𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨 𝐙𝐞𝐧𝐚 𝐎𝐟𝐟𝐢𝐜𝐚𝐥

  • Home
  • Ethiopia
  • Addis Ababa
  • 𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨 𝐙𝐞𝐧𝐚 𝐎𝐟𝐟𝐢𝐜𝐚𝐥

𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨 𝐙𝐞𝐧𝐚 𝐎𝐟𝐟𝐢𝐜𝐚𝐥 "ላይክ በማድረግ እዉነተኛናትኩስ መረጃዎችን ያግኙ"

“የሕወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴና ማዕከላዊ የቁጥጥር ኮሚሽን የሕወሃት ጠቅላላ ጉባዔ በኹለት ወራት ውስጥ እንዲካሄድ መወሰናቸውን ፓርቲው አስታውቋል። ፓርቲው፣ የኹለቱ አካላት የጋራ መድረክ የጉባዔ...
25/02/2024

“የሕወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴና ማዕከላዊ የቁጥጥር ኮሚሽን የሕወሃት ጠቅላላ ጉባዔ በኹለት ወራት ውስጥ እንዲካሄድ መወሰናቸውን ፓርቲው አስታውቋል።

ፓርቲው፣ የኹለቱ አካላት የጋራ መድረክ የጉባዔውን አጀንዳ መምረጣቸውንም ገልጧል። ፓርቲው ጨምሮም፣ በመጪው ሳምንት በክልል ደረጃ የዞንና የወረዳ ከፍተኛ ካድሬዎች ስብሰባና ከዚያም በዞን፣ ወረዳና ጣቢያ ደረጃ የአመራር፣ የአባላትና የሕዝብ ተወካዮች መድረክ ለማካሄድ ከውሳኔ ተደርሷል ብሏል። ምርጫ ቦርድ ሕወሃትን ከሕጋዊ ፓርቲነት የሰረዘበት ውሳኔ ግን እስካኹን እንደጸና ነው።

“በአማራ ክልል በተፈጸመ የድሮን ጥቃት በጥቂቱ 30 ንጹሃን መገደላቸው ተነገረ።በክልሉ ሰሜን ሸዋ ዞን ሳሲት በተባለችው ከተማ አቅራቢያ 50 ሰዎችን ያሳፈረ አይሱዙ ተሽከርካሪ መንገደኞችን ለ...
25/02/2024

“በአማራ ክልል በተፈጸመ የድሮን ጥቃት በጥቂቱ 30 ንጹሃን መገደላቸው ተነገረ።

በክልሉ ሰሜን ሸዋ ዞን ሳሲት በተባለችው ከተማ አቅራቢያ 50 ሰዎችን ያሳፈረ አይሱዙ ተሽከርካሪ መንገደኞችን ለማውረድ በቆመበት ተፈጽሟል በተባለው ጥቃት 18 ሰዎች መቁሰላቸውንም ነው የአይን እማኞችን የጠቀሰው የሪሊፍ ዌብ ዘገባ የሚያሳየው።

የድሮን ጥቃቱ ሲፈጸም በአካባቢው በመከላከያ ሰራዊትና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ጦርነት እንዳልነበር የተናገሩት ነዋሪዎች፥ ጥቃቱ ከተፈጸመ በኋላም ድሮኖች በአካባቢው ሲንቀሳቀሱ እንደነበር ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በአማራ ክልሉ ግጭት ድሮኖችን በስፋት እየተጠቀመ መሆኑን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን በቅርቡ ባወጣው መግለጫ ማሳወቁ ይታወሳል።

“የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የቲክቶክ አካውንት ከፍተው ቪዲዮ ማጋራት ጀምረዋልፕሬዝዳንቱ ቲክቶክ በመንግስት ተቋማት ጥቅም ላይ እንዳይውል የሚያግድ ህግ ላይ ፊርማቸውን ማኖራቸው ይታወሳ...
13/02/2024

“የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የቲክቶክ አካውንት ከፍተው ቪዲዮ ማጋራት ጀምረዋል

ፕሬዝዳንቱ ቲክቶክ በመንግስት ተቋማት ጥቅም ላይ እንዳይውል የሚያግድ ህግ ላይ ፊርማቸውን ማኖራቸው ይታወሳል።

የቻይናው ባይትዳንስ ኩባንያ ንብረት የሆነው ቲክቶክ የደህንነት ስጋት ደቅኗል በሚል ያሳለፉት ውሳኔን ተከትሎ በርካታ የፌደራል ተቋማት ይህን መተግበሪያ በቢሮ ውስጥ መጠቀም መከልከላቸው አይዘነጋም።

““ኢንተርኔት‼️‼️➖➖➖➖➖➖➖➖➖ኢንተርኔት የተመለሰላቸው የፖርት ሱዳን ነዋሪዎች ደስታቸው እየገለጹ ነው‼️በእርስ በእርስ ጦርነት ውስጥ በምትገኘው ሱዳን ምሥራቃዊ አቅጣጫ ባለችው ፖርት ሱዳ...
13/02/2024

““ኢንተርኔት‼️‼️
➖➖➖➖➖➖➖➖➖
ኢንተርኔት የተመለሰላቸው የፖርት ሱዳን ነዋሪዎች ደስታቸው እየገለጹ ነው‼️
በእርስ በእርስ ጦርነት ውስጥ በምትገኘው ሱዳን ምሥራቃዊ አቅጣጫ ባለችው ፖርት ሱዳን፣ ኢንተርኔት የተመለሰላቸው ነዋሪዎች ደስታቸውን አደባባይ ወጥተው በጭፈራ እየገለጹ እንደሚገኙ በሥፍራው የምትገኘው የስካይ ኒውስዋ ዩስራ ኤልባጊር ዘግባለች።

