Fegegeta radio show/ፈገግታ የራዲዮ ፕሮግራም

Fegegeta radio show/ፈገግታ የራዲዮ ፕሮግራም Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Fegegeta radio show/ፈገግታ የራዲዮ ፕሮግራም, Broadcasting & media production company, Addis Ababa.

21/02/2024
07/02/2024

ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ወደ አገር እንዳይገቡ ተከለከሉ

| ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የኒውዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በአሜሪካ የነበራቸውን ሐዋርያዊ አገልግሎት ጨርሰው ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ እንዳይገቡ መከልከላቸው ተሰምቷል።

ብፁዕነታቸው ከሳምንታት በፊት በቋሚ ሲኖዶስ እውቅና ወደ ሀገረ ስብከታቸው በመሄድ የአጋእዝተ ዓለም ሥላሴ ዓመታዊ በዓል፣ የከተራና የጥምቀት በዓላትን ከመንፈስ ልጆቻቸው ጋር ያከበሩ ሲሆን ለአዳጊ ሕጻናትም ማዕረገ ዲቁና መስጠታቸው ይታወቃል።

ብፁዕነታቸው በአሁኑ ሰዓት ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያው እንደሚገኙ ታውቋል።

ምንጭ:- ማኀበረ ቅዱሳን

 #ትዝብት ሀገራችን ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በተለያየ ችግር ተወጥራ ህዝቡ ግራ ገብቶት በልቶ ማደር ወጥቶ መግባት ብርቅ እየሆነበት መጥቷል።ገሚሱ በጦርነት ንብረቱ ወድሟል፤ ከፊሉ ተፈናቅሏል፤...
13/03/2022

#ትዝብት

ሀገራችን ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በተለያየ ችግር ተወጥራ ህዝቡ ግራ ገብቶት በልቶ ማደር ወጥቶ መግባት ብርቅ እየሆነበት መጥቷል።
ገሚሱ በጦርነት ንብረቱ ወድሟል፤ ከፊሉ ተፈናቅሏል፤ ሌላው በኑሮ ውድነት ናላው ዞሮ ብቻውን እያወራ መሄድ ጀምሯል።

በሌላ በኩል ደግሞ የሀገሪቱን የተመሣቀለ ሁኔታ እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም በድሀው ህዝብ ለይ የሚቆምሩ ኑሮ ይበልጥ እንዲነድ ቤንዝል የሚያርከፈክፋ ከሆዳቸው ውጪ ህሊና የሚባል ያልፈጠረባቸው ዱሁሮች እጅግ ተበራክተዋል።

መሠረታዊ ፍጆታዎች ለይ ያለምንም ሀፍረት ከሚገባቸው በላይ ትርፍ የሚያጋብሱ፣ ጤናን የሚጎዳ ጥራትና ደረጃውን ያልጠበቀ ምርት በማስገባት በህዝብ ነፍስ የሚቀልዱ የምድር ጉዶች ያለማንም ከልካይ እንደልባቸው በድሀው ህዝብ ለይ ይፈነጫሉ።
በግፍ ያገኙትንም ገንዘብ በውጪ ምንዛሬ ከተለያዩ የአለም ክፍሎች የመጡና የተለያየ ስያሜና ደረጃ ያላቸውን አረቄ ሲጋቱ ያድራሉ።
በአንድ ምሽት በመቶ ሺህ የሚቆጠር ገንዘብን ያለ ማንም ሃይ ባይ አንድ ግለሰብ በየምሽት ጭፈራ ቤቱ ሲበተን ያድራል። ድህነት ያንገላታቸው የድሀ ወጣት ሴቶች ለእነዚሁ ማሰብ ለተሳናቸው ግለሰቦች በርካሽ ዋጋ ለአፀያፊ የዝሙት ስራ ይቀርባሉ።

በሃጢአት እና በማጭበርበር የመጣ ገንዘብ ስለሆነ ለመልካም አገልግሎት እና ለደሀው ያገሬ ሰው ልማት አይውልም።

ይልቁንም በዲያብሎስ የሚጋለቡ የምሽት ጭፈራ ቤቶች ሲሳይና አረቄ ቸርችረው በሚሊዮን የሚያጋብሱ ተራ የመጠጥ ነጋዴዎች ኪስ ማደለቢያ ነው የሚሆነው።

እነዚህ የተለያየ ስም የተሰጣቸው የለሊት ጭፈራ ቤቶች አብዛኛዎቹ ከጥልቁ የሳጥናኤል መንፈስ አሰራር ጋር ጥብቅ ቁርኝት ስላላቸው አዘውትሮ መሄድ የለመደ በቀላሉ ይላቀቅ ዘንድ ይሳነዋል።
/ለነገሩ በውድቅት ለሊት ሰክሮና አይምሮን ስቶ በዝሙት መንፈስ ሲጨፍሩ ማደር ከመንፈስ ቅዱስ አሠራር የተለየ መሆኑ ግልፅ ነው።/
ኢትዮጵያ ውስጥ ከ98% በላይ የሚሆነው ህዝብ በአንድ ወይም በሌላ መልኩ አማኝ እንደሆነ ይታወቃል።
ቢያንስ በፈጣሪ ህልውና ያምናል ፈጣሪ ደግሞ በየትኛውም ሐይማኖት በኩል ያለው አስተምህሮት፦ ሌብነትን ያወግዛል። ስካርንና ዝሙትን አብዝቶ ይፀየፋል። ዘረኝነትን፣ መለያየትንና አድመኝነትን ይቃወማል።

ስግብግብነት፣ ግለኝነት፣ አድመኝነት፣ ራስ ወዳድነት፣ ስካር፣ ዝሙት፣ መዋሸት፣ ማጭበርበር፣ ማመንዘር እነዚህንና እነዚህን የመሳሰሉትን የምትፈፅሙ ሁሉ የዲያብሎስ ባሪያዎች ናችሁ።

እናንተ የተጠላችሁ፣ የተናቃችሁ፣ የተዋረዳችሁና ህዝብ የተፀየፋችሁ ናችሁ።
ፖለቲካውን፣ ኢኮኖሚውንና ስልጣኑን ባመዛኙ የተቆጣጠራችሁት ደግሞ እናንተ ናችሁ። በእናንተ ቁጥጥር ስር ያለች አገራችን ኢትዮጵያ ከድህነት አረንቋ ተላቃ ትበለጽግ ዘንድ አይቻላትም።

መጀመሪያ ራሣችሁን አፅዱ፡ አረቄ እየጠጡ መጨፈር አቁሙ በሸፍጥና ሴራ የምትነግዱትን ንግድ ወደ ጤናማ ስርአት አስገቡ። ራስን ብቻ መውደድ ስለማይጠቅም ለወገናችሁ ደሀው ማህበረሠብ አስቡ።

እዚህ አለም ላይ ህያው ሆኖ የሚቀር ማንም የለም እንደምትሞቱ እያሠባችሁ የህያዋን ያህል ልፉ።
ያኔ እድገት ብልጽግናችን ይረጋገጣል፣ የአገራችን ከፍታም እውን ይሆናል።

