All Ethiopian Tube

All Ethiopian Tube All in one is The Biggest Media In Africa new movie. sports news. different project. funny. jokes. in general all in one.

03/05/2024

Jobs

Afar Language Speaker
አፋረኛ ቋንቋ ተናጋሪ

እንግሊዘኛ የሚችል

ስራው
ከእንግሊዘኛ ወደ አፋረኛ መተርጎም የሚችል
ለአጭር ግዜ
ኮምፒዩተር ያለው
ኢንተርኔት ያለው

ስራውን በግዜ ማድረስ የሚችል
እስከ ሰኞ ያናግረን

21/04/2024

ሀይሌ በ አንድ ወቅት
ለ ኢትዮጲያ ዲሞክራሴ ቅንጦት ነው አለ
እውነቱን ነው ሌላው የዚች ሀገር ፖለቲካ ከድጡ ወደ ማጡ እየሄደ እየለየለት ነው

19/03/2024
አስከሬናቸውን ሳያገኙ ቁፋሮ እንደማያቆሙ በደላንታ ወረዳ ማዕድን ማውጫ ጉድጓድ ውስጥ የተቀበሩ ወጣቶች ቤተሰቦች ተናገሩበአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ደላንታ ወረዳ 018 ቀበሌ ልዩ ስሙ አለኋ...
17/03/2024

አስከሬናቸውን ሳያገኙ ቁፋሮ እንደማያቆሙ በደላንታ ወረዳ ማዕድን ማውጫ ጉድጓድ ውስጥ የተቀበሩ ወጣቶች ቤተሰቦች ተናገሩ

በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ደላንታ ወረዳ 018 ቀበሌ ልዩ ስሙ አለኋት ተብሎ በሚጠራ ስፍራ ነበር ኦፓል ማዕድን በማውጣት ላይ የነበሩ ወጣቶች መውጫቸው በአለት የተደፈነባቸው፡፡

ኦፓል ማዕድን በማውጣት ስራ የተደራጁ ወጣቶቹ ጥር 29 ቀን 2016 ዓ.ም ምሽት ላይ በቁፋሮ ላይ እያሉ እንደተናደባቸው የማህበሩ ቡድን መሪ መኳንት ለጌ ለአል ዐይን አማርኛ ተናግሯል።

እንደ መኳንት ገለጻ ከሆነ “ዘጠኝ ወጣቶች አዳራቸውን ኦፓል ማዕድን ለማውጣት እየቆፈሩ እያለ መውጫ በራቸው በአለት ተደፍኖባቸዋል፡፡ከዚያ ጊዜ ጀምሮ የአካባቢው ህዝብ፣ ቤተሰቦቻቸው እና የመንግስት ተቋማት ወጣቶቹን በህይወት ለመታደግ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል፡፡

ይሁንና ቦታው አለታማ እና ለመረዳዳት አስቸጋረ በመሆኑ ምክንያት የተደረገው ጥረት ውጤታማ እንዳልሆነ የሚናገው መኳንት አሁን ላይ መንግስት እና የአካባቢው ማህበረሰብ ጥረታቸውን ሙሉ ለሙሉ ማቋረጣቸውን አክሏል፡፡

መሬት ውስጥ ከተቀበሩት ወጣቶች ውስጥ የሶስቱ ሚስቶቻቸው ነፍሰጡሮች ሲሆኑ ከባድ ጊዜ እያሳለፉ እንደሆነ ተገልጿል

ትናንት ለሊት ከንግድ ባንክ የሌላችሁን ገንዘብ ለወሰዳችሁ ተማሪዎች በሙሉ፣በማወቅም ይሆን ባለማወቅ የወሰዳችሁትን ብር መልሱ አለበለዚያ ግን ተጠያቂ ትሆናላችሁ እየተባላችሁ ነው። ግር የሚለው...
16/03/2024

ትናንት ለሊት ከንግድ ባንክ የሌላችሁን ገንዘብ ለወሰዳችሁ ተማሪዎች በሙሉ፣

በማወቅም ይሆን ባለማወቅ የወሰዳችሁትን ብር መልሱ አለበለዚያ ግን ተጠያቂ ትሆናላችሁ እየተባላችሁ ነው።

ግር የሚለው ግን ንግድ ባንክ እስካሁን ይህን በርካቶች የሌላቸውን ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ያወጡበትን ድርጊት በይፋ አለማሳወቁ ነው። "የሲስተም ችግር እንጂ የሳይበር ጥቃት አልደረሰብኝም" የሚል መግለጫ አሁን አውጥቷል።

የተፈፀመበት ዝርፊያስ?

ሌላው አለም ላይ ቢሆን መጀመርያ ድርጊቱ ይፋ ይደረጋል፣ ከዛም ምን ያህል ገንዘብ፣ በየትኛው አካባቢ ካሉ ተገልጋዮች፣ በምን መልኩ፣ የወሰዱ ሰዎች ላይ የሚወሰዱ አካሄዶች... ወዘተ የሚሉ መረጃዎች ቢያንስ ለደንበኞች ይነገራል።

ምስል: ማህበራዊ ሚድያ

ይች ከትማ የት ነች
12/03/2024

ይች ከትማ የት ነች

የዚች ሀገር አክቲቪስቶች ጦርነቱን ለምን እንደሚፈልጉት ላስረዳ  አንደኛ : አብዘሀኛወቹ የዩቲዩብ ጡረተኞች ናቸው ማለቴ ተጨፈጨፈ ብለው የሚሰሩት ብዙ ተመልካች አለው ታረቁ ሰላም ወረደ ብለው...
12/03/2024

የዚች ሀገር አክቲቪስቶች
ጦርነቱን ለምን እንደሚፈልጉት ላስረዳ

አንደኛ : አብዘሀኛወቹ የዩቲዩብ ጡረተኞች ናቸው ማለቴ ተጨፈጨፈ ብለው የሚሰሩት ብዙ ተመልካች አለው ታረቁ ሰላም ወረደ ብለው ከሚሰሩት
ሁለተኛ : ብዙወቹ የሚኖሩት ውጭ ነው ያ ማለት የ እነሱ ልጅ ወይም ቤተሰባቸው በጦርነቱ ሰለባ የሚሆነው በጣም በትንሹ ነው

ሶስተኛ : ጦርነቱን የሚፈልጉት ለመለመን ነው በቃ ንቃ የሀገሬ ህዝብ ሆይ በቃ ጦርነት በቃኝ ልትል ይገባል ውጭ ሶፋ ላይ ቁጭ ብለው ከሚያባሉህ ሰወች እራስህን ልትጠብቅ ይገባል

የመንግስትን በቀጣይ ፖስት ጠብቁ

10/03/2024

የ አርሰሴናል ቋጠሮ የአንድ ነው

ዲዛየርን 3 ሚሊየን የገዛችሁ ፈጣሪ ይሁናችሁ መኪና ሊቀንስ ነው
09/03/2024

ዲዛየርን 3 ሚሊየን የገዛችሁ ፈጣሪ ይሁናችሁ
መኪና ሊቀንስ ነው

  ዛሬ አሁን፣ በዚህ ደቂቃ 17,000 አውሮፕላኖች በረራዎችን በአለም ዙርያ እያከናወኑ ይገኛሉ። የዩክሬን የአየር ክልል ተለይቶ ከበራራ ነፃ እንደሆነ ያሳያል፣ ከሩስያ ጋር ባለው ግጭት አደ...
07/03/2024

ዛሬ አሁን፣ በዚህ ደቂቃ 17,000 አውሮፕላኖች በረራዎችን በአለም ዙርያ እያከናወኑ ይገኛሉ።

የዩክሬን የአየር ክልል ተለይቶ ከበራራ ነፃ እንደሆነ ያሳያል፣ ከሩስያ ጋር ባለው ግጭት አደጋ ሽሽት መስመር በመቀየራቸው።

Via Flight Radar

SKY ተወለደ* ነፍሰጡርዋን ያዋለደው የአውሮፕላን አብራሪ   | በቅርቡ አንድ የታይላንድ አውሮፕላን ድርጅት ተሳፋሪዎችን ይዞ ከታይዋን ወደ ባንኮክ መብረር ይጀምራል፡፡ከተሳፋሪዎች መካከል አ...
06/03/2024