አስር ወራት በተሻገረው የሱዳን ጦርነት፣ አንደኛው ተፋላሚ የአገሪቱ ጦር መሪ ጀነራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን በአሁኑ ሰዓት መቀመጫቸውን ያደረጉት በፖርት ሱዳን ነው።

“አሜሪካ የሰሜን ኮሪያ ሚሳይል ጥቃት የኪም አስተዳዳር ማብቃያ ይሆናል ስትል አስጠነቀቀችሰሜን ኮሪያ ደቡብ ኮሪያ፣ ጃፖን እና አሜሪካ ሊደርሱ የሚችሉ በርካታ የረጅም ርቀት ሚሳይሎች ሰርታ ሞ...
17/12/2023

“አሜሪካ የሰሜን ኮሪያ ሚሳይል ጥቃት የኪም አስተዳዳር ማብቃያ ይሆናል ስትል አስጠነቀቀች

ሰሜን ኮሪያ ደቡብ ኮሪያ፣ ጃፖን እና አሜሪካ ሊደርሱ የሚችሉ በርካታ የረጅም ርቀት ሚሳይሎች ሰርታ ሞክራለች

በመዲናዋ ከ900 በላይ በሚሆኑ ህገወጥ የስፖርት ውርርድ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ‼️በ   በተለያዩ ክፍለ ከተሞች በተደረገ የክትትልና የቁጥጥር ስራ በህገወጥ ተግባር ላይ በተሰማሩ 926 የ...
17/12/2023

በመዲናዋ ከ900 በላይ በሚሆኑ ህገወጥ የስፖርት ውርርድ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ‼️
በ በተለያዩ ክፍለ ከተሞች በተደረገ የክትትልና የቁጥጥር ስራ በህገወጥ ተግባር ላይ በተሰማሩ 926 የስፖርት ውርርድ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ፡፡

በእነዚህ የስፖርት ውርርድ ቤቶች ውስጥ ህገወጥ ተግባር እንደሚፈፀምና በነዋሪዎች ላይ እንዲሁም በትምህርት ቤቶች አካባቢ ሁከት እየፈጠሩ እንደሚገኙ የህዝብ ቅሬታ በመቅረቡ የአዲስ አበባ ፖሊስ፣ የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ፣ የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ እና የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን እርምጃ ወስደዋል ሲል ኢፕድ ዘገቧል።

ውርርድ ቤቶቹ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ሳይኖራቸው ማጫወት፣ ዕድሜያቸው 21 አመት ያልሞላቸው ባለመከልከል፣ ከትምህርት ቤቶችና ከእምነት ተቋማት አካባቢ እንዲርቁ የተቀመጠላቸውን ወሰን ባለመጠበቃቸው እና ጫት የማስቃም ህገ ወጥ ተግባራት መፈጸማቸው ተገልጿል።

በዚህም ምክንያት በጉለሌ ክፍለ ከተማ 152፣ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ 173፣ በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ 167፣ በልደታ ክፍለ ከተማ 49፣ በየካ ክፍለ ከተማ 87፣ በቦሌ ክፍለ ከተማ 276፣ በአቃቂ ክፍለ ከተማ 22 ህገወጥ የስፖርት ውርርድ ቤቶች ተሽገዋል ተብሏል።

31/07/2023

“ሩሲያ በሳኡዲ አረቢያ ይካሄዳል የተባለውን ንግግር አላማ መረዳት እፈልጋለሁ አለች

በሳኡዲ በዩክሬን ጉዳይ ይካሄዳል በተባለው ንግግር ላይ ምዕራባውያን ሀገራት፣ ዩክሬን እና ዋናዋና በማደግ ላይ ያሉ ሀገራት መጋበዛቸው ተገልጿል። ነገርግን ሩሲያ ለንግግሩ አልተጋበዘችም።

“ፑቲን ከዩክሬን ጋር የሚደረግ ንግግርን እንደማይቃወሙ ገለጹ"እየተገበሩ ያሉ የሰላም እቅዱአንቀጾች አሉ። ነገርግን የተወሰኑ አስቸጋሪ ወይም ለመግበር የሚያስቸግሩ ነገሮች አሉ።" ብለዋል ፑቲ...
30/07/2023

“ፑቲን ከዩክሬን ጋር የሚደረግ ንግግርን እንደማይቃወሙ ገለጹ

"እየተገበሩ ያሉ የሰላም እቅዱአንቀጾች አሉ። ነገርግን የተወሰኑ አስቸጋሪ ወይም ለመግበር የሚያስቸግሩ ነገሮች አሉ።" ብለዋል ፑቲን።
ሙሉውን ያንብቡ፦

የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ መሪ ለቀጠለው ግጭት የሱዳን ህዝብን ይቅርታ ጠየቁየሱዳን ፈጥኖ ደራሽ መሪ ጄኔራል መሀመድ ሃምዳን ዳጋሎ (ሄሚቲ) በጦርነቱ ተመተው ቆስለዋል፤ ሞተዋል የሚባሉ ወሬዎች ሲወ...
30/07/2023

የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ መሪ ለቀጠለው ግጭት የሱዳን ህዝብን ይቅርታ ጠየቁ

የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ መሪ ጄኔራል መሀመድ ሃምዳን ዳጋሎ (ሄሚቲ) በጦርነቱ ተመተው ቆስለዋል፤ ሞተዋል የሚባሉ ወሬዎች ሲወራባቸው ቢቆይም ከረጅም ጊዜ መሰወር በኋላ ብቅ ብለዋል።

በፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ በማበረዊ ትስስር ገጽ የተለቀቀው ቪዲዮ፤ ጄኔራል መሀመድ ሃምዳን ዳጋሎ (ሄሚቲ) ለቀጠለው ግጭት የሱዳን ህዝብን ይቅርታ ጠይቀዋል።

