18/01/2024
ልደት 🧁 🎂 🧁
ዛሬ የልበ ቀናዋ በልብ ህሙማን የሚሰቃዩ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ትልቅ ነገር እያደረገች ያለችው
የተወዳጇ አርቲስት መሰረት መብራቴ ልደት ነው
* ተወልዳ ያደገችው አዲስ አበባ ግቢ ገብርኤል አካባቢ ሲሆን
* አንድ ወንድም እና ሁለት ታናናሽ እህቶች አሏት
* በጣም ተወዳጅ ብለን ልንጠራት የምንችላት ተዋናይት
* ትወናን ከትምህርት ቤት ወደ ሰንበት ትምህርት ቤት አድጎ ወደ ቲቪ ድራማ በልጅነቱ በሻማ እንባ ድራማ ተቀላቅላለች
* በርካታ የመድረክ ስራዎች ላይ በትያትር ቤቶች እና ከሀገር ውጪ ትያትር ተውናለች፣
* ትንሽ የማይባሉ የሬድዮ ድራማኦች ላይም ተሳትፋለች።
በፊልም :-
* ጉዲፈቻ፣
* የፍቅር ሽምያ፣
* ዜማ ህይወት፣
* ንጉስናሁ ሰናይ፣
* የሞርያም ምድር፣
* ቫኬሽን ፍሮም አሜሪካ፣
* ሄሮሽማ
* ሀርየት የተወነችባቸው ናቸው።
የቲቪ ድራማ በይበልጥ:-
* ገመና፣
* ገመና ሁለት
* በቀናት መካከል ተጠቃሽ ናቸው።
* ከ200 በላይ ማስታወቂያዎችን ሰርታለች
* የሷ ጀግና ከሀገር ውስጥ አፄ ሚኒሊክ ሲሆኑ
* ከውጪ ደሞ ኔልሰን ማንዴላ ናቸው
* የምታደንቀው አክትረስ ጁሊያ ሮበተርስን ሲሆን
* ኳስ በጣም እንደምትወድም ስለ መሲ ህይወት ታሪክ ውስጥ የተፃፈው ያሳያል
እንኳን ተወለድሽ በሏት ❤️👍🎂🎂🎂
መልካም ልደት መሲያችን ፈጣሪ እረጅም እድሜ ከጤና ጋር ይስጥልን::
🙏🙏🙏
🌴🌴🌴