SKY ተወለደ

* ነፍሰጡርዋን ያዋለደው የአውሮፕላን አብራሪ

| በቅርቡ አንድ የታይላንድ አውሮፕላን ድርጅት ተሳፋሪዎችን ይዞ ከታይዋን ወደ ባንኮክ መብረር ይጀምራል፡፡

ከተሳፋሪዎች መካከል አንዲት ነብሰጡር ሴት መውለጃ ጊዜዋ ደርሷልና በረራ ላይ እያለች ምጥ ይጀምራታል፡፡

በአውሮፕላኑ ውስጥ ምጥ የያዛትን ሴት ለመርዳት አንድም የጤና ባለሙያ አልነበረም። አብራሪው እና የበረራ አስተናጋጆቹ ተጨነቁ፡፡ አውሮፕላኑም በመዳረሻው ለማረፍ ሰዓታት ይቀሩት ነበር፡፡ ምጥ በያዛት ሴት ጩሀት ተሳፋሪዎች ጭንቀት ውስጥ ገብተዋል፡፡

የአውሮፕላኑ አብራሪ የነበረው ጃካሪን ሳራርንራ ካስኩል ላለፉት 18 ዓመታት በአውሮፕላን አብራሪነት ልምድ ያለው ቢሆንም ከመሰረታዊ የቀይ መስቀል የህክምና ዕውቀት በስተቀር ስለማዋለድ የሚያውቀው ነገር አልነበረም፡፡

ይሁን እንጂ ምጥ ውስጥ ያለችውን ሴት በሚችለው አቅም በድፍረት ለመርዳት ወሰነ፡፡

የዋና አብራሪነት ኃላፊነቱን ለረዳት አብራሪው አስረከበ፡፡ ከዛም ምጥ ላይ ያለችውን ነብሰጡር ተሳፋሪን ከመሬት በላይ በሺዎች ማይል ርቀት ላይ ወንድ ልጅ በሰላም አንድትገላገል ማድረግ ችሏል፡፡

የአውሮፕላኑ የበረራ ሰራተኞች አዲስ የተወለደውን ወንድ ልጅ ህፃን "ስካይ" የሚል ስም አውጥተውለታል፡፡

አውሮፕላኑ እንዳረፈ ፈጣን ድጋፍ እንድታገኝም ደውሎ የጤና ባለሙያዎች እንዲዘጋጁ በማድረግ የሠራው ስራ በበርካቶች አየተሞካሸ ይገኛል ሲል የዘገበው ኒውስ ናሽናል ነው፡፡

 #መልካምዜና የኢትዮጵያ አየር መንገድ እስካሁን ካሉት አውሮፕላኖች በግዝፈቱ የሚልቅ 777X የተባለ አውሮፕላን ከቦይንግ ኩባንያ ለመግዛት ስምምነት ፈፀመ አየር መንገዱ ስምምነቱን ዛሬ የፈፀ...
05/03/2024

#መልካምዜና የኢትዮጵያ አየር መንገድ እስካሁን ካሉት አውሮፕላኖች በግዝፈቱ የሚልቅ 777X የተባለ አውሮፕላን ከቦይንግ ኩባንያ ለመግዛት ስምምነት ፈፀመ

አየር መንገዱ ስምምነቱን ዛሬ የፈፀመው እነዚህን ቢያንስ የነጠላ ዋጋቸው 440 ሚልዮን ዶላር (24.6 ቢልዮን ብር) የሆኑ ስምንት አውሮፕላኖች ለመግዛት ሲሆን ይህም የውሉን ዋጋ ከ 3.5 ቢልዮን ዶላር (197 ቢልዮን ብር) በላይ ያደርገዋል። ውሉ አየር መንገዱ እስከ 20 ተጨማሪ አውሮፕላኖች ለመግዛት መብት እንደሚሰጠው ቦይንግ ያወጣው መግለጫ ያሳያል።

የእነዚህ ቦይንግ 777X (777-9) አውሮፕላኖች ግዢ አየር መንገዱን ከአፍሪካ ቀዳሚ ያደርገዋል።

ቦይንግ 777X አውሮፕላኖች የድሪምላይነር አውሮፕላን ሞዴል መሰል ሆነው የተሰሩ ሲሆን በተሻለ መልኩ የዘመኑ ቴክኖሎጂዎች ተገጥመውለታል። አውሮፕላኑ የተሰራበት ካርበን ፋይበር የነዳጅ ወጪውን እስከ 10 ፐርሰንት እንዲቀንስ ያደርገዋል ተብሏል።

በዩኔስኮ በርካታ ቅርሶችን ያስመዘገቡ ሀገራትየመንግስታቱ ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስ እና ባህል ተቋም (ዩኔስኮ) በ168 ሀገራት 1 ሺህ 199 ቅርሶችን የአለም ቅርስ አድርጎ መዝግቧል።ጣሊ...
04/03/2024

በዩኔስኮ በርካታ ቅርሶችን ያስመዘገቡ ሀገራት

የመንግስታቱ ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስ እና ባህል ተቋም (ዩኔስኮ) በ168 ሀገራት 1 ሺህ 199 ቅርሶችን የአለም ቅርስ አድርጎ መዝግቧል።

ጣሊያን፣ ቻይና፣ ፈረንሳይ እና ጀርመን በርካታ ቅርሶችን በማስመዝገብ ቀዳሚዎቹ ሀገራት ናቸው።

ዩኔስኮ ከሁለተኛው የአለም ጦርነት በኋላ ሲቋቋም አላማው ምን ነበር? ለመጀመሪያ ጊዜ የመዘገበው የአለም ቅርስስ የት ይገኛል? ተጨማሪ ያንብቡ፦

ጣሊያን፣ ቻይና፣ ፈረንሳይ እና ጀርመን በርካታ ቅርሶችን በማስመዝገብ ቀዳሚዎቹ ሀገራት ናቸው

በምርጫ አሸንፎ ሥልጣን መያዝ አገርን እስከማፈራረስ ድረስ ሊያዘልቅ የሚያስችል የይለፍ ወረቀት አይደለም!   | በወቅታዊ ጉዳይ ከመኢአድ ፣ ኢህአፓ ፣ አንድ ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ፣ አ...
02/03/2024

በምርጫ አሸንፎ ሥልጣን መያዝ አገርን እስከማፈራረስ ድረስ ሊያዘልቅ የሚያስችል የይለፍ ወረቀት አይደለም!

| በወቅታዊ ጉዳይ ከመኢአድ ፣ ኢህአፓ ፣ አንድ ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ፣ አማራ ግዮናዊ ንቅናቄና እናት ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ

ያለፈበት ሂደት ምንም ይሁን የብልጽግና ፓርቲ በ፳፻፲፫ በተደረገዉ ስድስተኛ ዙር አገር አቀፍ ምርጫ አሸንፎ መንግስት መስርቷል፡፡ በወቅቱ በምርጫዉ የተሳተፍን የፖለቲካ ፓርቲዎችም አገር የነበረችበትን ነባራዊ ሁኔታ (ዉስጣዊ በትግራይ ክልል የነበረዉን ጦርነት ዉጫዊ ከግብፅ እና ሱዳን ጋር የነበረዉ ፍጥጫ) ግንዛቤ ዉስጥ በማስገባት የምርጫዉን ዉጤትና የፓርቲዉን አሸናፊነት ተቀብለን በሰላማዊ የፖለቲካ ትግል ለመንቀሳቀስ ፈቅደን በዚሁ ጎዳና እንገኛለን፡፡

