𝐀𝐘𝐃𝐀𝐍

𝐀𝐘𝐃𝐀𝐍 የፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ሼር ያድርጉ ቤተሰብ ይሁኑ እናመሰግናለን ለበለጠ መረጃ :- +251912939959

16/03/2024

የተጠሙ ጉሮሮዎች
ظمأ الحناجر
The thirsty throats
🍃🍃🍃🍃🍃
Ustaz Yassin Nuru / ياسين نورو

14/10/2023

እንዲህም አይነት ታሪክም አለ😢
🇵🇸 & 🇮🇱 ⚖️
እስኪ አስተያየታችሁን ስጡ

የእስራኤል እና የፍልስጤም ሃማስ ጦርነት፤*  ምን አዳዲስ ነገሮች ተከስተዋል?   | እስራኤል የጋዛ ኢላማዎች ላይ የአየር ድብደባ ፈጽማለች፤ ሃማስ ወደ እስራኤል ሮኬት መተኮሱን ቀጥሏልበእስ...
12/10/2023

የእስራኤል እና የፍልስጤም ሃማስ ጦርነት፤

* ምን አዳዲስ ነገሮች ተከስተዋል?

| እስራኤል የጋዛ ኢላማዎች ላይ የአየር ድብደባ ፈጽማለች፤ ሃማስ ወደ እስራኤል ሮኬት መተኮሱን ቀጥሏል

በእስራኤል 1300 ሰዎች በጋዛ ደግሞ 1200 ፍልስጤማውያን እስካሁን በጦርነቱ ሞተዋል

ሃማስ ባሳለፍነው ቅዳሜ በእስራኤል ላይ ያልተጠበቀ እና ድንገተኛ ጥቃት መሰንዘሩን ተከትሎ በእስራኤልና በፍልስጤም መካከል የተጀመረው ጦርነት ዛሬ ስድስተኛ ቀኑን ይዟል።

በሃማስ ጥቃት እና በእስራኤል የአየር ድብደባ ከሁለቱም ወገኖች የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ2 ሺህ 500 ማለፉ ተነግሯል።

የእስራኤል መከላከከያ ኃይል ባወጣው መረጃ መሰረት በሃማስ ጥቃት የሞቱ እስራኤላውን ቁጥር 1300 የደረሰ ሲሆን፤ ከ3 ሺህ 300 በላይ ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል።

አሜሪካ በሃማስ ጥቃት የተገደሉ ዜጎቿ ብዛት 22 መድረሱን አስታውቃለች።

ታይላንድም በሃማስ ጥቃት በእስራዔል ውስጥ የተገደሉባት ዜጎቿ ቁጥር 21 መድረሱን ገልጻለች።

የፍልስጤም ባለስልጣናት በሰጡት መረጃ ደግሞ በእስራኤል የአየር ድብደባ የሞቱ ፍልስጤማውያን ቁጥር 1 ሺህ 200 መድረሱን የገለጹ ሲሆን፤ 5 ሺህ 600 ሰዎች ቆስለዋል።

የተመድ የስደተኞች ኤጀንሲ በእስራኤል የአየር ድብደባ 338 ሺህ ሰዎች ከጋዛ መፈናቀላቸውን አስታውቋል።

እስራኤል በጋዛ የምታካሂደውን የአየር ድብደባ ቀጥላለች፤ እስራኤል በአንድ ሌሊት በጋዛ የሚገኙ 200 ኢላማዎች መትታለች።

የእስራኤል ጦር የአየር ድብደባዎቹ የሃማስን ዋሻዎች እና ቤትዎርኮችን ኢላማ ያደረጉ መሆኑን አስታውቋል።

እስራኤል ከአየር ድብደባ በተጨማሪ በምድር ውጊያ ለማካሄድ 300 ሺህ ወታደሮቿን ወደ ጋዛ ድንበር አስጠግታለች።

እስራኤል በትናትናው እለት አዲስ “የጦርነት ጊዜ ካቢኔ" አዋቅራለች፤ ኮሚቴው ውስጥ ታዋቂው የተቃዋሚ መሪ ቤኑ ጋንዝ ተካተዋል።

ሃማስ ወደ እስራኤል የተለያዩ ክፍሎች ሮኬት መተኮሱን አሁንም ቀጥሎበታል።

እስራኤል እግረኛ ጦሯን ወደ ድንበር ማስጠጋቷን ተከትሎም፤ ሀማስ "የሚያስፈራን ነገር የለም"የሚል አስተያየት ሰጥቷል።

የቀድሞው የሀማስ ኃላፊ ካሊድ ማሻል ጎረቤት ሀገራት እየተደረገ ባለው የጸረ- እስራኤል ውጊያ እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል።

ማሻል የጆርዳን፣ የሶሪያ፣ የሊባኖስ እና የግብጽ ህዝብና መንግስታት ፍልስጤማውያንን የመርዳት ትልቅ ኃላፊነት አለባቸው ብለዋል።

ሃማስ ቡድን እስራኤል ላይ ለምን ጥቃት ከፈተ?

የሃማስ ቃል አቀባይ ካሊድ ካዶሚ በበኩሉ፤ ቡድኑ በእስራኤል ላይ የጀመረው ወታደራዊ ዘመቻ ባለፉት አስርት ዓመታት ፍልስጤማውያን ላይ ለተፈጸመው ግፍ ምላሽ ነው ብሏል።

“ዓለም አቀፍ ማህበረሰብ በጋዛ የሚፈጸመውን ግፍ እንዲያስቆም እንፈልጋለን” ያለው ቃል አቀባዩ፤ “አል ኣቀሳን ጨምሮ ቅዱሳን ስፍራዎቻችን ለዘመቻው መጀመር መነሻ ነው” ብሏል።

መሳሪያ የታጠቀ ማንኛውም ፍልስጤማዊ ጦርነቱን እንዲቀላቀል ጥሪ ያቀረበው ሃማስ፤ የዌስት ባንክ ታጣቂዎች፣ የአረብ ማህበረሰብ እና ሙስሊም ሀገራት ዘመቻውን እንዲቀላቀሉ በቴሌግራም በለቀቀው መግለጫ ጥሪ አቅርቧል።

11/10/2023
11/10/2023

ት ክ ክ ል ❤️

የልጃችን ከፍተኛ ውጤት የትጋቷ ፍሬ ነው - የተማሪ ሃናን ወላጆች ልጃቸው ትምህርቷን በሚገባ ተከታትላ ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገቧ ኩራትና ደስታ እንደተሰማቸው የ12ኛ ክፍል ከፍተኛ ውጤት ያመ...
10/10/2023

