Ethio Nice

Ethio Nice "ኢትዮ ናይስ የምርጦች ምርጫ" አዳዲስ እና ወቅታዊ መረጃዎች፣አዝናኝ ቪዲዮዎች በየቀኑ ይደርስዎታል

12/04/2024
ራብ ጊዜ አይሰጥም የዩክሬን አርሶ አደሮች የጥይት መከላከያ ለብሰው እርሻቸውን ቀጥለዋልየሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት ከተጀመረ 70 ቀናት ሞልቶታልበደቡባዊ ክልል የሚኖሩ የዩክሬን አርሶ አደሮች ማሳ...
07/05/2022

ራብ ጊዜ አይሰጥም
የዩክሬን አርሶ አደሮች የጥይት መከላከያ ለብሰው እርሻቸውን ቀጥለዋል
የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት ከተጀመረ 70 ቀናት ሞልቶታል
በደቡባዊ ክልል የሚኖሩ የዩክሬን አርሶ አደሮች ማሳቸውን ለማረስ የጥይት መከላከያ እየለበሱ መሆኑ ታውቋል።

ዩክሬን የሰሜን አትላንቲክ ቃልኪዳን ጦር ወይም ኔቶን እቀላቀላለሁ ማለቷን ተከትሎ ከሩሲያ ጋር ወደ ጦርነት ካመራች 70ኛው ቀን ላይ ይገኛል።

በዚህ ጦርነት ምክንያት ከ6 ሚሊየን በላይ ዩክሬናዊያን ወደ ጎረቤት ሀገራት የተሰደዱ ሲሆን ከተሞች፣ መኖሪያ መንደሮች እና መሰረተ ልማቶች በመውደም ላይ ይገኛሉ።

የሁለቱ ሀገራት ጦርነት በተለይም የስንዴ ልማት ስራዎች የሚከናወኑበት ወቅት ላይ መሆኑ ስንዴ አምራች ዩክሬናዊያን አርሶ አደሮችን በመፈተን ላይ ነው።

ይህ የስንዴ አዝመራ ወቅት እንዳያልፋቸው የሰጉ ዩክሬናዊያን ገበሬዎች የጥይት መከላከያ ጃኬት እና ሄልሜት አድርገው ስንዴ ማልማታቸውን ቀጥለዋል ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።

አርሶ አደሮቹ ከሩሲያ የሚተኮሱ ሚሳኤሎች እና ከባድ መሳሪያዎች እንዳያገኟቸው የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም ላይ ናቸው።

የጦርነቱ ተኩስ ልውውጥ ሲበረታ መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ በመደበቅ ተኩስ ጋብ ሲል ደግሞ ወደ ማሳቸው ጥይት የማይበሳቸው ሄልሜቶችን እያደረጉ በመሄድ ስራቸውን ቀጥለዋልም ተብሏል።

በተለይም የሩሲያ ሮኬት ጥቃቶች በጣም አስፈሪ ናቸው የሚሉት እነዚህ ዩክሬናዊያን አርሶ አደሮች ጦርነቱ አጠቃላይ ህይወታቸውን እንደቀየረው እና ወቅቱ እንዳያልፋቸውም ትግል ላይ መሆናቸውን አክለዋል።

በዩክሬን ልዩ ዘመቻ በሚል ይፋዊ ጦርነት የጀመረችው ሩሲያ አሜሪካ እና የአውሮፓ ህብረትን ጨምሮ በተለያዩ ሀገራት ከ6 ሺህ በላይ ማዕቀቦች ተጥሎባታል።

ምዕራባዊያን በተለይም የሩሲያ ነዳጅ በዓለም እንዳይሸጥ ማዕቀቦች የተጣሉባት ሲሆን፤ ሩሲያ በበኩሏ ወዳጅ አይደሉም ያለቻቸው ሀገራት ነዳጅ በሩብል እንዲገዙ ውሳኔ አስተላልፋለች።

Italian troops surrendered to Ethiopian army after they were defeated and humiliated in a failed attempt to invaded Ethi...
04/05/2022

Italian troops surrendered to Ethiopian army after they were defeated and humiliated in a failed attempt to invaded Ethiopia in 1896. Ethiopia defeated Italy at the Battle of Adowa. They resisted European imperialism and remains the only African country that was never COLONIZED.

