እኔ የምለው /Ene Yemelewe/

እኔ የምለው /Ene Yemelewe/ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from እኔ የምለው /Ene Yemelewe/, Digital creator, Addis Ababa.
(2)

16/04/2024
15/04/2024
"የስፖርት ማዘውተሪያዎች ለኅብረተሰብ ተጠቃሚነት!"የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የኅብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በመደበኛና በ90 ቀናት ዕቅድ በርካታ ፕሮጀክቶችን ግንባታ ለአ...
15/04/2024

"የስፖርት ማዘውተሪያዎች ለኅብረተሰብ ተጠቃሚነት!"

የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የኅብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በመደበኛና በ90 ቀናት ዕቅድ በርካታ ፕሮጀክቶችን ግንባታ ለአገልግሎት ዝግጁ እያደረገ ይገኛል ። በተለይም የዘመናት የሕዝብ ጥያቄ የነበረውን የስፖርት ማዘውተሪያ ሥፍራ ችግር ለመፍታት በ2016 በጀት ዓመት ሰፊ እንቅስቃሴዎች ተደርገዋል።

በወረዳ 14 የሚገኘው የወረገኑ ሁለገብ የመዝናኛና ስፖርት ማዕከል አስተዳደሩ ለፍጻሜ ያበቃው ፕሮጀክት ሲሆን፣ 3 በ1 የስፖርት ሜዳ ፣ የመዋኛ ገንዳ፣ የሜዳ ቴኒስ፣ የሕፃናት መጫወቻ፣ ቤተ መጻሕፍት እና ሌሎች አገልግሎት መስጫዎችን ያካተተው ይህ ማዕከል ከክፍለ ከተማው አልፎ በከተማ ደረጃም ተጨማሪ የመዝናኛና የስፖርት ማዘውተሪያ አማራጭ እንደሆንን የሕዝባችንን የዘመናት ጥያቄ በውጤት የሚመልስ ስኬታችን እንደሆነ ይታመናል ።

ሚያዚያ 7/2016

“አዲስ ገጽታ፣ አዲስ የሥራ መንፈስ!”የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ምቹና የዘመነ የሥራ አካባቢን ለመፍጠር፣ አገልግሎት አሰጣጥን ለማዘመን እንዲሁም የሠራተኞችን የማገልገል ዝግጁነት ለማሳደግ...
12/04/2024

“አዲስ ገጽታ፣ አዲስ የሥራ መንፈስ!”

የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ምቹና የዘመነ የሥራ አካባቢን ለመፍጠር፣ አገልግሎት አሰጣጥን ለማዘመን እንዲሁም የሠራተኞችን የማገልገል ዝግጁነት ለማሳደግ አቅዶ በስፋት እየሠራ ይገኛል፡፡ በዚህ መሠረትም የተለያዩ ሴክተር ጽ/ቤቶች የማዘመን ሥራዎችን እየሠሩ ናቸው፡፡

የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የኮሚዩኒኬሽን ጽ/ቤት ይህንን የአስተዳደሩን ተልዕኮ ለማሳካት የተለያዩ ሥራዎችን አከናውኗል፡፡ ጽ/ቤቱ ቢሮውን የማዘመን ሥራዎችን በማከናወን የአመራርና የፈጻሚ ወንበርና ጠረጴዛዎችን በአዲስ መልክ ያሟላ ሲሆን፣ የሠራተኞች የደንብ ልብስ ለአገልግሎት አብቅቷል፡፡ በተጨማሪም ጽ/ቤቱ የአስተዳደሩን ይፋዊ ዌብሳይት፣ የጽ/ቤቱን ሎጎ እና ኪውአር ኮድ በማዘጋጀት ለሥራ ዝግጁ እያደረገ ይገኛል፡፡ የማኀበራዊ ሚዲያ ተከታዮች የማፍራት ሥራን በከፍተኛ ትኩረት ያከናወነው የኮሚዩኒኬሽን ጽ/ቤት በአዲስ አበባ ከተማ ካሉት ክፍለ ከተሞች በተከታይ ብዛት ቀዳሚ መሆን ችሏል፡፡