የልጃችን ከፍተኛ ውጤት የትጋቷ ፍሬ ነው - የተማሪ ሃናን ወላጆች
ልጃቸው ትምህርቷን በሚገባ ተከታትላ ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገቧ ኩራትና ደስታ እንደተሰማቸው የ12ኛ ክፍል ከፍተኛ ውጤት ያመጣችው ተማሪ ሃናን ናጂ አህመድ ወላጆች ገለጹ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኘው የክሩዝ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዋ ሃናን የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት 649 በማስመዝገብ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ውጤት አምጥታለች፡፡

ተማሪ ሃናን የ12ኛ ክፍል ፈተናን ጥሩ ውጤት ለማስመዝገብ እቅድ አውጥታ በሚገባ ስታጠና እንደነበር ትናገራለች፡፡

ብዙ ጊዜዋን በማንበብ እንደምታሳልፍ፣ አስተማሪ ከማስተማሩ በፊት ቀድማ የክፍለ ጊዜውን ትምህርት ይዘት እንደምታነብ፣ ይህ ልምድም አስተማሪው ሲያስተምር ጉዳዩን በደንብ እንድረትረዳ እንደሚያስችላት ትገልጻለች፡፡

ለሁሉም የትምህርት አይነቶች እኩል ትኩረት በመስጠት ለፈተናው አስፈላጊውን ዝግጅት ቀድማ ማጠቀቋን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ገልጸለች፡፡

ለሁሉም ነገር ትኩረት ሰጥተው ከሰሩ የማይሳካ ነገር የለም የምትለው ሃናን÷ ተማሪዎች ከሰው ከመጠበቅ ይልቅ ራሳቸውን ዝግጁ አድርገው ለውጤት መስራት አለባቸው ብላለች፡፡

ኢንተርኔትን ለትምህርቷ ግብዓት ለሚሆኑ መረጃዎች እንደምትጠቀም ገልጻ÷ አላማና ግብ አስቀምጣ አጥንታ ባገኘችው ውጤት ደስተኛ መሆኗንም አንስታለች፡፡

በቀጣይም ፋርማኮሎጂ የማጥናት ፍላጎት እንዳላት ነው የነገረችን፡፡

የተማሪ ሃናን ናጂ እናት ወ/ሮ ሽኩሪያ ሽፋ እና አባት አቶ ናጂ አሕመድ በበኩላቸው÷ልጃቸው በርትታ በማጥናት የልፋቷን ውጤት በማግኘቷ ከፍተኛ ኩራትና ደስታ እንደተሰማቸው ተናግረዋል።

ተማሪ ሃናን ለትምህርቷ ልዩ ትኩረት እንደምትሰጥና ለየትኛውም የሚያዘናጋ ሁኔታ ቦታ እንደማትሰጥም አስረድተዋል፡፡

አላማዋን ለማሳካት እቅድ አውጥታ እያንዳንዱን ነገር ከመፈጸም ወደ ኋላ እንደማትል የሚናገሩት ወላጆች÷ በቀጣይ ጥሩ ደረጃ ላይ እንደምትደርስ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

ተማሪዎች በትክክለኛው የህይወት መስመር እንዲጓዙ የወላጆች ሚና ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመው÷ ለዚህም አስፈላጊውን ክትትልና ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባ አንስተዋል፡፡

የልጃችን ከፍተኛ ውጤት የትጋቷ ፍሬ ነው በማለት ገልጸው፤ በዚሁ ቀጥላ ወደ ፊት የምትፈልግበት ደረጃ ላይ እንደምትደርስ በእርግጠኝነት ተናግረዋል።

የክሩዝ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ርዕሰ መምህር አቶ ጀማል እድሪስ÷ተማሪ ሃናን መልካምሥነ-ምግባር ያላት፣ ለትምህርቷ ልዩ ትኩረት የምትሰጥና የሚቸግራትን ሁሉ አስተማሪዎቿን ከመጠየቅ ወደኋላ የማትል ናት ሲሉ ይገልጻሉ፡፡

ከክፍል ጓደኞቿ ጋር መረዳዳትን የምትወድ፤ የምታውቀውን ለሌሎች የምታካፍል የትምህርት ቤቱ አረዓያ የሆነች ልዩ ተማሪ መሆኗንም አውስተዋል፡፡

10/10/2023

የክሩዝ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪ የሆነችው ሀናን ናጂ አህመድ በተፈጥሮ ሳይንስ 649 ውጤት በማስመዝገብ ከዘንድሮ ተፈታኞች በቀዳሚነት ተቀምጣለች፡፡..
በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኘው የክሩዝ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪ የሆነችው ሀናን ናጂ በተፈጥሮ ሳይንስ 649 ውጤት በማስመዝገብ ነው ከዘንድሮ ተፈታኞች ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገበችው፡፡..
በ2015 ዓ.ል የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተናን 356 ሺህ 878 የተፈጥሮ ሳይንስ እና 488 ሺህ 221 የማህበራዊ ሳይንስ በአጠቃላይ 845 ሺህ 188 ተማሪዎች መውሰዳቸው ተገልጿል።.
ከ488 ሺህ 221 የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ውስጥም የማለፊያ ውጤት ያመጡት 8 ሺህ 250 ብቻ መሆናቸው ተገጿል፡፡..
በሌላ በኩል ከ356 ሺህ 878 የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች ውስጥ 22 ሺህ 974 ተማሪዎች የማለፊያ ውጤት ማምጣታቸው ተጠቅሷል፡፡..

06/10/2023

ማሻ አላህ ❤️

04/10/2023

የፍቅር መቀስ ምርጥ ኢስላማዊ ድራማ

04/10/2023

አንተ ወዳጅ ሆይ!
ተፈቃሪህ እኚህ ናቸው 🥺
© Minber Tv/ሚንበር ቲቪ
Ustaz Yassin Nuru / ياسين نورو

03/10/2023

የስንብት አማና Engr/Ustaz Bedru Hussein - በድሩ ሁሴን

10/09/2023

Mashaallah

ዒድ ሙባረክ ❤️
27/06/2023

ዒድ ሙባረክ ❤️

መልካም ጁምዓ ይሁንልዎ ! «ፈገግታ አይለይህ። ምንም አይነት ኪሳራ የለውም።ጌታህ አልለ።ሪዝቅህም የተመዘገበ ነው።እድሜህ የተገደበ ነው።በዙሪያህ የሞላውን ውበት ለማየት ትችል ዘንድ ራስህን ...
26/05/2023

መልካም ጁምዓ ይሁንልዎ !

