Zemenu Jenberie - ዘመኑ ጀንበሬ

ነገ ጥር 6 የአፄ ቴዎድሮስ(ጃውሰው)   #ልደት ነው!አፄ ቴዎድሮስ ተፈረደባቸው የንጉሱ ትዕዛዝቴዎድሮስ ለአንድ ታማኝ ወታደራቸው ጥብቅ ትዕዛዝ አስተላልፈው “በፈርቃ በር በኩል እርጉዝ ሴት ...
14/01/2024

ነገ ጥር 6 የአፄ ቴዎድሮስ(ጃውሰው) #ልደት ነው!
አፄ ቴዎድሮስ ተፈረደባቸው
የንጉሱ ትዕዛዝ

ቴዎድሮስ ለአንድ ታማኝ ወታደራቸው ጥብቅ ትዕዛዝ አስተላልፈው “በፈርቃ በር በኩል እርጉዝ ሴት እንኳን ብትሆን እንዳታልፍ ጠንክረህ ጠብቅ” አሉት።
ከጥቂት ቀናት በኋላ ደግሞ ሌላውን ወታደራቸውን ጠርተው “ፈረስ እያለዋወጥክ ይህን ወረቀት የጁ አድርሰህ በስድስት ቀን ውስጥ በአስቸኳይ ተመለስ” ብለው አዘዙ። መልክተኛው ወታደር መልክቱን ለማድረስ ፈርቃ በር በሚባለው ቦታ ማለፍ ግድ ሆነበት። ፈረሱን እየጋለበ ፈርቃ በር ደረሰ። አስቀድሞ ማንንም እንዳያሳልፍ የታዘዘው የፈርቃ በር ዘበናም የንጉሱን መልዕክት እንዳያልፍ ከለከለው።
መልዕክተናው “ከንጉሡ በስድስት ቀን የጁ ደርሼ እንድመለስ በአስቸኳይ ተልኬ ነው ልለፍ” አለው።

የፈርቃ በር ጠባቂም “ከንጉሥ ከተላክ አትከልክሉት ይለፍ የሚል በማህተም የተደገፈ የይለፍ ደብዳቤ ካለህ አሳየኝ እና አሳልፍሃለሁ ካልሆነ ግን እኔም የንጉሥ ትዕዛዝ ስላለብኝ አታልፈም” ሲል መለሰለት።

መልዕክተኛው ወታደርም የንጉሥ ትዛዝ ሆኖበት በግድ አልፋለሁ ብሎ መንገድ ሲጀምር ጠባቂው ወታደር በጥይት ተኩሶ ገደለው።

የሟቹ መልዕክተኛ ወገኖችም ጉዳዩን ከሰሱና ለፍርድ አፄ ቴዎድሮስ ዘንድ ቀረቡ። በችሎት የተቀመጡት ፈራጆች ሁሉ ገዳይ ላይ ፈረዱ “እምቢ አልፋለሁ ቢልህ ለንጉሥ ማመልከት ሲኖርብህ እንዴት የንጉሥ መልዕክተኛ ትገላለህ ለጥፋትህ ሞት ይገባሃል” ሲሉ ፈረዱበት።
አንድ አስተዋይ ፈራጅ ከተቀመጡበት ተነስተው “መታየት የሚገባው ከንጉሡ የተሰጠው ትዕዛዝ ነው።

ንጉሡ የፈርቃ በር ጠባቂን ጠርተው ያለኔ ፈቃድ እርጉዝ ሴት እንኳን እንዳታልፍ ብለው አዘዙ። መልዕክተኛውን ደግሞ በአስቸኳይ የጁ ደርሶ እንዲመጣ በማዘዛቸው በዚያ በፈርቃ በር በኩል ማለፍ ነበረበት። ስለዚህ ጥፋቱ የሚመለከተው ንጉሥ ነገስቱን ነው። ነገር ግን ብርሃን ናቸውና ምን ይደረግ” ብለው ተቀመጡ።

