መልህቅ Podcast

መልህቅ Podcast A Podcast produced by GCME that helps Christian youths grow holistically.

Melhik Podcast S2E41ከጓደኛ መራቅከቤተልሔም አበራ ጋር ያደረግነውን ቆይታ ተከታተሉን።አቅራቢዎች ሳሮን ዮሐንስ እና ትንሳኤ ፈቃዱ ናቸው።በግሬት ኮሚሽን ሚኒስትሪ ኢትዮጵያ እየተዘጋ...
10/02/2024

Melhik Podcast S2E41

ከጓደኛ መራቅ

ከቤተልሔም አበራ ጋር ያደረግነውን ቆይታ ተከታተሉን።
አቅራቢዎች ሳሮን ዮሐንስ እና ትንሳኤ ፈቃዱ ናቸው።
በግሬት ኮሚሽን ሚኒስትሪ ኢትዮጵያ እየተዘጋጀ የሚቀርብ ፖድካስት
ለጓደኛዎ ያጋሩ

Melhik Podcast S2E40የስሜት መለዋወጥከሰብለወንጌል ጥላሁን ጋር ያደረግነውን ቆይታ ተከታተሉን።አቅራቢዎች ሳሮን ዮሐንስ እና ትንሳኤ ፈቃዱ ናቸው።በግሬት ኮሚሽን ሚኒስትሪ ኢትዮጵያ ...
18/01/2024

Melhik Podcast S2E40

የስሜት መለዋወጥ

ከሰብለወንጌል ጥላሁን ጋር ያደረግነውን ቆይታ ተከታተሉን።
አቅራቢዎች ሳሮን ዮሐንስ እና ትንሳኤ ፈቃዱ ናቸው።
በግሬት ኮሚሽን ሚኒስትሪ ኢትዮጵያ እየተዘጋጀ የሚቀርብ ፖድካስት
ለጓደኛዎ ያጋሩ

Christmas Special Program🌲🎄Melhik Podcast S2E39 "እግዚአብሔር ምን ያህል እንደወደደኝ ሳስብ ይገርመኛል"ከአቤነዘር ለገሰ ጋር ያደረግነውን ልዩ የበዓል ፕሮግራም ተ...
06/01/2024

Christmas Special Program🌲🎄
Melhik Podcast S2E39

"እግዚአብሔር ምን ያህል እንደወደደኝ ሳስብ ይገርመኛል"

ከአቤነዘር ለገሰ ጋር ያደረግነውን ልዩ የበዓል ፕሮግራም ተከታተሉን።
አቅራቢዎች ሳሮን ዮሐንስ እና ትንሳኤ ፈቃዱ ናቸው።
በግሬት ኮሚሽን ሚኒስትሪ ኢትዮጵያ እየተዘጋጀ የሚቀርብ ፖድካስት
ለጓደኛዎ ያጋሩ

Melhik Podcast S2E38Perfectionismከዮዲት ዶዳ ጋር ያደረግነውን ቆይታ ተከታተሉን።አቅራቢዎች ሳሮን ዮሐንስ እና ትንሳኤ ፈቃዱ ናቸው።በግሬት ኮሚሽን ሚኒስትሪ ኢትዮጵያ እየተ...
26/11/2023

Melhik Podcast S2E38

Perfectionism

ከዮዲት ዶዳ ጋር ያደረግነውን ቆይታ ተከታተሉን።

አቅራቢዎች ሳሮን ዮሐንስ እና ትንሳኤ ፈቃዱ ናቸው።

በግሬት ኮሚሽን ሚኒስትሪ ኢትዮጵያ እየተዘጋጀ የሚቀርብ ፖድካስት
ለጓደኛዎ ያጋሩ

ለእግሬ መብራት is now available. Check out the link in our bio to listen
23/06/2023

ለእግሬ መብራት is now available. Check out the link in our bio to listen

Melhik Poscast S2E14Tomorrow special episode with ILLASHA FEKADU
06/01/2023

Melhik Poscast S2E14
Tomorrow special episode with ILLASHA FEKADU

Recap on Season 2 Episode 1 -10 Link in bio
15/12/2022

Recap on Season 2 Episode 1 -10
Link in bio

Follow us On TikTokFind us on Social MediasGoogle Podcast | Apple Podcast | Spotifyለጓደኛዎ ያጋሩ መልህቅ Podcast
25/10/2022