«ፈገግታ አይለይህ። ምንም አይነት ኪሳራ የለውም።ጌታህ አልለ።ሪዝቅህም የተመዘገበ ነው።እድሜህ የተገደበ ነው።በዙሪያህ የሞላውን ውበት ለማየት ትችል ዘንድ ራስህን አስውብ…።»

ፈገግ ያለ ቀን ተመኘንልዎ 🧡

Telegram - t.me/SeyaMehdi - ተቀላቀሉን !
YouTube - https://youtu.be/s2l7lEiEn6I - SUBSCRIBE 🔔

+ Share

«አላህና መላእክቱ በነብዩ ላይ የአክብሮት እዝነትን ያወርዳሉ። እናንተ ያመናችሁ  ሆይ! በእርሱ ላይ የአክብሮት እዝነትን አውርዱ። የማክበርንም ሰላምታ ሰላም በሉ።»       [ሱረቱል አህዛ...
19/05/2023

«አላህና መላእክቱ በነብዩ ላይ የአክብሮት እዝነትን ያወርዳሉ። እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በእርሱ ላይ የአክብሮት እዝነትን አውርዱ። የማክበርንም ሰላምታ ሰላም በሉ።»
[ሱረቱል አህዛብ 33:56 ]

(ሰለላሁ🧡አለይሂ🧡ወሰለም)

! 😇

Telegram - t.me/SeyaMehdi - ተቀላቀሉን !
YouTube - https://youtu.be/s2l7lEiEn6I - SUBSCRIBE 🔔

+ Share

مآذن  #بيت الله  #الحرام
07/05/2023

مآذن #بيت الله #الحرام

20/04/2023

ኢድ ሙባረክ አላህ ዒባዳችንን ይቀበለን❤️

ሰበር ዜና!በዛሬው ዕለት ማለትም ዕለተ ሐሙስ ምሽት ሚያዝያ 12 ቀን 2015፣ የሱዑዲት ዐረቢያ የሥነ- ፈለክ ሳይንቲስቶች የዘመኑ ቴክኖሎጂ ባፈራው ቴሌስኮፕ በመታገዝ ባደረጉት ቅኝ፣ አዲሲቷ...
20/04/2023

ሰበር ዜና!

በዛሬው ዕለት ማለትም ዕለተ ሐሙስ ምሽት ሚያዝያ 12 ቀን 2015፣ የሱዑዲት ዐረቢያ የሥነ- ፈለክ ሳይንቲስቶች የዘመኑ ቴክኖሎጂ ባፈራው ቴሌስኮፕ በመታገዝ ባደረጉት ቅኝ፣ አዲሲቷ የሸዋል ወር ጨረቃ ለመታየት በመቻሏ፣

የሸዋል ወር የመጀመሪያው ዕለት የሚጀምረው፣ ማለትም ዒድ አል-ፊጥር የሚውለው በነገው ዕለት፣ ዕለተ ዐርብ ሚያዝያ 13 ቀን 2015 መሆኑ ተረጋግጧል ሲል "ሐረመይን ሸሪፈይን" የዜና ምንጭ ዘግቧል፡፡

🛑ዘካቱል ፊጥር / የፍስግ ምጽዋት/🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🎈ዘካተል ፊጥር የረመዳን ወር ፆም መጠናቀቅ ተከትሎ በወቅቱ ሙስሊም ሁኖ በህይወት ባለ ሰው በነፍስ ወከፍ ግዴታ የሚሆን የዘካ / ሰደቃ...
20/04/2023

🛑ዘካቱል ፊጥር / የፍስግ ምጽዋት/
🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋

🎈ዘካተል ፊጥር የረመዳን ወር ፆም መጠናቀቅ ተከትሎ በወቅቱ ሙስሊም ሁኖ በህይወት ባለ ሰው በነፍስ ወከፍ ግዴታ የሚሆን የዘካ / ሰደቃ/ አይነት ነው ፡፡ ለግንዛቤ ያህል ዘካተል ፊጥር ከዘካተል ማል ይለያል ።

🎈እያንዳንዱ አባወራ ወይም እማወራ ወይም አስተዳዳሪ የራሱን ጨምሮ በእርሱ ስር እየቀለባቸው ላሉ ቤተሰቦቹ ሁሉ መስጠት ይኖርበታል ፡፡

🛑 ማስረጃ

🎈 አብዱላህ ኢብን አባስ አላህ ይውደዳቸውና እንዲህ ይላሉ፤
‹‹የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም
በ እርሳቸው ላይ ይሁን) ዘካተል ፊጥር ለፆመኛ በጾሙ ወቅት ከፈፀማቸው ጥቅም አልባ ውድቅ ንግግሮችና ተግባሮች ጥፋት እንዲሁም የተቃራኒ ፆታ ስሜትን ቀስቃሽ ለሆኑ ንግግሮቹ ጥፋት ማፅጃ ይሆንለታል ። ለሚስኪኖች (ድሆች) መብል ሲሆን በግዴታ መልኩ ደንግገውላታል ። ስለዚህም ከኢድ ሰላት በፊት (ዘካውን በመስጠት ግዴታውን የተወጣ) ተቀባይነት ያለው ዘካን ሰጥቷል፤ ከ ኢድ ሶላት ቦሃላ ዘካውን የሰጠ እንደማንኛውም ሰደቃ አንዱ እንደሆነ ይታሰብለታል ።))
(አቡዳውድ እና ኢብኑ ማጃህ ዘግበውታል)።

🎈 ኢብኑ ሙንዚር አል ኢጅማዕ’ በተሰኘው ኪታባቸው ‹‹ዒልምን የተማርንባቸው
ዑለሞች ሁሉ ዘካተል ፊጥር ግዴታ መሆኑን
ተስማምተውበታል›› በማለት የ ኡለሞችን አጠቃላይ ስምምነት (ኢጅማዕ) የተገኘበት መሆኑን ጠቁመዎል ።

🛑 የተደነገገበት ጥበብ

ከላይ ግዴታነቱን ለማመላከት በተጠቀሰው ሀዲስ እንደተጠቀሰው ፣ ድሆች በባዕሉ (ዒድ) እለት ሰዎችን ከመለመን እንዲድኑና የእለቱ ደስታ ተካፋይ እንዲሆኑ ማድረግ እንዲሁም በፆም ወቅት ተከስተው ላለፉ አንዳንድ ጉድለቶች (ግድፈቶች) ማሟያ እንዲሆን ነው ።

