Iftu Abdella

Iftu Abdella ፍቅር

10/06/2024
10/06/2024
02/06/2024

የፅንፈኝነት አስተሳሰብን በማረም ህብረብሔራዊ አንድነትን እናፀናለን!

ጽንፈኝነት የነጠላ ትርክት ላይ ብቻ በመንጠልጠል በየእኔ ብቻ አመለካከት የታጠረ ህብረብሔራዊነትንና የወል ዕውነቶችን የማይቀበል አፍራሽ አስተሳሰብ ነው።፣ የእኔ ብቻ ትክክል ነኝ የሚልና ከእዛ ውጭ ያሉ ዕይታዎች ሁሉ እውነት አይደሉም ብሎ የሚያስብ የነጠላ ትርክት ዕሳቤ ነው ጽንፈኝነት።

ፓርቲያችን ብልጽግና የነጠላ ትርክቶችን በማረም አካታችና ሁሉን ዓቀፍ የሆ የፖለቲካ ስርዓትን መነሻ አድርጎ ኢትዮጵያን በህብረብሔራዊ አንድነት ለማጽናት እየሰራ ይገኛል። ጽንፈኝነትን በመከላከል ብሔራዊ ገዥ ትርክትን በማስረጽ ለትውልድ የምትመችና የበለፀገችዋን ኢትዮጵያ ለማየት የሁላችንንም ጥረት የሚጠይቅ ነው።

ብልጽግና የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ዕውንነት አብቦ የብሔር የሕዝቦች መስተጋብራዊ አንድነት ይበልጥ ተጠናክሮ እንዲቀጥልና የጋራ ብልፅግናን ማስፈን እንዲቻል ሁሉም ዜጋ በመደመር ዕሳቤ የወል ዕውነቶችን ማጽናትና ማስቀጠል ይገባል። ችግሮቻችን ሁሉ በወንድማማችነትና እህትማማችነት በጋራ በመፍታት ከዋልታረገጥ አስተሳሰብ በመላቀቅ የጋራ የሆነች የበለጸገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ።

https://heylink.me/YEKAPROSPERITYPARTY/

20/05/2024

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከመስከረም 24 ቀን 2015 ዓ.ም እስከ መስከረም 24 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ያደረጏቸው ንግግሮች እና ያስተላለፏቸው መልእክቶችን የያዘው 'ከመስከረም እስከ መስከረም' መጽሕፍ ዛሬ ይፋ ይሆናል::

20/05/2024

ዘመኑን በዋጀ ዕሳቤና ትጋት ትውልድ ተሻጋሪ መሰረት በመጣል አድስአበባን የአፍሪካ የብልጽግና ተምሳሌት ከተማ እናደርጋለን!

13/05/2024

የሀገር መገንቢያ መንገድ ትውልድን በማነፅ ውስጥ ያለው ሚስጥር ነው!

መደመር በለውጥ መንገድ ላይ የተወለደ የአተያይ ፓራዳይም ነው። ቁስሎች እንዲጠገኑ፣ ህመሞች እንዲድኑ፣ ችግሮች እንዲፈቱ፣ ፈተናዎች እንዲታለፉ፣ ያለፈውን ጉዟችንን መመልከቻና የቀጣይ ጉዟችን ጠቋሚ፣ አዲስ የእሳቤ ማዕቀፍ ነው።
..የመደመር ነገ_ ትውልድ ነው። እርግጠኛ የሀገር መገንቢያ መንገድም ትውልድን በማነፅ ውስጥ ያለው ሚስጥር ነው። የዛሬ መልካም ውጤቶችና እሴቶች ቀጣይነት የሚረጋገጠው በትውልድ ውስጥ ሲሰርጹ ነው። የመደመር ግብ ሀገር የሚያጠናክር እሴትና ባህል መገንባት ስለሆነ፤ ራሱን ትውልድ የሚግባባበትና የሚነጋገርበት ቋንቋ ለማድረግ ይተልማል። በፍቅር፣ በወንድማማችነትና በኅብር የሚግባባ ትውልድን ለማነጽ።

መደመር የዛሬን ትውልድ አቅም በማሰባሰብ፣ ካለፈው ትውልድ የወረሳቸውን ጥንካሬዎች በማሳደግ፣ እንዲሁም ክፍተቶችን በማረም፣ የቀጣዩን (የመደመር) ትውልድ የምንመለከትበት የሃሳብ መነጽርና የመግባቢያ ሰነዳችን ነው። ይህ የትውልድ ግንባታ እውን እንዲሆን፤ በተገዳዳሪ አፍራሽ እይታዎች (ፓራዳይሞች) ውስጥ የመደመር እይታንና እሴትን ያለማሰለስ በትጋት ማስረፅና ማጠናከርን ይጠይቃል።

(ከመደመር ትውልድ መፅሀፍ ከገፅ V_VI የተወሰደ)
በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ /ፅ/ቤት
መልካም የስራ ሳምንት ይሁንላችሁ!