ገዳይ የሆነ ዜና :-(በጦፎኛ)ሼኽ አልዓሙዲን በአቶ አብነት ገብረመስቀል ላይ አዲስ ክስ መሰረቱ። የክሱ ጭብጥም : አቶ አብነት ገ/መስቀል :  መጠኑ:-  አስራ ሶስት ሚሊየን : የሆነ ገንዘ...
05/04/2022

ገዳይ የሆነ ዜና :-(በጦፎኛ)
ሼኽ አልዓሙዲን በአቶ አብነት ገብረመስቀል ላይ አዲስ ክስ መሰረቱ። የክሱ ጭብጥም : አቶ አብነት ገ/መስቀል : መጠኑ:- አስራ ሶስት ሚሊየን : የሆነ ገንዘብ: ያለአግባብ ከሚድሮክ ኩባንያ በመውሰዳቸው ሲሆን : ተከሳሽ :-አቶ አብነት ገብረመስቀልም ዛሬ: ለፌዴራሉ ከፍተኛው ፍርድቤት ቀርበው በሰጡት የክስ መልስ :

"ሚድሮክ ኩባንያን ለማስተዳደር ወደ ሥራ ስገባ :አቶ አሊ አልአሙዲን "ደሞዝህን እራስህ ትወስናለህ" ብለውኝ ስለነበር: የተፈራረምነው ውልም ስለሌለ : በተነጋገርነው መሰረት :ደሞዜን እራሴ በመወሰን : የአንድ አመት ደሞዜ የሆነውን የላቤን ውጤት : አስራሶስት ሚሊየን ብር :ወስጃለሁ " ብለዋል።

ጎበዝ :ዝም ብለን ተሞኝተን እንጂ :-

" የራስን ዕድል በራስ መወሰን " የተባለው መብት : ትክክለኛ ትርጉምማ ይሄ ነው እንጂ ዴ!

👍👍👍👍
05/04/2022

👍👍👍👍

" ኧረ እባካችሁ ያልተዘጋ የጠጅ ጀሪካን ካለ ዝጉ! አግማማችሁን "......የ31 ቁጥር አንባሳ ባስ ቲኬት ቆራጭ!" እኔን ነውኮ! " አለኝ አንድ በጠጅ ፊቱ እስኪመሽ የሰከረ ሞልፋጣ! " እ...
05/04/2022

" ኧረ እባካችሁ ያልተዘጋ የጠጅ ጀሪካን ካለ ዝጉ! አግማማችሁን "......የ31 ቁጥር አንባሳ ባስ ቲኬት ቆራጭ!
" እኔን ነውኮ! " አለኝ አንድ በጠጅ ፊቱ እስኪመሽ የሰከረ ሞልፋጣ!
" እማማ መቼ የሚነጠር ቅቤ ነው? " ይላል ሰካራሙ የጸጉር ቅቤያቸውን በተመስጦ እያሸተተ።
" አምቡሌያም! " አሉ እማማ።
" ግፉ ግፉ ግፉ "
" ማንን ነው ? "
" በሩ አልዘጋ ብሎ ነው።"
ሾፌሩ ወርዶ መጨረሻ የመጣሁት እኔ ስለነበርኩ መቀመጫዬን ይዞ ወደ ዉስጥ ይገፋኛል። አፈርኩ፡..ሆ!
" መሃሉ ባዶ ነው ጠጋ ጠጋ በሉ ! "
" ተባበሩ! " ትላለች ትኬት ቆራጯ
" ይሄ ሰዉዬ መቀመጫዬን እንደ ፓፓዬ ታቅፎ መቅረቱ ነዉንዴ?! "....... መናደድ ጀመርኩ።
በመጨረሻም በሩ " ችስስስስ " ብሎ ተዘጋ!
ነጭ ሽንኩርት፣ ጠጅ፣ ጫማ፣ ብብት፣ ቅቤ፣ ለውዝ፣ቅመሞች...በቀጥታ ስርጭት ከ 31 ቁጥር የሚተላለፉልኝ ጠረኖች ናቸው መቼስ ! የቅድሙ ሰካራም ( የሞላው ጀሪካን ) ፍዝዝ ብሎ እያየኝ
" ሊጣላኝ ነው አቡ! አቡ...አቢ.....ቲ! "
አደራሽን ማርያም! አልኩ በሆዴ። እላዬ ላይ ከልብሶት የጋራዥ በር መስዬ እንዳልቀር በአዛኝቷ!
ከፊቴ ከኋላዬ ከጎንና ጎኔ በወፋፍራም ሰዎች ተጣብቄ ቀረሁላችሁ። እንደዛን ቀን ቀጥ ብዬ ቆሜ አላውቅም!
" ፍሬንድ "
" አቤት "
" ሶፍት አለሽ? "
" ምነው? "
" ምንም!........ ላቤ አይኔ ውስጥ ሊገባ ነው "
" እና? " ኮስተር ብሎ
" እጄን ማንቀሳቀስ አልቻልኩም፡ ጥረጊልኝ!?
ላቤ ቀጥ ብሎ ይወርዳል። እጆቼ ቢንቀሳቀሱ መጀመሪያ የሚነኩት አጠገቤ ያሉትን አዛውንት ሙሃሂት ይሆናል!
እስጢፋኖስ ስንደርስ፡ ጅራፍ ምላሷ፡
" ጠጋ ጠጋ በሉ! መሃሉ ባዶ ነው ".... ኧረ በወለላይቱ!
በሩ ሲከፈት ወደበሩ ተንሸራትቼ በሩ ስር ሽጉጥ ብዬ ቀረሁ.....እንደ ስሙኒ ቂጣ!
በሩ ሲዘጋ ፊቴ በበሩ መስታወት ተጣብቆ ቁጭ!
ከላዬ ላይ ህዝቤን ከነድውለቱ ተሸክሜ ጉዞ ወደ ሽሮ ሜዳ!........ባፋንኩሉ!
የተረሳ ነገር! ግራ እግሬስ? ከረገጥኩበት ወደ 15 ደቂቆች አለፉኝ! እግርም ይናፍቃል?
" አንዴ ልርገጥ? "
" ማንን? " አለኝ አንድ ጠማማ! ( ቲሸርቱ ላይ የቅንጅት ጣት ታትሟል.....አሄሄ! )
" አይደለምኮ ግራ እግሬ አየር ላይ........"
አንዱ አቋረጠኝ
" ተመስገን በል! " አለኝ እንደ ህዋ ጠፈርተኛ አየር ላይ ተንሳፎ!
ፊቴ ከመስታወቱ ጋር ከመጣበቁ የተነሳ ከውጪ ለሚመለከተኝ ሁሉ የማሳዝን ፍጡር መሰልኩ። የሆነ ፌርማታ ስንደርስ ከዉጪ ክላስ ሜቴን ትራንስፖርት ሲጠብቅ ተያየን!
ሊለየኝ አልቻለም! እጆቼ ስለማይነቃነቁ በአይኖቼ ስቅበዘበዝ አየኝና አማተበ!.....ምናባቱ ሆነ?
በኋላ እንደነገረኝ ሌላ ፍጡር መስየው ነው። የምሬን ነው።
" ወርዳችሁ አስወርዱኝ! " አለ አንዱ በንዋይ ደበበ ድምጽ።...... ኤጭ!! እንደገና ልንፈርስ ነው!
" በታክሲ ተመለስ! "....
" ዋ ዛሬ! "
ወረድን። ሰውየው ሰው ላይ እየዋኘ ወረደ። አዳዲስ ሰዎች ገቡ! በምን ልግባ?.........
" ሹፌር አንዴ አቁም....አቁም......ኧረ ልግባ..........ሃሎ!...አፈር ያስበላህ አቦ! "

