Gohe Tv Broadcasting service

Gohe Tv Broadcasting service ጎህ የህዝብ ድምፅ🇪🇹
(1)

"Our Strategic Partnership challenges us in more than one way.If it is accepted, in terms of principles, that Africa mus...
14/02/2024

"Our Strategic Partnership challenges us in more than one way.
If it is accepted, in terms of principles, that Africa must, for its peace, its security
and its sustainable development, count first and foremost on its own strengths,
its own genius, its own chain of solidarity, no one can deny the relevance, at this
stage of our evolution, of the need for mutually beneficial Partnerships with
others."

"የእኛ ስልታዊ አጋርነት ከአንድ በላይ በሆነ መንገድ ይፈትነናል።
ተቀባይነት ካገኘ፣ ከመሠረታዊ መርሆች አንፃር፣ አፍሪካ ለሰላሟ፣ ለደህንነቷ መረጋገጥ አለባት"

H.E. MOUSSA FAKI MAHAMAT
CHAIRPERSON OF THE AFRICAN UNION COMMISSION
FORTY FOURTH ORDINARY SESSION OF
THE EXECUTIVE COUNCIL

አንጋፋው ጋዜጠኛ ገነነ መኩሪያ (ሊብሮ) ከዚህ አለም በሞት ተለየ። የስፖርት ጋዜጠኛ ገነነ መኩሪያ የሀገራችንን ስፖርታዊ ክንውኖችን የሚያቀርብ እንዲሁም ከስፖርታዊ ክንዋኔዎች በተጨማሪ በጠቅ...
23/01/2024

አንጋፋው ጋዜጠኛ ገነነ መኩሪያ (ሊብሮ) ከዚህ አለም በሞት ተለየ።
የስፖርት ጋዜጠኛ ገነነ መኩሪያ የሀገራችንን ስፖርታዊ ክንውኖችን የሚያቀርብ እንዲሁም ከስፖርታዊ ክንዋኔዎች በተጨማሪ በጠቅላላ እውቀቱ እና መረጃ አያያዙ በርካታ እውቀቶችን ያስጨበጠ ጋዜጠኛ ነበር።
በተለያዩ የራዲዮና ቴሌቭዥን ፕሮግራሞች ላይ ታሪኮችንና ወጎችን በማቅረብም በሚዲያው ላይ ከአርባ አመታት በላይ አገልግሏል።
አንጋፋው ጋዜጠኛ ገነነ መኩሪያ “ ሊብሮ “ በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ዛሬ ንጋት ላይ ህይወቱ ማለፉ ተሰምቷል።
ጎህ ቴሌቪዠን ለመላው ቤተሰቦቹ ፣ ጓደኞቹ እና አድናቂዎቹ መፅናናትን ይመኛል ።

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ፤ የ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያው መንፈቅ ዓመት የሥራ አፈጻጸም በተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል።ኢትዮ ቴሌኮም የሦስት ዓመት ሊድ የዕድገት ...
23/01/2024

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ፤ የ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያው መንፈቅ ዓመት የሥራ አፈጻጸም በተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል።

ኢትዮ ቴሌኮም የሦስት ዓመት ሊድ የዕድገት ስትራቴጂ ቀርፆ ተግባራዊ ማድረግ ከጀመረ አንድ ዓመት ተኩል ጊዜ አስቆጥሯል ብለዋል።

በዚህም ዲጂታል ኢትዮጵያን ዕውን ማድረግ የሚችል አቅም እየገነባ መሆኑንም ገልፀዋል።

በግማሽ ዓመቱ አዳዲስ 232 የሞባይል ጣቢያዎች መገንባታቸውን ጠቁመው የ3ጂ፣ 4ጂ እና 5ጂ ማስፋፊያዎች መስራታቸውን ተናግረዋል።

በዚህም እስካሁን 463 ከተሞች የ4ጂ አገልግሎት ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልጸው በበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት 40 አዳዲስ ከተሞች ላይ ተደራሽ መደረጉን አብራርተዋል።

በርካታ የገጠር ቀበሌዎችም ላይ የኔትወርክ ማስፋፊያ እና አዳዲስ ግንባታ መከናወናቸውን ጠቁመዋል።

ኢትዮ ቴሌኮም በዓለም ካሉ 774 የቴሌ ኦፕሬተሮች መካከል 19ኛ ደረጃ ላይ መቀመጡን ጠቁመው፤ በአፍሪካ ከሚገኙ 195 ኦፕሬተሮች መካከል ደግሞ 2ኛ ደረጃ ላይ መሆኑንም ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ገልፀዋል።

በበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት 42 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር አጠቃላይ ገቢ ማግኘቱን ጠቁመው፤ የውጭ ምንዛሬ ከሚያስገኙ አገልግሎቶችም 84 ነጥብ 7 ሚሊየን ዶላር ገቢ አግኝቷል ብለዋል።

ይህም ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር 26 በመቶ ዕድገት ማስመዝገቡን ተናግረዋል።

በአጠቃላይ በበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት 11 ነጥብ 5 ቢሊየን የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን ጠቁመው ይህም ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ14 በመቶ ዕድገት አሳይቷል ብለዋል።

ከጋዜጠኞች ለተነሳላቸው ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡት ዋና ስራ አስፈፃሚዋ በተለየዩ የሀገሪቱዋት ክፍል ያጋጠመው የፀጥታ ችግር የአገልግሎት መቋረጥ፣የቴሌኮም ማጭበርበርና የግንባታ ስራ ግበዓቶች እጥረት እንዲሁም የገበያ አለመረጋጋት በግማሽ አመቱ እንደ ተግዳሮት ተጠቅሰዋል።

Interms of enhancing quality of service,networks coverage & capacity, various projects are underway while 5G mobile tech...
23/01/2024

Interms of enhancing quality of service,networks coverage & capacity, various projects are underway while 5G mobile technology service is already commercialized in certain cities,during half year, vast mobile network expansions and capacity enhancements have been done to serve additional 678.2 k customers over a 3G network, 1.1 million customers over a 4G network, 148.2k over 5G network .as a result a total capacity of serving additional 1.9 million customers where created, which brought the total mobile network capacity to 81 million.

ኢትዮቴሌኮም በ2016 በጀት ዓመት መንፈቅ 43 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ ገቢ ማግኘቱን ገለፀ።መንግስታዊው የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢ ኢትዮ ቴሌኮም፤ ባለፈው መንፈቅ ዓመት 42.9 ቢሊዮን ብር ...
23/01/2024

ኢትዮቴሌኮም በ2016 በጀት ዓመት መንፈቅ 43 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ ገቢ ማግኘቱን ገለፀ።

መንግስታዊው የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢ ኢትዮ ቴሌኮም፤ ባለፈው መንፈቅ ዓመት 42.9 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ። ኢትዮ ቴሌኮም በዚሁ ጊዜ ውስጥ የደንበኞቹን ቁጥር 74.6 ሚሊዮን መድረሱንም ገልጿል።

ኢትዮ ቴሌኮም ይህን የገለጸው የ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የስራ አፈጻጸሙን አስመልክቶ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ነው። ተቋሙ በዚህ ጊዜ ውስጥ ያስገባው ገቢ፤ ከእቅዱ 98 በመቶውን ያሳካ መሆኑን የኩባንያው ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሪት ፍሬሕይወት ታምሩ ተናግረዋል።።

ገቢው ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር 26 በመቶ ዕድገት ያሳየ መሆኑንም ዋና ስራ አስፈጻሚዋ ገልጸዋል። ኢትዮ ቴሌኮም በ2015 የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ያገኘው ገቢ 33.8 ቢሊዮን ብር ሲሆን በወቅቱ ያስመዘገበው ትርፍ ደግሞ 8.18 ቢሊዮን ብር ነበር። ተቋሙ ዘንድሮ በግማሽ ዓመት ብቻ 11 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማግኘቱም ይፋ ተደርጉዋል።

 የ19ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሜየርሊግ ጨዋታ ነገ በሚደረጉ መርሃ ግብሮቾ ይጀምራል፡፡ አስቶንቪላ ከ ማንችስተር ዩናይትድ የሚያደርጉት መርሃ ግብር ከተጠባቂ ጨዋታወች መካከል የመጀመሪያዉ ነ...
25/12/2023


የ19ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሜየርሊግ ጨዋታ ነገ በሚደረጉ መርሃ ግብሮቾ ይጀምራል፡፡ አስቶንቪላ ከ ማንችስተር ዩናይትድ የሚያደርጉት መርሃ ግብር ከተጠባቂ ጨዋታወች መካከል የመጀመሪያዉ ነዉ፡፡

 የፋይናንስ ተቋማት አገልግሎቶቻቸውን በቴሌብር ለማቅረብ የሚስችል የዲጂታል ፋይናንስ ገበያ አገልግሎት ተጀመረ*******************,(ኢ ፕ ድ) ኢትዮ ቴሌኮም የፋይናንስ ተቋማት አገ...
22/12/2023


የፋይናንስ ተቋማት አገልግሎቶቻቸውን በቴሌብር ለማቅረብ የሚስችል የዲጂታል ፋይናንስ ገበያ አገልግሎት ተጀመረ
*******************,
(ኢ ፕ ድ)
ኢትዮ ቴሌኮም የፋይናንስ ተቋማት አገልግሎቶቻቸውን በቴሌብር ለደንበኞቻቸው ለማቅረብ የሚስችል የዲጂታል ፋይናንስ ገበያ እና የዲጂታል አክሲዮን ግዢና ሽያጭ አገልግሎቶችን በይፋ አስጀመረ።