🛑 መጠኑ

* የዘካተል ፊጥር መጠን ኢብኑ ኡመር ረዲየላሁ አንሁ ከነብያችን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ይዘው ባስተላለፉት ሀዲስ እንዲህ ብለዋል: – ‹‹የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በሳቸው ላይ ይሁን) ከተምር ወይም ከገብስ አንድ ቁና መስጠት በ እያንዳንዱ ሙስሊም፤ ባሪያም ሆነ ጨዋ (ባሪያ ያልሆነ)፣ሴት፣ ህፃን፣ አዋቂ ላይ ግዴታ አድርገዋል፡፡ እንዲሁም ሰዎች ወደ (ዒድ) ሰላት ከመውጣታቸው በፊት ለሚገባቸው ሰዎች እንዲደርስ አዘዋል፡፡›› (ቡኻሪና ሙስሊም )

1 ሷዕ / ቁና/ በመካከለኛ ሰው እጅ አራት እፍኞች ነው ። ወደ ኪሎ ግራም ሲቀየር እንደየ እህሉ ክብደትና ቅለት ይለያያል ። ለምሳሌ ፣
— አንድ ቁና (ሳእ) ፉርኖ ዱቄት 2.5 ኪሎ
— አንድ ቁና (ሳእ) ጤፍ 2·85 ኪሎ
— አንድ ቁና (ሳእ) ሩዝ 2·75 ኪሎ
— አንድ ቁና (ሳእ) ስንዴ 2·5 ኪሎ
— አንድ ቁና (ሳእ) ገብስ 2 ኪሎ
— አንድ ቁና (ሳእ) ማሽላ 2·63ኪሎ
— አንድ ቁና (ሳእ) በቆሎ 2·5 ኪሎ

🛑 ግዴታ የሚሆነው በማን ላይ ነው

— ሙስሊም በሆነ
— ረመዷን ወር ሲጠናቀቅ በህይወት የነበረ
— በእለቱ ለ24 ሰዓት ለራሱና ለሚያስተዳድራቸው ሰዎች ወጪ የሚያደርገው ሀብት ኑሮት ከዚያ የተረፈ ባለው ሰው ።

— * ዘካተል ፊጥር በነፍስ ወከፍ የሚደረግ ኢባዳ ስለሆነ በቤተሰብ ስር የሚኖር ሰው ለራሱ ሚያወጣበት ነገር ካለው ቤተሰቦቹን ከመጠበቅ ራሱ ማውጣት ይኖርበታል ።

🛑 ግዜው

* ዘካተል ፊጥርን ማውጣት ግዴታ የሚሆነው የረመዷን ወር የመጨረሻው እለት
ፀሀይ ከጠለቀችበት ወይም ዒድ መሆኑ ከተረጋገጠበት ሰዓት አንስቶ የኢድ ሷላት ተሰግዶ እስኪጠናቀቅ ድረስ ነው ፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ኢብኑ ዑመርን ጨምሮ ሌሎቹም ሰሀቦች (ረዲየላሁ አንሁም) ከዒድ አንድ ወይም ሁለት ቀን ቀድሞ ዘካተል ፊጥርን ማውጣት እንደሚቻል ይገልጻሉ ሲተገብሩትም ነበር ።

* ዘካተል ፊጥርን ከ(ዒድ) ሰላት በኋላ ማዘግየት የተከለከለ ነው ። ድንገት አንድ ሰው ረስቶ ወይም ሳይመቸው ቀርቶ በወቅቱ ሳያወጣ ቢቀር ባስታወሰና በተመቸው ወቅት ማውጣት አለበት ።

🛑 የሚሰጠው ነገር
* ለዘካተል ፊጥር የሚሰጡ የእህል አይነቶችን በተመለከተ አውጪዎቹ በሀገራቸው ከሚመገቡዋቸው እህሎች ውስጥ ይሆናል ለምሳሌ እንደ ተምር ፣ ዱቄት ፣ እሩዝ ፣ በቆሎ፤ ጤፍ …. ወዘተ ባሉ የምግብ እህል አይነቶች
ነው ። ይህን አስመልክተው የአላህ መልእተኛው ነብያችን (የአላህ ሰላትና ሰላም በሳቸው ላይ ይሁን) በሀዲሳቸው የጠቀሷቸው የምግብ እህሎች ( ገብስ፤ ተምር፤ ዘቢብ) ፣ የመሳሰሉት ሲሆኑ፣ ነገር ግን የምግብ አይነቶቹ በነዚህ ላይ ብቻ እንደማይገደቡ የኢስላም ሊቃውንቶች ያስረዳሉ ። በዚህም መሰረት በማንኛውም አካባቢ የሚኖር ሙስሊም ማህበረሰቡ አዘውትሮ ከሚመገባቸው የምግብ እህሎች ዘካተል ፊጥሩን ማውጣት ይችላል፡፡

🛑 ለማን ይሰጥ

* ዘካተል ፊጥር ለምስኪኖች እና ለድሆች ብቻ ነው ሚሰጠው አብደላህ ብኑ አባስ ባስተላለፉት ሀዲስ ላይ ነብያችን (የአላህ ሰላትና ሰላም በሳቸው ላይ ይሁን) ‹‹ለምስኪኖች መብል …›› በማለት ስለገለፁ ።

🛑 በዘካተል ፊጥር ስለመወከል

* ዘካተል ፊጥር የሚሰጥበት ወቅት የተገደበና ግዜውም አጭር ከመሆኑ አንፃር አውጪዎች ባሉበት ሀገር ወይም ሁኔታ ምክንያት በተወሰነለት ግዜ ማውጣት ካልቻሉ ወቅቱ ሳያልቅ ዘካውን ሚያወጣላቸው ሰው መወከል ይችላሉ ። በተመሳሳይ ዘካተል ፊጥርን የሚቀበሉ ምስኪኖችም ራሳቸው መቀበል ካልቻሉ ሚቀበልላቸውን ሰው መወከል ይችላሉ ።

* ተወካዪች ከሁለቱም ከሰጪና ከተቀባይ ወገን ከተወከሉ ወቅቱ ካለፈም በኋለ ለምስኪኖች ቢሰጡ ችግር የለውም ነገር ግን የተወከሉ በሰጪዎች ብቻ ከሆነ የግድ ወቅት ሳያልፍ ለሚገባቸው ሰዎች ማድረስ ይኖርባቸዋል ።

🛑 ለሌላ አካባቢ ስለመስጠት

* አግባቡ ዘካተል ፊጥርን ወደ ሌላ ቦታ ከመላክ
እያንዳንዱ ሙስሊም በጾመበት ቦታ ማውጣቱ ቢሆንም የሚቀበል ሚስኪን ከሌለ ችግረኞች ወዳሉበት ቦታ መላክ ይቻላል ።

