Journal press media

Journal press media Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Journal press media, Digital creator, Addis Ababa.

09/08/2023
09/08/2023

የመደመር አንድነት አንድአይነትነት አይደለም!
ኢትዮጵያ በዚህ ሰአት ከገባችበት ውስብስብ ፖለቲካዊ ችግሮች ወደ ተሻለ ደረጃ መሻገር የምትችለው የመደመርን ፅንሰ ሀሳብን በሙሉ ቁመና በመተግበር መሆኑ አያሻማም።

መደመር ሀሳቡ ጥልቅ የሆነ እንደ ኢትዮጵያ ላሉ ህብረ ብሄራዊ እና ቀለመ ብዙ ሀገሮች ላይ መተግበር እምቅ የሆኑ ጉልበቶችን በአንድ ላይ በማውጣት፣ ልዩነቶችን አንደ እድል በመውሰድ ሀገርን ወደ ተሻለ ምእራፍ የማሻገር አቅም ያለው የአንድነት ሀሳብ ነው።

ሁሉም የኔ ነው የሚለውን ቀለም በዙሪያው ካሉ ኢትዮጵያውያን ጋር በሰላም፣ በመቻቻል እና በመከባበር በአንድ ላይ አዋህዶ የሚፈጥረው ሀምራዊ የሆነው አንድነት እና የሚፈጥራትን ሀገር ማየት ነው የመደመር ፅንሰ ሀሳብ።

30/07/2023
30/07/2023

ጠንካራና ቅቡልነት ያለው ዘላቂ ሀገረ መንግሥት መገንባት፣

የብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካ ፕሮግራም ዋነኛ ዓላማ ጠንካራና ቅቡልነት ያለው፣ የብሔር ማንነትን እና የሀገራዊ አንድነትን ሚዛን የጠበቀ ሀገረ መንግሥት መገንባት ነው። ከጠንካራ ሀገረ መንግሥት ግንባታ አንጻር ፓርቲያችን ሕዝብ ከቀጥተኛ የህልውና አደጋ ተጠብቆ የልማት፣ የእኩልነት እና የነጻነት ፍላጎቶቹ እንዲሟላለት የሚያስችል ነጻ፣ ገለልተኛና ብቃትን መሰረት ያደረገ ሀገራዊ ተቋማዊ አደረጃጀት መገንባት ያስፈልጋል ብሎ ያምናል። በመሆኑም የሀገረ መንግሥት ግንባታ ጅምራችን ጠንካራና የማይናወጥ ተቋማዊ መሰረት ያለው እንዲሆን የብልጽግና ፓርቲ ግቡ አድርጎ ይንቀሳቀሳል።

የብልጽግና ፓርቲ ዴሞክራሲን በተቋማዊና ሕዝባዊ ባህል ላይ መገንባት አስፈላጊ እንደሆነ ይገነዘባል። በሌላ በኩል ከሀገረ መንግሥት ቅቡልነት አንጻር የብልጽግና ፓርቲ የኢትዮጵያ ሀገረ መንግሥት ጥንካሬን ለማሳደግ በሕገ መንግሥታችን የተቀመጠውን አንድ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ማኅበረሰብ የመፍጠር ግብ ለማሳካት ይሠራል።

በመሆኑም የሀገረ መንግሥቱን ቅቡልነት በሚጨምሩና ሀገራዊ መግባባትን በሚያመጡ፣ የሕዝቦችን ግንኙነት በሚያሳልጡ እና የእውነተኛ ዕርቅ መንፈስን በሚያጎለብቱ ፖለቲካዊ ርምጃዎች ላይ ትኩረት አድርጎ ይንቀሳቀሳል።

ፓርቲያችን የሀገረ መንግሥት ግንባታችን ኅብረ ብሔራዊ አንድነትን የተላበሰና ብዝኃነትን የሚያንፀባርቅ መሆን እንዳለበት በጽኑ ያምናል።

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Journal press media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Share