"ጦር ኃይሎች ላሉ ወንድሞቻችን አፋጣኝ መፍትሄ ከፈለጋችሁ፤ አመራራችሁን ቀይራችሁ በ72 ሰዓት ውስጥ ስምምነት ላይ እንደርሳለን" ብለዋል።

“አፍሪካ አዲስ የሀይል ማዕከል እየሆነች ነው”- ፕሬዝዳንት ፑቲንየሩሲያ ፕሬዝዳንት በሩሲያ አፍሪካ ጉባዔ መዝጊያ ላይ ባደረጉት ንግግር የአፍሪካ የኢኮኖሚ እና ፖለቲካ ሚና እያደገ መጥቷል ማ...
30/07/2023

“አፍሪካ አዲስ የሀይል ማዕከል እየሆነች ነው”- ፕሬዝዳንት ፑቲን

የሩሲያ ፕሬዝዳንት በሩሲያ አፍሪካ ጉባዔ መዝጊያ ላይ ባደረጉት ንግግር የአፍሪካ የኢኮኖሚ እና ፖለቲካ ሚና እያደገ መጥቷል ማለታቸውን አርቲ ዘግቧል።

"የምዕራባዊያን ሀገራት ተጽዕኖ በተቃራኒው እየቀነሰ መጥታል" ያሉት ፕሬዝዳንቱ "አፍሪካ አዲስ የሀይል ማዕከል እየሆነች ነው" ሲሉም አክለዋል።

ይሁንና በአፍሪካ አሁንም የቅኝ ግዛት አመለካከት አልተወገደም የሚሉት ፕሬዝዳንት ፑቲን ይህ አመለካከት በቀድሞ ቅኝ ገዢ ሀገራት በግልጽ ይንጸባረቃልም ብለዋል።

“የዋግነሩ አዛዥ የቨግኒ ፕሪጎዚን ከቤላሩስ ወደ ሩሲያ ተመለሱአዛዡ ከሩሲያ ጦር ጋር ግጭት ውስጥ መግባታቸውን ተከትሎ የመፈንቅለ መንግሥት ክስ ቀርቦባቸው ነበር
06/07/2023

“የዋግነሩ አዛዥ የቨግኒ ፕሪጎዚን ከቤላሩስ ወደ ሩሲያ ተመለሱ

አዛዡ ከሩሲያ ጦር ጋር ግጭት ውስጥ መግባታቸውን ተከትሎ የመፈንቅለ መንግሥት ክስ ቀርቦባቸው ነበር

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የትግራይ ህዝብን ይቅርታ ጠየቀችቤተክርስቲያኗ ዘጠኝ ኤጲስ ቆጶሳትን መምረጧን ገልጻለች። የተመረጡት ኤጲስ ቆጶሳት ከ10 ቀናት በኋላ በዓለ ሲመታ...
06/07/2023

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የትግራይ ህዝብን ይቅርታ ጠየቀች

ቤተክርስቲያኗ ዘጠኝ ኤጲስ ቆጶሳትን መምረጧን ገልጻለች። የተመረጡት ኤጲስ ቆጶሳት ከ10 ቀናት በኋላ በዓለ ሲመታቸው ይፈጸማል ተብሏል።

“እስራኤል ጦሯን ከዌስትባንኳ ጀኒን ማስወጣት ጀመረችበሁለት ቀናቱ ዘመቻ 13 ፍልስጤማውያን የተገደሉ ሲሆን በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል።
05/07/2023

“እስራኤል ጦሯን ከዌስትባንኳ ጀኒን ማስወጣት ጀመረች

በሁለት ቀናቱ ዘመቻ 13 ፍልስጤማውያን የተገደሉ ሲሆን በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል።

ኢቢሲ በጉማ አዋርድ ላይ ግንባሯን በጥይት መመታቷንና አፏን በሽቦ መለጎሟን በሚያሳይ ሜካፕ የቀረበችውን ፍላጎት አብርሃምን ከስራ አገደ‼️ሰኔ 2/2015 ምሽት በአዲስ አበባ ስካይላይት ሆቴል...
05/07/2023

ኢቢሲ በጉማ አዋርድ ላይ ግንባሯን በጥይት መመታቷንና አፏን በሽቦ መለጎሟን በሚያሳይ ሜካፕ የቀረበችውን ፍላጎት አብርሃምን ከስራ አገደ‼️
ሰኔ 2/2015 ምሽት በአዲስ አበባ ስካይላይት ሆቴል በተካሄደው 9ኛው የጉማ ሽልማት ላይ የወገኗን መታፈን በሜካፕ ያሳየችው የቴሌቭዥን ፕሮግራም አዘጋጇና ታዋቂ ቲክቶከሯ ፍላጎት አብርሃም/የልጅ ማኛ/ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን /ኢቢሲ/ ከነበራት የኢትዮጵያን አይዶል የዳኝነት ስራዋ ተሰናብታለች።
ፍላጎት ከዚህ በፊት በአትዮጵያ ብሮድካስት ኮርፖሬሽን የተሰጥኦ ውድድር /ኢትዮጵያን አይዶል/ ላይ በዳኝነት ስራ ቀረፃዎችን ከውና እንዲሁም ከሚዲያው ጋር ውል ተዋውላ ነበር።
ይሁን እንጂ ተቋሙ አዲስ በገነባውና ነገ በሚያስመርቀው የሚዲያ ኮምፕሌክስ ህንፃ ዛሬ ምሽት በጀመረው የኢትዮጵያን አይዶል ውድድር ላይ በፍላጎት ቦታ ከዚህ ቀደም በውድድሩ የዳኝነት ስራ ላይ ያልነበረው አርቲስት ሰራዊት ፍቅሬ ተተክቷል።
ሚዲያው ፍላጎትን ከዚህ ስራዋ ያገደበትን ምክንያት በግልፅ ማወቅ ባይችሉም ፣ በጉማ አዋርድ ላይ በሜካፕ ባስተላለፈችው መልዕክት ሳይሆን እንዳልቀረ ተገምቷል።

