Abol ምን አዲስ አለ! What is new!

 #ማይናማር" በህይወት እወጣለሁ ብዬ አላሰብኩም ነበር " - ሽኩር  (የአይን ምስክር)" ስሜ ሽኩር ይባላል።የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ዓለምን ባመሰቃቃላ ግዜ እኔ ሥራ ካጡ ሰዎች አንዱ ነበርኩ።...
29/11/2024

#ማይናማር

" በህይወት እወጣለሁ ብዬ አላሰብኩም ነበር " - ሽኩር (የአይን ምስክር)

" ስሜ ሽኩር ይባላል።

የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ዓለምን ባመሰቃቃላ ግዜ እኔ ሥራ ካጡ ሰዎች አንዱ ነበርኩ።

በአገራችን ያለው የኢኮኖሚ ሁኔታ ጉዳዩን የበለጠ አባብሶት የነበረ ቢሆንም ለመኖር ሲባል ለ 7ወር የህል በመምህርነት አገልግያለሁ። ነገር ግን ገቢዬ ፍላጎቴን ለማሟላት በቂ አልነበረም።

አንድ ቀን በታይላንድ ውስጥ የውሂብ ማስገቢያ ኦፕሬተር ለመሆን በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የስራ ማስታወቂያ አየሁ።

በጣም ማራኪ መስሎ ታየኝ። በወር 1,000 ዶላር ቃል ገቡልኝ።

ማረፊያ ቦታ እና በቀን 8 ግዜ የምግብ ሰዓት እንደለው ተነገረኝ።

ቤተሰቤን እና ራሴን ከድህነት ለማላቀቅ እና የተሻለ ህይወት ለመኖር ወደ ታይላንድ መሄድ እንዳለብኝ አሰብኩ።

በማስታወቂያው ላይ ያለውን ቁጥር አግኝቼ የመፃፍ ችሎታዬን እና የእንግሊዝኛ ችሎታዬን በቪዲዮ ገመገሙ።

ከዛም ታይላድ ከሄድኩ በኃላ ተወዳደርኩ እና ፈተናውን አልፌ በመቀጠሬ ኩራት ተሰማኝ።

🛬 ስራው ለህልሜ መልስ ይሆናል ብዬ ነበር 🛬

በታይላንድ ውስጥ ያለው ስራ ለህልሜ መልስ ይሆናል ብዬ አስቤ ነበር ፤ ለቤተሰቤ እና ለጓደኞቼ የተሻለ ህይወት ይሰጥልኝ ይሆን ብዬም ነበር።

ነገር ግን ያሰብኩት ነገር ቅዠት ሆኖ ተገኘ።

ባንኮክ አየር ማረፊያ ስደርስ አንድ ሰው ወደ መድረሻው በር ወሰደኝና ሹፌሩን እንድጠብቅ ነገረኝ።

ሹፌሩ እኔንና ሌላ ሠራተኛ ጨምሮ እዞን ሄደ።

እዞን የሄደው ማይ-ሶት ወደምትባል የታይላንድ ትንሽ ከተማ (ማይናማር ጋር ትዋሰናለች) ወደዛ ነው።

ያኔ ጨለማ ስለነበር ምን እየሆነ እንዳለ ሙሉ በሙሉ አላውቅም ነበር።

ጥቂት ሰዎች ወደ እኛ መጡ፣ እና በጀልባ እንድንገባ አስገደዱን። ሳንፈልግ ወደ ማይናማር ወሰዱን። ማይናማር ወዳለው ግቢ ስንደርስ ደነገጥኩ፣ ፈራሁ ፤ አቅመ ቢስ ሆንኩኝ።

🏦 አሰሪዎቻችን ህይወታችንን ተቆጣጠሩት 🏦

ግቢው ሰፊና በህንጻዎች የተሞላ ነበር።

እያንዳንዱ ሕንፃ አራት ፎቆች ያሉት ሲሆን እያንዳንዱ ወለል 16 ክፍሎች አሉት። እያንዳንዱ ክፍል አራት ተደራቢ አልጋዎች አሉት።

በግቢው ውስጥ አሠሪዎቻችን ሕይወታችንን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጠሩት።

በሳምንት ሰባት ቀን እስከ 16 ሰአት እንድንሰራ አድርገውናል።

በሥራ ላይ እያለ እንቅልፍ ከተሰማን ወይም እግሮቻችንን ትይዩ ካላደረግን እንቀጣለን።

በግቢዎቹ ውስጥ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ነበሩ።

በጣም ብዙ ኢትዮጵያዊያን ፣ ህንዶች፣ ፊሊፒኖዎች፣ ፓኪስታናውያን፣ ቻይናውያን፣ ኢንዶኔዥያውያን፣ ሩሲያውያን፣ ዩክሬናውያን፣ ታይላንድ፣ ጃፓናውያን፣ አፍሪካውያን ከኡጋንዳ እና ኬንያ እና የአካባቢው ማይናማር ሰዎች ጭምር ይገኙበታል።

👨‍💻 ስራው ማጭበርበር ነበር 👨‍💻

በግቢው ውስጥ የነበረው ስራ አሰቃቂ ነበር።

ዋናው ሥራው በCrypto-currency ማጭበርበሮች በዓለም ዙሪያ ካሉ ሰዎች ገንዘብ መስረቅ ነበር።

አሰሪዎቻችን በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የውሸት መገለጫዎችን (ፌክ ፕሮፋይል የሴት / የወንድ) እንድንፈጥር አስገድደውናል።

የተዘጋጀውን ስክሪፕት ተከትዬ፣ ከአሜሪካ ፣ ከጃፓን እንዲሁም ከታይዋን የውጭ ዜጎች እንዲወዱኝ አድርጌአለሁ።

አመኔታቸዉን ካገኘሁ በኋላ ብዙ ገንዘብ ማግኘት እንዲችሉ የCrypto-currency መድረክን አስተዋውቄያለሁ።

ግን ሁሉም ውሸት ነበር።

እስከ ዛሬ ድረስ የተገደድኩበትን ሥራ ከቤተሰብ ወይም ከጓደኞቼ ጋር ለመካፈል አፍራለሁ።

ሰዎችን በማጭበርበር ተጸየፍኩኝ ነገር ግን ምንም ምርጫ አልነበረኝም ፤ ለህይወቴ እፈራ ስለነበር ነው።

🪖 ቦታው በታጠቁ ሰዎች ነው የሚጠበቀው 🪖

ከዚያ ቦታ ለማምለጥ ምንም መንገድ አልነበረም። 10 ጫማ ከፍታ ያላቸው ግድግዳዎች በላዩ ላይ ሽቦዎች ነበሯቸው።

ቦታው በታጠቁ ሰዎች ከፍተኛ ጥበቃ ይደረግለት ነበር።

ከግቢው ለማምለጥ የሚደረግ ማንኛውም ሙከራ የሞት ምኞት ነው።

ሰዎችን ማጭበርበር አለመቻል ማለት አካላዊ ጉዳት ወይም ሞትንም ያስከትላል።

አንድ ጓደኛችን ለቅጣት ወደ ‘ ውሃ እስር ቤት ’ ተላከ። ተደብድቦ ወደ ቢሮው ተመለሰ ከዛ በኃላ ማውራትም ሆነ መሄድ አልቻለም።

ሞባይል ስልኮቻችንን፣ ፓስፖርቶቻችንን እና ሁሉንም የግል ማህደሮች የባንክ ካርዶችን ጨምሮ ነው የተወሰደው።

የሚሉንን ያህል ብንሰራም ቃል የገቡትን ገንዘብ በፍጹም አይከፍሉም።

💰 3000 ዶላር ከፈልን 💰

ወደ ቤት ሀገሬ ለመምጣት በጣም ፈለኩኝ።

ነገር ግን አጋቾቼ ለመልቀቅ 5,000 ዶላር መክፈል እንዳለብኝ ነገሩኝ።

የሌለኝ እና ማድረግ የማልችለው ገንዘብ ስለሆነ ከሌሎች ሰዎች ጋር በመሆን ከአለቃው ጋር በድጋሚ ለመደራደር ሞከርን።

3000 ዶላር ከፈልኩኝ፣ በመጨረሻም ለቀቁኝ።

ማይናማር ወደ ባንኮክ መሻገር በጣም አስፈሪ ነበር ነገር ግን የአለህ ፊቃድ ሁኖ ከዛ እስር ቤት ወጣሁ።

ከዚያ መከራ በመትረፌ እፎይታ ተሰማኝ።

በህይወት እወጣለሁ ብዬ አላሰብኩም ነበር። ለዚህ እድል እና እንዲወጣ ለረዱኝ ሰዎች የዘላለም አመስጋኝ እሆናለሁ።

ወደፊት እየሄድኩ፣ አዲስ ጅምር እፈልጋለሁ። አሁን ቤተሰቤን ለማስተዳደር ጥሩ ሥራ እየፈለግኩ ነው።

💻 በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የውሸት ማስታወቂያ አያለሁ 💻

አሁንም በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የውሸት የስራ ማስታወቂያዎችን እያየሁ ነው። ይህን ሳይ በግቢው ውስጥ የታሰሩትን ሰራተኞች አስባለሁ።

የሀገራት መንግስታት እንዲሁም ሌሎች ኤጀንሲዎች ሰዎችን ከህገወጥ ዝውውር እና ከግዳጅ የጉልበት ስራ ለመጠበቅ ስለዚህ ጉዳይ የበለጠ ግንዛቤ እንደሚገነቡ ተስፋ አደርጋለሁ።

ይህ መቆም አለበት !