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ ስለ አገልግሎቶቹ ማብራሪያ በሰጡበት በወቅት እንደገለፁት፤ አገልግሎቶቹ ሁሉም ባንኮች ኢንሹራንሶች እና ሌሎች የፋይናንስ ተቋማት አገልግሎታቸውን በቴሌ ብር መተግበሪያ በማስቀመጥ ለበርካታ ዜጎች ተደራሽ እንዲሆኑ ያስችላል።

ይህም ብሔራዊ ባንክ በ2025 በአገር ደረጃ የፋይናን አግልግሎትን 70 በመቶ ለማድረስ ያስቀመጠዉን ግብ ለማሳት እና ዲጅታል ፋይናንሲንግን ለማሳደግ ይረዳል ብለዋል።

በተጨማሪም ሁለተኛው የአክሲዮን አገልግሎቶችን ለመግዛትና ለመሸጥ የሚያስችል ሲሆን፤ በዚህም ህጋዊ የሆኑ ባለአክሲዮኖች አገልግሎታቸውን በማቅረብ ብስልክ ቢቻ ለበርካታ ዜጎች ተደራሽ ይሆናሉ ሲሉ ገልፀዋል።

 የ18ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሜርሊግ ጨዋታ ትላንት ሲደረግ  ክሪስታል ፓላስ ከብራይተን ያደረጉት ጨዋታ በአቻ ዉጤት ተጠናቋል፡፡  ዛሬም አንድ መርሃ ግብር አምስት ሰዓት ላይ ይደረጋል፡፡ት...
22/12/2023


የ18ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሜርሊግ ጨዋታ ትላንት ሲደረግ ክሪስታል ፓላስ ከብራይተን ያደረጉት ጨዋታ በአቻ ዉጤት ተጠናቋል፡፡ ዛሬም አንድ መርሃ ግብር አምስት ሰዓት ላይ ይደረጋል፡፡

ትላንት ምሽት አምስት ሰዓት ላይ ክሪስታል ፓላስ እና ብራይተን ያደረጉት የ18ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሜርሊግ ጨዋታ በአቻ ዉጤት ተጠናቋል፡፡
ክሪስታል ፓላስ ባሳለፍነዉ የዉድድር አመት ወደ ወራጅ ቀጠናዉ ላለመዉረድ ሲታገሉ መቆየተቻዉ ይታወሳል፡፡ በዘንድሮዉ የዉድድር አመትም የ76 አመቱን ሮይ ሀዲሰንን በዋና አሰልጣኝነት በድጋሜ ወደ ክለቡ በማምጣት ጥሩ የዉድድር አመትን ለማሳለፍ ቢሞክሩም እያሳለፉት ያለዉ፡የዉድድር አመት ግን እንዳሰቡት እየሆነላቸዉ አይደለም፡፡
በፕሪሜርሊጉ አስራ ስምንት ጨዋታቸዉን አድርገዉ አስራስምንት ነጥቦችን በመያዝ አስራአምስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡
ትላንት ያደረጉትን ጨዋታም በአቻ ዉጤት አጠናቀዋል፡፡ በተቃራኒዉ ያማረ እግር ኳስን የሚጫወቱት ብራይተኖች በምሽቱ የተሻለ የኳስ ቁጥጥር እና የጎል ማግባት ሙከራወችን ቢያደርጉም ክሪስታል ፓላስ ላይ ሙሉ ሶስት ነጠብ ይዘዉ መዉጣት አልቻሉም፡፡
በዚህ ጨዋታ ላይም ጆርዳን አዩ ለክሪስታል ፓላስ በመጀመሪያዉ የጭታ አጋማሽ ጎል ማስቆጠር ሲችል ደኒ ዉየሊቤክ ለብራይተን ከረፍት መልስ የአቻነት ጎል ማስቆጠር ችሏል፡፡

ዛሬም ምሽት አምስት ሰዓት ላይም አስቶን ቢላ ከሸፊልድ ዩናይትድ ጭታቸዉን በቪላ ፓርክ ያደርጋሉ፡፡
አስቶን ቪላወች በኡና ኤምሬ ስር ከወትሮዉ በተለየ ጥሩ የዉድድር አመትን እያሳለፉ ይገኛሉ፡፡ በተለይም በሜዳቸዉ የሚቀመሱ አይደለም፡፡ አርሰናል እና ማንችስተርሲቲ እንኳን በቪላ ፓርክ ሽንፈትን ቀምሰዉ ተመልሰዋል፡፡
አስቶን ቪላም ዛሬ ምሽት በፕሪሜርሊጉ መጨረሻ ደረጃ ላይ የተቀመጠዉን ሺፊልድ ዩናይትድን በሜደዉ የሚያስተናግድ ይሆናል፡፡ እናም የሚያሸንፍ ከሆነ ለጊዜዉም ቢሆን ፕሪሜርሊጉን በአንደኝነት የሚመሩ ይሆናል፡፡
በተቃራኒዉ ሸፊልድ ዩናይትዶች ከሜዳቸዉ ዉጭ እስካሁን ምንም ጨዋታ ማሸነፍ አልቻሉም ፡፡ እስካሁን ድረስ 17 ጨዋታወችን አድርገዉ ማሸነፍ የቻሉት ሁለት ጨዋታወችን ብቻ ነዉ፡፡
ታዲያ እነዚህ ሁለት ክለቦች ዛሬ ምሽት በቪላ ፓርክ ጨዋታቸዉን ያደርጋሉ፡፡

 በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር እና በኢሚግሬሽንና የዜግነት አገልግሎት መካከል የኢ-ፓስፖርት ሥርዓትን ከዲዛይን ጀምሮ ደህንነትን መሰረት ያደረገ የሲስተም ግንባታ ላይ በጋራ መስራ...
21/12/2023


በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር እና በኢሚግሬሽንና የዜግነት አገልግሎት መካከል የኢ-ፓስፖርት ሥርዓትን ከዲዛይን ጀምሮ ደህንነትን መሰረት ያደረገ የሲስተም ግንባታ ላይ በጋራ መስራት የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ።

ስምምነቱ የ24/7 የሳይበር ደህንነት ጥበቃ አገልግሎትን እንደሚያካትትም ተመላክቷል።

በስምምነቱ ላይ የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ሶካ ባስተላለፉት መልዕክት ኢመደአ የኢንፎርሜሽንና የኢንፎርሜሽን መሠረተ-ልማት ደህንነት መጠበቅ ኃላፊነቱና ተልእኮው መሆኑን ገልጸዋል።

በዚህም ለመንግስት ቁልፍ ተቋማትን የ24/7 የደህንነት ጥበቃ ከማድረግ ባሻገር ክልከላ ያለባቸውን ሶፍትዌሮችና ሀርድዌሮችን አበልጽጎ የማስታጠቅ ሥራን እየሠራ እንደሚገኝም አክለዋል፡፡

አቶ ሰለሞን አያይዘውም ዛሬ የተደረገው ሥምምነት የኢ-ፓስፖርት ሥርዓትን ከዲዛይን ጀምሮ ደህንነትን መሰረት ያደረገ የሲስተም ግንባታና የ24/7 የሳይበር ደህንነት ጥበቃ አገልግሎትን መስጠት የሚያስችል ነው ብለዋል።

በተጨማሪም የሳይበር ደህንነት ኦዲት፣ አገልግሎቱ ያሉበትን የሳይበር ደህንነት ሥጋትና የተጋለጭነት ክፍተቶችን የመለየትና የመድፈን ስራዎችን በመስራት ተቋሙ የጀመረዉን በቴክኖሎጂ የመዘመን እንቅስቃሴ የሚደግፍ መሆኑን ጠቁመዋል።

በመግባቢያ ስምምነቱ መሰረት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ለኢሚግሬሽንና የዜግነት አገልግሎት የቴክኒክ ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጸዋል።

የኢሚግሬሽንና የዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት በበኩላቸው ከኢመደአ ጋር በጋራ ለመስራት መስማማታቸው እንዳስደሰታቸዉ ገልጸዋል።

ተቋማቸው የሚሰጠውን አገልግሎት በማዘመን የኢ-ፓስፖርት አገልግሎት ለመስጠት እና ተቋሙ በባህሪው የሚይዛቸው መረጃዎች ሚስጥራዊነት እና ደህንነታቸው የተጠበቀ እንዲሆን ከኢመደአ ጋር መሥራት አማራጭ የሌለው ጉዳይ መሆኑን ጠቁመዋል።

ወደፊትም በርካታ ሥራዎችን በጋራና በትብብር እንደሚሰሩ ዋና ዳይሬክተሯ መግለጻቸውን ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

 ሊቨርፑል በካራባዉ ካፕ ጨዋታ  ውየስትሃምን በማሸነፍ  ወደ ግማሽ ፍፃሜዉ ማለፍ ችሏል፡፡ሊቨርፑል  በሩብ ፍፃሜ ጨዋታ በአንፊልድ ዉየስታሃምን ጋብዞ በሰፊ የጎል ልዩነት አሸንፏል፡፡ በጨዋታ...
21/12/2023