በሐዋሳ ከተማ ግብረሰዶማዊነትን የሚያወግዝ ሰልፍ ተካሄደ‼️በትናንትናው እለት በሲዳማና በደቡብ ክልሎች መቀመጫ በሐዋሳ ከተማ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ/ግብረሰዶማዊነትን/ እና ጽንስ ማቋረጥን የሚ...
05/07/2023

በሐዋሳ ከተማ ግብረሰዶማዊነትን የሚያወግዝ ሰልፍ ተካሄደ‼️
በትናንትናው እለት በሲዳማና በደቡብ ክልሎች መቀመጫ በሐዋሳ ከተማ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ/ግብረሰዶማዊነትን/ እና ጽንስ ማቋረጥን የሚያወግዝ ሰልፍ ተካሒዷል።

ሰልፉን ያዘጋጁት በከተማዋ ከሚገኙ 22 የቃለ ሕይወት አጥቢያ ቤተ-ክርስቲያናት የተውጣጡ ምዕምናን ናቸው። ሠልፈኞቹ ከትላንት በስቲያ እሁድ በከተማዋ ዋና ዋና ጎዳናዎች እየተዘዋወሩ ባሰሙት መፈክር የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ እና ጽንስ ማቋረጥን አውግዘዋል።
ሠልፈኞቹ በተመሳሳይ ፆታዊ ግንኙነት እና በውርጃ ላይ ያላቸውን ተቃውሞ ያሰሙት የጹሁፍ መልዕክቶችን በማንገብና መፈክሮችን በማሰማት ነው ፡፡ ሠልፈኞቹ ካሰሟቸው መፈክሮች መካከል “ ግብረ ሶዶማዊነትን እንቃወማለን “ ፣ “ ጽንስ ሕይወት አለው “ ፤ “ ህይወትን መግደል ሀጢያት ነው “ የሚሉ ይገኙባቸዋል ፡፡

የተቃውሞ ሠልፉን ያካሄዱት በሀዋሳ ከተማ ከ22 የቃለ ህይወት አጥቢያ ቤተክርስቲያናት የተሰባሰቡ ምዕመናን መሆናቸውን ከሠልፉ አስተባባሪዎች አንዱ መጋቢ ፍፁምዘለቀ ይናገራሉ ፡፡
ሠልፉ ያስፈለገበት ምክንያትም አገር ፣ ከተማ ፣ ህዝብ እንዲነቃ ለማድረግ መሆኑን የገለጹት መጋቢ ፍፁም “ ህዝቡ ጉዳዩን እንደተራ ነገር ሊያየው አይገባም ፡፡ አስከፊነቱን ሊረዳ ይገባል ፡፡ አዲስ ነገር አይደለም እየተባለ በማህበረሰቡ ውስጥ ሥፍራ እያገኘ ወጣቶችንም ከመንገድ እያስቀረ ይገኛል ፡፡ ሠልፉ ህብረተሰቡ ይህን እንዲውያቅ ለማድረግ የታሰበ ነው “ ብለዋል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር የተለያዩ ውሳኔዎች አሳለፈ******************************ትምህርት ሚኒስቴር የተለያዩ ውሳኔዎች አሳልፏል።ትናንት የተሰጡት የሬሜዲያል ፕሮግራም ፈተናዎች መሰ...
04/07/2023

ትምህርት ሚኒስቴር የተለያዩ ውሳኔዎች አሳለፈ
******************************

ትምህርት ሚኒስቴር የተለያዩ ውሳኔዎች አሳልፏል።

ትናንት የተሰጡት የሬሜዲያል ፕሮግራም ፈተናዎች መሰረዛቸውን የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

የ2014 ዓ.ም 12ኛ ክፍል ረሜዲያል ተጠቃሚ ተማሪዎች ፈተና ትናንት ሰኔ 26/2015 ዓ.ም በዩኒቨርስቲዎች መሰጠት መጀመሩ ይታወቃል።

ይሁን እንጂ በፈተና ሂደት በተፈጠሩ ችግሮች ምክንያት የትምህርት ሚኒስቴር የሚከተሉትን ውሳኔዎች ያሳለፈ መሆኑን እንገልጻለን።

1) ሰኔ 26/2015 የተሰጡት የሬሜዲያል ፕሮግራም ፈተናዎች ተሰርዘው ተማሪዎች በቀሩት የትምህርት ዓይነቶች ብቻ እንዲመዘኑ

2)ቀደም ብሎ በሁሉም ሬሜዲያል ፕሮግራም ተጠቃሚ ተማሪዎች ባላቸው ተቋማት ፈተናውን በአንድ ጊዜ ለመስጠት የታቀደው ተሻሽሎ በተለይም ከ150 በላይ የሆኑና ከ200 በላይ ካምፓስ ያላቸውን የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፈተና ቀርቶ ወደ ፊት በሚወሰን አግባብ ፈተናው በመስከረም ወር 2016 ዓ.ም እንዲሰጥ

3 በመንግስት ተቋማት የሬሜዲያል ፕሮግራም ተጠቃሚ የሆኑትን ተማሪዎች በተያዘው ፕሮግራም መሰረት የሚሰጥ መሆኑን እንገልጻለን።

 #ትግራይ‼➖➖➖➖➖➖➖➖➖በትግራይ ክልል በጦርነቱ "በእያንዳንዱ ቤት" የደረሰውን ሰብዓዊ ቀውስ የሚያሳይ ጥናት ሊወጣ ነውበትግራይ ክልል አጠቃላይ ውድመቱን በቁጥር የሚገልጽ ጥናት እያደረገ ...
03/07/2023