ህብረተሰባችን ከህገወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎችና ህገ ወጥ ጉዞ ራሱንና ልጆቹን መጠበቅ አለበት። "

(ሽኩር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ)

ምንጭ፡ tikvahethiopia

ጨካኝ ጊዜ❗️በእረፍቷ ቀን ቅዳሜ ልጇን ይዛ ወላጆቿን ለመጠየቅ ወደ ወላጇቿ ቤት ሄደች ።በቀን 14/03/2017 ቅዳሜ ምሽት ከወላጆቿ ጋር ስትጫዎት መሳሪያ የታጠቁ አጋቾች በገጠሯ መንደር የ...
29/11/2024

ጨካኝ ጊዜ❗️

በእረፍቷ ቀን ቅዳሜ ልጇን ይዛ ወላጆቿን ለመጠየቅ ወደ ወላጇቿ ቤት ሄደች ።

በቀን 14/03/2017 ቅዳሜ ምሽት ከወላጆቿ ጋር ስትጫዎት መሳሪያ የታጠቁ አጋቾች በገጠሯ መንደር የምትገኘውን ቤት በር አንኳኩ።

በሩ ሲከፈት መሳሪያ ተኩሰው አባት ከመቀመጫቸው እንዳይነሱ አዘው ደጋግመው እየተኮሱ ወደ ቤት ዘለቁ ።
ሁሉም የቤተሰብ አባላት ተኩሱን ፈርተውና ተደናግጠው መሬት ላይ ተኙ። በዚህ መካከል የምታለቅስ ህጻን ልጇን አቅፋ ስታለቅስ የነበረችው እንግዳ በጠላፊዎች እጅ ወደቀች ። ጨካኞች ልጇን ከእቅፏ ነጥቀው አያት ሰጥተው " በወላድ አምላክ ልጄን ተውልኝ " እያሉ የሚማጸኗቸን ደካማ እናት ክፉ ጨካኞች ተሳለቁባቸው ።

ከመሳለቅ አልፈው እናቷን በሰደፍ መትተውና ረግጠው ደብድበዋቸው ልጃቸውን በኃይል ጠልፈው ሄዱ .

አጋቾች በወላጆቿ እጅ ገብቶ የማያውቀውን ገንዘብ ጠይቀው ገንዘብ ካልሰጡ እርምጃ እንደሚወስዱ አሳዎቁ .

የእኛ ጉዶች የእኛ አጋች ጠላፊዎች በእናት ላይ የማይራሩ በዚህ ልክ ጨካኞች ናቸው ❗️

ይህን አሳዛኙ አጋጣሚ ያጋራው ጋዜጠኛ ነቢዩ ሲራክ ነው።

ዓዲግራት እና የከንቲባ ሹመትአንደኛውን ከንቲባ የአቶ ጌታቸው ረዳ ጊዜያዊ አስተዳደር ሲሾም አንዱን በደብረጽዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው የህወሓት ቡድን የሾመው ነው።ከትላንት በስቲያ የጊዜያዊ አ...
29/11/2024

ዓዲግራት እና የከንቲባ ሹመት

አንደኛውን ከንቲባ የአቶ ጌታቸው ረዳ ጊዜያዊ አስተዳደር ሲሾም አንዱን በደብረጽዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው የህወሓት ቡድን የሾመው ነው።

ከትላንት በስቲያ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ምስራቃዊ ዞን ፅ/ቤት በፃፈው የሹመት ደብዳቤ የዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ መምህሩን ዓለም አረጋዊን የከተማይቱ ከንቲባ አድርጎ ሾሟል።

አቶ ዓለም የሹመት ደብዳቤ እንደደረሳቸው አረጋግጠዋል።

" ጊዜያዊ አስታዳደሩ በተቋቋመበት ህግ እና አሰራር መሰረት ወደ ስራ ገብቻለሁ አሁን ላይ በፅ/ቤት ስራ ርክክብ እያደረኩ ነው " ብለዋል።

ትላንትና ደግሞ በደብረጽዮን (ዶ/ር) የሚመራው የህወሓት ቡድን ዓዲግራት ከተማ በተካሄደ የም/ቤት ጉባኤ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ የነበሩትን ረዳኢ ገ/እግዚአብሔርን የከተማው ከንቲባ አድርጎ ሾሟል።

አቶ ረዳኢ ሹመቱን አረጋግጠዋል።

" TPLF ተወዳድሮ በተመረጠበት ትግራይ እስካሁን ያለው የTPLF ም/ቤት አባላት ናቸው ፤ እኔም እንደ TPLF አንድ አካል ተወካይ ሆኜ ነው የቀረብኩት " ሲሉ ሹመቱ በም/ቤት እንደፀደቀላቸው ተናግረዋል።

አቶ ዓለም ስለ ረዳኢ ሹመት የማውቀው የለም ብለዋል።

" በምክር ቤት ስለተደረገው ሹመት በማህበራዊ መገናኛ ነው ያየሁት በይፋ በመንግሥት መዋቅር አልሰማሁም " ሲሉ ተናግረዋል።

አቶ ረዳዒ ደግሞ በጊዜያዊ አስተዳደሩ የተሰጠው ሹመት ምንም ተቀባይነት የሌለው ነው ብለዋል።

" ሹመት እንደተሰጠው ሰምቻለሁ ያው ትግራይም ኢትዮጵያም ውስጥ ካለው ነባራዊ ሁኔታ አካሄዳችን የአንድ ከተማ አስተዳደር የወረዳ አስተዳደር የራሱ ምክር ቤት አለው ምክር ቤቱ ነው ከንቲባም ፣ የወረዳ አስታዳዳሪም ፣ ካቢኔም የሚያፀድቀው በዚህ ም/ቤት ያላለፈው ከንቲባ ወይም አስተዳዳሪ የመሆን እድል የለውም " ብለዋል።

" እንደ ድርጅት ከምክር ቤት ውጭ ከመጣ ተቀባይነት አለው ብዬ አላምንም እንደ ህወሓት አቋማችን ይሄው ነው " ያሉት ረዳኢ ከምክር ቤት ውጭ ማንም ሰው ደብዳቤ እየፃፈ የሚሾመው ተቀባይነት የለም ሲሉ ጊዜያዊ አስተዳደሩ የሰጠውን ሹመት አጣጥለዋል።

ምንጭ፡ Tihvahethiopia

 #ማይናማር🚨🔴 “ ልጆቻችን በስቃይ ውስጥ ነው ያሉት። መንግስት አንድ መፍትሄ ይፍጠርልን ” - የወላጆች ኮሚቴ🔵 “ ከአገራቱ ጋር የስራ ሥምሪት ስምምነት ባለመኖሩ፣ ሰዎቹም ያቀኑት በህገ ወ...
24/11/2024

#ማይናማር🚨

🔴 “ ልጆቻችን በስቃይ ውስጥ ነው ያሉት። መንግስት አንድ መፍትሄ ይፍጠርልን ” - የወላጆች ኮሚቴ

🔵 “ ከአገራቱ ጋር የስራ ሥምሪት ስምምነት ባለመኖሩ፣ ሰዎቹም ያቀኑት በህገ ወጥ መንገድ በመሆኑ ያሉበት ቦታና ቁጥራቸውን በትክክል ለማወቅ አስቸጋሪ ሆኗል ” - ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር

ማይናማር የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ወላጆች ኮሚቴ አዋቅረው የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ልጆቻቸው ካሉበት አስከፊ ሁኔታ እንዲያወጣላቸው እየጠየቁ ቢሆንም እስካሁን ልጆቻቸው ወደ አገር ባለመመለሳቸው ጥልቅ ጭንቀት ላይ መሆናቸውን በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል ተናግረዋል።

መንግስት ለጉዳዩ ይበልጥ ትኩረት እንዲሰጥም በአጽንኦት ጠይቀዋል።

የኮሚቴው በዝርዝር ምን አለ ?

“ ልጆቻችን አሁንም እየተገረፉ፤ እየተደበደቡ ነው። 18 ሰዓት እያሰሯቸው ነው። ጭራሽ ገንዘብ ካልገባና አጨበርብረው ብር ካላመጡ 24 ሰዓት ሙሉ ኮምፑዩተር ላይ ቁጭ ስለሚያደርጓቸው ፌንት እየነቀሉ የሚወድቁበት ሁኔታ አለ።

ልጆቻችን በስቃይ ውስጥ ነው ያሉት። መንግስት አንድ መፍትሄ ይፍጠርልን። በአካባቢው ያሉ ዲፕሎማቶች እንዲሰሩ የሚያሳስብ ነው የኛ ማመልከቻ።

ታግተው ካሉት ውስጥ 2 ሴት ወጣቶች መለቀቃቸውን ብቻ ነው የማውቀው። እኛ ወደ 153 ወጣቶችን ዝርዝር ነው ይዘን ወደ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር እየሄድን ያለው።

ከእነዛ ውስጥ ወደ 2 ሴቶች ብቻ ናቸው የወጡት። በመንግስት በኩል ወደ 31 ወጣቶች ወጥተዋል የሚል ዜና ነው ያየነው። በተጨባጭ የወጡትን ልጆች አላየናቸውም።

ይሄው 11ኛ ወራችን ነው በማመልከቻ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር መመላለስ ከጀመርን እካሁን ጠብ ያለ መፍትሄ የለም። ከ3,000 በላይ ኢትዮጵያን ናቸው እዛ እየተሰቃዩ ያሉት።

በስቃይ ላይ የሚገኙት ቢያንስ ከመጀመሪያ ድግሪ በላይ የትምህርት ደረጃ ያላቸው ልጆች ናቸው። ይሄ ለቤተሰብ ብቻ ሳይሆን ለአገርም ኪሳራ ነው። ለኛም ትልቅ ጭንቀት ነው ሆኖብን ያለው ” ብሏል።

የኢትዮጵያ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትርን እየተመላለሳችሁ እየጠየቃችሁ ከሆነ ምን ምላሽ ሰጣችሁ? የሚል ጥያቄ ያቀሰብንለት ኮሚቴው፣ “ ‘ለተወካዮች እናሳውቃለን በዛ በኩል ነው መታዬት ያለበት፤ ቶኪዮ ያለው ነው ማይናማርን የሚመለከተው’ የሚል መልስ የሚሰጡን ” ብሏል።

