍታት አይቻልም - ዶ/ር ይልቃል ከፋለ

“ፈተናዎችን ወደ እድል በመቀየር ህዝባችንን እናሻግራለን” በሚል መሪ ቃል የከፍተኛና መካከለኛ አመራር ኮንፈረንስ በባህር ዳር ተጀምሯል።

በኮንፈረንሱ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ክቡር ዶ/ር ይልቃል ከፋለ ክልሉን መሪ በማሳጣትና የክልሉን ህዝብ ሰላም በመናድ የሚመጣ ውጤት አይኖርም ያሉ ሲሆን አመራር በመግደል የአማራ ክልልን ችግር መፍታት አይቻልም ሲሉ ተናግረዋል ።

ርዕሰ መስተዳድሩ አያይዘውም ለህዝብ የገባናቸውን ቃሎች ቆጥረን ለመፈጸም ርብርብ ማድረግ ይገባል ያሉ ሲሆን በጽንፈኞች አጀንዳ እየተመራን ከልማት እና ከብልጽግና ጉዟችን ልንገታ አይገባም ብለዋል።

ያጋጠመን ችግር ውስብስብና አስቸጋሪ ነው ያሉት ዶ/ር ይልቃል ይህንኑ በጥልቀት በመገምገም እና ለመፍትሔዎቹ አቅጣጫ የሚያስቀምጥ ኮንፈረንስ በማስፈለጉ ምክንያት መድረኩ መዘጋጀቱን ተናግረዋል።

ብልጽግና ፓርቲ የአማራን ህዝብ ጥያቄዎች ለማስመለስ በሂደት ላይ ያለና ለተፈጻሚነቱ እየተጋ ያለ ፓርቲ መሆኑንም ገልጸዋል።

የአማራ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ዶ/ር ጋሻው አወቀ በበኩላቸው የአማራ ህዝብ መሰረታዊ ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ ሰላማዊ እና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መልኩ ትግል ይደረጋል ብለዋል።

በክልሉ የገጠመንን ችግር በውል ተረድቶ ወደ ዕድል በመቀየር ከልሉን በብቃት የሚመራ ፓርቲ እና መንግስት በመኖሩ ለዚሁ ዓላማ የሚታገል ቁርጠኛ አመራር እና አባል እንዲሁም ህዝብን የሚያነሳሳ የሚዲያ እና ኮምዩኒኬሽን ስራ ይሰራልም ሲሉ ዶ/ር ጋሻው ተናግረዋል፡፡

ኮንፈረንሱ ለመላው የፓርቲው አመራር እና አባል በክልሉ ወቅታዊ ሁኔታዎች ላይ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ያለመ መሆኑን የተናገሩት ዶ/ር ጋሻው ጠንካራ የፖለቲካ እሳቤና የተስተካከለ የፖለቲካ ትግል ማድረግ ይጠበቅታልም ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ከ1ሺህ 400 በላይ በክልሉ የሚገኙ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች ተሳታፊ መሆናቸውም ተገልጿል።

ኮንፈረንሱ በቅርቡ ህይወታቸውን ላጡት ለአቶ ግርማ የሽጥላ እና አብረዋቸው ለተሰው ወንድሞች የጧፍ ማብራት ስነ ስርዓት በማካሄድ ተጀምሯል።

ከዛሬ ሐሙስ ግንቦት 10/2015 ዓ/ም ጀምሮ ለተከታታይ ቀናት የሚካሄድ ኮንፈረንስ መሆኑም ተገልጿል።

ኮንፈረንሱ "ፈተናዎችን ወደ ዕድል በመቀየር ህዝባችንን እናሻግራለን" በሚል መሪ ቃል ይካሄዳል።

መረጃው፦ የአማራ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ነው።

የአማራ ክልል ብልፅግና ፓርቲ መግለጫ"ፈተናዎችን ወደ እድል በመቀየር ህዝባችንን እናሻግራለን” በሚል መሪ ቃል የአመራር ኮንፈረንስ ከግንቦት 10 ቀን ጀምሮ ይካሄዳል - የአማራ ክልል ብልፅግ...
17/05/2023