ሊቨርፑል በካራባዉ ካፕ ጨዋታ ውየስትሃምን በማሸነፍ ወደ ግማሽ ፍፃሜዉ ማለፍ ችሏል፡፡
ሊቨርፑል በሩብ ፍፃሜ ጨዋታ በአንፊልድ ዉየስታሃምን ጋብዞ በሰፊ የጎል ልዩነት አሸንፏል፡፡ በጨዋታዉ ሁሉም ነገር ተቆጣጥረዉ ማምሸት የቻሉት ሊቨርፑሎች መዶሻወቹ ላይ አምስት ጎሎችን አስቆጥረዋል፡፡
ባሳለፍነዉ እሁድ ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር ጨዋታቸዉን አድርገዉ 13 የጎል ሙከራወችን አድርገዉ ወደ ጎል መቀየር ግን ተስኗቸዉ ያመሹት ሊቨርፑሎች በትላንት ምሽቱ ጨዋታ ግን ሁሉን ነገር አርመዉ የገቡ ይመስላል፡፡
ሊቨርፑሎች ከተደጋጋሚ ጠንካራ ሙከራወች በኅላ ዶሚኒክ ሶቦዝላይ ከ25 ያርድ አካባቢ አክርሮ የመታት ኳስ ወደ ጎልነት ስትቀየር ወደ ግማሽ ፍፃሜዉ መግባታቸዉ ገና ጨዋታዉ ሳይጠናቀቅ ያስታዉቅ ነበር፡፡
ለሊቨርፑልም ኮርትስ ጆንስ ሁለት ጎሎችን ሲያስቆጥር ማህመድ ሳላህ እና ኮዲ ጋክፖ ሌሎች ጎሎችን አስቆጥራዋል፡፡
ኮርትስ ጆንስ በዉድድር አመቱ የመጀመሪያዉን ሁለት ጎሎች በምሽቱ ጨዋታ ማስቆጠር ችሏል፡፡
በዚህ ጨዋታ ላይም እንግሊዚያዉዩ ባለተስፍ ወጣት ተጫወች ኢሌይት ጨዋታዉን በቋሚነት ጀምሮ ድንቅነቱን ይበልጥ በትላንትናዉ ጨዋታ አሳይቷል፡፡ ለየረገን ክሎፕም ተጨማሪ ማስረጃወችን ይበልጣ ማሳየት ችሏል፡፡
ሊቨርፑል በሜዳዉ ዉየስትሃም ላይ አምስት ጎሎችን አስቆጥሮ ለ10ኛ ጊዜ ከፍ አድርጎ ለማንሳት ትልቅ መነሳሳት ላይ ይገኛል፡፡ ይህን ዋንጫ ለ9ኛ ጊዜ በማንሳተም የመጀመሪያዉ ክለብ ነዉ፡፡

የዲቭድ ሞይሱ ቡድን ውየስትሃም አሳዛኝ ምሽትን አሳልፈዋል፡፡ በዚህ ጨዋታ ላይም አምስት
ጎሎችን አስተናግደዉ አንድ ጎል በጆርዳን ጎል አማካኝነት አስቆጥረዉ ከዉድድሩ ተሳንብተዋል፡፡
በወልቭስ ላይ ባደረጉት አስገራሚ ድል ለሊቨርፑልም ቀላል ተጋጣሚ እንደማይሆኑ የተገመተ ቢሆንም ተከታታይ ኳሶችን በማግኘት ለተቃራኒ ቡድን ስጋት የሚሆኑበትን እድል ግን መፍጠር አልቻሉም፡፡
አሰልጣኝ ዲቪድ ሞይስ ከጭዋታዉ መጠናቀቅ በኅላ በሰጡት አስተያይትም አፈፃፅማችን በጣም ጥሩ ነበር፡፡ ነገር ግን ከመጀመሪያ ደቂቃ ጀምሮ የመተንፈስ ዕድል አላገኘንም፡፡ የተጫወትነዉ በጣም ፍጥነት የተሞላበት ጨዋታ ነበር በማለት አስተያይታቸዉን ሰጠዋል፡፡
ሊቨርፑል ፣ፉልሃም ፣ቼልሲ እና ሚድልስቦሮዉ ወደ ቀጣዩ ዙር ያለፉ ክለቦች ሲሆኑ ሊቨርፑል በግማሽ ፍፃሜዉ ጨዋታም በመለያ ምት ኤቨርተንን አሸንፎ ወደ ግማሽ ፍፃሜ ማለፍ የቻለዉን ፍልሃምን የሚያገኝ ይሆናል፡፡ ጨዋታዉም ጥር ስምንት የሚደረግ ይሆናል፡፡ ከሁለት ሳምንት በኅላም የፍፃሜዉ ጨዋታ ይደረጋል፡፡

 የአፍሪካ ሀገራት የኤሌክትሮኒክ አስተዳደርና የዲጂታላይዜሽን ምክክር መድረክ በሩሲያ እየተካሄደ ይገኛል****(ኢ ፕ ድ) በሩሲያ ሞስኮ እየተካሄደ በሚገኘው መድረክ የአፍሪካ ሀገራት ቴክኖሎጂ...
20/12/2023


የአፍሪካ ሀገራት የኤሌክትሮኒክ አስተዳደርና የዲጂታላይዜሽን ምክክር መድረክ በሩሲያ እየተካሄደ ይገኛል
****
(ኢ ፕ ድ)

በሩሲያ ሞስኮ እየተካሄደ በሚገኘው መድረክ የአፍሪካ ሀገራት ቴክኖሎጂን በመጠቀም በሀገራቸው የሚካሄደውን የኢኮኖሚ ስርዓት ለማዘመን የሄዱበትን የስኬት ጉዞና ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ ለሚደረጉ የቴክኖሎጂ ሽግግሮች ተሞክሮ ይቀርብበታል።

ኢትዮጵያን ወክለው በመድረኩ እየተሳተፉ የሚገኙት የአብርሆት ቤተ-መጽሐፍት ዋና ዳይሬክተር ውባየሁ ማሞ (ኢ/ር) የኢትዮጵያን የዲጂታል መታወቂያ አሰጣጥ፣ የኤሌክትሮኒክ ግብይቶችንና ኢትዮጵያ ዲጂታል ኢኮኖሚን ለመገንባት የምታደርገውን ጥረት በተሞክሮነት አቅርበዋል።

በጉባዔው የአፍሪካ ሀገራት ከሩሲያ የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ተሞክሮዎችን በመውሰድ አዳዲስ የቴክኖሎጂ አሰራሮችን ተግባራዊ ያደርጉበታል ተብሎ ይጠበቃል።

በመድረኩ 37 የአፍሪካ ሀገራት ተሳትፎ እያደረጉ መሆኑ ታውቋል።

 ትላንት በተደረገ የካራባዉ ካፕ ጨዋታ ቼልሴ ፤ፉልሃም እና ሚድልስቦሮዉ ወደ ግማሽ ፍፃሜ ማለፍቸዉን አረጋግጠዋል፡፡በካራባዉ ካፕ ሩብ ፍፃሜ ጨዋታ ትላንት  ሶስት መርሃ ግብሮች የተካሂዱ ሲሆ...
20/12/2023


ትላንት በተደረገ የካራባዉ ካፕ ጨዋታ ቼልሴ ፤ፉልሃም እና ሚድልስቦሮዉ ወደ ግማሽ ፍፃሜ ማለፍቸዉን አረጋግጠዋል፡፡
በካራባዉ ካፕ ሩብ ፍፃሜ ጨዋታ ትላንት ሶስት መርሃ ግብሮች የተካሂዱ ሲሆን ቼልሲ ፣ ፉልሃምና ሚድልስቦሮዉ ወደ ግማሽ ፍፃሜ ያለፉ ክለቦች መሆን ችለዋል፡፡
ከተጠባቂ መርሃ ግብሮች መካከል የነበረዉ የቼልሲ እና የኒዉካስትል ዩናይትድ ጨዋታም በመለያ ምት ቼልሲወች አሸንፈዉ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፍ ችለዋል፡፡
ኒዉካስትል ዩናይትድች በዚህ ጨዋታ ላይ ዊልሰን ቀድሞ ባስቆጠራት ጎል ቀድመዉ መሪ የሆኑበትን እድል ቢያገኙም ቼልሲወች ደቂቃወች ሊጠናቀቁ በሰከንዶች ልዩነት ጎል አስቆጥረዉ ወደ ጭማሪ ደቂቃ ያለፈበትን እድል ማስተካከል ችለዋል፡፡ ሙሉ የጭዋታዉ ጊዜ በአንድ አቻ የተጠናቀቀዉ ይህ ጨዋታም በመጨረሻም ቼልሲወች በመለያ ምት አሸንፈዉ ግማሽ ፍፃሜዉን ተቀላቅለዋል፡፡
ሌላኛዉ መርሃግብር የኢቨርተን እና የፉልሃም ጨዋታ በተመሳሳይ በመለያ ምት የተጠናቀቀ መርሃ ግብር ነበር፡፡
ኤቨርተኖች የፍይናሻል ፊር ፕላይ ህግን በመጣሳቸዉ አስር ነጥብ ከተቀነሰባቸዉ በኅላ ይበልጥ ጠንካራ ሆነዉ ለመቅረብ እየታገሉ ይገኛሉ ፡፡ በምሽቱ ጨዋታም ማይክል ኪን በራሱ መረብ ላይ ከረፍት በፊት ጎል አስቆጥሮ ፍልሃሞችን መሪ ያደረገ ቢሆንም ቤቶ በመጨረሻም ለኢቨርተን ጎል አስቆጥሮ ወደ ጭማሪ ደቂቃ ማምራት ችለዉ ነበር ፡፡ ጭማሪ ደቂቃወች ጨርሰዉ ወደ ፔናሊቲ ያመሩት ሁለቱ ክለቦች ኦናና እና ጎዩ የኢቨርተንን ሁለት ፔናሊቲወችን አምክነዉ ፍልሃሞች ወደ ግማሽ ፍፃሜዉ ሲያልፉ በተቃራኒዉ ኢቨርተኖች ወደ ግማሽ ፍፃሜዉ ሳያልፉ ቀርተዋል፡፡
ሜድልስቦሮዉ እና ፓርት ቫሊ ያደረጉት ጨዋታ በሚድልስቦሮዉ 3-0 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡

ዛሬም በካራባዉ ካፕ ሩብ ፋፃሜ ጨዋታ አንድ ቀሪ መርሃ ግብር ይደረጋል፡፡ በዚህ ጨዋታም ሊቨርፑል ዊስትሃምን በአንፊልድ ይጋብዛል፡፡ ሊቨርፑል በዘንድሮዉ የዉድድር አመት ወደ ሻንፒወን ሽፑ የተወረወረዉን ሊስተርሲቲን አሸንፎ ወደ ሩብ ፍፃሜዉ ማለፉ ይታወሳል፡፡ የሊግ ዋንጫዉን ያነሳል ተብሎ ከሚገመቱ ክለቦች መካከል የየርገን ክሎፕ ቡድን የመጀመሪያዉ ነዉ፡፡ በተቃራኒዉ ውስትሃም ዩናይትድ የሊቨር ፑል ቀላል ተጋጣሚ እንደማይሆን ይጠበቃል ፡፡ ጠንካራዉን አርሰናልን በሰፊ የጎል ልዩነት አሸንፎ ወደ ሩብ ፍፃሜዉ ማለፉ ይታወሳል፡፡ ታዲያ ሁለቱ ክለቦች ዛሬ ምሽት አምስት ሰዓት ላይ በአንፊልድ ወደ ቀጣዩ ዙር ለማለፍ የሚፍለሙ ይሆናል፡፡

 የቤቲንግ ጨዋታ እያደረሰ ያለውን ጫና ለመቀነስ እየተሰራ ነው- ከ3 ሺህ በላይ በሚሆኑ የቤቲንግ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወስዷል**************(ኢ.ፕ.ድ)ቤቲንግ በመዲናዋ ማህበራዊ፣ ኢኮ...
19/12/2023


የቤቲንግ ጨዋታ እያደረሰ ያለውን ጫና ለመቀነስ እየተሰራ ነው
- ከ3 ሺህ በላይ በሚሆኑ የቤቲንግ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወስዷል
**************
(ኢ.ፕ.ድ)
ቤቲንግ በመዲናዋ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፓለቲካዊ ጉዳዮች ላይ እያደረሰ ያለውን ጫና ለመከላከል እየተሰራ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር ሰላምና ፀጥታ ቢሮ አስታወቀ።

የቤቲንግን ጫና ለመቆጣጠር እየተሰራ ባለው ስራም ከ3 ሺህ በላይ የቤቲንግ ቤቶች ላይ እርምጃ መውሰዱን ቢሮው ተናግሯል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ሀላፊ ወይዘሮ ሊዲያ ግርማ በዛሬው ለዕት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ ቤቲንግ በማህብረሰቡ ላይ እያደረሰ ያለውን ሁለተናዊ ጫና ለመከላከል በትኩረት እየተሰራ ነው።በተሰራው ስራ 3ሺህ 241 የቤቲንግ ማጫወቻ ቤቶች ላይ እርምጃ ተሰዷል።

ቤንቲግ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው እንዳይገኙ በማድረግ ትውልድን እየገደለ ነው፤ በማህበራዊና በኢኮኖሚ ላይ ጫና እያሳደረ ይገኛል ብለዋል።

ቤቲንግ በማህብረሰቡ እያደረሰ ያለውን ጉዳት ለመቆጣጠርና እንቅስቃሴውን ለመገደብ እርምጃ እተወሠደ ሲሆን የብሔራዊ ሎተሪ ያወጠውን ህግ ተላልፈው ከ21 እድሜ በታች ሲያጫወቱ፤ ከትምህርት ቤቶች 200 ራዲየስ ባልራቁና ከተፈቀደላቸው ውጭ የወንጀል ምሽግ በሆኑ 3 ሺህ 241 ቤቶች ላይ የማሸግ እምጃ ተወስዷል ሲሉ አብራርተዋል።

ብሔራዊ ሎተሪ ያወጣውን ህግ እየተላለፉ ያሉ ቤቲንግ ቤቶችን የመለየት ሥራ በመስራት እርምጃ የመውሰድ ሥራ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

ቤቲንግ በማህብረሰቡ እያደረሰውን ጫና ለመቀነስ እየተሠራ ያለው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አመላክተዋል።

 ማንችስተር ሲቲ በአለም የክለቦች ዋንጫ   የጃፓኑን ክለቦ ኦራዋ ሪድስን በግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ይገጥማል፡፡  ማንችስተር ሲቲ በአዉሮፓ መድረክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሻንፒወን መሆናቸዉን ተከትሎ  በ...
19/12/2023


ማንችስተር ሲቲ በአለም የክለቦች ዋንጫ የጃፓኑን ክለቦ ኦራዋ ሪድስን በግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ይገጥማል፡፡ ማንችስተር ሲቲ በአዉሮፓ መድረክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሻንፒወን መሆናቸዉን ተከትሎ በዚህ መድረክ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ይሳተፋሉ፡፡
ምሽት 3:00 ላይም ወደ ጃፓን አቅንተዉ በኪንግ አብደላህ ስቴድየም ለመፋለም ዝግጅታቸዉን አጠናቀዋል፡፡ የሁለቱ ክለቦች አሸናፊም በፍፃሜ ጨዋታ የብራዚሉን ክለብ ፍሎሚኔንስን የሚያገኙ ይሆናል፡፡

 ዛሬ ምሽት 4:45 ጀምሮ  የእንግሊዝ ካራባዉ ካፕ የዕሩብ ፍፃሜ ጨዋታወች ይደረጋሉ፡፡ ከነዚህም መካከል ኤቨርተን ከፉልሃም እንዲሁም ፖርት ቮሊ ከሜድልስቦሮዉ ጨዋታቸዉን ያደርጋሉ፡፡የሳን ዳ...
19/12/2023


ዛሬ ምሽት 4:45 ጀምሮ የእንግሊዝ ካራባዉ ካፕ የዕሩብ ፍፃሜ ጨዋታወች ይደረጋሉ፡፡ ከነዚህም መካከል ኤቨርተን ከፉልሃም እንዲሁም ፖርት ቮሊ ከሜድልስቦሮዉ ጨዋታቸዉን ያደርጋሉ፡፡
የሳን ዳይሽ ቡድን ኢቨርተን በፕሪሜርሊጉ ተከታታይ ጨዋታወችን በማሸነፍ ምርጥ አቋማቸዉ ላይ ይገኛሉ፡፡ በካራባዉ ካፕ ጨዋታም አስቶንቪላን እና በርንሊን አሸንፈዉ አስከ ዕሩብ ፍፃሜዉ መጓዝ ችለዋል፡፡ በተቃራኒዉ ፍልሃሞች ያደረጓቸዉን ተከታታይ ሁለት የፕሪሜርሊግ ጨዋታወች በሰፊ የጎል ልዩነት አሸንፈዋል፡፡ በሁለት የፕሪሜር ሊግ ጨዋታ ብቻ 10 ጎሎችን የተቃራኒ መረብ ላይ ማሳረፍ ችለዋል፡፡ ታዲያ ሁለቱ ክለቦች ዛሬ ምሽት በጉዲሰን ፓርክ ጨዋታቸዉን ያደርጋሉ፡፡
በተመሳሳይ ሰዓት ሁለቱ የሻንፒወስ ሽፕ ክለቦች ፓርት ቮሊ እና ሜዲሊስቦሮዉ በቫሊ ፓርክ ወደ ግማሽ ፍፃሜዉ ለማለፍ ጨዋታቸዉን ያደርጋሉ፡፡
ቼልሲ ከኒዉካስትል የሚያደርጉት ጨዋታም ከተጠባቂ መርሃግብሮች መካከል የመጀመሪያዉ ነዉ፡፡ኒዉካስትል ዩናይትድ በፕሪሜርሊጉ ጠንካራ ተፎካካሪ መሆኑ አይዘነጋም፡፡ በሻንፒወስ ሊጉም ቢሆን ወደ 16 ለማለፍ ጠንካራ ፍክክርን አድርገዉ በመጨረሻም ከዉድድሩ ውጭ መሆናቸዉ ይታወሳል፡፡ በካራባዉ ካፕ ጨዋታም ማንችስተር ዩናይትድን አሸንፈዉ ወደ እሩብ ፍፃሜ ማለፍ ችለዉ ነበር፡፡ በተቀራኒዉ ቼልሲ በፓቼቲኒወ ስር በሁሉም ዉድድሮች የቡድኑን ዉህደት ለማግኘት ሲቸገር ይስተዋላል፡፡ በፕሪሜሪሊጉም ደካማ እንቅስቃሴን እያደረጉ ይገኛሉ፡፡
ታዲያ እነዚህ ሁለቱ ክለቦች ምሽት 5:00 ላይ ጨዋታቸዉን በስታንፎርድ ብሪጅ ያደርጋሉ፡፡

 ቡልቡላ የተቀናጀ አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክ ለ100 ሺህ ዜጎች የሥራ ዕድል ይፈጥራል*************(ኢ.ፕ.ድ)ቡልቡላ የተቀናጀ አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክ በሙሉ አቅሙ ወደ ሥራ ሲገባ 100 ...
18/12/2023


ቡልቡላ የተቀናጀ አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክ ለ100 ሺህ ዜጎች የሥራ ዕድል ይፈጥራል
*************
(ኢ.ፕ.ድ)
ቡልቡላ የተቀናጀ አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክ በሙሉ አቅሙ ወደ ሥራ ሲገባ 100 ሺህ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ እድል እንደሚፈጥር የኦሮሚያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን አስታወቀ፡፡

የኦሮሚያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ሥራ አስኪያጅ ሰናይት መብሬ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ኦሮሚያ ክልል ውስጥ 80 በመቶ የሆነውን ኢኮኖሚ በግብርና የሚሸፈን ነው፡፡