ፍቅሬ ፍቅርሻ

ካፒቴን አየነው እንዴት መቄዶንያ ተገኙ!!!============================ካፒቴን አየነው ዘገዬ ወለጋ ሆሮጉድሩ አውራጃ በ1946ዓ.ም ተወልዱ።እንደማንኛው ልጅ ውሃ ረጭተው አፈር...
05/04/2022

ካፒቴን አየነው እንዴት መቄዶንያ ተገኙ!!!
============================
ካፒቴን አየነው ዘገዬ ወለጋ ሆሮጉድሩ አውራጃ በ1946ዓ.ም ተወልዱ።
እንደማንኛው ልጅ ውሃ ረጭተው አፈር ፈጭተው በጥሩ አስተዳደግ ያድጋሉ!
እድሚያቸው ለትምህርት ሲደርስም የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በሆሮጉድሩ 1_8 ተምረዋል።
ካፒቴን አየነው በትምህርታቸው የደረጃ ተማሪ በመሆናቸው ወደ አ/አ በመምጣት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ከ9_12 ክፍል በጥሩ ውጤት አጠናቀቁ።
የ12ኛ ዓመት ትምህርታቸውን በጥሩ ሁኔታ ካጠናቀቁ በኃላ ወደ ኢትዮጵያ አየር ሀይል ገብተው ስልጠና ጀመሩ!
የተሰጣቸውን ስልጠና በአግባቡ ወስደው ባሳዩት የተሻለ አፈፃፀም የቀድሞው የኢትዮጵያ አየር ሀይል ካፒቴን ለተሻለ ስልጠና ወደ ሩሲያ በቀድሞው ሶቪት ህብረት ስልጠና እንዲያገኙ እና ሀገራቸውን በተሻለ ሙያ እንዲያገለግሉ ይላካሉ።
ካፒቴን አየነው ለሀገራቸው በነበራቸው ጥልቅ ፍቅር የተላኩበትን ስልጠና በሚገባ አጠናቀው ወደ ኢትዮጵያ ተመለሱ።
ካፒቴን ተመልሰው እረፍት አልፈለጉም የመጀመሪያ ምድባቸው ወደ ሆነው አሰብ ለ5 ዓመት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ አገልግለው!
ወደ ድሬዳዋ የስራ ዝውውር አድርገው 12 ዓመት አገለገሉ።
በዚህ ጊዜም ትዳር መስርተው ልጆችን ወልደው ማሳደግ ጀምረዋል።
በዚህ ሰዓትም መንግስት ወድቆ ሽግግር ሲደረግ ከስራ ተባረው ለከፋ ችግር ይዳረጋሉ።
መንግስት በቅነሳ መልኩ ያባረራቸው ካፒቴን በተለያዩ ስራዎች ሲንገላቱ ላለፉት 3 አስርት ዓመታት ልጆቻቸውን ማሳደግ አቅቷቸው ለስደት ተዳረጉ።
ካፒቴን አዲስ አበባ መጥተው የአገለገሏት ሀገር እንደ ካፒቴን አክብራ አልተቀበለቻቸውም
ካፒቴን ውስጣቸው እያረረ መንገድ ላይ ተኝተው መልካም ጊዜን ይጠብቁ ነበር ።
አንድ ቀን አንድ ሰው ስለመቄዶንያ ነግሮ የሚገኝበትን ቦታ ጠቁሟቸው መጥተው በር ላይ ሲደርሱ ዶ/ር ብንያም በለጠን አግኝተው አናግረውት በሁኔታው አዝኖ በደስታ ተቀበላቸው።
በአሁኑ ሰዓት መቄዶንያ ማንኛውም ፕሮግራም ሲደረግ አስተባባሪ ሆነው እያገለገሉ የሚገኙ የማዕከሉ ግራማ ሞገስ ናቸው።
ልጆቼን ማግኘት እፈልጋለሁ?
በአሁኑ ሰዓት ቤተሰቦቼ የት እንደሚኖሩ አላውቅም ስለዚህ ልጆቼ ሁላችሁም መልዕክቴን ለሁሉም በማድረስ ተባበሩኝ። ስልክ ቁጥር በ8131 ይደውሉልን አመሰግናለሁ።
ካፒቴን አየነው ዘገዬ
ምንጭ መቄዶንያ