የአማራ ክልል ብልፅግና ፓርቲ መግለጫ

"ፈተናዎችን ወደ እድል በመቀየር ህዝባችንን እናሻግራለን” በሚል መሪ ቃል የአመራር ኮንፈረንስ ከግንቦት 10 ቀን ጀምሮ ይካሄዳል - የአማራ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት

ከነገ ሐሙስ ግንቦት 10/2015 ዓ/ም ጀምሮ በአማራ ክልል ወቅታዊ ሁኔታዎች እና የቀጣይ መፍትሔ አቅጣጫዎች ላይ የሚመከር ኮንፈረንስ ሊካሄድ መሆኑን የአማራ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡

የፓርቲው የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ዶ/ር ጋሻው አወቀ ኮንፈረንሱን አስመልክተው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ "ፈተናዎችን ወደ ዕድል በመቀየር ህዝባችንን እናሻግራለን" በሚል መሪ ቃል በክልሉ የሚገኙ የከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች ኮንፈረንስ ይካሄዳል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በክልሉ አስተማማኝ ሰላም እንዲሰፍን ማድረግ እና የተጀማመሩ የልማት ስራዎችን አጠናክሮ በማስቀጠል የክልሉን ህዝብ ተጠቃሚነት ማሳደግ ዓላማ ያደረገ ኮንፈረንስ መሆኑን በመግለጫው ተመላክቷል፡፡

የአማራ ህዝብ መሰረታዊ ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ ሰላማዊ እና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መልኩ ትግል ይደረጋል ያሉት ኃላፊው ኮንፈረንሱ የአማራ ክልልን ወደ ፊት ለማስፈንጠር ግብ አስቀምጦ ይመክራል ብለዋል፡፡

ኮንፈረንሱ ለመላው የፓርቲው አመራር እና አባል በክልሉ ወቅታዊ ሁኔታዎች ላይ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ያለመ መሆኑን የተናገሩት ዶ/ር ጋሻው አመራሩ ጠንካራ የፖለቲካ እሳቤና የተስተካከለ የፖለቲካ ትግል ማድረግ ይጠበቅታልም ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በኮንፈረንሱ ከ1ሺህ 400 በላይ በክልሉ የሚገኙ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች የሚሳተፉ ሲሆን ይህንኑ የሚመጥን በቂ ቅድመ ዝግጅት መደረጉም ተገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ ህገ መንግስት "መደበኛ ባልሆነ መንገድ" መሻሻል መጀመሩን ሰላም ሚንስቴር ተናገረ!የኢትዮጵያ ህገ መንግስት "መደበኛ ባልሆነ መንገድ" መሻሻል መጀመሩን የሰላም ሚንስትር ዴኤታ ስዩ...
17/05/2023

የኢትዮጵያ ህገ መንግስት "መደበኛ ባልሆነ መንገድ" መሻሻል መጀመሩን ሰላም ሚንስቴር ተናገረ!

የኢትዮጵያ ህገ መንግስት "መደበኛ ባልሆነ መንገድ" መሻሻል መጀመሩን የሰላም ሚንስትር ዴኤታ ስዩም መስፍን (ዶ/ር) ተናግረዋል።

የኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት ለውጥ ያስፈልገው ይሆን? ከሆነስ የትኞቹ ድንጋጌዎች በሚል የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲቲዩት ጥናት አካሂዷል።የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲቲዩት ባደረገው ጥናት ማብሰሪያ ላይ የሰላም ሚንስትር ዴኤታ ስዩም መስፍን (ዶ/ር) ምንም እንኳን ህገ መንግስቱ አልተሻሻለም ይባል እንጂ የተለያዩ አንቀጾች በአዋጅና በትርጉም እንዲሁም በሌላ መንገድ ተሻሽለዋል ብለዋል።

ህገ መንግስቱ በመደበኛም ይሁን በኢ-መደበኛ መንገድ እንደሚሻሻል የጠቀሱት ሚንስትር ዴኤታው፤ ህገ መንግስቱ ሙሉ ሊሆን እንደማይችል ተናግረዋል። የፌዴራሉ አባል ክልሎችን የሚደነግገው አንቀጽ 47 ስለመሻሻሉ ጠቅሰዋል።

