Light of Man

Light of Man Hojii Yesus Kiristoos fannoo gubbaatti , dhala namaatiif fiixaan baasee, maal fa'a? Namni har'a gatii Kiristoos baasetti deebi'ee gatii maaliif baasa?

14/05/2023

አንድ ወጣት በሀገረ ፓሪስ ጎዳና ለጎዳና እየዞረ ድምጹን ከፍ አድርጎ "ኢየሱስ ክርስቶስ አያድንም....." እያለ በአደባባይ ይጮሃል። ይህንን የወጣቱን ንግግር ያደመጡት አንድ አባት ወደ ወጣቱ ጠጋ ይሉና "ልጄ አንዴ ላስቸግርህ! ከዚያ ፊት ለፊት ካለው የፍራፍሬ መደብር 1 ኪሎ ብርቱኳን አምጣልኝ!?" ይሉታል።
ወጣቱም፤ ሳያቅማማ እሺታውን ገልጾ ይገዛላቸውና አምጥቶ ይሰጣቸዋል።

አባትም ብርቱኳኑን ተቀብለዉት እዚያውኑ አንድ በአንድ እየላጡ አንዳችም ሳያስቀሩ ይበሉና "ልጄ ብርቱኳኑ እንዴት ነው? ይጣፍጣል አይደል?" አሉት።

ወጣቱም በሠውየው ይናደደና "ሰውዬ ያምዎታል እንዴ? ብርቱኳኑን ብቻዎን ከበሉ በኋላ እንዴት እኔን ጣፋጭነቱን ይጠይቁኛል? ሳልበላዉ እኔ ጣዕሙን እንዴት ላውቅ እችላለሁ?" ይላቸዋል። ንዴት እየተናነቀው።

አባትም "አየህ ልጄ፦ ልክ እንደዚህ ብርቱኳን የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስን ጣዕምም ስላልቀመስከው አልገባህም። ስለዚህ ልጄ አሁኑኑ ወደቤቱ ወደ ደጁ ግባና ጣዕሙን ቅመሰው ያን ጊዜም የኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነትና ጣዕም በደንብ ይገባሃል" አሉት። እንዴት እኛ ስላልቀመስነው ነገር መናገር ይቻለናል?

ወንድሜ ዛሬ በኢየሱስ ካልሆንክ በሞት ነህ! ልትበላ፤ ልትጠጣም ትችላለህ! ልትተኛ ልትነሳ ትችላለህ! ልትሰራ ላትሰራ ትችላለህ! በኢየሱስ ካልሆንክ ግን በሌላ ኃይማኖት ሳይሆን በሞት ነህ! እባክዎን ሕይወት የሆነውን የነገስታት ሁሉ ንጉስ የሆነዉን ኢየሱስ ክርስቶስን ተቀብለው ከዘላለም ሞት ያምልጡ።

"መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና።" የሐዋርያት ስራ - 4፥12

“ኢየሱስም፦ ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ፤ የሚያምንብኝ ቢሞት እንኳ ሕያው ይሆናል።” ዮሐንስ - 11፥25

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Light of Man posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category