በማይናማር ስለሚገኙ ኢትዮጵያዊያንና ቤተሰቦቻቸው ዜጎቹ በስቃይ ውስጥ እንደሆኑ፣ ለዚህም መንግስት መፍትሄ እንዲሰጣቸው እየተማጸኑ እንደሆነ በመግለጽ፣ ምን እየሰራ ነው ? ጉዳዩ ተስፋ አለው ? ስንል የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴርን ጠይቀናል።

የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው በበኩላቸው ተከታዩን አጭር ምላሽ ሰጥተዋል።

አምባደር ነብያት ጌታቸው ፦

“ ባለፈው ሳምንት መግለጫ ሰጥተን ነበር። በዛ ላይ እስከ ባለፈው ሳምነት መጨረሻ ያሉ ደቨሎፕመንቶችን ነው ያቀረብነው።

ከዚያ ወዲህ የክትትል ሥራ ነው የተሰራው ቶኪዮ ያለው ኤምባሲያችን ከማይናማር መንግስት አካላት ጋር በዚህ ሳምነት ውስጥ ክትትል እንደተደረገ ተገልጾልናል። እስካሁን ያለው ሂደት እዚህ ላይ ነው ያለው።

እስካሁን በተደረገ ጥረት 31 ዜጎቻችን ከነበሩበት አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ወጥተው ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ማድረግ ተችሏል።

ከአገራቱ ጋር የስራ ሥምሪት ስምምነት ባለመኖሩ እና ሰዎቹም ያቀኑት በህገ ወጥ መንገድ በመሆኑ ያሉበት ቦታ እና ቁጥራቸውን በትክክል ለማወቅ አስቸጋሪ ሆኗል።

መንግሥት ለዜጋ ተኮር ቅድሚያ ትኩረት ስለሚሰጥ ጥረቱን አጠናክሮ ይቀጥላል።

አሁንም ህብረተሰባችን ከህገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎችና ህገ ወጥ ጉዞ ራሱንና ልጆቹን መጠበቅ አለበት።

መገናኛ ብዙኃንም ይህን ጉዳይ ልዩ ትኩረት ሰጥተው መስራት ይገባል። ዜጎቻችን የህገ ወጥ ሰዎች አዘዋዋሪዎች ሰለባ መሆን የለባቸውም ” ብለዋል።

ቤተሰቦቻቸው በጣም ተጨንቀው እያለቀሱ ነው። ታጋቾቹም አብረዋቸው የነበሩ የሌሎች አገራት እየተለቀቁ ስለሆነ የኢትዮጵያ መንግስትም ጫና ቢያደርግ የመውጣት እድል እንዳላቸው እየገለጹ ነው፤ እንዲያው ሚኒስቴር መስሪያ ቤትዎ ምን ያህል ጥረት አድርጓል ? ስንል ለአምባሳደሩ ጥያቄ አቅርበናል።

አምባሳደር ነብያት ፤ “ ከአገራቱ ጋር የሥራ ስምሪት ስምምነት ያለበት ቦታ አይደለም። ሰዎቹም የሄዱት ሕገ ወጥ በሆነ መንገድ ነው። ያሉበትን ቦታና ቁጥራቸውን ራሱ በትክክል ለማወቅ እጅግ አዳጋች ነው ” ብለዋል።

“ የማይናማር መንግስት ከሚቆጣጠረው አካባቢም ያሉ አይደሉም ለዛነው ችግሩ እጅግ አስቸጋሪ የሆነው ” ሲሉ አክለዋል።

ምንጭ: tikvahethiopia

 #ማይናማር🚨🔴 “ አምልጠን እንኳ ብንወጣ ያመለጠውን ኢትዮጵያዊ ለሚይዙ 500 ዶላር ይከፈላቸዋል። ” -ኢትዮጵያዊያን በማይናማር🔵 “ ደብድበውት ራሱን አያውቅም ወጣቶች ተሸክመው ሆስፒታል ሲ...
24/11/2024

#ማይናማር🚨

🔴 “ አምልጠን እንኳ ብንወጣ ያመለጠውን ኢትዮጵያዊ ለሚይዙ 500 ዶላር ይከፈላቸዋል። ” -ኢትዮጵያዊያን በማይናማር

🔵 “ ደብድበውት ራሱን አያውቅም ወጣቶች ተሸክመው ሆስፒታል ሲወስዱት የውጪ ዜጋ አናክምም ብለው መለሱት ” - በእንባ የታጀቡ እናት

ሰርተን እንለወጣለን፣ ቤተሰብም እንለውጣለን ብለው ከአገር የወጡ በርካታ ኢትዮጵያዊያን በማይናማር በስቃይ ውስጥ መሆናቸው ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ መገለጻችን አይዘነጋም።

ኢትዮጵያዊያኑ ከሀገር ሲወጡ የተነገራቸውና አሁን ያሉበት ሁኔታ የማይገናኝ ነው።

ጉልበታቸው እየተበዘበዘ ከሆኑም ባሻገር የሚፈጸምባቸው ድብደባና የአካል ጉዳት አሰቃቂ መሆኑን የገፈቱ ቀማሾች ከዚህ ቀደም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸው ነበር።

የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር በበኩሉ፣ ኢትዮጵያዊያኑን ወደ አገራቸው ለመመለስ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየተየጋገረ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መግለጹ ይታወሳል።

የኢትዮጵያዊያኖቹ ጉዳይ አሁንስ ከምን ደረሰ ?

በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ፣ ያገቷቸው አካላት ካሉበት አገር መንግስት ጋር ያላቸውን ግንኙት…በተመለከተ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ማብራሪያ የጠየቃቸው በማይናማር የሚገኙት ኢትዮጵያዊያን፣ በጣም በከፋ ሁኔታ ውስጥ መሆናቸውን በሀዘን ስሜት ገልጸው፣ የመንግስትን እርዳታ ጠይቀዋል።

በዝርዝር ምን አሉ ?

“ የኢትዮጵያ መንግስት ሙሉ ኃላፊነት ወስዶ ከረዳን ብቻ ነው መውጣት የሚቻለው። የሌሎች አገራት እንዳደረጉት። ነገር ግን የተባልነው ነገር የለም እስካሁን በስቃይ ላይ ነን።

ያለንበት አገር ብዙም የተጠናከረ መንግስት የለውም። እንደሚታወቀው ወታደራዊ መንግስት ነውና። መንግስት ከመንግስት ጋር ተነጋግሮ ሊያስወጣን ከቻለ ብቻ ነው እንጂ።

እንወጣለን በሚል ተስፋ እያደረግን፣ እያለምን ነው እንጂ እስካሁን ምንም የተባልነው ነገር የለም። የኢትዮጵያ መንግስት ጫና ካላደረገ በስተቀር የያዙን ሽፍታዎችና የአገሪቱ መንግስት በጥቅም የተሳሰሩ ናቸውና መውጣት ይከብዳል።

አምልጠን እንኳ ብንወጣ ያመለጠውን ኢትዮጵያዊ ለሚይዙ 500 ዶላር ይከፈላቸዋል። ስለዚህ ተሳክቶልን ብናመልጥ እንኳ የአካባቢው ማህበረሰብ ይዞ አሳልፎ ይሰጠናል።

ሽፍቶቹ በቁጥር ብዙ ባይሆኑም መመሪያ የተሰጣቸው ናቸው። በየቦታው ተሰራጭተው ነው የሚጠብቁት። ከእገታ ቦታው ወጣ ብለው በእስናይፐር የሚጠብቀ አሉ። በቁጥር ትንሽ ቢሆኑም የተጠናከረ ጥበቃ ላይ ያሉ ሽፍቶች ናቸው የያዙን።

የሚያሰሩን ቻይናዎች ናቸው። ያለነው ማይናማር ነው። ዜጎቹ ግን የቻይና ናቸው። ከአገሪቱ መንግስት ጋር በጥቅም የተሳሰሩ ናቸው። ለዚሁ መንግስት ግብር ይከፍላሉና ነገሩን ከባድ ያደረገው ከመንግስት ጋር የተያያዙ መሆናቸው ነው።

ወታደራዊ መንግስት ነው ያለው። ስለዚህ ከእኛ ከሚሰበሰው ገቢ ውስጥ ለመንግስት ይከፈላል። ለዛም ነው ሽፍቶቹ ደኀንነታቸው ተጠብቆ ሙሉ ድፍረት አግኝተው የሚሰሩት። የሕግ ከለላም አላቸው ነገሩ የተሳሰረ ነው። አጠቃላይ የአገራቱ መንግስት ሁኔታውን ሁሉ ያውቃል።

በስልክ እየደወልን ቤተሰብን ከመጠየቅ በስተቀር የኢትዮጵያ መንግስት ስለመውጣታችን እንዲህ ነው ያለን የሰማነው ነገር የለም። እባካችሁ በሕይወት ድረሱልን ” ሲሉ ተማጽነዋል።

ልጆቻቸው፣ የትዳር አጋሮቻቸው፣ እህትና ወንድሞቻቸው በማይናማር በከፋ ሁኔታ የሚገኙ ቤተሰቦች በበኩላቸው፣ ለወራት በከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ እንደሆኑ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ልጃቸው የታገተባቸው አንዲት እናት እያለቀሱ በሰጡን ቃል፣ “ እኛም በጭንቀት ተሰቃዬን እንዴት አድርጌ እንደምገልጽ አላውቅም ” ሲሉ ጭንቀታቸውን አጋርተዋል።

እኝሁ እናት አክለው ፦

“ ደብድበውት ራሱን አያውቅም ወጣቶች ተሸክመው ሆስፒታል ቢወስዱት 'የውጪ አገር ዜጋ አናክምም ' ብለው መለሱት።

እንደ ዜጋ መንግስት በዚህ ጉዳይ ላይ ጣልቃ መግባት ሲገባው ‘የራሳቸው ጉዳይ’ የተባለ ነው የሚመስለው። በጣም ያሳዝናል ለመናገር በጣም ነው የሚቸግረኝ።