ሆኖም የሚመረተው ምርት በባህላዊ መንገድ ተመርቶ እና ምንም እሴት ሳይጨመርበት ለሀገር ውስጥ እና ለውጭ ገበያ እየቀረበ ይገኛል፡፡

እዚህ ላይ ሥር ነቀል ለውጥ ለማምጣት ኢንዱስትሪ ፓርኮች ሚናቸው ትልቅ ነው ያሉት ሥራ አስኪያጇ፤ ቡልቡላ የተቀናጀ አግሮ ኢንዱስትሪ የገበሬውን ምርት በቀጥታ ወደ ተጠቃሚው ከማድረስ ባለፈ እሴት ጨምሮ በማምረት ለሀገር ውስጥና ለውጭ ገበያ ያቀርባል ብለዋል፡፡

ይህም ከውጭ የሚገቡ ምርቶች በሀገር ውስጥ ከመተካት ባለፈ የውጭ ምንዛሬን ለማምጣት ትልቅ ሚና እንደሚኖረው አብራርተዋል፡፡

እንደ ወይዘሮ ሰናይት ገለፃ፤ በአሁኑ ጊዜ 30 የሚሆኑ ባለሀብቶች ኢንደስትሪ ፓርኩ ውስጥ ለመስራት ውል ገብተዋል፡፡ አንድ የማር ማቀነባበሪያ ፋብሪካም ሥራ ጀምሯል፡፡

በፓርኩ ውል የገቡት ባለሀብቶች ሁሉም ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን የጠቀሱት ኃላፊዋ፤ የሚጠቀሙት ግብዓት በሀገር ውስጥ የሚገኝ በመሆኑ በፓርኩ ውስጥ መሥራት ለሚፈልግ የሀገር ውስጥ ባለሀብት ቅድሚያ የሚሰጥበት ሁኔታ እንዳለ አብራርተዋል፡፡

የቡልቡላ የተቀናጀ አግሮ ኢንዱስትሪ ሥራ አስኪያጅ አደም አብዱራህማን በበኩላቸው፤ ኢንዱስትሪው የግብርና ምርቶችን እያቀነባበረና እሴትን እየጨመረ የሚያመርት መሆኑን ጠቅሰው፤ በዚህም 90 በመቶ የሚሆነው ምርት ወደ ውጭ ይልካል ብለዋል፡፡

ኢንዱስትሪው አትክልትና ፍራፍሬ፣ ቡናና ቅመማ ቅመም፣ ጥራጥሬዎች፣ ሥጋ፣ ሰብል እና ማር የሚያቀነባብር ሲሆን ፓርኩ በሙሉ አቅሙ ወደ ሥራ ሲገባ 100 ትላልቅ ባለሀብቶችን በመያዝ 100 ሺህ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ እድል መፍጠር ይችላል ብለዋል፡፡

እስካሁን ተዋውለው በገቡ ባለሀብቶችም 11 ሺህ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ እድል መፈጠሩን አብራርተዋል፡፡

ፓርኩ አስፈላጊ መሠረተ ልማቶች ሁሉ የተሟላለት መሆኑን የጠቀሱት ኃላፊው፤ ባለሀብቶች በፓርኩ ማልማት እንዲችሉ የኦሮሚያ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የተለያዩ ሥራዎች እየሠራ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

 የ17ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሜርሊግ ጨዋታ ትላንት ምሽት ሲጠናቀቅ  አርሰናል  መሪነቱን ከሊቨርፑል ተረክቧል፡፡ አርሰናል ፈታኙን የሮበርቶ ዲዘርቢን ቡድን ብራይተን ሆቭ አልቢወንን በሜደዉ...
18/12/2023


የ17ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሜርሊግ ጨዋታ ትላንት ምሽት ሲጠናቀቅ አርሰናል መሪነቱን ከሊቨርፑል ተረክቧል፡፡
አርሰናል ፈታኙን የሮበርቶ ዲዘርቢን ቡድን ብራይተን ሆቭ አልቢወንን በሜደዉ ኢምሬትስ ጋብዞ ማሸነፍ ችሏል፡፡ የተሻለ የኳስ ቁጥጥር እና የጎል ሙከራወችን ማድረግ የቻለዉ አርሰናል በመጨረሻም አሸነፎ የፕሪሜር ሊጉን የደረጃ ሰንጠረዥ በአንድ ነጥብ ከተከታዩ ከፍ በማለት መቆናጠጥ ችለዋል፡፡
ጠንካራ ፈተና በአርሰናል ላይ ማድረግ ተስኖት ያመሸዉ ብራይተን የ2-0 ሽንፈትን አስተናግዷል፡፡ ብራይተን እንደ ማካልስተር ፣ ካይሴዶ አይነት ኮከቦቹን በዘንድሮዉ የዉድድር አመት ለሌሎች ክለቦች አሳልፎ መስጠቱ ደካማ የዉድድር አመትን ከወትሮዉ በተለየ ሊያሳልፍ እንደሚችል ይታሰባል፡፡
ያለፋት አምስት ጨዋታወችን አድርጎ ሁለት አሸንፎ ፣ሁለት ተሸንፎ ፤አንድ አቻ በመዉጣት 26 ነጥቦችን በመሰብሰብ ዘጠነኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡
በተመሳሳይ ሰዓት የተደረገዉ የብሬንትፎርድ እና የአስቶንቪላ ጨዋታ ፤ በአስቶን ቫላ አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡
በዚህ ጨዋታ ላይ ብሬንትፎርዶች ጥሩ ጨዋታን ተጫዉተዉ ከአስቶን ቪላ ላይ ነጥብ ይዘዉ ለመዉጣት ቢሞክሩም የኡና ኤምሬ ቡድን ይህን ሊፈቅዱላቸዉ አልቻሉም ፡፡
ብሬንትፎርድ በሊውስ ፖተር ጎል ከረፍት በፊት ጎል አስቆጥረዉ መሪ የሆኑበትን እድል ቢያገኙም "ቤን ሚ "በቀጥታ ቀይ ካርድ ከሜዳ መዉጣቱ ለሽንፈታቸዉ በቂ ምክንያት ነበር፡፡ አስቶን ቪላ አሊክስ ሞረኒወ እና ኦሊ ዋትኪንስ 77 እና 85ኛዉ ደቂቃ ላይ ጎል አስቆጥረዉ ከሊቨር ፑል እኩል 38 ነጥቦችን ሰብስበዉ ደረጃቸዉን አጠናክረዋል፡፡
አስቶንቪላዎች እንደ ቶተንሃም ፤ ማንችስተር ሲቲ እና አርሰናል አይነት ክለቦችን በማሸነፍ ትክክለኛ የፕሪሜርሊግ ተፎካካሪ መሆናቸዉን እያሳዩ ይገኛሉ፡፡
ከተጠባቂ መርሃ ግብሮች መካከል የነበረዉ የሊቨር ፑል እና የማንችስተር ዩናይትድ ጨዋታ ያለምንም ግብ በአቻ ዉጤት ተጠናቋል፡፡
ሁለቱን ቡድኖች ከአንድ መቶ አመታት በላይ የታሪክ ተቀናቃኞች ናቸዉ፡፡ ማንችስተር ዩናይትድ በአለፈዉ የዉድድር አመት ከግማሽ ደርዘን ጎል በላይ በአንድ ጨዋታ በአንፊልድ አስተናግደዉ መመለሳቸዉ ይታወሳል፡፡

ሊቨርፑሎች በትላንትናዉ ጨዋታ የማሸነፍ ቅድመ ግምት የተሰጣቸዉ ቢሆንም የኤሪክ ቴን ሃግ ቡድን ይህን ዕድል እንዲያሳኩ አልፈቀዱላቸዉም፡፡
ሊቨርፑሎች በዚህ ጨዋታ ላይ የተሻለ የኳስ ቁጥጥር እና የተሳኩ ጎል የማግባት ሙከራ ቢያገኙም ኳስና መረብን ማገናኘት አልቻሉም፡፡
የሊቨርፑል የማሃል ተከላካይ ቨርጅል ቫንዳይክ ዛሬ ጨዋታዉን ለማሸነፍ የገባዉ አንድ ቡድን ብቻ ነበር ፡፡ ነገር ግን ይህ አልተሳካም በማለት አስተያይቱን ሰጥቷል፡፡
ከ17ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሜርሊግ ጨዋታ መጠናቀቅ በኅላ አርሰናል በ39 ነጥብ ፕሪሜርሊጉን መምራት ሲችል ሊቨር ፑል እና አስቶንቪላ 38 ነጥቦችን በመያዝ ተከታዮችን ደረጃ ይዘዋል፡፡

 ኢትዮ ቴሌኮምና የሥራ ክህሎት ሚኒስቴር  በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ።የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፍጻሚ ፍሬህይውት ታምሩና የሥራ ክህሎት ሚኒስቴር       ሚኒስትር ...
15/12/2023


ኢትዮ ቴሌኮምና የሥራ ክህሎት ሚኒስቴር በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ።
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፍጻሚ ፍሬህይውት ታምሩና የሥራ ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፍሪያት ካሚል ሁለቱ ተቋማት በጋራ አብረው መስራት በሚያስችላቸው ዙሪያ ተፈራረሙ። በጋራ ትብብር ፊርማ ስነ፟ ስራዓቱ ወቅት የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፍጻሚ ፍሬህይውት ታምሩ በስጡት ማብራሪያ ወጣቶች ያመረቶቸውን ምርቶች በቀላሉ በኢ- ኮሜርስ አማካኝነት ወደ ገበያ ማውጣት እንዲችሉ የሚያስችል ስምምነት መሆኑን ገልጸዋል።