እዚህ ጋር እንግዲህ በዚያ ዘመን የነበረውን ንጉሥ የሚያስተች ዲሞክራሲ ሳናደንቅ አናልፍም። የአስተዋዩ ፈራጅ ንግግር ብቻ ሳይሆን የንጉሡም ምላሽ የሚደንቅ ነው።

አፄው ምን አሉ መሰላችሁ ከመቀመጫቸው ብድግ ብለው “እንዲህ ነው መሸምገል፣ ሁለት ጠጉር ማብቀል” ብለው የአስተዋዩን ፈራጅ ፍርድ ካደነቁ በኋላ “በደለኛው እኔ ነኝ ፍረዱብኝ” ብለው በተከሳሹ ወታደር ቦታ ወርደው ቆሙ። ከዛም ፈራጆች በሰጡት ፍርድ መሰረት ለሟች ወገኖች በቂ የደም ካሳ እንዲከፍሉ አፄ ቴዎደሮስ ላይ ፈረዱና ጉዳዩ በዚህ ተቋጨ።

ነገ ጥር 6 የአፄ ቴዎድሮስ ልደት ነው። መልካም ልደት ከወዲሁ

15/05/2023
14/05/2023

አርሰናል ፈርሰናል ተብሎ በሚጠረው ወደ ቀድሞው አቋሙ በዛሬው ዕለት ተመለሰ!!

 #ለትውስታ ያክል .....!!!
08/05/2023

#ለትውስታ ያክል .....!!!

 #ይሄ ነገር እውነት ነው ቤተሰብ??? ከሆነ ግን በጣም........
28/04/2023

#ይሄ ነገር እውነት ነው ቤተሰብ???
ከሆነ ግን በጣም........

17/04/2023

ከበዓል ማግስት ወደ አጀንዳችን...!!

16/04/2023

አርሴናል አላቹህ???
2:2

16/04/2023

በመላው አለም የምትገኙ ውድ ኦርቶዶክሳዊያን እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም አደረሳቹህ!!!

14/04/2023

አኔ እንኮ የሚገርመኝ አሸባሪ የሚባለው ኦነግ ሸኔ ሳይሆን መንግስት መሆኑን የሚያውቅ ሰው መጥፋቱ ብቻ ነው!!

ዛሬም ሸኔ ነው ልትሉን እንዳይሆን.....????

14/04/2023

ተመከር ሆዳሙ ካቢኔ???

የወረዳ ካቢኔ እባካቹህ ለማይረባ ጥቅማ ጥቅም ብላቹህ እህት ወንድማቹህን አሳልፋችሁ አትስጡ!!
ለእናንተ ሆድ ተብሎ መስዋዕት እንሁን???

14/04/2023

የአማራ ክልል ሆዳሙ ካድሬ ከህዝብ ስቃይ ሆዴ ይበልጥብኛል በማለት አሁንም ህዝቡን በቀን ጅብ እያስበላ ይገኛል!!

09/04/2023

በመጨረሻም አርሴናል እጅ ሰጠ!

09/04/2023

አሁንም በድጋሜ አልተግባባንም!!

09/04/2023

የአማራ ክልል አመራሮች ግራ ተጋብተው እኛንም ግራ እያጋቡን ነው!!
ምን ይሻላል???
“ ዶክተር ይልቃል በመግለጫ" ከተናገረው!!

09/04/2023

ለመላው ኦርቶዶክሳዊያን እንኳን ለሆሳዕና በአል በሰላም አደረሳቹህ!!

08/04/2023

አልተግባባንም!!

በታራክ ያየነው አሁን በተግባር ተፈፅሟል!!
08/04/2023

በታራክ ያየነው አሁን በተግባር ተፈፅሟል!!