እንደ ወላድ ይጨንቃል። ተቸግረን አሳድገን እንዲህ ሲሆኑ። እንደ ሀገር እኛ ከኡጋንዳ ሀገር በታች ነው እንዴ የኛ ሀገር መንግስት ! እንዲያው ጆሮ ዳባ ብለውን ነው እንጂ።

የውጪ ጉዳይ ቆንጽላ ጽህፈት ቤት ተሰባስበን አነጋግረን ነበር ከ15 ቀናት በፊት።

ልጆቻችን አካለ ጎደሎ እየሆኑ፣ በሥነ ልቦና እየተሰቃዩ፣ እየተጎዱ ነው ዳግም ሌላ ወጣት እንዳይሄድ ስንል ‘የመንቀሳቀስ መብትን መንፈግ ነው የሚሆነው እኛ እንዴት ብለን እናሳግዳለን ?’ ነው ያሉን ” ሲሉ ገልጸዋል።

ገና የ8 ወር ልጅ ይዘው የቀሩ የትዳር አጋራቸው በማይናማር እንደታገተባቸው የገለጹ ሌላኛዋ እናት በበኩላቸው፣ ባለቤታቸው በከፋ ሁኔታ እንደሚገኝ፣ ልጅ አዝለው ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ድረስ ቢሄዱም አጥጋቢ ምላሽ እንዳላገኙ ተናግረዋል።

በዝርዝር ምን አሉ ?

“ ባለቤቴ ማይናማር በስቃይ ውሰጥ ነው። ከሄደ 5 ወራት አስቆጥሯል። ‘የሥራ እድል አለ’ ተብሎ በደላሎች አማካኝነት ነበር ወደ ታይላንድ የሄደው። በሙያው ሐኪም ነው። ከሄደ በኋላ ግን ታይላንድ አይደለም የቀረው ወደ ማይናማር ነው የወሰዱት።

ያለበት ሁኔታ በጣም ከባድ ነው። የጨለማ ክፍል የሚባል አለ፤ ድብደባ አለ። በነገረኝ መሠረት አሰቃቂ ሁኔታ ነው። እኔም መፍትሄ ፍለጋ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ልጅ አዝዬ ጭምር ብዙ ጊዜ ተመላልሻለሁ።

የሚሰጠኝ ምላሽ በራሳቸው ፍላጎት እንደሄዱ፣ በሕገወጥ መንገድ እንደሄዱ ነው። ከሦስት ቀናት በፊትም ሂጀ ነበርና ከታች ያሉት የቀረበውን ቅሬታ ካሳወቁ ከ10 ወራት በላይ እንዳስቆጠረ፣ ግን መፍትሄ እንዳልተገኘለት ነው የነገሩኝ።

‘ ከላይ ያሉት አካላት ናቸው መስራት ያለባቸው ’ ነው ያሉኝ። ጥሩ መልስ የሰጠን የኤምባሲ አካል ግን አላገኘንም። ቤተሰቡ በጭንቀት ውስጥ ነው ያለው። ባለቤቴ ከሄደ በኋላ ኑሮው ከብዶኛል።

ስለእርሱ መጨነቁ፣ የኑሮ ውድነቱ ተደራረቡብኝ። የባለቤቴ ደመወዝ ተቋርጧል። አዲስ አበባ ከተማ ላይ ብቻዬን ልጅ እያሳደኩ ስቃይ ላይ ነኝ።

የኢትዮጵያ መንግስት በደንብ ትኩረት ሰጥቶ ቢሰራበት የማይናማር መንግስት ሊለቃቸው እንደሚችል ባለቤቴ ነገሮኛል። ባለቤቴ ጋር የነበሩ የህንድ አገር ዜጎች ወጥተዋል። መንግስት መፍትሄ ይስጠን ” ሲሉ ተማጽነዋል።

ማይናማር ውስጥ የሚገኙ የታጋች ኢትዮጵያዊያኑ ወላጅች ያቋቋሙት ኮሚቴ በበኩሉ፣ መፍትሄ እየጠየቀ መሆኑን የገለጸ ሲሆን፣ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ምን እየሰራ እንሆነ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ከሰጠው ምላሽ ጋር በቀጣይ ይቀርባል።

ምንጭ: tikvahethiopia

'ብስኩት ሰርቀህ በልተሀል' በማለት የገዛ ልጁን ሁለት እጆች በእሳት ያቃጠለው ወላጅ አባት በቁጥጥር ስር ዋለ።በ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ አ...
24/11/2024

'ብስኩት ሰርቀህ በልተሀል' በማለት የገዛ ልጁን ሁለት እጆች በእሳት ያቃጠለው ወላጅ አባት በቁጥጥር ስር ዋለ።

በ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ዕድገት ቀበሌ ህዳር 05 ቀን 2017 ዓ.ም ከረፋዱ 7:00 ሰዓት ላይ የስድስት አመቱ ታዳጊ ከጎረቤት ብስኩት መሸጫ ሻይ ቤት ከሌሎች ህፃናት ጋር በሁለት ዙር 15 ብስኩት ሰርቆ በመብላቱ መሆኑን ፖሊስ አመልክቷል፡፡

ብስኩት ሰርቀው በመብላቱ ለወላጅ አባቱ ስሞታ መድረሱን ተከትሎ ሁለት እጆቹን በሚነድ እሳት እንዲቃጠል በማድረጉ ፖሊስ ተጎጂውን ታዳጊ ወደ ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ቲቺንግ ሆስፒታል በመውሰድ ህክምና እየተደረገለት እንደሚገኝ ገልጿል ።

ምንጭ፡ ዋሱ መሀመድ

የአፋልጉኝ ተማጽኖ   | የተፈላጊ ስም ሀረገወይን መሰረት አቡሀይ ትባላለች። ልዩ ምልክት በመሀል ደረቷ ላይ በልብ ችግር ምክንያት ኦፕሬሽን ተሰርቶላታል። ሕክምናዋን ለመከታተል ህዳር 10 ቀ...
23/11/2024

የአፋልጉኝ ተማጽኖ

| የተፈላጊ ስም ሀረገወይን መሰረት አቡሀይ ትባላለች። ልዩ ምልክት በመሀል ደረቷ ላይ በልብ ችግር ምክንያት ኦፕሬሽን ተሰርቶላታል።

ሕክምናዋን ለመከታተል ህዳር 10 ቀን 2017ዓ.ም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋናው ቢሮ ፊት ለፊት ከቤተዛታ ላብራቶሪ የደም ናሙና ከቀኑ 8:00 ሰአት ሰጥታ ወደ ቤቷ አልተመለሰችም ።

የለበሰችው ከውስጥ ነጭ ቲሸርት ብጫ አበባ ያለው ፤ ቀይና ጥቁር እስኩየር ሸሚዝ
እና ከታች ብጫ ጉርድ ቀሚስ ነው ።

ያለችበትን የሚያውቅ በስልክ ቁጥር
0941605160 ደውሎ ቢያሳውቀን ውለታ እንከፍላለን

ፈላጊ ታዛ ስንቄ
ምንጭ፡ ጌጡ ተመስገን

አሳዛኝ አደጋ❗ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ የሚጓዝ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ከሲኖ ትራክ ተጋጭቶ የበርካቶ ህይወት ማለፉ ተሰምቷል በጣም በርካታ ሰዎች ደሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል።በዚህም ምክንያት ...
23/11/2024

አሳዛኝ አደጋ❗

ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ የሚጓዝ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ከሲኖ ትራክ ተጋጭቶ የበርካቶ ህይወት ማለፉ ተሰምቷል በጣም በርካታ ሰዎች ደሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

በዚህም ምክንያት መንገዱ ለረጅም ሰዓት መዘጋቱ የተነገረ ሲሆን፤ በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች ወደሆስፒታል የማድረስ ሥራ እየተሰራ መሆኑን ተዘግቧል።

በአደጋው በርካታ ሰዎች መጎዳታቸውን እንዲሁም ለጊዜው ቁጥራቸው ያልታወቀ ሰዎች ሕይወት ማለፉን የተናገሩት ነዋሪዎቹ፤ የሲኖ ትራክ ተሸከርካሪው ረዳት ከመኪና ለማውጣት ከአንድ ሰዓት በላይ ጥረት ቢደረግም ሕይወቱን ማትረፍ አለመቻሉን ተናግረዋል፡፡

19/08/2024

"ድርጊቱ በሞት ፍርድ የሚስቀጣ ነው!"
ችግሩ ያለው ከወንጀል ህግ ክፍተት ነው! ሊታረም የሚችለው የህግ ማሻሻያ በማድረግ ብቻ ነው!

| በሙያዬ በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተከላካይ ጠበቃ ነኝ በዚህም ድርጊቱ አዲስ አበባ ላይ ተፈፅሞ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የከባድ ነብስ ግድያ ችሎት የሚታይ ቢሆን እና የወንጀል ድርጊት ፈፃሚው ጠበቃ የማቆም አቅም ኖሮት ጠበቆች ሁሉ ህሊናቸው ፈትኗቸው ለገንዘብ ብለን እንዲህ ያለውን ወንጀል ፈፅሟል ተብሎ ለተከሰሰው ተከሳሽ ተወክለን አንከራከርም ቢሉ እንኳን ፍትሕ እንደይጓደል እኔ እስካልተቃወምኩ ድረስ (የኢትዮጵያ ህግ ዘግናኝ ጉዳይ አልይዝም ብየ ከመቃወም የሚከለክለኝ ሆነ ለመያዝ የሚያስገድደኝ ህግ ባይኖርም አለም አቀፍ ህጎች ግን የመቃወም መብትን ይሰጣሉ) ለተከሳሽ ከሚቆሙ ተከላካይ ጠበቆች አንዱ እሆን ነበር።