ከ1 ሺህ ወራት ኢባዳ የላቀ ምንዳዋ ሚዛን የሚደፋው “ለይለቱል ቀድር”በዚህ ሣምንት በሚጠናቀቀው የረመዷን ወር ከ1 ሺህ ወራት ወይም ከ83 ዓመት ከ3 ወራት ኢባዳ በላይ የላቀ ምንዳ ያላት አ...
17/04/2023

ከ1 ሺህ ወራት ኢባዳ የላቀ ምንዳዋ ሚዛን የሚደፋው “ለይለቱል ቀድር”

በዚህ ሣምንት በሚጠናቀቀው የረመዷን ወር ከ1 ሺህ ወራት ወይም ከ83 ዓመት ከ3 ወራት ኢባዳ በላይ የላቀ ምንዳ ያላት አንድ ሌሊት “ለይለቱል ቀድር” ትገኛለች፡፡

ይችን በረከተ ብዙ “ለይለቱል ቀድር” ምዕመኑ በንቃት እንዲጠብቃት አስተምኅሮቱ ያዛል፡፡

"ረመዷን" ማለት . . .

በቁርአን ላይ እንደተገለጸው፥ ከአላህ ዘንድ የወራት ቁጥር 12 ናቸው። እነሱም፦ ሙሀረም፣ ሰፈር፣ ረቢዕ አልአወል፣ ረቢዕ አልሳኒ፣ ጅማድ አልኡላ፣ ጅማድ አልአኺራ፣ ረጀብ፣ ሻዕባን፣ ረመዷን፣ ሸዋል፣ ዙል ቀኢዳ እና ዙል ሂጃ ናቸው።

ከላይ በቀረበው አገላለጽ መሰረት፥ "ረመዷን" ማለት ከ12ቱ ወራት የዘጠነኛው ሥያሜ ነው።

"ረመዷን" ከሌሎቹ ወራት በምን ይለያል?

ረመዷን ከሌሎች ወራት የሚለይበት በርካታ ምክንያት እንዳሉት ይገለጻል።

ከሌሎች ወራት ከሚለይባቸው ምክንያቶች አንዱ "ቁርአን የወረደበት ወር መሆኑ ነው" ይላሉ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ዋና ጸሐፊ ሼኽ ሃሚድ ሙሣ። ይህም በቁርአን ላይ ስለመጠቀሱ በማረጋገጥ።

በተጨማሪም ረመዷን የሠደቃ፣ የራህመት፣ የጀነት በር የሚከፈትበት፣ የጀሃነም በር የሚዘጋበት፣ በጎ ሥራዎች ሲሠሩ ከአላህ ዘንድ እጥፍ ክፍያ (አጅር) የሚያስገኝ በመሆኑ ከሌሎች ወራት እንደሚለይ ያብራራሉ።

እንዲሁም ረመዳን "ለይለቱል ቀድር" የተሰኘች የ1ሺህ ወራት የአምልኮ ምንዳ ልታስገኝ የምትችል አንዲት ሌሊት የምትገኝበት ወር በመሆኑ ልዩ ነው ይላሉ።

ስለ "ረመዷን" ጾም አላህ ምን አለ?

የበረከት ማግኛ ወር በመሆኑ ሙስሊሞች እንዲጾሙ ይጠበቃል ነው ያሉት ሼኽ ሃሚድ።

ይህንም "እናንተ ምዕመናን ሆይ በእናንተ ላይ ጾምን እንድትጾሙ ግዴታ ተደርጎባችኋል፤ ከእናንተ በፊት በነበሩት ምዕመናን ላይ ግዴታ እንደተደረገው ሁሉ በእናንተም ላይ ግዴታ ተደርጓል" ብሎ አላህ በቁርአን ላይ ተናግሯል ይላሉ።

በሌላ በኩል "ከእናንተ መካከል የታመመ ሰው ካለ ወይም በጉዞ ላይ ከሆነ መጾም ስለማይችል ጾሙን ይተው እና በሌላ ጊዜ ያልጾመውን ያህል ቀን ቆጥሮ 'ቀዷ' (እዳውን) እንዲከፍል አዝዣለሁ" ሲል አላህ በቁርአን የተናገረውን አንስተዋል።

ይህን መፈፀም እንደሚጠበቅም አስገንዝበዋል።

"እናንተን ሊያግራራላችሁ ነው እንጂ አላህ የሚፈልገው ሊያስጨንቃችሁ አይፈልግም" ብሎ በተናገረው መሰረት በወቅቱ መጾም ላልቻሉ አማራጭ መቀመጡን ነው ዋና ጸሐፊው የሚያስረዱት።

የ "ረመዷን" ትሩፋት!
የረመዷን ወር በርካታ ትሩፋት እንዳሉት ነው ሼኽ ሃሚድ ሙሣ የሚያመላክቱት።

ቁርአን በብዛት የሚቀራበት፣ "ቀልቦች" ወደ ፈጣሪያቸው ቀጥ የሚሉበት፣ ርኅራሔ የሚበዛበት፣ ሠደቃ የሚሠደቅበት፣ የቸርነት፣ የልገሣ፣ የደግነት፣ የተካፍሎ መብላት እና የእንረዳዳ ወር መሆኑ ከትሩፋቶቹ መካከል እንደሚጠቀሱ ያነሳሉ።

የ "ረመዷን" የመጨረሻ ሣምንት!

የረመዷን ወር በሦት አሥር ቀናት የሚከፈል ሲሆን፥ ከሦስቱ አሥሮች የመጨረሻው አሥር ("አሸረ አልአዋኺር") ይሰኛል።

እንደ ሼኽ ሃሚድ ሙሣ ገለፃ፥ በአጠቃላይ "ረመዷን" የ "ኢባዳ" ወር ቢሆንም የሦስተኛው አሥር ቀናት የተለዩ በጾም በጸሎት ማሳለፊያ ጊዜ (የ"ኢባዳ" ሌሊቶች) ናቸው።

የረመዷን የመጨረሻው ሣምንት ሌሊቶች ከሌሎች ሣምንታት የሚለዩበት ምክንያት እንዳለም ይገልጻሉ።

ከምክንያቶቹ መካከል፥ ነብዩ መሐመድ (ሰለሏህ ዓለይሂ ወሰለም) ያደርጉት እንደነበረው "ሥራ ትቶ፣ እራስን አቅቦ ለ"ኢባዳ" ማስቀመጥ ቀኑንም ሌሊቱን በመስጂድ ማሳለፍ ("ኢህቲካፍ" መግባት) አንዱ ነው" ይላሉ።