 የ17ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሜር ሊግ ጨዋታ  ኖቲንግሃም ፎረስት እና ቶተንሃምን የሚያደርጉት ጨዋታ ብቸኛዉ የዛሬ መርሃ ግብር ነዉ፡፡የ17ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሜር ሊግ ጨዋታ ዛሬ ማታ...
15/12/2023


የ17ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሜር ሊግ ጨዋታ ኖቲንግሃም ፎረስት እና ቶተንሃምን የሚያደርጉት ጨዋታ ብቸኛዉ የዛሬ መርሃ ግብር ነዉ፡፡
የ17ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሜር ሊግ ጨዋታ ዛሬ ማታ 5:00 ላይ በሲቲ ግራዉንድ ስቴድየም ኖቲንግሃም ፎረስት እና ቶተንሃምን ያገናኛል፡፡
የ1980 እና የ1979 የአዉሮፓ ሻንፒወስ ሊግ ሻንፒወኖች ኒቲንግሃም ፎረስት ለብዙ አመታት ወረጅ ቀጠናዉ ላይ ሲዳክሩ ቆይተዉ ከአንድ አመት በፊት ወደ ሊጉ ማደጋቸዉ ይታወሳል፡፡ ታዲያ ባደጉበት አመትም ተመልሰዉ ላለመዉረድ ሲታትሩ ከቆዩ በኃላ በመጨረሻም ከወረጅ ቀጠናዉ መትረፍቸዉ ይታወሳል፡፡
በዘንድሮዉ የዉድድር አመትም ካለፈዉ አመት በተሻለ አቋም በስቴቭ ኩፐር ስር እያሳዩ ይገኛሉ፡፡
ኒቲንግሃም ፎረስት ያለፈትን አምስት የፕሪሜር ሊግ ጨዋታወችን ሁሉንም ማሸነፍ አልቻለም፡፡ አራት ተሸንፎ አንድ ጨዋተ በአቻ ዉጤት አጠናቋል፡፡
በተቃራኒዉ ቶተንሃም ሆትስፐር በዘንድሮዉ የዉድድር አመት በፓስቴኮጉሉ ስር የተሻለ የፕሪሜር ሊግ አመትን እያሳለፈ ይገኛል፡፡

ቶተንሃም ሆትስፐር እንደ ማዉሪስዮ ፖቸቴንዮ ፣ ጆዜ ሞሪኒዉ ፣ ኑኖ እስፒሪቶ ሳንቶስ አይነት አሰልጣኞችን በተለያዩ ጊዚያት ወደ ክለቡ ቢያመጣም ዋንጫን ለማግኘት ግን አይና አፍር ሲሆን ይስተዋላል፡፡ ዋንጫን ወደ ካዘነዉ ካስገባ ዘመናትን አስቆጥራል፡፡
በዚህ የዉድድር አመትም በፕሪሜር ሊጉ ጅማሮ ጥሩ እንቅስቃሴን ማድረግ ቢችሉም እንደ ማዲሰን ፣ ቫንድ ቪን እና ፒሪሲች አይነት ተጫዋቾችን በጉዳት ምክንያት ማጣቱ ተደጋጋሚ ሽንፈቶችን እንዲያስተናግድ ምክንያት እንደሆነዉ ይነገራል፡፡
ቶተንሃም በአስራ ስድስተኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሜር ሊግ ጨዋታ የፕሪሜርሊጉ ተፎካካሪ ቡድኖች መካከል የሆነዉን ኒዉ ካስትል ዩናይትድን በሰፊ የጎል ልዩነት አሽንፎ ኖቲንግሃም ፎረስትን ከሜዳዉ ዉጭ አቅንቶ የሚገጥም ይሆናል፡፡
ያለፉትን አምስት የፕሪሜርሊግ ጨዋታወችንም ሶስቱን ተሸንፎ አንድ አቻ ወጥቶ አንድ አቻ ወጥቶ ከመሪዉ ሊቨር ፑል በ 7 ነጥቦች እርቆ 39 ነጥቦችን በመያዝ አምስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡
ሁለቱ ክለቦች ምሽት አምስት ሰዓት ዘ ሲቲ ግራዉንድ ስቴድየም የሚፍለሙ ይሆናል፡፡

13/12/2023

መልካም የገና በዓል . . . . . 2016 ዓ.ም ለ ገና በዓል አብራቹን መስራት ለምትፍልጉ. . . https://youtu.be/VXOeQQpNifs

 ትላንት በተደረገ የአዉሮፓ ሻንፒወስ ሊግ ጨዋታ ማንችስተር ዩናይትድ ከአዉሮፓ መድረክ ዉጭ ሆናል፡፡ ሌሎች የሻንፒወስ ሊግ ጨዋታወችም ተካሂደዋል፡፡
13/12/2023


ትላንት በተደረገ የአዉሮፓ ሻንፒወስ ሊግ ጨዋታ ማንችስተር ዩናይትድ ከአዉሮፓ መድረክ ዉጭ ሆናል፡፡ ሌሎች የሻንፒወስ ሊግ ጨዋታወችም ተካሂደዋል፡፡

 አፍሪካ በአንድ የመገበያያ ገንዘብ ለመጠቀም ልትመክር ነውአዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 2፣ 2016  የአፍሪካ ሀገራት በአንድ የመገበያያ ገንዘብ መጠቀም በሚያስችላቸው ሥርዓት ላይ ሊመክሩ መሆኑ ተ...
13/12/2023


አፍሪካ በአንድ የመገበያያ ገንዘብ ለመጠቀም ልትመክር ነው

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 2፣ 2016 የአፍሪካ ሀገራት በአንድ የመገበያያ ገንዘብ መጠቀም በሚያስችላቸው ሥርዓት ላይ ሊመክሩ መሆኑ ተገለጸ፡፡ የሀገራቱ ምክክር የአፍሪካን የገንዘብ ኅብረት በፍጥነት ዕውን ለማድረግ እንደሚያስችል የአፍሪካ ኅብረት መረጃ አመላክቷል፡፡ የሥርዓቱ ዕውን መሆን የአፍሪካን ማዕከላዊ ባንክ ፣ የአፍሪካን ኢንቨስትመንት ባንክ እና የአፍሪካን የገንዘብ ፈንድ ለማቋቋም ያስችላል ተብሏል፡፡

 የአዉሮፓ ሻንፒወስ ሊግ የመጨረሻ የምድብ ጨዋታ ዛሬ ምሽት  ይደረጋል፡፡ በዚህም ጨዋታ 2:45 በምድብ ሁለት የሚገኙት አርሰናል ከፒኤስቪ እንዲሁም  ሌንስ ከሲቢያ በሚያደረጉት ጨዋታ ይጀመራ...
12/12/2023


የአዉሮፓ ሻንፒወስ ሊግ የመጨረሻ የምድብ ጨዋታ ዛሬ ምሽት ይደረጋል፡፡ በዚህም ጨዋታ 2:45 በምድብ ሁለት የሚገኙት አርሰናል ከፒኤስቪ እንዲሁም ሌንስ ከሲቢያ በሚያደረጉት ጨዋታ ይጀመራል፡፡
በአዉሮፓ ሻንፒወስ ሊግ የመጨረሻ ዙር ጨዋታ ዛሬ ምሽት ሲደረጉ አርሰናል ከፒኤስቪ 2:45 ላይ በሚያደርጉት ጨዋታ ይጀመራል፡፡
አርሰናል ቀድሞ ከምድቡ ማለፉን ቢያረጋግጥም የኒዘርላንዱን ክለብ የሚገጥም ይሆናል፡፡ ፒኤስቪም የሁለተኛ ደረጃዉን ለማጠናከር በፒሊፕስ ስቲዲየም የእንግሊዙን ክለብ የሚያስተናግድ ይሆናል፡፡ የሌንስ እና የሲቢያ ጨዋታም በተመሳሳይ ሰዓት ይደረጋል፡፡
የማንችስተር ዩናይትድ እና የባየርንሙኒክ ጨዋታ ከምሽቱ ተጠባቂ የሻንፒወስ ሊግ መርሃ ግብሮች መካከል የመጀመሪያዉ ነዉ፡፡
ባየርንሙኒክ ምንም እንኳን ከምድቡ ማለፉን ቀድሞ ቢያረጋግጥም በሻንፒወስ ሊጉ በኮፓሃገን አቻ መዉጣቱ እና በቦንደስ ሊጋዉ ከኢንተርፍራንክ ኢፈርት ጋር በነበራቸዉ ጨዋታ የ5-1 ሽንፈትን ማስተናገዱ የማንችስተር ዩናይትድ ቀላል ተጋጣሚ እንደማይሆን ይጠበቃል፡፡
በተቃራኒዉ ማንችስተር ዩናይትድ ወደ ጥሎ ማለፉ የሚያልፍበት መንገድ ምንም እንኳን ጠባብ ቢሆንም ባየርን ሙኒክን ማሸነፍ ግን ግድ ይሆንበታል፡፡ የማያሸንፋ ከሆነ 16 ውስጥ ሳይገባ የሚሰናበት ይሆናል፡፡
ማንችስተር ዩናይትድች የማርከስ ራሽፎርድ እና የአንቶኒ ማርሻያልን ግልጋሎት በህመም ምክንያት አያገኙም ፡፡
አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሃግ ቡድኑ እየተሰራ እንደሆነ እና በቅርቡ ለዉጦችን እንደሚኖሩ ደጋግመዉ ቢናገሩም በሁሉም ዉድድሮች ለዉጦችን ለማግኘት ሲቸገሩ ይስተዋላል፡፡
በምሽቱ ጨዋታም በአዉሮፓ መድረክ ለመቆየት የቻሉትን ሁሉ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል፡፡
በተመሳሳይ ምድብ ላይ የሚገኙት ጋላታሳራይ ከፖንሃገን የሁለትኝነት ደረጃቸዉን ለማግኘት በፓርከን ሲቲድየም የሚፍለሙ ይሆናል፡፡
ሌሎች የምሽት የሻንፐመወስ ሊግ ጨዋታወች ይካሂዳሉ ፡፡ እስካሁን ድረስ በምድቡ ምንም ሽንፈት ያላስተናገደዉ ሪያል ማድሪድ ወደ ጀርመን አቅንቶ ዩኔን በርሊን ጋር ጨዋታዉን ያደርጋል፡፡
ሌሎች ጨዋታወችም ቀጥለዉ ሲካሄዱ
ናፖሊ ከስፓርቲንግ ብራጋ
ሳልዝበርግ ከ በነፊካ
ኢንተርሚላን ከ ሪያልሶሲሳይድ አምስት ሰዓት ላይ የሚደረጉ ጨዋታወች ናቸዉ፡፡

 አለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ወይም አይ ኤም ኤፍ ሀብታም የአፍሪካ ሀገራት ዝርዝርን ይፋ አደረገ።ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይ ኤም ኤፍ) በአሁኑ ወቅት ከአፍሪካ ሀገራት መካከል ሀብታም...
12/12/2023


አለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ወይም አይ ኤም ኤፍ ሀብታም የአፍሪካ ሀገራት ዝርዝርን ይፋ አደረገ።

ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይ ኤም ኤፍ) በአሁኑ ወቅት ከአፍሪካ ሀገራት መካከል ሀብታም የሆኑትን ዝርዝር አስነብቧል፡፡
በተለያዩ ተለዋዋጭ የኢኮኖሚ መመዘኛዎች ይህ ደረጃ ሊለወጥ እንደሚችል በዘገባው ተዳሷል፡፡
ተቋሙ ባወጣው ደረጃ በኢኮኖሚዋ በቀዳሚነት የምትጠቀሰው ከ200 ሚሊየን በላይ የህዝብ ብዛት ያላት ምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ናይጄሪያ ናት፡፡
ናይጄሪያ በፈረንጆቹ 2022 አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርቷ ከ450 ቢሊየን ዶላር ሲሆን ፥ በዚህ አያያዟ ረዘም ላለ ጊዜ የአፍሪካ የሀብት ቁንጮ ሀገር ሆና መቆየቷ አይቀርም ሲል አይ ኤም ኤፍ ገምቷል፡፡
በፈረንጆቹ 2028 አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርቷ ከ900 ቢሊየን ዶላር እንደሚሆን ድርጅቱ ግምቱን ያስቀመጠ ሲሆን ፥ ናይጄሪያ በነዳጅና በጋዝ ምርቷ ትታወቃለች፡፡
በቀጣይም ሀብታሟ ሀገር ደቡብ አፍሪካ ሆና ተቀምጣለች፡፡ ደቡብ አፍሪካ በማዕድን ማውጣት ፣ ግብርና እና አገልግሎቷ ትጠቀሳለች፡፡
ግብጽ ፣ አልጄሪያ፣ ሞሮኮ፣ አንጎላ፣ ኬኒያ ጋና እና ታንዛኒያ ከሦሥት እከ ዘጠኝ ያሉ ደረጃዎች ላይ ተቀምጠዋል፡፡
ኢትዮጵያ በአይ ኤም ኤፍ ሪፖርት መሰረት ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት እያስመዘገበች እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን ፥ በዚህም በ10ኛ ደረጃ ላይ መቀመጧም ነው የተገለጸው፡፡
ይህም ኢትዮጵያ የፈጣን እድገቷ ምክንያት በዋነኝነት ግብርና፣ ማኑፋክቸሪንግ እና መሰረተ ልማት እንደሆነ ተቋሙ አሳውቋል፡፡

 አዲስ አበባ፣ ሕዳር 28 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኤሎን መስክ ኩባንያ ከሆኑት አንዱ ‘ቴስላ አውቶሞቲቭ’ ቴስላ ሳይበር ትራክ የተሠኘ በቅርፅም ሆነ በዓይነት የተለየ የኤሌክትሪክ መኪና ለ...
11/12/2023


አዲስ አበባ፣ ሕዳር 28 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኤሎን መስክ ኩባንያ ከሆኑት አንዱ ‘ቴስላ አውቶሞቲቭ’ ቴስላ ሳይበር ትራክ የተሠኘ በቅርፅም ሆነ በዓይነት የተለየ የኤሌክትሪክ መኪና ለሽያጭ ይዞ ብቅ ብሏል፡፡
መኪናውን ከሌሎች የኤሌክትሪክ መኪናዎች ለየት የሚያደርገው ጥይት በማይበሳው፣ ቀለም በማያስፈልገው፣ በማይዝግ ስቴይንለስ ስቲል ብረት ስለተሠራ መሆኑን ከኩባንያው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
የመኪናው መስኮቶች ከተዘጉ ምንም ዓይነት ድምፅ ከውጪ የማያስገቡና ግጭት ቢደርስባቸው በቀላሉ የማይሰበሩ መሆናቸው ተጠቁሟል፡፡
የመኪናው ጣራ ድርብ ሲሆን በሰፊው ጠንካራ መሥታወት ሰማይን መመልከት ያስችላል፡፡
3 ሺህ 104 ኪሎ ግራም የሚመዝነውና አራት ባለ 20 ኢንች ዙሪያ መጠን ያላቸው ጎማዎች የተገጠሙለት ተሽከርካሪ ነው።
እስከ 1 ሺህ 134 ኪሎ ግራም ክብደት የመጫን እና እስከ 4 ሺህ 990 ኪሎ ግራም የመጎተት ዓቅም አለውም ተብሏል፡፡
መኪናውን በማየት ብቻ ጠንካራ መሆኑን መመስከር እንደሚቻል የተገለጸ ሲሆን፤ የግንባታ ዕቃዎችን መጫን ሲፈልጉ ውስጥ ሆነው በሚሠጡት ዲጂታል ትዕዛዝ ብቻ መኪናውን ወደ “ፒክ አፕ ሞድ” መቀየር ይቻላል፡፡
ወለሉ እጅግ በጣም ጠንካራ በሆነ ንጣፍ የተሠራ በመሆኑ ተጨማሪ ንጣፍ ማሠራት አያስፈልግም ብሏል ኩባንያው፡፡
አራቱም ጎማዎች በራሳቸው ኃይል እንዲሽከረከሩ እና ወደታዘዙበት አቅጣጫ እንዲተጣጠፉ ተደርጎ የተሰራው ይህ መኪና፤ ውስጡ ከፊት ከሾፌሩ ጋር የ2 ሰዎች፣ ከኋላ የ3 ሰዎች መቀመጫዎች አሉት፡፡
መካከል ላይ መኪናው ከፍ ስለሚል ውጭውን በዲጂታል ቴክኖሎጂ የታገዘ ወለል አድርጎ የሚያሳይ 18 ነጥብ 5 ኢንች ስፋት ያለው ስክሪን ተገጥሞለታል፡፡
9 ነጥብ 4 ኢንች ስክሪን ከኋላ የተካተተለት ይህ መኪና አንድ ጊዜ ቻርጅ ተደርጎ እስከ 550 ኪሎ ሜትር መጓዝ ይችላል ተብሏል።
ባትሪውን በተመለከተ ግን ኩባንያው ዝርዝር መረጃዎችን አላወጣም።
ቴስላ ሳይበር ትራክ የኤሌክትሪክ መኪና እስከ ፈረንጆቹ 2025 የሚቆይ 80 ሺህ ዶላር የመሸጫ ዋጋ ተቆርጦለታል፡፡

 ባሳለፍነዉ እሁድ በተደረገ የእንግሊዝ ፕሪሜርሊግ  ጨዋታ ቼልሲ ፣ኒዉካስትል ዩናይትድ እና ዉየስትሃም ሽንፈትን ሲያስተናግዱ ማንችስተር ሲቲ  ፤ቶተንሃም እና ፋልሃም ተጋጣሚያቸዉን ማሸነፍ ች...
11/12/2023


ባሳለፍነዉ እሁድ በተደረገ የእንግሊዝ ፕሪሜርሊግ ጨዋታ ቼልሲ ፣ኒዉካስትል ዩናይትድ እና ዉየስትሃም ሽንፈትን ሲያስተናግዱ ማንችስተር ሲቲ ፤ቶተንሃም እና ፋልሃም ተጋጣሚያቸዉን ማሸነፍ ችለዋል፡፡

 #ጎህዜናበ15 ሳምንት የእንግሊዝ  ፕሪሜርሊግ የመጨረሻ ቀን ጨዋታ ትላንት ምሽት ተደረገዋል፡፡ በምሽቱ ጨዋታም ቶተንሃም እና ኒዉ ካስትል ዩናይትድ ሳይታሰብ ተሸንፈዉ ሳምንቱን አጠናቀዋል፡፡...
08/12/2023