ዛሬ ግን ይህን ፅሁፍ የምፅፈው የቀድሞ ዐቃቤ ህግነት እና የረዳት ዳኝነት ሙያየን መሰረት በማድረግ ከከሳሽ ከህግ አንፃር ከአሁን ሙያዬ በተቃራኒው እያነፀርኩ ነው የምፅፈው።

እዚህ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ በማነጋገር ላይ የሚገኘው በሰባት ዓመቷ ህፃን ፌቨን ላይ የተሰራውን ግዙፋዊ ተደራራቢ ዘግናኝ ወንጀል እናቷ ወ/ሮ አበቄለሽ ከእዮኃ ሚዲያ ጋር ያደረገችውን ቆይታ ስሜቴን ተቆጣጥሬ አዳመጥኩት።

በዚህም እንደ የህግ ባለሙያ የነገሩን ፍሬ ነገር፣ ለጉዳዮ ተግባራዊ የሚደረገውን የወንጀል ህግ ድንጋጌዎች፣ በፍርድ የተሰጠው ውሳኔ እና የሟች እናት ፍትህ ለማግኘት ያደረገችውን ጥረት እና በተበዳይነት ያጋጠሞትን ውጣ ውረዶች በአንድ ላይ በመመዘን ከህግ አንጻር የራሴን እይታ እንደሚከተለው አቀርባለሁ።

1ኛ የነገሩ ፍሬ ነገር በአጭሩ

የሟች ህፃን ፌቨን እናት ከሚዲያ ጋር ባደረገችው ቆይታ መሠረት የተፈፀመው ድርጊት ፍሬ ነገር በአጭሩ፦

"የሟች እናት ድርጊቱን ከፈፀመው ፍርደኛ ቤት ውስጥ ከእህቷ እና ሁለት ልጆቿ ጋር ተከራይታ ትኖራለች። በሙያዋ ነስር ስለሆነች ብዙውን ግዜ የሰባት ዓመት ልጇን ለእህቷ እና ለአከራይ እንዲጠብቋት ሰጥታ ነው የምትውለው/የምታድረው። በዚህም የድርጊቱ ፈፃሚ ፍርደኛ ህፃኗን የመጠበቅ የመቆጣጠር ማህበራዊ ግዴታ አለበት።

ድርጊቱ በተፈፀመ እለት የሟች ህፃን ፌቨን አክስት ሟች ህፃን ፌቨን ከበር ላይ ወድቃ ስታገኛት የህፃኗ አፍ በአረፋ ተሞልቶ፣ ሰውነቷ (ጭኗ እግሯ) በምላጭ ተተርትሮ (ይህንም ስታስረዳ ወድቃ ሞተች ለማሰኘት ነው በማለት ትገልጸዋለች) አንድ እግር ጫማ አድርጋ (አንድ እግሩ ከፍርደኛው ቤት ውስጥ በኋላ እንደተገኘ) ልብሷ በውሃ በስብሶ ነብሷ አልፎ እንዳገኘቻት።

ፍርደኛው ከቤት ከሶፋ ላይ ቁጭ ብሎ እርዳኝ እያለች ስትማፀነው ምንም አይነት ምላሽ እንዳልሰጣት በኋላ ላይ የፍርደኛ ቤተሰቦች የቡዳ መድሃኒት ወደሚያጠጣ ሰው እንደወሰዷት እና ለህፃን ፌቨን እናት ተደውሎ እንደተነገራት እና ወደ ሆስፒታል ተወስዳ ስትመረመር የወንጀል ድርጊቱ ፈፀሚ ሽንት ቤት ውስጥ (ተ*ደፍራ ሞ*ታለች) ብሎ ሲናገር ፓሊሶች ሰምተው ተጠርጥሮ እንደተያዘ ከቃለ መጠየቁ የነገሩን ዋና ዋና ፍሬ ነገር መረዳት ይቸላል።

ከህክምና ማስረጃ አንፃር ሟች ህፃን ፌቨን የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ለንፅህና እና ክብር ፍፁም ተቃራኒ በሆነ መንገድ ተፈፅሞባት (ለመግለጽ የሚዘገንን) ህይወቷ አልፎ እንደመጣች እና አንገቷ ላይ የአምስት ጣት አሻራ ያለው መብለዝ እንደነበር የሟች እናት በቃለ መጠየቋ የህክምና ማስረጃው ምን እንደሚል ገልፃለች። ቴክኒካል ጉዳዮችን (የሞቷ መንስኤ፣ የወንድ ልጅ ፈሳሽ ዘረ፣ ሌሎች ቅንጣቶች) አስገድዶ መደፈርን እና ግድያን የሚያስረዱ ጉዳዮች ማስረጃው ላይ ነው የሚኖሩት።

እነዚህን ፍሬ ነገሮች ማስረጃዎችን መሰረት በማድረግ ጉዳዮን በመጀመሪያ ደረጃ የሰማው ፍርድ ቤት በተከሳሽ ላይ የጥፋተኝነት ፍርድ በመስጠት የ25 ዓመት ፅኑ እስራት የቅጣት ውሳኔ ሰጥቷል። ስለዚህ ጉዳዮ በፍርድ ውሳኔ ያገኘ ጉዳይ ስለሆነ ምክንያታዊ የሆነ ኃሳብ እና አስተያየት መስጠት ይቻላል።

2ኛ ድርጊቱ የተላለፈው እና የሚያቋቁመው የወንጀል ህግ ድንጋጌዎች

ፓሊስ የምርመራ መዝገብ አጣርቶ ለዐቃቤ ህግ በሚያቀርብበት ወቅት ዐቃቤ ህግ የፓሊስን የምርመራ መዝገብ ተመልክቶ በወ/መ/ሥ/ሥ/ህግ አ/ቁ 38 መሠረት አራት የህግ አማራጮች ይኖሩታል።

1ኛ በፓሊስ የተጠናቀረው የምርመራ መዝገብ የተሟላ ነው ብሎ ከወሰነ ድርጊቱ የተላለፈውን እና ያቋቋመውን የወንጀል ህግ ድንጋጌ ከነ ማስረጃዎች ጠቅሶ ክስ መመስረት፤(አ/ቁ 109 እስከ 122)

2ኛ ማስረጃዎች ለመጠበቅ ሲባል የቀዳሚ ምርመራ ማድረግ (አ/ቁ 80 እስከ 93)

3ኛ የፓሊስ የምርመራ መዝገብ የሚቀው ነገር ካለ ተጨማሪ ምርመራ እንዲደረግ ተጨማሪ ምርመራ የሚያስፈልግባቸውን ጉዳዮች በነጥብ ጠቅሶ ለመርማሪ ፓሊስ መዝገቡን መመለስ፣

4ኛ ክስ ለመመስረት የሚያስችል የተሟላ ማስረጃ ስለሌለ እና ይህ ማስረጃ በተጨማሪ ምርመራ ሊሟላ ካልቻለ መዝገቡን በመዝጋት ተጠርጣሪን ማሰናበት ናቸው። (አ/ቁ 42)
በያዝነው ጉዳይ ዐቃቤ ህግ ከፓሊስ የቀረበለት መዝገብ የተሟላ ነው ብሎ ስለወሰነ በፍርድ ቤት ክስ መስርቷል።

ዐቃቤ ህግ በህፃን ፌቨን ላይ በተሰራው ወንጀል የጠቀሰው የህግ ድንጋጌ ምንድን ነው?
በህፃን ፌቨን ጉዳይ ማስረጃዎችን መሰረት በማድረግ ሊጠቀስ የሚገባው ድንጋጌ ምንድን ነው?

የህፃን ፌቨን እናት ወ/ሮ አበቅየለሽ፣ አክስቷ እና የህክምና ማስረጃዎችን መሰረት በማድረግ እጅግ ቢያንስ ሁለት ተደራራቢ ክሶች በዐቃቤ ህግ ሊመሰረቱ ይገባል፡፡ እነዚህም፡-

1ኛ ክስ ሌላ ወንጀል ለመፈፀም እንዲመቸው ወይም የተፈፀመን ወንጀል እንዳይገለፅ ለማድረግ ሲል ጨካኝነቱን እና ነውረኝነቱን በሚያሳይ ሁኔታ ከበድ የሆነ የሰው ግድያ መፈፀም (የኢፊድሪ የወንጀል ህግ አ/ቁ 539 (1) (ሐ))

2ኛ ክስ በህፃናት ልጆች ላይ የሚፈፀም የግብረ ስጋ ድፍረት በደል (የኢፊድሪ የወንጀል ህግ አ/ቁ 627 (1))

ከለይ የተጠቀሱት የወንጀል ህግ ድንጋጌዎች የሚያስከትሉትን የቅጠት መጠን ደሞ እንመልከት።

1ኛ ክስ አ/ቁ 539 (1) (ሐ) ደሞ በእድሜ ልክ ፅኑ እስራት ማለትም 25 ዓመት ወይም በሞት ያስቀጣል። 2ኛ የኢፊድሪ የወንጀል ህግ አ/ቁ 627 (1) ከ15 ዓመት እስከ 25 ዓመት በሚደርስ የፅኑ እስራት ቅጣት ያስቀጣል።

እነዚህ ሁለት ድንጋጌዎች ከሳሽ ዐቃቤ ህግ በሶስት የተለያዮ ክሶች (ክስ 1፣ 2) ብሎ እንደ ቅደም ተከተላቸው በአንድ የክስ አቤቱታ በህፃን ፌቨን ጉዳይ ሊያቀርባቸው የሚገባ እና በአንድ ላይ ተጠቃለው በአንድ አቤቱታ ሊቀርቡ የሚችሉ ናቸው። ይህ ሊሆን የሚችለው ደሞ ወንጀለኛው (ስለተፈረደበት) ህፃን ፌቨን በተገለፀው አግባብ (በሚዘገንነው ሁኔታ ደ*ፍሯ*ት እና ይህን ግዙፋዊ የበደለ ወንጀሉን እንዳይታወቅ ከደ*ፈ*ራት በኋላ በዘግናኝ ሁኔታ ህይወቷን ካጠፋው ነው።)

