06/10/2024
ከመሬት መንቀጥቀጡ ጋር በተያያዘ፦
በተለይ በጋራ መኖሪያ(ኮንደሚኒየሞች) አካባቢ በአደጋዎች ወቅት ያለው ''የችግሮች ምላሽ አሰጣጥ'' በተቻለ መጠን ትምህርት ያስፈልገዋል።
የአደጋው መንስዔ አንድ ሆኖ ሳለ የሰው የበዛ መሸበር በራሱ ግን ሌላ ችግር የሚያስከትል ነው። በአለመረጋጋቱ ምክንያትና ከነዋሪው መብዛት የተነሳ ከዋናው ችግር በኋላ የሚሰሙ ሌሎች መጠነኛ ችግሮች ይሰማሉ። ችግሩ ምን እንደሆነ በቅጡ ሳይለዩ እንኳ ከሕንፃዎች ወርዶ ለማምለጥ በሚደረግ ሙከራ መውደቅ፣ መሰበርና ሌሎች ከልብ ጋር የተያያዙ ችግሮች ተጠቃሽ ናቸው።
በርግጥ የሚፈጠረው አደጋና ተከትሎት የሚመጣው መረበሽ ለእንዲህ አይነት የተረጋጋ ውሳኔ ጊዜ የማይሰጥ ሊሆን ይችላል። ሆኖም ጥንቃቄና መረጋጋትም ያድናል!