15/03/2023

ሹመት‼️

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት የገቢዎች ቢሮ ኃላፊን ጨምሮ አዳዲስ ሹመቶችን መስጠቱ ተገልጿል።

ሹመቶቹ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት 2ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባዔ እየተካሄደ በሚገኝበት ወቅት ነው የተሰጠው።

በዚህም ፡-

1. ዶክተር ጀማሉ ጀንበሩ - በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአረንጓዴ ውበትና ልማት ቢሮ ሃላፊ
2. አቶ ቢኒያም ምክሩ - የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ሃላፊ
3. አቶ አብርሃም ታደሰ - የአዲስ አበባ የህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ቢሮ ሃላፊ
4. አቶ አብዱልቃድር ሬድዋን - የፋይናንስ ቢሮ ሃላፊ
5. አቶ አደም ኑሪ - የገቢዎች ቢሮ ሃላፊ
6. አቶ በላይ ደጀን - የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሃላፊ
7. ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ - የአዲስ አበባ የቴክኒክና ትምህርት ስልጠና ቢሮ ሃላፊ
8. አቶ ካሳሁን ጎንፋ - የአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ዋና ስራ አስፈጻሚ
9. አቶ አያሌው መላኩ - የመሬት ይዞታ ማስለቀቅና አቤቱታ ሰሚ ጉባዔ ሃላፊ
10. ወ/ሮ እናታለም መለሰ - የአዲስ አበባ የኮሙኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ ሆነው ሹመታቸው በሙሉ ድምፅ ጸድቋል፡፡

ተሿሚዎቹ በምክር ቤት ፊት ቀርበው ቃለ መሃላ ፈጽመዋል ።

 #ማስታወቂያበአቅም ማሻሻያ  (Remedial )ፕሮግራም መቅደላአምባ  ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ ተማሪዎች ብቻበ 2014 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ የ...
15/03/2023

#ማስታወቂያ

በአቅም ማሻሻያ (Remedial )ፕሮግራም መቅደላአምባ ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ ተማሪዎች ብቻ

በ 2014 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ የ Remedial ፕሮግራም ለመከታተል መቅደላአምባ ዩኒቨርስቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች የተደረገ ማስተካከያ ስላለ ምደባችሁን እንደገና ገብታችሁ እንድታዩ እናሳስባለን፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር!

 #ተፈተዋል ! #ሰበር ዜና…!"…እነ መምህር ምሕረተአብ፣ እነ ፌቨን ተፈተዋል…! የብፁዕ አቡነ አብርሃም እና የብፁዕ አቡነ ጴጥሮስን መንፈሳዊ ሰላማዊ ትግል የምንገልፅበት አንደበት የለንም!...
21/02/2023

#ተፈተዋል !

#ሰበር ዜና…!

"…እነ መምህር ምሕረተአብ፣ እነ ፌቨን ተፈተዋል…! የብፁዕ አቡነ አብርሃም እና የብፁዕ አቡነ ጴጥሮስን መንፈሳዊ ሰላማዊ ትግል የምንገልፅበት አንደበት የለንም!!!

 #ኢትዮጵያውያን የተናበቡበት ነው! የአፍሪካ ጉዳይ ማድረግም ያስፈልጋል።በአገር ቤት ብቻ ሳይሆን በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትናን  ላይ የታ...
13/02/2023

#ኢትዮጵያውያን የተናበቡበት ነው! የአፍሪካ ጉዳይ ማድረግም ያስፈልጋል።

በአገር ቤት ብቻ ሳይሆን በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትናን ላይ የታወጀውን ጥቃት በቁጣ ተቃውሟቸውን እያሰሙበት ነው። ይህ በለንደን የተደረገ ሰልፍ ነው። በሌሎች አገራትም ሰልፎች እየተደረጉ ነው።