የብልጽግና መንግሥት በምርጫ ሥልጣን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ ምክንያቱና አጥፊዉ ማንም ይሁን ሕወሐት የለኮሰዉን ጦርነት ተከትሎ በሰሜኑ የአገራችን ክፍል በትግራይ፣ በአማራና በአፋር ክልሎች አንድ ሚሊየን የሚገመት ሕዝብ እንዳለቀበት እና በብዙ ቢሊየን ዶላሮች የሚገመት ንብረት የወደመበትን የእርስ በርስ ጦርነት አገራችን ኢትዮጵያ አስተናግዳለች፡፡ ከዚሁ ጊዜ ቀደም ብሎ በጀመረዉና እስከ ዛሬ በዘለቀዉ በኦሮሚያ ክልል ከኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ጋር በሚደረገዉ ዉጊያ የአብዛኛዉ የኦሮሚያ ክልል ነዋሪዎች በአማጽያኑና በመንግሥት ኃይሎች መካከል እንደ ገና ዳቦ ከላይና ከታች እሳት እየነደደባቸዉ በክልሉ ነዋሪ አማርኛ ተናጋሪ ማህበረሰብ ደግሞ ከዘር ማጥፋት ያልተናነሰ እልቂት ሲከናወንበት እንደቆየና አሁንም ድረስ ክልሉና የክልሉ ኗሪ በዚሁ ተጠምዶ ፍጅቱም እንደቀጠለ ይታወቃል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ መንግሥት ባለፉት ሰባት ወራት በአማራ ክልል እያከናወነ ያለዉ ክልል አቀፍ ጦርነት የክልሉን ኗሪዎች ለከፋ ጉስቁልና የዳረገ ከመሆኑም ባሻገር በተለያዩ ጊዜያት የመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች በሰላማዊ ዜጎች ላይ በሚወስዱት የበቀል እርምጃ ቁጥራቸዉ ቀላል የማይባል በውጊያው ተሳታፊ ያልሆኑ ዜጎች በግፍ ተገድለዋል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ ማንነታቸው ያልታወቀ ኃይሎች በክልሉ መንግሥት ባለሥልጣናት ላይ በሚፈጽሟቸዉ የደፈጣ ጥቃቶች የመንግሥት ሹማምንትና የሥራ ኃላፊዎች ተገድለዋል፡፡

አገር የገባችበትን የእርስ በርስ ጦርነት ተከትሎ የፌዴራል መንግሥት በአማራ ክልል ከሰሞኑ የከፈተዉ መጠነ ሰፊ ጦርነትና በአገር መከላከያ ሠራዊት እንዲሁም በፋኖ ታጣቂዎች መንገዶች እንዲዘጉና የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ እንዲቆም መደረጉ በክልሉ ከታወጀዉ ጦርነት ጋር ተደምሮ ክልሉን ወደ ምድራዊ ሲኦልነት እየለወጠ እንደሆነ ለመረዳት አያዳግትም።

ይህን መግለጫ ያወጣን ፓርቲዎች አገራችን እየሄደች ያለችበት ጎዳና ትክክል አለመሆኑን በመግለጽ ችግሩ ያለ ቅድመ ሁኔታ ሁሉን አቀፍ ድርድር በማድረግ በጠረጴዛ ዙሪያ እንዲፈታ ለመንግሥት ተደጋጋሚ ጥሪ ማስተላለፋችን ይታወሳል፡፡ ይሁን እንጂ ጥሪያችን ሰሚ በማጣቱ የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብም ትርጉም ያለዉ ተጽዕኖ በመፍጠር አገር የገባችበት ችግር በጠረጴዛ ዙሪያ እንዲፈታ ጥረት ማድረግ ባለመቻሉ አገራችን ከዕለት ወደ ዕለት ወደ ከፋ ሁኔታ ተገፍታ ዛሬ ላይ የአማራ ክልልን የሚያህል የአገራችንን አንድ ሦስተኛ ያህል ሕዝብ የያዘ አካባቢ መንግሥታዊዉ የአገር መከላከያ ሠራዊት መንበሩን ለማጽናት የፋኖ ኃይሎች ደግሞ በክልሉና ከክልሉ ዉጪ በሚኖር ሕዝብ ላይ ለአሥርት ዓመታት እንደ ደረሰ የሚያምኑትን በደል ለማስወገድ የሚቻለዉ በኃይል ብቻ እንደሆነ በማመን በሚደረገዉና ከሰሞኑ በተጠናከረ መልኩ በተከፈተ ዘመቻ ክልሉ የጦር አዉድማ ሆኗል፡፡

በወንድማማቾች መካከል የሚደረግ ጦርነት በየትኛዉም መልኩ የማይደገፍ ቢሆንም ተዋጊ ኃይሎች ብቸኛ መዉጫ አድርገዉ ከመረጡት የዉጊያን ሕግ ተከትሎ መከናወን ሲኖርበት ባለፉት ጥቂት ወራት ለመታዘብ እንደተቻለው "ዝሆኖቹ ሲጣሉ የሚሞተዉ ሣሩ" እንደሚባለዉ በተዋጊ ኃይሎች መካከል በሚደረገዉ ዉጊያ የበቀል እርምጃ በሚመስል መልኩ ያለ አንዳች ተጠያቂነት ሰላማዊና መሣሪያ ያልታጠቀዉ ሕዝባችን በግፍ እየተገደለ የመከራን ዘመን እየገፋ ይገኛል፡፡

አገር በእንደዚህ መልኩ እያረረች ባለችበት በዚህ ጊዜ እኛ በአገሪቱ ሕግ መሠረት በፖለቲካ ፓርቲነት ተመዝግበን የምንገኝና ይህን መግለጫ ያወጣን የፖለቲካ ፓርቲዎች ዝምታን በመምረጥ ቆሞ ተመልካች መሆን የኅሊና ወቀሳን ከማሳደሩም በላይ በዚህ የአገራችን ጥቁር ቀን የፖለቲካ ሜዳ ዉስጥ አለንበትና የታሪክ ተወቃሽ መሆናችን አይቀርም፡፡ ከኅሊናና ከታሪክ ወቀሳ ነጻ ለመሆን በሌላ መልኩ ልናደርገዉ የምንችለዉ እጅግ ዉሱን መሆኑንም እንረዳለን፡፡

ሻዕቢያና ጀብሃ ኤርትራን ከኢትዮጵያ ለመገንጠል በግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት ከጀመሩት የሽምቅ ዉጊያ ጀምሮ ሕወሃት ባደረገዉና በሌሎችም የአማጽያን እንቅስቃሴን በኃይል ለመቀልበስ የተደረጉ ሙከራዎች መተኪያ የሌለዉን የዜጎቻችንን ሕይወት ከመቅጠፍና አገራችን የሌላትን ሃብት ከማዉደም በስተቀር አንዳቸዉም በድል እንደተጠናቀቁ ዋቢ መጥቀስ አይቻልም፡፡

ዛሬም በአገራችን እየተካሄደ ያለዉ የእርስ በርስ ጦርነት ከዚህ የተለየ ዉጤት እንደማያመጣ ለመገመት ነቢይ መሆን አይሻም፡፡ ምናልባትም ባልተጠበቀ አጋጣሚ የክልሉን ሕዝብ በኃይል መድፈቅ ቢቻል እንኳ በዚህ ዓይነት መልኩ በኃይል ዝም ያለ ሕዝብ ሰጥ ለጥ ብሎ በቀጣይ ለመንግሥት ይገዛል ማለት አንድም የሕዝቡን ሥነ ልቡና አለማወቅ አንድም የዋህነት ነዉ፡፡ ከዚህ በመነሳት የመከራ ጽዋ እለት እለት እንዲጎነጭ የፈረድንበት ሕዝባችን የዘመነ ነገር ፈጥረንለት ኑሮውን ማሻሻል ባናስችለው እንኳ በለመደዉ መንገድ ሕይወቱን እንዲገፋ ምድሪቱን ሲኦል አናድርግበት፡፡ የተፈጥሮ ሞቱን እስኪሞትም እንታገሰዉ፡፡ ይህ ብቸኛ ልናደርግለት የምንችለዉ ዉለታ መሆኑንም እንረዳለት፡፡