አሜሪካ ከሰሞኑ አዲስ ሚስጥራው የሃይፐርሶኒክ ሚሳዔል ሙከራ አድርጋለችየአሜሪካ ጦር ባሳለፍነው የፈረንጆቹ ወር ሚስጥራዊ የሃይፐርሶኒክ ሚሳዔል ሙከራ ማድረጉ ተሰምቷል።ጦሩ የሚሳዔል ሙከራውን ...
05/04/2022

አሜሪካ ከሰሞኑ አዲስ ሚስጥራው የሃይፐርሶኒክ ሚሳዔል ሙከራ አድርጋለች

የአሜሪካ ጦር ባሳለፍነው የፈረንጆቹ ወር ሚስጥራዊ የሃይፐርሶኒክ ሚሳዔል ሙከራ ማድረጉ ተሰምቷል።

ጦሩ የሚሳዔል ሙከራውን ለሁለት ሳምንታት ሚስጥራዊ አድርጎ የቆየው ከሩሲያ ጋር ያለው ያለውን ውጥረት ላለማባባስ እንደሆነም ዴይሊ ሜይል ዘግቧል። አሜሪካ የሃይፐርሶኒክ ሜሳዔል ሙከራውን ያካሄደችው በምእራብ የባህር ዳርቻ ላይ ሲሆን፤ ሙከራውም ከ B-52 ቦምብ ጣይ የጦር አውሮፕላን ላይ መካሄዱ ታውቋል።

በሙከራው ወቅትም ሚሳዔሉ በ65 ሺህ ጫማ ከፍታ ላይ ከ480 ኪሎ ሜትር በላይ የተጓዘ ሲሆን፤ በአጠቃላይ 5 ደቂቃ ያክል አየር ላይ መቆየቱም ነው የተገለፀው።

አዲሱን የአሜሪካ ሃይፐርሶኒክ ሜሳዔል ምን የተለየ ያደርገዋል?

“ሃይፐርሶኒክ” የሚለው ቃል ከድምፅ እስከ 15 እጥፍ የሚፈጥን ማንኛውም ነገር የሚገልጽ ሲሆን፤ በሰዓት 6 ሺህ ኪሎ ሜትር ወይም ከዚያ በላይ የሚበር፤ በሌላ አገላለጽ እጅግ በጣም ፈጣን የሚለውን ለመግለጽ ጥቅም ላይ ይውላል።

አሜሪካ ከሰሞኑ የሞከረችው ሚሳዔልም ከጦር ጀቶች ላይ የሚወነጨፍ ሲሆን፤ ከድምፅ እስከ 15 እጥፍ የሚፈጥን መሆኑ ተነግሯል።

በዚህም ሚሳዔሉ በ5 ደቂቃ ውስጥ ከ480 ኪሎ ሜትር በላይ በሰዓት ደግሞ ከ6 ሺህ 173 ኪሎ ሜትር በላይ መብረር የሚችል መሆኑ ታውቋል።