በዚሁ ከቀጠልንና አሸሸ ገዳሜያችንን ካልተውን ከድጡ ወደ ማጡ እንዲሉ እየባሰ እንደሚሄድ ምንም ጥርጣሬ የለኝም።
የሚያሳዝነው በእናንተ ዳፋ ህዝብ አንገት መድፋቱና መጎሳቆሉ ነው።
ህሊና ካላችሁ አድምጡት!
ከሌላችሁ ገለል በሉ።
እግዚአብሔር ይርዳን!!
ቢኒያም ጋሻው

#ትዝብት

ሀገራችን ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በተለያየ ችግር ተወጥራ ህዝቡ ግራ ገብቶት በልቶ ማደር ወጥቶ መግባት ብ

 #ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የአራት ትውልድ አርቲስቶች/ድምፃውያን በአንድ መድረክ ተገናኝተው ስለ ኢትዮጵያ ሊያዜሙ ነው።ሐሙስ ጥር 19/2014 በወዳጅነት ፓርክ እንዲሁም ቅዳሜ ጥር 21/2014 ...
04/01/2022

#ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የአራት ትውልድ አርቲስቶች/ድምፃውያን በአንድ መድረክ ተገናኝተው ስለ ኢትዮጵያ ሊያዜሙ ነው።

ሐሙስ ጥር 19/2014 በወዳጅነት ፓርክ እንዲሁም ቅዳሜ ጥር 21/2014 በመስቀል አደባባይ ታላቅ የገቢ ማሰባሰቢያ የሙዚቃ ዝግጅቶች ያቀርባሉ።

ገቢውም ሙሉበሙሉ በጦርነቱ ለተጎዱ እና ለተፈናቀሉ ወገኖች ይውላል በማለት በዛሬው እለት (26/04/2014) በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አሣውቀዋል። ድምፃውያኑን በመወከል አርቲስትና አክትቪስት ታማኝ በየነ መላው አገር ወዳድ የሆነ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ትኬት በመግዛት አላማውን እንዲደግፍ ጥሪውን አቅርቧል።
ጋዜጣዊ መግለጫው ለይ የተገኙት ድምፃውያን፦ ፀሀዬ ዮሐንስ፣ አረገኻኝ ወራሽ፣ ፀጋዬ እሸቱ፣ ማዲንጎ አፈወርቅ፣ ታደለ ሮባ፣ አቦነሽ አድነው፣ ፍቅራዲስ ነቅዐጥበብ፣ ሕብስት ጥሩነህ፣ ሚካኤል በላይነህ፣ ያሬድ ነጉ፣ ዳዊት ፅጌ ሲሆኑ፡ ከአስተባባሪዎች መካከል ታማኝ በየነ ፣ ሰይፉ ፋንታሁን፣ አቻሬ፣ በፍቃዱ አባይ ተገኝተዋል።ተባባሪዎች ደግሞ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (EBC) ዋፋ ማርኬቲንግና ይሳቃል ኢንተርቴይመንት ናቸው።

በመግለጫው ለይ አንጋፋውን ድምፃዊ መሀሙድ አህመድን ጨምሮ በርካታ ድምፃውያን እንደሚገኙ የዝግጅቱ አስተባባሪ አርቲስቶች ገልፀዋል።

 #ዶክተር አብይ አሕመድን ማሸነፍ በፍጹም አይቻልም። ይሄንን ሁሉም አለም አምኖ ሊቀበለው ይገባል ። ሱሌማን አብደላከትግራይ ወደ አዲስ አበባ የሚሄደው ባቡር ተጠምዞ ወደመቀሌ እየሄደ ነው።ግ...
30/11/2021

#ዶክተር አብይ አሕመድን ማሸነፍ በፍጹም አይቻልም። ይሄንን ሁሉም አለም አምኖ ሊቀበለው ይገባል ።

ሱሌማን አብደላ

ከትግራይ ወደ አዲስ አበባ የሚሄደው ባቡር ተጠምዞ ወደመቀሌ እየሄደ ነው።

ግብፃዊ የፖለቲካ ተንታኝ አልሸርቅ ሚዲያ ላይ ከተናገረው የተወሰደ።

አሜሪካ አውሮፓ ሁሉም ከኛ ጋር ቆመው ነበር። የህወሓት ተዋጊዎች አስገራሚ በሚመስል መልኩ ወደ አዲስ አበባ እየገሰገሱ ነበር። በዚህ ሁለት ወይም ሦስት ቀናቶች ውስጥ አዲስ አበባ ገቡ፣ ይሄንን ሰውየ ተገላገልን ብየ ለመናገር ትንሽ ሰአት ቀረኝ ስል፣ ሰውየው ጭራሹንም ጦሩን እራሴ እመራለሁ ብሎ መግለጫ ሰጠ።

ወርዶ ሲያዋጋ ቆየ። ህወሓት ይቆጣጠረዋል የተባለውን የጅቡቲ መንገድ ነፃ አወጣ። አፋር ክልል ሙሉ በሙሉ ነፃ ሆነ። ኮምቦልቻ ባቲና ጋሸ ጭፍራ የሚባሉ ወሳኝ ወታደራዊ ቦታዎችን ያዘ። አሁን ነገሮች ተቀያይረዋል። ከትግራይ ወደ አዲስ አበባ የሚሄደው ባቡር ተጠምዞ ወደመቀሌ እየሄደ ነው። በየትኛውም ቀን ወይም ሳምንት ውስጥ መከላከያ መቀሌ ይገባል። የህወሓት ተዋጊዎች አቅም አንሷቸዋል። የሎጀስቲክ የሰው ሀይል የውጊ መጨለም ገጥሟቸዋል። በዚህ ደረጃ ላይ ቆመው ወደኋላ እየሸሹ ነው።
አሜሪካና የአውሮፓ ህብረት የኛ ሀይል በኢትዮጵያ መንግስት ላይ የፈጠረው ተፅዕኖ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እልህና ቁጭትን ዘርቷል። ሚሊየኖች ወደ ጦር ግንባር እየሄዱ ነው። ጦረነቱ ከአብይ አሕመድ ስረአት ተላቆ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር የሚደረግ ጦርነት ሆኗል። አፍሪካዊ የፀረ አፓርታይድ ትግል ነው ተብሎ በአፍሪካውያን እየተቀነቀነ ነው። አብይ ስልጣኑን አልፈልግም ሀገሬ ትቀድማች ሞቼ ወይም ተዋግቸ ኢትዮጵያን አስቀጥላለሁ ብሎ ወደ ጫካ ሲገባ ነው ነገሮች የተቀያየሩት። ህዝቡ እንዳለ ግንፍል ብሎ ወጣ ። ሁሉም ነገር ተቀይሯል።

ከዚህ ቡሀላ የግብፅ ጉዳይ ከአብይ አሕመድ እጅ እንዳሎጣ እመኑት። ካይሮ ላይ ወላሂ ወላሂ ብሎ እንደከዳን አሁን ፈጣሪ ክዶት ይገረሰሳል ብለን ስንጠብቅ
ጦርሜዳ ተዋጊ ሆኖ ማሸነፍ ጀምሯል። ከዚህ ቡኋላ የሚደረጉ ውጊያዎች ከአብይ
ጋር ሳይሆን የኢትዮጵያን ህዝብ ጋር የሚደረግ ውጊ ሆኗል። እሱ ሲነሳ ህዝቡ
እንደ ህዝብ ''ሆ'' በሎ ነው የወጣው። ህዝብን ከጎኑ አሰለፈ ማለት ነገሮች ተቀያየሩ ማለት ነው። አብይ አሕመድን ማሸነፍ በፍጹም አይቻልም። ይሄንን ሁሉም አለም አምኖ ሊቀበለው ይገባል ።