#ትግራይ‼
➖➖➖➖➖➖➖➖➖
በትግራይ ክልል በጦርነቱ "በእያንዳንዱ ቤት" የደረሰውን ሰብዓዊ ቀውስ የሚያሳይ ጥናት ሊወጣ ነው

በትግራይ ክልል አጠቃላይ ውድመቱን በቁጥር የሚገልጽ ጥናት እያደረገ መሆኑን ጊዜያዊ አስተዳደሩ ለአል ዐይን አማርኛ ገልጿል።

በሰሜኑ ጦርነት ሰብዓዊ ቀውሱን የሚገልጽ መረጃ በመንግስት በኩል ይፋ ባይደረግም፤ ቁሳዊ ውድመቱና ኪሳራው ግን 28 ቢሊዮን ዶላር መሆኑ ተነግሯል።
ያድርጉ

“የልጄን ሕይወት በአንድ ሚሊዮን ብር ገዛሁ” ልጃቸውን ከእገታ ያስለቀቁ አባት➖➖➖➖➖➖➖➖➖በአማኑኤል ከተማ ነዋሪ የሆኑ እና የማስለቀቂያ ገንዘብ የተጠየቀባቸው የመምህር አንለይ ልጅን ጨምሮ...
03/07/2023

“የልጄን ሕይወት በአንድ ሚሊዮን ብር ገዛሁ” ልጃቸውን ከእገታ ያስለቀቁ አባት
➖➖➖➖➖➖➖➖➖
በአማኑኤል ከተማ ነዋሪ የሆኑ እና የማስለቀቂያ ገንዘብ የተጠየቀባቸው የመምህር አንለይ ልጅን ጨምሮ ወደ ሰባት የሚደርሱ ሰዎች በአጋቾቹ እጅ በመውደቃቸው ከተማዋ በሐዘን ድባብ ውስጥ ሰንብታለች። አጋቾቹ ለአንዳንዶቹ ማስለቀቂያ 500 ሺህ ብር ሲጠይቁ፣ ለሌሎቹ ደግሞ አንድ ሚሊዮን ብር በመጠየቃቸው የቤተሰባቸው አባል በታጣቂዎች የተያዘባቸው ሰዎች ጎዳና ላይ ነጠላ ዘርግተው መዋጮ አስከመሰብሰብ ደርሰዋል።

“ለወራት ደመወዝ የተቋረጠባቸው የፊንጫ ስኳር ፋብሪካ ሠራተኞች መቸገራቸውን ገለጹ‼️የፊንጫ ስኳር ፋብሪካ ሠራተኞች፥ “የሁለት ወር ደመወዛችን ስላልተከፈለን፣ ከነቤተሰቦቻችን ለችግር ተዳርገና...
01/07/2023

“ለወራት ደመወዝ የተቋረጠባቸው የፊንጫ ስኳር ፋብሪካ ሠራተኞች መቸገራቸውን ገለጹ‼️
የፊንጫ ስኳር ፋብሪካ ሠራተኞች፥ “የሁለት ወር ደመወዛችን ስላልተከፈለን፣ ከነቤተሰቦቻችን ለችግር ተዳርገናል፤” ሲሉ ለአሜሪካ ድምፅ ተናገሩ።
በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን የሚገኘው ፊንጫ ስኳር ፋብሪካ ሥራ ያቆመው፣ እአአ ግንቦት 20 ቀን 2023 እንደነበር ያስታወሱት ሠራተኞቹ፣ የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት አካባቢውን ተቆጣጥሮ በነበረበት ወቅት በደረሰበት ጉዳት፣ ፋብሪካው እስከ አሁን ሥራ አለመጀመሩን አክለው ገልጸዋል።

 #በአውሮፓዊቷ ሀገረ ፈረንሳይ አንድ ወጣት በፓሊስ መገደሉን ተከትሎ የተቀሰቀሰው ተቃውሞ እንደቀጠለ ነው‼️በአውሮፓ፤ በፈረንሳይ ከተማ፣ ትራፊክ ፖሊስ አንድ አልጀሪያዊ ወጣት ተኩሶ መግደሉን...
01/07/2023

#በአውሮፓዊቷ ሀገረ ፈረንሳይ አንድ ወጣት በፓሊስ መገደሉን ተከትሎ የተቀሰቀሰው ተቃውሞ እንደቀጠለ ነው‼️
በአውሮፓ፤ በፈረንሳይ ከተማ፣ ትራፊክ ፖሊስ አንድ አልጀሪያዊ ወጣት ተኩሶ መግደሉን ተከትሎ፣ህዝብ በወሰደው የአፀፋ እርምጃ እስካሁን ከ 300 በላይ ፖሊሶች ጉዳት ደረሶባቸው ቁስለኛ ሆነዋል።

በመላው የፈረንሳይ ከተማ ከፍተኛ ህዝባዊ አመፅ ተቀጣጥሎ ዛሬ ሶስተኛ ቀኑን ይዟል።አመፁ ያስደነገጠው የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት በሚዳያ ብቅ ብሎ ተማፅኖ አቅርቧል።

ይህን ግዙፍ የአሸዋ ሀብት አያችሁት❗❓❓ይህ ወንዝ በተለምዶ አዳባይ ተብሎ ይጠራል። ወንዙ በሰሜን ሸዋ ዞን ስር የሚገኙ ሶስት ወረዳዎች (መንዝ ማማ፣መንዝ ላሎ፣ጅሩ) ያዋስኑታል። አዳባይ ታላ...
30/06/2023