የትኛውም ጦርነት መቋጫዉ ድርድርና ስምምነት መሆኑን መረዳት ተገቢ ሲሆን እንደ ኢትዮጵያ ለግማሽ ምዕተ ዓመት በግጭትና መጠፋፋት አዙሪት ለተጠመደች አገር ደግሞ ይህን ለመገንዘብ የግፉ ግንባር ቀደም ገፈት ቀማሽ በሆነው ሕዝብ ጫማ ዉስጥ እግርን አስገብቶ መመልከትን ይጠይቃል፡፡

ስለዚህ እኛ ይህን መግለጫ ያወጣን የትብብር ፖለቲካ ፓርቲዎች፤

1. መንግሥት በአማራ ክልል የከፈተዉን መጠነ ሰፊ ዘመቻ በአስቸኳይ እንዲያቆም እንጠይቃለን፡፡

2. መንግሥት በአማራ ክልል ለሚገኙ የፋኖ ኃይሎች እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል ለሚንቀሳቀሰዉ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አስቸኳይ የተኩስ አቁም ጥሪ እንዲያቀርብና ጦርነቱን በሰላማዊ ድርድር ለመፍታት ፍላጎቱንና ዝግጅቱን በይፋ እንዲገልጽ እንጠይቃለን።

3. ከመንግሥት ጋር በአማራ ክልል ዉጊያ ላይ የሚገኙ የፋኖ ኃይሎች እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት በተ.ቁ 2 ለተጠቀሰዉ "የተኩስ አቁምና የድርድር ጥሪ" አዎንታዊ ምላሽ በመስጠት የእርስ በርስ ጦርነቱ በድርድር እልባት እንዲያገኝ ተገቢውን እንድታደርጉ እንጠይቃለን።

4. የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የሰሜኑ ጦርነት በፕሪቶሪያ ስምምነት እልባት እንዲያገኝ ላደረገዉ እገዛ እያመሰገንን አሁንም በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች እየተካሄዱ ያሉ የእርስ በርስ ጦርነቶች በሰላማዊ መንገድ በድርድር እንዲቋጩ በመንግሥት ላይ ተፅዕኖ በማሣደርና ድርድሩን በማመቻቸት ለአገራችን ኢትዮጵያ ዉለታ እንድትዉሉ እንጠይቃለን፡፡

ከላይ ያስቀመጥናቸዉ ነጥቦች አገራችን ኢትዮጵያን ከገባችበት የእልቂት መንገድ ብቸኛዉ መውጫ መንገድ መሆኑን በመረዳት ሁሉም አካላት የየበኩላቸዉን እንዲያደርጉ እየጠየቅን ይህን ባለማድረግ አገርን ወደ ከፋዉ መግፋት ከታሪክ ተጠያቂነት በመለስ፤ ይዋል ይደር እንጅ ህጋዊ ተጠያቂነትን እንደሚያስከትል ኃላፊነት እንደሚሰማን የፖለቲካ ፓርቲዎች አቋማችንን እንገልጻለን።

በመጨረሻም በምርጫ አሸንፎ ስልጣን መያዝ አገርን እስከማፈራረስ ድረስ ሊያዘልቅ የሚያስችል የይለፍ ወረቀት አለመሆኑን አጽንኦት ሰጥተን ለመግለጽ እንወዳለን።

እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ!

መኢአድ ፣ ኢሕአፓ ፣ አንድ ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ፣ ዐማራ ግዮናዊ ንቅናቄ ፣ እናት ፓርቲ

የካቲት ፳፪ ቀን ፳፻፲፮ ዓ.ም
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

በድሀ ላይ የሚደረግ ግፍ 😭አደይ :- ለቪዲዮ እንኪ 10 ሺህ ብላኝከዛ ቪዲዮውን አጥፍታው 10 ሺህ ብሩን ተቀብላኝ 1 ሺህ ሰጠችኝ::ያሳዝናል 😭ፊዬና የምትባል ልጅ በቲክ ቶክ እንደዚህ አይነ...
02/03/2024

በድሀ ላይ የሚደረግ ግፍ 😭

አደይ :- ለቪዲዮ እንኪ 10 ሺህ ብላኝ
ከዛ ቪዲዮውን አጥፍታው 10 ሺህ ብሩን ተቀብላኝ 1 ሺህ ሰጠችኝ::

ያሳዝናል 😭

ፊዬና የምትባል ልጅ

በቲክ ቶክ እንደዚህ አይነት ልጆች ከህዝብ ብዙ እየተቀበሉ እየረዳን ነው እያሉ

በቪዲዮ ይሄ ያክል ብር ሰጠን እያሉ ከቪዲዮ ጀርባ ግን የሰጡትን ገንዘብ መልሰው እየተቀበሉ ይገኛል::

ለእኚህ እናትም ለቪዲዮ 10 ሺህ ሰጥታቸው
ከቪዲዮ ጀርባ 10 ሺህ ተቀብላ 1 ሺህ ብር ስጥታ ሸኝታቸዋለች::

አሳዛኝ ትውልድ ና እጅግ ስንምግባር የጎደለው ትውልድ በቲክቶክ ተፈጥሯል::

አደይ አይዞኝ

በድሀ ላይ የሚደረግ ግፍ ይቁም

😭

🌴🌴🌴

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቢቢሲ አማርኛ ዛሬ የሰራውን "አየር መንገዱ በሶማልያ አየር ክልል መብረር አቆመ" የሚል ዘገባውን የተሳሳተ ነው ብሏል። ግዜው ግን የመረጃ ነው፣ Flight Radar...
02/03/2024

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቢቢሲ አማርኛ ዛሬ የሰራውን "አየር መንገዱ በሶማልያ አየር ክልል መብረር አቆመ" የሚል ዘገባውን የተሳሳተ ነው ብሏል።

ግዜው ግን የመረጃ ነው፣ Flight Radar ላይ እንደሚታየው ሁሉም የአየር መንገዱ የመንገደኞች በረራዎች በጅቡቲ በኩል እየተከናወኑ ነው፣ ይህ ምስሉ ላይ የምትመለከቱት ዛሬ ከደቂቃዎች በፊት የነበረ የበረራ መስመር ነው።

ባይሆን የጭነት (ካርጎ) በረራዎች በሶማልያ የአየር ክልል መብረር አልቆሙም ቢል ይሻላል። አስተባብል ተብሎ ከላይ ተነግሮት ሊሆን ይችላል፣ እውነታው ግን ይኸው ነው።

በ 1 ዓመት ቀላል እስራትና በ2 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ ተወሰነ   | ኮሜዲያን ያሬድ ዘላለም (ልጅ ያሬድ) በተከሰበት የወንጀል ክስ በአንድ አመት ቀላል እስራት እና በሁለት ሺህ...
01/03/2024

በ 1 ዓመት ቀላል እስራትና በ2 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ ተወሰነ

| ኮሜዲያን ያሬድ ዘላለም (ልጅ ያሬድ) በተከሰበት የወንጀል ክስ በአንድ አመት ቀላል እስራት እና በሁለት ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ ተወሰነ።

የቅጣት ውሳኔውን የወሰነው የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ህገመንግስታዊና በህገመንግስት ስርዓቱ ላይ የሚፈጸሙ የወንጀል ጉዳዮችን የሚመለከተው ችሎት ተከሳሹ ያቀረበውን አምስት የቅጣት ማቅለያ አስተያየቶችን ይዟል።

የፍትህ ሚኒስቴር የተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ በኮሜዲያን ያሬድ ዘላለም ላይ ሶስት ክሶችን አቅርቦበት ነበር።