የፌዴራልና የክልል የጋራ ገቢዎች የሚወስነው አንቀጽ 58 እንዲሁም መሬት አስተዳደርን የሚደነግገው አንቀጽ 89 እና ሌሎች አንቀጾች መሻሻላቸውን ስዩም መስፍን (ዶ/ር) አንስተዋል።ህገ መንግስቱን በሚመለከት ሦስት አይነት ምልከታዎች አሉ ያሉት ሚንስትር ዴኤታው፤ "ህገ መንግስቱ ረብ የለውም፣ በፍጹም መነካት የለበትም እንዲሁም ሁሉንም ባካተተ መልኩ ይሻሻል" የሚሉ ለየቅል ሀሳቦች መኖሯቸውን ተናግረዋል ሲል አሚኮ ዘግቧል።

ሚንስትር ዴኤታው "ጠቃሚው ሀሳብ ሁሉንም ባካተተ መልኩ ይሻሻል" የሚለው እንደሆነ አንስተዋል።ህገ መንግስቱን ማሻሻል እጅግ አስፈላጊ እንደሆነ ያነሱት ስዩም መስፍን (ዶ/ር)፤ የማይሻሻል ከሆነ ጥያቄ የሚያነሱ አካላት ሙሉ በሙሉ በኃይል የመቀየር እንቅስቃሴ እና ፍላጎት ሊያሳዩ እንደሚችሉ ገልጸዋል።

ህወሓት ለምርጫ ቦርድ ውሳኔ ምላሽ እንደሚከተለው ሰጥታለችየኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የድርጅታችን ህ.ወ.ሓ..ት ህጋዊ ሰውነት የመመለስ ጥያቄ አስመልክቶ በሰጠው ውሳኔ ላይ ከህ.ወ.ሓ.ት ...
17/05/2023

ህወሓት ለምርጫ ቦርድ ውሳኔ ምላሽ እንደሚከተለው ሰጥታለች

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የድርጅታችን ህ.ወ.ሓ..ት ህጋዊ ሰውነት የመመለስ ጥያቄ አስመልክቶ በሰጠው ውሳኔ ላይ ከህ.ወ.ሓ.ት የተሰጠ መግለጫ

ውሳኔው በፎቶ ተያይዟል

 # አሳዛኝ ክስተት😭😭ለበቀልም ለፍርድም አትቸኩሉ!!!   ውሻው ለባለቤቷ ቤተኛ እጅግ ለማዳና ታማኝ ነው። በዚህም የተነሳ እናት የሆነ ቦታ ለመሔድ ከፈለገች ያለ ምንም መሳቀቅ ህፃኑን ከውሻ...
16/05/2023

# አሳዛኝ ክስተት😭😭
ለበቀልም ለፍርድም አትቸኩሉ!!!

ውሻው ለባለቤቷ ቤተኛ እጅግ ለማዳና ታማኝ ነው። በዚህም የተነሳ እናት የሆነ ቦታ ለመሔድ ከፈለገች ያለ ምንም መሳቀቅ ህፃኑን ከውሻው ጋር በመተው የፈለገችበት ቦታ ደርሳና ሐጃዋን ከውና አጠናቃ ትመለሳለች ስትመለስም ልጇ ከውሻው ጋር እየተጫወተ ወይም በእቅፉ ውስጥ ተኝቶ ታገኘዋለች።

አንድ ቀን ግን እንደጠበቀችው ሳይሆን ጉዳይዋን ከውና ስትመለስ ከወትሮው የተለየ አስደንጋጭ ክስተት ጠበቃት በዓይኗ ያየችውን አሰቃቂ ክስተት ማመን አልቻለችም ። አካባቢው በደም አበላ ተነክሯል ወለሉ አካባቢው የህፃኑ ዳይፐር ሳይቀር በደም ጨቅይቶ ተዝረክርኳል።

ለማመን አልቻለችም እግሯን ብርክ ያዘው ግድግዳውን ተደገፈች በዚህ መሀል ውሻው ቀስስ ብሎ ከአልጋው ስር ብቅ አለ በድንጋጤ ወደኋላ ሸሸች ያ ታማኝ ውሻዋ አፉና መላው ሰውነቱ በደም ተነክሯል እንዴት !? አለች በብስጭት ልጄን! ብላ ጮኸች ጮኻም አላቆመችም በውሻው ላይ የበቀል የብስጭት የንዴት እጆቿን ክፉኛ ሰነዘረች።

ከማድ ቤት የብረት ዘንግ በማምጣት ውሻውን እንዳይድን አድርጋ ቀጥቅጣ ለህልፈት ዳረገችው የልጄን ገዳይ ተበቀልኩት በሚል ስሜትም ትንሽ ዕርካታ ነገር ተሰማት፤ ከዛም እስቲ ትንሽ እንኳን የተረፈ የልጄ አካል ካለ ልፈልግ ብላ ስታፈላልግ ውሻው ከወጣበት አልጋ ጀርባ የሚያምርና በደም የተነከረ ህፃን ልጅ በጀርባው ተንጋሎ እግሩን ወደ ላይ እያወራጨ ቁልጭ ቁልጭ እዪለ ይጫወታል።

በደስታም በፀፀትም ውስጥ በመሆን አፈፍ አድርጋ አቀፈችው፤ ወደ ጎን ስትመለከት ደግሞ ትልቅ እባብ ለሁለት የተከፈለ ተቦጫጭቆ ተጥሎዋል፣ ህፃኑን ለማጥቃት የመጣ መርዛማ እባብ ነበርና ታማኙ ውሻ ህፃኑን ለማዳን ባደረገው ግብግብ እባቡን በመግደል ህፃኑን ልጅ ለማዳን ችሏል።

አንዳንዴ ነገሮችን ሳናጣራና ሰከን ሳንል የምንወስዳቸው ዕርምጃዎች ለከፋ ፀፀት ይዳርጉናል።

የኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት ለውጥ?ውድ አንባቢያን ከኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት አንቀፆች ውስጥ የትኞቹ እንዲለወጡ ትፈልጋላችሁ?====================የኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት ለውጥ ያስፈልገው ...
16/05/2023

የኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት ለውጥ?
ውድ አንባቢያን ከኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት አንቀፆች ውስጥ የትኞቹ እንዲለወጡ ትፈልጋላችሁ?
====================
የኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት ለውጥ ያስፈልገው ይሆን? ከኾነስ የትኞቹ ድንጋጌዎች በሚል የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲቲዩት ጥናት አካሒዷል።

በዚህ የጥናት ውጤት ይፋ ማድረጊያ እና መወያያ መድረክ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ምክትል አፈጉባኤ ዘሃራ ሁመድን ጨምሮ የፖሊሲ ባለሙያዎች፣ የሰብአዊ መብት ተቋማት ኀላፊዎች፣ ሚኒስቴር ዴኤታዎች እና ሌሎችም ተገኝተዋል።

በፕሮግራሙ የመነሻ ሃሳብ ያቀረቡት የኢፌዴሪ የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲቲዩት ዋና ዳይሬክተር በየነ ጴጥሮስ (ፕሮፌሰር) ሕገ መንግሥቱ ከተረቀቀበት ጊዜ አንስቶ የክርክር ምንጭ መኾኑን ጠቅሰዋል።

በተለያዩ አካባቢዎች ለሚፈጠሩ ችግሮች፣ መፈናቀሎች እና ብሔር ተኮር ግጭቶች ሕገ መንግሥቱ መሰረታዊ ድጋፍ ይሰጣል የሚሉ ሃሳቦች ይደመጣሉ፡፡ በሌላ በኩል የማንነት መሰረት ነው የሚሉም አሉ፡፡ በዚህ ምክንያት ጥናት መሥራት አስፈልጓል ብለዋል። ሕገ መንግሥቱ የሊህቃኑ ብቻ ሳይኾን የሕዝብም በመኾኑ ሁሉንም ያማከለ ሀሳብ ይዞ መጓዝ ይገባል ነው ያሉት።

በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ስዩም መስፍን (ዶ.ር) ሁሉም የሕገ መንግሥት ድንጋጌዎች በተለያየ መንገድ የሚሻሻሉበትን ሁኔታ አስቀምጠዋል። በመደበኛም ይሁን በኢመደበኛ መንገድ ሕገ መንግሥቱ እንደሚሻሻልም አስገንዝበዋል።