በእኔ እምነት ወላጅ እናቷ ባስረዳችው (የእህቷን ቃል እና የህክምና ማስረጃውን በተመለከተ በሰጠችው ቃል መሰረት) ህፃን ፌቨን መጀመሪያ የተፈፀመበት ወንጀል የአሰገድዶ መድፈር ወንጀል ሲሆን ከዛ ወንጀል በኋላ ወንጀለኛው ህፃን ፌቨንን ወንጀሉን ታወጣብኛለች ብሎ በማሰብ (በተለይ በሴት አካሏ ላይ የደረሰውን ጉዳት ለመሸፈን የማይቻል በመሆኑ) ህፃን ፌቨንን አንቆ በዘግናኝ ሁኔታ ገድሏታል። ይህ በሆነ ግዜ ግዙፋዊ የተዛመዱ እና የተደራራቡ ወንጀሎች እንደተፈፀመ ይቆጠራል።

እዚህ ሚዲያ ላይ ለጉዳዩ ቅርበት ካላቸው አካላት ከሰጡት መግለጫ የተረዳሁት ዐቃቤ ህግ የኢፊድሪ የወንጀል ህግ አ/ቁ 539 (1) (ሐ) ጠቅሶ የተደራራቢ ወንጀል ክስ እንዳቀረበ ነው፡፡ ይህ መሆኑ የህጻን ፌቨን እናት በዐቃቤ ህግ ላይ ጠንከር ያለ አቤቱታ ስታቀርብ የነበረ ከመሆኑ አንጻር የድንጋጌ አጠቃቀስ ችግር ሊኖር ይችላል የሚለዉን ግምቴን ቀርፎታል፡፡ ዐቃቤ ህግ ከክስ አመሰራረት አንጻር ከደሙ ንጹህ ነው እያልኩ ነው፡፡

በመርህና እና በልዮ ሁኔታ ደረጃ ፍርድ ቤት ከተጠየቀው ዳኝነት ውጭ ፍርድ ሊሰጥ አይችልም። በወንጀል ጉዳይ አቃቤ ህግ ድርጊቱ የሚያቋቁመውን የህግ ድንጋጌ ሲጠቅስ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ አለበት። ምክኒያቱም አንዴ ክስ ከተመሰረተ በኋላ ክሱን አሻሽሎ ከዚህ በፊት ከጠቀሰው ድንጋጌ ቅጣቱን ወደሚያከብድ ድንጋጌ መለወጥ አይችልም። በሞት የሚያስቀጣ ድርጊትን በእድሜ ልክ ፅኑ እስራት በሚያስቀጣ ድንጋጌ ክስ ከመሰረተ በኋላ ላይ ፍርድ ቤቱ ማስረጃዎችን ሲሰማ ድርጊቱ በሞት የሚያስቀጣ መሆኑን ካረጋገጠ የዐቃቤ ህግ ክስ ላይ የተጠቀሰውን ድንጋጌ ቀይሮ ቅጣቱን ወደሚያከብደው የሞት ድንጋጌ መቀየር አይችልም። ነገር ግን በተቃራኒው ድርጊቱ በእድሜ ልክ ፅኑ እስራት የሚያስቀጣ ሁኖ እያለ ዐቃቤ ህግ በሞት የሚያስቀጣውን ድንጋጌ ጠቅሶ ከከሰሰ ፍርድ ቤቱ በማስረጃ ወዳረጋገጠው የእድሜ ልክ እስራት በወንጀል ህግ አንቀፅ ቁጥር 112 መሠረት ቀይሮ ሊወስን ይችላል። በግልፅ ቋንቋ ፍርድ ቤት ጉዳዮን አቅልሎ የመወሰን ስልጣን እንጅ በክሱ ከተጠቀሰው በላይ አክብዶ ሊወስን አይችልም። ለዚህም ነው በወንጀል ጉዳይ ዐቃቤ ህግ የመጀመሪያው ዳኛ ነው የሚባለው።

3ኛ የፍርድ ቤቱ ውሳኔ

ትልቁ ቅሬታ ያለው እዚህ ላይ ነው፡፡ አብዛኞቻችን በፍርድ ቤቱ የተሰጠው ውሳኔ በቂ እና የድርጊቱን ግዙፋዊ ጥፋት የሚመጥን አይደለም የሚል ቅሬታ አለ፡፡ ይህ ለምን ሆነ ብለን እንመርምር፡፡

ፍርድ ቤቱ ተካሳሽን በኢፊድሪ የወንጀል ህግ አ/ቁ 539 (1) (ሐ) እና 627 (1) ጥፋተኛ ካለዉ በኋላ በቀጥታ የሚገባው የግራ ቀኙን የቅጣት አስተያየት ተቀብሎ በተሻሻለው መመሪያ ቁጥር 2/2006 መሰረት ቅጣት ወደ ማስላት ነው፡፡ በዚህም በዐቃቤ ህግ በኩል ያለዉን የቅጣት ማክበጃና በተከሳሹ ላይ ሊጣል የሚገባውን ተከሳሽን ያርማል ያስተምራል ያለውን ደረጃ እና እርከን ጠቅሶ አስተያየት ይሰጣል፡፡

ከወንጀል ድርጊቱና ከኢፊድሪ የወንጀል ህግ አ/ቁ 84 (1) አንጻር በዐቃቤ ህግ በኩል ሊቀርብ የሚገባዉ ሆነ የሚችለው የሚከተለው ነው፡፡
በ1ኛ ክስ ተከሳሽ ተከሶ ጥፋተኛ የተባለበት 539 (1) (ሐ) ድንጋጌ በተሻሻለው መመሪያ ቁጥር 2/2006 መሰረት ደረጃ እና እርከን የወጣለት ሲሆን ይህም ደረጃ 2 እርከን 39 ላይ ይወድቃል፡፡ በ2ኛ ክስ 627 (1) ደረጃ 2 እርከን 35 ላይ ይወድቃል፡፡

ጠቅላላ የቅጣት ማክበጃን በተመለከተ፤

1ኛ ማክበጃ ከኢፊድሪ የወንጀል ህግ አ/ቁ 84 (1) (ሀ) አንጻር ወንጀለኛው ወንጀሉን የፈጸመዉ በፍጹም ፍቃደኝነት በመሆኑ፤ (የወንጀሉ ባህሪ በፍጹም ፍቃደኝነት ብቻ የሚሰራ በመሆኑ)

2ኛ ማክበጃ ከኢፊድሪ የወንጀል ህግ አ/ቁ 84 (1) (ለ) አንጻር ወንጀለኛው ወንጀሉን የፈጸመዉ የተጣለበትን እምነት በማጉደል በመሆኑ በመሆኑ፤ (እንደ አከራይ ህጻን ፌቨን እንዲጠብቃት እና እንዲንከባከባት እናት እምነት ጥላበት በመሆኑ)

3ኛ ማክበጃ ከኢፊድሪ የወንጀል ህግ አ/ቁ 84 (1) (ሐ) አንጻር ወንጀለኛው ወንጀሉን የፈጸመዉ ራሷን መከላከል በማትችል ህጻን ላይ በመሆኑ፤

ልዩ የቅጣት ማክበጃን በተመለከተ፤

ከኢፊድሪ የወንጀል ህግ አ/ቁ 85 አንጻር ወንጀለኛው ወንጀሉን የፈጸመዉ ግዙፋዊ ተደራራቢ ወንጀሎች በመሆኑ በአ/ቁ 184 እና 185 መሰረት የተከበረው ፍርድ ቤት ሁለቱም ደረጃ እና እርከኖች በሞት ፍርድ የሚስቀጡ ስለሆነ ቅጣቱን አክብዶ ጣራውን በመውሰድ በሞት ቅጣት እንዲቀጣ እንዲወስን ሊያሳስብ ይችላል አልያ ይገባል፡፡

በተከሳሽ ጠበቃ በኩል ደሞ ራሱን የቻለ የቅጣት አስተያየት ሊቀርብ ይችላል፡፡ በዚህም ተከሳሽ የቤተሰብ አስተዳዳሪ ነዉ፣ ከዚህ በፊት መልካም ጠባይ አለዉ (ሪከርድ የለበትም)፣ የህዳሴ ግድብ ቦንድ ገዝቷል እየተባለ መሰል የቅጣት ማቅለያወችን ሊያቀርብ ይችላል፡፡ እዚህ ላይ ዐቃቤ ህግ በተከሳሽ በኩል የሚቀርቡ የቅጣት አስተያየቶች በሙሉ በማስረጃ እንዲደገፉ የማሳሰብ ግዴታ አለበት፡፡ የማስረጃዎችን እውነተኝነትም መመርመር አለበት፡፡

ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙን አስተያየት በመመዘን በቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 2/2006 መሰረት ለድርጊቱ የወጣለትን እርከን እና ደረጃ ማለትም ለ1ኛ ክስ ደረጃ 2 እርከን 39 ለ2ኛ ክስ ደረጃ 2 እርከን 35 በመውሰድ 1ኛ ክስ የመጨረሻ የቅጣት ጣራ ስለሆነ ከማክበጃ አንጻር ከዚህ በላይ አይከብድም፡፡ 2ኛ ክስ ላይ ሶስት ማክበጃወች ሲወሰዱ ከእርከን 35 ወደ እርከን 38 ያድጋል፡፡ በተከሳሽ በኩል በጠበቃው በኩል የቀረቡ እና በማስረጃ የተረጋገጠ 1 የቅጣት ማቅለያ ቢያዝለት 1ኛ ክስ ወደ እርከን 38 ሁለተኛ ክስ ወደ እርከን 37 ዝቅ ይላል፡፡