ሱሌማን አብደላከትግራይ ወደ አዲስ አበባ የሚሄደው ባቡር ተጠምዞ ወደመቀሌ እየሄደ ነው።

ግብፃዊ የፖለቲካ ተንታኝ አልሸርቅ ሚዲያ ላይ ከተናገረው የተወሰደ
አሜሪካ አውሮፓ ሁሉም ከኛ ጋር ቆመው ነበር። የህወሓት ተዋጊዎች አስገራሚ በሚመስል መልኩ ወደ አዲስ አበባ እየገሰገሱ ነበር። በዚህ ሁለት ወይም ሦስት ቀናቶች ውስጥ አዲስ አበባ ገቡ፣ ይሄንን ሰውየ ተገላገልን ብየ ለመናገር ትንሽ ሰአት ቀረኝ ስል፣ ሰውየው ጭራሹንም ጦሩን እራሴ እመራለሁ ብሎ መግለጫ ሰጠ።

ወርዶ ሲያዋጋ ቆየ። ህወሓት ይቆጣጠረዋል የተባለውን የጅቡቲ መንገድ ነፃ አወጣ። አፋር ክልል ሙሉ በሙሉ ነፃ ሆነ። ኮምቦልቻ ባቲና ጋሸ ጭፍራ የሚባሉ ወሳኝ ወታደራዊ ቦታዎችን ያዘ። አሁን ነገሮች ተቀያይረዋል። ከትግራይ ወደ አዲስ አበባ የሚሄደው ባቡር ተጠምዞ ወደመቀሌ እየሄደ ነው። በየትኛውም ቀን ወይም ሳምንት ውስጥ መከላከያ መቀሌ ይገባል። የህወሓት ተዋጊዎች አቅም አንሷቸዋል። የሎጀስቲክ የሰው ሀይል የውጊ መጨለም ገጥሟቸዋል። በዚህ ደረጃ ላይ ቆመው ወደኋላ እየሸሹ ነው።
አሜሪካና የአውሮፓ ህብረት የኛ ሀይል በኢትዮጵያ መንግስት ላይ የፈጠረው ተፅዕኖ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እልህና ቁጭትን ዘርቷል። ሚሊየኖች ወደ ጦር ግንባር እየሄዱ ነው። ጦረነቱ ከአብይ አሕመድ ስረአት ተላቆ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር የሚደረግ ጦርነት ሆኗል። አፍሪካዊ የፀረ አፓርታይድ ትግል ነው ተብሎ በአፍሪካውያን እየተቀነቀነ ነው። አብይ ስልጣኑን አልፈልግም ሀገሬ ትቀድማች ሞቼ ወይም ተዋግቸ ኢትዮጵያን አስቀጥላለሁ ብሎ ወደ ጫካ ሲገባ ነው ነገሮች የተቀያየሩት። ህዝቡ እንዳለ ግንፍል ብሎ ወጣ ። ሁሉም ነገር ተቀይሯል።

ከዚህ ቡሀላ የግብፅ ጉዳይ ከአብይ አሕመድ እጅ እንዳሎጣ እመኑት። ካይሮ ላይ ወላሂ ወላሂ ብሎ እንደከዳን አሁን ፈጣሪ ክዶት ይገረሰሳል ብለን ስንጠብቅ
ጦርሜዳ ተዋጊ ሆኖ ማሸነፍ ጀምሯል። ከዚህ ቡኋላ የሚደረጉ ውጊያዎች ከአብይ
ጋር ሳይሆን የኢትዮጵያን ህዝብ ጋር የሚደረግ ውጊ ሆኗል። እሱ ሲነሳ ህዝቡ
እንደ ህዝብ ''ሆ'' በሎ ነው የወጣው። ህዝብን ከጎኑ አሰለፈ ማለት ነገሮች ተቀያየሩ ማለት ነው። አብይ አሕመድን ማሸነፍ በፍጹም አይቻልም። ይሄንን ሁሉም አለም አምኖ ሊቀበለው ይገባል ።

ሱሌማን አብደላ

ጠቅላይ ሚነስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ከዛሬ 14/03/2014 ጀምሮ ወደ ግንባር በመዝመት የኢትዮጵያ አገር መከላከያ ሠራዊትን ይመራሉ።
23/11/2021

ጠቅላይ ሚነስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ከዛሬ 14/03/2014 ጀምሮ ወደ ግንባር በመዝመት የኢትዮጵያ አገር መከላከያ ሠራዊትን ይመራሉ።

አገራችን  #ኢትዮጵያ ላይ የሚደረግ ጫናን የሚቃወሙ ሰልፎች በበርካታ አገራት ተደረጉትውልደ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን በሰሜን አሜሪካ፣ ዩናይትድ ኪንግደም እና እስራኤልን ጨምሮ በበርካታ...
22/11/2021

አገራችን #ኢትዮጵያ ላይ የሚደረግ ጫናን የሚቃወሙ ሰልፎች በበርካታ አገራት ተደረጉ

ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን በሰሜን አሜሪካ፣ ዩናይትድ ኪንግደም እና እስራኤልን ጨምሮ በበርካታ ከተሞች የምዕራብ አገራትን ጫና በመቃወም ለኢትዮጵያ መንግሥት ያላቸውን ድጋፍ አደባባይ በመውጣት ገለጹ።

ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን የኢትዮጵያ መንግሥት ከህወሓት አማጺያን ጋር በሚያደርገው ጦርነት ምዕራባውያን አገራት ለፌደራሉ መንግሥት ድጋፍ እንዲሰጡ ጠይቀዋል።

መንግሥታዊው ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ በ27 ከተሞች የድጋፍ ሰልፉ መካሄዱን ዘግቧል።

የድጋፍ ሰልፉ ከተደረገባቸው ከተሞች መካከል፤ ዋሽንግተን ዲሲ፣ ኒው ዮርክ፣ ሎስ አንጀለስ፣ ኦስቲን፣ ሂውስተን፣ ቶሮንቶ፣ ኦታዋ፣ ካልጋሪ፣ ዊኒፒግ እና ለንደን ተጠቃሽ ናቸው።

የካናዳው ሲቢኤስ ኒውስ በካናዳዋ ማኒቶባ ግዛት ዊኒፒግ ከተማ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የኢትዮጵያ መንግሥት ከህወሓት ጋር በሚያደርገው ጦርነት የካናዳ መንግሥት ለኢትዮጵያ መንግሥት ድጋፍ እንዲያደርግ አደባባይ ወጥተው ጠይቀዋል ሲል ዘግቧል።

በዊኒፒግ ከተማ የተዘጋጀውን የድጋፍ ሰልፍ ካስተባበሩት መካከል አንዱ የሆኑት ማርቆስ ተገኝ፤ "በኢትዮጵያ ውስጣዊ ጉዳይ በተለይ አሜሪካ ጣልቃ መግባት ማቆም አለባት፤ ኢትዮጵያውያን የራሳቸውን ችግር በራሳቸው እንዲፈቱ መፍቀድ አለባት" ሲሉ ሲቢኤስ ኒውስ ተናግረዋል።