Follow us On TikTok

Find us on Social Medias

Google Podcast | Apple Podcast | Spotify

ለጓደኛዎ ያጋሩ መልህቅ Podcast

Melhik Podcast Season 2 Episode 4Wishful Thinking ከዎስታንት  ጋር ያደረግነውን ቆይታ ተከታተሉን።አቅራቢዎች ሳሮን ዮሐንስ እና ትንሳኤ ፈቃዱ ናቸው።በግሬት ኮሚሽ...
20/10/2022

Melhik Podcast Season 2 Episode 4
Wishful Thinking

ከዎስታንት ጋር ያደረግነውን ቆይታ ተከታተሉን።

አቅራቢዎች ሳሮን ዮሐንስ እና ትንሳኤ ፈቃዱ ናቸው።

በግሬት ኮሚሽን ሚኒስትሪ ኢትዮጵያ እየተዘጋጀ የሚቀርብ

04/10/2022
Season 2 intro is now available on all podcast platforms and telegram.
22/09/2022

Season 2 intro is now available on all podcast platforms and telegram.

ነፍስ አትዋሽም ዝምም አትልምእንደ በጎች ትቅበዘበዙ ነበርና፤ አሁን ግን ወደ ነፍሳቹ እረኛ እና ጠባቂ ተመለሳችኋል። 1ኛ ዼጥሮስ 2፡25በዚህ ዘመን በተደጋጋሚ ከምንሰማቸው እኛም ከምንለው ቃ...
08/08/2022

ነፍስ አትዋሽም ዝምም አትልም

እንደ በጎች ትቅበዘበዙ ነበርና፤ አሁን ግን ወደ ነፍሳቹ እረኛ እና ጠባቂ ተመለሳችኋል። 1ኛ
ዼጥሮስ 2፡25
በዚህ ዘመን በተደጋጋሚ ከምንሰማቸው እኛም ከምንለው ቃል ውስጥ ‘busy ነኝ’ የሚለው ነው።
ለዚህም ምክንያቱ ብዙ ጊዜያችንን ራሳችንንም የሚፈልጉ ነገሮች መኖራቸው ነው። 24 ሰአታቱን
በተለያዩ ነገሮች ተወጣጥረን ቀን ይነጋል ይመሻል፤ በዚህ ‘busy’ በሆነው ቀናችን መሃል ግን
ሁሌም ከውጭ የምንሰማቸው ድምፆች በጨመሩ ቁጥር ድምፁ የሚቀንስ ፤ ከተጣበበው ቀናችን
መሃል ላፍታ የዝምታን ጊዜ ስናገኝ የሚጨምር ፤ ነገር ግን መቼም ቢሆን የማይጠፋ ፥ የማያቋርጥ
የነፍስ ጩኸት አለ። እንደስጋችን ነፍሳችን ማብቅያዋ ምድር ላይ አይደለም። ይህን ተቀበልነውም
