
31/01/2025
እንዲያ ተሞሽሬ አምሮብኝ ተውቤ….
አማረብሽ ሲለኝ መላው ቤተሰቤ…..
አይዞሽ ሙሽሪት አይበልሽ ቅር ትዳር ጥሩ ነው ያሞቃል ፍቅር
አይዞሽ ሙሽሪት አይበልሽ ከፋ ሁሉም ያገባል በየወረፋ (2)
እየተባለ የተዘፈው
ሰርጌ ትዝታው ዛሬም ህያው ነው
(አስቴር አወቀ)
ሰርግ የተጋቢዎች ትዝታ ብቻ አይደለም ፤ የዝግጅቱ ታዳሚ፣የድግሱ አጋፋሪ የጥንዶቹ ቤተሰብ፣ ወዳጅ ዘመድ ፣አጃቢም ጭምር እንጂ፡፡ምን ይሄ ብቻ ሰርግ ቢዝነስም ጭምር ነው፡፡ የሰርግ ግብዓት ከሆኑ ነገሮች እስከ ሰርገኛ
የሰርግ ማድመቂያ የሆኑ ነገሮችን ሻጩም አከራዩም ሰሪውም ከሰርግ ትዝታ ጋር ልዩ መስተጋብር እና ቁርኝት አለው ፡፡ ታዲያ እንዲህ ተዋናዩ ብዙ የሆነው ሰርግ አልፎም በትዝታ የመናፈቁ አልፎም ህያው የመሆኑ ምንያት በሰው ልብ ውስጥ እና ታሪክ ውስጥ ያለው ስፍራም ከፍ ያለ መሆኑ ያለ ምክኒያት አይደልም አይረሴ ሆኖ በመከወኑ እንጂ ፡፡ እኛም ዛሬ ያስደመመሙን የተለያዩ የሰርግ ከንውኖች ልናስቃኛችሁ ወደድን። ተከታዩን ሊንክ በመጫን ቪድዮውን ይመልከቱ።
https://youtu.be/Dp2P5pedxi0