በሌላኛዋ የካናዳ ከተማ ካልጋሪ ተመሳሳይ የድጋፍ ሰልፍ መካሄዱን ሲቲቪ ኒውስ ካልጋሪ ዘግቧል። ለፌደራሉ መንግሥት ድጋፍ ለመስጠት በተጠራው ሰልፍ ላይ ሰዎች (ከአሁን በኋላ ይብቃ) እንዲሁም (እጃችሁን አንሱ) የሚሉ መፈክሮችን ይዘው መውጣታቸው ሲቲቪ ኒውስ ካልጋሪ አሳይቷል።

በተመሳሳይ በአሜሪካ ቴክሳስ ግዛት ኦስቲን ከተማ ተመሳሳይ ድጋፍ አድርገዋል። "እነዚህ በኢትዮጵያ ያሉ ጉዳዮች ናቸው፤ እራሳችን መፍታት እንችላለን። እዚህ የተገኘነው እባካችሁ አቁሙ፤ የራሳችንን ጉዳይ እራሳችን እንፈታዋለን ለማለት" በማለት የኦስቲን ሰልፍ ተሳታፊ የሆነው ቴድ ኃይሉ ለሲቢኤስ ኦስቲን ተናግሯል።
ምንጭ BBC Amharic

15/10/2021
ከእንግዶቻችን በከፊል።
15/10/2021

ከእንግዶቻችን በከፊል።

14/10/2021

ምሥራቅ ወለጋ ውስጥ በተፈጸሙ ጥቃቶች 15 ሰዎች መገደላቸውን የክልሉ መንግሥት ተናገረ

በኦሮሚያ ክልል፣ በምሥራቅ ወለጋ ዞን፣ በኪረሙ ወረዳ ውስጥ በሚገኘው ሀሮ ከተማ ባለፈው እሁድ መስከረም 30 ቀን 2014 ዓ.ም የተጸፈመ ጥቃትን ተከትሎ የሰዎች ሕይወት መጥፋቱን እና ንብረት መውደሙን የዓይን እማኞች ለቢቢሲ ገለጹ።

በምሥራቅ ወለጋ ሀሮ በተባለ አካባቢ በተፈጸመ ጥቃት በርካታ ንጹሀን ሰዎች እንደተገደሉ፣ ከቤት ንብረታቸው እንደተፈናቀሉ እንዲሁም የንብረት ውድመትም እንደደረሰ ተነግሯል።

እሁድ፣ መስከረም 30/2014 ዓ.ም ከተፈጸመው ጥቃት ጋር በተያያዘ የ15 ሰዎች ሕይወት መጥፋቱን መረጃ እንዳላቸው የኦሮሚያ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

በርካታ የቤተሰቦቻቸው አባላት እንደተገደሉባቸው እና ሌሎችም የአንድ ቤተሰብ አባል የሆኑ የአካባቢው ነዋሪዎች በዚህ ግጭት ሳቢያ ሕይወታቸውን እንዳጡ የዓይን እማኞች ለቢቢሲ ተናግረዋል።

በአማራ እና በኦሮሞ ወገን ያሉ ማኅበረሰቦች ለተፈጸመው ጥቃት እርስ በእርስ በመወነጃጀል ለደረሰው ጥቃት አንዳቸው የሌላኛቸውን ወገን ተጠያቂ ያደርጋሉ።

በአንድ በኩል ግጭቱ የተነሳው በነዋሪዎች መካከል እንደሆነ ሲነገር፣ በሌላ በኩል ደግሞ እራሱን የኦሮሞ ነጻነት ጦር የሚለው እና መንግሥት ሸኔ የሚለው ቡድን እንዲሁም የአማራ ኃይሎች ከግጭቱ ጋር በተያያዘ እጃቸው አለበት የሚሉ ውንጀላዎች ይሰማሉ።

ባለፈው ዓመት ነሐሴ ወር እንዲሁም በዚህ መስከረም ላይ በአካባቢው ጥቃቶች ተፈጽመው የብዙዎች ሕይወት መቀጠፉ አይዘነጋም።
ምንም BBC Amharic

Thank you!🙏
12/10/2021

Thank you!🙏

በፕሮግራማችን ለይ ከቀረቡት ተወዳጅ፣ ታዋቂና አንጋፋ የጥበብ ባለሞያዎች በከፊል።
12/10/2021

በፕሮግራማችን ለይ ከቀረቡት ተወዳጅ፣ ታዋቂና አንጋፋ የጥበብ ባለሞያዎች በከፊል።

12/10/2021

ፈገግታ የመዝናኛ እና የመረጃ ፕሮግራም ጥቅምት 5 ቀን 2008 ዓ.ም ነበር ለመጀመሪያ ግዜ አየር ለይ የዋለው (የተጀመረው )።
የመጀመሪያው እንግዳችን ደግሞ ደራሲና ፀሀፌተውኔት ሀይሉ ፀጋዬ ነበር ከዛ በተለያየ የሞያ ዘርፍ የተሠማሩ የኪነ-ጥበብ ሰዎች፣ ድምፃውያን፣ደራሲዎች፣ ተዋናዮች፣ ሙዚቃ አቀናባሪዎች፣የፈጠራ ባለሞያዎች፣ጋዜጠኞች እና ኮሜዲያኖች ቀርበው ለአድማጮች ልምዳቸውን አካፍለዋል።
እንግዳችን ሆነው ልምዳቸውን ያካፈሉንን ሁሉ ከልብ እናመሠግናለን።
በተለይ አድማጮቻችንን እጅግ በጣም እናመሠግናለን!!
ከ450 በላይ እንግዶች የቀረቡ ሲሆን በጣም የጥቂቶችን ምስል እናቀርባለን 5 ዓመት አብረውን የተጓዙትን አድአድማጮች ሁሌም ሰምተው የሚደውሉልንን የጥቂቶቹን ስም ከ4ቱም ማዕዘን ጠርተን እናመሠግናለን!!🙏🙏

ስፖንሰሮቻችንንም በጣም እናመሠግናለን !🙏🙏🙏
ኤም ኤ ኤች ኤ ድሬ ላይት ትሬዲንግ
ለገሀር አጠቃላይ ሆስፒታል
ሄኒከን ኢትዮጵያ
ዶ/ር ሠላማዊት ስፔሻላይዝድ የጥርስ ህክምና ክሊኒኮች
BGI, jorka, A.M printing, እና ሌሎች ያልጠቀስናቸውን ሁሉ አብዝተን እናመሠግናለን🙏🙏

12/10/2021

በኢትዮጵያ በኮቪድ-19 የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ6 ሺህ በላይ ሆነ

በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ ሳቢያ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ስድስት ሺህ ማለፉን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

ባለፉት ጥቂት ወራት በአገሪቱ ውስጥ በወረርሽኙ ሳቢያ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በአሳሳቢ ሁኔታ መጨመሩን በየዕለቱ የሚወጣው መረጃ የመለክታል።

የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ ባለፈው ሳምንት ማብቂያ ላይ እንደተናገሩት በኮሮናቫይረስ ተይዘው ለሞት ከተዳረጉት ሰዎች መካከል ሁሉም በሚባል ደረጃ ያልተከተቡ ናቸው።