በምሳሌት ያነሱት 391 አንቀጽን የያዘው የሕንድ ሕገ መንግሥት 105 ጊዜ ተሻሽሏል ነው ያሉት። በመኾኑም ሕገ መንግሥቱ ሙሉ ሊኾን እንደማይችል የሌሎችን ሀገራትን ሕገ መንግሥት በመጥቀስ አንስተዋል።

ሚኒስትር ዴኤታው ምንም እንኳን ሕገመንግሥቱ አልተሻሻለም ይባል እንጂ የተለያዩ አንቀጾቹ በአዋጅ እና በትርጉም እንዲሁም በሌላ መንገድ ተሻሽለዋል ብለዋል። የፌዴሬሽን ምክርቤት ለእነዚህ ሕገ መንግሥት ማሻሻያዎች ዕውቅና ያልነፈገ በመኾኑ እንዲሻሻል እንደፈቀደ ይቆጠራል ነው ያሉት። በምሳሌነትም የፌዴራሉ አባል ክልሎችን የሚደነግገው አንቀጽ 47 ስለመሻሻሉ ጠቅሰዋል። በተመሳሳይ የፌዴራል እና የክልል የጋራ ገቢዎች የሚወስነው አንቀጽ 58 እንዲሁም መሬት ማሥተዳደርን በተመለከተ የሚደነግገው አንቀጽ 89 እና ሌሎች አንቀጾች መሻሻላቸውን አንስተዋል።

ሕገ መንግሥትን በተመለከተ በሀገር ደረጃ 3 ምልከታዎች አሉ ያሉት ዶክተር ስዩም አንደኛው ሕገ መንግሥቱ ረብ የለውም የሚል ሲኾን ሁለተኛው ደግሞ በፍፁም መነካት የለበትም የሚል ነው፡፡ ሦስተኛው ደግሞ ሁሉንም ባካተተ መልኩ ይሻሻል የሚል እንደሚገኝበት ሚኒስትር ዴኤታው ጠቅሰው ጠቃሚው ሀሳብ ሁሉንም ባካተተ መልኩ ይሻሻል የሚለው እንደኾነ አስገንዝበዋል።

ሕገ መንግሥቱን ማሻሻል እጅግ አስፈላጊ እንደኾነ ያነሱት ሚኒስትር ዴኤታው ሕገ መንግሥቱ የማይሻሻል ከኾነ ጥያቄ የሚያነሱ አካላት ሕገ መንግሥቱን ሙሉ በሙሉ በኃይል የመቀየር እንቅስቃሴ እና ፍላጎት ሊያሳዩ እንደሚችሉ አስረድተዋል። በሀገሪቱ ያሉ የግጭት እና የአለመግባባት ጉዳዮችን በቀላሉ ለመፍታትም እንዲያስችል ሁሉንም ያማከለ ሀሳብ ይዞ ቢሻሻል መልካም እንደኾነም አሳስበዋል።

ውድ አንባቢያን ከኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት አንቀፆች ውስጥ የትኞቹ እንዲለወጡ ትፈልጋላችሁ?

12/05/2023
11/05/2023

ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ ግብር የማስከፈያ ምጣኔዎች

• ከግብር ነፃ ከሆነው በስተቀር ቀጣሪው ለተቀጣሪው በሚከፍለው ማንኛውም የገንዘብ መጠን ላይ ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ ግብር ይከፈልበታል፡፡
• ቀጣሪ ማለት ተቀጣሪን የቀጠረ ወይም ለተቀጣሪው ደመወዝ የሚከፍል ሰው ነው፡፡
• ተቀጣሪ ማለት ደግሞ ራሱን ችሎ የሚሰራን የስራ ተቋራጭ ሳይጨምር በሌላ ሰው /በቀጣሪው/ መሪነትና ቁጥጥር ስር ሆኖ አገልግሎት ለመስጠት በቋሚነት ወይም በጊዜያዊነት የተቀጠረ ግለሰብ ሲሆን የድርጅት ዳይሬክተር፣ ወይም በድርጅቱ አመራር ውስጥ ኃላፊነት የተሰጠውን ሌላ ሰው እንዲሁም ተሿሚንና የህዝብ ተመራጭን ጨምሮ የመንግስት ስራ ኃላፊን ያጠቃልላል፡፡

• ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ የሚከተሉትን ይጨምራል፡፡
👉 ከሰራተኛው ቅጥር ጋር በተያያዘ ሰራተኛው የተቀበለው የደመወዝ ምንዳ፣ አበል፣ ጉርሻ፣ ኮሚሽን፣ የመልካም ስራ አፈፃፀም ማበረታቻ ስጦታ ወይም ሌላ የአገልግሎት ክፍያ፣

👉 ሰራተኛው ከቅጥር ውሉ ጋር በተያያዘ በዓይነት የሚቀበለው ማንኛውም ጥቅማጥቅም ዋጋ፣

👉 ተቀጣሪው ከስራ ሲቀነስ ወይም ከስራ ሲለቅ ወይም ስራን እንዲለቅ ለማግባባት የሚከፈል ገንዘብን ጨምሮ የስራ ውል በመቋረጡ ምክንያት በፈቃደኝነት፣ በስምምነት ወይም በዳኝነት ውሳኔ መሠረት የተቀበለ ሰው ማንኛውም የገንዘብ መጠን፣

• ቀጣሪው ለተቀጣሪው ከተከፈለው የገንዘብ መጠን ላይ ግብሩን ሳይቀንስ ከራሱ ግብሩን የከፈለ እንደሆነ የተከፈለው ግብር በተቀጣሪው ደመወዝ ላይ ተደምሮ ግብሩ ይሰላል፡፡

ለምሳሌ፡- የ4ሺ 500 ብር ተቀጣሪ ግብር ተቀንሶበት የተጣራ ደመወዙ ይህ ነው፡፡
ይህ ደመወዝ ተራ ቁጥር 4 ላይ የሚያርፍ ሲሆን ስሌቱ፡-
ተቀናሽ ግብር = የወር ደመወዝ x የማስከፈያ መጣኔ - ተቀናሽ ብር
ተቀናሽ ግብር = 4,500 x 20% - 302.50
ተቀናሽ ግብር = 597.50
የተጣራ ደመወዝ = አጠቃላይ ደመወዝ - ተቀናሽ ግብር
የተጣራ ደመወዝ = 4,500 – 597.50
የተጣራ ደመወዝ = 3ሺ 902 ብር ከ50 ሳንቲም (ይህ የጡረታ ተቀናሽን አያካትትም)

ይህን ጠቃሚ መረጃ ሼር ያድርጉ

ጠቃሚ ሰነዶች ለማውረድ ሊንኩን ይጠቀሙ👇
👉 t.me/joinchat/TE8_8RXdfIsqGEKn
👉 t.me/joinchat/TE8_8RXdfIsqGEKn
👉 t.me/joinchat/TE8_8RXdfIsqGEKn
👉 t.me/joinchat/TE8_8RXdfIsqGEKn

ሳሙኤል ግርማ
የሕግ አማካሪ እና ጠበቃ

በስልክ +251 911 190 299
በፌስቡክ 👉 Fb.me/Tebekasamuel
በ ቴላግራም 👉 T.me/Tebekasamuel


#ጠበቃ #ሕግ #ሳሙኤልግርማ #ህግ #ጠበቃሳሙኤል
0911-190-299

ethiopia news today ethiopia news 2022 ethiopia news amharic news amharic news ሰበር ዜና habesha news habesha news ሀበሻ ዜና ዜና መከላከያ

#ሀበሻ

11/05/2023

ጠቃሚ ሰነዶች ለማውረድ ሊንኩን ይጠቀሙ 👇
👉 t.me/joinchat/TE8_8RXdfIsqGEKn
👉 t.me/joinchat/TE8_8RXdfIsqGEKn
👉 t.me/joinchat/TE8_8RXdfIsqGEKn
👉 t.me/joinchat/TE8_8RXdfIsqGEKn

ሳሙኤል ግርማ
የሕግ አማካሪ እና ጠበቃ

በስልክ +251 911 190 299
በፌስቡክ 👉 Fb.me/Tebekasamuel
በ ቴላግራም 👉 T.me/Tebekasamuel

09/05/2023

Address

Addis Ababa

Telephone

+251912230944

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio News -ኢትዮ መረጃ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Share



You may also like