በመሆኑም ወደ መስጂድ ለ "ኢህቲካፍ" የገባ ምዕመን ጊዜ የማይሰጥ ጉዳይ ካላጋጠመው በስተቀር ከመስጂድ መውጣት የማይቻልበት ሣምንት መሆኑንም ነው የሚጠቅሱት።

ሌላኛው ምክንያት በእነዚህ ሌሊቶች፥ የተራዊህ እና የተሃጁድ ሶላት ይሠገዳል፣ ሌሊቶቹ ያለዕንቅልፍ ቁርአን በመቅራት እንዲያልፉ ይደረጋል፣ መሻይኾች፣ ዑለማዎችና የመስጂድ አሰጋጆች በተለያየ የሶላት ወቅት ላይ (በዙህር፣ ዓስር፣ መግሪብ፣ ኢሻ)፣ በማኅበራዊ ጉዳይ፣ በሥነ ምግባር፣ በአምልኮ እንዲሁም በእምነቱ ዘሪያ (በዓቂዳ ጉዳይ ላይ) ምክር ይሰጣሉ ነው ያሉት።

ሼኽ ሃሚድ ሙሣ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር በነበራቸው ቆይታ እንዳሉት፥ ሙስሊሞች "ረመዷን" ን ለቀጣዮቹ 11 ወራት የባሕርይ፣ የሥነ ምግባር፣ የአምልኮ የጥንካሬ እና የብቃት አቅም የሚያጎለብቱበት ልዩ ወር ነው።

የመጨረሻው ሣምንት ሌሊቶችንም በንቃት በኢባዳ እንደሚያሳልፏቸው ነው የሚናገሩት።

በዚሁ የረመዷን የመጨረሻ ሣምንት የጾም ወቅት በኢትዮጵያ በበርካታ መስጂዶች የተሃጁድ ሶላት እንደሚሠገድም ነው የጠቆሙት።

በተጨማሪም ረጅም ሩኩዕ፣ ረጅም ስጁድ፣ረጂም ቂያም ያካተተ ሶላት ይሠገዳል ነው ያሉት።

በአጠቃላይ ይህ ሁሉ ለኢባዳ የሚደረገውን መስዋዕትነት በአላህ እንደመገዛት የሚከፈለውን መስዋዕትነት ለማሰልጠን ጭምር መሆኑን ያነሳሉ።

ከ1 ሺህ ወራት ኢባዳ የላቀ ምንዳ ያላት አንድ ሌሊት (ለይለቱል ቀድር)

ከቅዱሱ የረመዷን ወር የመጨረሻ ሣምንት ውስጥ ‹‹ለይለቱል ቀድር›› የምትባል በረከቷ የበዛ ሌሊት አለች፡፡ ይችኑ ሌሊት ‹‹ኸይሩን ሚን አልፊሸህር›› ብሏታል ቁርአን፡፡

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ዋና ጸሐፊ እንዳሉት፥ "በእዚች ሌሊት ላይ ጠንክሮ ማምለክ የ1 ሺህ ወር ወይም (83 ከ3 ወራት በላይ) አላህን የመገዛት ያህል ይቆጠራል"፡፡

ሙስሊሞች ይችን በረከተ ብዙ ሌሊት በኢበዳ ለማሳለፍ በንቃት መጠበቅ እንደሚገባቸውም መክረዋል፡፡

ሼኽ ሃሚድ፥ ‹‹ከአሥሩ ቀናት መካከል የትኛዋ ነች›› ተብለው ነብዩ መሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ተጠይቀው እንደነበር አንስተዋል፡፡

ነብዩም ሲመልሱ ‹‹ተነግሮኝ ልነግራችሁ ስመጣ እረሳሁት›› እንዳሉ ይናገራሉ፡፡

ለምንድን ነው አላህ ያስረሳቸው? ለሚለው ጥያቄ ‹‹ያቺ ቀን ከተነገረች ሙስሊሞች ያቺን ቀን ብቻ ኢባዳ አድርገው ሌሎቹን ቀናት ችላ እንዳይሏቸው ነው። አሥሩንም ቀናት በትጋት ኢባዳ እንዲያደርጉ ታስቦ ነው›› ብለዋል ነብዩ፡፡

እና እንዴት እናድርግ ሲሏቸውም " ለማንኛውም በጎደሎ ቁጥር ፈልጓት" የሚል ምላሽ መስጠታቸውን ሼኽ ሃሚድ አብራርተዋል። ጎደሎ ቁጥር ማለትም፥ "21ኛው፣ 23ኛው፣ 25ኛው፣ 27ኛው እና 29ኛው ሌሊቶች ናቸው። ነብዩ ቁርጥ አድርገው ሳይናገሩ ከእነዚህ መካከል ፈልጓት ነው ያሉት።

የነብዩ መሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ባለቤት አይሻ ነብዩን "ለይለቱል ቀድር" ሲያጋጥመኝ ምንድን ነው ማለት ያለብኝ ብለው ጠይቀዋቸው ነብዩ ሲመልሱ "ጌታዬ አንተ ይቅርታን ትወዳለህና ይቅር በለኝ" ብለሽ ሌሊቱን ሙሉ ዱዓ አድርጊ ብለው እንደመከሯቸውም ነው የተገለጸው።

ነብዩ መሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) አሥሩንም ሌሊቶች እንቅልፍ ያለባቸውን ቤተሰቦቻቸውን ቀስቅሰው የጋራ ኢባዳ እና የጋራ አምልኮ (በጀመዓ መጸለይ) በማድግ ሳይተኙ ያሳልፉ ነበር ያሉት ሼኽ ሃሚድ÷ እኛም እሳቸውን የምንከተል በመሆናችን ‹‹በአላህ መልዕክተኛ መልካም አርአያ አላቸው፤ እሳቸው የሚሉትን ሥሩ›› ስለተባልን ኢባዳችንን አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል፡፡

ሌሊቱ በዱዓ፣ በጸሎት፣ እንዲያልፍ አላህ ይቅር እንዲል ሙስሊሞች የሚማፀኑበት ሌሊት መሆኑም ተመላክቷል።

ረመዷን ሠደቃ የሚሰጥበት፣ አቅመደካሞች የሚረዱበት፣ የመተጋገዝ ወር እና ለማፍጠሪያ ማዕድ ማጋሪያ ጊዜ መሆኑን አስገንዝበዋል።

በዮሐንስ ደርበው FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)