ዳያስፖራው የጀመረው ንቅናቄ የሚያኮራ ነው። በሰልፎቹ ጥቃቱ የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የአፍሪካ ጭምር መሆኑን ማሳየት ያስፈልጋል። የአፍሪካ ነፃነት ምልክት የሆነት ተቋም፣ የአፍሪካ ምልክት የሆነው ሰንደቅ፣ በአፍሪካ አገር በቀል የሆነውን ፊደል ጠልተው ነው እናፈርሳታለን ያሉት። ዋና ዋና የአፍሪካ አገራትንም ጭምር የሚመለከት መልዕክት ይዞ በመውጣት፣ ዶክተር ወዳጀነህ እንደገለፀው "የአፍሪካ ትምክት" የሆነች ተቋም መጠቃቷን ማሳወቅ ያስፈልጋል። አፍሪካውያንም፣ በዓለም የሚገኙ ጥቁሮችንም ባለውለታቸው እንደተጠቃች ማሳወቅ ያስፈልጋል። ጉዳዩ የአፍሪካ መሆኑን የሚያሳዩ መልዕክቶች በስፋት መተላለፍ አለባቸው። ሰልፈኞቹ በአቋም መግለጫቸው ቤተ ክርስቲያን ያላትን አስተዋፅኦና የተፈጠረውን የሚገልፅ ዝርዝር አዘጋጅተው ለአፍሪካ አገራት ኤምባሲዎች ማስገባት ቢችሉም መልካም ነው።

 #አርባ ምንጭ ቅዱስ ገብርኤል ..!!
06/02/2023

#አርባ ምንጭ ቅዱስ ገብርኤል ..!!

Exam for Awash Bank
16/05/2022

Exam for Awash Bank

💻 ኮምፒውተር ላይ በአማርኛ እንዴት እንደሚፃፍ ያውቃሉ?ሲጽፉስ ምን ያህል ይፈጥናሉ?=========================■ ጠቃሚ መረጃ ነው!! ላልደረሰው ያዳርሱ አሁኑኑ ሼር ያድርጉት፡፡...
16/05/2022

💻 ኮምፒውተር ላይ በአማርኛ እንዴት እንደሚፃፍ ያውቃሉ?ሲጽፉስ ምን ያህል ይፈጥናሉ?
=========================

■ ጠቃሚ መረጃ ነው!! ላልደረሰው ያዳርሱ አሁኑኑ ሼር ያድርጉት፡፡

❖መጀመሪያ Power ge'ez Software ያወረዱ እና install ያድርጉት ከዛም አማርኛ መፃፍ ስትፈልጉ power ge'ez status phonetic Unicode Mode (ፎ) ላይ ያድርጉት በ English መፃፍ ስትፈልጉ ደግሞ power ge'ez status English Mode (ኢ) ላይ አድርገው ከዛ በኋላ ከታች ባለው ፍሰት መሰረት ይተይቡ(ይፃፉ)!