ይህን ግዙፍ የአሸዋ ሀብት አያችሁት❗❓❓
ይህ ወንዝ በተለምዶ አዳባይ ተብሎ ይጠራል። ወንዙ በሰሜን ሸዋ ዞን ስር የሚገኙ ሶስት ወረዳዎች (መንዝ ማማ፣መንዝ ላሎ፣ጅሩ) ያዋስኑታል። አዳባይ ታላቁ የጀማ ወንዝ፣የበረሳ እና ሌሎች ወንዞች የሚገናኙበት ቦታ ነው። ይህ ቦታ ለአጎራባች ወረዳዎች እጅግ ቅርብ ቢሆንም እስካሁን ክልሉም ሆነ ዞኑ አጠቃላይ ወረዳው መንገድ ባለመሰራቱ ምክንያት እጅግ ግዙፍ ነጭ ወርቅ (አሸዋ) ተዳፍኖ በመቆየቱ የኢኮኖሚ ምንጭ ሳይሆን ቀርቷል። ለዘመናት ለወጪ ወራጅ ቁጭት ሆኖ ተዳፍኖ ቆይቷል። በዚህ አመት ግን አዳባይ ለልማት አርበኞች እጅ ወደላይ ብሏል፣ ሊማረክ ትንሽ ቀርቶታል። የመንዝ ማማ ወረዳ፣ የመንዝ ላሎ ወረዳ፣የአካባቢው ተወላጆች ይህን የዘመናት ቁጭት ወዲያ ብለው የመንገድ ስራውን በራሳቸው በጀት እና ከአካባቢው ተወላጆች እያሰባሰቡ አስጀምረውታል። እስካሁን ጥሩ ሄደዋል። የአዳባይ መንገድ መሰራት ለአካባቢው ነዋሪዎች ሌላ እድል ይዞ መጥቷል፣ መንገድ የደምስር እንደመሆኑ መጠን አካባቢው ላይ የሚመረቱ ምርቶችን በቀላሉ ወደ ገበያ ለማድረስ ትልቅ እገዛ አድርጓል። በጥቅሉ እነዚህን የልማት ፈር ቀዳጆች መደገፍ ግድ ስለሆነ ክልሉ፣ዞኑ፣አጎራባች ወረዳዎች እና ባለሀብቶች በርቱ ልንላቸው ስለሚገባ መንገድ አሰሪ ኮሚቴው የፊታችን እሁድ ሰኔ 25/2015 ዓ.ም በደብረብርሃን ጌትቫ ሆቴል ለልማት ወዳድ አካላት አጠቃላይ ውይይት ስለጠሩ እንድትገኙልን ሲሉ በአክብሮት ጠርተዋል።
"አዳባይ በልማት አርበኞች ይደባያል"

Fake news alert‼️ዩኒሴፍ በ24ሺህ ብር ደመወዝ ማስታወቂያ አውጥቷል በሚል የውሸት ድረገፅ ከፍተው ገንዘብ እየሰበሰቡ ይገኛሉ። ባገኘሁት መረጃ UNICEF ምንም አይነት ማስታወቂያ አ...
30/06/2023

Fake news alert‼️
ዩኒሴፍ በ24ሺህ ብር ደመወዝ ማስታወቂያ አውጥቷል በሚል የውሸት ድረገፅ ከፍተው ገንዘብ እየሰበሰቡ ይገኛሉ። ባገኘሁት መረጃ UNICEF ምንም አይነት ማስታወቂያ አላወጣም። እንዳይጭበረበሩ ለሌሎች ሼር በማድረግ ተባበሩ(አዩዘሀበሻ)።

30/06/2023

“ከ500 ሺህ እስከ 1ሚሊዮን ብር ከፍለዉ የተለቀቁ ሹፌሮች ‹ያገቱን ታጣቂዎች የመንግስት ፀጥታ ሐይሎችን የደንብ ልብስ የለበሱ ናቸው› አሉ‼️
ሰኔ 10 ቀን 2015 ዓ.ም መንግስት ሸኔ በሚለው ራሱን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት እያለ በሚጠራው ታጣቂ ቡድን አባላት ከ30 በላይ የከባድ መኪና አሽከርካሪና ረዳቶች መታገታቸውን አሻም ከሰለባዎቹ መረዳት ችላለች፡፡

ለአጋቾቹ የተጠየቁትን ከፍተኛ ገንዘብ ከፍለው የተለቀቁት ሰለባዎቹ እንደሚሉት ‹እገታውን የፈፀሙት ታጣቂዎች የመንግስት የፀጥታ ሀይሎችን የደንብ ልብስ የለበሱ ናቸው › ስሜና ድምፄ ለደህንነቴ ሲባል ይቆየኝ ያለና ታግቶ 500 ሺህ ብር ከፍሎ የተለቀቀ ረዳት በበኩሉ ‹ ሸኔ ከተባለዉ ታጣቂ ቡድን አምልጠን 7 ሰአት የፈጀ ጉዞ ካደረግን በኋላ በክልሉ ሚሊሻ ተይዘን ከ100 እስከ 150 ሺህ ብር ለእኛ ካልከፈላችሁን ለሸኔ አሳልፈን እንሰጣችኋለን በሚል አግተዉ ቤተሰብ ጋር እያሥደወሉን ገንዘብ ተቀብለዉ ለቅቀዉናል › ሲል ተናግሯል፡፡

ሌላኛው ሰለባ ደግሞ ‹መንግስት ሸኔ ሲል የሚጠራቸዉ ቡድን አባላት ናቸዉ ያገቱን ያሉ ሹፌርና ረዳቶች አጋቹ ቡድን ወስዶ በአርሶ አደር ቤት አስቀምጦ እየመገበ ገንዘብ ቤተሰቦቻችን እንዲያመጡ በየደቂቃዉ ያስደዉላል› ሲሉ ይናገራሉ፡፡

አሻም ያነጋገረቻቸው ወላጅ ልጃቸውን ከአጋቾቹ ገንዘብ በመክፈል ያስለቀቁ አንድ ወላጅ ደግሞ ያለፉበትን ውጣ ውረድ ለአሻም አሰረድተዋታል፡፡ለልጃቸው ሲሉ ‹ቤታቸውን ሽጠዋል፤ በእምነት ተቋማት፣ ነጠላ ዘርግተው› ለምነዋል፡፡