ሚሳዔሉ በውጊያ ላይ ኢላማን ጠብቆ ለመዋጋት ወደር የለውም የተባለ ሲሆን፤ ሚሰዔሉን መትቶ መጣል ከባድ መሆኑም ተነግሮለታል።

05/04/2022

ባምላክ ተሰማ የዓለም ዋንጫ እንደሚዳኝ ፊፋ አስታወቀ

ብዙ የተባለለት የኳታር የዓለም ዋንጫ በቀጣይ ዓመት ከኅዳር 12 እስከ ታኅሣሥ 9 ድረስ ሲካሄድ በዳኝነት በውድድሩ ላይ ከሚሳተፉ አርቢትሮች መካከል ስምንቱ አፍሪካዊያን መሆናቸውን ፊፋ አሳውቋል።

በዚህም ባለፈው የካሜሩን አፍሪካ ዋንጫ ከፍተኛ አድናቆትን ያገኘው ኢትዮጵያዊው አርቢትር ባምላክ ተሰማ ፊፋ የዓለም ዋንጫውን ይዳኛሉ ብሎ ዝርዝራቸውን ይፋ ካደረገው አፍሪካዊያን ዳኞች አንዱ በመሆን የኳታርን ትኬት መቁረጡን አረጋግጧል።

ከባምላክ በተጨማሪም በዓለም ዋንጫው ላይ የሚዳኙ አፍሪካዊያን ሙስጠፋ ጎርባል ከአልጄሪያ፣ ሬዱያኔ ጅያድ ከሞሮኮ፣ ፓፓ ባካሪ ጋሳማ ከጋምቢያ፣ ቪክተር ጎሜዝ ከደቡብ አፍሪካ፣ ጃኒ ሲካዝዌ ከዛምቢያ፣ ማጉኤቴ ንዲያዬ ከሴኔጋል፣ ጃኩኤስ ንዳላ ከኮንጎ መሆናቸው ተረጋግጧል።

ባምላክ ተሰማ በ2018 የሩስያ ዓለም ዋንጫ ላይ በአራተኛ ዳኝነት አገልግሎ የተመለሰ ሲሆን በቅርቡ በካሜሩን አዘጋጅነት በተካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ላይ የሴኔጋል እና ቡርኪናፋሶን የግማሽ ፍፃሜን ጨዋታ ያጫወተ ሲሆን ከቀናት በፊትም ለአለም ዋንጫ ማጣሪያ የመጀመሪያ ጨዋታ ባማኮ ላይ ማሊ ከቱኒዚያ ያደረጉትን ጨዋታ በመሀል ዳኝነት መምራት እንደቻለ ኢፕድ በዘገባው አስታውሷል።

AddisWalta - AW
አዲስ ዋልታ
Walta Media and Communication Corporate

05/04/2022

የጀርመን ፖሊስ በሩሲያ ቋንቋ የሚሰራ እና በድር አምባ የሚካሄድ የሃይድራ የጥቁር ገበያ ትስስርን ከኢንተርኔት ላይ ማገዱን አስታወቀ። ፖሊስ ቡድኑ የሚገለገልበትን 23 ሚሊዮን ዩሮ ወይም 25 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣ ቢትኮይን መያዙን ገልጿል።
በጎርጎሪዮሱ 2015 የተመሰረተው ሃይድራ ወይም የበይነ መረብ የገበያ የትስስር መድረክ ፤ ህገ-ወጥ መድሃኒቶችን በመሸጥ፣ በተሰረቁ የክሬዲት ካርድ መረጃዎችን በመጠቀም ፣ የውሸት ምንዛሪ እና የውሸት የመታወቂያ ሰነዶችን በመስረቅ እንዲሁም በሚስጠራዊ ትስስሩ ላይ የሚሳተፉ ሰዎችን ማንነትን በመደበቅ ሲያሳትፍ መቆየቱን የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘግቧል። ህገ ወጥ የኢንተርኔት የገበያ ትስስሩ ከ17 ሚሊዮን በላይ ደንበኞች እና ከ19 ሺ በላይ አቅራቢዎች እንደነበሩት የጀርመን ፌዴራል ፖሊስ አስታውቋል። ሃይድራ የገበያ መድረክ በጎርጎርሳውያኑ 2020 ብቻ ከ1.23 ቢሊዮን ዩሮ በላይ የሚያወጣ ግብይት ሳይፈጽም እንዳልቀረ ፖሊስ በመግለቻው አመልክቷል። የፖሊስ መርማሪዎች የሀይድራ የገበያ ማዕከል የሆነውን የኢንተርኔት መቆጣጠርያ ወይም ሰርቨር በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን እና «መዝጋታቸውን» ዘገባው አመልክቷል።
በወንጀል ድርጊቱ የተጠረጠሩ "በኢንተርኔት ላይ ወንጀል ነክ የንግድ መድረኮችን በመስራት ላይ ናቸው" በማለት ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑንም አመልክቷል። ህገ ወጥ የኢትንተርኔት የገበያ ትስስር መድረኩ ላይ በርካታ አሜሪካውያን ባለስልጣናትን በማሳተፍ ክትትል መደረግ የተጀመረው በነሐሴ 2021 መሆኑን ያመለከተው የፖሊስ ዘገባ የቢትኮይን ዲጂታል የመገበያያ ገንዘብ በዚሁ መስመር የሚደረጉ ግብይቶችን ለመደበቅ አገልግሎት ላይ መዋሉ በተለይ ወንጀለኞችን ለመያዝ ሲደረጉ የነበሩ ክትትሎች እና ምርመራዎችን አስቸጋሪ አድርጎት ቆይቷል ፤ ብሏል።