15/04/2023

ب،ع غعس

መዲና የሚገኝ ድንቅ ታሪካዊ ምንጭ


Engr/Ustaz Bedru Hussein - በድሩ ሁሴን

[ اللَّهُمَّ لَكَ أَسْلَمْتُ، وَبِكَ آمَنْتُ وَعَلَيْكَ تَوَكَّلْتُ، وَإِلَيْكَ أَنَبْتُ، وَبِكَ خَاصَمْتُ، وَإِلَيْكَ ح...
11/04/2023

[ اللَّهُمَّ لَكَ أَسْلَمْتُ، وَبِكَ آمَنْتُ وَعَلَيْكَ تَوَكَّلْتُ، وَإِلَيْكَ أَنَبْتُ، وَبِكَ خَاصَمْتُ، وَإِلَيْكَ حَاكَمْتُ، فَاغْفِرْ لِي مَا قَدَّمْتُ وَمَا أَخَّرْتُ، وَمَا أَسْرَرْتُ وَمَا أَعْلَنْتُ، أَنْتَ الْمُقَدِّمُ وَأَنْتَ الْمُؤَخِّرُ، لاَ إِلَهَ إِلاَّ أَنْتَ ]

10/04/2023

እባካችሁ ለሁሉም እንዲዳረስ ሼር አድርጉ እህታችንን እንርዳት 😭😭😭😭😭

እህታችን ራህማ (ዝናሽ) የሁለት ልጆች እናት ናት አልጋ ላይ ከዋለች አመታት ተቆጠሩ ተንቀሳቅሳ መስራት ባለመቻሏ የሰው እጅ ለማየት ተገዳለች ። የቤት ኪራይ የቀለብ የህክምና ወጪዋ መድሃኒት መግዣ ተቸግራለች። አሁን ግን ነገሮች ወደከፋ ደረጃ እየተለወጡ ጤናዋም አስጊ ሁኔታ ላይ ይገኛል ። ለልጆቿ መኖር ትመኛለች ። መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ለዚህች ምስኪን እናት ይደርስላት ዘንድ ትብብራችሁን እንጠይቃለን።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000464498137 ዝናሽ ከድር
አቢሲኒያ ባንክ 131711565 ዝናሽ ከድር

ይደውሉ
0938293462
0911024522
0912939959

ከተራዊሕ ሶላት በኋላ በነብዩ ሙሐመድ (ﷺ) መስጂድ ውስጥ ካሉ ምሰሶዎች አንዱን ተደግፌ እያለ በምስሉ የምትመለከቱት ኡዝቤክስታናዊ ወንድሜ ከጀርባዬ ካለው መደርደሪያ ላይ ቁርኣን ለማንሳት መ...
09/04/2023

ከተራዊሕ ሶላት በኋላ በነብዩ ሙሐመድ (ﷺ) መስጂድ ውስጥ ካሉ ምሰሶዎች አንዱን ተደግፌ እያለ በምስሉ የምትመለከቱት ኡዝቤክስታናዊ ወንድሜ ከጀርባዬ ካለው መደርደሪያ ላይ ቁርኣን ለማንሳት መጣ። በተሰባበረ የዐረብኛ ቋንቋ ለመግባባት ሞከርን። በተለያዩ አጋጣሚዎች ያገኘኋቸው የሌላ አገር ሙስሊም ዜጎች "ከየት አገር እንደመጣሁ" ሲጠይቁኝ የምሰጠው የተለመደ ምላሽ «ከነጃሺ ፣ ከኡሙ አይመን እና ከቢላል አገር» የሚል ነው።

ከዚህ ወንድሜ ጋር የተለያዩ ጉዳዮችን አንስተን እያወራን ለተወሰኑ ደቂቃዎች ከተቀመጥን በኋላ ኡስታዝ በድር ሑሰይን ወደ ማረፊያችን እንድንሄድ በርቀት ምልክት አሳየኝ። እኔም ለመንቀሳቀስ ስዘጋጅ ኡዝቤኪስታናዊው ወንድሜ «እባክህ አምስት ደቂቃ ያህል እንኳ ስለ ቢላል የሆነ ነገር ንገረኝ» አለ። «እሺ» ብዬ ወሬዬን ለመወጠን ስዘጋጅ አቀማመጡን አሳመረ። በትኩረት ማዳመጥ ጀመረ። ቢላል በአሳዳሪው ኡሙያ የደረሰበትን ጭካኔ የተሞላበት የበረሃ ስቃይ እና መለኮትን ለማወጅ ከአንደበቱ ይወጣ የነበረውን "አሐዱን አሐድ" አንድ ሁለት እያልኩ ስነግረው እንደ ህጻን ነፈረቀ። ፊቱ በእንባ ወረዛ። ሁለት እጆቹን በትከሻዬ ላይ አሳልፎ ከረጂም ዓመታት መጠፋፋት በኋላ እንደተገናኘ ወዳጅ ተጠመጠመብኝ። ካለንበት ቦታ በቅርብ ርቀት ላይ ክብ ሰርተው የተቀመጡት የካዛኪስታን ዜጎች አይናቸውን እኛ ላይ አሳረፉ። እኔም ኡዝቤኪስታናዊ ወንድሜን አቅፌ ትከሻውን መታ መታ በማድረግ ተሰናበትሁ።

ኢትዮጵያዊያን በረገጡበት ቦታ ሁሉ አንገታቸውን ቀና ማድረግ እንዲችሉ ምልክት ከሆኑ ወርቃማ ስብዕናዎች መካከል አንዱ ቢላል ኢብኑ ረባሕ (ረ.ዐ)

Ahmed

08/04/2023

https://www.facebook.com/profile.php?id=100063612075565&mibextid=ZbWKwL

وَإِذَا سَأَلَكَ عِبَادِي عَنِّي فَإِنِّي قَرِيبٌ ۖ أُجِيبُ دَعْوَةَ الدَّاعِ إِذَا دَعَانِ ۖ فَلْيَسْتَجِيبُوا لِي وَلْيُؤْمِنُوا بِي لَعَلَّهُمْ يَرْشُدُونَ

ባሮቼም ከእኔ በጠየቁህ ጊዜ (እንዲህ በላቸው)፡- እኔ ቅርብ ነኝ፡፡ የለማኝን ጸሎት በለመነኝ ጊዜ እቀበለዋለሁ፡፡ ስለዚህ ለኔ ይታዘዙ፤ በኔም ይመኑ፤ እነሱ ሊመሩ ይከጀላልና፡፡

[ሱረቱል በቀራ]

ፎቶ :- ታላቁ ላይ የጎዳና ኢፍጣር
08/04/2023

ፎቶ :- ታላቁ ላይ የጎዳና ኢፍጣር

🛑 ኢድ አደባባይ ታላቁን የጎዳና ላይ ኢፍጣር ለማዘጋጀት ዝግጅቱን አጠናቆ ታዳሚያንን እየጠበቀ ነው!🛑 እግሮች ሁሉ ወደ ኢድ አደባባይ ያመራሉ!🛑 ሁላችሁም ተጋብዛቹሃል።
08/04/2023

🛑 ኢድ አደባባይ ታላቁን የጎዳና ላይ ኢፍጣር ለማዘጋጀት ዝግጅቱን አጠናቆ ታዳሚያንን እየጠበቀ ነው!