አልተቀበልነውም ነፍሳችን ጠንቅቃ ታውቃለች ረጅሙን የዘላለም መቆያዋን ለማስተካከል ደግሞ
ሁሌም ፈጣሪዋን፣ የተፈጠረችበትን አላማ ለማወቅና ለማድረግ ትጓጓለች። ይህን የሚነግራት
ደግሞ ፈጣሪዋ መሆኑን በሚገባ ታውቃለች። በመሆኑም ነፍሳችን ቢገባንም ባይገባንም በየእለቱ
ፈጣሪዋን በመፈለግ ውስጥ ‘buስy’ በሆነው ቀናችን ውስጥ ሰላም እየነሳችን ፈጣሪን
ትናፍቃለች።
ይህን የነፍሳችንን ጩሀት በብዙ ነገሮች ለመመለስ እንሞክራለን ሳይሳካም ሲቀር ‘ignore’
ለማድረግ እንሞክራለን። ለመመለስ ከምንሞክርባቸው መንገዶች አንዱ ጥያቄዋን ተቀብለን
ፈጣሪ ይገኝበታል ብለን ወደምናስበው ሃይማኖት ገብተን ደረቅ የሃይማኖት ስርአቶችን እና
ተግባራትን በማከናወን ሃይል የሌለው የሃይማኖት መልክ ይዘን ምንም እንኳን ነፍሳችን አሁንም
ፈጣሪዋን ብትፈልግም በስርዓት ውስጥ እንዳገኘችው አድርገን ደጋግመን እየነገርናት ዝም
ለማሰኘት መሞከር ነው። በዚህ ሙከራ ውስጥ ራሳችንንም ሌሎችንም እያታለልን የውሸት
ነገሮችን እንደ እውነት አድርገን ተቀብለን እንኖራለን፤ ሌላው ጥያቄውን ለመመለስ ሳይሆን
‘ignore’ ለማድረግ የምንሞክርበት መንገድ ደግሞ ጩኸቷን ላለመስማት አይምሯችንን እንዳያስብ
እንደሱስ ባሉ ሌሎች ነገሮች መወጠር ነው። ነገር ግን ነፍስ እንደሌሎች ሰዎች እንደራሳችን
አይምሮም አትታለልም። የውጪው ጩኸት ስለበዛም ዝም አትልም ሁሌም ትጮሃለች
ትጣራለች።
ለዚህ ለማያቋርጠው የነፍሳችን ጩህት ትክክለኛ እና በቂ መልስ ያለው ራሱ የፈጠራት ጋር ብቻ
ነው። እርሱን በትክክል ስታገኝ አቅጣጫን አጥታ ንፋስ ወደፈለገው የሚገፋት በባህር ላይ ያለች
መርከብ መልህቋን በባህሩ ላይ በምትጥልበት ጊዜ ቀጥ ብላ እንደምትቆም እረፍት አጥታ
የመጣው ሁሉ ወደፈለገው የሚወስዳት ነፍሳችን እረፍት ይሆንላታል ፀንታም ትቆማለች።
ፈጣሪዋን ደግሞ በሌሎች ሰዎች አልያም መንገዶች ሳይሆን በሚገባን መልኩ ራሱን በገለጠበት
ፍፁም በሆነው ቃሉ ውስጥ ታውቀዋለች፤ ባወቀችው ልክ ደግሞ ታውቆ የማያልቅ የማይጠገብ
ማንነቱን ለማወቅ በፀሎት እና በቃሉ እየበረታች እርሱን ወደመምሰል ታድጋለች ያን ጊዜ ፍፁም
እረፍት እና ደስታ ይሆንላታል።