በአገሪቱ ውስጥ ከሰኔ ወር አጋማሽ ጀምሮ እሰከ ነሐሴ ወር አጋማሽ ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ በወረርሽኙ ከሞቱ ሰዎች መካከል አንድ ግለሰብ ብቻ የመጀመሪያውን የኮቪድ መከላከያ ክትባት የወሰደ ሲሆን ሌሎቹ በሙሉ ያልተከተቡ መሆናቸው ተገልጿል።

በኢትዮጵያ በኮሮና የሞቱ ሰዎች ወደ 6 ሺህ ሲጠጋ ሁሉም በሚባል ሁኔታ ያልተከተቡ መሆናቸው ተገለጸ
በኢትዮጵያ ውስጥ የኮሮናቫይረስ መከላከያ ክትባት መሰጠት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ወደ ሦስት ሚሊየን የሚጠጉ ሰዎች መከላከያ ክትባቱን ማግኘታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመልክቷል።

በሽታው በአገሪቱ ውስጥ መገኘቱ ከታወቀ ጊዜ ጀምሮ ለሞት የተዳረጉ ሰዎች አሃዝ አስከ ሰኞ ጥቅምት 01/2014 ዓ.ም አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 6026 ደርሷል።

የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ በበሽታው የሚያዙ፣ በጽኑ የሚታመሙና የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር ለመጨመሩ በአገሪቱ ውስጥ አደገኛው የዴልታ ዝርያ መኖሩ፣ በአንድ ስፍራ በብዛት የሚደረጉ መሰባሰቦችና የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ማድረግን ጨምሮ የበሽታውን የመከላከያ መመሪያዎች በአግባቡ ተግባራዊ አለማድረግ ምክንያት መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

ጨምረውም በበሽታው የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መሆኑንና ባለፈው ሳምንት ብቻ 308 ሰዎች የሞቱ ሲሆን ይህም ወረርሽኙ ከበኢትዮጵያ ከተከሰተ በኋላ ከፍተኛው የሞት አሃዝ ሆኖ እንደተመዘገበ ሚኒስትሯ ገልጸዋል።

በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ውስጥ በየዕለቱ በአማካይ ከአንድ ሺህ በላይ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው በምርመራ የሚረጋገጥ ሲሆን፤ ባለፈው ሳምንት በየቀኑ በአማካይ 44 ሰዎች ህይወታቸው እንዳለፈ ተገልጿል።

ከእነዚህ ውስጥም 324,450ው ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን 6,026ቱ ደግሞ ህይወታቸው ማለፉንም የጤና ሚኒስቴር አመልክቷል።
ምንጭ BBC Amharic

 እንኳን ደስ አልዎት!!መልካም የስራ ዘመን ይሁንላችሁ !
04/10/2021


እንኳን ደስ አልዎት!!

መልካም የስራ ዘመን ይሁንላችሁ !

ነገ ለሚካሄደው የመንግሥት ምስረታ ለትራፊክ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች******************************የኢፌዴሪ የመንግስት ምስረታ ፕሮግራም በስኬት እንዲጠናቀቅ የፀጥታ አካላት አስ...
03/10/2021

ነገ ለሚካሄደው የመንግሥት ምስረታ ለትራፊክ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች
******************************

የኢፌዴሪ የመንግስት ምስረታ ፕሮግራም በስኬት እንዲጠናቀቅ የፀጥታ አካላት አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አጠናቀው ወደ ሥራ መግባታቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

በፕሮግራሙ ላይ ለመታደም በርካታ እንግዶች ወደ መዲናዋ እንደሚመጡ የጠቀሰው ፖሊስ እንግዶቹ በአጀብም ሆነ ለልዩ ልዩ ጉዳይ በሚንቀሳቀሱበት ወቅት ህብረተሰቡ በተለይ ደግሞ አሽከርካሪዎች ቅድሚያ በመስጠት የተለመደ ትብብራቸውን እንዲያደርጉ የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረኃይል ጠይቋል፡፡

የመንግስት ምስረታው ፕሮግራም በሚካሄድበት መስቀል አደባባይ አካባቢ ከዛሬ ጀምሮ ግራና ቀኝ በሁለቱም አቅጣጫዎች ለአጭርም ሆነ ለረጅም ጊዜ ተሸከርካሪን አቁሞ መሄድ ፍፁም የተከለከለ መሆኑን አስታውቋል፡፡

በነገው ዕለት ደግሞ ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ የመንግስት ምስረታው ፕሮግራም እስከሚጠናቀቅ ድረስ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት መንገዶች ለትራፊክ ዝግ እንደሚሆኑ ግብረኃይሉ አስታውቋል፡-

1. ከሚያዚያ 27 አደባባይ ወደ ውጪ ጉዳይ ሚ/ር
2. ከአዋሬ በአዋሬ ገበያ ወደ ፓርላማ
3. ከሴቶች አደባባይ ወደ ካሳንቺስ
4. ከሴቶች አደባባይ በእንድራሴ ሆቴል ወደ ካሳንቺስ ቶታል
5. ከ22 ወደ ቅዱስ ኡራኤል እንዲሁም ከኤድናሞል በአትላስ ሆቴል ወደ ቅዱስ ኡራኤል ቤተ-ክርስቲያን
6. ከአትላስ ሆቴል በደሳለኝ ሆቴል ሩዋንዳ
7. ከኤምፔሪያል ሆቴል ወደ ብራስ ሆስፒታል
8. ከገርጂ ኮሪያ ሆስፒታል ውስጥ ውስጡን ወደ ብራስ ሆስፒታል
9. ከጎሮ አዲሱ መንገድ መሄጃ ወደ ብራስ ሆስፒታል
10. ከቦሌ ሚካኤል ወደ ቀለበት መንገድ እንዲሁም ከቦሌ ሚካኤል ወደ ሩዋንዳ ማዞሪያ
11. ከካዲስኮ አደባባይ ወደ ቦሌ ሚካኤል ዋናው ቀለበት መንገድ
12. ከቡልቡላ ወደ ቦሌ ሚካኤል
13. ከመስቀል ፍላውር ወደ ጎርጎሪዮስ አደባባይ
14. ከጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ እንዲሁም ከጎተራ ወደ ወሎ ሰፈር አጎና ሲኒማ
15. ከጎፋ ማዛሪያ አዲሱ መንገድ መስቀለኛ ወደ ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያ ለገሃር
16. ከቡልጋርያ ማዞሪያ ወደ ገንት ሆቴል እንዲሁም ከቡልጋርያ ማዞሪያ ወደ አፍሪካ ህብረት አደባባይ
17. ከልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሜክሲኮ አደባባይ ወደ ለገሃር እንዲሁም ከከፍተኛ ፍርድ ቤት ኑር ህንፃ በባልቻ መስቀለኛ ወደ አረቄ ፋብሪካ
18. ከሞላ ማሩ ወደ ቅድስት ልደታ ቤተ-ክርስቲያን
19. ከተክለ ሃይማኖት በርበሬ በረንዳ ወደ ዲ-አፍሪክ ሆቴል
20. ከተክለ ሃይማኖት ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል
21. ከአብነት ፈረሳኛ በቀድሞ 5ኛ ፖሊስ ጣቢያ ጎማ ቁጠባ ወደ ብሔራዊ ቴአትር
22. ወሎ ሰፈር፣ ኦሎምፒያ፣ መስቀል አደባባይ ብሔራዊ ቤተ- መንግስት ግቢ ገብርኤል መታጠፊያ ሸራተን አዲስ አራት ኪሎ
23. ጎርጎሪዮስ አደባባይ

የጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ በዓለ ሢመት ነገ መስከረም 24 ቀን ማለዳ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲሁም ከቀኑ 7 ሰዓት ጀምሮ በመስቀል አደባባይ ከተለያዩ ሀገራት ጥሪ የተደረገላቸው...
03/10/2021

የጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ በዓለ ሢመት ነገ መስከረም 24 ቀን ማለዳ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲሁም ከቀኑ 7 ሰዓት ጀምሮ በመስቀል አደባባይ ከተለያዩ ሀገራት ጥሪ የተደረገላቸው የሀገር መሪዎች፣ ጠቅላይ ሚንስትሮች ከፍተኛ የመንግሥት ተወካዮች በሚገኙበት ይፈፀማል።
#እስካሁን :-
✔የቱርክ፣
✔የሕንድ፣
✔የቻይና፣
✔የናይጄሪያ፣
✔የአፍሪካ ኅብረት፣
✔የምሥራቅ አፍሪካ ሃገራትና የሌሎች ሃገራትም መሪዎችና ከፍተኛ ባለሥልጣናት እንደሚታደሙም ታውቋል። ለተጋባዥ እንግዶቹም ልዩ የእራት መርሐ ግብር በአድሱ መከላከያ ግብ ውስጥ እንደሚኖርም ተነግሯል። ለበዓለ ሢመቱ ሲባል መስቀል አደባባይ በልዩ ሁኔታ አሸብርቋል።

 ዓለምን በአመራር ሰጪነትህ ቀናተኞች ቢበዙም አስደምመሃል ። ውስብስብ ችግሮቻችንን ቢበዙም ልዩነትን ማገናዘብ ለሚችል አዕምሮ ለዉጡ ግልጽ ነው።ከምንም በላይ ጀምረህ ያሳየህን ተጨባጭ ስራዎች...
03/10/2021


ዓለምን በአመራር ሰጪነትህ ቀናተኞች ቢበዙም አስደምመሃል ። ውስብስብ ችግሮቻችንን ቢበዙም ልዩነትን ማገናዘብ ለሚችል አዕምሮ ለዉጡ ግልጽ ነው።ከምንም በላይ ጀምረህ ያሳየህን ተጨባጭ ስራዎች ተስፋ እንድጥልብህና ለኢትዮጵያውያን 1ኛም 2ኛም 3ኛም ምርጫችን ነህ።ባለፉት ሶስት ዓመታት የመሪነት ጊዜህ ✦ጠንካራ የህዝብ ተቋም እንገነባለን
✦ በህዝብ የተመረጠ መንግስት ይሾማል
✦ባትመርጡኝ በህዝብ ለተመረጠ ስልጣንን ለማስረከብ ዝግጁ ነኝ ስትል ዛሬ ዛሬ ያኔ ሰኔ 14 በማለዳ ያለቀስቃሽ ወጥቶ ድምጹን ለምትመራው ፓርቲ የሰጠ ህዝብ መስከረም 24 መንግስት ሊመሰረት ሰዓታት ሲቀሩ ካንተ የምጠብቀውን ምኞት በገፄ ላሰፍር ተገደድኩ ።


ዶክተር አብይ አህመድ
በልዩ የአመራር ብቃት የዚች ሀገር ጦስ እንደ ጎረቤት ሀገራት ከመበታተን ታድገሃል።በተሸረበው የክፋት ወጥመድ ልክ እርስ በእርስ ከመጠፋፋት አድነሃል ። ዛሬ ያ በህዝብ ካልተመረጥኩ ወንበር ላይ አልቀመጠም ያልከው አልፎ ተመርጠኻል። ካንተ አመራር እጅግ ተስፋ የምናረጋቸው እንደሚሳኩም እርግጠኛ የምንሆንበት ብዙ ነገር አለ። እንደለመድከው በነገው መንግስት ምስረታ እንደምታስደምመን አልጠራጠርም ።ነገ አዲስ የብርሃን ፀሀይ ለሀገሬ የምትወጣበት ቀን ነው። የብልጽግና መሰረት ስሩን የሚሰድበት ነው። አፍሪካውያን የራሳቸውን መሪ በራሳቸው ፍላጎት ያለምንም ጣልቃ ገብነት የሚያፀድቁበት ዕለት ይሆናል።ትክክለኛው የኢትዮጵያ ትንሣኤ በመደመር ፍልስፍና እውን የሚሆንበት ቀን ነው።የሰፊው ህዝብ ድምጽ የሚከበርበት ዕለት መስከረም ሃያ አራት ።
፪ሺህ፩፬

Via - Lalisa Befkadu Nagesso

"መዲናችን አዲስ አበባ ለዚህ ታሪካዊ ቀን ዝግጅቷን አጠናቃለች" - ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤበነገው ዕለት መስከረም 24 ለሚከናወነው አዲስ የመንግስት ምስረታ አዲስ አበባ ከተማ ዝግጅቷን ...
03/10/2021

"መዲናችን አዲስ አበባ ለዚህ ታሪካዊ ቀን ዝግጅቷን አጠናቃለች" - ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

በነገው ዕለት መስከረም 24 ለሚከናወነው አዲስ የመንግስት ምስረታ አዲስ አበባ ከተማ ዝግጅቷን ማጠናቀቋን የከተማዋ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አሳወቁ ።

የከተማዋ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ያስተላለፉት መልዕክት ፦

የነገው ቀን ፈጣሪ ለምድራችን ቃልኪዳን የገባልንን ከፍታ በክብር የሚጀምርበት ቀን ነዉ። መዲናችን አዲስ አበባም ለዚህ ታሪካዊ ቀን ዝግጅቷን አጠናቃለች።

ከመላዉ ህዝባችን ጋር እጅግ ብዙ አይነት ፈተና ያየንበት ፤ ብዙዎች የህይወት ዋጋ የከፈሉበት ፣ ገሚሱ በወቅታዊ ፈተና የወደቀበት ፣ የፈራም ወደኋላ የተመለሰበት/የካደበት ፣ በራስ ወዳድነት እና በጥቅማጥቅም ተጠልፈው የተንጠባጠቡበት፣ ጥቂቶች ቆራጦች ከእናት ጡት ነካሾች ጋር ኢትዮጵያን ለማዳን የተዋደቅንበት እና እዉነተኛ ወዳጆቻችንን ያወቅንበት ነው ። እነሆ ነገ አዲስ ምዕራፍ የሚጀምርበት ፤ ሕዝቡ በነቂስና በነፃነት የመረጠዉን መንግስት ነገ መስከረም 24 /2014 ዓ.ም ይመሰርታል።

ውድ የሃገሬ ልጆች በእርግጥ ያንን ሁሉ አልፈን ለዚህ አዲስ ምዕራፍ መድረሳችን በታሪካችን ልዩ ስፍራ አለው።
እንኳን ደስ አላችሁ!!

ለዚህ የዴምክራሲ ጭላንጭል በመላዉ አገራችን ለፈነጠቀበት ታላቅ ቀን ዋጋ የከፈላችሁ፤ እየከፈላችሁም ላላችሁ የኢትዮጵያ ሀቀኛ ልጆች ምንጊዜም ዘላለማዊ ክብርና ሞገስ ይገባችኋል !!