ከቀረቡበት ክሶች መካከል በኮምፒዩተር የሚፈጸም ወንጀል ድንጋጌን መተላለፍ፣ የቤተክርስቲያንና የሰዎችን ክብርና መልካም ስም ማጉደፍ እንዲሁም የጥላቻ ንግግር ማሰራጨት የሚሉ ተደራራቢ ክሶች ይገኙበታል።

ኮሜዲያን ያሬድ ዘላለም የቀረበበት ክስ እንዲሻሻል የክስ መቃወሚያውን በጽሁፍ ያቀረበ ቢሆንም በዐቃቤ ሕግ በኩል ክሱ ሊሻሻል የሚችልበት የህግ አግባብ እንደሌለ ተጠቅሶ መልስ ሰጥቷል።

ፍርድ ቤቱም ግራ ቀኙን መርምሮ ተከሳሹ ያቀረበው የክስ መቃወሚያ ጥያቄ የህግ አግባብነት የለውም በማለት ውድቅ አድርጎታል።

ከዚህም በኋላ ተከሳሹ በክሱ ላይ የተጠቀሰውን የወንጀል ድርጊት አለመፈጸሙን በመጥቀስ የዕምነት ክህደት ቃሉን በመስጠቱ ዐቃቤ ሕግ የሰውና የሰነድ ማምረጃውን አቅርቧል።

የቀረበውን ማስረጃ የመረመረው ችሎቱ ተከሳሹ የቀረቡበት ሶስት ክሶች ተጠቃለው በአዋጅ ቁጥር 1185/2012 አንቀጽ 4 እና 7 መሰረት እንዲከላከል ብይን ሰጥቷል።

ሶስቱም ክስ በአንድ እንዲጠቃለል የታዘዘው የወንጀል ድርጊቱ በሀሳብ፣ በጊዜና በቦታ ተመሳሳይ መሆኑን በምክንያትነት ተጠቅሶ ነበር።

ተከሳሹ የመከላከያ ማስረጃ አለኝ ማለቱን ተከትሎ ፍርድ ቤቱ ተከሳሹ ያቀረባቸውን የሰው መከላከያ ማስረጃዎችን ቃል አዳምጧል።

ተከሳሹ የሰው የመከላከያ ማስረጃ ያቀረበ ቢሆንም የዐቃቤ ሕግ ማስረጃን በተገቢው መከላከል ባለመቻሉ እና በክስ ዝርዝሩ ላይ የተጠቀሰውን የወንጀል ድርጊት መፈጸሙ በፍርድ ቤቱ በመረጋገጡ በዛሬው ቀጠሮ የጥፋተኝነት ፍርድ ተሰጥቶበታል።

ዐቃቤ ሕግ ድርጊቱ ታስቦ የተፈጸመ መሆኑን ጠቅሶ ቅጣቱ ከብዶ እንዲጣል ጠይቋል።

ፍርድ ቤቱ ተከሳሹ ለአካባቢ ጥበቃ ያበረከተውን አስተዋጾኦ፣ የቤተሰብ አስተዳዳሪና የቀደመ የወንጀል ሪከርድ እንደሌለው ገልጾ ያቀረበውን የቅጣት ማቅለያ ይዞለታል።

ፍርድ ቤቱ በድርጊቱ የእርስ በእርስ ግጭት አለመፈጠሩንና ጉዳት አለመድረሱን ከግምት ውስጥ በማስገባት በዕርከን 6 መሰረት በአንድ ዓመት ቀላል እስራትና በሁለት ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ ወስኗል።

የአዲስ አበባ ማረሚያ ቤት ተከሳሹ እጁ ከተያዘበት ከነሃሴ 26 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ያለውን ጊዜ ታሳቢ እንዲያደርግ ታዟል።

በታሪክ አዱኛ

Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! Tekilu Tekilu Yakob, ኤርዶጋን አልያስ, ኢሳይያስ፡ሞላ፡ ውበቴ, አብዱ የበህል ...
01/03/2024

Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! Tekilu Tekilu Yakob, ኤርዶጋን አልያስ, ኢሳይያስ፡ሞላ፡ ውበቴ, አብዱ የበህል እቀዎች ሸጭ, Gena Usmen

መንግስት ዘንድሮ በሀገሪቱ የተከሰተውን የምግብ እጥረት ለመፍታት 3.2 ቢልዮን ዶላር (ከ180 ቢልዮን ብር በላይ) ያስፈልገኛል ብሏል። የአደጋ ሥጋትና ሥራ አመራር ኮሚሽነሩ አምባሳደር ሽፈራ...
28/02/2024

መንግስት ዘንድሮ በሀገሪቱ የተከሰተውን የምግብ እጥረት ለመፍታት 3.2 ቢልዮን ዶላር (ከ180 ቢልዮን ብር በላይ) ያስፈልገኛል ብሏል።

የአደጋ ሥጋትና ሥራ አመራር ኮሚሽነሩ አምባሳደር ሽፈራው ተክለማርያም ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጋር በጋራ በመሆን ለለጋሾች ባቀረቡት እና ዛሬ በተመለከትኩት አንድ ሰነድ ላይ ይህ 3.2 ቢልዮን ዶላር አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው 10.4 ሚልዮን ዜጎች ድጋፍ ይውላል ተብሏል።

"ይህን [የገንዘብ መጠን በማሳካት ረገድ] የሚጠብቀን ስራ እጅግ ሰፊ ነው" ያሉት ኃላፊው የሀገር ውስጥ ግጭቶች እና የአየር ንብረት ለውጥ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ድጋፍ ፈላጊዎች አስከትሏል ብለዋል።

ይህን መረጃ ሳነብ የታወሰኝ ሀሳብ...

አለም ከጋዛ እስከ ዩክሬን፣ ከሱዳን እስከ አፍጋኒስታን ባሉ ቀውሶች ተወጥሮ ተይዟል፣ ሰብአዊ ድጋፎችም እየተመናመኑ መጥተዋል። ምናልባት ኤክስፖርት እያረግን ነው ያልነውን ስንዴ እና እየገነባናቸው ያሉ የመዝናኛ እና የቱሪስት መዳረሻ ሪዞርቶችን እና ፓርኮችን ለግዜው ገታ አድርገን ለዜጎች የተራበ እና የተጠማ ጉሮሮ ብንደርስ በምድርም፣ በሰማይም ደግ ስራ አይሆንም?

አንዳንድ ሰራተኞቹ ፎርጅድ ወይም እውቅና የሌለው የትምህርት ማስረጃ አላቸው የሚል መረጃ በቅርቡ የወጣበት ኢቢሲ መረጃውን ያወጣብኝ የቀድሞ ሰራተኞዬ "ተአማኒነቴ እንዲቀንስ አድርጓል" በማለት...
28/02/2024

አንዳንድ ሰራተኞቹ ፎርጅድ ወይም እውቅና የሌለው የትምህርት ማስረጃ አላቸው የሚል መረጃ በቅርቡ የወጣበት ኢቢሲ መረጃውን ያወጣብኝ የቀድሞ ሰራተኞዬ "ተአማኒነቴ እንዲቀንስ አድርጓል" በማለት 10 ሚልዮን ብር ካሳ ይክፈለኝ ብሎ ከሷል።

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) አቶ ወገን አበበ የተባለ ግለሰብ "የኢቢሲ 400 ሰራተኞች ፎርጅድ የትምህርት ማስረጃ ነው ያላቸው" በማለት ስሜን አጥፍቷል፣ በዚህም ምክንያት የደረሰብኝን የ10 ሚልዮን ብር ኪሳራ ይክፈለኝ ብሎ ክስ እንደመሰረተ ከፍርድ ቤት ምንጮች፣ ከራሱ የኢቢሲ ሰራተኞች እንዲሁም ከአቶ ወገን ያገኘሁት መረጃ ያሳያል።

ለፌደራል የመጀመርያ ፍርድ ቤት፣ ኮልፌ ምድብ ፍትሀብሄር ችሎት መስከረም ወር 2016 ላይ የቀረበው እና የተመለከትኩት ይህ አቤቱታ እንደሚያትተው መረጃው የወጣበት ሰሞን የአዲስ አመት መዳረሻ ስለነበር ተቋሙ ማግኘት የሚገባውን ከፍተኛ ገቢ አቶ ወገን እንዲያጣ አድርገዋል ይላል።

