EBC ወጣቶች

EBC ወጣቶች ትክክለኛ የመረጃ ምንጭ

በ29ኛው ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ነገ ቅዳሜ 11 ሰዓት ላይ አርሰናል ከሊድስ ዩናይትድ የሚያደርጉትን ጨዋታ በቀጥታ በኢቲቪ መዝናኛ ይከታተሉ።
31/03/2023

በ29ኛው ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ነገ ቅዳሜ 11 ሰዓት ላይ አርሰናል ከሊድስ ዩናይትድ የሚያደርጉትን ጨዋታ በቀጥታ በኢቲቪ መዝናኛ ይከታተሉ።

የከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክት   | ”ቦታዬ፤ መብቴ፤ ድምፄ” በሚል መሪ ቃል ቅድሚያ ለሴቶች የ5 ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር በከተማችን ተካሂዷል። የሴቶችን ተጠቃሚነትና ተሳትፎ ለማሳደግ መ...
26/03/2023

የከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክት

| ”ቦታዬ፤ መብቴ፤ ድምፄ” በሚል መሪ ቃል ቅድሚያ ለሴቶች የ5 ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር በከተማችን ተካሂዷል። የሴቶችን ተጠቃሚነትና ተሳትፎ ለማሳደግ መሰል የግንዛቤ ማስጨበጫና የማነቃቂያ መድረኮች ሚና የጎላ ነው። ይህን ደማቅ ፕሮግራም ላዘጋጃችሁ እና ላስተባበራችሁ ሁሉ ምስጋናዬን ለማቅረብ እወዳለሁ።

በጫሞ ሐይቅ ላይ በደረሰ የጀልባ የመገልበጥ  አደጋ የ8 ሰዎች ሕይወት  ማለፋን የጋሞ ዞን አስታወቀ*****የጋሞ ዞን ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ አለማየሁ አልጎ እንደገለ...
26/03/2023

በጫሞ ሐይቅ ላይ በደረሰ የጀልባ የመገልበጥ አደጋ የ8 ሰዎች ሕይወት ማለፋን የጋሞ ዞን አስታወቀ
*****
የጋሞ ዞን ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ አለማየሁ አልጎ እንደገለጹት ከአቅም በላይ ዕቃ፣ ሰው እና እንስሳ ጭኖ የነበረ የሞተር ጀልባ መነሻውን አማሮ ልዩ ወረዳ አልፋጮ መድረሻውን አርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ ያደረገ ነበር።

አጠቃላይ 8 ሰዎችና እንስሳትና እቃን ጨምሮ ከመጫን አቅም በላይ ጭኖ የነበረው ጀልባ በከባድ ንፋስ የቀላቀለ ዝናብ ምክንያት በጫሞ ሐይቅ ላይ በተነሳ ማዕበል ተገልብጦ መስጠሙን አቶ አለማየሁ ገልጸዋል።

የጋሞ ዞን አስተዳደር አደጋው ከደረሰበት ሠዓት ጀምሮ ፖሊሶችን እና የጀልባ ኦፕሬተሮችን በማሰማራት ፍለጋ ቢያደረግም እስከአሁን አስክሬን ማግኘት እንዳልተቻለ ኃላፊው ተናግረዋል ።

የጋሞ ዞን አስተዳደር በአደጋው የ8 ሰዎች ሕይወት በማለፉ የተሰማውን ሐዘን መግለጹን ከዞኑ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የብፁዕ አቡነ ባስልዮስ ሣልሳይ እና የብፁዕ ዶ/ር አቡነ አረጋዊ  ሥርዓተ ቀብር ተፈፀመ*****************************የብፁዕ አቡነ ባስልዮስ ሣልሳይ እና የብፁዕ ዶ/ር  አቡነ...
26/03/2023

የብፁዕ አቡነ ባስልዮስ ሣልሳይ እና የብፁዕ ዶ/ር አቡነ አረጋዊ ሥርዓተ ቀብር ተፈፀመ
*****************************

የብፁዕ አቡነ ባስልዮስ ሣልሳይ እና የብፁዕ ዶ/ር አቡነ አረጋዊ ሥርዓተ ቀብር ቅዱስ ፓትርያርኩ፣ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ ከፍተኛ የመንግሥት ባለ ሥልጣናት፣ የሌሎች እምነት ተቋማት መሪዎች፣ ቤተሰቦቻቸው በተገኙበት ቅድስት ሥላሴ ካቴደራል ተፈጸመ።

የሁለቱ ብፁዓን አባቶች የሽኝት መርሐ ግብር በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል መካሄዱን የኢኦተቤ መገናኛ ብዙኀን አገልግሎት ሥርጭት ድርጅት መረጃ ያመለክታል።

በሽኝት መርሐ ግብሩ ላይ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፣ ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ ፣ብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሓፊ ፣ በርካታ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ የሃይማኖት ተቋማት የበላይ ጠበቂ አባቶች፣ የፌዴራልና የክልሎች ከፍተኛ የሥራ ሓላፊዎች፣ ከድሬዳዋና ከጂቡቲ እንግዶች እንዲሁም ምዕመናን ተገኝተዋል።

