ኢትዮ ራይት ethio raght

ኢትዮ ራይት ethio raght Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ኢትዮ ራይት ethio raght, Broadcasting & media production company, Addis Ababa.

የሩስያ እና ዩክሬን ጦርነት ከጀመረ ግዜ አንስቶ ለመጀመርያ ግዜ የዩክሬንን እህል ጭኖ ዛሬ ጉዞ የጀመረው ግዙፍ መርከብ የጭነቱ መዳረሻ ኢትዮጵያ እንደሆነ ታውቋል። የአለም ምግብ ፕሮግራም የ...
12/08/2022

የሩስያ እና ዩክሬን ጦርነት ከጀመረ ግዜ አንስቶ ለመጀመርያ ግዜ የዩክሬንን እህል ጭኖ ዛሬ ጉዞ የጀመረው ግዙፍ መርከብ የጭነቱ መዳረሻ ኢትዮጵያ እንደሆነ ታውቋል።

የአለም ምግብ ፕሮግራም የገዛው ይህ የእህል ጭነት በኢትዮጵያ ለሚገኙ የድርቅ እና ጦርነት ተጎጂዎች እንደሚከፋፈል ታውቋል። የሩስያ እና ዩክሬን ጦርነት ባስከተለው የምግብ ንረት ብዙ የአፍሪካ እና የላቲን አሜሪካ ሀገራት የመጀመርያውን ጭነት ለማግኘት ቢፈልጉም የአለም ምግብ ፕሮግራም ወደ ኢትዮጵያ እያጓጓዘው እንደሆነ ታውቋል።

ቱርክ፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ የአፍሪካ ህብረት፣ ዩክሬን እና ሩስያ ለዚህ መሳካት ቁልፍ ሚና ነበራቸው።

"Brave Commander" የተባለው ይህ መርከብ ከ23,000 ሜትሪክ ቶን በላይ እህል የጫነ ሲሆን ከጥቂት ቀናት በኋላ ጅቡቲ ወደብ ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል።

*** የእህሉ መምጣት በርሀብ ለሚሰቃዩት ዜጎቻችንን እጅግ ትልቅ ነገር ነው። ነገር ግን በህዳሴ ግድብ ያየነው ተስፋ እውን ሆኖ የውጭ እርዳታ ሳንጠብቅ ራሳችንን የምንችልበት ወቅት እንዲያመጣልን መስራትም፣ መፀለይም ይገባል።

Photo: File

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ኢትዮ ራይት ethio raght posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share