ክሱ አክሎም "ተከሳሽ በፈጠሩት የስም ማጥፋት ዘመቻ ምክንያት የከሳሽን መስሪያ ቤት ተአማኒነት ከፍተኛ ጥርጣሬ ውስጥ በመክተታቸው፣ ወቅቱም የበአል ሰሞን እንደመሆኑ ከብር አስር ሚልዮን በላይ የሚሆን ገቢ እንዲያጣ ምክንያት ሆነዋል" ይላል።

በዚህ ተመሳሳይ ጉዳይ ከዚህ በፊት በወንጀል ተከሰው፣ ኋላ ላይ ግን ነፃ ወጥተው የነበሩት አቶ ወገን አሁንም በህግ ፊት ራሳቸውን ለመከላከል ዝግጁ እንደሆኑ ነግረውኛል።

አቶ ወገን እና ሌላ አንድ ግለሰብ ለፌደራል የስነምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የአንዳንድ የኢቢሲ ሰራተኞችን የትምህርት ማስረጃ ሀሰተኛነት ማስረጃ ማስገባታቸው ታውቋል።

በማስረጃው ላይ (የተወሰነው በምስሉ ላይ ይታያል... ስማቸውን አስቀርቼዋለሁ) በወር እስከ 47,000 ብር የሚከፈላቸው የትምህርት ማስረጃቸው ፎርጅድ የሆኑ ወይም እውቅና የሌለው የሆኑ ሰራተኞች እንዳለ ግለሰቦቹ ለፀረ-ሙስና አስረድተዋል።

እነዚህ ሁለት ግለሰቦች ያቀረቡት መረጃ "የተጭበረበረ ዲግሪ እንዲሁም ማስተርስ የትምህርት ማስረጃ በማስገባት መስርያ ቤቱ ላይ ለከፍተኛ የደሞዝ ወጪ ከመዳረግ ጀምሮ የባሰ ወደሚባል ደካማ መስርያ ቤት እያረገው ይገኛል" ብለዋል።

አክለውም "አመራሮች እኛ ባሳየነው መንገድ ተጠቅመው ወደ 320 ሰራተኛ እንዲጣራ ወደ ኢ.ፌ.ድ.ሪ ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ተልከው ውጤቱም ፎርጅድ መሆኑ ተረጋግጦ፣ መካከለኛ አመራሩም እነሱም እንደማይቀርላቸው ሲያወቁ ጉዳዩን ለማፈን እየጣሩ ነው። የጠቆምናቸው ሰራተኞችም ዛቻና ማስፈራርያ እያደረሱብን ነው" ብለዋል።

😥ሀዋሳ😥የቀብር ሰረዓታቸው😥1:- ጤናዬ ፍቃዱ ሀዋሳ ቅ/ገብርኤል ገዳም 6:00 ሰዓት2:-በረከት አለባቸው(ሹፌር) አለታ ወንዶ ቅ/ሚካኤል ቤተክርስቲያን 8:00ሰዓት3:-ገዛኸኝ ገ/ስላሴ ነገ ...
26/02/2024

😥ሀዋሳ

😥የቀብር ሰረዓታቸው😥

1:- ጤናዬ ፍቃዱ ሀዋሳ ቅ/ገብርኤል ገዳም 6:00 ሰዓት

2:-በረከት አለባቸው(ሹፌር) አለታ ወንዶ
ቅ/ሚካኤል ቤተክርስቲያን 8:00ሰዓት

3:-ገዛኸኝ ገ/ስላሴ ነገ 6:00 ሚሽን መቃብር

4:-ደስታ ኑሬቦ 6:00 ሰዓት ቅ/ገብርኤል ገዳም

5:-አዲሱ ወልዴ (ቤሊ) ቅ/ገብርኤል ገዳም ዛሬ 6:00 ሰዓት

6:-ብርሀኑ ወልዴ ቅ/ገብርኤል ገዳም ዛሬ 6:00 ሰዓት

7:-አለልኝ ተመስገን(ኪያ) ቅ/ገብርኤል ገዳም ዛሬ 6:00 ሰዓት

8:-ቢንያም አዳነ ቅ/ገብርኤል ገዳም ዛሬ 6:00 ሰዓት

9:-ፍቃዱ ከበደ ቅ/ገብርኤል ገዳም 6:00 ሰዓት

10:-ወንዴ (ወንዴ ሸራ)ቅ/ገብርኤል ገዳም ዛሬ 6:00 ሰዓት

11:-ምናልካቸው (ሚና)ቅ/ገብርኤል ገዳም ዛሬ 6:00 ሰዓት😭😭😭😭
ነፍስ ይማር ወንድሞቼ 😭
ለቤተሰባቸው፣ ለዘመድ ወዳጃቸውና ለመላው የሀዋሳ ህዝብ መፅናናትን እመኛለሁ 🙏

አቶ ደመቀ መኮንን የዓለም አቀፉ የጥቁር ሕዝቦች የታሪክ፣ የቅርስና የትምህርት ማዕከል የጠቅላላ ጉባኤ ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡየካቲት 16/2016 አቶ ደመቀ መኮንን የዓለም ዐቀፍ የጥቁር ህ...
24/02/2024

አቶ ደመቀ መኮንን የዓለም አቀፉ የጥቁር ሕዝቦች የታሪክ፣ የቅርስና የትምህርት ማዕከል የጠቅላላ ጉባኤ ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ

የካቲት 16/2016 አቶ ደመቀ መኮንን የዓለም ዐቀፍ የጥቁር ህዝቦች የታሪክ፣ የቅርስና የትምህርት ማዕከል የጠቅላላ ጉባኤ ፕሬዝዳንት ሆነው ተመርጠዋል።

የጥቁር ህዝቦች የታሪክ፣ የቅርስ እና የትምህርት ማዕከል የመጀመሪያ ጉባኤ በአዲስ አበባ ተካሂዷል።

ጉባኤው የቀድሞ የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የዓለም አቀፍ የጥቁር ህዝቦች የታሪክ፣ የቅርስ እና ትምህርት ማዕከል የጠቅላላ ጉባኤ ፕሬዚዳንት አድርጎ ሾሟል።

ማዕከሉ አቶ ፀጋዬ ጨማን የማዕከሉ ዋና ፀሐፊ አድርጎ መምረጡንም ኢቢሲ ዘግቧል።

የጥቁር ህዝቦች ንቅናቄ መስራችና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች የማርከስ ጋርቬ ልጅ ጁሊየስ ጋርቬን (ዶ/ር) የማዕከሉ የበላይ ጠባቂ ሆነዋል።

የዓለም የጥቁር ህዝቦች ታሪክ ቅርስ እና ትምህርት ማዕከል የጥቁር ህዝቦችን ታሪክ፣ ባህልና ቅርሶችን በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ለማስተዋወቅና ጠብቆ ለማቆየት የተቋቋመ ማዕከል ነው።

ማዕከሉ የተመሠረተው አዲስ አበባ ሲሆን መቀመጫውንም በአዲስ አበባ አድርጓል።

በቅርብ ግዜያት ከሰማሁዋቸው አስደማሚ መረጃዎች አንዱ ይህ "ባለፈው ስድስት ወር ከ4 ሚልዮን በላይ ቱሪስቶች የአማራ ክልልን ጎበኙ" የሚል ዜና ነው። ይህ ማለት በአንድ ቀን ከ22 ሺህ በላይ...
24/02/2024

በቅርብ ግዜያት ከሰማሁዋቸው አስደማሚ መረጃዎች አንዱ ይህ "ባለፈው ስድስት ወር ከ4 ሚልዮን በላይ ቱሪስቶች የአማራ ክልልን ጎበኙ" የሚል ዜና ነው።