የራሺያ የምፅአት ቀን መሳሪያ፡ የሞተው እጅ (Dead Hand)‼️***የአሜሪካ እና ራሺያ ቁመት መለካካት ከጥንት ጀምሮ ነው፡፡ እሰጥ አገባቸው በሁለቱ ብቻ ቢሆን ባልከፋ ነበር፡፡ ግና ጎራ ...
17/03/2022

የራሺያ የምፅአት ቀን መሳሪያ፡ የሞተው እጅ (Dead Hand)‼️
***
የአሜሪካ እና ራሺያ ቁመት መለካካት ከጥንት ጀምሮ ነው፡፡ እሰጥ አገባቸው በሁለቱ ብቻ ቢሆን ባልከፋ ነበር፡፡ ግና ጎራ የለየም ጎራ ያለየም ከገፈቱ ቀማሽ መሆኑ እንደማይቀር ግን ከዚህ በፊት የነበሩትን የጦርነት ታሪኮቻቸውን እንዲሁም አሁነ እየሆነ ያለውን ጎራ መለየት መታዘብ ብቻ በቂ ነው፡፡
የቀዝቃዛው ጦርነት በአሜሪካ እና በሶቪዮት ህብረት መካከል ለግማሽ ክፍለ ዘመን ገደማ የከረመ የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካ እንዲሁም አንዳንዴ የወታደራዊ ፍጥጫ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ታዲያ ይህ ጦርነት ለአለማችን ካተረፈላት ከፍተኛው ስጋት መካከል አውዳሚ የኑክሌር ቦምቦችን ግንባታ እና እነርሱን ተሸክመው የሚከንፉ እጅግ በጣም ፈጣን ሚሳኤሎች በግንባር ቀደምትነት ይቀመጣሉ፡፡ ታዲያ ፈስ ያለበት ዝላይ አይችልም ነውና ሁለቱም አገራት አንዱ አንዱን ሊያጠቃ ይችላል በሚል ስጋት ሰውነታቸው እየራደ ነው የኖሩት፡፡
በዚህ ወቅት ነበር ሶቪዮት ህብረት የመጨረሻው የምፅአት ቀን የተባለውን መሳሪያ የገነባችው፡፡ መሳሪያውን እጅግ አስከፊ ያደረገው ደግሞ አንዲት ጥቃት በሶቭዮት ህብረት የኑክሌር ጦርነት ውስጥ ገብታለች ብሎ ካሰበ እንዲሁም ሶቭዮቶች መከላከል የማይችሉበት የመጨረሻ ህቅታቸው ላይ እንደደደረሱ ካወቀ ሲስተሙ በአፀፋው በሶቭዮት ምድር ሁሉ የሚገኙ ኑክሌር ቦምቦችን የታጠቁ ሚሳቼሎችን ጨምሮ ሁሉንም ሚሳኤሎች አውቶማቲካሊ ይተኩሳቸዋል፡፡ እንግዲህ ከዚያ በኋላ በምድራችን ላይ የሚሆነውን ጥፋት እናንተው ስሩት፡፡
ሲሰተሙን ያኔ ሶቭዮት ህብረት “ፓራሜትር” ብላ ስትጠራው ምዕራባዊያን ደግሞ “የሞተ እጅ” ብለው ይጠሩታል፡፡ አንግዲህ እስከአሁን ያሉ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ከሆነ ደግሞ ራሺያዎቹ ዛሬም ድረስ ይህን ሲስተም ምናልባት ያቺ የቁርጥ ቀን ከመጣችብን ብለው አስቀምጠውታል፡፡
በርግጥ ስለመሳሪያው ብዙም የሚታወቅ ነገር የለም፡፡ ራሺያዎችም ምስጢር አድረገው እንደያዙት አሉ፡፡ መሳሪያውን ከገነቡት አንዳንደ የቀድሞ ባለሙያዎች ምስክርነትን በማየት፣ ከቀድሞ የራሺያ ባለስልጣናት እንዲሁም ከበርካታ የግል ጋዜጠኞች መረጃ በመነሳት ግን በትክክልም ሩሲያ መሳሪያው አሁንም እንዳላት መናገር ይቻላል፡፡
መሳሪያው በሩሲያ ምድር ውስጥ የሚገኙ ሚሳኤሎችን በሙሉ በአንድ ጊዜ ለማዘዝ የሚያስችል ነው፡፡ በነገራችን ላይ ታዲያ መሳሪያው እንደሌሎች መሳሪያዎች ሁሉ በየቀኑ አክቲቭ አይደረግም፡፡ ልክ እንደመጠባበቂያ መሳሪያ ያለ ነው፡፡