ስለ ኢሬቻ በዓል ምንነትና ለምን እንደሚከበር |========= #ኢሬቻ ማለት ማምለክ እና ማመስገን ማለት ነው፡፡ይሄን ስላደረግህልኝ፣ከክረምት ወደ በጋ (ብራ)ስላሸጋገርከኝ አመሠግናለሁ እየተ...
02/10/2021

ስለ ኢሬቻ በዓል ምንነትና ለምን እንደ
ሚከበር |
=========

#ኢሬቻ ማለት ማምለክ እና ማመስገን ማለት ነው፡፡
ይሄን ስላደረግህልኝ፣ከክረምት ወደ በጋ (ብራ)
ስላሸጋገርከኝ አመሠግናለሁ እየተባለ ፈጣሪ
የሚመሰገንበት ነው፡፡ ኢሬቻ ሠፊ አገልግሎቶች አሉት፡፡
መነሻውም በጣም የራቀ ነው፡፡ ሠው ማምለክ
ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ የመጣ ነው።በተለይ የኦሮሞን
ብሔር ጨምሮ #በኩሽቲክ የቋንቋ ክፍል ውስጥ
የሚጠቃለሉ ብሄሮች ሃይማኖቶች ከመምጣታቸው
በፊት ኢሬቻ (እርጥብ ሣር) ይዘው ነው ፈጣሪያቸውን
የሚለማመኑት፡፡
ለጋብቻ ጥያቄ በራሱ (ኢሬቻ) እርጥብ ሣር አገልግል
ውስጥ ተጨምሮ ነውየሚላከው፡፡ እንግዲህ እነዚህን
ነገሮች በምናይበት ጊዜ ኢሬቻ ሃይማኖታዊ ዳራ ያለው
መሆኑን እንገነዘባለን፡፡ ድሮ ሠዎች መልዕክተኛ ሲልኩ
እርጥብ ሣርቆርጠው በመስጠት፣ “አደራህን በፈጣሪ
ስም ይህን መልዕክት አድርስልኝ”ብለው ይልኩታል፡፡
እንግዲህ ቃል በቃል ሲገለፅ፤ ኢሬቻ ሣር ወይም
የተመረጡ ዛፎች ቅጠል ማለት ነው፡፡
እምነቱ ምንድን ነዉ?
========
የሃይማኖቱ ስም #ዋቄፈና ነው፡፡ የእምነቱ ተከታይ
#ዋቄፈታ ነው የሚባለው፡፡ከዋቄፈና ሃይማኖታዊ በአላት
አንዱ ኢሬቻ ነው፤ ሌሎችም ብዙ በአላት አሉ፡፡ሌላው
ከዚህ ሃይማኖታዊ በአል ጋር በልማድ አብሮ
ተቀላቅሎ የሚከወን ነገር አለ፡፡ ለምሣሌ ቡና
ማፍላት፣ ዛፍ ቅቤ መቀባት፣ ስለት ማግባት፣ ሽቶ ውሃ
ውስጥ መወርወር የመሣሠሉ አሉ፡፡ እነዚህ ሁሉ በግለሰቦች የሚደረጉ
#ልማዶች ናቸው እንጂ #የሃይማኖቱ መርሆች
የሚያዛቸው አይደሉም፡፡ ሃይማኖቱ #በጭራሽ እነዚህን
ነገሮች አይፈቅድም። የኦሮሞ ህዝብ የተለያዩ
ሃይማኖቶች ተከታይ ነው፡፡ በክርስትናውም
በእስልምናውም ሃይማኖት ውስጥ ያሉ አሉ፡፡
እነዚህ እንዴት ነው የዚህ በአል ተሣታፊ የሚሆኑት?

የበዓሉ አከባበር ምን ይመስላል?
=======
የኦሮሞ ህዝብ በየቦታው ያለና ሠፊ ስለሆነ የበአሉ
#ትውፊታዊ አከባበር ወጥነትየለውም፡፡ የተለያዩ
ክዋኔዎች ይንፀባረቃሉ፡፡ በአከባበርም ይለያያሉ፡፡
መሠረታዊ ስርአቱ ግን እሬቻ (እርጥብ ሣር) ይይዛሉ፣
በእለቱ የሚዘመሩ መዝሙሮች ይኖራሉ። ነገር ግን
እነዚህ መዝሙሮች በቱለማ፣ በሜጫ እንዲሁም
በቦረና የተለያዩ ናቸው፡፡ ዋናው ነገር ግን መዝሙሩን
እየዘመሩ ወደ “መልካ” (ወንዝ)ይሄዳሉ፡፡ እዚያም
ሲደርሡ “በክረምት ወቅት ያሉትን ተግዳሮቶች
አሣልፈህ ለዚህ ላደረስከን በጣም እናመሠግናለን”
ይላሉ፡፡ በዚያው ቀንም ግለሠቦችኢሬቻውን ይዘው
የጐደለባቸውን ለፈጣሪያቸው በፀሎት እየነገሩ
መለመን ይችላሉ፡፡ #መልካው (ወንዙ) ምልክትነቱ
ከዚህ በኋላ በጋ ሆኗል፣ ወንዙም ጎድሏል፤ ዘመድ
ከዘመድ ወንዝ እየተሻገረ መጠያየቅ ይችላል ብሎ
የሚገልፅነው፡፡ በእለቱ ሽማግሌዎች ሃይማኖታዊ
ንግግሮች ያደርጉና በድሮው ባህል እርድ ይኖራል፣
ይበላል ይጠጣና ፈጣሪን በተለያዩ ጨዋታዎች
እያመሠገኑ ወደየ መጡበት ይመለሣሉ ማለት ነው፡፡
ሃይማኖቱን የሚመሩት እነማን ናቸው?
ምዕመናኑ #“ሚሤንሣ” ይባላሉ፡፡ በገልማ (ቤተ-
አምልኮ) ውስጥ በዝማሬ አገልግሎት የሚሠጡት #ዋዩ
ይባላሉ፡፡ የሚባሉት ደግሞ ፀሎት
አድራሽናቸው፡፡ #ሉባ የሚባለው የተለያዩ የአስተዳደር
አመራር ቦታዎችን የሚያከፋፍል ነው፡፡ ቀጥሎ
የሚመጣው #ጉላ ነው፡፡ #ጉላ ከተጠቀሡት በላይ ሆኖ
በማዕከላዊ ደረጃ ሃይማኖቱን የሚመራ ነው፣ ይህ
ግለሠብ በሃይማኖቱ ላይ #ከ13 አመት በላይ ያገለገለ
መሆን ይኖርበታል፡፡ በሌላ በኩል በገዳ ባህላዊ
አስተዳደራዊ ስርአት በኩልም የሚመጣ የጐላ ደረጃ
አለ፡፡ የመጨረሻው ደረጃ ይባላል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በኢትዮጵያ እርምጃ መደንገጣቸውን ገለጹየተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ ኢትዮጵያ የተቋማቸው ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችን ከአገር እንዲወ...
30/09/2021

የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በኢትዮጵያ እርምጃ መደንገጣቸውን ገለጹ
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ ኢትዮጵያ የተቋማቸው ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችን ከአገር እንዲወጡ መወሰኗ "አስደንግጦኛል" ሲሉ ሐሙስ ምሽት ባወጡት መግለጫ አስታወቁ።