ይህ ማለት በአንድ ቀን ከ22 ሺህ በላይ ቱሪስቶች ወደ ክልሉ ሲጎርፉ ነበር ማለት ነው።

እውነታው ግን የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ በታወጀበት ክልሉ ዜጎች ከአንድ ከተማ ወደ ሌላ ከተማ ተዘዋውረው መስራት ያልቻሉበት፣ ትምህርት መማር ያቃተበት፣ ቱሪስት ቀርቶ ወደ ክልሉ ሄዶ ቤተሰብ መጠየቅ አስቸጋሪ ሆኖ የሚገኝበት ሁኔታ ይገኛል። በሚስተዋለው የጸጥታ ችግር ከቱሪዝም የሚያገኙት ገቢ በመቀነሱ መነኮሳት ጭምር ከገዳማት ለመፈናቀል ተገደዋል።

በነገራችን ላይ የአለም ባንክ በ2020 ባወጣው ግምት (ምስሉ ላይ የኢትዮጵያ መንግስት ተቋማትም አጋርተውት ይታያል) በአጠቃላይ ኢትዮጵያን የጎበኙ ቱሪስቶች ቁጥር 518,000 ገደማ ነበር።

ህወሓት ሚስጥር ለጠላት አሳልፈው ሰጥተዋል ያላቸውን ሁለት የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትን አባረረህወሓት በፌስቡክ ገጹ ባወጣው መግለጫ የቀድሞ የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ ኬሪያ ኢብራሂምን እና...
24/02/2024

ህወሓት ሚስጥር ለጠላት አሳልፈው ሰጥተዋል ያላቸውን ሁለት የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትን አባረረ

ህወሓት በፌስቡክ ገጹ ባወጣው መግለጫ የቀድሞ የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ ኬሪያ ኢብራሂምን እና የቀድሞ የትራንስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሙሉ ገብረ እግዚአብሄርን ከማዕከላዊ ኮሚቴ እና ከፓርቲው አባልነት ማባረሩን አስታውቋል።

ፓርቲው እነዚህ ሁለት አባላት ሚስጥር ለጠላት አሳልፎ በመስጠት በስብሰባ መገምገማቸውን እና ይህን ተከትሎም እንዲባረሩ መደረጉን ገልጿል።

ፓርቲው እስር ላይ ከነበሩት የፖርቲው አባላት ውስጥ ዶ/ር አዲሳለም ባሌማ እና ዶ/ር ኣብርሃም ተከስተ በስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልነታቸው እንዲቀጥሉ አድርጊያለሁ ብሏል።

ፓርቲው እስር ላይ ከነበሩት የፖርቲው አባላት ውስጥ ዶ/ር አዲሳለም ባሌማ እና ዶ/ር ኣብርሃም ተከስተ በስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልነታቸው እንዲቀጥሉ አድርጊያለሁ ብሏል

በቦሌ አየር ማረፊያ በፍተሻ እና ጥበቃ አካላት ተጓዦች ላይ የሚፈፀም ውንብድና እና ዝርፊያ! ድርጊቱ የተፈፀመው ሰኞ እለት (የካቲት 11/2016) ምሽት ላይ ነበር። ስሟን የማልጠቅሳት ትውል...
24/02/2024

በቦሌ አየር ማረፊያ በፍተሻ እና ጥበቃ አካላት ተጓዦች ላይ የሚፈፀም ውንብድና እና ዝርፊያ!

ድርጊቱ የተፈፀመው ሰኞ እለት (የካቲት 11/2016) ምሽት ላይ ነበር። ስሟን የማልጠቅሳት ትውልደ ኢትዮጵያዊ፣ የአሜሪካ ዜግነት ያላት ተጓዥ ማታ 5 ሰአት ወደ አሜሪካ ላለባት ጉዞ ቀደም ብላ 2 ሰአት ቦሌ ኤርፖርት ትደርሳለች።

በፍተሻው ወቅት "ሻንጣሽን ከፍተሽ አሳዪን፣ ማሽኑ የሆነ ነገር ያሳየናል" በማለት ሻንጣዎቿን አስከፈቱ። በዚህ ወቅት የያዘችውን የግል መገልገያ ጌጣጌጥ እና በህጋዊ መንገድ የያዘችውን ዶላር ይመለከታሉ። ቀጥላም ሁኔታውም ስታስረዳኝ እንዲህ ብላለች:

"እነዚህ ለብዙ አመታት ያደርግኳቸው ከቤተሰቦቼ እንዲሁም ከባለቤቴ የተሰጡኝ ጌጣጌጦች ናቸው። የሌላ ሀገር ዜግነት ላለው ዶላር እስከ 10,000 በህጋዊ መንገድ ይፈቀዳል፣ እኔ የያዝኩት ከዚህ በጣም ያነሰ ነበር። ጌጣጌጥ ደግሞ ማስመስገብ እንዳለብኝ አላውቅም ነበር። ስለዚህ ፈታሿን ይቅርታ ከዚህ በሗላ አስመዘግባለሁ አልኳት፣ ከዛም በሊፍት አድርጋ ለብቻዬ የሆነ ቦታ ወሰደችኝ።"

"በዚህ ወቅት ሌሎች ሰራተኞች 'በጥሺላት' እና 'በቃ ስጫት' ይሉኝ ነበር። እኔም ግራ ገብቶኝ የእኔ መሆኑን ማረጋገጥ ከፈለጋችሁ ጌጣጌጡ የሚታይበት የድሮ ፎቶ ላሳያችሁ ብላቸውም ፈቃደኛ አልሆኑም። ከዛም ተለቅ ወዳለች ሌላ ሴትዮ ጋር ወሰደችኝ። የሴትዮዋ መልስ ደግሞ 'የሀገሪቱን ሁኔታ አታውቂም? ሀገሪቷ እኮ ወርቅ ያስፈልጋታል!' ነበር።"

"በዚህ ሁሉ መሀል ይቺ ትልቅ ሴትዮ ተስማሚ፣ ካልሆነ በሙሉ ይወረሳል አለችኝ። ምን ማለት ነው ስላት በግልፅ ወርቁን አካፍዪ አለችኝ። በዚህ ወቅት ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩ። እንደማይለቁኝ ስለገባኝ፣ ስልክ እንዳወራም ስለከለኩሉኝ ብዙ ትዝታዬ ያለበትን ጌጣጌጤን ከሚወስዱ ከእሱ ውጪ እንስማማ አልኳቸው።"

"ከዛም ወደ ቦርሳዬ እየጠቆመች 'እሺ ዶላር ይዘሽ አይቻለሁ፣ እሱን አምጪ አለችኝ'። የያዝኩት ዶላር እና ብር ደግሞ የራሴንም፣ የዘመድ እና ጓደኛም ብዙ ትርፍ ሻንጣ ስለያዝኩ ለእሱ የምከፍለው ነው አልኩ። ክፈችው ብላ ትንሽ አስቀርታ የምትፈልገውን ወሰደች። ተባብረንሽ ነው የለቀቅንሽ ብለው ሂጂ አሉኝ፣ ይህ ሁሉ ሆኖ የመጨረሻ ተሳፋሪ ሆኜ ወደ ጉዞዬ ቀጠልኩ።"

Note 1: ከበርካታ ወራት በፊት እንዲህ አይነት ኤርፖርት ላይ በፀጥታ እና ፍተሻ አካላት በተለይ ወደ አረብ አገራት የሚሄዱ ዜጎች ላይ የሚፈፀም ዝርፊያን መረጃ አቅርቤ ነበር። ይህ ተጨማሪ ማሳያ ነው።

Note 2: በኤርፖርት ያሉ እንዲህ አይነት ጉዳዮች ሲነሱ አንዳንዶች በቀጥታ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር ያያይዙታል፣ ነገር ግን የኤርፖርት ጥበቃ የሚከናወነው በአየር መንገዱ ሳይሆን በሌሎች የመንግት የደህንነት እና የፅጥታ አካላት ነው።