አሻም የሰላበዎቹን ቅሬታ መነሻ በማድረግ የመከለከያ ሰራዊትን፣ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስንና የኦሮሚያ ክልልን ለማነጋገር ሞክራለች፡፡ ለአሻም ጥያቄ ምላሽ የሰጡት የፌደራል ፖሊስ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ጄላን አብዲ መረጃውን ሀሰት ነው ሲል አጣጥለውታል፡፡

‹በሠራዊቱ ውሰጥ ይህንን የወረደ ተግባር የሚፈፅም አመራርም ሆነ አባል የለም።› ሲሉም አስተባብለዋል፡፡

‹ነገር ግን ኅብረተሰቡን ለማሳሳት በተለያዩ ጊዜ የአዲስ አበባ ፖሊስ፣ የፌደራል ፖሊስ እና የሌሎች ፀጥታ አካላት የደንብ ልብስ ለብሰው ሲዘርፋ የነበሩ የተደራጁ የዝርፊያ ቡድኖች በተለያዩ ጊዜ በቁጥጥር ሥር ውለው ለፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ተደረገው ህጋዊ እርምጃ እየተወሰደባቸው ያሉ አሉ።›

አርሰናል ➖➖➖➖➖➖➖➖➖አርሰናል 105 ሚሊዮን ፓውንድ በሚጠጋ ዋጋ የዌስት ሃሙን እንግሊዛዊ አማካይ ዴክለን ራይስን ለማስፈረም ተስማምቷል።
29/06/2023

አርሰናል
➖➖➖➖➖➖➖➖➖
አርሰናል 105 ሚሊዮን ፓውንድ በሚጠጋ ዋጋ የዌስት ሃሙን እንግሊዛዊ አማካይ ዴክለን ራይስን ለማስፈረም ተስማምቷል።

በአማራ ክልል ደብረብርሃን ከተማ አካባቢ በሚገኙ ሁለት የተፈናቃዮች መጠለያዎች የኩፍኝ በሽታ መቀስቀሱን ሪፖርተር ዘግቧል‼️ኩፍኝ የተቀሰቀሰባቸው "ወይንሸት" እና "ቻይና" የተሰኙ 27 ሺህ ...
29/06/2023

በአማራ ክልል ደብረብርሃን ከተማ አካባቢ በሚገኙ ሁለት የተፈናቃዮች መጠለያዎች የኩፍኝ በሽታ መቀስቀሱን ሪፖርተር ዘግቧል‼️
ኩፍኝ የተቀሰቀሰባቸው "ወይንሸት" እና "ቻይና" የተሰኙ 27 ሺህ ተፈናቃዮች የተጠለሉባቸው መጠለያዎች መኾናቸውን የሰሜን ሸዋ ዞን የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ቢሮ መግለጡን ዘገባው ጠቅሷል። የደብረ ብርሃን ከተማ ጤና ቢሮ በበኩሉ፣ በሽታው ባለፉት ኹለት ሳምንታት ከተከሰተ ወዲህ በኹለቱ መጠለያዎች 116 ሰዎች በበሽታው እንደተያዙ ገልጧል ተብሏል። ቢሮው፣ ለበሽታው መቀስቀስ በምክንያትነት የጠቀሰው በተፈናቃዮች መጠለያ ያለውን "ከፍተኛ የምግብ እጥረት" እንደኾነ ዘገባው አመልክቷል። በምግብ እጥረት ሳቢያ ሕይወታቸው ያለፈ ተፈናቃዮች ስለመኖራቸው ከተፈናቃዮቹ ሰምቻለኹ ያለው ሪፖርቱ፣ የዞኑ አደጋ መከላከል ቢሮ ግን የሰው ሕይወት በምግብ እጥረት ማለፉን ማስተባበሉን ጠቅሷል።

Update‼️በደቡብ ጎንደር ዞን እብናት ትናንት በፋኖ እና በወረዳው የፀጥታ አካላት በነበረው ውጊያ ከፖሊስ እና ከአድማ ብትና የሟቾቹ ቁጥር አምስት ደርሷዋል። ከእነዚህ ሟቾች ውስጥ የወረዳ...
28/06/2023

Update‼️
በደቡብ ጎንደር ዞን እብናት ትናንት በፋኖ እና በወረዳው የፀጥታ አካላት በነበረው ውጊያ ከፖሊስ እና ከአድማ ብትና የሟቾቹ ቁጥር አምስት ደርሷዋል። ከእነዚህ ሟቾች ውስጥ የወረዳው የሚሊሻ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ሻንበል ሲሳይ ይገኝበታል(ስርዐተ ቀብሩ ዛሬ ተፈፅሟል)። ዛሬ ረፋድ ድረስ ሌሎች አስኬረናቸው ያልተነሳ እንዳለ የአይን እማኞች ለአዩዘሀበሻ ገልፀዋል።
ከወጣት ፋኖዎች በከል ደግሞ 9 የሚሆኑት ከቀላል እስከ ከባድ የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል ። ይህን ተከትሎ በወረዳው ዛሬም ውጥረት ነግሷል።

 #በደቡብ ክልል በስልጤ ዞን የትምህርት ማስረጃን የማጣራት ስራ መጀመሩን ተከትሎ ከ200 በላይ መምህራን ስራ ጥለው ጠፉ‼️በስልጤ ዞን የትምህርት ማስረጃን ትክክለኛነት ለማረጋገጥ በተሰራ የ...
28/06/2023