🛑 እግሮች ሁሉ ወደ ኢድ አደባባይ ያመራሉ!

🛑 ሁላችሁም ተጋብዛቹሃል።

🛑 ወደ ታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጣር በኢትዮጵያ-3 ሲመጡ ምዕመናን ሊከተሏቸው የሚገቡ ደንቦች1-  የተለመደውን ለጸጥታ አካላት እና ለበጎ ፍቃድ አስተባባሪዎች ፍተሻ ትብብር ማድረግ2-  የሰላት...
08/04/2023

🛑 ወደ ታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጣር በኢትዮጵያ-3 ሲመጡ ምዕመናን ሊከተሏቸው የሚገቡ ደንቦች

1- የተለመደውን ለጸጥታ አካላት እና ለበጎ ፍቃድ አስተባባሪዎች ፍተሻ ትብብር ማድረግ

2- የሰላት መስገጃ ይዘው ይምጡ

3- ለማፍጠሪያ የሚሆንና ከሙስሊም እህትና ወንድሞቻች በማካፈል ኢፍጣርን ለሌሎች በማጋርት የሚገኘውን አጅር ተቋዳሽ እንዲሆኑ ጥሪ እናደርጋለን፡፡ ምግቦቹ እንደ ቴምር፣ ውሃ እና የታሸጉ ምግቦች መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

4- ማንኛውም ለደህንንት አጠራጣሪ ሁኔታዎች ከተመለከቱ ለበጎ ፍቃደኛ አስተባባሪዎችና ለጸጥታ አካላት በአፋጣኝ እንዲያሳውቁ

5- የጎዳና ላይ ኢፍጣር ዝግጅት ዋና ዓላማ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ከሌሎች ጋር ኢፍጣርን በማጋራት የሚገኘውን አጅርና ደስታ እንዲያጣጥም ከማስቻል ባሻገር እኛ ሙስሊሞች ምንም ዓይንት ልዩነት ሳይገድበን ህብር ብሄራዊ አንድነታችንን በማሳየት ለሃገራችን ሰላምና ዕድገት በጋራ አላህን የምንማጸንበት ዝግጅት ስለሆነ ከዝግጅቱ ዓላማ ውጪ ከሆኑ ድርጊቶች በመቆጠብ ኢስላማዊ ስነምግባራችንን ለሌሎች ዓርኣያ በመሆን ማሳየት

6- በዕለቱ በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች በመጠለያ ካምፕ ውስጥ ለሚገኙ ገንዘብ ስለሚሰበሰብ ከወዲሁ በረመዳን ለተቸገሩ ድጋፍ በማድረግ የሚገኘውን ታላቅ አጅር እንዲሸመቱ የአቅሞን ገንዘብ ይዘው ወደ ዝግጅቱ እንዲመጡ ጥሪ እናስተላልፋለን፡፡

የረመዳን ጾምን አስመልክቶ በአዲስ አበባ ከተማ የጉዳና ላይ ኢፍጣር ይደረጋል። የኢፍጣር ፕሮግራሙ በሰላም እንዲከናወን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስፈላጊውን ዝግጅት ማጠናቀቁ  አስታውቋል፡፡ ***...
07/04/2023

የረመዳን ጾምን አስመልክቶ በአዲስ አበባ ከተማ የጉዳና ላይ ኢፍጣር ይደረጋል። የኢፍጣር ፕሮግራሙ በሰላም እንዲከናወን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስፈላጊውን ዝግጅት ማጠናቀቁ አስታውቋል፡፡
********************************************************

"ኢፍጣራችን ለወገናችን" በሚል መሪቃል የፊታችን ቅዳሜ መጋቢት 30 ቀን 2015 ዓ/ም በአዲስ አበባ ከባምቢስ በመስቀል አደባባይ እስከ ሜክሲኮ አደባባይ ባለው ጉዳና ላይ የኢፍጣር ፕሮግራሙ የሚካሄድ ይሆናል፡፡

ፕሮግሙ በሰላም ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡ ፕሮግሙ በሚካሄድበት ወቅት የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር፡-

* ከቅዱስ ኡራኤል ወደ መስቀል አደባባይ
* ከኦሎምፒያ ወደ መስቀል አደባባይ
* ከአራተኛ ክፍለ ጦር ወደ መስቀል አደባባይ
* ከልደታ ከፍተኛ ፍ/ቤት ፣ በለገሃር ወደ መስቀል አደባባይ
* ከጎማ ቁጠባ ወደ መስቀል አደባባይ
* ከአራት ኪሎ ወደ መስቀል አደባባይ
* ከካዛንቺስ ወደ መስቀል አደባባይ
* ከጥቁር አንበሳ ሼል ወደ መስቀል አደባባይ
* ከቴዎድሮስ አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ
* ከንግድ ማተሚያ ቤት ወደ መስቀል አደባባይ
* ከሜትሪዎሎጂ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስዱ መንገዶች ከቀኑ 6:00 ሠዓት እስከ ምሽት 2:00 ሠዓት ድረስ ድረስ ዝግ እንደሚሆኑ አዲስ አበባ ፖሊስ ገልፆ አሽከርካሪዎች ሌሎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ መልእክቱን አስተላልፏል፡፡

የተከበረው መስጂደል-ሃረም ኢማምና ኻጢብ ሸይኽ ሱደይስ ከወላጅ አልባ ህፃናት ጋር  የአፍጥር ግዜ ሲያሳልፉ
07/04/2023

የተከበረው መስጂደል-ሃረም ኢማምና ኻጢብ ሸይኽ ሱደይስ ከወላጅ አልባ ህፃናት ጋር የአፍጥር ግዜ ሲያሳልፉ

Address

Addis Ababa

Telephone

+251912939959

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when 𝐀𝐘𝐃𝐀𝐍 posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to 𝐀𝐘𝐃𝐀𝐍:

Videos

Share