24/05/2024
የዕጩ ዶክተሩ የመጨረሻ ማስታወሻ !!!
ሞት የማይቀር ዕዳ መሆኑን ባውቅም ቀጠሮ ተሰጥቶት ቀን ሲቆረጥ ግን ያስፈራል! ይገርማል! ሞት እንዲህ ያስፈራል ? በጣም ፈራሁ !መኖር ለካ እንዲ ያጓጓል ? በእውነት ጓጓሁ ! ፤ ልጆቼ አሳሱኝ! እንደ አዲስ ናፈቁኝ ! ትንሹ ወንድ ልጄ ! እህቶቹ ፤ ውዴ ፣ ጓደኞቼ ፣ዘመዶቼ ፣ የልጅነት አብሮ አደጎቼ ፤ባልደረቦቼ ፣የሀገሬ ልጆች ያደኩበት መንደር ሁሉም ናፈቁኝ ! እጣፈንታዬን ረገምኩት !
ወንድሞቼ ሆይ ዛሬ ጭላንጭል የመኖር ዕድል እና ዘላለማዊ እንቅልፍ በህይወቴ ተፋጠዋል ። ሁለት ምርጫ ይባል እንጂ ነገሩስ ምርጫ አይደለም ። ለአንድ ተራ አስተማሪ ሚሊዮን ብር ከፍሎ ህይወቱን ማዳን እንዴት ይቻለዋል ? ከፍቶኛል! ሆድ ብሶኛል ! ! ወንድማችሁ በጥልቅ ሀዘን ውስጥ ነኝ ።
ግን ሀዘኔን ለማን ልስጥ ? ሰው ተቸግሯል ! የቸገረውን ሰውስ ምን ብዬ ላስቸገር ? ግን ነብስናትና ጨነቀኝ !! ያለኝን ሀብትና ንብረት በመሸጥ የኩላሊት እጠበት በሳምንት ሦስቴ እያደረኩ ከልጆቼ ጋር ያለኝን እድሜ ላማራዝምና ህይወቴን ለማቆየት ሞከርኩ ጣርኩ ! ወዳጆቼን ፣ ጓደኞቼን አስቸገርኩ ያው ትርፉ መከራን በቤተሰቤና ወዳጆቼ ላይ ማዝነብ ሆነ ፤ የእውነት !አሁን ደከመኝ ! አልቻልኩም ! የጥቁር አንበሳ ሆስፒታልም ከንግዲህ በዲያሊስስ መቆየት አትችልም አቅሙ ካለህ ወደ ውጪ ሄደክ... አለኝ ። ወይ አቀም ! እቅሜና ተስፋዬ አምላኬና ወገኖቼ ብቻ ናቸው ። ዝም ካላችሁኝ በዝምታ አንቀላፋለሁ ከራራላችሁልኝ ደግሞ በእናንተ በኩል ይሰራል !
የሆነ ጊዜ ያነበብኩት አንድ የመቃብር ላይ ጽሁፍ ትዝ አለኝ ጽሁፉ " አሞኛል ብዬ ነግሪያችሁ ነበር " ይላል
ያው እኔም ቢቀለኝ ብዬ ነው የነገርኳችሁ ።
ወንድሞቼ ሆይ አሞኛል !
ከፉ ደዌ ከምወዳቸው ልጆቼ ሊለየኝ ነውና እርዳታችሁ ያስፈልገኛል ! በፍጹም ተስፋ አልቆርጥም ህይወቴ እስካለች ተስፋ አደርጋለሁ ግን
አ ሞ ኛ ል ቢሆንም ከህመሜ ድኜ ዶክትሬቴን ተቀብዬ ለምስጋና በዚሁ እመለስ ይሆናል !?
እሱ ካለ ?🤲
ሀብት ንብረት የለኝም ያፈራሁት ሀብት ልጆቼ ተማሪዎቼ ብቻ ናቸው !
ወንድማችሁ እጩ ዶ/ር መ/ር አዲሱ ዳንኤል
ከአርባምንጭ ትምህርት ኮሌጅ !
ስልክ+251916881107
መረጃውን ሼር በማደረግ ድጋፋችንን እንጀምር !
ስም= አዲሱ ዳንኤል ሻሎ
የባንክ አካዉንት
1. ንግድ ባንክ
1000032842392
2. አብስንያ ባንክ
S/A 5442672
3. ቡና ባንክ
1869501007218