By: Meklit Tasew

Bonus Episode with Dr. Tariku Fufa, Part 3 last episode is now available on all podcast applications and our telegram ch...
21/06/2022

Bonus Episode with Dr. Tariku Fufa, Part 3 last episode is now available on all podcast applications and our telegram channel. You can find the link in our bio.

ሴትነት - Melhik Devotionalእኛ ፍጥረቱ ነንና፤ እንመላለስበት ዘንድ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጀውን መልካሙን ስራ ለማድረግ በክርስቶስ ኢየሱስ ተፈጠርን። ኤፌሶን 2፡10የፆታ ጉዳ...
17/06/2022

ሴትነት - Melhik Devotional

እኛ ፍጥረቱ ነንና፤ እንመላለስበት ዘንድ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጀውን መልካሙን ስራ ለማድረግ በክርስቶስ ኢየሱስ ተፈጠርን። ኤፌሶን 2፡10
የፆታ ጉዳይ በየዘመናቱ ጎራ አስለይቶ ሲያከራክር የኖረ እና ያለም ጉዳይ ነው። አንዳንዶች በተለይም በሰለጠነው አለም ያሉ ሰዎች ፅንፍ ይዘው ልዩነቱን እጅግ እያጠበቡ ሲመጡ እናያለን። ሊሎች ደግሞ በተቃራኒው ልዩነቱ እጅግ በማግዘፍ ሰውን ከማንነቱ ውጪ በፆታው ብቻ ሲመዝኑ እናያለን። ሴቶች ላይ የሚደርሰው ግፍ ብዛት ተፈጥሮ ራሱ የበደላቸው እንዲመስለን ያደርጋል ይህን ለመከላከል ከህግ አውጪዎች ጀምሮ የተለያዩ አካላት ህግ በማውጣት እና በማስተማር ስለሴቶች እኩልነት ብዙ ቢነገርም አሁንም ድረስ ግን አለም ለሴቶች ከባድ ቦታ ሆና እንደቀጠለች ናት። ከዚህም ተነስተው ብዙ ሴቶች ሴትነትን ሲጠሉት ይስተዋላል።
የውጪውን ትተን በክርስቲያኖች መካከል ራሱ ከተፈጠርንበት አላማ ጀምረን ብዙ የአመለካከት ልዩነቶች አሉ አንዳንዶች የወንድን ቀድሞ መፈጠር እና እግዚአብሔርም ሴትን ሲፈጥር ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም ምቹ ረዳትን እንፍጠርለት የሚለውን ቃል በመያዝ ሴት ወንድን ለመርዳት ብቻ የተፈጠረች እና የህይወት አላማዋ ስኬትም ጥሩ ሚስት በመሆኗ አለፍ ሲልም መልካም እናት በመሆኗ ላይ ብቻ የተመረኮዘ አርገው ሲቆጥሩት እናያለን። ነገር ግን የተፈጠርንበትን አላማ ለመረዳት ያለን ብቸኛ አማራጭ ራሱ ፈጣሪያችንን መጠየቅ ሲሆን እርሱ ደግሞ ገና ሳንጠይቀው በቃሉ ውስጥ ለምን እና እንዴት እንደፈጠረን ገልጦ እናገኛለን። በዘፍጥረት መፅሃፍ ላይ እግዚአብሔር በመልኩ እና እንደምሳሌው ወንድ እና ሴት አድርጎ እንደፈጠራቸው እናያለን፤ ይቀጥልና እንዲበዙ እንዲባዙ ምድርንም እንዲሞሏት እንዲገዟትም ሲያዛቸው እንመለከታለን። ያ ማለት እግዚአብሔር ሰውን የፈጠረበት አላማ በፍጥረቱ መሃል የበረከቱ ማሳያዎች ሆነን የእርሱን መልክ እንድንገልጥ እና ፍጥረቱንም እንድንገዛለት እንደሆነ እንረዳለን። መግዛት ደግሞ መንከባከብ እና መጠበቅ መምራትም እንደሆነ እንረዳለን። ይህ በእንዲህ እንዳለ የወንድ ቀድሞ መፈጠርን ምክንያት በማድረግ የሴትን የመፈጠር አላማ ከሱ ጥቅም አንፃር ብቻ መመልከት እይታችንን ከፈጣሪ አንስተን ወደ ሰው እንድናዞር ከማድረጉም በተጨማሪ ያላገቡ ሴቶችን ያላካተተ እይታ ይሆንብናል። ራስ ወዳድ ለሆነው የሰው ባህሪም ቃሉን በተሳሳታ መንገድ መጠቀሚያ እንዲያደርግ መንገድ ይከፍታል። አዳምም ሄዋንን ሲያያት ሴት ብሎ የጠራት አንቺ ከእኔ ታንሻለሽ ወይም ረዳቴ ብቻ ነሽ ለማለት ሳይሆን ሴት ከሚለው የቃል ትርጉም ትወክይያለሽ፣ ትተኪያለሽ አልያም ምትኬ ነሽ ለማለት እንደሆነ እንረዳለን ያ ማለት ከውድቀት በፊት መበላለጥ አይደለም በእግዚአብሔር ፥ በአዳምም ልብ ውስጥ የሌለ ሃሳብ ነው። ከውድቀት በፊት የተፈጠርንበት አላማ ይህ መሆኑን ከተረዳን በአዲስ ኪዳንም በኤፌሶን መፅሐፍ ላይ እግዚአብሔር ለሴት ያለው አላማ ከውድቀት በኋላ እንኳን እንዳልተለወጠ አስቀድመን እንመላለስበት ዘንድ ያዘጋጀውን መልካም ስራ ለማድረግ በክርስቶስ እየሱስ ተፈጠርን ከሚለው ቃል እንረዳለን።
የተፈጠርንበትን አላማ ከፈጣሪያችን አንፃር በሚገባ ስንረዳ በምድር ላይ የምናያቸው ሴትነትን አሳንሰው እንድንጠላው የሚያደርጉ ነገሮች ሁሉ የእግዚአብሔር ተቀዳሚ አላማው ሳይሆን በሃጢያት ምክንያት የመጡ የእርግማን እና የሰው ልጅ ራስ ወዳድነት ያመጣቸው ነገሮች መሆናቸውን እንረዳለን። መፅሐፍ ቅዱስ ያለንን ሁሉ ለእግዚአብሔር ክብር እንድናውልና እንድናደርገው ይነግረናል። ያ ማለት ሴት በመሆናችን እግዚአብሔር የሰጠንን ድንቅ ተፈጥሮ ከወንድ ጋር ያለንን ልዩነትም በደስታ ተቀብለነው ለክብሩ ማዋል አለብን።
መንፈሳዊ ወይም ልባም ሴት በምሳሌ መፅሐፍ ላይ እንደተጠቀሰችው በውጫዊ ነገሯ ላይ ብቻ ያላተኮረች እና እግዚአብሔርን የምትፈራ በውስጥም በውጪም ትጉ የሆነች እና በክርስቶስ ያላትን ዋጋ አውቃ እንደሃና ምናምንቴ አላመሆኗን የተረዳች ሴት ናት። ልባም ሴት ያለችበትን ቤት፣ ቦታ፣ መስሪያ ቤት ትሰራለች ምድራዊውንም ሰማያዊውንም ቤት በጥበብ ትሰራለች። ዋጋዋን ከፍ የሚያደርገው አለም በተለያየ መልኩ እንደሚሰብከው ያላት ውጫዊ ገጽታ ወይም የከበቧት ሰዎች ብዛት ሳይሆኑ ክርስቶስ እንደሆነ ስለምትረዳ ዕለት ተዕለት ከእርሱ ጋር ያላትን ግንኙነት በትጋት ትጠብቃለች ፤ በኑሮዋም እርሱን ትገልጣለች። እግዚአብሔር ሲፈጥራት ከወንድ ጋር ያላትን ልዩነት በደስታ ተቀብላ በምድር ላይ የሚያበቁ ነገሮች ለማግኘት ሳይሆን ለሰጪው ክብር ትጠቀምበታለች። የህይወት ተቀዳሚ አላማዋ ጥሩ ባል ማግባት አይደለም ለትልቁ ዘላለማዊው ትዳር መዘጋጀት እንጂ፤ ብታገባም ግን ትልቁን ትዳር አድምቃ የምትገልጥበት እና የምትዘጋጅበት ይሆናል።
መፅሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ወዳጆች እንደሆንን እና ሃሳቡንም እንደሚገልጥልን ይናገራል በመሆኑም እንደመንፈሳዊያን ልባም ሴቶች ከወዳጃችን ጋር በጸሎት እና በቃሉ ጊዜ በማሳለፍ በየአቅጣጫው ለሚሰማው ጩኸት ጆሮ ሳንሰጥ ለህይወታችን ያለውን አላማ በማወቅ በፍጥረቱ መካከል ስንመላለስ መልኩን እየገለጥን ለክብሩ በመኖር ዘላለማዊ ለሆነው ትዳራችን ልንዘጋጅ ይገባል።
ተጨማሪ የምንባብ ክፍል፦ ዘፍጥረት 1-3፣ ኤፌሶን 2፡10፣ ምሳሌ 31፣ ዩሐንስ 15፡15