ከባድ አውሎ ንፋስ በሁለት የአሜሪካ ግዛቶች ውስጥ ቢያንስ 26 ሰዎችን ህይወት ቀጠፈ**************************ደቡባዊ የአሜሪካ ግዛቶችን በመታው ከባድ አውሎ ንፋስ ምክንያት በ...
26/03/2023

ከባድ አውሎ ንፋስ በሁለት የአሜሪካ ግዛቶች ውስጥ ቢያንስ 26 ሰዎችን ህይወት ቀጠፈ
**************************

ደቡባዊ የአሜሪካ ግዛቶችን በመታው ከባድ አውሎ ንፋስ ምክንያት በሚሲሲፒ እና በአላባማ ውስጥ ቢያንስ የ26 ሰዎችን ሕይወት ቀጠፈ።

በአሁኑ ወቅትም በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች ፈልጎ የማዳን ጥረት እየተደረገ ሲሆን፣ የሚሲሲፒ ግዛትም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተደንግጎባታል።

በሚሲሲፒ ግዛት ውስጥ የምትገኘው ሮሊንግ ፎርክ የተባለችው ከተማ ከሞላ ጎደል የወደመች ሲሆን፣ ጎዳናዎች በከባድ አውሎ ነፋሱ ምክንያት ከጥቅም ውጪ በሆኑ መኪኖች፣ በቤቶች ፍርስራሾች እና በመስታወት ስብርባሪዎች ተሸፍነዋል።

ከባድ አውሎ ንፋሱ ግዛቶቹን የመታው ነዋሪዎች እንቅልፍ ላይ በነበሩበት እኩለ ሌሊት ላይ ስለነበረ የማስጠንቀቂያ ደወልን የሰማ አልነበረም ተብሏል።

ከአደጋው መትረፋቸውን ተአምር ነው ያሉት ፍራንሲስኮ ማክናይት የተባሉት ነዋሪም፣ በውድቅት ሌሊት የነቁት በከባዱ የአውሎ ንፋስ ድምጽ መሆኑን ገልጸው፣ የዚያን አይነት የፋስ ድምጽ በሕይወታቸው ሰምተው እንደማያውቁ ተናግረዋል።

የሚሲሲፒ አገረ ገዢ ቴት ሪቭስ በከባዱ አውሎ ንፋስ የተመቱ የግዛቲቱን ከተሞች ቅዳሜ ዕለት በመጎብኘት ነዋሪዎችን ያነጋገሩ ሲሆን፣ የግዛቲቱ አስተዳዳሪ ያለውንም ሁኔታ “አሰቃቂ” ሲሉ በትዊተር ገጻቸው መግለፃቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

አደጋውን ተከትሎ ከሚሲሲፒ የደረሳቸው መልዕክት “ልብ የሚሰብር ነው” ያሉት ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን፣ የፌደራል መንግሥቱ ጉዳት የደረሰባቸውን ለመደገፍ “የሚችለውን ሁሉ ያደርጋል” ሲሉ ቃል ገብተዋል።

ከሚያሽከረከረው ባጃጅ ላይ የተረሳ 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ*****************  በድሬዳዋ ከተማ ከሚያሽከረከረው ባጃጅ ላይ የተረሳ 150ሺህ ብር ለባለቤቱ ...
26/03/2023

ከሚያሽከረከረው ባጃጅ ላይ የተረሳ 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ
*****************

በድሬዳዋ ከተማ ከሚያሽከረከረው ባጃጅ ላይ የተረሳ 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል።

መኮንን ግርማ ኑሮን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ ባጃጅ ላይ ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው።

ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015 ዓ.ም እንደተለመደው ለስራ በድሬዳዋ ጎዳና ላይ ከምሽቱ ሶስት ሰአት ላይ ባጃጁን እያሽከረከረ ሳለ የድሬዳዋ ከተማ ነዋሪ የሆኑት አቶ መሀመድ ዑስማን ከሳቢያን ወደ ኦርቢት ለመሄድ በሱ ባጃጅ ተሳፍረው ወደተባለው ቦታ ማድረሱን ተናግራል።

ይህ ከሆነ ከአንድ ሰአት በኋላ ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እና እንድመለከት ተነገረኝ የሚለው ወጣቱ፤ ከተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሬ ስመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ በርካታ ብር ተቀምጦ ማግኘቱን እና ወዲያው ገንዘቡን ይዞ ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳሬክቶሬት በመምጣት 150ሺህ ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ተናግሯል።

ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፣ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ያገኘነው መረጃ አመልክቷል።

ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ዑስማን በበኩላቸው፤ ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የምሽት ባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልፀው፣ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

Address

Addis Abebe
Addis Ababa
1000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when EBC ወጣቶች posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to EBC ወጣቶች:

Share

Nearby media companies