ራሺያ አጣብቂኝ ወስጥ ብትገባ፣ ለተቃጣባት ጥቃት አፀፋ የመመለስ አቅም ላይ ባትሆን አልያም ራሺያ ብትወድም እና ማንም ደሟን መመለስ የማይችል ሰው በአገሪቷ ባይኖር መሳሪያው የራሱን ልኬት በመውሰድ ኑክሌሮቿን በሙሉ በሞግዚትነት ተቀብሎ ጠላቶቿ ላይ ያዘንባቸዋል፡፡ ምናልባት እዚህ ላይ “አንዴት እንዴት ነው ነገሩ?” የሚል አንባቢ ካለ ይህን እንበል፣
ሲስተሙ ስራውን እንዲሰራ በተደረገ ቅጽበት የመጀመሪያ ስራው የሚያደርገው በርካታ ዳሰሳዎችን ማካሄድና የኑክሌር ጦርነት ተጀምሯል ወይንስ አልተጀመረም የሚለውን ማጣራት ነው፡፡ ዳሰሳዎቹ የግፊት አነፍናፊዎችን፣ የመጠን መቆጣጠሪያዎችን፣ የራዲየሽን መለያዎችን ጨምሮ በርካታ መንገዶችን ያካተተ ሲሆን ከሚመለከታቸው ባለስልጣን ጋር ያለው ግንኙነት እየሰራ እንደሆነ አልያም መቋረጡንም አብሮ ያጣራል፡፡
ሲስተሙ እነዚህን ሁሉ ማጣራቶች አድረጎ የኑክሌር ጦርነት ተጀምሯል የሚል መደምደሚያ ላይ ከደረሰ አውቶማቲካሊ ከመሬት ውስጥ የተቀበረ አንድ ሮኬት ይተኩሳል፡፡ ይህ ሮኬት ደግሞ የራሺያን ግዛት እያቋረጠ በመክነፍ በአገሪቱ ሁሉ በተጠንቀቅ ላይ ላሉ የሚሳኤል ሳይቶች አገር አቋራጭ ሚሳኤሎቻቸውን እንዲተኩሱ የሬዲዮ መጎድ ይልክላቸዋል፡፡ ይሄኔ ሁሉም የሚሳኤል ሳይቶች በጉያቸው የሸሽጓቸውን ሚሳኤሎች ሁሉ በቅፅበት መተኮስ ይጀምራሉ፡፡ እንግዲህ ፓራሜትር የሚባለው የራሺያዎቹ መሳሪያ ጠቅለል ብሎ ሲገለፅ ይህን ይመስላል፡፡
እንግዲህ አሁን ራሺያና ዩክሬን በጀመሩት ጦርነት መካከል አሜሪካና ምዕራባዊያን ጣልቃ ገብተው ራሺያን ከጥቅም ውጭ ለማድረግ የኑክሌር ጦርነት ቢቀሰቅሱ ራሺያዎች ደግሞ የአፀፋ ምላሽ እንዳይሰጡ ሆነው ቢዳከሙ፣ መሪዎቻቸው በጠላት እጆች ቢወድቁና አገሪቷ በሌሎች አዛዥነት ውስጥ ብትገባ፣ የሳተላይት ግንኙነት ገደል ቢገባ አልያም ሁሉም የመገናኛ መንገዶች ከጥቅም ውጭ ቢሆኑ ፓራሜትር ልክ ሶስት ቅድመ ሁኔታዎች እንደተሟሉለት ስራውን ይጀምራል፡፡
- በመጀመሪያ በራሺያ አመራር ከጥልቅ እንቅልፉ መቀስቀስ አለበት፡፡
- ሁለተኛው ደግሞ ከማዘዣ ጣቢያው ጋር ያለው ግንኙነት መቋረጡን ማረጋገጥ አለበት፡፡
- ሶስተኛ ከላይ የነገርናችሁ አነፍናፊዎቹ የኑክሌር ጦርነት እንደተጀመረ ማረጋገጫ ሊሰጡት ይገባል፡፡
እነዚህ ሶስት ነገሮች ከተሟሉለት የሚያስፈልገው ምናልባትም “ተኩስ” የሚለውን ቁልፍ የሚጫን አንድ ሰው ብቻ፡፡ ከዚያ በኋላ ያለውን ማሰብ ነው፡፡ (አንድ ኑክሌር ቦምብ ሊያስከትል የሚችለውን ውድመት ከገፃችን ላይ ፈለግ ፈለግ አድርገው ያንብቡ)
በነገራችን ላይ ሩሲያ በ6000 የኑክሌር ቦምቦች ባለቤትነት ከአለማችን አንደኛ አገር መሆኗን ልብ ይሏል፡፡
ውድ የሰዋሰው ቤተሰቦች ታዲያ ይህ ሲስተም በጦርነት ጊዜ ተመትቶ እንዳይወድም አልያም ራሱ በሚፈጽመው የአፀፋ ጥቃት እንዳይጠፋ በማሰብ ከመሬት ስር ነው የተገነባው፡፡