Bonus Episode with Dr. Tariku Fufa, Part 1. You can find the link in our bio.
03/06/2022

Bonus Episode with Dr. Tariku Fufa, Part 1. You can find the link in our bio.

ፍቅር ምንድን ነው? - Melhik Devotionalፍቅር እንደዚህ ነው እግዚአብሔር ራሱ እንደወደደን ስለ ሃጢያታችንም ማስተሰርያ ይሆን ዘንድ ልጁን እንደላከ እንጂ እኛ እግዚአብሔርን እንደወ...
26/05/2022

ፍቅር ምንድን ነው? - Melhik Devotional

ፍቅር እንደዚህ ነው እግዚአብሔር ራሱ እንደወደደን ስለ ሃጢያታችንም ማስተሰርያ ይሆን ዘንድ ልጁን እንደላከ እንጂ እኛ እግዚአብሔርን እንደወደድነው አይደለም። 1ኛ ዩሐ 4፡10
በየዘመናቱ ስለፍቅር ብዙ ተነግሯል ብዙ ተዘፍኗል ተዘምሯልም በተወራው ልክ ባይሆንም ብዙ ተኑሯል። ፍቅር እጅግ ሰፊ እና ጥልቅ የሆነ ሃሳብ በመሆኑ በአጭር ቃል ለመናገር እና ለመግለፅ ያዳግታል። የፍቅር አይነቶች ብለን ለምንዘረዝራቸው ነገሮች የምንሰጣቸው የተለያዩ ትርጓሜዎች አሉ። በእነዚህ ዓለም ፍቅርን በምትገልፅባቸው መንገዶች ውስጥ በብዛት የምናስተውለው የጋራ ነገር ሁሉም አይነት ፍቅር ሲተረጎም ከተፈቃሪው ማንነት አንፃር መሆኑ ነው። ተፈቃሪ ለመፈቀር የሚያበቃ አፍቃሪን የሚስብ አልያም የሚጠቅም አንዳች ነገር እንዳለው ይነግሩናል። ለምሳሌ ባል ስለሚስቱ ሲያወራ የወደዳት ስለቁንጅናዋ አልያም ስላላት መልካም ባህሪ መሆኑን ሲናገር ልጅ ደግሞ ስለእናት ፍቅር ሲያወራ 9 ወር በሆዷ ተሸክማ አጥብታና ተንከባክባ ስላሳደገችው መሆኑን ይናገራል።
መጽሐፍ ቅዱስ ግን ከዚህ በተለየ መልኩ ፍቅርን ይገልፅልናል የ በሚል ፊደል ጀምሮ ፍቅር የሚል ቅጥያን ሳያስከትል ፍቅር እግዚአብሔር ነው ይለናል ይቀጥልና ፍቅር የሌለው እግዚአብሔርን እንደማያውቅ ይናግረናል። ፍቅር ዓለም እንደምትለው የሚስበንን ነገር ስናይ የሚፈጠር እና የሳበን ነገር ሲጠፋ አብሮ የሚጠፋ ስሜት ሳይሆን ራሱ እግዚአብሔር ነው ባህሪው ብቻ ሳይሆን ማንነቱ ነው ያ ማለት በተፈቃሪው ላይ ካየነው የሚስብ ነገር የሚመጣ ወይም የሳበንን ነገር ለራሳችን ለማድረግ ካለን ጥልቅ መሻት የሚመጣ አምኖናዊ የራስ ወዳድነት ስሜት አይደለም። ፍቅር ራስን መስጠት ነው የምንቀበለውን ነገር ሳንጠብቅ ያለንን ሁሉ መስጠት ነው። ይህ ፍቅር ደግሞ በእቅፉ ውስጥ ባለው በአንድ ልጁ ተተረከ ፍቅር የተወሳሰበ ሃሳብ ሳይሆን የተኖረ በሚገባን መልኩ እንደ አምሳላችን የተገለፀ ነው። ቃሉ እንደሚል ፍቅር የከፈለልንን ዋጋ አይተን ክርስቶስን እንደ ወደድነው ሳይሆን ብዙዎቻችን እንደምንክደው እንኳን እያወቀ ፍቅሩ የአመፃችንን ብዛት ሸፍኖልን የባርያን መልክ ይዞ ራስን እስከመስጠት እንደወደደን እንደርሱ ነው።
ሁሉም የፍቅር አይነቶች የምንላቸው ሁሉ ከበቂ በላይ በሆነው በእግዚአብሔር ፍቅር ማለትም እርሱ እኛን የወደደበትን መውደድ በመረዳት እና በእርሱ በመርካት ካልተቃኙ በስተቀር እውነተኛ ሊሆኑ አይችሉም ምክንያቱም ፍቅር ከራሱ ከእግዚአብሔር የምንካፈለው ነገር እንጂ በራሳችን ወይም ከምድራዊ ነገር በመነሳት የምናገኘው ስሜት አይደለም።
በአከባቢያችን ያሉ እንወዳቸዋለን የምንላቸውን ሰዎች በእውነተኛ ፍቅር ለመውደድ ፍቅር ወደሆነው እና በሚገባን መልኩ ወደተረጎመው ወደ እግዚአብሔር መጠጋት አለብን። እርሱን ደግሞ በቃሉ ውስጥ እና በፀሎት እናገኘዋለን። ተጨማሪ የንባብ ክፍሎች፦ 1ኛ ዩሐ 4፡ 7_21, 1ኛ ጴጥ 4፡8, ዪሐ 1፡18

By: Meklit Tasew

Bonus Episode Part 3 last part with Dr. Bekele Shanko is available now. You can listen by using the link in our bio.
19/05/2022

Bonus Episode Part 3 last part with Dr. Bekele Shanko is available now. You can listen by using the link in our bio.