ችግሩ የሚመጣዉ እዚህ ላይ ነው ምንም እንኳን የትኛውም አይነት ዘግናኝ ወንጀል ቢሰራ በኢትዩጵያ ህግ አ/ቁ 108 መሰረት ከፍተኛው የእስራት ጣራ 25 ዓመት ሲሆን ከፍተኛው ቅጣት ደሞ የሞት ፍርድ ነው፡፡ በዚህም ምከኒት የተደራረቡ እና የተዛመዱ ግዙፋዊ ወንጀሎች በተፈጸሙ ግዜ ይህን ማስላት፣ የእያንዳንዱን ቅጣት መደመር ዋጋ የለውም፡፡ የህግ ማሻሻያ የሚያስፈልገው መሰረታዊ ጉዳይም ይህ ነወ፡፡

4ኛ ለምን በሞት አልተቀጣም

(የኢፊድሪ የወንጀል ህግ አ/ቁ 117 መሰረት የሞት ቅጣት የሞት ቅጣት ለመወሰን አራት ምክኒያቶች ተሙልተው መገኘት አለባቸው፡፡ እነዚህም
1ኛ ወንጀሉ ፍጻሜ ያገኘ እንደሆነ፣
2ኛ ወንጀሉ እጅግ ከባድ መሆኑ፣
3ኛ ወንጀለኛው አደገኛ በመሆኑ፣
4ኛ በልዩ ህጉ ድርጊቱ በሞት እንዲያስቀጣ ተደንግጎ ከሆነ
5ኛ ለወንጀለኛው ቅጣትን የሚያቀልለት ምክኒያት የታጣ በመሆኑ
6ኛ ወንጀለኛው ወንጀሉን በፈጸመበት ግዜ እድሜው ቢያንስ 18 ዓመት የሞላው ሲሆን ብቻ ነው፡፡ እንዚህ ሁሉም ተሞልተው ሲገኙ ብቻ ነው የሞት ፍርድ ሊፈረድ የሚችለው፡፡
በእኔ እምነት ከላይ ከተ/ቁ 5 በስተቀር በህጻን ፌቨን ጉዳይ ሁሉም ቅድመ ሁኔታዎች ተሟልተዋል፡፡ ለወንጀለኛው አንድ የቅጣት ማቅለያ ከተያዘለት ብቻ ነው ከሞት ፍርድ ውጭ የ25 ዓመት ጽኑ እስራት ቅጣት ሊወሰን የቻለዉ አልያ የሚችለው፡፡ ይች አንድ የቅጣት ማቅለያ ተከሳሽን ከሞት ፍርድ ታድነዋለች አልያ አድናዋለች፡፡

5ኛ የወ/ሮ አበቅየለሽ ፍትህ ለማግኘት ያደረገችው ጥረት እና ያጋጠማት እንግልት።

የፌቨን እናት ባደረገችው ቃለ መጠየቅ እጅጉን ሰረበሸኝ ነገሮች መካከል በፍትህ ሥርዓቱ ያጋጠማት እንግልት ነው። ሁኔታውን በራሷ አንደበት እንዲህ ስትል ትገልፀዋለች፦

"ለህይወቴ እየሰጋሁ ለምስክሮች መጥሪያ የማደርስ እኔ ነኝ... ከህክምና ተቋም ማስረጃዎችን የማመጣ አመት እኔ ነኝ... ያመጣኋቸው ማስረጃዎችም ጠፉ ተብለው እንደገና አፅፌዋለሁ።...:ዐቃቤ ህጉ በዚህ ማስረጃ በነፃ ነው የሚለቀቅ ብሎኝ መጀመሪያ ላይ ያከማትን ዶክተር እባክህን ፃፍላት በየ ለምኘ አፅፌ አምጥቻለሁ። ዐቃቤ ህጉ መዝገቡ ፍሬ የለውም ብሎኝ የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ ኃላፊዋ መዝገቡ ፍሬ እንዲያፈራ የምታደርገው እኮ አንተና ፓሊስ ናችሁ ብላ ተከራከረችው እኔም መጀመሪያ ካያት ዶክተር ማስረጃ አስመጥቸ ሰጠሁት እና ልጁ በነፃ ቢወጣ ምንም እንኳን ሴት ብሆንም አንተን ነው የምጠይቅህ ብየ አልኩት..." ትላለች። በሚያሳዝን ሁኔታ እነዚህ ሁሉ ስራዎች የፓሊስ እና የዐቃቤ ህግ ኃላፊነቶች ነበሩ። በምን አግባብ የሟችን እናት እነዚህን ተግባሮች እንድታከናውን እንዳደረጓት ግራ የሚገባ ነው። እንዲ አይነት ንግግር ለግል ተበዳይ ለዛውም ፍትህ ፈልጋ ለመጣች እናት ፈጽሞ አይደረግም፡፡ ይህ ጠንካራ ክስ ምላሽ ያስፈልገዋል፡፡ በእኔ አሁናዊ ሞያ ከተበዳይ በተቃራኒ ቆሜ እንኳን እየተከራከርኩ የግል ተበዳዩችን ስሜት እጠብቃለሁ፣ ለስሜታቸው እጠነቀቃለሁ፣ ያለብኝን የሙያ ግዴታ አስረዳለሁ፡፡ ዐቃቤ ህግ ሲኮን ደሞ ያለበት ግዴታ ከፍ ያለ ነው የሚሆነው፡፡ ከዚህ አንጻር የወ/ሮ አበቅየለሽ አቤቱታ የሚመለከታቸው አካላት ማብራሪያ ሊሰጡበት እና ተገቢውን የእርምት እርምጃ ሊወሰድ ይገባል፡፡

መደምደሚያ

በተለያ ግዚ በህጻናት ላይ አልያ በሌሎች ላይ የሚፈጸሙ ግዙፋዊ ወንጀሎች ተመጣጣኝ ቅጣት አያገኙም ለሚለው መሰረታዊ ቅሬታ መፍትሔው የህግ ማሻሻያ እንዲደረግ ግፊት ማድረግ ብቻ ነው፡፡ ይህ ሲሆን ነው የወ/ሮ አበቅየለሽ ሆነ ሌሎች ወንድም እህት እናት እና አባቶቻችን እምባ ሊታበስ የሚችለው ትክክለኛ ፍትሕም ሊሰፍን የሚችለው፡፡

ቴዎድሮስ ታደሰ በላይ
ፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተከላካይ ጠበቃ
ምንጭ - ጌጡ ተመስገን

17/08/2024

በህወሓት ስም እንዳይቀሳቀስ ታገደ‼️

በ14ኛው የጨረባ ጉባኤ ያልተሳተፉ የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ አባላት ከዛሬ ጀምሮ በየትኛውም መድረክ በህወሓት ስም እንዳይቀሳቀሱ ማገዱን አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ህወሓት እያካሄደ ያለው ጉባኤ ላይ የሚወሱንትን የትኛውም ውሳኔ ተቀባይንት እንደሌለው መግለፁ ይታወቃል።

16/08/2024

ደሴ..!‼

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ደሴ ድስትሪክት በመጭው እሁድ ነሐሴ12/2016 ደሴ እና አጎራባች አካባቢዎች ከጧቱ 12:00 አስከ ምሽቱ 12:00 ለሀልይ ማሻሻያና ለከፍተኛ ጥገና ሲባል መብራት እንደሚቋረጥ እወቁልኝ ብሏል።
ምንጭ - ዋሱ መሀመድ

በጋምቤላ ክልል 4 ወረዳዎች የጎርፍ አደጋ ተከስቷል። ከ16 ሺህ በላይ ነዋሪዎች ከመኖሪያ ቀያቸዉ ተፈናቅለዋል።በሀገሪቱ ደጋማ አካባቢ በጣለው ከባድ ዝናብ ፦- በጎግ፣ - በላሬ፣- በጆርና -...
11/08/2024

በጋምቤላ ክልል 4 ወረዳዎች የጎርፍ አደጋ ተከስቷል።

ከ16 ሺህ በላይ ነዋሪዎች ከመኖሪያ ቀያቸዉ ተፈናቅለዋል።

በሀገሪቱ ደጋማ አካባቢ በጣለው ከባድ ዝናብ ፦
- በጎግ፣
- በላሬ፣
- በጆርና
- በዋንቱዋ ወረዳዎች በሚገኙ ቀበሌዎች ላይ የጎርፍ መጥለቅለቅ ተከስቶ ነው ወገኖቻችን የተፈናቀሉት።

ተፈናቃዮቹን ለጊዜዉ ደረቃማ በሆኑ አካባቢዎች እንዲሰፍሩ ተደርጓል ተብሏል።

የጎርፍ አደጋዉ በቤት ዉስጥ ባሉ ቁሳቁሶች እንዲሁም በቁም እንስሳትና በሰብል ላይም ጉዳት ማድረሱን ገልፀዋል።

የጎርፍ መጥለቅለቁ በሚቀጥሉት ጊዜያት ከዚህ የከፋ ጉዳት ሊያስከትል ይችላል ተብሏል። ለዚህም ነዋሪዎች አስፈላጊውን ዝግጅትና ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንዲያደርጉ የክልሉ አደጋ ስጋት ስራ አመራር አሳውቋል።

.