ዋና ፀሐፊው አንቶኒዮ ጉቴሬዝ የኢትዮጵያ መንግሥት በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተቋማት ውስጥ በተለያዩ ኃላፊነቶች ላይ የሚገኙ ሰባት ግለሰቦች በአስቸኳይ አገሪቱን ለቀው እንዲወጡ ማዘዙ ተከትሎ ነው የተሰማቸውን የገለጹት።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የመንግሥት ውሳኔውን በተመከተ ለመንግሥታቱ ድርጅት በጻፈው ደብዳቤ ላይ ግለሰቦቹ በአገሪቱ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ገብተዋል በማለት በ72 ሰዓታት ከኢትዮጵያ እንዲወጡ አዟል።

ዋና ፀሐፊው በመግለጫቸው ሁሉም የተባበሩት መንግሥታት ሰብዓዊ ተግባራት የሚመሩት በሰብዓዊነት፣ ከአድልዎ ነጻ በሆነ መንገድ፣ በገለልተኛነት እና በነጻነት መሆኑን አስታውሰው፤ በዚህም ድርጅታቸው በኢትዮጵያ በችግር ላይ ላሉ ሰዎች ምግብ፣ መድኃኒት፣ ውሃ እና ንጽሕና መጠበቂያ የመሳሰሉ ሕይወት አድን እርዳታዎችን እያቀረበ ይገኛል ብለዋል።

"የመንግሥታቱ ድርጅት ሠራተኞችም ይህን በኢትዮጵያ እየተገበሩ ስለመሆኑ ሙሉ እምነት አለኝ" በማለት፤ ተመድ ሰብዓዊ እርዳታን የሚጠብቁ ኢትዮጵያውያንን ለመርዳት ጽኑ ፍላጎት እንዳለው ገልጸው።

ዋና ፀሐፊ ጉቴሬዝ "የሚመለከታቸው የመንግሥታቱ ድርጅት ሠራተኞች አስፈላጊ ሥራቸውን እንዲቀጥሉ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር እየተነጋገርን ነው" ብለዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ግለሰቦቹን በተመከተ ለመንግሥታቱ ድርጅት በጻፈው ደብዳቤ ላይ ግለሰቦቹ በአገሪቱ ውስጥ ጉዳይ ውስጥ ጣልቃ ገብተዋል ያለ ሲሆን በ72 ሰዓታት ከኢትዮጵያ እንዲወጡም አዟል።

መንግሥት በ72 ሰዓታት ውስጥ ከአገር እንዲወጡ ያዘዘው

የተባበሩት መንግሥታት የሕጻናት አድን የኢትዮጵያ ተወካይ አደል ኾደር

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ እርዳታ መስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ማርሲ ቪጎዳ

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ እርዳታ መስተባበሪያ የጽህፈት ቤቱ የሰላምና ልማት አማካሪ ክሰዌሲ ሳንስኩሎቴ

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ እርዳታ መስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ምክትል ኃላፊ ሳኢድ ሞሐመድ ሄርሲ

የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብት ድርጅት የክትትል፣ የሪፖርት እና አድቮኬሲ ቡድን መሪ የሆኑት ሶኒ ኦንዬግቡላ

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በኢትዮጵያ ምክትል የሰብዓዊ እርዳታ አስተባባሪ የሆኑት ግራንት ሌኢተይ እና

የተባበሩት መንግሥታት ተጠባባቂ የሰብአዊ እርዳታ አስተባባሪ ጋዳ ኤልታሂር ሙዳዊ ናቸው።
ምንጭ BBC News Amharic

የኢሬቻ በአል ቅዳሜ በአዲስ አበባ እና እሁድ በቢሾፍቱ /ደብረዘይት/ በድምቀት ይከበራል።እንኳን አደረሳችሁከፀጥታ ስራ ጋር በተያያዘ ነገ በመስቀል አደባባይ እና ዙሪያው የሚገኙ መንገዶች ለተ...
30/09/2021

የኢሬቻ በአል ቅዳሜ በአዲስ አበባ እና እሁድ በቢሾፍቱ /ደብረዘይት/ በድምቀት ይከበራል።

እንኳን አደረሳችሁ

ከፀጥታ ስራ ጋር በተያያዘ ነገ በመስቀል አደባባይ እና ዙሪያው የሚገኙ መንገዶች ለተወሰነ ሰዓት ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ
**************************

ከፀጥታ ስራ ጋር በተያያዘ ነገ በመስቀል አደባባይ እና ዙሪያው የሚገኙ መንገዶች ለተወሰነ ሰዓት ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፤ ህብረተሰቡ ይህንን ተገንዝቦ የተለመደ ትብብሩን እንዲያደርግ ጥሪ ተላልፏል።

የከተማችንን ሰላምና ፀጥታ ለማስጠበቅ የፀጥታ አካላት ልዩ ልዩ ተግባራትን እያከናወኑ ይገኛል፡፡ በዚህም አበረታች ውጤት ማግኘት ተችሏል ያለው ፖሊስ፤ ዓርብ መስከረም 21 ቀን 2014 ዓ.ም ከጧቱ 3:00 ሰዓት ጀምሮ ከፀጥታ ስራ ጋር በተያያዘ ለሚከናወን ተግባር በመስቀል አደባባይ እና በዙሪያው የሚገኙ መንገዶች ለተወሰነ ሰዓት ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

በዚህም መሰረት፦

• ከቦሌ አየር መንገድ በሚሊኒዬም አዳራሽ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ወሎ ሰፈር አደባባይ

• ከመገናኛ ወደ መስቀል አደባባይ የሚውስደው መንገድ 22 ማዞሪያ

• ከ4ኪሎ በውጭ ጉዳይ ሚ/ር ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ፓርላማ መብራት

• በቸርችር ጎዳና ፒያሳ ወደ መስቀል የሚወስደው መንገድ ቴዎድሮስ አደባባይ

• ከጦር ሃይሎች በለገሃር ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት

• ከጀሞ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ የሚወስደው መንገድ ሳር ቤት አደባባይ

• ከሳሪስ ፣ በጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ አጎና
ሲኒማ
• ከቦሌ ፣ አትላስ ቅዱስ ዑራኤል ቤ/ከርስቲያን የሚወስደው መንገድ ኤድናሞል አደባባይ

• ከአዋሬ ወደ ካሳንቺስ የሚወስደው መንገድ ሴቶች አደባባይ

• ከልደታ በጌጃ ሰፈር ፣ ጤና ጥበቃ የሚወስደው መንገድ አብነት ፈረሰኛ አካባቢ

ነገ መስከረም 21 ቀን 2014 ዓ/ም ዓርብ ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ ለጊዜው መንገዶቹ ለተሽከርካሪ ዝግ መሆናቸውን ህብረተሰቡ ተገንዝቦ የተለመደውን ትብብር እንዲያደርግ የአዲስ አበባ ፖሊስ መልእክቱን አስተላልፏል፡፡

29/09/2021

Wel-come to our New page
ፈገግታ የሬዲዮ ፕሮግራም አዲስ ገፅ/page

Address

Addis Ababa

Telephone

+251973407717

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Fegegeta radio show/ፈገግታ የራዲዮ ፕሮግራም posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share