Bonus Episode Part 2 With Doctor Bekele Shanko is available now. You can listen by using the link in our bio.
08/05/2022

Bonus Episode Part 2 With Doctor Bekele Shanko is available now. You can listen by using the link in our bio.

Bonus Episode with Dr. Bekele Shanko, Part 1ዛሬ ከዶ/ር በቀለ ሻንቆ ጋር ቆይታ አርገናል ተከታትሉን።አቅራቢዎች ሳሮን ዮሐንስ እና ትንሳኤ ፈቃዱ ናቸው።በተሻለ ጥራት...
30/04/2022

Bonus Episode with Dr. Bekele Shanko, Part 1

ዛሬ ከዶ/ር በቀለ ሻንቆ ጋር ቆይታ አርገናል ተከታትሉን።

አቅራቢዎች ሳሮን ዮሐንስ እና ትንሳኤ ፈቃዱ ናቸው።

በተሻለ ጥራት ለመስማት ከታች ባሉት የፖድካስት አማራጮች Subscribe ያድርጉ።

Google Podcast | Apple Podcast | Spotify

ለጓደኛዎ ያጋሩ

30/04/2022

From Epsiode 22

የእግዚአብሕር ቃል የመጨረሻው እሴታችን ነው

ዶ/ር ደስታ ሳሙኤል

24/04/2022

ክርስቶስ በድሎ ሳይሆን ተበድሎ ነው ይቅርታ ያደረገው።

From Episode 19

Christ is risen!
24/04/2022

Christ is risen!

18/04/2022

መልህቅን በመስማት የተጠቀማችሁት ነገር ካለ፤ በፅሁፍ፥ በድምፅ፥ ብትፈልጉ በመደወል አካፍሉን

ስልክ ቁጥራችን +251986689090

መልህቅ ፖድካስት

ለጓደኛዎ ያጋሩ

16/04/2022

የዮሴፍ ስመኝ ምስክርነት ስለመልህቅ ፖድካስት

መልህቅን በመስማት የተጠቀማችሁት ነገር ካለ፤ በፅሁፍ፥ በድምፅ፥ ብትፈልጉ በመደወል አካፍሉን

ስልክ ቁጥራችን +251986689090

መልህቅ ማስታወቂያሰላም አድማጮቻችን እንደምን ቆያችሁየመጀመሪያውን ምዕራፍ ጨርሰን ሁለተኛውን ምዕራፍ ልንጀምር ከጫፍ ደርሰናልነገር ግን ሁለተኛውን ምዕራፍ ከመጀመራችን በፊት በመጀመሪያው ምዕ...
15/04/2022

መልህቅ ማስታወቂያ

ሰላም አድማጮቻችን እንደምን ቆያችሁ

የመጀመሪያውን ምዕራፍ ጨርሰን ሁለተኛውን ምዕራፍ ልንጀምር ከጫፍ ደርሰናል

ነገር ግን ሁለተኛውን ምዕራፍ ከመጀመራችን በፊት በመጀመሪያው ምዕራፍ ከተጠቀሙ ሰዎች ብዙ ምስክርነቶችን መስማት እንፈልጋለን።

ስለዚህ መልህቅን በመስማት የተጠቀማችሁት ነገር ካለ፤ በፅሁፍ(message)፥ በድምፅ፥ ብትፈልጉ በመደወል ብታካፍሉን እጅግ እጅግ በጣም መነሳሳት ይሆነናል። ከሁሉ በላይ ደግሞ እግዚአብሔርን አብረን እናመሰግናለን።

ስልክ ቁጥራችን +251986689090

መልህቅ ፖድካስት

ለጓደኛዎ ያጋሩ

Season 2 coming soon      #
05/04/2022

Season 2 coming soon #

29/03/2022

Walk in love from Episode 8

26/03/2022

The books are ready!

Address

Gurdshola Holy City Center
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when መልህቅ Podcast posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to መልህቅ Podcast:

Videos

Share

Category



You may also like