#በደቡብ ክልል በስልጤ ዞን የትምህርት ማስረጃን የማጣራት ስራ መጀመሩን ተከትሎ ከ200 በላይ መምህራን ስራ ጥለው ጠፉ‼️
በስልጤ ዞን የትምህርት ማስረጃን ትክክለኛነት ለማረጋገጥ በተሰራ የማጣራት ተግባር የትምህርት ማስረጃቸው ሀሰተኛ ሆኖ የተገኘባቸው የተወሰኑ መምህራን በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተከትሎ ስራ ጥለው የጠፉ መምህራን ቁጥር ከ200 በላይ መድረሱ ተነግሯል ።
ባለፉት 11 ወራት በዞን 7715 የትምህርት ማስረጃዎች ህጋዊነት የማጣራት ስራ የተሰራ ሲሆን ከተጣሩት የትምህርት ማስረጃዎች ውስጥ የመምህር 82 ፣ የጤና ባለሙያ 1 ፣ የግብርና ባለሙያ 4 ፣ የፋይናንስ ባለሙያ 1 እና የጤና ጣቢያ ድጋፍ ሰጪ ሠራተኛ 1 በድምሩ 89 ሀሰተኛ ሆነው ተገኝተዋል ።
እስካሁን ባለው ሂደት 33 ግለሰቦች በህግ ቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው እየታየ እንደሚገናኝ እና ቀሪዎቹ አካባቢውን ለቀው መጥፋታቸው ተገልጿል ።
በዚህ ሂደት ጠንከር ያለ ቁጥጥር ማድረግ ሲጀመር ለኛም አይቀርልንም በሚል ከመምህርነት ስራ ገበታቸው ለቀው የጠፉ ቁጥራቸው ከ200 በላይ መድረሱን በዞን የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት መምሪያ ኢንስፔክሽን ቡድን መሪ የሆኑት አ/ቶ አብዱ በድሩ መናገራቸውን ብስራት ራዲዮን ዘግቧል።
በተጨማሪ የብቃት ማረጋገጫ ህጋዊነት ማጣራት በተመለከተ መቶ ከመቶ በማረጋገጥ የሰው ሃብት ማሟላት ለመፈጸም ታቅዶ በተሰራ ስራ በ2015 በጀት ዓመት በ11 ወራት ውስጥ በዞን 911 የብቃት ማረጋገጫዎች (COC) ህጋዊነት የተጣራ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 23ቱ ሀሰተኛ ሆነው የተገኙ እና ህገወጥ ክፍያ ሲፈጸምላቸው የነበሩ አካላት ሁሉም በህግ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ በማድረግ በየተቋሞቻቸው ህጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃ እየተወሰደ እንደሚገኝም ነው የተናገሩት።

እንኳን ለኢደል-አደሃ የአረፍ በአል በሰላም አደረሳቹ ኢድ_ሙባረክ
27/06/2023

እንኳን ለኢደል-አደሃ የአረፍ በአል በሰላም አደረሳቹ ኢድ_ሙባረክ

27/06/2023

የሰሜን ኮሪያ ፀረ አሜሪካ ሰልፍ

ሰሜን ኮሪያ 120 ሺህ ሰዎች የተሳተፉበት አሜሪካን የሚያወግዝና የኒውክሌር ጦርነት ማስጠነቀቂያ መልእክት ያዘለ ሰልፍ አካሄደች።

በሰልፉ ላይ ሰሜን ኮሪያውያን “የበቀል ጦርነት” አሜሪካን ለማጥፋት ብለዋል።

እንዲሁም” አሜሪካ ሙሉ በሙሉ በእኛ ቀለበት ውስጥ ነች፤ ኢምፔሪያሊስት አሜሪካ የሰላም አውዳሚ ነች” የሚሉየሚሉ መፈክሮች ተሰምተዋል።

ጀነራል አበባው የልዩ ኃይል መልሶ የማደራጀት ቀሪ ሥራዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲጠናቀቁ አሳሰቡሕዝባዊ ሚሊሻን መልሶ ለማደራጀት እና የልዩ ኃይል መልሶ የማደራጀት ሥራ በምን ደረጃ ላይ እን...
25/06/2023

ጀነራል አበባው የልዩ ኃይል መልሶ የማደራጀት ቀሪ ሥራዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲጠናቀቁ አሳሰቡ

ሕዝባዊ ሚሊሻን መልሶ ለማደራጀት እና የልዩ ኃይል መልሶ የማደራጀት ሥራ በምን ደረጃ ላይ እንዳለ ለመገምገም ያለመ ውይይት ተካሂዷል።

በውይይት መድረኩ የሀገር መከላከያ ከፍተኛ መኮንኖች፣ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከፍተኛ አመራሮች፣ የክልል ፖሊስ ኮሚሽነሮች፣ የከተማ አስተዳደሮች ፖሊስ ኮሚሽነሮች እና የክልል የፀጥታ ቢሮ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል።

የመከላከያ ሰራዊት ምክትል ኢታማጆር ሹም ጀነራል አበባው ታደሰ በመድረኩ ላይ እንደገለጹት÷ የሀገርን ኢኮኖሚ ለማሳደግ ጠንካራ የፀጥታ መዋቅር ያስፈልጋል፡፡

በፀጥታ ተቋማት የተደራጀ ጥናት እና ውይይት በሀገራዊ ኃላፊነት ለሁሉም የሚጠቅም አንድ ወጥ የሆነ የሠራዊት ኃይል መፍጠር ተችሏል ነው ያሉት።

Address

Addis Ababa

Opening Hours

Monday 01:00 - 23:00
Tuesday 01:00 - 23:00
Wednesday 01:00 - 23:00
Thursday 01:00 - 23:00
Friday 01:00 - 23:00
Saturday 01:00 - 23:00
Sunday 01:00 - 23:00

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when 𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨 𝐙𝐞𝐧𝐚 𝐎𝐟𝐟𝐢𝐜𝐚𝐥 posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Share