እነዚህ የጽ/ቤታችን የለውጥ ሥራዎች የክፍለ ከተማችን አስተዳደር ለጀመረው ዘመናዊ አገልግሎት የመስጠት ተልዕኮ ለማሳካት የሚኖረው ሚና ከፍተኛ ነው፡፡ በሥራዎቻችን የሕዝብን እርካታ ለማሳደግና የአስተዳደራችንን ራዕይ ለማሳካት የጀመርነውን ጥረት አጠናክረን እንቀጥላለን፡፡

06/04/2024
የመሪ ተምሳሌት  የለውጥ ዓርማ... የድል ብስራት!!  በለውጡ 6ኛ ዓመት ጉዞ
06/04/2024

የመሪ ተምሳሌት የለውጥ ዓርማ... የድል ብስራት!! በለውጡ 6ኛ ዓመት ጉዞ

06/04/2024
አይን አይቶ ፍርድ ይስጥልዩነት ግልፅ ነው የሚዛናዊነት ጉድለት እንጅ
31/03/2024

አይን አይቶ ፍርድ ይስጥ
ልዩነት ግልፅ ነው የሚዛናዊነት ጉድለት እንጅ

ዛሬ ጠዋት ከቦሌ ካርጎ እስከ አቃቂ ድልድይ በመሰራት ላይ የሚገኘውን የአረንጓዴ ልማት ስራ ተዘዋውረን ጎብኝተናል።ከተማችንን ጽዱ፣ ውብ እና አረንጓዴ ለማድረግ የጀመርነው የኮሪደር ልማት አካ...
31/03/2024

ዛሬ ጠዋት ከቦሌ ካርጎ እስከ አቃቂ ድልድይ በመሰራት ላይ የሚገኘውን የአረንጓዴ ልማት ስራ ተዘዋውረን ጎብኝተናል።

ከተማችንን ጽዱ፣ ውብ እና አረንጓዴ ለማድረግ የጀመርነው የኮሪደር ልማት አካል የሆነው ይህ የአረንጓዴ ልማት ስራ የህጻናት መጫዎቻዎችን፣ መናፈሻዎችን እንዲሁም የተለያዩ ለአካባቢው ነዋሪዎች ግልጋሎት የሚሰጡ ስራዎችን የሚያካትት፣ ከ200 ሺሕ ካሬ በላይ ሽፋን ያለው እና ከቦሌ ካርጎ እስከ አቃቂ ድልድይ ድረስ 9.5 ኪ ሜ የሚረዝም ሲሆን ስራውን በአጭር ጊዜ ውስጥ በማጠናቀቅ ለህዝብ ክፍት እናደርጋለን።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ይህ ሀገር ወይም ከተማ የት ነው ብላችሁ ከማሰባችሁ በፊት ልንገራችሁ እዚሁ አዱ ገነት ቦሌ ነው። በአጭርግዜ በጥራትና በፍጥነት የተሰራ የጀግኖች አመራሮቻችን ጥንካሬ ያየንበት ትልቅ ስራ ነው...
29/03/2024

ይህ ሀገር ወይም ከተማ የት ነው ብላችሁ ከማሰባችሁ በፊት ልንገራችሁ እዚሁ አዱ ገነት ቦሌ ነው። በአጭርግዜ በጥራትና በፍጥነት የተሰራ የጀግኖች አመራሮቻችን ጥንካሬ ያየንበት ትልቅ ስራ ነው።

ይህ የምታዩት ዘመናዊ የእግር ኳስ ሜዳ የት ይሆን ብላችሁ እንዳትጨነቁ እዚሁ 7/24 የመስራት ተሰጥኦ ያላት በቆራጥና በታታሪዋ በወ/ሮ አለምፅሐይ ሽፈራው በአመራር ሰጭነት በጥራት በፍጥነት ...
29/03/2024

ይህ የምታዩት ዘመናዊ የእግር ኳስ ሜዳ የት ይሆን ብላችሁ እንዳትጨነቁ እዚሁ 7/24 የመስራት ተሰጥኦ ያላት በቆራጥና በታታሪዋ በወ/ሮ አለምፅሐይ ሽፈራው በአመራር ሰጭነት በጥራት በፍጥነት የተሰራ ቦሌ ቡልቡላ ነው።

Address

Addis Ababa

Telephone

+251910177617

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when እኔ የምለው /Ene Yemelewe/ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to እኔ የምለው /Ene Yemelewe/:

Videos

Share