ከባዱን ፈተና ወደ ፋሽን የቀየረው ኤድጋር ዳቪድስ! 1995 ላይ ከልዊስ ቫንሀሉ አያክስ አምስተርዳም ጋር በመሆን የቻምፕየንስ ሊግን ዋንጫ የተሞሸረው ሆላንዳዊው ኤድጋር ዳቪድስ ወደ ጣሊያን ...
17/03/2022

ከባዱን ፈተና ወደ ፋሽን የቀየረው ኤድጋር ዳቪድስ!
1995 ላይ ከልዊስ ቫንሀሉ አያክስ አምስተርዳም ጋር በመሆን የቻምፕየንስ ሊግን ዋንጫ የተሞሸረው ሆላንዳዊው ኤድጋር ዳቪድስ ወደ ጣሊያን አቅንቶ ለጁቬንቱስ መጫወቱ ይታወሳል።
በወቅቱ በከፍተኛ የእራስ ህመም ይሰቃይ የነበረው ሆላንዳዊው ኮከብ ወደ ሆስፒታል ሲያቀና አይኑ መታመሙ ተነግሮታል።ህመሙ ደግሞ "ግላኮማ" የሚባለው የአይን በሽታ ነበር፡፡ይህ በሽታ ደግሞ አይን ላይ በሚፈጠረው ጫና ምክንያት ከአይናችን የኋላ ክፍል ያለው የኦፕቲክ ነርቭን የሚያጠቃ ነበር፡፡
ኦፕቲክ ነርቭ የአይን ብርሀንን ወደ አንጎል የሚልክ በመሆኑ የዚህ ጥቃቅን ነርቭ መጎዳት የአይን ብርሀን እስከማሳጣት እንደሚደርስ የህክምና ባለሙያዎች ይገልጻሉ፡፡
ዳቪድስም ያጋጠመው ህመም የዓይን ብርሀኑን ሊያሳጣው የሚችል እንዲሁም የእግርኳስ ህይወቱን በአጭሩ የሚቀጭ በመሆኑ በጁቬ ፣በሆላንድ እንዲሁም በመላ እግርኳስ ወዳጆች ጭምር ድንጋጤን ፈጥሯል።
ከእግርኳስ ገለል ብሎ ከህክምና ባለሙያዎች ጋር የአይኑን ብርሀን ለማትረፍ ጭንቅ ውስጥ የገባው ዳቪድስ አይኑ የቀዶ ጥገና እንደሚያስፈልገው ተነግሮት ነበር፡፡
ፈጥኖ ወደ ሀኪም በማቅናቱ የተጠቀመው ዳቪድስ አይኑ ቀዶ ጥገና ተደርጎለት የአይን ብርሀኑን እንዳያጣ ተደረገ፡፡
አንገብጋቢው ጉዳይ መላ ቢያገኝም ቀጣዩ ጥያቄ ግን ተጫዋቹ ወደ እግርኳስ መመለስ ይችላይ ወይ? የሚለውን መልስ መስጠት ነበር፡፡ አይን ወይስ ኳስ?
ሀኪሞች ከባዱን ጥያቄ ዳቪድስ አይኑን እየጠበቀ መነጽር አድርጎ እንዲጫወት ፈቀዱ፡፡
ዳቪድስ አእምሮውን አሳምኖ በከፍተኛ ተነሳሽነት መነጽሩን አድርጎ ሜዳ ላይ በመጫወት ከባዱን ፈተና ተጋፍጧል፡፡
ተጫዋቹ ከአይኑ ላይ በማትለየው መነጽሩ በቀላሉ ይለይ የነበረ ሲሆን ይህን ፈተና ወደ ሌላ መነጋገሪያ ቀይሮት ነበር፡፡
የተለያዩ ቀለም ያላቸው የመነጽር አይነቶች አይኑ ላይ እያደረገ አይኑን እየጠበቀ እንዲሁም ስራውን እየሰራ ከባዱን ፈተና ወደ ፋሽን ቀይሮ ቄንጠኛው/Stylish/ ዳቪድስ ሁሉ እየተባለ እንደነበር ይታወሳል፡፡

27/06/2021

ብርቱካን ሚዴቅሳ በቃሊቲ እስር ቤት ውስጥ-ለትውስታ

27/06/2021

ቀብርና ማስታወቂያ እረ በሳቅ it makes your day የደረጀ ሀይሌ እና የበውቀቱ ስዩም አስቂኝ ጭውውት

18/06/2021

ethio nice

Address

Ethionicetube@Gmail. Com
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio Nice posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Ethio Nice:

Share



You may also like