Photo: File

እንዲህ አይነትም አባት አሉ 😯 🙏🙏🙏❤️❤️❤️አንድ መስሪያ ቤት ለስራ ጉዳይ ሄጄ ልብ የሚነካ ነገር ተመለከትኩ አንድ አባት ልጁን ታቅፎ የእለት ተግባሩን ሲከውን አየሁት ጠጋ ብዬ ሳናግረው ...
24/02/2024

እንዲህ አይነትም አባት አሉ 😯

🙏🙏🙏❤️❤️❤️

አንድ መስሪያ ቤት ለስራ ጉዳይ ሄጄ ልብ የሚነካ ነገር ተመለከትኩ አንድ አባት ልጁን ታቅፎ የእለት ተግባሩን ሲከውን አየሁት

ጠጋ ብዬ ሳናግረው ሰራተኛ ስላጣሁ ብዙ ግዜ ከእኔ ጋር ነው ምትውለሁ

በዚ ደሞ በጣም ነው ደስ የሚለኝ ብሎ መለሰለኝ

እኔ የዓመቱ ምርጥ አባት ብዬዋለሁ።

Via Yam Yeruk

❤️❤️❤️🙏🙏🙏

🌴🌴🌴

ኮሜዲያን ያሬድ ዘላለም (ልጅ ያሬድ) በተከሰሰባቸው የወንጀል ክስ ጥፋተኛ ተባለአዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2016  ኮሜዲያን ያሬድ ዘላለም በቅጽል ስሙ ልጅ ያሬድ በተከሰሰባቸው የወንጀል ክ...
23/02/2024

ኮሜዲያን ያሬድ ዘላለም (ልጅ ያሬድ) በተከሰሰባቸው የወንጀል ክስ ጥፋተኛ ተባለ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2016 ኮሜዲያን ያሬድ ዘላለም በቅጽል ስሙ ልጅ ያሬድ በተከሰሰባቸው የወንጀል ክስ ጥፋተኛ ተባለ።

የጥፋተኝነት ፍርዱን የሰጠው የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ህገመንግስታዊና በህገመንግስት ስርዓቱ ላይ የሚፈጸሙ የወንጀል ጉዳዮችን የሚመለከተው ችሎት ነው።

የፍትህ ሚኒስቴር የተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ በኮሜዲያን ያሬድ ዘላለም ላይ ሶስት ክሶችን አቅርቦበት ነበር።

ከቀረቡበት ክሶች መካከል በኮምፒዩተር የሚፈጸም ወንጀል ድንጋጌን መተላለፍ፣ የቤተክርስቲያንና የሰዎችን ክብርና መልካም ስም ማጉደፍ እንዲሁም የጥላቻ ንግግር ማሰራጨት የሚሉ ተደራራቢ ክሶች ይገኙበታል።

ኮሜዲያን ያሬድ ዘላለም የቀረበበት ክስ እንዲሻሻል የክስ መቃወሚያውን በጽሁፍ ያቀረበ ቢሆንም በዐቃቤ ሕግ በኩል ክሱ ሊሻሻል የሚችልበት የህግ አግባብ እንደሌለ ተጠቅሶ መልስ ተሰጥቷል።

ፍርድ ቤቱም ግራ ቀኙን መርምሮ ተከሳሹ ያቀረበው የክስ መቃወሚያ ጥያቄ የህግ አግባብነት የለውም በማለት ውድቅ አድርጎታል።

ከዚህም በኋላ ተከሳሹ በክሱ ላይ የተጠቀሰውን የወንጀል ድርጊት አለመፈጸሙን በመጥቀስ የዕምነት ክህደት ቃሉን በመስጠቱ ዐቃቤ ሕግ የሰውና የሰነድ ማስረጃውን አቅርቧል።

የቀረበውን ማስረጃ የመረመረው ችሎቱ ተከሳሹ የቀረቡበት ሶስት ክሶች ተጠቃለው በአዋጅ ቁጥር 1185/2012 አንቀጽ 4 እና 7 መሰረት እንዲከላከል ብይን ተሰጥቷል።

ሶስቱም ክስ በአንድ እንዲጠቃለል የታዘዘው የወንጀል ድርጊቱ በሀሳብ፣ በጊዜና በቦታ ተመሳሳይ መሆኑን በምክንያትነት ተጠቅሶ ነበር።

ተከሳሹ የመከላከያ ማስረጃ አለኝ ማለቱን ተከትሎ ፍርድ ቤቱ ተከሳሹ ያቀረባቸውን የሰው መከላከያ ማስረጃዎችን ቃል አዳምጧል።

ተከሳሹ የሰው የመከላከያ ማስረጃ ያቀረበ ቢሆንም የዐቃቤ ሕግ ማስረጃን በተገቢው መከላከል ባለመቻሉ እና በክስ ዝርዝሩ ላይ የተጠቀሰውን የወንጀል ድርጊት መፈጸሙ በፍርድ ቤቱ በመረጋገጡ በዛሬው ቀጠሮ የጥፋተኝነት ፍርድ ተሰጥቶበታል።

ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኝ የቅጣት አስተያየት ለመጠባበቅ ለየካቲት 22 ቀን 2016 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በዚሁ ጉዳይ ዙሪያ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ዕምነት ተከታይ ምዕመናንን እና የማህበረሰቡን ክብርና ስነ-ልቦናን ከግምት ውስጥ በማስገባት የክሱ ዝርዝር ጉዳይ በሚዲያ እንዳይሰራጭ ትዕዛዝ መስጠቱን ተከትሎ ዝርዝር ጉዳዮችን ከመግለጽ ተቆጥበናል።

"ከምንሰቃይ ወደ ሀገራችን መልሱን ወይም ግደሉን ብለናቸዋል"--- በሳውዲ እስር ቤት የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሳውዲ አረቢያ ውስጥ ሽመቲ የሚባል ማጎርያ ካምፕ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በቃላት ሊገ...
23/02/2024

"ከምንሰቃይ ወደ ሀገራችን መልሱን ወይም ግደሉን ብለናቸዋል"--- በሳውዲ እስር ቤት የሚገኙ ኢትዮጵያውያን

ሳውዲ አረቢያ ውስጥ ሽመቲ የሚባል ማጎርያ ካምፕ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በቃላት ሊገለፅ የማይችል ስቃይ ውስጥ እንደሚገኙ እና አሳሪዎቻቸውን "ከምንሰቃይ ወደ ሀገራችን መልሱን ወይም ግደሉን ብለናቸዋል" የሚል መረጃ አድርሰውኛል።

እነዚህ በመቶዎች የሚቆጠሩ ታሳሪዎች የተሻለ ኑሮ ፍለጋ ድንበሮችን አቆራርጠው ሳውዲ አረቢያ የገቡ ሲሆን አሁን ላይ ያሉበት ሁኔታ ተስፋ አስቆራጭ በመሆኑ ከሶስት ቀን በፊት የርሀብ አድማ እንደጀመሩ ተናግረዋል።

"አይናችን እያየ አብረውን የታሰሩ ሰዎች በርሀብ እና በሽታ እየሞቱ ነው፣ የሞተ ሰው አስከሬን እንኳን አያነሱም። በአንድ ክፍል ውስጥ ከ300 እስከ 400 ሰው አለ። በዚህ ከቀጠለ አንድም ሰው በህይወት አይወጣም፣ ስለዚህ ብንሙትም እንሙት ብለን አድማውን ጀምረናል" ብለዋል።

"በያዝናቸው ስልኮች ይመለከተዋል ለተባለ የኢትዮጵያ መንግስት ቢሮ ሁሉ ደውለናል፣ ምንም መልስ የለም" የሚሉት እነዚህ ዜጎች በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ያላችሁ ወገኖቻችን ድምፃችሁን አሰሙልን ብለዋል።

ፎቶ: ፋይል

Address

Addis
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when All Ethiopian Tube posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to All Ethiopian Tube:

Videos

Share