06/08/2024
ልቤ፣ ለብዙ ድክመቶችሽ ምን ሰበብ ታቀርቢያለሽ?
በተወዳጅሽ በኩል እንደዚህ ያለ ቋሚነት ፣ ባንቺ በኩል ታማኝነት የጎደለው ድርጊት!
በእሱ በኩል ብዙ ልግስና ፣ ባንቺ እንዴት ያለ ተቃራኒነት!
ከእሱ ብዙ ጸጋዎች፣ ባንቺ የተፈጸሙ ብዙ ስህተቶች!
በልብህ ውስጥ እንደዚህ ያለ ቅናት ፣ እንደዚህ ያለ ክፉ ምናብ እና የጨለማ ሀሳብ ፣
እሱ ግን ተጣሪ፣ ታላቅ መንፈሰ-ጣዓም
ለምን ይህ ሁሉ ጣዓም? መራራ ነፍስህ ጣፋጭ እንድትሆን።
ለምን ይህ ሁሉ ጥሪ? ከቅዱሳን ጋር እንድትቀላቀል።
ከኃጢአታህ ንስሐ ስትገባ፤ በከንፈሮችህ ላይ ስሙ ሊበዛ፤
በዚያች ቅጽበት ህያው ሊያደርግህ ይስብሃል።
በበደልህ ላይ ስትፈራው፣ የመዳንን መንገድ አጥብቀ ስትይዝ፤
በዚያች ቅጽበት እንዲህ ያለ ፍርሃትን በልብህ ውስጥ ሰላደረገው ስለ ምን አታዩም?
ዓይንህን ካሰረ አንተ በእጁ እንዳለ ጠጠር ነህ።
ሲሻው እንደዚህ ያንከባልልልሃል፣ ሲሻው በአየር ላይ ይጥልሃል።
ሲሻው የብር፤ የወርቅ ና የእንስትን ፍቅር በልብህ ይተክላል።
ሲሻው ብርሃን በነፍስህ ውስጥ ያስገባል።
በዚህ በኩል ወደ ምትወዳቸው ይስብሃል፣
በዚያ በኩል ወደ ማይወዱክ ይስብሃል፣
በእነዚህ አዙሪት ውስጥ መርከቧ ያላት አማራጭ ወይ ማለፍ ወይ መውደቅ ነው።
ብዙ ጸሎቶችን አቅርቡ፣ በሌሊትም እጅግ በጣም አልቅስ፣
የገደል ማሚቱ ከሰባቱ ሰማያት ወደ ጆሮዎቻህ እስክታስተጋባ ድረስ።
የሹዓይብ(ዮቶር) ጩኸት፣ ልቅሶ እና እንባ እንደ በረዶ ድንጋይ ከድንበሩ ሁሉ ባለፈ ጊዜ፤
በማለዳም አዋጅ ከሰማይ መጣለት።
“ኃጢአተኛ ከሆንክ ይቅር አልኩህ ለኃጢአትህም ይቅርታ ሰጠሁ። የምትፈልገው ገነት ነው? እነሆ እሱንም ሰጥችኋለሁው;
እንግዲያው ዝም በል፤ ልመናህንም አቁም!"
ሹዐይብም(ዮቶር) መልሶ፡- “ይህን ወይም ያንን አልፈልግም። እኔ የምመኘው አንተን ፊት ለፊት ማየት ነው፤
ሰባቱ ውቅያኖሶች ሁሉ ወደ እሳት ቢቀየሩም፤
እርሱን ባገናኘው ብቻ እዘፈቅባቸዋለው።
ነገር ግን እሱን ከማየት ከተባረርኩ፣ በእንባ የረጠቡ አይኖቼ ከዚያ ራእይ ከታገቱ፣
እኔ በገሃነም እሳት ውስጥ ለመኖር የበለጠ ተስማሚ ነኝ; ገነት አይገባኝም።
ያለ እሱ ፊት ገነት ለእኔ የጥላቻ ሲኦል ናት፣
በዚህያም በሟችነት ጠረን እበላለው፣
ያለሱ፤ የዘላለማዊነት ብርሃን ግርማ ወዴት ነው?
"ቢያንስ ልቅሶህን አስተካክል፣ ልቅሶ ከወሰን በላይ ያለፈ ጊዜ፤ እይታህ ይቀንሳል፤ አይን ይታወራል" አሉት
እንዲህም አለ፡- “በመጨረሻም ሁለቱ ዓይኖቼ እሱን የሚያዩ ከሆነ፣ የእኔ አካል ሁሉ ዓይን ይሁን፣
እንግዲያውስ ስለ ዕውርነት ስለ ምን ልዘን?
ዳሩ ግን ይህ ዓይኔ ለዘላለም እሱን የተነፈገ ከሆነ
ተወዳጁን ሊያይ የማይገባው ዕውር ይሁን!”
በዚህ ዓለም ውስጥ, እያንዳንዱ ሰው ለሚወደው ቤዛ ይሆናል፤
ፍቅር ለአንዱ የደም ከረጢት ነው ፣ የሌላው ፀሀይ ግርማ ነው።
እያንዳንዱ ሰው የሚወደውን፣ ጥሩም ይሁን መጥፎ፣ ለራሱ ተፈጥሮ የሚስማማውን ነው የሚመርጠው፤
ዳሩ ግን ለማይረባው ራሳችንን ስንሰዋ ማየት እንዴት ያሳዝናል!
አንድ ቀን አንድ መንገደኛ ከያዚድ ጋር በአንድ መንገድ ጉዞ ይጀምራል፤
ባያዚድ እንዲህ አለው፤"ምን ለመነገድ መረጥክ አንተ ወንበዴ?"
ሰውየውም፣ “እኔ አህያ ሹፌር ነኝ” ሲል መለሰ።
ባያዚድ፣ “ከእኔ ተለይ!—ጌታ ሆይ፣ አህያው ግደልበት፤ ያንተ ባሪያ እንዲሆን ዘንድ!” አለ።
ጀላሉዲን ሩሚ