09/05/2024

ሰው ተኮር በሆኑ ልማቶች ለክ/ከተማችን ሁለንተናዊ ለውጥ በጋራ እንተጋለን!

አቶ መገርሳ ገላና
የየካ ክ/ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሀላፊ

የፓርቲያችን መርህና ዕሴት በሆነው ሰውን ማዕከል ያደረጉ የልማት ስራዎች የካን የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግና በሁለንተናዊ ማህበራዊ ተጠቃሚነት ነዋሪዎቿን ተሳታፊና በማድረግ አመርቂ ዕምርታዎች ተመዝግበዋል። ከዚህ አኳያ ፓርቲያችን ብልጽግና የህዝብን ቀጥተኛ ተጠቃሚነት ባረጋገጠ መልኩ በርካታ ሰውተኮር ፕሮጀክቶችን ጨምሮ የክ/ከተማችንን ሁለንተናዊ ገፅታ ከመቀየር ባሻገር የጎላ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ያለው የኮሪደር ልማት በመስራት ላይ ነው።

በብልጽግና ፓርቲ ታቅደውና ተነድፈው እየተተገበሩ የሚገኙ ሰውተኮር ተግባራቶችና መሰረተልማቶች የካን ብሎም አዲስ አበባን የብልፅግና ተምሳሌት ለማድረግ የተጀመረውን ሁለገብ እንቅስቃሴና ትጋት የሚያሳይና ለመጭው ትውልድ ዕዳን ሳይሆን ምንዳን ለማሻገር የሚያመለክት መሆኑን ነው።

የፓርቲያችን መሰረት ሰው ስለሆነ ህዝብን ማዕከል ባደረገ የልማት ስራ የአዲስአበባን ስምና ክብር በሚመጥን ለውጥ የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ የተጀመሩ ሰፋፊ ስራዎች ላይ በልዩ ትኩረት መትመምና መትጋት ይጠበቃል። በመሆኑም በወንድማማችነትና እህትማማችነት ዕጅ ለዕጅ ተያይዘን ከተማችን ወደሚመጥናት ብልጽግና የምታደርገውን ጉዞ ማጠናከር ይገባል።

ሁለንተናዊ ተምሳሌትነት ለማረጋገጥና የነዋሪዎችን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ሁሉንአቀፍ ሰው ተኮር ልማቶችን በማሳለጥ ትብብርና አብሮነትን ማጠንከር ይጠበቃል። በብልጽግና የህዝብን ፍላጎትና ተጠቃሚነት ባከበረ መልኩ ለክ/ከተማችን ሁለንተናዊ ለውጥ በጋራ በመትመም በትኩረት በመሰራት ሁሉም የልማት ስራዎች በዜጎች ላይ ተጨባጭ ለውጥ እንዲያመጡ ታቅደው በታሰበላቸው ፍጥነትና ጥራት እየተከወኑ ናቸው።

በአጠቃላይ አደናቃፊና አሳሪ ከሆኑ ዕሳቤዎች በመላቀቅ የክ/ከተማችንን ገፅታ በመቀየር የከተማችን ስምና ታሪኳ ወደሚመጥናት ከፍታ በማሻገር ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ፍትሃዊነትና ተጠቃሚነት የተረጋገጠባት ተምሳሌታዊት ከተማን እንገንባ። ሰላማችንን በጋራ፣ ልማታችንን በህበረት አድርገን በህብረብሔራዊ አንድነት ፀንተን የወል ዕውነቶቻችንን መሰረት ባደረገ ብሔራዊ ገዥ ትርክት ከዕዳ ወደምንዳ መሻገርና ለከተማችን ሁለንተናዊ ለውጥ መትጋት ያስፈልጋል።

https://heylink.me/YEKAPROSPERITYPARTY/

04/05/2024

የጋራ ግብረ-ኃይሉ በዓሉ ያለምንም የፀጥታ ችግር በሰላም እንዲከበር ዝግጅት ማጠናቀቁን ገለጸ!

የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይል ሕዝበ ክርስቲያኑ ትንሣኤን በዓል ያለምንም የፀጥታ ችግር በሰላም እንዲያከብር በሁሉም ክልሎች እና በሁለቱም ከተማ አስተዳደሮች ዝግጅቱን አጠናቆ ወደ ተግባር መግባቱን አስታወቀ፡፡

ሕዝቡም ሰላምና ደኅንነትን ለማረጋገጥ በሚካሄደው የፀጥታ ማስከበር ሥራ ውስጥ በባለቤትነት እያደረገ ያለውን ተሳትፎ የበለጠ አጠናክሮ በመቀጠል የአካባቢውን ሰላምና ደኅንነት የሚያውኩ አጠራጣሪ ነገሮችን ሲመለከት ለፀጥታ አካላት ጥቆማ በመስጠትና አስፈላጊውን ትብብር በማድረግ ከጋራ ግብረ-ኃይሉ ጎን በመሆን የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ጥሪውን አቅርቧል።

ግብረ-ኃይሉ ለመላው የክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልካም ምኞቱንም አስተላልፏል።

04/05/2024

መልካም የስቅለት በዓል!!

ብልፅግና ፓርቲ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ መልካም በዓልን ይመኛል።

የኢትዮጵያ መከላከያ ጠንካራ ሰራዊትን በመፍጠር ከአፍሪካ ቀዳሚ ሆኗል
03/05/2024

የኢትዮጵያ መከላከያ ጠንካራ ሰራዊትን በመፍጠር ከአፍሪካ ቀዳሚ ሆኗል


19/04/2024

ብልፅግናን ማረጋገጥ ለኢትዮጵያ እና ለህዝቦቿ የእድገት፣ የብርሃን፣ የልምላሜ እና የከፍታ ዘመን እንዲመጣ መትጋት ነዉ!!

ብልፅግና የመደመር ውጤት ነው፤መደመር መንገዳችን ብልፅግና መዳረሻችን ስንል ዋናው አላማችን ኢትዮጵያ ሀገራችን ባለፉት የለውጡ አመታት ፓርቲያችን ብልፅግና በነደፈው የመደመር እሳቤ ባስመዘገበቻቸው የፖለቲካና የማህበራዊ ሁለንተናዊ ድሎችን ማስፋት በለውጡ አጥቢያ ላይ ለሀገራችን ህዝቦች በገባነው ቃል መሠረት የተሰሩ ደረጃ በጀረጃ የታቀዱ ተግባራትን በመፈጸም ስህተቶችን የዘመናት ጥያቄዎችን በመመለስ ሂደት ውሰጥ የሚኖሩ ስህተቶችን ያለምሬት በማረም ለቀጣይ ትውልድ ምንዳን እንጂ እዳን ላለማውረስ የመደመር እሳቤን በሙሉ አቅም ወደተግባር በመቀየር የኢትዮጵያ ሀገራችን ትንሳኤ ማሳካት ማብሰር የዚህ ትውልድ ትልቅ የቤት ስራ ነው

በመሆኑም የመደመር እሳቤያችንን በተቀመጠለት ሂደት ከዳር ለማድረስ በሚደረግ ርብርብ አደናቃፊ የሆኑ እና የፓርቲያችን ቀይመስመር ተብለው በደማቅ የተፃፉትን ሀረጎችን በፅኑ ትግል ላይ መርህን መሠረት በማድረግ መደመርን መንገዳችን መድረሻችን ሁለንተናዊ ብልፅግናን በማረጋገጥ ለኢትዮጵያ እና ለህዝቦቿ የእድገት፣ የብርሃን፣ የልምላሜ እና የከፍታ ዘመን እንዲመጣ ከጨለማ ወጥተን ብሩህ የሆነውን ብርሃን ማየት የጋራ ህልማችን በመሆኑ በመደመር እሳቤ ወደ ብልፅግና ጎዳና በህብረት መጓዝ ይጠበቅብናል፡፡

https://heylink.me/YEKAPROSPERITYPARTY/

13/04/2024

Ida'amuu, Daandii Milkaa’hinaa!

Daandichi diriiraa fi baldhaadha. Isa kaayyoo fi galma qabu hunduma imalchiisa. Hin qoodu, hin dhiibu, hunda hammataadha.
Daandiin baldhaa fi diriiraan bakka yaadan ariitiin gahuuf mijataadha. Kunis baay’ina , qulqullina, ariitii fi kalaqaan waan jalqabe saffisiisee galma isaa milkeessa.

Gufuuleen akka naannummaa, gosummaa fi dhibaa’ummaa ammoo daandicha ni dheeressu, yeroon galma yaadan bira qaqqabuuf qormaata ta'u. Imala eegalame dhaabuuf garuu humnas ta'ee gahumsa hin qabanu.

Ida’amuun daandiidha. Galmi isaa badhaadhina hunda galeessa dhugoomsuudha. Agarsiistotni milkaa’ina galmichaas federaalizimiin dhugaa diriiree ofiin of bulchuu fi hiree ofii ofiin murteeffachuu , qabeenya, aadaa fi duudhaa ofiitti sirnaan fayyadamuu fi ibsachuun kan itti nuuf isaan ijoodha.