⁉️
👇👇👇👇👇👇👇👇

https://t.me/+WFrW4zZkWBI2Yjdk

👆👆👆👆👆👆👆

◕ሀ➭H_ሁ➭Hu_ሂ➭Hi_ሃ➭Ha_ሄ➭Hy_ህ➭He_ሆ➭Ho

◕ለ➭L_ሉ➭Lu_ሊ➭Li_ላ➭La_ሌ➭Ly_ል➭Le_ሎ➭Lo

❖ሐ➭Shift+h_ሑ➭Shift+hu_ሒ➭Shift+hi_ሓ➭Shift+ha_ሔ➭Shift+hy_ሕ➭Shift+he_ሖ➭Shift+ho

◕መ➭M_ሙ➭Mu_ሚ➭Mi_ማ➭Ma_ሜ➭My_ም➭Me_ሞ➭Mo

❖ሠ➭Shift+s_ሡ➭Shift+su_ሢ➭Shift+si_ሣ➭Shift+sa_ሤ➭Shift+sy_ሥ➭Shift+se_ሦ➭Shift+so

◕ረ➭R_ሩ➭Ru_ሪ➭Ri_ራ➭Ra_ሬ➭Ry_ር➭Re_ሮ➭Ro

◕ሰ➭S_ሱ➭Su_ሲ➭Si_ሳ➭Sa_ሴ➭Sy_ስ➭Se_ሶ➭So

❖ሸ➭Shift+s_ሹ➭Shift+su_ሺ➭Shift+si_ሻ➭Shift+sa_ሼ➭Shift+sy_ሽ➭Shift+se ሾ➭Shift+so

◕ቀ፡➭Q ቁ፡➭Qu ቂ፡➭Qi ቃ፡➭Qa ቄ፡➭Qy ቅ፡➭Qe ቆ፡➭Qo

◕በ፡➭B ቡ፡➭Bu ቢ፡➭Bi ባ፡➭Ba ቤ፡➭By ብ፡➭Be ቦ፡➭Bo

◕ተ፡➭T ቱ፡➭Tu ቲ፡➭Ti ታ፡➭Ta ቴ፡➭Ty ት፡➭Te ቶ፡➭To

◕ ቸ፡➭C ቹ፡➭Cu ቺ፡➭Ci ቻ፡➭Ca ቼ፡➭Cy ች፡➭Ce ቾ፡➭Co

◕ነ፡➭N ኑ፡➭Nu ኒ፡➭Ni ና፡➭Na ኔ፡➭Ny ን፡➭Ne ኖ፡➭No

❏ኘ፡➭Shift +n ኙ፡➭Shift +nu ኚ➭Shift+ni ኛ፡➭Shift +na ኜ፡➭Shift +ny ኝ፡➭Shift + ne ኞ፡➭Shift +no

◕ከ፡➭Ka ኩ፡➭Ku ኪ፡➭Ki ካ፡➭Ka ኬ፡➭Ky ክ፡➭Ke ኮ፡➭Ko

❖ ኸ ☛capslock + Shift + h
ኹ ☛capslock + Shift + hu
ኺ ☛capslock + Shift + hi
ኻ ☛Capslock + Shift + ha
ኼ ☛Capslock + Shift + hy
ኽ ☛Capslock + Shift + he
ኾ ☛Capslock + Shift + ho

❏ኀ፡➭ Capslock + H ኁ፡➭ Capslock + HU ኂ፡➭Capslock + HI ኃ፡➭Capslock + HA ኄ፡➭Capslock + HY ኅ፡➭Capslock + HE ኆ፡➭Capslock + HO

❏አ፡➭Capslock X ኡ፡➭Xu ኢ፡➭Xi ኣ፡➭Xa ኤ፡➭Xy እ፡➭Xe ኦ፡➭XoDe

❖ዐ፡➭Shift +x ዑ፡➭Shift +xu ዒ➭Shift +xi ዓ፡➭Shift +xa ዔ➭Shift +xy ዕ፡➭Shift +xe ዖ➭Shift +xo

✪ወ፡➭W ዉ፡➭Wu ዊ፡➭Wi ዋ፡➭Wa ዌ፡➭Wy ው፡➭We ዎ፡➭wo

✪ዘ፡➭Z ዙ፡➭Zu ዚ፡➭Zi ዛ፡➭Za ዜ፡➭Zy ዝ፡➭Ze ዞ፡➭Zo

❏ዠ፡➭Shift + Z ዡ፡➭Shift + Zu ዢ፡➭Shift + Zi ዣ፡➭Shift +Zaዤ፡➭Shift + Zy ዥ፡➭Shift +Ze ዦ፡➭Shift + Zo

✪ፈ፡➭F ፉ➭Fu ፊ፡➭Fi ፋ፡➭Fa ፌ፡➭Fy ፍ፡➭Fe ፎ፡➭Fo

✪ ፐ፡➭P ፑ፡➭Pu ፒ፡➭Pi ፓ፡➭Pa ፔ፡➭Py ፕ፡➭Pe ፖ፡➭Po

✪ገ፡➭G ጉ፡➭Gu ጊ፡➭Gi ጋ፡➭Ga ጌ፡➭Gy ግ፡➭Ge ጎ፡➭Go
👉 https://t.me/+WFrW4zZkWBI2Yj

Address

Addis Ababa
212121

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Zemenu Jenberie - ዘመኑ ጀንበሬ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Zemenu Jenberie - ዘመኑ ጀንበሬ:

Share