#ጎህዜና
በ15 ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሜርሊግ የመጨረሻ ቀን ጨዋታ ትላንት ምሽት ተደረገዋል፡፡ በምሽቱ ጨዋታም ቶተንሃም እና ኒዉ ካስትል ዩናይትድ ሳይታሰብ ተሸንፈዉ ሳምንቱን አጠናቀዋል፡፡
የሳንዳይሽ ቡድን ኢቨርተን በፍይናሻል ፊር ፕላይ ህግን መጣሱን ተከትሎ 10 ነጥብ ተቀንሶበት ወደ ወራጅ ቀጠናዉ እንዲወረወር ምክንያት መሆኑ ይታወሳል፡፡ ታዲያ በምሽቱ ጨዋታ በጉዲሰን ፓርክ ጠንካራዉን ኒዉ ካስትልን ዩናይትድን ጋብዞ ሳይታሰብ 3-0 በሆነ ዉጤት አሸንፏል፡፡
ሚችኒሊ ፣ ዳኩሬ እና ቢቶ የኤቨርተንን ወሳኝ ጎሎች አስቆጥረዋል፡፡ ኤቨርተነን ማሸነፉን ተከትሎ ሉተን ታዉን ፤ በርንሊ እና ሸፊሊድን በልጦ 17ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡
በሌላ የምሽት መርሃ ግብር ቶተንሃም በሜዳዉ በዲቨድ ሞይሱ ቡድን ዉየስትሃም ተረተዋል፡፡
የአንጊ ፖስቴኮጉሉ ቡድን በሊጉ ጅምሮ ጥሩ የአጨዋዉት ዘይቤ በግር ኳሱ አለም ቢያስመለክቱም በሰሞኑ ጨዋታ ግን በዉጤት ማጣት ቀዉስ ዉስጥ ገብተዋል፡፡ ያደረጓቸዉን አምስት ተከታታይ ጨዋታወች አንዱን እንኳን ማሸነፍ አልቻሉም፡፡ ትላንት ምሽትም ምንም እንኳን ቀድመዉ በአርጀንቲናዊ ተከላካይ ክሪስቲያን ሮሚሮ አማካኝነት ጎል አስቆጥረዉ 50 ደቂቃወችን ያክል 1-0 ሲመሩ ቢቆየም ጃሮድ ቦዉን እና ዋርድ ፕሮስ ለዉስትሃም ጎል ማስቆጠራቸዉን ተከትሎ ቶተንሃሞች በሜዳቸዉ እንዲሸነፋ ምክንያት ሆኗቸዋል፡፡

 #ጎህዜና የሒሳብ ትምህርት ዉጤት በዓለም አቀፍ ደረጃ ማሽቆልቆሉ ተገለጸ።ዋና መቀመጫውን ፈረንሳይ ፓሪስ ያደረገው የኢኮኖሚ ትብብር እና ልማት ድርጅት በየዓመቱ የሒሳን እና ሳይንስ ትምህርት...
08/12/2023

#ጎህዜና የሒሳብ ትምህርት ዉጤት በዓለም አቀፍ ደረጃ ማሽቆልቆሉ ተገለጸ።

ዋና መቀመጫውን ፈረንሳይ ፓሪስ ያደረገው የኢኮኖሚ ትብብር እና ልማት ድርጅት በየዓመቱ የሒሳን እና ሳይንስ ትምህርት ፈተናዎችን ይሰጣል፡፡

ድርጅቱ በ2022 የተሰጡ ዓለም አቀፍ ፈተና ውጤቶችን ይፋ ያደረገ ሲሆን 700 ሺህ የዓለማችን ተማሪዎች ፈተናውን እንደወሰዱ ተገልጿል፡፡

በ81 የዓለማችን ሀገራት ያሉ ታዳጊዎች የሒሳብ፣ ሳይንስ እና ማንበብ ፈተናዎችን የወሰዱ ሲሆን የሒሳብ ፈተና ውጤት በበርካታ ሀገራት ዝቅ እንዳለ ድርጅቱ በሪፖርቱ አስታውቋል፡፡

የነገ የዓለማችንን መሪዎች እና ተመራማሪዎችን ለመለየት የሚሰጠው ይህ ፈተና ከዚህ በፊት ጥሩ ውጤት ያስመዘግቡ የነበሩ ሃገራት ውጤት አልቀናቸውም።

ፈተናው ላይ ከተቀመጡ አራት ተማሪዎች መካከል አንዱ በሒሳብ ዝቅተኛ ውጤት አምጥቷል የተባለ ሲሆን በተለይም የሲንጋፖር ተማሪዎች የዓለማችን ከፍተኛ ውጤት አምጥተዋል ተብሏል፡፡

ጃፓን፣ ኢስቲኒያ፣ ቻይና፣ ካናዳ እና ደቡብ ኮሪያ በሒሳብ እና ሳይንስ ትምህርቶች የተሸለ ውጤት ያስመዘገቡ ተጨማሪ ሀገራት ናቸው፡፡

ጀርመን፣ አሜሪካ፣ ኔዘርላንድ፣ ኖርዌይ፣ ፖላንድ በሒሳብ ትምህረት ዝቅተኛ ውጤት እንዳስመዘገቡ ተገልጿል፡፡

ከአፍሪካ በብቸኝነት ሞሮኮ ተማሪዎቿን ያስፈተነች ሲሆን ከዚህ በፊት ከነበረው ውጤት ጋር ተቀራራቢ ውጤት እንዳስመዘገቡ ይሄው ተቋም በሪፖርቱ አስታውቋል፡፡

በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ትምህርት ቤቶች መዘጋት፣ ተማሪዎች ጊዜያቸውን በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ማዋል እና የመምህራን ብቃት መቀነስ ለተማሪዎች ውጤት መቀነስ ዋነኞቹ ምክንቶች ሆነው ተገኝተዋል ተብሏል፡፡

ጥናቱን የሰራው ኦሲድ የተሰኘው ተቋም ከፈረንጆቹ 2000 ሺህ ዓ.ም ጀምሮ በየዓመቱ 15 ዓመት የሆናቸው የዓለማችንን ተማሪዎች የሒሳብ፣ ሳይንስ እና ማንበብ አቅማቸውን ለመለካት ፈተና በመስጠት ይታወቃል፡፡
ዘገባው ነአል አይን ነው።

ክልል፤ ህዳር 25/2016(ኢዜአ) ፡- የሸገር ከተማ አስተዳደር ህገ ወጥ ንግድና ኮንትሮባንድ ላይ ጠንካራ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ አቶ ጉዮ ገልገሎ ገለጹ...
06/12/2023

ክልል፤ ህዳር 25/2016(ኢዜአ) ፡- የሸገር ከተማ አስተዳደር ህገ ወጥ ንግድና ኮንትሮባንድ ላይ ጠንካራ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ አቶ ጉዮ ገልገሎ ገለጹ። ህገ ወጥ ንግድና ኮንትሮባንድ በአገሪቷ አጠቃላይ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ላይ የተለያዩ ተጽእኖዎችን እያደረሰ ይገኛል። ለአብነት የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር በበጀት ዓመቱ ሶስት ወራት በ402 የንግድ ድርጅቶች ላይ በተደረገ የክትትልና የቁጥጥር ስራ ህግን ተከትለው ባልሰሩ 37 ንግድ ድርጅቶች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰዱን መግለጹ ይታወቃል። እርምጃው የተወሰደባቸውም የንግድ ድርጅቶቹ ከተሰጣቸው የንግድ ፈቃድ መስኮችና ዓላማዎች ውጪ ሲሰሩ የነበሩ፣ ባልፀና ወይም ባልታደሰ ንግድ ፊቃድ ሲነግዱ የተገኙ፣ ባስመዘገቡት የስራ አድራሻ ያልተገኙ እንዲሁም የቅርንጫፍ አድራሻ ያላስመዘገቡ በመሆናቸው እንደሆነ በማከል ። በተመሳሳይ የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን በየሳምንቱ በሚያወጣቸው መግለጫዎች ከፍተኛ ግምት ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች ከአገር ሲወጡና ሊገቡ ሲሉ እየተያዙ መሆኑን ያመለክታል። ኮሚሽኑ ከጥቅምት 29 እስከ ህዳር 5 ቀን 2016 ዓ.ም ባደረገው ክትትል 284 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ የገቢ እና የወጪ የኮንትሮባንድ እቃዎች በተለያዩ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች መያዙን በድረ ገጹ ማስፈሩምይታወሳል። ህገ ወጥ ንግድና ኮንትሮባንድን በመከላከልና በመቆጣጠር ረገድ በአገሪቷ ካሉ ዋና ዋና ከተሞች መካከል በቅርቡ የተመሰረተው የሸገር ከተማ አስተዳደር ምን ዓይነት ተሞክሮ እንዳለው ተጠይቋል። ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉት የሸገር ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ጉዮ ገልገሎ፣ ከተማ አስተዳደሩ ህገ ወጥ ንግድና ኮንትሮባንድ መከላከል ላይ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል። ባለፈው ዓመት ብቻ አስተዳደሩ ባደረገው ጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር ከህገ ወጥ ንግድና ኮንትሮባንድ ቁጥጥር ጋር በተያያዘ 58 ሚለዮን ብር ለመንግስት ገቢ መደረጉን ገልጸዋል። ፉሪ፣ ሰበታ፣ ቡራዩና ጣፎ አካባቢዎች ደግሞ የኮንትርባንድ ንግዱ በብዛት የሚተላለፍባቸው አካባቢዎች መሆናቸውን ጠቅሰው፤ በተጠቀሱት ስፍራዎች ጠንካራ ቁጥጥር እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል። በዚህም በተያዘው በጀት ዓመት በሩብ ዓመት ብቻ 28 ሚሊዮን ብር የሚገመት የኮንትሮባንድ እቃ በቁጥጥር ስር መዋሉንም ገልጸዋል። በቀጣይም የቁጥጥር ስራው እንደሚጠናከር ገልጸው አስተዳደሩ በድርጊቱ ተሳትፈው የተገኙ አካላት ላይ ጠንካራ እርምጃ መውሰዱን ይቀጥላል ብለዋል። የሸገር ከተማ አስተዳደር በአዲስ አበባ ዙሪያ ያሉ አካባቢዎችን ይዞ የተመሰረተ ከተማ መሆኑ ይታወሳል።

Address

Addis Ababa

Website

http://tiktok.com/@gohetv0

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gohe Tv Broadcasting service posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Gohe Tv Broadcasting service:

Videos

Share

Category