Dirreen dimokiraasii baldhachuun namuu diriirfatee akka bobba’u, hojjatee akka of danda’uu fi qabeenya horachuu, kunuunfachuu fi waan barbaade gaafatee deebii argachuu akka danda’u daandii kanatu akeeke.

01/04/2024

የከተማዋን የስራ ባህል የቀየረው የኮሪደር ልማት ስራ ዛሬም በየካ ክ/ከተማ 7/24 ተጠናክሮ ቀጥሏል

አዲስ አበባን ክብሯንና ስሟን የሚመጥን ከተማዊ ገፅታ ከማላበስ ባሻገር የኢትዮጵያ ብሎም የአፍሪካ የብልጽግና ተምሳሌት የሆነች ውብና ማራኪ ከተማ ለማድረግ በከተማ አስተዳደሩ ሰፋፊ ስራዎች እየተተገበሩ ይገኛል። የከተማ አስተደዳሩ የመዲናዋ ህዝቦች ሁለንተናዊ ማህበራዊ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት በማረጋገጥ በየዕለቱ አዳዲስና አንጸባራቂ የብልጽግና ውጤቶች የሚታዩባት ትሆን ዘንድ ተግቶ እየሰራ ይገኛል።

በመዲናዋ የሚገነቡ ታላላቅ ሜጋ ፕሮጀክቶችና ሰው ተኮር ተግባራት የከተማዋን ገፅታና ስም ከማደስ ባሻገር ነዋሪዎቿን የለውጡ ተቋዳሽ በማድረግ አመርቂ ዕምርታዎችን በማስመዝገብ የብልጽግና ማሳያ ተምሳሌት መሆን ችላለች።

ከዚህ አኳያ በየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የህዝብን ቀጥተኛ ተጠቃሚነት ባረጋገጠ መልኩ የኮሪደር ልማት በመተግበር ላይ ሲሆን ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ የከተማዋን ገፅታ ከመቀየር ባሻገር በርካታ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ይኖረዋል። ፕሮጀክቱ የሚሰራባቸውን የመንገድ ዳርቻ የወሰን ማስከበር ተግባር በወረዳ 05፣ 07 እና 08 የመንገድ ስራው የነዋሪውን ጥያቄ በሚፈታና ተሳታፊነታቸውን ባረጋገጠ ሁኔታ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

የመንገድ ኮሪደር ፕሮጀክቱን በተመለከተ የክፍለ ከተማው ባደረገው ውይይትመሰረት ነዋሪዎች፣ የንግዱ ማህበረሰብ፣ ኢምባሲዎች፣ የፌደራል እና የከተማ አስተዳደሩ የመንግስት ተቋማት የልማት አጋርነታቸውን በተግባር እያሳዩ ይገኛል። የኮሪደር ልማቱ ሲጠናቀቅ ከተማዋን አለም አቀፍ ተወዳዳሪ ከማድረግ ባለፈ የስማርት ሲቲ ስታንዳርድን በማሟላት የከተማዋን ገጽታ በመቀየር የነዋሪዎችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ መሆኑን አስተያየት ሰጭዎች ተናግረዋል።

በክ/ከተማችን እየተሳራ የሚገኘው ይህ የኮሪደር ልማት ፓርቲያችን ብልጽግና የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ አረጋግጣለሁ ብሎ ሲነሳ በተሳፋ ብቻ ሳይሆን የሚጨበጥና የሚታይ ራዕይና እውነትን አንግቦ መሆኑን በግልፅ የሚያሳይ ነው። በዚህም ሁለንተናዊ ከፍታን ለማረጋጋጥ በትልቁ በማሰብ ታላላቅ ፕሮጀክቶችን ከውኖ ለህዝብ አገልግሎት ክፍት ማድረግ እንደሚቻል በተደጋጋሚ ማረጋገጥ ተችሏል።

በአጠቃላይ እንደ የካ ክ/ከተማ አዲስ አበባን የብልፅግና ተምሳሌት ለማድረግ የተጀመረው ሁለገብ እንቅስቃሴ አጠናክሮ በማስቀጠል ነገን ዛሬ በመስራት ለመጭው ትውልድ ሁለንተናዊ ብልጽግናዋ የተረጋገጠ ሀገርን እየገነባን መሆኑን ማሳያ የኮሪደር ልማት ነው ።

በወንድማማችነትና እህትማማችነት ዕጅ ለዕጅ ተያይዘን ከተማችን ወደሚመጥናት ብልጽግና የምታደርገውን ጉዞ ማጠናከር ይገባል!

https://heylink.me/YEKAPROSPERITYPARTY/

01/04/2024

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Iftu Abdella posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share