ምንጭ - tikvahethiopia

ኢትዮጵያ በትግስት አሰፋ አማካኝነት በፓሪስ ኦሎምፒክ ሶስተኛውን ብር አግኝታለች። 1. ሲፋን ሀሰን2. ትግስት አሰፋ3. ሄለን ኦብሪ
11/08/2024

ኢትዮጵያ በትግስት አሰፋ አማካኝነት በፓሪስ ኦሎምፒክ ሶስተኛውን ብር አግኝታለች።
1. ሲፋን ሀሰን
2. ትግስት አሰፋ
3. ሄለን ኦብሪ

መግለጫበኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ የሐዋሳ ቅርንጫፍ በመደበኛው የፓይለት ስልጠና ልምምድ ላይ የነበረ ቀላል የተማሪዎች መለማመጃ አውሮፕላን (Dimond DA40NG) አየር ላይ ሳለ ባጋጠመ...
10/08/2024

መግለጫ

በኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ የሐዋሳ ቅርንጫፍ በመደበኛው የፓይለት ስልጠና ልምምድ ላይ የነበረ ቀላል የተማሪዎች መለማመጃ አውሮፕላን (Dimond DA40NG) አየር ላይ ሳለ ባጋጠመው የቴክኒክ ችግር ምክንያት አርሲ ነጌሌ አካባቢ ለማረፍ ተገድዷል። ይህንን ተከትሎ በመደበኛ ስልጠናው ላይ የነበሩት አስተማሪውና ተማሪው የመለማመጃ አውሮፕላኑ ሕብረተሰቡ ላይ አደጋ በማያደርስ ሁኔታ ለማሳረፍ ከፍተኛ ጥረት ያደረጉ ቢሆንም ለማረፍ በተደረገው ጥረት መሬት ላይ በነበረች አንዲት ታዳጊ ላይ ጉዳት ደርሷል።ለተፈጠረው ሁሉ እያዘንን ለታዳጊዋ ቤተሰቦች ፍፁም መፅናናትን እንመኛለን።

የአደጋው መንስኤ በሚመለከታቸው አካላት በመጣራት ላይ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን።

የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርስቲ

10/08/2024
የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ያደረገው የዋጋ ጭማሪ ፦➡️ አዲስ ፓስፖርት ፦ መደበኛ 5000 ብር ፤ አስቸኳይ 2 ቀን 25 ሺህ ብር ፤ 5 ቀን 20 ሺህ ብር➡️ የፓስፖርት እድሳት ፦1...
06/08/2024

የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ያደረገው የዋጋ ጭማሪ ፦

➡️ አዲስ ፓስፖርት ፦ መደበኛ 5000 ብር ፤ አስቸኳይ 2 ቀን 25 ሺህ ብር ፤ 5 ቀን 20 ሺህ ብር

➡️ የፓስፖርት እድሳት ፦

1ኛ. እድሳት ፦ መደበኛ 5000 ብር ፤ አስቸኳይ 2 ቀን 25 ሺህ ብር ፤ 5 ቀን 20 ሺህ ብር

2ኛ. የፓስፖርት ገጽ ያለቀባቸው ፦ መደበኛ 5000 ብር ፤ አስቸኳይ 2 ቀን 25 ሺህ ብር ፤ 5 ቀን 20 ሺህ ብር

3ኛ. እድሳት የሚፈልጉ እና እርማት የሚያስፈልጋቸው ፦ መደበኛ 12 ሺህ 500 ብር ፤ አስቸኳይ 2 ቀን 32 ሺህ 500 ብር ፤ 5 ቀን 27 ሺህ 500 ብር

4ኛ. ፓስፖርት ቀን ያለው እና ፓስፖርታቸው የተበላሸ ፦ መደበኛ 13 ሺህ ብር ፤ አስቸኳይ 2 ቀን 33 ሺህ ብር ፤ 5 ቀን 28 ሺህ ብር

5ኛ. ፓስፖርቱ ቀን ያለው ፤ ፓስፖርታቸው የተበላሸ እርማት የሚፈልጉ ፦ መደበኛ 20 ሺህ 500 ብር ፤ አስቸኳይ 2 ቀን 40 ሺህ 500 ብር ፤ 5 ቀን 35 ሺህ 500 ብር

➡️ የጠፋ ፓስፖርት ፦

1ኛ. የጠፋ ፓስፖርት ፦ መደበኛው 13 ሺህ ብር ፤ አስቸኳይ 2 ቀን 33 ሺህ ብር ፤ 5 ቀን 28 ሺህ ብር

2ኛ. የጠፋ ፓስፖርት እርማት ፦ መደበኛ 20 ሺህ ብር ፤ አስቸኳይ 2 ቀን 40 ሺህ 500 ብር ፤ 5 ቀን 35 ሺህ 500 ብር

ምንጭ. tikvahethiopia

የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ተደረገ   | ከዛሬ ከሀምሌ 3 ቀን 2016 ዓም ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት ጀምሮ ከአውሮፕላን ነዳጅ በስተቀር በቤንዚን፣ በኬሮሲን፣ በነጭ ናፍጣ፣ በቀላል ጥቁር ናፍጣና በከባድ...
10/07/2024

የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ተደረገ

| ከዛሬ ከሀምሌ 3 ቀን 2016 ዓም ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት ጀምሮ ከአውሮፕላን ነዳጅ በስተቀር በቤንዚን፣ በኬሮሲን፣ በነጭ ናፍጣ፣ በቀላል ጥቁር ናፍጣና በከባድ ጥቁር ናፍጣ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ ተደርጎል። የሌትር ዋጋ ዝርዝር:

ቤንዚን …………………………… ብር 82.60
ነጭ ናፍጣ……………………… ብር 83.74
ኬሮሲን ……………………………ብር 83.74
የአውሮፕላን ነዳጅ …………….ብር 70.83
ቀላል ጥቁር ናፍጣ…………….ብር 65.48
ከባድ ጥቁር ናፍጣ…………….ብር 64.22

10/07/2024

ልጆቻችን ... በማይናማር !

በርካታ የሀገራችን ልጆች ፦
- የወጣትነት እድሜያቸው ሳያልፍ ህይወታቸውን ለመቀየር፣
- ደክመው ያሳደጓቸውን ቤተሰቦቻቸውን ለማገዝ እንዲሁም፣
- እድሜያቸው ሳይገፋ ቤተሰብ መስርተው ጥሩ ኑሮ ለመኖር ሲሉ ወደ ተለያዩ ሀገራት ይሰደዳሉ።

አንዳንዶቹ እጅግ አደገኛ ነው የተባለውን የህገወጥ ስደት በእግር ፣ በበረሃ ፣ በባህር አድርገው ይጓዛሉ።

አንዳንዶች ደግሞ እዚሁ ሀገር ውስጥ በየከተማው በተቀመጡ ደላሎች ማካኝነት ተታለው ምንም እንኳ በኤርፖርት በኩል ከሀገር ቢወጡም የሚሄዱት ግን መጀመሪያ ወደ ተባለው ቦታ ሳይሆን ሌላ እጅግ አደገኛ ቦታ ነው።

ለአብነት ማይናማር ይጠቀሳል።

የሀገራችንን ልጆች ' ታይላንድ ነው ለስራ የምትሄዱት ' ተብለው በደላሎች ተታለው ከሀገር የሚወጡ ሲሆን የሚወሰዱት ግን ወደ ማይናማር (ማያዋዲ) ነው።

ማይናማር ከደረሱ በኋላ የሚወሰዱት የቻናይና ማፊያ ቡድኖች ወደያዟቸው ቦታዎች እጅግ ደህንነት ወደ ሌለባቸው ስፍራዎች ነው።

በዛም የተለያዩ ህገወጥ ስራዎችን እንዲሰሩ በኃይል ያስገድዷቸዋል።

ከኢትዮጵያ ሲወሰዱ 1200 ዶላር እንደሚከፈላቸው ቢነገራቸውም እዛ ከደረሱ በኋላ ግን ለወራት ጉልበታቸውን ይበዘብዙታል። ስቃይና መከራ ይደርስባቸዋል።

ልጆቹ ድብደባ ፣ በኤሌክትሪክ ሾክ፣ በሰንሰለት መገፈ ጭምር ነው የሚደርስባቸው።

ያለ ምግብ መጠጥ እስርም ይፈጽምባቸዋል።

ህይወታችንን እንቀይራለን ብለው የሄዱት ወጣቶች በስቃይ እና መከራ ውስጥ ያልፋሉ። ለወራት ያህል ስራ እያሉ እያሰሯቸው በኪሳቸው አንድም ብር የላቸውም።

በነገራችን ላይ በስፍራው የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የሌሎች በርካታ ሀገር ዜጎችም አሉ።

አንዳንድ ሀገራትም ልጆቻቸውን ያስወጣሉ።

በታይላንድ ጎረቤት፣ ማይናማር (በርማ፣ ማይዋዲ) የሚገኙ ' ድረሱልን ፍትህ እንሻለል ' ሲሉ ቃላቸውን የሰጡ የሀገራችን ልጆች፦

- ለስራ ተብለው ወደ ታይላንድ የሄዱ ከ1500 በላይ ኢትዮጵያውያን እንዳሉ፤

- በአሁን ሰዓት ላይ የሚገኙት ማይናማር (በርማ) ፤ ማያዋዲ (Myanmar-Myawaddy) በሚባል ቦታ እንደሆነ፤

- በህገወጥ የቻይና ጋንጎች ተይዘው በአሰሪዎች ከፍተኛ ግፍ እየተፈጸመ እንዳለ፤

- በግዴታ ህገወጥ ስራ (ሰዎችን በማጭበርበር ገንዘብ መቀበል / Online Scamming) ስራ የሚያሰሯቸው እንደሆነ፤

- ከፍተኛ ድብደባ፣ የኤሌክትሪክ ቶርቸር፣ ሴቶችን መድፈር ፣ ምግብ መከልከል እንዲሁም እስከ መግደል የሚደርስ ግፍ እየተፈጸመ እንደሆነ፤

- እስከ አሁን በርካታ ሰዎች በድብደባና ቶርቸር ብዛት ህይወታቸው እንዳለፈ፤

- ካሉበት የስቃይ ቦታ ነጻ ወጥተው ወደ ሀገራቸው መመለስ እንዲችሉ የህዝብንና የመንግስትን እገዛ እንደሚያስፈልጋቸው፤

- በኤጀንሲዎች በኩል ወደ ታይላንድ ለስራ ለመሄድ ፕሮሰስ ላይ ያሉ ወገኖችም ጥንቃቄ እንዲያደርጉ
.. ድምጻቸው አሰምተዋል።

ምንጭ - TikvahEthiopia

ምን አዲስ አለ!
What is new!

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Abol posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Abol:

Videos

Share

Nearby media companies